Saturday, May 23, 2020

ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነው ለሚሉ ሁሉ የሰጠሁት መልስ ጌታቸዉ ረዳ Ethiopian Semay ሳን ሆዘ ካሊፎርንያ አሜሪካ ግንቦት 1991 ዓ/ም የተዘገበ Sunday, May 23/2020


ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነው ለሚሉ ሁሉ የሰጠሁት መልስ
ጌታቸዉ ረዳ
Ethiopian Semay
ሳን ሆዘ 
ካሊፎርንያ አሜሪካ 
ግንቦት 1991 /  የተዘገበ
Sunday, May 23/2020
ይህ መልስ የግንቦት 7ቱ አመራር አባል ንአምን ዘለቀ ኢሳያስ የኢትዮጵያውያን ወዳጅ ነው ብሎ በፌስቡከሉ በጻፈው አሳፋሪ ድጋፍ መልስ ነው።  ይህ ሰነድ በመጽሐፌ ውስጥ በሰነድ ከተዘገበው የታሪክ ማሕደር  ለናንተ እንዲያመች አሳጥሬ ያቀረብኩት የታሪክ ማስረጃ ነው። ኢሳያስ በአገራች ዜጎች በመላው ኤርትራ  አውራጃዎች የተፈጸሙ  ግፎች  እና ወንጀል ተመልክታችሁ መፍረድ የናንተው ድርሻ ነው። እኔ ያለኝን አቅም ለማሳየት ክሬአለሁ።የመፍረድ የናንተ ነው።   በክፍል ሁለት “ታማኝ በየነ እባክህን ከግንቦት 7 አንዳርጋቸው ጋር የተሸላለማችሁበትን አንበሳችሁን አምጣ በለው እና በምትኩ የመሪህን የፒኮክ አርማ ሸልመው!  የሚል ትችት በሚቀጥሉት ቀናቶች አቀርባለሁ። ሑን ወደ ተነሳሁበት ትችት ልግባ።

ኢትዮጵያዊያን አሥመራ ዉስጥ በጥይትና በዱላ ሲደበደቡ ወያነ ትግራይእሰየዉ!” ያለበት የታሪክ ማሕደር ስል ያቀረብኩት መከራከሪያ እነሆ።
የፎቶግራፍ ማሕደር (1) 1983 / ከኤርትራ የተባረሩ ኢትዮጵያዊያን አዲስ አበባ ፕላስቲክ መጠለያ ውስጥ የሚኖሩት ዜጎቻችን ናቸው። ከላይ በፎቅ ላይ የተያያዘው ፎቶግራፍ ማለት ነው።

ከጥሎ ያለው ፎቶ ኤርትራ ብትገነጠል ጦርነትና ስቃይ ይቆማል ሲሉ የዋሹንን የዉሸታቸዉ ማስረጃ የሆነዉ ማህደርና ለኤርትራኖች ስደቱና ለመከራዉአማራ” ነዉ እያሉ ሲከሱት የነበሩትንዛሬ አማራ ኤርትራ ዉስጥ በሌለበት ጊዜ” ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያጥይትወደ ተኮሱባት አገርኢትዮጵያበሺዎቹ ተሰድደዉ በትግራይ መጠለያ ዉስጥ የሚኖሩ ናቸዉ።

 3ኛዉ ፎቶግራፍ፤- የስነልቦና ምህርት / ትዝታ ገብሩ ናቸዉ።በ1983 የተፈናቀሉትን ኢትዮጵያዊያን ለመርዳት ከዉጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ ሄደዉ ያዩት አሳዛኝ ሁኔታ ያብራራሉ። ወደ ታሪኩ እንግባ። 


አህያን የጦር ሠራዊት ልብስ አልብሰዉ 
የጦር ሠራዊት ጫማ አድርገዉለት በለዉ ዉሽ 
እያሉ ኢትዮጵያዉያኖችን አህያዉን እያሳዩ ነበር 
የሚደበድቡን……” "ከዱላ ከጥይት” ተረፈዉ መንገድ ላይ እየንተጠባጠበ እንዲሞት የሚያዳክሙበት ዘዴ ነበር።ሕዝቡ አየዘፈነ "በስድብ በዱላ" እየደበደበን፤ "10 አመት ልጅ የወደቀ ክላሽ አንስቶ ነበር ሰዉ “የሚገድለዉ።የወጣዉ። ከሰዉ ልጅ የማይጠበቅ ከእንሰሳ ያልተሻለ አስተሳሰብ የነበራቸዉ ያን ጊዜ ነዉ።ሲማቱ አንገት እግር እጅ አይሉም ዝም ብለዉ ነዉ ያገኙበት ቦታ ላይ ብቻ "አድጊ!!" እያሉ ትግሬዉን ";ቅማላም" አማራዉን "አህያ" እያሉ ነበር በዱላ ይደብድቡን ነበር።


