Saturday, December 28, 2013

ግንቦት 7 እያካሄደ ያለው ማፊያዊ የግድያ እና የአፈና ዘመቻ ተጋለጠ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ)

ግንቦት 7 እያካሄደ ያለው ማፊያዊ የግድያ እና የአፈና ዘመቻ ተጋለጠ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ) December 29, 2013
እነዚህ ፎቶግራፍ ላይ የሚታዩ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ከኤርትራ ምድር ሸሽተው በበጎ አድራጊ ወገኖቻቸው እርዳታና ተባባሪነት በድብቅ ላይ ይገኛሉ። በግንቦት 7 ያዙልኝ ባይነት በሻዕቢያ አፋኝ ሰዎች እየታደኑ ስለሆኑ ተደብቀው ይገኛሉ። ታሪካቸው ወደ ታች እንመለከታለን።
ካረንት አፌርስ (ECADF) (ኢትዮጵያን ካረንት አፌርስ) ድረገጽ እና ፓልቶክ በተባለ የመወያያ መድረክ ላይ ተለጥፎ በነበረው አስፈሪ የማፊያ መሳይ ማስተወቂያ ነው ጽሑፌን የምጀምረው። ቴድሮስ ይባላላል። የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ታጋይ የነበረ ነው። ስለ ቴድሮስ መታፈን እና ግድያ ከላይ በጠቀስኩት የግንቦት 7 ደጋፊ ድረገጽ የተለጠፈው አስፈሪ ማስታወቂያ እንዲህ ይነበባል፡

ይ ህ ሰው   አደ ገኛ    ይፈለጋል!! የሚል ስታወቂያ  ከረንት አፌርስ የመ ያያ ረክ እና ድረገጽ ላይ  ተለጥፎ የነበረ ነው። እንዲህ ያለ አስፈሪ እና የሰው ልጅ በነፃነት ምርጫን የመምረጥ ተጻራሪ የአፈና ባሕሪ ሚዲያዎች ተባባሪዎች ሆነው የግድያ እና የአፈና ስራ እንዲቀጥል ሲጥሩ ማየት አስፈሪ ክስተት ከመሆን አልፎ፤ እንዲህ ያለ የግድያ እና የሰው ልጅ ማስፈራራት ባሕሪ ማስታወቂያ መለጠፍ የሚያሳየን ምልክት ቢኖር በሚቀጥለው መጪው ስርዓትም ቢሆን የግንቦት 7  መሪዎች እና ተከታዮቹ ስልጣን ላይ ቢወጡ ከወያኔ እኩል ወይንም በባሰ መልኩ አፋና እና ነብሰገዶዮችን በሕዝቡ ላይ የሚያሰማሩ መሆናቸው ጠቋሚ ምልክት ነው።ኢካዴፍ እና ኢሳት የመሳሰሉት ሁሉ የግንቦት 7 ፕሮፓጋንዳ አሰራጪዎች ስለሆኑ የምትለግሱት የገንዘብ ዕርዳታ ካለ ካሁኑኑ አቋማችሁን መመርመር ይኖርባችሗል።
 
ባለፈው ዓመት በውሽት ደልለው ከወሰዷቸው መካክል ዕድል አጋጥሞት ያመለጠው ቴዎድሮስ የሰጠውን ምስክርነት እዚህ በመጫን ያዳምጡ።