Friday, July 28, 2023

ጦርነቱ የትግራይ ሪፑብልክ ምስረታ ነበር ማስረጃውም ይኼው በታጋዮች አንደበት ጌታቸው ረዳ 7/28/23

 

ጦርነቱ የትግራይ ሪፑብልክ ምስረታ ነበር ማስረጃውም ይኼው በታጋዮች አንደበት

ጌታቸው ረዳ

7/28/23

የትግራይ መሪዎች ሕዝባቸውን በጦርነት ለመማገድ ለ49 አመት ያስደምጡን የነበረውን መፈክር፤ ከመሪያቸው ከመለስ ዜናዊ እስከ ደብረጽዮን እስከ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ከሚከተልዋቸው የዲያስፖራ ምሁራን ደናቁርት

“ካልቶቻቸው” ድረስ ስያስተጋቡት የነበረው የገደል ማሚቶ ጩኸታቸው የምንከተለው ጦርነት 'Just War' (ፍትሓዊ ጦርነት) ነው የሚል ነበር። ይህ መፈክር በሰፊው ሲያስተጋቡት እንደነበር ሁላቸሁም ታስታውሳላችሁ ብየ እገምታለሁ።

ወያኔ የታወቀበት ጸረ ኢትዮጵያዊነቱ እና ጸረ አማራነቱን በመከተል ከሥልጣን ሲወገድ፤ እንደ ፋሺስትነቱ ባሕሪ በሱሪ እንጂ በውይይት ስለማያምን አገር ለመገንጠል ‘ኢፍትሓዊ ጦርነት’ ከፍቶ 'በአገር ላይ ውድመትና የሰው ዕልቂት’ ማስከተሉን እንኳን እኛ፤ በጦርነቱ የተካፈሉት  የግንጣላ ታጋይ አባሎቹ በከፍተኛ ቁጭትና ልቅሶ ተደጋጋሚ ሠላማዊ ሰልፍ በማድረግ በመሪዎቻቸው ላይ ንዴትና ዘለፋ እያስተጋቡ እንደሆነ ከወደ መቀሌ የሚሰራጩት የስዕለ ድምፅ መቅረጾች አሳይተውናል።  

ታዲያ ይህንን አሳዛኝ የትግሬዎች ዕብሪት ልጁን በከንቱ መሰዋት መሆኑን እምባ እየተናነቀው በቁጭት የተናገረው በቃለ መጥቅ ያስደመጠን “ታጋይና ተዋናይ ብርሃነ ጫሕማ” የተባለ የወያኔ ታጋይ የጦርነቱ ዋና ዓላማ ለምን እንደነበረ ከአንደበቱ እንስማ። ቃለ መጠይቁ ረዢም ስለሆነ አስፈላጊዋን ክፍል ብቻ ቆርጬ  ወደ አማርኛ ተርጉሜ ነው በዚህ የቪዲዮው ቅጅ በጽሑፍ የለጠፍኩት።

የአማርኛ - ትርጉም፤-

<< (በዚህኛው ጦርነት) በትግራይ በረሃ ውስጥ እያለን ወጣቶችና ትላላቅ አዛውንቶች ተሰብስበን ለትላልቅ የህወሓት መሪዎች የሚከተለው ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር፡ ይኸውም << ልክ እንደ የ 17 አመቱ ትግል ከኢትዮጵያ ጋር እንቀጥላለን ልትሉን ነው? ወይንስ ታላቋን ትግራይ ለመመስረት ነው ዋናው የጦርነቱ ዓላማ? እንዳለፈው ሁሉ ቁማር እንዳትጫወቱብን! ብለን ደጋግመን ጥያቄ አቀረብንላቸው። የጦርነቱ ዓላማ ምን እንደሆነ  አሁኑኑ እንዲያሳውቁን ብለን ደጋግመን ጠየቅናቸው። "ከእንግዲህ አይደገምም፣ በፍጹም አይታሰብም፣ ከኢትዮጵያውያን ጋር አንቀጥልም፣ መቼም አንሆንም፣ አንደግመውም ብለው ነገሩን። እኛም እንደዚህ ከሆነ መስዋዕት እንከፍላለን ብሎ ኣእላፍ ወጣት ረገፈ።  መስዋዕት ከፈልን (ትግራይን እንደ ሃገር) ነፃ ካወጣን በኋላ ግን ፍትሕ እንድታሰፍኑ፤አካለስንኩላን ተገቢ እንክብካቤ እንዲሰጣቸው ነው የምንጠብቀው ብሎ ወጣቱ በፈቀዱ ወድዶ በገፍ ተሰዋ።…>>