 ባጠቃላይ መንግስት ተፈናቃይነታችን በግልጽ የተቀበለዉ አይመስለንም።ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ፍቅር በነበረችበት ወቅት ኢሳያስ አፈወርቅ አዲስ አበባ መጥተዉ በነበረበት ወቅት ኤርትራ ያፈናቀለችዉ ሰዉ የለም" ሲሉ የኛም ባለስልጣኖች ትክክለኛ ናቸዉ ብለዉ ነበር ያረጋገጡላቸዉ። እኛ ደግሞ ኢሳያስን ክሕደት ስንሰማ ኢሳያስ በተጠቂዎች አገርም መጥተው ይህንን ሲናገሩ መሪዎቻችንም አብረው ውሽትን ሲደግፉ ስንገነዘብ አገር እንደሌለን አመንን፡ እጅግም ነው በመገረም የተዋጥነው>>


  (ከኤርትራ በግፍ እንዲወጡ የተደረጉ ኢትዮጵያዊን ከተናገሩት ጥቅስ የተወሰደ


እንባ እንባ ይለኛል ይተናነቀኛል 
ግን እንባ ከየት አባቱ
ርቋል ከረጢቱ 
ሳቅ ሳቅም ይለኛል 
ስቆ ላይስቅ ጥርሴ 
ስቃ እያለቀሰች 
መከረኛ ነብሴ።” 
(ደራሲ በአሉ ግርማ ከኦሮማይ መጽሃፍ።



ወሩ ግንቦት ነዉ። ወያኔ የተባለ ጸረ ኢትዮጵያ ቡድን ኢትዮጵያን የተቆጣጠረበት ወር ነው። ጊዜ ያረጃል ይላሉ። እያረጀ በሄደ ቁጥር አስታዋሽ ሲያጣ በሂደቱ (በወቅቱ) የተፈጸሙ ወንጀሎችና የድርጊቱ ፈጻሚዎች፤ በህዝቡ ሕሊና አየተረሱ መሄዳቸዉ እርግጥ ነዉ። ወያኔዎችና ሻዕብያዎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸሙት ከባድ ወንጀልና ክህደት አስታዋሽ እያጡ በተረሱ ቁጥር፡ ወያኔዎቹ መኩራራቱን እየቃጣቸው ነዉ። የዋሃን አድናቂዎቻቸዉምስለ ኢትዮጵያዊያን ቤዛ የሚሄዱ፤ የሰላም ሰዎችእያሉ ያሞጉሱዋቸዋል (መታደል ይሉታል ይሄ ነዉ!) እንደ እነ ንአምን ዘለቀ እና አንዳርጋቸው ጽጌ ብርሃኑ ነጋ ኤፍሬም ማዴቦ መሳይ መኮንን ፋሲል የኔአለም፤ ሲሳይ አገና፤አምባሳደር ካሳ ከበደ  …..የመሳሰሉትንም ኢሳያስ የኢትዮጵያውያን ወዳጅ ነው እያሉ ያሞግሱታል፡ ስለዚህም ተቸግረናል።

ማሕደሮች ህያዉ አስካልሆኑ ድረስ አዲሱ ትዉልድ ከመረጃ እጦትና ከማንበብ ልምድ አንጻር ደካማ በመሆኑ የወንጀለኞቹ ድርጊቶች ደጋግመን ማስተወስ ሊኖርብን ነዉ። ለዚህም ነዉ በዚህ ዓምድ ባለፉት ጊዜያቶች የተፈጸሙ ብሄራዊ የታሪክ ክህደቶችና ወንጀሎች ደግመን ላላወቁ መልሰን ለማሳወቅ፤ላወቁትም ቢሆን በቸልተኝነት እንደቀላል ነገር ተደርጎ ከሕሊናቸዉ እንዳይረሳ ለማስታወስ ዋና ዋናዎቹ ወንጀሎቻቸዉን እየመረጥኩ ለአንባቢዎች አቀርባለሁ። 


በዛሬዉ ዓምድ የቀረበዉ የወየኔና የሻዕብያ የወንጀል ማሕደር ሪፖረተር መጽሄት መስከረም 1991 / ዕትሙ ላይተፈናቃይነታችንን መንግሥት በግልጽ የተቀበለዉ አይመስልምበሚልየኤርትራ ተፈናቃዮች ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴለሕዝብ ያስተላለፈዉ ኡሮሮ/አቤቱታ ከመለስ ዜናዊ እና ከኢሕአዴግ የተሰጠ መግለጫ አንኳር ነጥቦችን እያጣቀስን ወያኔ ለኤርትራ ሕዝብ እንጂ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳልቆመ ከማስረጃ ጋር ታሪክ የዘገበዉ ድርጊታቸዉን አቀርባለሁ። አያይዞም ተፈናቃዮቹ አዲስ አበባ እንደገቡ ለስሙ መጠለያ ተብሎ እንድያርፉበት የተመደበላቸዉከፕላስቲክና ከቡትቶ ጨረቅ የተጠጋገነገሳ” (“ጋሳ”) መሳይ መጠለያ ቤቶች ዉስጥ በተፈናቃዮች ላይ የደረሰ አሰቃቂ ሕይወት በወቅቱ የዓይን ምስክሮች ከዘገቡት አብሮ ይቀርባል። እዚህ የቀረበዉ ላንባቢያን እንደሚመች የተቀነጨበ እንጂ ሙሉዉን አይደለም። ሙሉውን “የወያኔ ገበና ማሕደር” በሚለው መጽሐፌ ውስጥ ቀርቧል።