http://ginbot7d.org/audio/LetterInsiderPartf1.m3u http://ginbot7d.org/audio/LetterInsiderFromPartf2.m3u ይህንን ሰው ነው ኢካዴፍ/ECADF የተባለው ድረገጽ “አደገኛ ተፈላጊ” እያለ ታድኖ እንዲታፈንና እንዲገደል በሕይወቱ ላይ ማስተወቂያ ለጥፈውበታል። አሁን በየቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት ባቋቋሙት “መንግስታቸው” ሰው አንዲታፈን ሲያዙ መንግሥት ሲሆኑ ምን ያደርጉን ይሆን? ድረገጹ የሚያከሂደው ግለሰብ ደግሞ ከናዳ ውስጥ የሞቀ ኑሮ እየኖረ ነው ሰው ለምን ከአንዳርጋቸው ጽጌ አፈና እና ብልሹ ችሎታ ሸሸ በማለት የሸሸ ሁሉ መገደል አለበት እያለ በድረገጹ እና በፓልቶክ ክፈሉ የለጠፈው (ድረገጽና ፓልቶኩ  የሚያካሂዱት ሰውየው እንደልቡ ሲሆን ሴትዮዋ ደግሞ ሙያየ ምስክር እያለች ራስዋን የምትጠራ የድሮ ራዲዮን ሰራተኛ ነበረች የምትባል የትግሬ ሕዝብ ጠሊታነቷ በግልጽ በመናገር ዘረኛነቴን እኮራበታለሁ አንጂ  አላፍርበትም “ከእንግዲህ ወዲህ ዘረኛ ነኝ” እያለች የምትናገር በዘረኛነቷ የምትኮራ ሴት ነች )። ይህ ፓልቶክ እና ድረገጽ ነው ታማኝ በየነ የተባለው የኢሳት አፈቀላጤ “ሓብላቒ” በትግርኛው ቋንቋ ሓብለቒ (ማርኛው ምናልበት ዘብራቂ (?) “እናት ክፍሌ” እያለ በማሞኳሸት የሚኩራራበት እና  የሚጠራው። አንዳንድ ተቺዎች ይህንን የፓልቶክ ክፍል በዘረኛ እና በሰካራሞች ሁሌም ስለሚጣበብ  “በቅባ ቀዱስ ታጥቦ የማይጠራ ክፍል” ይሉታል፤፡

ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ ‘የተባሉ ሁለት የወያኔ  አገልጋይ የነበሩ ወዳጆቹም (በተለይም አንዳርጋቸው ጽጌ ወያኔን በመወከል ፋሺስታዊው የወያኔ የጐሳ ርዕዮተ አለሙ ክፍል ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ ተወካይ እና ግምባር ቀደም ተሟጋች ካድሬ እንደነበረ እራሱ ነግሮናል።)

እነኚህ ሁለቱ ‘ቅንጅት’ ሲባል የነበረው ሀገራዊ የፖለቲካ ተቃወሚ ድርጅትን እንዴት ሾልከው ገብተው አንዳመከኑት ብዙዎቻችሁ ታስታውሷቸዋላችሁ።

ከዚያም ቀጥለው በርቱካን መዲቅሳ የተባለቺው ወጣት ዳኛን አንደ አበባ መሃላቸው ላይ በማስገባት እሷን እየገፉ እነሱ ከሗላ ሆነው የተጫወቱት ማፊያዊ “ኮንሰፒራሲ” ተንኮላቸው አንዴት እንዳከናወኑት እና እሷንም ከሃይሉ ሻውል ቡድን ነጥለው ከጨዋታ ውጭ አንዴት  እንዳደረጓት ታስታወሳለችሁ። በሗላ ብርሃኑ ነጋ ኡደት ሲፈጽምበት በነበረበት አገር እዚሁ አሜሪካ ውስጥ በመቅረት “ምስጢራዊ እገዛ” እና እንክብካቤ ተደርጎለት ግንቦት 7 የተባለ  ተቃዋሚ ድርጅት በመመስረት በርከት ያሉ ‘አቃጣሪ ሊሂቃንን’ በማሰባሰብ ማሕበረሰቡን በማጃጃል መጠኑ የማይታወቅ የገንዘብ ገቢ እና ሙገሳ አግኝቷል።
