Wednesday, May 23, 2018

ለወ/ት እየሩሳሌም ተስፋው የምጠይቀው ጥያቄ አለኝ (ጌታቸው ረዳ (Editor Ethio Semay)



ለወ/ት እየሩሳሌም ተስፋው የምጠይቀው ጥያቄ አለኝ
 (ጌታቸው ረዳ (Editor Ethio Semay)
ታስታውሱ እንደሆን በፈረንጆች የወራት አቆጣጠር በወርሃ ‘መይ’ አንዳርጋቸው ጽጌን በሚመለከት ለወ/ት መሰረት አበራ የሰጠሁት አስተያየት መኖሩን ይታወሳል። እንደ አስፈላጊነቱ ሁለተኛ ክፍል አቀርባለሁ ብየ ነበር። ዛሬም በተመሳሳይ የማቀርበው ጥያቄና አስተያየት ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላት ተብላ እስር ቤት ታስራ ቆይታ አሁን ባለው ‘መለስተኛ ለውጥ’ በቀርቡ ከእስር በነፃ የተለቀቀቺው ወጣት እየሩሳሌም ተስፋው ለተባለች ነው ጥያቄየ።

ይህች ልጅ በግንቦት 7 ድርጅት ልቧ በፍቅር የደነዘዘ መሆኑን ባለፈው ወራት ባሳየቺው እንቅስቃሴ እና በምትጽፈው ጽሁፍ ብቻ ሳይሆን ፤እሰር ቤት ሆናም ልቧ ወደ ኤርትራ እንደሸፈተ ሳታመነታ መጻፍዋን እናስታውሳለን። ሁሉም ሴት ወጣቶች የሚኖሩት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ሰለ ግንቦት 7 ድርጅት መሪዎች በቂ መረጃ ይኑራቸው አይኑራቸው የማውቀው ነገር የለኝም። መረጃ የላቸውም እንዳልል፤ በተከታታይ ለበርካታ አመታት ስለ አንዳርጋቸው እና ብርሃኑ ነጋ ፖለቲካዊ መስመርም ሆነ ስብዕና ከኔ ጀምሮ ብዙ ሃያሲዎች እና የሰብአዊ መብት ተመጓች ኢትዮጵያውያን የዘገቡት እና የተከራከርንበት ስለሆነ ይህ ድርጅትም ሆነ አድናቆታቸው የሚግሱበት ምክንያት ከመረጃ እጥረት ነው ማለት አልችልም። አንደኛዋ የጻፈውን ብሔረተኛነትን የሚያበረታታውና የሸዋ መሳፍንትም ሆነ የኢትዮጵያ አመሰራረት እና ዜጎችዋ ከውስጥ ያመቁት ደስተኛ ያለመሆንን፤ አገራችን ያላት የመቶ አመት ዕድሜ ዝባዝንኬ የለፈለፈበት መጽሐፍን እንደወደደቺለት ነግራናለች። ስለዚህ ከመረጃ እጥረት አይደለም ማለት ነው።

በዚህ መልክ በግንቦት 7 ፖለቲካ ፍቅር የከነፈቺው እየሩሳሌም ተስፋው ስለ አንዳርጋቸው ብዙ፤ብዙ ብላለች። ስለ ግንቦት 7 ብዙ ብዙ ብላለች። ስለስዋ እንወያያለን። ወራቱን በሙሉ ብዙ ሰዎች ስለ አንዳርጋቸው ጀግናነት፤ የነፃነት ጠበቃ፤ ሰብአዊ ተሟጋች ወዘተ… በሚሉ ቃላቶች ሲያሽሞነሙኑት ስምተናል። ስለሆነም  በዛው በሰብአዊ ጠበቃነቱና ሰብአዊነቱ ምክንያት መታሰር እንደሌለበት ከእስር መፈታት እንዳለበት ከዚች ልጅ ጀምሮ እስከ ብዙ ተቺዎች “ሰብአዊ ተሟጋች እና የነፃነት ታጋይ” ስለሆነ “መፈታት አለበት የሚል መከራከሪያ ይዘው ነው ‘ለስር ይፈታ” የሚሉት መነሻቸው። እኔ ደግሞ አንዳርጋቸው ይፈታ በሚለው ችግር የለብኝም፤ መፈታት ያለበት ግን “አንዳርጋቸው ሰብአዊ ተሟጋች፤የነፃነት ታጋይ፤ለሰው ልጆች እና ለታጋዮቹ ተቆርቋሪ” የነበረ ሰው ስለነበር ይፈታ በሚሉት ክርክር ግን አልስማማም። ምክንያቴን ካሁን በፊት ገልጸጫለሁ፤ዛሬም እንመለከተዋለን። 

ወደ ልጅትዋ ከመግባታችን በፊት አንዳርጋቸው እንዴት ታሰረ የሚለው መላምት ብዙ ሰዎች የመሰላቸውን አስተያየት ገልጸዋል። አንዳርጋቸው ማን እንዳሳሰረው በእርግጠኛነት አውቃለሁ ብለው ከነ ኢመይል አድራሻቸው እና ስማቸውን መዝግበው በሚዲያ ያስነበቡን Bombshell Report on the kidnapping of Andargachew Tsege-Gondar Hebret chairman Abebe Negatu and Colonel Fistum (Haileeysus Adamu ኃይለኢየሱስ አዳሙ እንዴት ለመጠለፍ እንደበቃ ይነግሩናል።