ይህ ዓምድ ሊቀርብ ምክንያት ከሆኑት አንዱ ምክንያትበጉንበት ወርዉስጥ በወያኔ የተፈፀሙ ወንጀሎች ለማስታወስ ሲሆን፤ ሌላናዉ ደግሞ 28 የጎንደር ገበሬዎች በሱዳን መንግሥት ወታደሮች ታፍነዉ ወደ ሱዳን እስርቤት ተወርዉረዉ በረሃብ ሲሰቃዩ፤ በዉጭ አገር የምንኖር ዜጎች የድረሱላቸዉ አቤቱታ ስናሰማ የመለስ ዜናዊ የዉጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ተቀዳ ዐለሙ እና ስዩም መስፍን ሀሰትበማለት ሁኔታዉ ከማጣጣላቸው በላይ፤ተቃቀወሚዉንበሬ ወለደብሎ በኮነነነበት ምላሳቸው፤ሊደብቁት የሞከሩትን ዜና በአገር ወዳዶች ጠንካራ ትግል የዜናዉ እዉነተኛነት ሊያምን ተገድዷል።

ተቃዋሚዉን ክፍልበሬ ወለደእያሉ ያልሆነ ሆኗል እያሉ ያወራሉ ሲል ተቃዋሚን የመኮነኑን ሱስ ፤በጎንደሩ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን1983 / ጭምር በሻዕቢያ መንግስት (ተብየዉ) ህፃናት በያዙ እናቶች ላይ ጥይት በጠራራ ፀሃይ እየተተኮሰባቸዉ በእሩምታ እየተገደሉ፤ የተቀሩት እየተደበደቡ፤ምራቅ እየተተፋባቸዉ፤እየተሰደቡ፤ተዋረደውና ተገፍተዉ ንብረታቸዉ እየተቀሙ የተባረሩት ኢትዮጵያዊያን ሠላማዊ ዜጎች (ትግሬዎችም ጭምር) መለስ ዜናዊና ድርጅቱ ስለድርጊቱ እዉነተኛነት እንዲያብራራ ሲጠየቅበሬ ወለደየተቃዋሚዎች ወሬ ነዉ፤ግፍ አልተፈጸመም (“ሀሰት”) ከማለቱ በላይ ፡የተባረሩትም ሰላማዊ ዜጎች ሳይሆኑ .የስለላና የግድያ ቡድን የነበሩ ናቸዉ። በማለት ሁንታዉ ለመደበቅ እንደሞከረ ይታወሳል። የዚህ ቡድን ድብቅ ምስጢሮችና ወንጀሎች ወደ ሗላ በወቅቱ የተዘገቡትን የታሪክ ማሕደሮች ምን እንደዘገቡ እንደገና መመልከቱ ስለሚረዳ፤ ያለቻችሁን ትንሽ የመዝናኛ ጊዜችሁንመስዋእት” (ተዘጋጅቶ ቀረበላችሁን የሕዘባችሁ ግፍ በነፃማንበብመስዋዕት ከተባለ ማለቴ ነዉ) በማድረግ የሕዝባቸሁን ግፍ እንድታስታዉሱ ይረዳችሁ ዘንድ እነሆ እነድታነብቡ እጋብዛለሁ። 


በዚህ አጋጣሚ የተፈናቃዮቹን እሮሮ በመጽሄቱ ላይ አሳትሞ ለሕዝብ እንዲዳረስ ላደረገዉ ለሪፖርተር መጽሄት ምስጋና እናቀርባለን። በወቅቱ የተዘገበዉ የተፈናቃዮቹ እሮሮ ታሪክ እንዲህ የሚል ነበር። 


"1983 . በኤርትራ በነበረ ሁኔታ የመንግሥት ለዉጥ ሲደረግ የኤርትራ ሕዝብና መንግሥት በተለይም ሻዕብያ እዚያ የነበርነዉ ኢትዮጵያዉያንን በከፍተኛ ግፍና በደል ነዉ ያባረረን። ይኸዉም በጥይትና በዱላ እየጨፈጨፈ ነዉ ከሃገሩ እንድንወጣ ያደረገን ኤርትራ ለኤርትራዉያን !ኢትዮጵያዉያን ከአገራችን ይዉጡ! አስከዛሬ የተቀመጣችሁት ይበቃል፤ በሃገራችን ላይ ሃብትና ንብረት አፍርታችሗል። ጆንያ እንኳን መያዝ አትችሉም። በማለት እየጠፈጠፉና እየደበደቡ ነዉ ያስወጡን። ትንሽም ንብረት የያዘዉን ሰዉ ቪድዮ እያስነሱና መኪና ላይ ከተጫነ በሗላ በረሃ ላይ ሲደርስ አዉርደዉ ባዶ እጁን ነበር የሚያባርሩት እና ባገራቸዉ ላይ ከዉስጥ ብረት ከላይ ጎማ በለበሰ ዱላ ነበር የሚጨፈጨፉን። "አህያ የጦር ሰራዊት ልብስ አልብሰዉ የጦር ሠራዊት ጫማ አድርገዉ በለዉ ዉሽ እያሉ ኢትዮጵያዊያኖችን አህያዉን እያሳዩ ነበር የሚደበድቡን።"