የድርጅቱ መሪዎች ሥራ ተቀጥረው ኑሯቸው እየገፉ ለ6 ኣመት የህል ያለ ምንም ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከኣገር አገር እየዞሩ ጅላጅሉን ሕብረተሰብ የሕልም እንጀራ እያስቦኩ አዳራሽ ውስጥ ሲያንጨበጭቡት ቆይተው በሗላ ከኤርትራው የሻዕቢያ መሪ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመገናኘት ወታደራዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው ወደ አስመራ በመጓዝ የጠየቁት ተደረገላቸው። ሃረና በተባለው የማስለጠኛ ጣቢያ ቦታ ቢሰጣቸውም፤በሁለት አመት ውስጥ በድምሩ ከ37 ሰልጣኖች በላይ ማግኘት አልቻሉም። አሁን ከ7 እስከ 10 የሚሆኑ ታጋዮች እንደቀሩ ነው ከእዛው አምልጠው ነብሳቸውን ያዳኑ ታጋዮች እየገለጹልን ያሉ።
ከእስራት፤ ከድብደባ/ቶርች፤ከአምባ ገነናዊ ምስቅልቅ፤ከእርስ በርስ ንትርክ እና ድብድብ እና አናርኪ አስተዳዳር እየሸሹ ጎረቤት አገሮች ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ የግንቦት 7 ታጋዮች ሰሞኑን እያስተላለፉት ያለውን አስፈሪ አሳዛኝ ታሪክ እና የድረሱልን ተማጽኖ ግንቦት 7 ዲ በተባለው ድረገጽ ጥሪያቸውን ይፋ ሆኗል።
ሆኖም የህ የድረሱልን ጥሪ እና ግንቦት7 የተባለ በብርሃኑ ነጋ ፤ በኤፍሬም ማዴቦ እና አስመራ በሚኖረው አንዳርጋቸው ጽጌ የሚመራ ወንጀለኛ የማፊያ ድርጅት በነዚህ ግለሰቦች ሕይወት ላይ አደጋ ለመጣል ተሸሽገው ባሉባቸው አገሮች/በረሃዎች (በዊች ሃንት ዳሰሳ) በመከታታል አስጨንቀው “ሃራስ” በማድረግ አፍነው እንደገና ወደ ኤርትራ ለመውሰድ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ናቸው።
ይህ ዜና ግን የሕዝብ ዓይን እና ጀሮ ነኝ እያለ በውሸት የሚኮፈስ “ኢትዮጵያዊ ሚዲያ” ነኝ የሚለው ሌላኛው በግንቦት 7 በኩል በሻዕቢያ የሚደጐም ‘ኢሳት’ ሆን ብሎ ዜናው እንዳይሰራጭ አፍኖታል። ይህ በኢሳያስ እና በአረቦች ገንዘብ የሚተዳዳር ሳተላይት ቲቪ እና ራዲዮን የነዚህን ኢትዮጵያዊያን ፎቶግራፍ በግዳጅ ላይ እንዳሉ በማስመስል ሻዕቢያ በትከሻቸው ላይ የማያውቁትን ላውንቸር እና መትረየስ በግድ ጭኖባቸው ተሸክመውት የተነሱትን ፎቶግራፍ በየጊዜው በማሳየት ሕዝቡን በማሳሳት ዘመቻ በውሸት ተጠምዶ አንዴ ‘የድምሒት’ አንዴ የግንቦት 7 ‘ሕዝባዊ ሃይል’ ወታደራዊ ዜና እያለ ውሸት ሲያቦካ የነበረውን ዜና ጋብ በማድረግ ሕዝባዊ ሃይል ሲለን የነበረውን ወታደራዊ የግንቦት 7 ሃይል “ዛሬ” ምን በላው ለሚሉ ጠያቂዎች ምንም ምላሽ ሳይሰጥ ጣቢያው በባለቤትነት ከሚያስተዳድረው ከግንቦት 7 ጋር አፉን ዘግቶ ይገኛል።