እንዲህ ሲሉ ሰፊውን ታሪክ ባጭሩ በቅንፍ ላስነብባችሁ፡

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን የ ሻቢያው ኮሎኔል ፍፁም እና የጎንደር ህብረት ሊቀመንበር አበበ ንጋቱ ከአዜብ መስፍን ጋር ሁነው አሳልፈው እንዳስያዙት ማስረጃ አግኝቻለሁ። አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ ከመታሰራቸው 4 ዓመት በፊት አቶ ኤልያስ ክፍሌ የኢትዮጵያን ርቪው ዋና አዘጋጅ የሻቢያ ደህንነት ሰዎች ሊያፍኑት እቅድ እንዳላቸው መረጃ እንዳገኘ በ Ethiomedia ድህረ ገፅ ላይ በ December 18, 2010 ድርጊቱ ከመፈፀሙ በፊት አስጠንቅቆ ነበር። ሙሉ ፁሑፉን ከሚከተለው link ላይ ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ላይ ዋናው ቁልፍ ነጥብ ይሄ ፁሑፉ እና መረጃ አቶ አንዳርጋቸው የመን ላይ በ 2014 ከመታፈናቸው 4 ዓመት በፊት(before the effect ) የወጣ መሆኑ ነው ። 

''The Ethiopian Review, which addressed its demands to President Isaias Afewerki, also revealed that Eritrean government agents had a plan to kidnap Andargatchew Tsige, a top official of Ginbot 7, an opposition group outlawed in Ethiopia and had reportedly sought shelter in Asmara.'' http://www.ethiomedia.com/augur/4276 ሌላው በዚህ ፅሑፍ ላይ ያለው አስደንጋጭ መረጃ የጎንደር ህብረት ሊቀመንበር አቶ አበበ ንጋቱ በዚህ ድርጊት ውስጥ እጁ እንዳለበት ማሳየቱ ነው። ይሄ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከመታፈናቸው 4 ዓመት በፊት የወጣው መረጃ አቶ አበበ ንጋቱ ከአዜብ መስፍን ጋር በጋራ በመስራት በአስር ሺዎች የሚቆጠር ዶላር ለኮሎኔል ፍፁም መላኩን ያሳያል። በዚህ መረጃ መሰረት አቶ አበበ ንጋቱ ለሻቢያ እና ወያኔ ሰላይ ሁኖ (double agent) እየሰሩ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።” እያሉ ሰፊ ጽሑፍ ያስነብቡናል። ሙሉን ለማንበብ ከላይ የሰጠሁትን ርዕስ ጉጉል ብታደርጉ ታገኙታላች ።
አሁን ወደ ወ/ት እየሩሳሌም ተስፋው እንመለስ። 

ካሁን በፊት ዘሐበሻ በተባለው ድረገጽ ላይ የታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነውእየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት) በሚል ርዕስ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61148 እስረኛ ሆና በጻፈቺው አስመልክቼ (“ግንቦት 7 እና በቃሊቲ እስር ቤት የምትገኝ እሩሳሌም ተስፋው ደብዳቤ ጉዳይ”) በሚል ስለ ልጅትዋ ደህንነት አስቤ እስዋ በቁጭት ብትጽፍም ወያኔ ያንን ደብዳቤዋ እንደማስረጃ ወስዶ የከፋ እስር እና ግፍ እንዳይፈጽምባት “ጽሁፍዋን” ተቀብለው ያተሙላትን ድረገጾች ወቅሼአቸው ነበር። ለሃዘኔታየ መነሻ የሆነኝ ደግሞ ካሁን በፊት የሰማያዊ ፓርቲ አባል መኖርዋን እና ቃሊቲ ገብታ የተከሰሰቺበት ክስ ግን “በነብርሃኑ ተክለያሬድ መዝገብግንቦት 7› ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው አሁን የመከላከያ ምስክር ለማስደመጥ በቀጠሮ ላይ ናቸው። የሚል ከዘሐበሻ ሳነብ ነው ልጅትዋ “የለሁበትም” ለዚህም የመከላከያ ምስክር ለማስደመጥ በቀጠሮ ላይ እያለች እንዴት ልታስበልዋት ይህንን ጽሁፉዋን ታምላችሁ? በሚል ነው። አሁን ሳየው ግን ‘እንደዚያ አይነት ጽሑፍ እንዲታተመላት ልካ ስታበቃ ፤ በቀጣዩ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ግን ለምን እራስዋን መከላከል እንዳስፈለጋት አሁንም መልስ ያላገኘሀበት ጥያቄ ሆኖ አገኘሁት። ያኔ እኔ ልጅትዋ የግንቦት 7 አባል ልትሆን አትችልም ብየ በየዋህነት ነበር የተከራከርኩላት። በጽሁፍዋ መሰረት ግን በወቅቱ ወያኔ ይህች ልጅ በግንቦት 7 አባልነት ሲከስስ ክሱ መሰረት ነበረው ማለት ነው። 

ምክንያቱም በራስዋ ጽሑፍየታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው እየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት) በሚል ርዕስ ግንቦት 7 መሆንዋን እና ብትታሰርም ልብዋ ቀልብዋ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው። እንግዲህ ይህች ልጅ አሁንም ስለ ግንቦት 7 ፍቅር እንዳላት በምትጽፋቸው እና ካሁን በፊት በጻፈቻቸው መነሻ በማድረግ “ልቧ ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ከጓዶቿ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው’ ማለት ነው። ስለ አንዳርጋቸው ከመግባታችን በፊት ልጅትዋን የምጠይቃት “አሁን የታሰረው አከላትዋ ተፈትቷል። ዛሬም ልቧዋም ከጓዶቿ ጋር ኤርትራ በረሃ ከሆነ፤ቃሊቲ እስር ገብታ ለልብዋ የተማጸነቺው ቃል ኪዳን እውን ለማድረግ ማድረግ ያለባት ቀይ ባሕር አካባቢ ካሉት ጓዶቿ መቀላቀል ነው።

