Sunday, May 11, 2008

The 1941 Miracle in “Omedla” where the Flag & the king was encircled at a touch of a distance by a Rainbow. Miracle? Indeed










ጀግኖች ሆይ ሰማዩ ስለኛ ምን ይላል?




<አፄ ሃይለሥላሴም ሆኑ አፄ አምሃሥላሴ የምንመለከታቸዉ እንደተራ ሰዉ ነዉ።የአፄ ሃይለሥለሴ ቀብርም እንደተራ ሰዉ ሊፈፀም ይችላል። አፄ አምሃሥላሴም እንደተራ ሰዉ ሀገራቸዉ ሊገቡ ይችላሉ። ለመኖሪያቸዉም ሆነ ለጥበቃቸዉ ሃላፊነት የለብንም። የራሳቸዉ ጉዳይ ነዉ>>>> መለስ ዜናዊ -የህዋሕት መሪ (ምንጭ ዶክተር ጌታቸዉ መካሻ፦ ምንሊክ ቅፅ 2 ቁጥር 18 ጥቅምት 1993)






<<በማይጨዉ በመቀሌ በኩል…. መች ይገባ ነበር፤ በሰማይ ላይ መጣ በማናዉቀዉ አገር!>>




አንዳንድ ሰዎች አባቶቻችን ከወራሪ ጠላት ጋር ተናንቀው በድል የገቡበትን የድሉ ወራት የሚቆጥሩት ሰንደቅ ዓላማችን “ኦሜድላ” ጎጃም ዉስጥ በሱዳን ድመበር አጠገብ በንጉሱ እጅ የተሰቀለችበት ጥር 12 1933 ሲሆን፤ የሚከበረዉ ግን ሚያዚያ 27/1933 ዓ.ም ነዉ። ሁሉም የየራሳቸዉ ምክንያቶች ቢኖራቸዉም፤ ጣልያን ዉድ አገራችን ኢትዮጵያን ለመዉረር ሁለቴ ሞክሮ በጀግኖች ልጆቿና መሪዎቿ ተጋድሎ አልተሳካለትም። ጠlላት “ኤፒሪት” የተባለ በበርሜል የታሸገ መርዛማ ጋዝና የተለያዩ መረዛማ የዘይት ቦምቦች ከሰማይ በአይሮጵላን እንደ ዝናብ ባለማቋረጥ እየረጨና እየደበደበ ህዝቡንና አርበኞቹን ቢያፍንም ብዙ መከራ ችሎ መጨረሻ ላይ ድል ተመታ።




ይህ በአርዕስቱ ላይ የቀረበዉ ሽለላ (ቀረርቶ) በወቅቱ ካንድ ስሙ ባልታወቀ ኢትዮያዊ አረበኛ በጦር ሜዳ ሲዋጉ የተደመጠ ነበር።ፋሽስት ጣልያን በረጨዉ የኤፕሪት መርዝ ምክንያት የመጠጥ ዉሃ፤ወንዝ፤ሰብል ተመርዞ በብዙ ሺህ የሚገመት ሰዉ አለቀ።ዕጽዋቶች ስለተመረዙ ጠወለጉ፤ደረቁ፤ አገሪቱ ወደ ምድረበዳ ተለዉጣ፤ገጠሮች ጭር ፤ብለዉ ቤቶች ተዘግተዉ፤ ፊቷ ገርጥቷል።ከባድ ድንጋጤና ሞትን አስከተለ። ብዙ ስቃይ አለፈ።አርበኞች ሲወድቁ፤ ባንዳዎች ከጣልያን ጋር ሆነዉ የገዛ አገራቸዉን ወጉ (የዛሬ ወያኔዎች “ናቕፋና ምፅዋ” ላይ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ሆነዉ ኢትጵያዊያን አርበኞች ወታደሮችን በዉስጥ ቅጥረኞች ተንኮል ሸርበዉ ፈጅተዉ የጠላቶቻችን የኤርትራ ወንበዴዎችን ሰማያዊ ባንዴራ ታቅፈዉ በየዓለማቱ እየዞሩ “ሓዳስ ኤርትራ” እያሉ ሲያዜሙ የጨፈሩት ዓይነት ክህደት!!)