ይባስ ብሎ፤ ማስልጠኛ ጣቢያው ውስጥ አንዲት ጎጆ ከሁለት ፈርኬታ፤ጥቂት ሹካዎች ፤ሳህን አንዲት ትሎች የፈሉባት የደፈረሰ ውሃ የያዘች በርሜል፤ እና አንድ ‘ኮምፑተር ላፕ ታፕ’ እና 7 ታጋዮች ያሉት ‘ሕዝባዊ ሃይል” የሚባል ህይወት እንዳለው በማስመሰል የሚዋሸን “ኢሳት” የተባለው ጉደኛ  የዜና ጣቢያ፤ ባለፈው ወር “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል መሪ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመግደል የተላከ ነብሰገዳይ በሕባዊ ሃይል የስለላው ክፍል እና ችሎታ ተጋለጠ” በማለት አስቂኝ የሆነ የወያኔ  “አኬልዳማ’ የሚሉት የሚመስል ‘ድራማ’ በማዘጋጀት በተዳጋጋሚ በቲ ቪ ው ጋዜጠኞች ሲተች፤ሲኳል፤ሲሞገስ ሲለጠጥ እና ሲሰራጭ ሰምተናል።
ይህ ዜና ግን ውሸት የተጨመረበት መሆኑ በቅርቡ ታጋዮች አጋልጠውታል። ዜናው እውነትንት ቢኖረውም ግንቦት 7 እና የዚሁ ድርጅት ቲቪ የሆነው ኢሳት የተባለው ጣቢያ ያቀረቡት አቀራረብ ግን እጅግ የተጋነነ እና ውሸት የተጨመረበት እንደሆነ እና ‘የስለላና መረጃ ድርጅት” የሚባለው የግንቦት 7 ድርጅት “እንደሌለ እና ቢኖርም “ግድያ ከሸፈ” ከሚባለው ታሪክና ወቅት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ተጋልጣል። እራሱ በራሱ ፍላጐት አነሳሽነት ያጋለጠ “ሰላይ/ነብሰ ገዳይ ተያዘ” ተብሎ በግንቦት 7 እና በኢሳት የተሰራጨው የግለሰቡ ዜና  አጋጣሚውን ተጠቅመው ለድርጅቱ መጠቀሚያ ትኩስ ዜና ተደርጎ ማጋነኛ ፍጆታ /ለፕሮፓጋንዳ ስራ/ አንዴት እንደተጠቀሙበት ለሕይወታቸው ሰግተው አሁን ተሸሽገው ከሚገኙበት ቦታ በስልክ እውነተኛውን ምስጢር ነግረውናል።
ኢሳት ያስተላለፈው ዜና የሚጻረር አዲስ ክስተት ብቅ ሲል ግን ዜናው እንዳይታወቅ እና የነዚህ ግለሰዎች ሕይወት አደጋ ላይ እያለ እያወቀ ጀሮ ዳባ ማለቱ ለግንቦት ሰባት የቆመው “ኢሳት” በተጋዮች ሕይውት አስኮናኝ የሚዲያ ጨዋታ እየፈጸመ ነው። በግንቦት 7 እና ኢሳት አፈ ጮሌዎች የተጠለፈው ጅላጅል ሕዝብ ግድ ባይኖሮውም እኛ የቁርጥ ቀን ጥቂት ልጆች የነዚህ ወገኖቻችን ሕይወት አየተካታተልነው መሆኑን ኢሳት የተባለው የዜና ማሰራጫ እንዲያወቅው ይሁን።
ኢሳት ከዚህ በታች የሚከተለው ታሪክ “በሚገባ ያውቀዋል። ለምሳሌ ግንቦት7 በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና ውሸት ከሚችለው በላይ ሆኖበት ድርጅቱን በመልቀቅ የድርጅቱን ውሸትና የሚያደርሰውን አፈና እና ስቃይ በማስመልከት ዳንኤል የተባለው በቅርቡ ከድርጅቱ ሸሽቶ በኤርትራ አፋኝ ሃይሎች በእንዳርጋቸው ትዕዛዝ እየታደነ ያለው ዳኒኤል የተባለው የግንቦት 7 ታጋይ የተናገረውን እዚህ ያዳምጡ።
አሳት የተስፋዬ ገብረአብ ሻዕቢያነት ከሁለት አመት በፊት ሰነዱ እንደተገኘ አውቆት እያለ ከሕዝብ እንደደበቀው ሁሉ ኢሳትም ይህንን የዳኒኤል ቃለ መጠይቅ እና የድረሱልን ጥሪ ዜና ያውቃል። ሆኖም ሆን ብሎ ሌት ተቀን  የአንዳርጋቸው ጽጌ ግድያ ሙከራ ካንድ ገጽታ ብቻ አንዲታይ ያልጣረው የዜና ስርጭት እና መደበኛ ጊዜ ሰጥቶ ያላደረገው ፕሮፓጋንዳ ሙከራ አልነበረም።
