Saturday, September 19, 2020

ትግራይ እንደ የመንና እንደ ሐረር የመለወጡ አሳዛኙ ትዕይንት! የወያኔ ታላቁ ሴራ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) Saturday, September 19, 2020

 

ትግራይ እንደ የመንና እንደ ሐረር የመለወጡ አሳዛኙ ትዕይንት!

የወያኔ ታላቁ ሴራ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

Saturday, September 19, 2020

ህ.ወ.ሓ.ት የውጭ አገር ቅጥረኛነቱን ለማሳካት በራያና በእንደርታ እናቶች ላይ በአደገኛ እጽ እንዲያብዱ እያደረገ ነው!  ወያኔ ሲመሰረት በማኒፌስቶው ላይ ያሰራጨውን ለትግሉ መነሾ አብዛኛዎቻችሁ የምታውቁት ይመስለኛል። በጠላትነት የፈረጀው አማራ ሲሆን ተጠቂው ደግሞ ሕዝቤ ብሎ በውሸት የሚጠቀምበት የትግራይ ሕዝብ ነው። ወያኔ ሲመሰረት መጀመሪያ የጥቃት ኢላማ የሆኖው ኢትዮጵያዊነቱን አልክድም ያለውን እና የኢትዮጵያ ታሪክና የትግራይ ታሪክ ምንነቱን አዋህዶ ያወቀውን አዛውንቱን እየመረጠ ነበር በመግረፍ፤ በእሳት አቃጥሎ በመግደል (ከተቃጠሉት እና ከሞቱት ውስጥ የኔ ቤተሰቦች አሉበት)፤በማሰርና በመሰወር ነበር ትግሉን የጀመረው።

አልንበረከክም ያለውን የኦርቶኦክስ ሃይማኖት ቀሳውስትና ድያቆናትን መነኮሳትን ከገደለ በሗላ፤ በመቀጠል እነ ገብረኪዳን ደስታ የመሳሰሉ መርዛማ ጸረ ተዋህዶ ክርስትና እና ጸረ አማራ የሆኑትን ተዋጊዎቹን አስሰርጎ ወደ ገዳማትና ቤተክርሰትያን ተቋማት ቀሳውስትና ዲያቆናት በማስመሰል በማስገባት፤ ክርስትያን ሁሉ ከነ ቀሳውስቶቻቸው ጠመንጃ በማስታጠቅ የኮሚኒሰት እምነት ተከታዮች እንዲሆኑ በማድረግ፤ ሰው እየገደሉ ገበሬዎን በሽብር  አንቀጥቅጠው 17 አመት ገዝተውታል።

በነዚያ 17 አመት የጫካ ንግሥናቸው በመሪነት የተቀመጡት ኤርትራዊ ትውልድ ያላቸው እና እንዲሁም ዓድዋ፤ሽሬ እና አክሱም ትውልድ ያላቸው መሪዎች ጋር በመመሳጠር ከነሱ ውጭ ያለው እንደርታ ፤ተምቤን፤ራያ ፤ዓጋመ ሁለት አውላዕሎ የመሳሰሉት አካባቢዎች  ከወላጆቻቸው የተማሩት የትግርኛ ለዛቸው ወደ ኤርትርኛ ወይንም “አሽዓ”ዊ ትግርኛ ዘይቤ እንዲናገሩና እንዲጽፉ “የሕሊና አጠባ” በማድረግ በነዚህ አውራጃ ተወላጆች ላይ “የበታችነት ስሜት ተሰምቷቸው” ለዛቸውን ትተው የተሰጣቸውን “የሰለጠነ ለዛ” ነው ብለው የሚሉትብ የኤርትራኖቹ ልሳን በሰፊው በማሰራጨት ያንኑ “ገለመለ፤መዝነት እና ሕጂ” የሚለውን ኤርትርኛው እንዲናገሩ በራዲዮ በቴ/ቢዥን ሚዲያዎችና በጽሑፎች ከፍተኛ የሕሊና አጣባ በማድረግ “በነዚህ አውራጃ ገበሬዎች እና ወጣቶች ላይ “የባህልና የልሳን” ወረራ አድርጎባቸዋል።

 

መርዛማዎቹ የወያኔ መሪዎች 17 አመት ጫካ ውስጥ የጀመሩት የነዚህ አካባቢዎች እናቶችና ወጣቶች የማጥቃት ዘመቻቸውን ለ27 አመት እውን በማድረግ እናቶች በሚያሳብዱ እፆችና በሲጃራ ተበክለው ብልሹ ማሕበረሰብ ሆነው በድህነትና በሐዘን እንዲጎሳቆሉ በማድረግ እነሆ ቪዲየው ላይ ምትመለከቱት አሳዛኝ እውነታ ለማየት በቅተናል።