· እና በግፍ በመከራ በሞት ነዉ የወጣነዉ። በአሁኑ ሰዓት ተርፈን ያለነዉን ነዉ። በዚያ ሰዓት የተሰራዉ ግፍ ይህ ነዉ አይባልም። ያለ ቀለብ ሦስት አራት ቀን ሜዳ ላይ እንድንቀመጥ ከተሰቃየን በሗላ ነበር እየጨፈጨፉ የሚያባርሩን።ስለዚህ "ከዱላ ከጥይትየተረፈዉ መንገድ ላይ እየንተጠባጠበ እንዲሞት የሚያዳክሙበት ዘዴ ነበር።ሕዝቡ አየዘፈነ "በስድብ በዱላእየደበደበን፤ "10 አመት ልጅ የወደቀ ክላሽ አንስቶ ነበር ሰዉ “የሚገድለዉ" 


· እና በዚህ ሰዓት እናት አባት ልጅ እህት ተለያይተዉ በየሜዳዉ ላይ ነዉ የቀሩት እናት ህፃን ልጇን ታዝላ ስትሄድ ከመንገድ ርቀትና ካሳሩ ከምሬቱ የተነሳ ልጇን ጥላ ከበረሃ በስቃይ ነዉ የወጣችዉ። እና ብዙ ግፍ ነዉ የተሰራዉ። 


· በተለይም የጦር ሰራዊት ቤተሰብ ከሆነ ከተማ ዉስጥ እያዞሩ ከሗላዉ ህጻናቶች እየዘፈኑ ምራቅ እየተፉበት እየተዋረደ በዱላ እየተደበደበ ነበር የወጣዉከሰዉ ልጅ የማይጠበቅ ከእንሰሳ ያልተሻለ አስተሳሰብ የነበራቸዉ ያን ጊዜ ነዉ።ሲማቱ አንገት እግር እጅ አይሉም ዝም ብለዉ ነዉ ያገኙበት ቦታ ላይ ብቻ "አድጊ!!" እያሉ ትግሬዉን "ቅማላምአማራዉን "እያሉ ነበር ይደብድቡን ነበር። 


በዚያ ሰዓት እርምጃዉ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ ነበር፡በተለይም በመጀመሪያዉ ወቅት። በተለይ ትኩረት ተሰጥቶት የነበረዉ በአማራዉ እና በትግሬዉ ቤተሰብ ላይ እንዲሁም በሰራዊት ቤተስብ ላይ ነበር። አጋሜዎች አዉጡልን። ነዉ ያሉት ገና እንደመጡ።ከፍተኛ ጥላቻ ነበራቸዉ። ጥላቻቸዉ ደግሞ ከሻዕብያ አቀራረጽ የመጣ ነዉ። ህዘቡ ተቀርጿል። በተለይም ወጣቱ ክፍል።ወጣቱ ክፍል ገና ሻዓብያ ሲቃረብ ነዉ ጥላቻዉ የታየዉ። ምፅዋ ከተያዘ ጀምሮ ጥሩ አመለካከት አልነበራቸዉም። የጅምላዉጣ!” ነበር። 