ተቃዋሚ ነኝ የሚሉት አንዳንድ የዲያስፖራ ሚዲያዎች እያደሩ ማፊያዊ ሚዲያ ዓነት ለግለሰቦች አገልግሎት እና ዝና ውለዋል። በቅርቡ ይህ ኢሳት የተባለው የዜና ተቋም የግንቦት 7 መሪዎች እና የኢሳያስ አፈወርቂ ሰብአዊነት የሚሰብክ ልሳን በአንዳርጋቸው ጽጌ በኩል ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንዲተላለፍ ሲያደርግ፤ ኢካዴፍ ECADF (አትዮጵያን ካረንት አፈይርስ ድረገጽ) የተባለ ፓልቶክ እና ድረገጽ  ደግሞ የበኩሉን ማፊያዊ የግንቦት 7 ስራውን ለመወጣት ሲል ከግንቦት 7 “ቶርቸር’ አምልጠው የሚመሸሹ ዜጎችን “ተፈላጊ ወንጀለኞች” እያለ እንዲታፈኑ እና በያሉበት አንዲገደሉ ማሰታወቂያ በመለጠፍ ፋሺስታዊ/ማፊያ የባሕሪ በሽታ እየተናወጠው ነው።
 


ይህ ፎቶ ከግንቦት 7 እና ሻዕቢያ  አፈናና ግድያ በመከራ አምልጠው ከወጡት የህዝባዊ ኃይል ተብየው  አመራሮች አባስ/ ማስረሻ (የስልጠና ከፍል ኃላፊ) አና ኮስሞስ (የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) ነው

ይህ ፎቶ የኢሳት ቲቪ እና ECADF;  የግንቦት 7 ድረገጾች እና ኢካዴፍ ሕዝብን ለማሞኘት ለጥፈውት የነበረ የውሸት ፎቶግራፍ ነው። ውሸትነቱ ደግሞ በዚህ ፎቶገራፍ ብረት ይዘው የሚታዩ በነሱነታቸው በሚዲያ የተነገደባቸው ሰዎች ለምሳሌ ለውንቸር ይዞ የተነሳው የግንቦት 7 የስልጠና ክፍል ሃላፊ ተብሎ ተመድቦ የነበረው “አባስ (ማስረሻ)” የሚባለው ታጋይ ሻዕቢያ ላውንቸር አምጥቶ ለፎቶ ግራፍ ፍጆታ በትከሻው ይዞ እንዲነሳ የተደረገ መሆኑን እና የያዘው ላውነቸር ምንነቱ አይቶት አንደማያውቅ በቃለ መጠይቁ ተናግሯል።አብሮት ያለው መትረየስ የያዘው ደግሞ ዘመኔ ካሴ ይባላል። እሱም አንደዚሁ በትከሻው ተጭኖበት ለፎቶ ፍጆታ ግንቦት 7 የተጠቀመበት የውሸት እይታ ነው። በዚህ ጽሑፍ ላይ የተለጠፈው አውድዮ ቃለ መጠይቅ ለማስረጃ ይሆንዎት ዘንድ  ከራሳቸው ከአንደበታቸው ያድምጡ።
ይህ ጉደኛ ዘመን በእንዲህ ያሉ ተቃዋሚዎች እና የዜና ማሰራጫዎች እየታጀበ ጉደኛነቱ እያሳየን ያለው በጣም አስገራሚው የግንቦት 7 እና የኢሳት ቅንብር ውሸት ለየት ያደረገው የወሩ ጉደኛ ዜና ደግሞ  አንዳርጋቸው ጽጌ ለመግደል የተያዘው “ኦ ሚለዮኔም” በሚል ስያሜ የተቀነባባረው የግድያ ተልዕኮ ከወያኔ የተላከው ነብሰገዳይ በግንቦት7 የስለላ ድርጅት ተደርሶበት ተይዞ ስልክ ሲነጋጋር ለበርካታ ወራት በትእግስት እንዴት የስልኩን ልውውጥ እንዴት ይጠልፉት እንደነበረ ሳያፍሩ ለሕዝብ አስተላልፈውታል።