<<……መአት ምሁር፤ ስንት መሃንዲስ ጠፋ። ይህ ሁሉ የመጣው በመሪዎቻችን ምክንያት ነው ሰውዬው (አብይ አሕመድ ማለቱ ነው) ሁሉንም ነገር ከማድረግ በፊት,  ወንጀለኞች ናችሁ፤ ወንጀል ፈጽማችሗል፤ተጠያቂዎች ናችሁ የሕግ ትፈላጊዎች ናችሁ ሲላቸው  (በትዕቢት) “ቅልጥማችን ማን ይይዘዋል፤ በቅልጥማችን!! በቅልጥማችን!! ’’ እያሉ ህዝቡን ቀስቅሰው የትግራይን ሕዝብ አንክድም ብለው ቃል ስለገቡ ሕዝቡም ያንን በመስማት እንደ ቅጠል ረገፈ። ይህ ሁሉ ወጣት ከረገፈ በኋላ ግን መሪዎቻችን እንደ ቃላቸው ሊገኙ አልቻሉም…….።

…….እኔን የሚያሳዝነኝ የልጄን የሮዳስ ሰማዕትነት እና በሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች መበታተን አላሳዝነኝም ፤ ትግሉ መጨናገፉን አሳዝኖኛል። አካላታቸው የጎደሉ የ12 አመት ታዲጊ ወጣት አናብስትና አንበሶች ከመሰንከላቸው በፊት በጦርነቱ ወቅት ፓትሮል መኪና ከጠላት ማርከው ያስረብዋቸውን ዛሬ አካላታቸው ደክሞ በርሃብና በጥይት ሰንክለው መንገድ ላይ ሲጓዙ ደክመው እባካችሁ “አሳፍሩን” ሲልዋቸው “ሰምተው እንዳልሰሙ’ ዘግተዋቸው “አናሳፍርም” ብለው ንቀዋቸው ሲሄዱ ማየት ያሳዝናል።….>>

<<......አሁን የሚያሳዝነኝ ዋናው ነገር ሕዝብን መክዳታቸው ነው። አሸንፈን ሰሜን ሸዋ ድረስ ደረስን እነዚያ ‘እኛን ያጠፉን  አማራ ሊሂቃን’ መሸሽ ጀመረው ነበር። እዛ እንደደረስን ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ነው ወይ ዋናው ግስጋሴአችሁ ተብለው ሲጠየቁ “አናስተዳድራትም” ብለው ወደ ኋሊት ተመለሱና ትግሉ ተኮላሸ።  ከዚያም  የትግራይ ሕዝብ በረሃብ እያለቀ በጥቁር ገበያ  የእርዳታ እህል መሸጥ ጀመሩ።……>>

<<………ይህ ሁሉ ሰበብ እነሱም ሆኑ ልጆቻቸው ሥልጣናቸው እና ሃብታቸው እንዳይነካባቸው ከዚህ ሁሉ መዘዝ ርቀው ነበር የሚኖሩት። ስለዚህ ትግላችን ከሽፏል።  < የትግራይ መሪዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የትግራይን ወጣት እንደ ቅጠል እንዲረግፍ አደረጉ።በሴራ አጠፉት።ትግላችን ይቀጥላል::>>