ኦሜድላ፦ጃንሆይ ከስደት አገር በድል አድራጊነት ወደ አገራቸዉ ሲገቡ ጣልያን ኢትዮጵያን ከወረረ አራት ዓመት ከስምንት ወር በሗላ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ጥር 12 ቀን 1933 ዓ/ም የሰቀሉበት ቦታ ነዉ። በዚህ ታሪካዊ ቦታ፡ በጠላት እጅ ወድቃ የነበረችዉ ሰንደቃላመችን ለመጀመርያ ጊዜ ስትወለበለብ በዕለቱ በኦሜድላ የታየ ተአምር ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ የተነጋሩትን ልጥቀስ ፤-




“ከስደት በድል አድራጊነት ወደ ሃገራችን መብንመለስበት ጊዜ ጥር 12 ቀን 1933 ዓ.ም ኦሜድላ ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በሰቀልንበት ሰዓት ከሰማይ ቀስተ ደመና ዝቅ ብሎ ወርዶ በበላያችን ላይ ረቦ ተንሳፎ ነበር።> በአቡነ ቴዎፍሎስ የቀብር ስነሰርአት ላይ ሲናገሩ የተደመጠ ንግግር። ምንጭ (የዓፄ ሃይለስላሴ ታሪክ፤- በሪሁን ከበደ)።


ወደ ታሪኩ መለስ ብለን በጦርነቱ ጊዜ ስለ ንጉሡ ማዉሳት አስፈላጊ ይመስላኛልና ስለሳቸዉ የሚነገር የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ሃሰቦችን ያቀርባሉ። ጥቂት ሰዎች፤ ካዛዉንት፤ ካንዳንድ አርበኞችና አንዲሁም በጦር ሜዳዉና በፍዳዉ ያልነበሩ የዘመኑ ወጣቶችና ምሁራን ጭምር፤ ጃንሆይ ከጦር ሜዳ አንደሸሹና ዉጭ ሄደዉም ምንም እነዳልሰሩ እየተደረገ የሚነገር አለ። ሰዎች የመተቸት መብት እነዳለ ሆኖ፤ ሌሎች ደግሞ የሚያዩበት መነጸር ከነዚያ ለየት የሚል ስላለበት፤ ለማንኛዉም እዉነታዉን በማስረጃ የተደገፈ ታሪክ አቅርበን ከዛሬ ማንነታችን ጋር በማነጻጸር እንወያይ።




እኔ የማደንቀዉን የንጉሱን አርበኝትና አስተዋጽዖ፤ ምናልባት አንዳንድ የዘመናችን ምሁራን የንጉሱን አስተዋጽዖ ያናንቁት ይሆናል። በዚህ ላይ የምለዉ ነገር ፤ንጉሱ ከስርአታቸውና ከጊዜው አንጻር የሚችሉትን አድርገዉ አልፈዋል። ምሁራኖቻችን ከትችታቸዉ በፊትና ንጉሱን ካማሳነስ ተቆጥበዉ፤ ራሳቸዉ እየኖሩበት ያሉትን የዛሬዉን የዉርደት ኑሯቸዉ በጥሞና ራሳቸዉን መቃኘትና ራሳቸዉንና አገራቸዉን ነፃ የማዉጣቱ ሁኔታ ለምን አንዳልቻሉ አብሮ መመርመርና የራስን ጉድፍ ማየት፡ ካዛ ንጉሱን ቢተቹ ያምርባቸዋል እላለሁ። የማማሩ ጉዳይም ቢሆን ፤ገድላቸዉ አምሮ አነዲዘከር ከተፈለገ የተዘጉባት ወደቦችዋን መስከፈት ሲችሉ ብቻ ነዉ!! የዲሞክራሲዉ ኡኡታዉ ጋጋታዉ፤ ዉበቱ ፡ከዛ ክንዋኔ በሁዋላ ያምራል። “በሌለን አገር” ዲሞክራሲ ማዉራት እረኛ ጭር ሲለዉ የሚዘላብደዉ ቅንቀና ነዉ። እንቀጥል! እኛ ምን ሰራን? ንጉሱስ ምን ሰሩ?