እንዲህ ያልኩበትም ምከንያቴን ላስረዳ። በዛው በጻፈቺው ደብዳቤ እንዲህ ይላል፦
 ነጻ ለመውጣት መጀመሪያ ራስን ከታሰሩበት የፍርሓት እስር ነጻ በማውጣት ትግሉን መቀላቀል ነው። ድርጅታችን ግንቦት 7 ለነጻነት፣ ለፍትሕና ለዴሞክራሲ የተቋቋመ ነጻ አውጪ ድርጅት (ነው)እኔ ግንቦት 7 ነኝ፤ እናንተስ? ሁሌም እንደምለው የታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው፡፡  የነጻነት ታጋዩ ጀግናው አንዳርጋቸው ፅጌ አንድ ጊቢ ብንኖርም መገናኘት አልቻልንም፡፡ እንኳን አካልህን ወሬህንም በስንት ስቃይ ነው፡፡ እምሰማው ያንተ መታፈን ወያኔ እንደጠበቀው ትግሉን አላሽመደመደውም፡፡ እንደውም፣ ይበልጥ አጦዘው ለኛ ከቤት መውጣት ምክንያት አንተ ነህ፡፡ እኛ የአንተ ፍሬዎች ነን፡፡ ዛሬ ታፍነህ ቀንና ሌሊቱን መለየት የማትችልበት ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም የነጻነት ቀን ቀርባለችና እስከዛው ዕድሜህን ያርዝምልን፡፡ይህ ሕዝባዊ ኃይል የተመሠረተበት ዋናው ዓላማ የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ በሃገር ወዳድና ለሕዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች ምሁራንና ዜጎች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይልን መሠረቱ፡፡ይህ ሕዝባዊ ኃይል ሰንቆ የተነሳው ራዕይየሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠበት የዜጎች መብቶች፣ አገራዊ አንድነት፣ ደኅንነትና ጥቅም የተከበሩባት ጠንካራና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ሆና ማየትሲሆን ተልዕኮው ደግሞመንግሥትን በኃይል የማስወገድ ሠላማዊና የሥልጣን ሽግግር በአገሪቱ እንዲኖር የማስቻል እና ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነጻ እና ጠንካራ ብቃት ያላቸው ሕገ-መንግሥታዊ የመከላከያ የፖሊስና የደኅንነት ተቋማት እንዲኖሩ ማድረግነው፡፡ከዚህ ጊዜ በኋላም ለሥልጣኔ ያሰጉኛል ያላቸውን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሲቪክ ማኅበራት አመራሮች፣ ጦማሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች በአጠቃላይ ለም ብለው ጥያቄ እሚያነሱ ዜጎችን ግንቦት 7 በማለት በየወኅኒው እያሰራቸው ይገኛል፡፡ እንግዲህ ይህ ሕዝባዊ ኃይል ከላይ እንደገለጽኩላችሁ አሸባሪ ሊያሰኘው የሚችል ዓላማ፣ ራዕይም ሆነ ተልዕኮ የለውም፡፡ለዚህም ነው በዚህ ሰዐት ብዙ ወጣቶች ይህን ሕዝባዊ ኃይል በቆራጥነት እየተቀላቀሉት የሚገኙት፡፡…”
ስትል ሕዝባዊ ሃይል እያለች ስላለቺው እና ስለ ግንቦት 7 መሪዎች ምንነት ሕሊናዋን ጨምቃ በጻፈቺው ጽሑች የተቻላትን ያህል ግንቦት 7ን እንድናመነውና እንድናወድሰው አስነብባናለች። አሁን እንድትምልስልኝ የምፈልገው የሚከተሉት ጥያቄዎችን ነ

1)   በጻፍሺው መሰረት ነጻ ለመውጣት መጀመሪያ ራስን ከታሰሩበት የፍርሓት እስር ነጻ በማውጣት ትግሉን መቀላቀል ነው።” ብለሻል። ያንን ትምህርትሽ ሌሎች ወጣቶች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ነበርና አንቺ ዛሬ ‘አሁን ከፍርሃትም ከአካል እስርም ነፃ ነሽና ትግሉን እንድትቀላቀይ ይጠብቁሻል።”

2)- ትቀጥይና “ድርጅታችን ግንቦት 7 ለነጻነት፣ ለፍትሕና ለዴሞክራሲ የተቋቋመ ነጻ አውጪ ድርጅት (ነው)እኔ ግንቦት 7 ነኝ፤ እናንተስ?” ስትይ ጠይቀሻል። ግንቦት 7 ለፍትሕና ለነፃነት ለዲሞክራሲ የተቋቓመ ነፃ አውጪ ከሆነ እኔ ግንቦት 7 ነኝ አንተስ? ስትይ ለምትጠይቂያቸው ዜጎች የሚከተሉት ይያቄዎች ብያቀርቡልሽ እንዴት ተመልሺው አለሽ?