ወደ ኢትዮጵያ ድምበር በገባን ጊዜ የህወሓት ሰራዊት ወደ መሃል አገር ስለነበር አላጋጠመንም። የትግራይ ህዝብ ነዉ የተቀበለን። ቁም ነገረኛ ህዝበ ነዉ ያለዉ እያካፈለ እንኳን ወደ ሀገራችሁ ምድር እግዚአብሔር አበቃችሁ ነበር ያለን። እና አካባቢ ሚሊሽያ አንጂ ሰራዊት አልነበረም። አገባባችን ብትንትነ ያለ ነበር፡ ግማሹ በዛላምበሳ ግማሹ በራማ ነበር የገባነዉ።ከአዲግራት አዲስ አበባ የገባነዉ ሐምሌ 18/1983 / ሲሆን የመጀመርያ ተፈናቃይ ጃንሜዳ የደረሰዉና ድንኳን የተከለዉ።ከመንግስት የቀረበዉ ጥያቄ ግን ያልጠበቅነዉ ነበር።የኤርትራ መንግስት 60.000 በላይ አፈናቅሎብኛል የሚል ጥያቄ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አቤቱታና ሪፖርት ያቀርባል ብለን ስንጠብቅ በአስቸኳይ መኪና ያቀርባል፤መጠለያ እዛ ስላለ ትሄዳላችሁ ተባልን። እዚያ በረሃ ዉስጥ ለዳግም መፈናቀል ስንጋበዝ በእዉነቱ መራራ ሀዘን ነበር የተሰማን። ይህንን በሰላማዊ መንገድ ለመንግሥት አቤቱታ ብናቀርብም ምላሽ አጥተን ከነበርንበት መጠለያ ከጃንሜዳ ከማዕከላዊ ግቢ ዉስጥ በዱላ ተባረርን ተፈናቃዩ ገና ደሴ ያለዉ ወደ አዲስ አበባ እየተጠጋ ነዉ፤መቀሌ ያለዉ ወደ ደሴ እየተጠጋ ነዉ፤ እዚህ ያለዉ ደግሞ እየተባረረ ነዉ።ግን ያን ዱላ ስናይ፤ መንግሥት ይህ ጉዳይ ያዉቀዋል ወይስ አያዉቀዉም? ኢትዮጵያ ነን ወይስ አይደለንም? ነበር ያልነዉ።በወቅቱ የኢትዮጵያ ዜጎች ካልሆን በሩ ተከፍቶልን ጥገኝነት ወደምንጠይቅበት መሄድ እንፈልጋለን።ብለን በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቀን ነበር። (በዚህ አጋጣሚ በሚገርም ሁኔታ ይህ ከተፈጸመ ከ7 አመት በሗላ ዛሬ አብይ አሕመድ አገዛዝ ዜጎች አዲስ አባባ ውስጥ ተመሳሳይ ጥያቄና እሮሮ እያስተጋቡ ነው።) በጠ// ልዩ ቤት የነበሩ አቶ ሰገድ ደባልቀዉ የተባሉ ሁኔታዉን በአስቸኳይ በማጤን አሁን በምታየዉ 21 መጠለያ ዉስጥ እልባት አስኪሰጣቸዉ ድረስ እንዲቀመጡ በማለት ትዕዛዝ ሰጡልን። 


በተቀመጥነዉ 7 ዓመታት ግን የአማራዉ ልማት፤የትግራይ ልማት እየተባለ ቴሌ ቶን እተዘገጀ አስፈላጊዉ ልማት መቋቋም ሲደረግ በአዲስ አበባ ዉስጥ እናያለን።ከ57.000 ያላነሰ ተፈናቃይ ለሰዉ ልጅ በማይገባ የእህል መጋዘን በተሰራ ቤት ዉስጥ ታጭቆ በተስቦ ብሽታ በቀን ሦስትና አራት ሰዉ እየረገፈ ኢትዮጵያ ሕዝብ በመገናኛ ብዙሃን ይሄን ያህል ተፈናቃይ አለ፤ ይሄን ተፈናቃይ ህዝብ ለመርዳት እንረባረብ የሚል ጥያቄ አልቀረበም።ይሄ የተፈናቃይ ስራ ስፈጻሚ ኮሚቴ በጣም ነዉ የተሰማዉ። 


…….እጅግ የሚያሳዝነዉ የተለያዩ ድርጅቶች ብራቸዉን ይዘዉ ቢሮአችን ድረስ መጥተዉ መሬት ስጡን ቤት እንስራላቸዉ ብለዉ ጠይቀዋል ለነሱ መሬት የምንሰጠዉ የለንም። ከአዲስ አበባ ይዉጡ ነዉ የምንባለዉ።እርግጥ መዉጣቱ እንፈልገዋለን፤ ሰርተን መብላት እንፈልጋለን። ክልሎቹ ደግሞ አንቀበላችሁም ብለዉናል። ይህነን አቶ ስምኦን መቻሌ በቅርብ መግለጫ ሰጥተዉበታል። የተወስኑ ክልሎች እንቀበላለን ሲሉ የተወሰኑ ደግሞ አንቀበልም ብለዋል። እና አቅጣጫችን ጉዞአችንም የጨለመብን ህዝቦች ነን።ባለቤት ለንም።………..በአሁኑ ጊዜ ቁጭ ብላችሁ መብላት አትችሉም ፤ባምስቱ አመቱ መርሃ ግብር መሰረት ሰርታችሁ መብላት አለባችሁ ብለዉ በምግብ ለስራ ፕሮግራም አዲስ አበባ ወረዳዎች ዉስጥ ያሉ የፈነዱ ሽንት ቤቶችና የዉሃ ቱቦዎች ሕዘቡ አጎንብሶ እየሰራ ነዉና ስሩ አሉን። እሺ ብለን ሰራን። አራት ወር ሙሉ ክፍያ የለዉም! አቤት ብንልም ሰሚ የለም። በረሃብ ላይ ነን ያለነዉ።ቀን ምግብ ለስራ ያለክፍያ እንሰራለን ማታ ማታ በየቤተ ክርስትያኑ ሄደን እንለምናለን።እና ህይወታችን የተመሰቃቀለ ነዉ፤ ሚመለከተን ባለቤት ያጣን በመሆናችን ችግር ላይ ነን። ባጠቃላይ መንግስት ተፈናቃይነታችን በግልጽ የተቀበለዉ አይመስለንም።ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ፍቅር በነበረችበት ወቅት <<ኢሳያስ አፈወርቅ አዲስ አበባ መጥተዉ በነበረበት ወቅት ኤርትራ ያፈናቀለችዉ ሰዉ የለም፡>> ሲሉ የኛም ባለስልጣኖች ትክክለኛ ናቸዉ ብለዉ ነበር ያረጋገጡላቸዉ።ለምን ይዋሻሉ? ሲፈልጉ የሰዉ አገር ልትዘርፉ ነዉ ሄዳችሁት ይሉናል። ሲፈልጉ ወራሪዎች ናችሁ ይሉናል። ትላንትና አንድ የነበረ አገር ነዉ። ቪዛ የማይጠየቅበት ፤ፓስፖረት የማይጠየቅበት አገር ለምን ሄዳችሁ እንዴት እንባለላን? እና በጣም ነዉ የሚያሳዝነዉ።"


