Monday, May 11, 2020

ከሞት ጋር መጋጨት የአብይ አሕመድ አይቀሬው ዕጣ ፈንታ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


ከሞት ጋር መጋጨት የአብይ አሕመድ አይቀሬው ዕጣ ፈንታ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
የመጽሐፍ ቅዱስ አባባል ይመስለኛል፡ “በሰይፍ የመጣ በሰይፍ ይሄዳል” ይላል። አብይ አሕመድ ካሳደጉት የርዕየተዓለም አስተማሪዎቹ ኦነግ እና ወያኔዎች፤ ለየት ባለ መንገድ ወደ ሥልጣን ሲመጣ የውጭ ሃይላት ተጨምረውበት ‘ያለ ሰይፍ’ ያለ ብረት’ ሠልጣን ተቆጣጥሯል። በወቅቱ ሠልጣን ላይ የነበረው ወያኔ ባላሰበው ሁኔታ ድንገት ቁማር ተበላ።

እዚህ ላይ መዘንጋት የለለበት ለአብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣት ትልቁ ሚና የተጫወተው “ሕዝብ” እራሱ ነው። አስገራሚ የሚያደርገው በታሪክ የልታየ “ዕልል እያለ ገዳዩን ተሸክሞ ዙፋን ላይ እንዲቀመጥ ፈቅዶ፤ ሳምንት ሳይሞላው አገሪቱ በደም ማዕበል አስዋኛት። ረጋ በል እያልን ያስጠነቀቅነው ሕዝብም እምቢ ብሎን ዕልል እያለ ወደ ዕብደት የተለወጠው ‘አሽቃባጭ ሕዝብ’ በቅጽበት ዕሪታውን አቀለጠው”። ሞት ግድያ መፈናቀል፤ጠለፋ ዝርፍያ፤ሥርዓተ አልባ ሰፍኖ አገሪቱ “እያሪኮ” ሆነች።አገሪቱ “ደም፤ደም” ሸተተች።

አብይ አሕመድ የሥልጣን ጥመኛ ብቻ ሳይሆን የፋሺሰት ርዕዮት ተከታይ እና የፋስት ሕገመንግሥት አክባሪ በመሆኑ፤ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትም እጅግ ስለሚጣላ አማኞችዋ ሰንደቃላማቸው እየተነጠቁ፤ አንገታቸው በካራ ሲቀነጠሱ፤በዋይታና በዕሪታ ሲታመሱ “እኔ የቀበሌ ሚሊሺያ አይደለሁም ‘አልቃሽ ሕዝብን” “ሶፍት ቲሹ” ማቀበል ሰልችቶኛል፤ “እኔ ምን አደርጋለሁ”.. እያለ በአማኞች እሪታና ሞት ተሳለቀ። በሚገርም ሁኔታ ብዙዎቹ የሥልጣን ጥመኞችና ጨካኝ አምባገነኖች ቁጣ በተሞላው ሕዝብ ወይም በተንኮለኛ ገዳይ  እጅ ይልቅ ብዙዎቹ ረዢም ዕድሜ ያስቆጠሩ አምባገነኖች በእርጅና ወይም በበሽታ የመሞታቸው ዕድል ከፍተኛ ቢሆንም የዚህ ሰው ዕጣ ፈንታ ግን ልክ እንደ መለስ ዜናዊ እንደሚሆን መገመት ይቻላል።

ከ1966 ዓ.ም እስካሁን ድረስ በነበርንበትና በታዘብንበት ታሪካችን መለስ ብየ ስመለከተው አምባገነኖቹ በዜጎች ህይወት ዘገናኝ የጨካኜ ዕርምጃዎች በመፈጸምና በማስፈጸም የሄዱበት መንገድ ዛሬም ቀጥሏል፡፡