“ግንቦት 7 ለትግል ቆራጥ አላማ የነበራቸው አባላት በሆነ ባልሆነው ሰበብ እየተፈለገላቸው ብቻ መታሰር፤የተለመደ ክስተት ነው።….” እንጂ አንቺ እሩቅ ሆነሽ የምትመሰክሪለት የፍትሕ የዲሞክራሲና የነፃነት ድርጀት አይደለም” ብለው ቢሉሽ እንዴት ልተመልሺው ነው? እኛ ካንቺ በፊት ድርጅቱን የመሰረትን የተዋጊው ሃይል ገምቢ መስራቾች እና ባለስልጣኖች/አስልጣኞች/ የነበርን ነን ፤ እኔ ግንቦት 7 ነ አንተስ? ስትይ የምትጠይቂውን ጥያቄ ያየነውን የደረሰብንን ለማየት በግንቦት 7 እና ጓዶች ፍቅር የተሰለበው ልብሽ ምስክርነራችንን ለማረጋገጥ ደግሞ እራሲሽ ዛሬ ነጻ ነሽ እና ሄደሽ ታገይ እና ምስክርነታችንን አፍርሺው ብለው እዛው የነበሩት ሰዎች ቢጠይቁሽ ምን ትያለሽ?

3)-ሌላወ ደግሞ - “የነጻነት ታጋዩ ጀግናው አንዳርጋቸው ፅጌያንተ መታፈን ወያኔ እንደጠበቀው ትግሉን አላሽመደመደውም፡፡ እንደውም፣ ይበልጥ አጦዘው ለኛ ከቤት መውጣት ምክንያት አንተ ነህ፡፡ እኛ የአንተ ፍሬዎች ነን፡፡” ስትይ ትግሉ መሽመድመዱና አለመሽመድመዱን በትገልጪልን? ይበልጥ መጦዙንም ነግረሽማልና ግንቦት 7 ወደ ትግሉ ሜዳ ገባሁ ካለን ወደ 9 አመት ሆኖታል ያጦዘውን የብረት ትግሉና የተቆጣጠረውን ነፃ መሬት ብትነግሪን ለማናውቀው ጥሩ ዜና ነውና እንድትገልጪልን እንጠብቃለን። ካላወቅሺውም፤ የከነፈው ልብሽ ወደ ቀይ ባሕር ይሻገር እና የወጡት ነፃ መሬቶች ካሉ ዜናውን አብስሪን።

4)- እንዲህም ብለሻል- “አንዳርጋቸው እኛ ያንተ ፍሬ ነን። ብለሻል። ሌሎች ካንቺ በፊት ያነት ፍሬ ነን ብለው የተከተሉት እና በረሃ የገቡት ግን ያንተ ፍሬ ከመሆን ቢቀርብን ኖሮ ይህ ሁሉ “ስቃይ፤ግርፋት እና መገደል፤ከኑሮአችን መፈናቀል ባላየን ኖሮ” ብለው ለሚሉ ግርፋትና እስራት ውርደትና መፈናቀል ደርሶባቸው ሸሽተው ከመሞት ድነው ‘አንቺ የነጻነት የፍትህ የዴሞክራሲ” ድርጅት ነው የምትይውን በፍቅር ወላፈን የተንገበገብሽለትን ድርጅት “ወንጀለኛ፤ጸረ ዲሞክራሲ፤ቅጥረኛ እና ጸረ ነጻነትና ጸረ ፍትሕ ነው” ቢሉሽ መልስሽ ምንድነው? ይህህንን ላለማመን ከተገደድሽም አንዳንዶቹ አንቺ ያለሽበት አገር ውስጥ ስለሚኖሩ ፈቃድሽ ከሆነ “መመጎት” የምትችይበት ሁኔታ ቢመቻችልሽ ፈቃደኛ ነሽ? ካልሆነም ፈልገሺያቸው ለማግኘት ሞክሪ እና የድርጅቱ ድቅርሽ ይበልጥ ይግላል ወይንም እውነታውን ይጋፈጠዋል። ሕዝባዊ ሃይል እያልሽ የምታቆነጃጂለት ድርጅት ህዝባዊት ሳይሆን እንደ አንዳርጋቸው ያለውን አምባገነን ህዝባዊ ሃይል የምትያቸው ምስኪኖች ባልሆነው ሰበብ እየተፈለገላቸው የሚታሰሩ ለሰይል (ቶርች) የታደረጉ ሃይሎች ናቸው በዚህ አንድ ብትይን?