የንጉስ ተፈሪ የዲፐሎማቲኩና የጦር ሜዳ ዉሎ፦
የዲፕሎማሲዉ ዉሎ ረዥም በመሆኑ በይደር አናቆየዉ።ከዘህ በታች የምንመለከተዉ የንጉሱ የጦር ሜዳ ዉሎ ደራሲ አቶ በሪሁን ከበደ ከጻፉት “የዓፄ ሃይለስላሴ ታሪክ” የተገኘ የታሪክ ማሕደር ነዉ።ታሪኩ የቀረበዉ ቀለል ባለ በማይሰለች ከረዢሙ ታሪክ አጥሮ የቀረበ ነዉ (ረዣዥም ክንዉኖች ራሴ እየቆረጥኩ ከማሀልና ከመደምደምያዉ ጋር አጥሮ እንዲገናኝ አሳጥሬዋለሁ)።




ለዚህኛዉ አካባቢ ዉግያ 150 አይሮፕላኖች ተሰልፈዋል።የሚጥሉት ቦመብ ትልቅ፤ ትንሽና መካከለኛ ሆኖ ገሚሱ እንደወደቀ ቆይቶ ሚፈነዳ ነዉ። የጋዝ መርዙ ደግሞ ገሚሱ በሽታ (ሲሸትህ) ሚገድል፤ ገሚሱ ዓይን የሚያሳዉር፤ገሚሱ በፈላ ዉሃ እነደተጠበሰ አካላትን የሚያጉረበርብ ነበር። የተጠቀሱት አይሮፕላኖች ባንድነት እየተነሱ ኤፕሪት መርዝ በኢትዮጵያ ወታደር ላይ ሙሉዉን ቀን አዘነቡት። በዚህ ጊዜ የክብር ዘበኛዉኛም.ሲቪሉም በንጉሱ እየተማራ ያለቀዉ አልቆ የተረፈዉ ሲዋጋ ፤ሲቪል ሰረዊቱ በዚህ ቦመብ በጋዝ መረዝ ስለተረበሸ ወደ ሗላ መመለስ ጀመረ።




በዚህ ጊዜ ንጉሱ ጎራዴያቸዉን መዝዘዉ የቦምብና የመድፍ ነበልባል የመትረየስና የጥይት ዓረር በሚያፏጭበት መሃከል ገብተዉ ወዲያና ወዲህ እየተንጎራደደዱ በሚዋጉበትና በሚያዋጉበት ሰዓት የሚሸሸዉን ጦር አይተዉ በአዳራሹ ምን ብለህ ፎክረህልኝ ነበር? አሁን አኔ ንጉሰ ነገስትህ ፊቴን ሳልመልስ በመሃከልህ ሁኜ በመዋጋት ላይ እያለሁ እንዴት እኔን ጥለህ ወደ ሗላ ታፈገፍጋለህ? ብለዉ ሲወቅሱት፡ ይህ ንግግራቸዉ የሰራዊቱን ልብ አንደጦር ስለወጋዉ እንደገና እየተመለሰ በጦርነት ዉስጥ እየገባ ብዙ ስራ ሲሰራ ታይቷል።ይህነን የመሰለ ታላቅ ጦርነት የተደረገው የወታደር ክብር እንዳይዋረድና የኢትዮጵያ የዠግንነት ታሪክ እነዳያድፍ ለመጋደል ነበር።አንጂ የድሉ አክሊል በጣልያን እጅ የሆነዉ “በብሬሲና በቶሪኖ” ፋብሪካዎች አቋቋቁሞ መድፍና መትረየስ ታንክና ቦምብ የጋዝ መርዝና ኤኢሮፕላን በሰራች ጊዜ ነዉ።


ኢጣልያና ኢትዮጵያ ጦርነት ካደረጉ ጀምሮ በማይጨዉ የተደረገዉን ጦርነት የመሰለ ጦርነት ተደርጎ አያዉቅም ይባላል።ንጉሰነገስቱ ባሉበት የኢትዮጵያ ሰራዊት ለዘላለም ሕሊናን ማይወቅስ አኩሪ ሥራ ከሠራ በሗላ በጋዝና በመርዝ በቦምብ ተፈታ። ንጉሰነገስቱም ከጥዋቱ አስከ ሌሊቱ 5 ሰዓት ድረስ ተዋግተዉ ጦሩም ስለተፈታና ሌሊቱን ወደ ባዕታዋዪ ስለተጓዘ፤ ጃንሆይም ወደ ሰፈራቸዉ ወደ መሐን ተመለሱ። መጋቢተ 23 ቀን ረቡዕ መሐን ላይ ዉለዉ አድረዉ ቁስለናኛዉን ሲያስነሱ የሞተዉን ሲአስቀብሩ ዋሉ።