__________________ ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ ሻዕቢያዎች አስመራን እንደያዙ______ 
በኢትዮጵያዊያን ላይ ስለፈጸሙት ግፍ ወያኔዎች የሰጡት መግላጫ ባጭር ባጭሩ እንመልከት መለስ ዜናዊ እንዲህ ይላል፦



"የኤርትራ ጊዜዊ መንግስት በኤርትራ ዉስጥ የነበሩ የደርግ መንግሥት ያፈናና የጭፍጨፋ መሳሪያዎችን ከኤርትራ የሚያስወጣ ፖሊሲ አዉጥቷል። በዚሀ ፖሊሲ መሰረት ከኤርትራ የመዉጣት ግዴታ በተጫነባቸዉ የደርግ ሠራዊት አባላት፡ የደርግ ያፈናና የጭፍጨፋ ተቋሞች ሠራተኞች፤የተስፋየ ገብረኪዳን ቦዘኔዎች ያደራጃቸዉ የቲ. ግሩፕ አባላት ናቸዉ።>>


"ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ወታደሮች የደህንነት ሠራተኞችና የተስፋ /ኪዳን የማፍያ ቡድኖች እንደመጡ የመጠለያ እና የምግብ ችግር ለጥቂት ጊዜ አጋጥሟቸዋል።"


"የኤርትራ ጊዜያዊ መንግስት ከሰብአዊነት ዉጭ የሆነ እርምጃ እንደወሰደባቸዉ አስመስለዉ አቅርበዋል። በኤርትራ ዉስጥ በደርግ ስርዓት ተልእኮዎቹን ልያስፈጽሙ በተላኩ ሃይሎች በህዝቡ ላይ የደረሰዉን በደል ወደ ጎን ትተዉ ብዙ ሰዉ ከጥፋቱ እንዲድን ተብሎ የተወሰደዉን እርምጃ አጥላልተዉ አቀርቡታል።"


"አብዛኛዎቹ ከደርግ ስርዓት ጋር ባንድ ወይም በሌላ መልኩ የተነካኩ ስለነበር ደርግ ይሰራበት የነበረዉን ፖሊሲ በእምነትም በግድም ተቀብለዉ የቆዩ ናቸዉ። የደርግ ተልእኮ ለማስፈጸም ተንቀሳቅሰዉ በህዝቡ ላይ በደል ያደረሱ ናቸዉ። እርምጃ በተወሰደበት ጊዜም ምናልባት አንዳንዶቹ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ከሕዝብ ላይ የወሰዱት ሃብት ንብረት ቀርቶባቸዋል።ባንድ ወይም በሌላ መልኩ የኤርትራ ጊዜዊ መንግስት ያባረራቸዉ የኤርትራን ህዝብ የበደሉ ብቻ ናቸዉ" ( “ቅማላም አጋሜ፤አማራ-አድጊእየተባሉ ግፍ የተፈጸመባቸዉን በሺዎች የሚቆጠሩት ተፈናቃዩች ግፍ የፈጸሙ ወንጀለኞች ወይንምዘራፊዎችብሎ ዜጎቹን ሲሰድብ ይህ ኢትዮጵያዊ መንግሥት ነዉ፡ ብሎ ማለት ይቻላል? አይገርምም ወይ?ይህ ብሎ ሳያበቃ ከታች የተመለከተዉን ለሻዓብያ የተከላከለለትን ደግሞ ተመልከቱት


"በኤርትራ ጊዜዊ መንግስት በኩል በመልካም የተወሰደዉ እርምጃ ባጠቃላይ መልኩ በመልካም ፍላጎት የተመሰረተ ነዉ።"


"ማንም እንደሚያዉቀዉ፤ ብዙዎቹ በኤርትራዉ መንግስት በማንኛዉም መልኩ የሚቋቋም መንግሥት የኢትዮጵያን የባህር በር ዘግቶ ለስቃይ ይዳርገናል ሲባል ለነበረዉ አስመሳይ ፕሮፖጋንዳ ሰለባ ሆነን ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ የተፈጠረዉ ሁኔታ ይህ ስጋት መሰረተ ቢስ እንደነበር በአጭር ጌዜ አረጋግጠናል። የአሰብ ወደብ ለኢትዮጵያ ነፃ አገልግሎት እንዲሰጥ የተፈቀደበት ስምመነትና ትብብር ብቻ ለዚሁ ታላቅ ምስክር ነዉ።"