በማያዝም;-

5)-  ገና ትግሉን ሳይጀምረው ታጋዮቹን በመደብደብና በመግደል የተጠናወተው ድርጅት እየታገለ ያለው “የፖለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነጻ እና ጠንካራ ብቃት ያላቸው ሕገ-መንግሥታዊ የመከላከያ የፖሊስና የደኅንነት ተቋማት እንዲኖሩ ማድረግ ነውስትይ በሚገርም ምስክርነትሽ ለማስተማር ጥረሻል። ምንልባትም በቂ መረጃ ከሌለሽ “ከማንም ያልወገነ” ስለምትይው ጉዳይ አንድ ምሳሌ ልስጥሽ። የግንቦት 7 አፈቀላጤው ‘ኢሳት’ ብርሃኑ ነጋ- በየስድስት ወሩ ግማሽ ሚሊዮን (በአመት አንድ ሚሊዮን ዶላር) ከሚለግስለት ዕርዳታ ግማሽ ሚሊዮን ለኢሳት መድቦለታል። ይህም በርሃኑ በገዛ ንላሱ ሲናገር የተጠለፈ የስክ ንግግሩ የተናገረው ነው። ብርሃኑ ገንዘቡን የረዳው ማን መሆኑን ባይናገርም ይህ የዜና ምንጮች የዘገቡት ዜና “the grant was allocated by the Egyptian government and was facilitated by the Egyptian ambassador to the US, Mohamed Tawfik.” ይላል። ለጋሽዋ ግብፅ ስትሆን ‘መሐመድ ተውፊቕ’ በተባለው አሜሪካ ውስጥ የግብጽ አምባሲ ወኪል ነው ይላል። ብርሃኑ ግን ገንዘቡን ሲረከብ ‘መሪውን’ ሳይሆን ምክትሉ እንደሆነ እና ልገሳውም ‘ለኛ ጥቅም ስንል አንጂ ለናንተ ብለን እይደለምና ምስጋና አያስፈልገም’ ብሎኛል ሲል ብርሃኑ ግልጽ አድረጎ ነግሮናል። በተገኘው ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ግማሹ ኢሳት ለተባለው የግንቦት 7 አፈቀላጤ እንደሚሰጥ ብርሃኑ ተናገሯል። የተቀረው ለግ7 ስራ ማስኬጋ… ነው ብሏል። ኢሳት የግንቦት 7 መሆኑን የሚነግረን ይህ ማሰረጃ ከታጋዮቹ ምግብ፤ ስነቅ ጫማ…ይልቅ ይህ ለዚህ የዜና ማሰራጫ ቅድሚያ ሰጥቶታል። ለምን? ብለሽ ብትጠይቂኝ አንቺ ከላይ የጠቀስሺው “ካመንም ያልወገነ ድርጅት ወታደር፤ተቋም….” ምንትስ ምንትስ ለመመስረት ነው ስለምትይው ቅዠት ሳይሆን ሃቁ ግን የሚከለተለው ነው።

“የኢትዮጵያ ሕዘብ ጀሮና አፍ” ነው እያለ በማምታታት ‘ለግንቦት 7 የወገነ የዜና ተቋም መመስረት አንዲያመቸው ነበር ትልቁ  ድርሻ ለግንቦት 77 የሰጠው”። ያም ስላደረገ፤ በአንቺው ጀግናሽ አንዳርጋቸው ጽጌ የተደበደቡ፤የታሰሩ፤አሁንም አንዳሉና፤ ያለ ምንም ጥፋት ስለጠየቁ ብቻ ‘የታፈኑና የት አንዳሉ የማይታወቁ’ የተገደሉ ሰዎች አሉ። ይህንን ድብደባ እና ምስክርነት ያዩ ታጋዮቹ ሸሽተው መጥተው የግንቦት 7 ጉድ ለሕዝብ እንዲገልጹ ኢሳትን ቢጠይቁ መድረክ አንሰጥም አሉዋቸው። ያውም ደብዳቤ ጽፈው አንዳርጋቸው ያደረሰብንም ሆነ ብርሃኑ ነጋ እና አመራሮቹን በሕዘብ ፊት እንድንከራከር ከነሱ ጋር አገናኝታችሁ አወያዩን ብለው ቢጽፉም ይባስ በሎ ከሚዲያ ባሕሪና ደምብ ውጭ “የወያኔ ሰላዮች ናቸው” በማለት አብየቱታ አቅራቢዎቹን መድረክ በመከልከል፤ ከግንቦት 7 በላይ ግንቦት 7 ሆነው ስማቸውን ስያጠፉ መኖራቸውን በወቀቱ ገልጸነዋል። ስለዚህም ግንቦት 7 ስልጣን ላይ መጥቶ ያልወገነ ተቋም እንዲመሰርት ነው ትግሉ ብትይን ከመሳቅ ሌላ ማለት አይቻልም።

 በዚህ ሳትወሰኚ አንደሂ በማለት፤

“በአጠቃላይ ለምን ብለው ጥያቄ እሚያነሱ ዜጎችን ግንቦት 7 በማለት በየወኅኒው እያሰራቸው ይገኛል”። ስትይ ወያኔን ትከሺዋለሽ። ይህ ክስም ያንቺው ግንቦት 7 ድርጅትም “ጥያቄ ጠየቃችሁ እየተባሉ ብዙ ታጋዮች ታስረዋል፤ተደብድበዋል፤ እንዲገደሉ ለሻዕቢያ ተላልፈው ተሰጥተዋል..” ሲሉ እነ ሽታው ነግረውናል ። ሽታው ሽፈራው ማን ነው? ድርጅትሽ ለስቃይ ከዳረገው አንዱ ነው። ከታች ማን መሆኑን ታገኚዋለሽ።

ሽታው ሽፈራው ማለት፦

ሽታው ሽፈራው ለሦስት ወር ከዛፍ ጋር እየታሰረ ከጥዋት እሰከ ምሽት ለ 12 ሰዓታት አንድ ጊዜ ብቻ ውሃ እንዲጎነጭ እየተደረገ ሄሎኮፕተር/ወፌ ላላ/ እየተገረፈ ያሳለፈው መከራ በዝርዝር እንባ እየተናነቀው በቪዲዩ እና በድምጽ ገልልናል።

ሽታው እንዲህ ሲል ይነግረናል።

በሻቢያ መርህ መሰረት መንቀሳቀስ ለይስሙላ የተዘጋጀው ድርጅታዊ ሕገ ደንብ ተግባራዊ ያለመሆን፤አባላት በሻቢያ የጉልበት ስራ ላይ መጠመድ፤ለትግል ቆራጥ አላማ የነበራቸው አባላት በሆነ ባልሆነው ሰበብ እየተፈለገላቸው ብቻ መታሰር፤የተለመደ ክስተት ነው።….” ካለ በኋላ የነፃነት ታጋይ የምትይው ስለ ታጋይ አንዳርጋቸውም ታጋይነት አንዲህ ሲል ይነግረናል።