መጋቢት 24 ቀን ሀሙስ ምክር ተደርጎ ጦሩ ከማክሰኞ ሌሊት ጀምሮ ወደ ባዕታዋዪ ስለተጓዘ ወደዚያዉ ወታደሩ ወዳለበት እንሂድና ጦሩን አሰባስበን ቦታም ይዝን እንዋጋ። አሁን ካለንበት ቦታ ሁነን ለመዋጋት አንደገና ያለዉ ጦር አነስተኛ ነዉ፤ ሁለተኛም ቦታዉ አመች አይደለም የሚል ሃሳብ ከጦር አለቆቹ ቀረበ። ንጉሰነገስቱ ግን፤ እግራችን ከዚህ ከነቀልን የተበተነን ሰራዊት ሰብስቦ መዋጋት የሚቻል አይመስለኝምና ከዚህ ያለነዉ ብንዋጋ ይሻላል። የሚለዉ ሃሳብ ቢያቀርቡም፤ ባዕታዋዩ ሄደን ከዚያዉ ሁነን ብንዋጋ ይሻላል ሚለዉ ድምጽ ስላመዘነ፤ መጋቢት 24 ቀን ከሌሊቱ 6 ሰዓት ከመሐን ተነስተዉ ወደ በዕታዋዩ ሄዱ።


ባዕታዋዩ አንደደረሱ፡ ምከክር ተደረጋና ቁልፍ ቁልፍ የሆኑ 4 ቦታዎች ተመረጡና አነዲያዙ ተወሰነ።ጣልያንን በእግር ከመጣ ለመግጠም ሲጠባበቅ የነበረዉን ዝግጅት፤ ጣልያን በእግር መምጣቱ ትቶ መሐን ላይ አዲስ ምሽግ አዘጋጅቶ በመድፍ መደብደቡን መርዝ ማፍሰሱን ቀጠለበት። በዚህ ጊዜ ጦሩ ብዙ ጉዳት ስላደረሰበት አሁንም ተፈታና ፊቱን አዙሮ ወደ ኮረም ጉዞዉን ቀጠለ።




ከዚህ በሗላ በባዕታዋይ የነበረዉን ስነቅና ትጥቅ ለጦሩ አነዲታደል አድርገዉ ከዕደላ የተረፈዉን ልኬታዉ ያልታወቀዉን ስነቅና ትጥቅ ጠላት እነዳይጠቀምበት በእሳት እነዲቃጠል አድርገዉ፤ ዓርብ መጋቢት 25 ከምሽቱ 3 ሰዓት ተኩል ወደ ኮረም ጉዞ ጀመሩ።መጋቢት 26 ቅዳሜ ጥዋት አሸንጌ ደረሱ። በወቅቱ ራሱ ጣልያን ያመነበት 68 መኮንኖች፤ 332 ነጭ ለባሾች 876 ጣልያኖች እንደሞቱና 36 አይሮፕላኖች ተምትተዉ መዉደቃቸዉ አሱ ካመነበት 73 ቶን በላይ የሚመዘን የመረዝ ቦመብ መጣሉን ራሳቸዉ ጸፈዉታል።ነገር ግን የሞቱባቸዉ ከዛ በላይ ነዉ።
ከማይጨዉ ድል ሆኖ የተመለሰዉ ጦር ሄዶ የሰፈረዉ በባዕታዋዩ ነበር። ጦሩ በባዕታዋዩ ሄዶ ሲስፈር ጃንሆይ ግን የለቱ ዕለት ጦሩን ተክትለዉ ባዕታወዩ ተከትለዉ አልሄዱም።ለማይጨዉ ቅረብ ሆኖ ከሚገኘዉ መሐን ላይ መጋቢት 23 ቀን ረቡዕ የሞተዉን ሲቀብሩ ዉለዉ ነዉ መጋቢት 24 ቀን ሐሙስ ጦሩ ወደ አለበት ባዕተዋዩ የሄዱት።