በሚገርም ሁኔታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያሰቃዩት የነበሩት መሪዎቹ ሲሞቱ አስከሬናቸው እያለቀሰ የሚሸኝ ሕዝብ መሆኑን  በአፍሪካ ውስጥ ምናልባትም  በዓለም ከኮርያ ሕዝብ ቀጥሎ ሁለተኛ ፍጡር ያደረገዋል። ዕልል እያለ ይቀበላቸዋል፤ ዕደሜውን ሙሉ ያስለቅሱትና፤ሲሞቱ ደግሞ እያለቀሰ የአምባገነኖችን ሬሳ ይሸኛል። ሙሴ ሲሉት የነበረውን አብይ አሕመድ “ይሁዳ አስቆረታዊ” ነህ አሉት። ዛሬም እየሆነ ያለው የአብይ አሕመድ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን ብላችሁ በሃሳብ ለምትዋዥቁ ጠያቂዎች ዕታ ፈንታው በሦት ሃይሎች በሚተኮስበት ጥይት የሥልጣኑ መጨረሻ ይሆናል።

አበይ በወያኔዎች ጥይት ይሞታል፤ አብይ በኦሮሞ ጽንፈኞች ይገደላል፤ ሦስተኛው  ግብፆች ቅጥረኞችን በማሰማራት አብይን ይቀጩታል። ያ አይሆንም የሚል ሰው ካለ የመጨረሻው ዕጣ ፈንታ ወያኔዎች የሥልጣን ውርደታቸውን ለማካካስና ወያኔዎች ኢሳያስን ለማስገደል ያሴሩበትን የ20 ሚሊዮን ዶላር ሴራ ተብሎ እየተነገረ ያለው ምስጢር ለማካካስ ሲሉ አብይን መግደል ካልቻሉ የመጨረሻ እርምጃ ከፍተኛ ጦርነት በማስነሳት የተጧጧፈ ወግያ በመክፈት ኢትዮጵያን እንድትታመስ ያደረጋሉ።

ይህንን ለማድረግ የአብይ አሕመድን መንግሥት “ለመበተን” አዲስ ወታደራዊ ሃይል ካመዘጋጀታቸው ሌላ አሁን የኢሕአዴግ ወታደር ተብሎ እተጠራ ያለው ሠራዊት በጥሞና አድብቶ ሁኔታውን እየተከታተለ ያለው ውስጥ ለውስጥ እየተነጋገረ ያለው በወያኔ ነባር ታጋዮች የተጠቀጠቀ ስለሆነ፤ በቀላሉ አገሪቷን ወደ ቀውስ የመውሰድ ዐድሉ 100% ነው። የሳሞራ የኑስ እና የውጭ አገር ጀሮ ጠቢው ጻድቃን ገብረተንሳይ የሳምንቱ ዛቻና ማስጠንቀቂያ ለአብይ አሕመድ አስፈሪ ‘መርዶ’ ቢሆንም በዋናነት ግን አገሪቱ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንደምትገባ የማይገምት ሰው ካለ በሕልም ውስጥ ነው።

ወያኔዎች አብይን ወደ ቀውሱ ለማስገባት ሲፈልጉ ምልከቱም አብይ አሕመድ ያስሰማራቸው የብልጽግና “ሳተላይቶች” ተብለው የሚጠሩት አጼ ምኒሊክን በመኮነንና በመወንጀል ጊዜውን ያባተለ “ሓተታ 70 እንደርታ” በሚል የትግርኛ መጽሐፍ የጻፈ ሱሑል ሚካኤል የሚባለው እና የብልጽግና አባላት (ዓረና) ጨምሮ በመሰወር/በመግደል፤በማሰር“ ወያኔ ከአብይ አሕመድ ጋር ያለው ቅራኔ በማባባስ ወደ ጦርነት ያመራል። ይህ ትንታኔ የማይቀበል ሰው ካለ የትግራይ ፋሺስቶች ባሕሪ ያልተገነዘበ ነው። አብይ አሕመድ በወያኔዎች እና በጽንፈኛ ኦሮሞዎች ወይንም በግብጾች ሴራ ጥርሱን እየፋቀ ከሞት ጋር የሚጋጭ አጭር ዕድሜ ያለው ንጉሥ ነው።