"ግፋ እያሉ በመሃል አገር አካባቢ የሚናፈሱ ጎጆ አስማሚዎች ተበራክተዋል። 
በኤርትራ ጊዜያዊ መንግሰት የወሰደዉ እርመጃ አሉባልታዎች በመዛመት ላይ ይገኛሉ።>> (እዚህ ላይ ደግሞ አሉባልታ ብሎታል



"የኢትዮጵያ የሽግግር መንግስትና የኤርትራ ጊዜዊ መንግስት የሚወስዷቸዉ ገንቢ እርምጃች የሚያጥላሉበት ጉድለት ቢያጡባቸዉ በበሬ ወለደ ቅጥፈት ተሰማርተዋል።"


አሁን ደግሞ በመጠለያ ዉስጥ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አበባ
ዉስጥ የደረሰባቸዉ መከራ፤ የዓይን ምስክሮች በወቅቱ የታዘቡትን እንመልከት 


/ ትዝታ ገብሩ ይባላሉ።ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት ናቸዉ።የሚኖሩት ሆላንድ ነዉ።TPO (trans cultural psychosocial Organization) ዉስጥ በሙያቸዉ ለማገልገል በወቅቱ ወደ ኢትዮጵያ ሄደዉ የነበሩ ናቸዉ።በ1983 / መጨረሻ ኤርትራ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን የደረሰባቸዉን የስነልቦና ቀዉስ ለመቅረፍ የተሰማሩ ናቸዉ። የስነ ልቦና ሃኪሟ በወቅቱ እንዲህ ብለዉ ነበር። 


"እኔ መፈናቀል ለሚፈጥረዉ የዉስጥ ችግር ልሰራ ተዘጋጅቼ ነበር የመጣሁት እነጂ ሊሞት የደረሰ ሰዉ ያጋጥመኛል ብየ በፍጹም አልጠረጠርኩም።"


21 መጠለያ ተፈናቃዮች መኖራቸዉን ሳይ ደነገጥኩኝ


" ህክምና በተመለከተ ከቤተ ዛታ ክልኒክ / ኤርምያስ ሙሉጌታ ለሚባል ሰዉ ችግሩን ገልጨለት ፈቃደኛ በመሆን ባንድ ቀን ዉሰጥ 235 ሰዉ በላይ አከመልን። ህክምና ካገኙ በሗላ ሰዉነታቸዉ ደህና እየሆነ መጣ። የድሮ ቆዳቸዉ ሲመለሰ ፊታቸዉ ጠርቶ ሰዉ ሲመስሉ ስናይ የነዚህ ሰዎች ችግር ከዉስጣዊ ይልቅ የዉጫዊዉ ጉልህ እነደሆነ ተገነዘብን። ይህ ችግር ለማቃለል ወደ እርዳታ ድርጅት (ማልም) መሯሯጥ እንዳለብን አመንን።ሄደን ያገኘነዉ መልስ ግን አነሱን እንድንረዳ አይፈቀድልንም የሚል ነበር።"


" እኔ እነደታዘብኩት እንደስደተኛም/ተፈናቃዮችም የሚታዩ አልመሰለኝም። እኔ ረሴ ከስዊድን ልመጣ ስል ሊሰናቡን ከመጡ ወዳጆቼ አንዱ፡ምነድ ነዉ የምታደርጊዉ ሄደሽ?” አለኝተፈናቃዮች ጋር አልኩት” “የትኞቹ ተፈናቃዮች?” “የኤርትራ ተፈናቃዮች ጋርአልኩት።እንዴ ዘመዶቼ ከገደሉት ጋር ነሽ አብረሽ የምትሰሪዉ”? ብሎ ካጠገቤ ተነስቶ ሄደ።"


"የተፈናቃይ ሁለት የለዉም። ዛሬ ባይሆን ነገ ልጆቻቸዉ ኢትዮጵያን ይጠይቃሉ። የዛሬዉን እያዩ ነዉና የሚያድጉት።ምንም ሳያደርጉ ሊቀጡ አይገባም።"


"ስለ ተፈናቃዮች ያለዉ ግንዛቤ የተሳሳተ ይመስለኛል።እየተሰራ ያለዉ ሁሉ የግብር ይዉጣ ነዉ የሚመስለዉ።"


";የሚኖሩበት ቦታ እጅግ ይዘገንናል። መሬቱ ረግረግ በመሆኑ ዝናብ ብቻ አይደለም፡ ከስር ዪፈልቀዉንም ዉሃ መቋቋም አልቻሉም። ሰባት ዓመት በፕላስቲክ ቤት መኖር በጣም ከባድ ነዉ።"