 በማለት የደረሰው ጥፋት ለመድግም አሁንም  ትግሉ ይቀጥላል። >> ይላል  (የወያኔ ትግራይ ታጋይና የመድረክ ተዋናይ ‘ታጋይ ብርሃነ ጫሕማ’ ሰሞኑን ካደረገው የትግርኛ ቃለ ምልልስ የተቀነጨበ- ትርጉም (ጌታቸው ረዳ )

የሚገርመው ልጁ ወደ እሳት ጨምሮ ለወያኔ መሪዎች ህይወት ለመጠበቅ ሲባል ፤ ወድዶ በስጦታ “እንደ ፋሲካ በግ” ወጣት ልጁን ያውም ኢንጂኔር ማዕርግ ያለው ለመስዋዕትነት የሰጠ ፤ ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ ዘረኛው የመድረክ ተዋናዩ “ብርሃነ ጫሕማይ” የጦርነቱ  ዓለማ ትግራይ ሪፑብሊክ ለመመሥረት እንደነበር ነግሮናል።

ሕዝቡ የተካፈለበት ጦርነቱ እንዴት እንደነበር ከታፈኑት የሰሜን ዕዝ መካካል << የተከዳው የሰሜን ዕዝ- የታፈነው ወጥቶ አደር ማስታወሻ>> በሚል የዓይን መስክርነትን ያካተተ ታሪካዊ መጽሐፍ ጋሻዬ ጤናው (ቻቻው) ትግራይ ሕዝብ ሦስት አራት አይነት ነው። ይለናል።

ግማሹ የጁንታው ደጋፊ ሆኖ ሠራዊቱ እንደ አባቱ ገዳይ በክፉ ዓይኑ የሚያይ ነው። ዕድል ሲያገኝ በገጀራና በመጥረቢያ እየቆረጠና እየፈለጠ፤በካራ እየባረከ፤ በድንጋይ እየወገረ እና በጩቤ እየወጋ፤በርበሬ ዓይኑ ላይ እየበተነ፤ጣውላ ላይ በተመታ ሚስማር ጭንቅላቱን እየሰነጠቀ ገድሏል፤ አቁስሏል።

የሆነው ሆኖ በኛ ሠራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያዘዙና የመሩ የጁንታው ባለሥልጣናት ቢሆኑም፤ ሠራዊቱን እጅግ ዘግናኝና አሰቃቂ በሆነ መንገድ የገደሉ ግን ልዩ ኃይል ወይም ሚሊሽያ ሳይሆንየጁንታው ደጋፊ ሕዝብ እና እኛን የከዱ የሠራዊቱ አባሎች” ናቸው።
ልዩ ኃይሉና ሚሊሽያው የያዘው መሳሪያ ብቻ ነው፤የሚገድለውም በጥይት ነው። በካራ ያረዱ፤በጩቤ የወጉ፤ በገጀራ የቆረጡ በመጥረቢያ የፈለጡ፤ በድንጋይ የቀጠቀጡ አብዛኛዎቹ የጁንታው ደጋፊዎች ናቸው።ሌላኛው አስከሬንን በመኪና የረገጡ፤ ቁስለኛን በታንክ የጨፈለቁ የፍጥኝ አስረው ገደል የለቀቁከኛ የከዱ የትግራይ ተወለጆች የሠራዊቱ አባላት ናቸው።

ይህ የጁንታ ኃይል ነው እንግዲህ የሠራዊቱን የግንኙነት መረቦች ቆራርጦና መንገድ ዘግቶ ካምፑን የከበበ። ሠራዊቱ ከአቅም በላይ ተዋግቷል (ሁሉም አንድ ባይሆንም ዘጠኝ ቀን ሙሉ ርሀብና ውኃ ጥሙ ሳያሸንፈው የተዋጋ አለ። አምስት ቀን ሌሊትም ቀንም ከምሽጉ ሳይወጣ ጥይቱ እስከሚያልቅ የተዋጋ አለ። ሰባት ቀን ሙሉ ያለምንም ዳቦና ውኃ የተዋጋ አለ።አምስት ቀን ሌሊትም ቀንም ከምሽጉ ሳይወጣ ጥይት እስከሚያልቅ የተዋጋ አለ። ለሦስት ቀን በእልህና ወኔ ከጁንታው ኃይል የተፋለመ አለ። ማንም የሚደርስለት አልነበረም።