ታሪኩ ግን የግንቦት 7 እና የኢሳት ጋዜጠኞች አንዳናፈሱት ሳይሆን ልጁ በገዛ እራሱ ለነብሱ ሲል ኑዛዜ/ንስሃ ገብቶ ከላይ በፎቶግራፍ ለሚታየው ለዘመነ ካሴ (ለጋደኛው) ምስጢሩን ነግሮት ድርጅቱም ማወቅ አለበት ብሎ በንጽህና ራሱ በራሱ ያጋለጠና የሰጠ ሰው ንፀሁና መወደስ የነበረበት ሰው፤ የግንቦት 7 መረጃ ክፍል ደርሶበት ተጋለጠ ብሎ በውሸት ያልሆነ የሃሰት ወሬ አስሰምተውናል።
ሲያስደውለው የነበረው ደግሞ ዳኒኤል ነው።http://ginbot7d.org/audio/YegedeyaMukera.mp3 ዳንኤል ደግሞ በዚህ አውድዮ የምትሰሙት ከኤርትራ አምልጦ አሁን ከግንቦት 7 የሻዕቢያ አፈና የግድያ ቡድን ጥቃት ለማምለጥ ተደብቆ ሕይወቱ አደጋ እያንዣበበት ላይ ያለ ኢትዮጵያዊ ነው። አስገራሚው ድራማ ደግሞ፤ ተፈላጊው ተገዳይ አንዳርጋቸው ጽጌ ሳይሆን “ሻምበል ዳዊት” የተባለ በወያኔ የሚፈለግ ኤርትራ ውስጥ የኒገኝ የአማራ ድርጅት አባል ተፈላጊ ነው። ነግር ግን ድራማው ወደ አንዳርጋቸው ጽጌ እንደተደረገ ተደርጎ ተቀነባበረ። በሗላ ልጁ ግድያው ላንዳርጋቸው ጽጌ አንደተጠና ተደርጎ ‘ድራማ’ አንዲሰራ ከተገደደ በሗላ፤ በምስጢር ባንዳርጋቸው ፈቃድና ተባባሪነት ለሻዕቢያ ተላልፎ ለድብደባ እና ልዩ ምርመራ ለስቃይ ተዳርጎ እስካሁን ድረስ ሁኔታው የት አንዳለ የሚያውቅ ሰው የለም።
ይህ አሳዛኝ ወንጀል በግንቦት 7 ተቀነባብሮ በኢሳት ጋዜጠኞች በኩል ሰፊ ሽፋን እና ሰዓት ተሰጥቶት ሕዝብን በማደናገር ወንጀል ኢሳት ተባባሪ ሆኗል። ኢሳት የግንቦት7 እና በሻዕቢያ ገንዘብ የሚደጐም የዜና ተቋም ቢሆንም፤ ወደፊቱ ከዚህ መሳይ አደናጋሪ እና የሃሰተኛ ድርጅት ፕሮፓጋንዳ አሰራጭነት የወንጀል ተባባሪነቱ እንዲታቀብ እንማጸነዋለን።
ይህ የግንቦት ውሸት ዜና ኢሳት ሳይውቅ ነው ያሰራጨው አንኳ ቢባልም፤ ሰላዩን/ነብሰገዳይ ተብሎ የተወነጀለው ሰው እየተከታተለ ስልክ ሲያስደውለው ከነበረው በድራማው  ክንዋኔው የነበረው ታጋይ ዳኔኤል የሰጠው ቃለ መጠይቅ ይፋ ከሆነ በሗላ እንኳ ኢሳት (ገለልተኛ ሚዲያ ነኝ እንደሚለን እውነትነት ካለው) የዳኒኤልም ሆነ የቴድሮስ እና የመሳሰሉ በርከታ የግንቦት 7 (የሕዝባዊ ሃይል ተብዬ) ታጋዮች የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ዜና እና ያስተላለፉት ተማጽኖ አንደ ተቀረው ዜናዎቹ  ከየትም ድረገጽም ሆነ ከውጭና ከውስጥ አገር የዜና ማሰራጫዎች “ኮፒ ኤንድ ፔስት” አድርጎ ለሕዝብ እንደሚያሰደምጠው ሁሉ ፤የነዚህ ታገዮች የድረሱልን ጥሪም ሆነ በአንዳርጋቸው ጽጌ ትዕዛዝ በእስር ተዳርገው የቶርች ሰለባ የሆኑበትን የብሶት እሮሮ ለማስደመጥ ፈቃደኛነቱን አላሳየም። በዚህ ጥያቄ ኢሳት እምራለሁ ብሎ የተቀመጠ አንድ ደንቆሮ ኩናኩንት ብጤ በኢመይል ጠይቀው በዚህ ተፋጥጠን አንድ ሁለት ተባብለናል።