<<ካየሁት አሳዛኝ ገጠመኝ ልንገርህ። አዛዉነቶች አሉ፤ ታመሙ ፤ራሳቸዉ እንጀራ ቆርሰዉ መመገብ የማይችሉ፤ ማንም የማይረዳቸዉ አሉባቸዉ።ሰዉ በበሽታ እንጂ በችገር ሲሞት በጣም አበሳ ነዉ።አንዲት ሴት ነበሩ፡ አጥንታቸዉ ወትቷል።መናገር አይችሉም።በረሃብ የተነሳ አጥንት ብቻ ሰለቀሩ፡ መርፌ የሚወጋ ሰዉ፤ / ትዝታ አጥንት ብቻ ስለሆኑ ምወጋዉ ሰዉነት የለም አለኝ።ያኔ እኔ አዲስ ነኝ።ልክ መጠለያዉ ስገባ ትዝታ መጣች ሲሉ እሰማለሁ። ሴትየዋ እኔን በሆነ መንገድ ከተስፋ ጋር ያዙኝና ልክ ስመጣ ነዉ ሴትዮዋ ያረፉት። የመቀበሪያ ገንዘብ ስላልነበራቸዉ ለቤተክርስትያን የሚከፈለዉ ሰባት ብር በእጃቸዉ ስላልገባ የሙት ሴቲቱን እሬሳ ጥለዉ ሲሄዱ ማየት በጣም አሰቃቂ ነበር። ሴት ልጃቸዉአዴ ማሬእያለች ትንፈረፈር ጀመር። ሕይወታቸዉ ስላለፈ ብቻ ሳይሆን፤ ዉድ እናቷን መቅበርያ በማጣቷ! ፍታት ያለ ገንዘብ የለምና! ለቅሶ የመጡት ሞት ሞታቸዉን ሲያዩት ማየቴ አዘገነነኝ። 


ከበሩ ዉጭ ቁጭ ብለዉ ድርቅ ብለዉ ቀሩ። ገንዘቡ ቢሰበሰብ 53 ብር በላይ ሊያገኝ አልቻሉም። ለፍታቱ ተከፍሎ ለሬሳ ሣጥን 80 ብር ድረስ አስፈለገ። ዝናብ ስለነበረ ለታክሲ 20 ብር ተጨማሪ አስፈለገ። ንፍሮዉስ ኬት ይምጣ? ተፈናቃቹ በስንዴ መልክ የሚሰጣቸዉ ደመወዛቸዉን ካገኙ 8 ወር አልፎ ስለነበር የሚሰጡት ሳንቲም አልነበራቸዉም። አዎን ሴትዮዋ ተቀበሩ። ለቀብር የመጡት ሴቶች፡ ለኔም ሰዉ ደረሰላት አሰኘልኝ እያሉ ሲያለቅሱ የተሰማኝ ስሜት ልቤን ይቆነጥጠኛል ፤ልረሳዉ አልችልም፡ መርሳቱንም አልሻም።ወጣት ልጂቱም ከጥቂት ጊዜ በሗላ አረፈች።ስታሰታምማቸዉ የነበረችዉ እሷም በረሃብ ነበር የሞተችዉ። ሰዉ ሞቀበርበት ሳጥን ሲያጣ የሞት ሞት ነዉ።ምን ያህል እነኚህ ሰዎች እንደወደቁና ምን ያህል እንደተረሱ ያስደነገጠኝና ያሳሰበኝ ወቅት ነዉ።"


አሁን እንኳ በቅርቡ <<የህይወት ጉባኤ>> የሚባል ድራማ በተፈናቃዮች የተዘጋጀ ነበር፡የተፈናቃዮችን ችግር የሚያንጸባርቅ። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መጥቶ ቀርጾታል። ሙሉዉን ለሕዝብ እንደሚያሳዩ ነበር የተናገሩት። ይሄም ለኔም ሥራ ለተፈናቃዮቹም ትልቅ ተስፋ ነበር። ግን በዜና ብቻ ተናግረዉ ሳያሳዩት ቀሩ። ለምን እንደሆነ አልገባንም። ህዝቡና መንግሥት ችግራችነን ሲያይ እንደ መፍትሄ ይዘይድልናል ብለዉ ተስፋ አድርገዉ ነበር። ሳይሆን ቀረ። ለካ መንግሥት በኛ ቂም አለዉ፤ እኛን አይወደንም ነዉ ያሉት።ከዚህ በተረፈ ልሰራ የመጣሁበት ዓላማ በአሁኑ ሰአዓት ተግባራዊ ለማድረግ በጣም ከባድ ነዉ። ያለኝ ምርጫ ወይ እንደነሱ ተስፋ መቁረጥ ነዉ።"

ታሪክ ይዘግባል ፤የሰዉ ልጆች ሕይወት ያልፋል፤ የተዘገበዉ ታሪክ ግን አያልፍም። 
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር 
ጌታቸዉ ረዳ Ethiopian Semay
ካሊፎርንያ አሜሪካ
ግንቦት 1991 /  የተዘገበ