ሠራዊቱ ከጠለላት አይሮፕላን ለመዳን ገዞዉ በሌሊት ቢያደርግም ቀደም ሲል ጣልያን ሲሰበካቸዉ መሣርያ ያስታጠቃቸዉ ገንዘብ የሰጣቸዉ የራያና አዘቦ ኦሮሞ በየመንገዱ እያደፈጡ ሠራዊቱን ይፈጁት ጀመር።የሰዉ አገር ሊቀማ ነፃነት ሊገፍ ከመጣዉ የጋራ ጠላት ጋር ሲዋጋ ቆይቶ ድል ሆኖ ለሚመለስ ወገን እሕል ዉሃ ከማቀበል፡ ያም ቢቀር መንገዱን ሸኝቶና መርቶ መስደድ ሲገባ ቁስለኛ ተሸክሞ በደከመ ጉልበቱ በተራበ አንጀቱ ሚጓዘዉን ሠራዊት በየቦታዉ እያደፈጡ መግደል ይቅረታ የማይሰጠዉ የጭካኔ ታሪክ ነዉ።


ጦሩ ይህ አልበቃ ብሎት ሌሊቱን መጓዝ ትታችሁ በቀን ብትጓዙ አይሮፕላኑ አይነካችሁም፤ ንጉሱን አንጂ አናነተን አይደለም ብሎ ወረቀት በትኖ ሕዘቡ እዉነት መስሎት አምኖት በቀን መጓዝ ሲጀምር የመርዝ ዝናብ የሚረጭ አዉሮፕላን አዘጋጅቶ በመረዝ ፈጀዉ።



አንግዲህ ልብ በሉ! የሞተዉን ሲቀብሩ ዉለዉ መጋቢት 24 ጦሩ ወዳለበት ወደ ባዕታዩ ጦሩን ተክትለዉ የተበተነዉን ጦር አሰባስበዉ መመርያና ምክር ሰጥተዉ ሞራሉን ገንብተዉ ካሉበት አንደገና እዛዉ ቦታ ላይ ለመዋጋት ሲጠባበቁ የጠላት ጦር በእግር መዋጋቱን ትቶ ንጉሱ ባሉበት በመድፍና በመረዝ ያይሮፕላኑ ድብደባ ምክንያት መላወሻ ስላሳጣዉና በዚህ ስለተረበሸ ጦሩ ፊቱን ወደ አሸንግ እነዳዞረ ይታወሳል።




ከዚያ በሗላም ጃንሆይ አብረዋቸዉ ከቀሩት ጥቂት ታማኞቻቸዉ ጋር ሆነዉ ከዘሁ ተዋግቶ ከመሞት ጊዜና ቦታ እየለዋወጥን እየመረቱ መዋጋት ይሻላል ተብሎ ስለተምከረ በዛ የነበረዉ ስነቅና ትጥቅ እዛ ላለዉ ወታደር አከፋፍለዉ የቀረዉ ተቃጥሎ ወታደሩ ወዳለበት ወደ አሸንጌ እንደተከተሉት ልብ በሉ።




እንግዲህ <<በኢትየጵያ የጦር ታሪክ ሕዘቡ ንጉሱን ተከትሎ ይሔዳል አንጂ ንጉሱ ሕዘቡን ተከትሎ ሲሄድ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። አሁን በማይጨዉ ጦርነት ሲደረግ የሆነዉ ግን ሕዘቡ ሲቀድም ንጉሱ ሲከተለዉ ነዉ።>>
የኢትዮጵያ ህዘብ ንጉሰነገስቱን ቃል አክባሪ እነኳን ንጉሰነገስቱ ከታች ከስር አለቃዉን ፊቱን ካላዞረ የማይፈታ ኩሩ ሕዝብ መሆኑን በተደረጉት ጦርነቶች አስመስክሯል። በዚህ በማይጨዉ ጦርነት ግን ታይቶ የማይታወቅ አንግዳ የሆነ፤ በሰማይ ጦር ስለመጣበት ከጭንቁና ከሞቱ የተነሳ በኢትዮጵያ የጦር ታሪክ ተደርጎ የማያዉቅ ነገር ሲደረግ ታየ።ለዚህም በጦርነቱ የነበረ አንድ ወታደር እንዲህ ሲል አቅራራ (ሸለለ) ይባላል።


<< “በማይጨዉ በመቀሌ…..በኩል መች ይገባ ነበር፤ በሰማይ ላይ ገባ በማናዉቀዉ አገር!!!>>


ኢትዮጵያ ለዘላለም በነፃነትዋ ትኑር!
ጌታቸዉ ረዳ


ሳነሆዘ ካሊፎርኒያ


አሜሪካ (ሚያዝያ 2000 ዓ.ም)