የኢሰት ጋዜጠኞች የነ ኮስሞስ (ከሳውዝ አፍሪካ ወደ ኤርትራ ወደ ግንቦት 7 ሰልጣና የሄደው) በቶርች በእስራት የተሰቃየ ልጅ፤ የነ ቴድሮስ፤ የነ ዳኒኤል ወዘተ… ሕይውት እና በፋሺሰት ባሕሪ የሚንቀሳቀሰው በዘረኛው በአንዳርጋቸው ጽጌ ብልሹ አምባገነን አሰራር ተበሳጭተው ትግሉን ጥለው ለመሰናበት ጠይቀው ማመልከቻ አስገብተው ለእስራት፤ድብደባ እና ሞት፤ አንዲሁም ለሻዕቢያ የዘንጋዳ ቆራጭ የዳረጓቸው አንዳርጋቸው ጽጌ እና ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ኤፍሬም ማዴቦ ለእነዚህ ሕይወት ተጠያቂዎች ናቸው። ይህ ተደብቆ የቆየው የግንቦት 7 ወንጀልና ምስጢር ያጋለጠው ዳኒኤልም ሆነ ሌሎቹ እየተከታተላችሁ ለማደን እና ለማፈን የምታደርጉት የፋሺሰት ተግባር አንድታቆሙ ይህ ብዕርተኛ በጥብቅ ያስገነዝባል።
ግንቦት 7 ብሎ ራሱን የሚጠራ አጭበርባሪ የሻዕቢያ ተላላኪ በዜጎቻችን እና በታጋዮቹ ላይ እያደረሰው ያለው ግድያ እና ከድርጅቱ እየሸሹ የተደበቁ ሰዎችን እያባረረ ለማፈን እያደረገው ከአለው የወረበላ ባሕሪው ይታቀብ። አብዛኛዎቹ የግንቦት 7 መሪዎች ዋሺንግተን እና መኔሶታ ስቴት እየኖሩ በሰው ሕይወት ላይ ግድያ፤እስራት፤ቶርች አደና እና አፈና እንዲፈጸም ማድረግ እና ተባባሪ መሆን በሕግ አንደሚያስጠይቃቸው እና ለሚኖሩበት አገር እና የስደተኞች መስርያቤት እና አስሬ ወደ እሚሮጡበት ወደ ኮንግሬስ ጽ/ቤት እና ወደ ፕረዚዳንቱ ጽ/ቤት አቤቱታ ማቅረብ እንደምንችል እንዲያውቀት።  ይህ ብዕርተኛ በእነዚህ እየታደኑ ሽሽት ላይ ባሉት ሰዎች ህይወት የሚደርሰው አደጋ የግንቦት 7 መሪዎች እና ሚዲያዎቻቸው አንደሚሆኑ በብርቱ ማስጠንቀቂያ ያስገነዝባል!!!!!!! I am not joking here!
አሜሪካ ኮንግሬስ ድረስ እየሮጡ ስለ ሰብአዊነት መቆርቆርና ስለ ዲሞክራሲ ማጣት መለፍለፍ ፤ አውሮጳ አገረሮች እየሁዱ ገንዘብ ድጐማ መስበስብ ባንፃሩ ሰዎች እያሳፈኑ እና እየገደሉ እያሳደዱ ሰው መስሎ መለፍለፍ ማብቃት አለበት። የግንቦት 7 የሻዕቢያ አፋኝ ቡድን አፈና ለማምለጥ ተሸሽገው ካሉት ወገኖቻችን የተሰጠ የድረሱልን ጥሪ ለማንበብ ከዚህ በታች ቀርቧል። የሰብአዊ ድርጅት ተሟጋች ነኝ የሚል የኢሳት ሰውየም በመደበኛ የሰብአዊ ጉዳይ ክፈለጊዜው ሃቅ ካለው ይህንን አቤቱታ ለሕዝብ ይፋ አንዲያደርገው ይህ ጸሓፊ በብርቱ ያሳስባል።http://www.ginbot7d.org/documents/ኤርትራየሚፈፀምወንጀል.pdf  የሙለው እና ከዚህ ጋር በማያያዝ “ከግንቦት 7 የቀን ጅቦች እና ከሻዕቢያ መንጋጋ ያመለጡ ታጋዮች” የሚለውን http://www.ginbot7d.org/ ሙሉውን ያንብቡ።
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) getachre@aol.com Google-it!!!!!-(Ethiopian-Semay) www.ethiopiansemay.blogspot.com