ሠራዊቱ ምግብና ውኃ የለውም። የጁንታው ኃይል እንደፈለገ ምግብና መጠጥ ይቀርብለታል። ሠራዊቱ ጥይት እየቆጠበ ካልሆነ ካለቀበት ዕጣው በጁንታው እጅ መውደቅ ነው። ለጁንታው ኃይል ጥይት እንደ አፈርና ጭቃ ነው። ሁለት መቶ እና ሦስት መቶ የሚሆን ሠራዊት 1 5 መቶ እና ከዚያ በላይ የታጠቀ ኃይል ያሰልፋል። ኋላ ደግሞ ተራራ የሚሸፍን ሕዝብ አለ።

ሠራዊቱ አንድ ሰው ሲቆስልበትና ሲሞትበት የሰው ኃይሉ ይቀንሳል። ጁንታው ስለሰው አይጨነቅም። አምስት ታጣቂ ቢሞትበት አምሰት አውቶብስ ሰው አምጥቶ ይደፋል። ታዲያ እንዴት ይሄ ሠራዊት ትጥቅ አይፈታም?

እያለ ወያኔ መጀመሪያ በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ ጥቃት ሲፈጽም ደራሲው በግል ማስታወሻው በምስጢር እየመዘገበ ያየውን የተፈጸመው አገራዊና ሰብአዊ ወንጀል ባስጨናቂ ሁኔታ በነበረበት ወቅት ብርታትን የተሞላበት የእልህ ግብግብ ያየውን ለኛ አቅርቦልናል።

ይህ የሚያሳየን የትግሬዎች ፋሺስዝም ብሎ ብሎ ወደ እዚህ ወንጀል እንዴት እንደተሻገረና ሕዝቡ ወደ ጭለማ እየተጓዘ እንደሆነ የምናይበት መስተዋት ነው። ይህ ሁሉ ወንጀል ፈጽመው ሲያበቁ በድርጊታቸው ሳይጸጸቱና ሳያፍሩ ፤ይህ አረመኔ ወንጀላቸው ደብቀው አሁን ደግሞትግራይ ሪፑብሊክ አንመሰርታለንእየተባለ እየተፎከረ በሌላ መልኩ ደግሞባንክ ክፈቱልን፤ ጤፍ ላኩልን፤ስልክ ጀምሩልንእየተባለ እየተጮኸ ነው። በአማራ ሕዝብ ላይ ጠብ የለንም ይላሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የአማራን ልጆች ከጦሩ እየለዩ ሲረሽኑ ነበር።

አምሳለቃ ጋሻዬ እንኳን ተረፍክና ይህንን ጉድ ነገርከን! ወጣም ወረደ ግን አብይ አሕመድና ወያኔ ሁለቱም ለዚህ ሁሉ ወንጀል ተጠያቂዎች ናቸው!!>>፡ ይላል ከታፈኑት  የሠራዊቱ አባላት አንዱ በ”የተከዳው የሰሜን ዕዝ” በሚለው መጽሐፉ ያስቀመጠው።

የትግሬ ፋሺሰት ጀሌዎች ዛሬም ለከፋ መከራ እያከኩ እሳት በመጫር የራሳቸውና የጎረቤት ሕዝብ ህይወት ለማጥፋት እየተመኙ ነው። ምሕረት ይስጣችሁ ከማለት ምን ማለት ምን እንበል?

በመጨረሻም የጦርነቱ ዓላማ ምንንት የግንጠላ ዓላማ ነው እያል ስንከራከር ያላመናችሁን ሁሉ አሁን “ከፈረሱ አፉ” ከታጋዮቹ  አንደበት ለማስረጃ አቅርቤአለሁ። ሰነዱን ብትቀባበሉት ለታሪክ ይረዳል።

መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)