እዚህ ላይ ወዳጄ እና ወንድሜ ግርማ በቀለ ይህንን  ቪዲዮ እንድመለከተው ሲልክልኝ ከጻፈልኝ መልእክት ልጥቀስ፡

እንዲህ ይላል፡

“my dear brother Getachew, what I saw brought tears to my eyes. For all I know Tigrian mothers are very religious and devote Christians who never go to this level. What we are noticing is  the level of frustration with their lives and oppression.  These ladies could be the ones who lost their husbands, sons and daughters during the war and are now left without support. I could never imagine they would do what we saw without what they go through under this evil TPLF. It is the saddest episode to witness this. Lord have mercy on our country!” ሲል በሓዘን ጽፎልኛል።

ወያኔ ከመምጣቱ በፊት የትግራይ እናቶች እላይ እንደተገለጸው በሃይማኖት እና በባሀል ታንጸው ያደጉ እጅግ የተከበሩ እናቶቻችን መኖራቸው እኔም የትግይ ሰው እንደመሆኔ መጠን ምስክርነቴየን እሰጣለሁ። እርግጥ ነው እንዚህ መርዛማ መሪዎች ከመጡ በሗላ ግን የማሕበረሰቡ ላይ የተለያዩ ጉዳቶች አድርሰዋል። ጥቂቶቹ ወንድሜ ግርማ እንዳለው የተጠቀሱ ናቸው። ከዚያም በመጽሐፌ ውስጥ አንደጠቀስኩት የዋልድባ ሴት መነኮሲቶች “ኢሳት” ላይ ቀርበው በሰጡት ቃለመጠይቅ በትግሬዎቹ ወያኔዎች ብዙዎቹ እንደተደፈሩ ገልጫለሁ። ያ እንዳለ ሆኖ በመጀመሪያ ወያኔ እነዚህ ሰዎች በዚህ መልክ እንዲያብዱና እንዲበከሉ ድሮ ትግራይ ውስጥ የማይታወቁ ጫት፤ኮከይን፤ሲጃራ፤ሓሺሽ የመሳሰሉት ትግራይ ውስጥ እንዲሰራጭና፤ መቀሌ ከተማ ውስጥ የመቃሚያ /መመርቂያ/ ንግድ ቤቶች እንዲከፈቱ የፈቀደው ወያኔ ነው።

 

 እንደርታ ውስጥ ብዙ አመት የኖሩ ባለትዳሮች ከስራ በሗላ ጫት መቃሚያ ቤቶች እያመሹ ደሞዛቸው እንዳለ ለሱስ ስለሚያውሉት በርካታ ባለተርዳሮች ትዳራቸው ፈትተው አልባሌ ሜዳ ለይ የወደቁ እንደነበሩ ካሁን በፊት አንድ ሓተታ ጽፌ ነበር።

 

ከበርካታ አመታት በፊት መቀሌ ውስጥ የከተማው ፖሊስ ተራ ሰው መስሎአቸው በጋንጎቹ ተይዞ ቀምተውት፤ገደል ወርውረውት በማግስቱ ሲታይ ዋናው የፖሊስ ሹም መሆኑንም እራሱ የሰጠውን ማብራሪያ ማድመጤን ይታዋሳል።ባንኮች የመዘረፍና ሰላማዊ ዜጎች በአራት ማአዝን የተሰማሩ የተለያዩ ስሞች ያላቸው የከተማ ሌቦችና “ጋንጎች” በጠራራ ጸሓይ ሰዎችን በማስቆም የሚዘርፉ/የሚገድሉ/ ከዚያም አልፈው ህጻናት እያፈኑ ለገንዘብ እንደሚደራደሩባቸው “ከመቀሌ ፖሊስ” የተሰጠው የቪዲዮ ራፖር ገልጬ እንደነበርም ይታወሳል። አሁኑኑ ሽበት ያወጡ እናቶች በዚህ ሱስ ተበክለው በዚህ  ቪዲየው ላይ

አሳዛኝ ክስተት እያየን ነው።

ወያኔዎች  በድሃው የትግራይ ሕዝብ ላይ ተጭነው በእነሱ ላይ ጥብቅ የህይወት ቁጥጥር በማድረግ ፤ ሓብት እየደለቡ የድሃው ህይወት ቁልቁል እየሄደ የዜጎችን ሞት ባጭር እንዲቀጭ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ ከጀመሩ 27 አመት ሆኗቸዋል። ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዎች ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ በውጭ ዓለም እና በውስጥ አገር የሚኖሩ ብዙዎቹ ሕሊና ቢሶቹ የትግራይ ምሁራንና ደጋፊዎቻቸው ናቸው። ለሁለም ጊዜ አለው!  ከታች ያለውን ቪዲዮ ተጭናችሁ አሳዛኙን ትዕይንት እዩት።

አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ) https://www.facebook.com/100013357625158/videos/1043377612784150/