“…..በተለይ በአንዳርጋቸው በኩል ከፎቶ ግራፍ እና ከቪዲዮ ቀረጻ የዘለለ ስራ ለመስራት ያለመፈለግ፤ወደ አውሮፓ ለገንዘብ ስብሰባ ሲሄድ የሚለብሰውን ኮንጎ ጫማ ተሸክሞ ለመሄድ ጉጉት ያለበትን ያህል ሲመለስ ደግሞ ጠላት እንዳየች ጃርት የሸበተ ጸጉሩን እንጨፍርሮ ለሻቢያ ነው የማስረክባችሁ በሚል ስሜት ሁል ግዜም የሚገልጽ መሆኑ እና ሌሎችም ከሻቢያ ምድር ላይ የግድ ሊታጨዱ የሚገቡ ውጤቶች ሆነው ተገኝተዋል። በመሪዎች በኩል ያለውን ከወረቀትያልዘለለ የትግል ሞራል በማንሳት ትግሉ ከግለስቦች ጥቅም እና ከሻቢያ ፍጆታ የዘለለ ትርጉም የሌለው መሆኑን በተጨባጭ ስላየነው ድርጅቱ በፈጣን ኪሳራ ከመውደቅ አይድንም። ይህነን  ማስቀመጥም ይቻላል።”…

ይህንን አስመልክቶ፤ ከግንቦት 7 እና የሻዕቢያ አፈናና ግድያ በመከራ አምልጠው ከወጡት የህዝባዊ ኃይል አመራሮች አባስ/ ማስረሻ (የስልጠና ከፍል ኃላፊ) አና ኮስሞስ (የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) ቴዎድሮስ ስዩም (ምኒሊክ) (የምልመላ ክፍል ላፊ) ሽታው (አስተዳደር እና ፈይናንስ ሃላፊ)፤ ዳኒኤል፤ አንተነህ፤ ወዘተ ወዘተ… የመሳሰሉ ታጋዮች አንዳረጋቸው ጽጌ ከሻዕቢያ ጋር በጠበቀ ሴራ እየተመሳጠረ፤ ጨካኝነት እና ጸረ ኢትዮጵያ እና ጸረ ሰብአዊነት ስብእናውን ያዩትን “በእኛ ይብቃ” በሚል ጽፈው ያሰራ ጩትን መግለጫ፤  ሕሊና ላለን ሰዎች ያስደመመንን ሰነድ አስነብበውናል። ያንቺወ ታጋይ አንዳርፋቸው እና የከነፍሽለት ድርጅት ይህ ነው።
እስር ሆነሽ ስለጻፍሺው ደብዳቤ አስመልክቶ አንዲህ ብየ ነበር፡

“የእነ ስንታየሁን ቃለ መጠይቅ ያደመጣችሁ ሰዎች ሰሚራ ከኣንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ምን አይነት ግንኙነት እንደነበራቸው ይፋ እንደሆነ ታስታውሳላችሁ።ሆኖም የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ተብሏልና ፤ልጅቷ መከራ ውስጥ ሆና ግንቦት 7 ጓዶቿ ጋር ለመቀላቀል መንፈሷ እዛ እናዳለ ብትጽፍ የሚያስገርመን አይሆንም። እንኳን መከራ ውስጥ ያለ፤ እዚህ ውጭ አገር ተቀምጠው የግንቦት 7 ማንነት በመሪዎቹ አንደበት በግልጽ እየተነገራቸውም ድርጀቱን የምጠይቅ ድፈርት የላቸውም።” ብየ ነበር። አሁን ሳየው ግን ፍቅርሽ አሁን አልዛለም እና ሳይዝል ተሎ ቀይ በህር ‘ተሻግረሽ’ ወደ ጓዶችሽ ስትቀላቀይ ያኔ “እኔ ግንቦት 7 ነኝ አንተስ?” የምትይው ጥያቄሽ እዘ ሆነሽ እንድትደግሚልን እየተጠባበቅን ነው።

በመጨረሻም ስለቅንጅት አንስተሽ ስለ ግንቦት 7 መሪዎች አንዳርጋቸውሽ እና ብርሃኑ ነጋ የምትይው ቅንጅት ብርሃኑ ምን ሚና አንደነበረው በዚህ ልግለጽልሽ እና ልሰናበት
እስኪ አንዳንድ ጸሃፊዎች ብርሃኑን ያጋለጡበትን ማሕደር እንፈትሽ፤

የቅንጅት አመራሮች ጥቅምት 18 ቀን ገበሬውን ማጭድ አትዋዋስ፣ የቤት እመቤቶችን ሰፌድ አትቀባበሉ፣ የተቸገረ ኢህዴግ ብታገኙ አትመጽውቱ ብለው በመማማል ለጋዜጦች መረጃውንሊክአደረጉ፡፡ በነጋታው ጥቅምት 19 ቀን 1998 . / ብርሃኑ የነፍስ ሲያውጁበት በነበረው የቀስተ ዳመና ደብዳቤና ማህተም አማካኝነትአኛ ቀስተ-ደመናዎች የለንበትምአለ፡፡ አብሮ አቡኩቶ ጋገራው ላይ አኔ የለሁበትም የብርሃኑ ነጋ ባሕሪ ነበር። 

በረከት ሰምኦንኢትዮጵያ ፎረም ፎር ፖለቲካል ሲቪሊቲበሚባለው የወያኔ አሽከሮች የወያኔን ወለል የሚወለውሉበት ሀገረ አሜሪካ በሚገኘው የውይይት መድረክ ላይ ቀርቦ ያለውን ቃል በቃል  ላስቀምጥ / ብርሃኑ ብዙ ጊዜ የሚያነሳልኝ ነገር እኔ መቼም ይሄ ሂደት አስፈርቶኛል፡፡ አንተ ነው የምመጣው፡፡ አንተ ታድነኛለህየማይለኝ ጊዜ አልነበረም፡፡ (በረከት ሰምኦን) ሲል የብርሃኑ ባሕሪ ገልጾልናል።
 
እስኪ ሌላው የብርሃኑ ትዝታዎችና ማሕደር እናስታውስ። መቸም አስታዋሽ ሲያጣ ነገር እየተራሳ እነ ብርሃኑ ነጋነፃ አውጪዎች፤ቆራጦች….ጀግኖች.ማንዴላዎችእየተባለ እየተፏጨላቸው ሲንጨበጨብላቸው አድምጠናል። ብርሃኑ ግን ማሕደሩ ያንን አያሳይም።

ምሳሌ ልስጥ እጅግ በጣም የሚያሳፍረውና ለሕሊና የሚከብደው ነገር ደግሞ ሌላው የዶ/ ብርሃኑ የእስር ቤት የአራዳ ፖለቲካ ነው።  ይላሉ አንድ ጸሃፊ፤-

 እኔ የቀሰቀስኩበትም ሆነ ያነሳሳሁበት ጊዜ የለም፡፡ መታሰር አይገባኝም፡፡ አልፎ ተርፎም የቅንጅቱም ሥራ አስፈፃሚ አይደለሁም፡፡ ጥቅምት 22 የተሰበሰበው የቅንጅት ላእላይ ምክር ቤት የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ወስኖ በወ/ ብርቱካን ፊርማ መግለጫው ሲበተን አሞኝ አልተገኘሁም፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ አኔን ለማሰር የሚያስችል በቂ ምክንያት የለውም፡፡ እኔን ያሳሰረኝ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነው፡፡ ወደፊት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቦታ መያዝ የምችለው እኔ መሆኔን ስለሚያውቅ ነው  የሚል ነበር፡፡

በተለያየ አካባቢ አጋጣሚና በተደጋጋሚ ይህንን  እስር ቤት ውስጥ ሲያነሳው የነበረውአልነበርኩበትም”  ክሕደት በዓላማ አንድነት የተሳሳሩ የትግል አጋሮቹ ጋር በጋራ በወሰዱት አቋም ምክንያት መታሰሩን ጥያቄ የሚያነሳ ከሃዲና ሽሽታም ግለሰብ ነው፡፡ አሁንም ከነ ተስፋዬ ገብረአብ ጋር አስመራ ውስጥ  እየተሽሞነሞነ ወርቅ ፍለጋ የተሰማሩ የትግራይ ድሃ ወጠቶችን ከሻዕቢያ ጋር እየተነጋጋረ ከትግራይ ድምብር እያሳፈነ ለማጋፈጥ እንጂ እሱ እራሱ ጦር ሜዳ ሄዶ አንደማይዋጋ ከማህደሩ ማንነት የምናውቀው ግለሰብ ነው። በዚህ ወር ደግሞ በየሦስት ወሩ አሜሪካ ሲመላለስ (እንደሚወራው ከሆነ) በእግረመንገዱም ወደ በኤርትራ ሂሳብ በኩል የሚተላለፍ ወደ ናቅፋ የሚለወጥ ዶላር ለቃቅሞ ለመሄድ እንደገና መጥቷል።

አሁን የሚቆጨኝ ወ/ት እየሩሳሌም ተስፋው እስር ቤት ሆና የጻፈቺው እኔም ግንቦት 7 ነኝ፤ የታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው ብላ በታተመላት ጽሑፍ በገርነቴ ሳላውቅ ስለ ህይትዋ በማሰብ “የዚህ ወጣት ፎቶግራፍና የእጅ ጽሑፍ በይፋ ለወያኔ በማቀበል ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩባት ማየት አሳዛኝ ነው። በልጅቷ ላይ የከፋ መከራ እንዲደርስባት እያደረገው ያለው ሥራ መወገዝ አለበት።፡ልጅቷ በጭንቀትና ተስፋ መቁረጥ የጻፈቺውን ደብዳቤ ምክንያት እስር እያለች  አደጋ ቢደርስባት የዚች ልጅ ቤተሰብ ግንቦት 7  በሃላፊነት መጠየቅ አለባቸው” ስል በመቆርቆር የጻፍኩት አሁን ስህተተኛ መሆኔን እስዋም ዛሬም የድርጅቱ ፍቅርዋ እንዳለ መሆኑን በመግለጽዋ ስህተቴን አርሜአለሁ። እንደዚህ ከሆነ ወ/ት እየሩሳሌም ተስፋው ይጣቄዎቼን እንድትመልሺ እጠባበቃለሁ።

በመጨረሻ ሁለት ነገሮችን ላስጨብጥሽ፡
1)-አንዳርጋቸው ከእስር እንዲፈታ ፍላጎቴ ነው። ሆኖም ወያኔ ከፈታው እጅግ የሚመሰገን ነው። ምክንያቱም፤ አንዳርጋቸውን (ሻምበል ዳዊት የተባለው ሻዕቢያ) ለመግደል ወደ ኤርትራ የተላከ የወየኔ ሰላይ ትግሉን ከተቀላቀለ በሗላ፤ ሰለዩ ነብሰገዳይ እራሱን በመጸጸት ለነ ሽታው እና ለመሳሰሉት ታጋዮች ምስጢሩን በመግለጽ አሁን ግን ከልቤ አዝኜ ከልቤ ትግሉን እታገላለሁ ብሎ ለአመራሩ ለአንዳርጋቸው ጽጌ እንዲነግሩት ሲናዘዝ፤ አንዳርጋቸው ጽጌ ይህንን በራሱ የተናዘዛው ሰላይ አመስግኖ ትግሉ እንዲቀጥል ከማድረግ ይልቅ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲል “ሰላዩ እውነተኛ ታሪኩን ለማሳየት ሲል ራዲዮ ይዞ ከተመሳጠራቸው የወያኔ ላኪዎቹ ጋር በራዲዮ ሲነጋገር የተቀዳወን ድምጽ፤ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ እራሱ ትያትር በማቀናጀት ይህ ሰይጣናዊ ስራው ለኢሳት ዜና አስተላልፎ ‘እነ ሲሳይ አገና እና መሳይ መኮንን፤ፋሲል የኔአለም…” ሆነው ነገሩን ለሳምንት እያቦኩ እያደመቁ እያጋነኑ አንዳርጋቸውን እየጠየቁ ትያትር ሰሩበት። ከዚያም ልጁ ተይዞ ለሻዕቢያ ንንዲተላለፍ አደረገው። ለስቃይ ለግርፋት እንደሚዳረግ እውን ነው። በህይወት እንደማይኖር ግልጽ ነው። አሁን ያለው ጥያቄ እውን ሰውየው ሰላይ ነው ብሎ አንዳርጋቸው ካስገደለው ወይንም አሳስሮትም ከሆነ በህይወት ካለ ወያኔ ሻምበል ዳዊትንም ይሁን አንዳርጋቸውን ለመግደል የላኩትን ሰላይ አሳልፈህ ሰጥተኸዋል እና አንድንፈታህ ከፈለግህ ሰላያችንንም ጭምር ግንቦት 7 እንዲያስፈታው አስረክበን ብለው ለግንቦት7 ሳይጠይቁ (ከትግራይ የታፈሱ ወርቅ ለቃሚዎችም ጭምር) አንዳርጋቸውን እፈታለሁ ሲል አብይ አሕመድ መናገሩ ወያኔን ወይንም ሥርኣቱን ማመስገን አለብሽ። አላመሰግንም ወዶ ሳይሆን ተገድዶ ነው ካልሽም የግንቦት 7 ታጋዮች ናቸው ወያኔን አስገድደው አንዳርጋቸውን ያስፈቱት እስካላልሽ ድረስ ይሁንልሽ እንላለን። ሲፈታ ግን ወደ ትግሉ ሲሄድ አብረሽ ወይንም ቀድመሽ ቀይ ባሕር አንደምትሻገሪ ተስፋ አለን።
አንዳርጋቸው ሲፈታ ኤርትራ ያሉት በመሪዎችሽ ጣሰሩ የተገደሉ የተደበደቡ የሰው ልጆች (ዜጎቻችን) መብት የምንቆረቆር ከሆንን እነሱም አንዲለቀቁ ጥሪ እናቀርብላችሗለን። ስለ ሰላዩ ሰውየ አሳዛኝ ታሪክ የነገሩን ደግሞ ከዛው ሸሽተው ከመጡት የሰጡት ቃል ነውና አንረሳውም።

2)- እስር ቤት እያለሽ አምና ልክ በዚህ አመት May 22, 2017 (ፈረንጆች አቆጣጠር) ግንቦት 7 አመራሮች ባሉበት በኤርትራ ምድር) የድርጅት መሪዎችሽ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነው እያሉ ጥብቅና የቆሙለት “ግራዚያኒው ኢሳያስ አፈውርቅ” በተለያዩ ቦታዎች በትዕዛዙ እራሱ ቆሞ  እያየ በየአውራጃው እየሄደሰንደቃላማችን አንድትቦጫጨቅ እና አንድትረገጥ እንዳደረገው ሁሉ፤ ዛሬምየሙሶሎኒ ልጆችያንኑ ያደጉበትን ጋጠወጥ ባሕሪያቸውን በመድገም የኢትዮጵያን ሕዝብ ምልክት የሆነው አርማችንን  ቦጫጭቆ በመጣል፤ በሰልፈኞች ጫማ እተረገጠና በታዳጊ ወጣቶች መጫማያ እየተቀላ ሲጨፍሩና ሲተፉበት ወደ እሚያሳየው የዱርየዎች ግብረ ትዕይንት እንድታይ እና ግንቦት 7 ትሽ ምን ያህል አዋራጅ መሆኑን ታዘቢ።ይህንን ለማየት 2017 Eritrean Independence Carnival Show ምርኢት ካርኒቫል (May 22, 2017) በሚከተለው ዩ ቱብ አድራሻ ተመልከቺ። (ከታች ያሉት ሁለት ጸረ ኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አክባሪዎች ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው (ደ/ር ዜሮ) እና የግንቦት 7 አመራራር ለሻዕቢያ ማዕቀብ እንዲቃወሙ ኢትዮጵያውያንን የቀሰቀሰ እና ያስረባበረ የሻዕቢያው ወዳጅ ንአምን ዘለቀ ናቸው።
              አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)