Friday, February 11, 2022

የትግራይ “ናዚትራ” ርእየተ ዓለም“ የናዚ ጀርመን “ሊበንስራም” ቀጥተኛ የመስፋፋት ቅጂ ነው ጌታቸው ረዳ (ETHIOPIAN SEMAY) 2/11/2022

 

የትግራይ “ናዚትራ” ርእየተ ዓለም“

የናዚ ጀርመን “ሊበንስራም” ቀጥተኛ የመስፋፋት ቅጂ ነው

ጌታቸው ረዳ

(ETHIOPIAN SEMAY)

2/11/2022



በምስል የቀረቡ ሁለቱ ካርታዎች የመጀመሪያው “የናዚትራ” መንጋዎች (የትግራይ ናዚ መንጋዎች) የፈጠሩት የትግራይ ነባር ካርታ ነው የሚሉት በ2014 ዓ.ም (በ2022) “የተፈበረከ” አዲስ “የዓባይ ትግራይ” ካርታ ሲሆን ሁለተኛውና በክብ የተመለከተው የትግራይ አውራጃዎችና ወሰኖች በነባሩዋ ትግራይ ክ/ሃገር የነበሩ አውራጃዎችን እና ይዞታዎች ከእውነተኛው ከመጽሐፈ አከሱም የተገኘ የካርታ ማስረጃ ነው። ነባር የሚለው ካርታ በነባርነት የሚታወቀው “ትግራይ” በክብ “መልክኣምርዋ” የተመለከተው በ8 አቅጣጫዎች/ማዝኖች/ የተጎራበተና ወሰኖችዋንም ማመሰከሪያ የቀረበ “ነባር” የትግራይ ይዞታ ነው። ናዚትራዊው ኪዳነ አመነ የፈበረከው ካርታ እና የቦታ ስሞች በነባሩ የትግራይ ካርታ ከሚለው ብምዕራቡም ሆነ ደቡባዊ ከሚላቸው ቦታዎች  “አንድም” ለማስረጃ  አይገኙም።

ይህ ካልኩ ዘንድ ወደ ርዕሱ ልግባ።

ዛሬ የማቀርብላችሁ በማንነት ቀውስ ከሚሰቃዩት፤ ያልሆኑትን “ለመሆን” ከሚከጅላቸው ፤ እንደ “ሰው ሳይሆን እንደ ጎሰኛ” የሚያስብ በሰውልጅት ማሰብ ካቆሙት ትግራይ ውስጥ ከተወለዱ የሰው አራዊቶች (ሁማን ቢሰትስ) መካካል ከላይ ስሙ የተጠቀሰው የ ”ናዚትራ” መንጋዎች  “የባይቶና አመራር አባል” ከሆነው “ኪዳነ አመነ” ስላቀረበው ስለ መጪዋ ታላቅዋ ትግራይ የሚያሳይ የተስፋፊነት ማስታወቂያ ስለ አዲሱ ካርታው  እንወያያለን።

የ “ናዚትራው” ቡድን ሰሞኑን ብቅ ብሎ ይዞት የመጣው ርዕስ “ትግሬ በተፈጥሮ ከአማራ ጋር አትዋሰንም” በማለት ያንን እውን ለማድረግ ደግሞ ከየት እንደፈጠረው የማይታወቅ የትግራይ ነባራዊ አዲሱ ካርታ “ሞነጫጭሮ” እንደ የርዕዮተ ዓለም አባቶቹ “ጀርመኖች” ከዚህም ከዚያም እንደ ቡልኮ “በተለያዩ ቀለሞች ቀባብቶ” በማገናኘት በፌስቡኩ ለጥፎ እያስሳቀን ካለው አንዱ የናዚትራው መንጋ “ኮሚዲያን” ኪዳነ አማነ ለዛሬ የመወያያ ርዕስ አቀርብላችሗለሁ።

በኪዳነ አመነ ጽፉፍ “ትግሬ በተፈጥሮ ከአማራ ጋር አትዋሰንም” ሚልባቸው ሦስት ነጥቦቹን ከትግርኛ ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁ። እንዲህ ይላል፦

በተፈጥሮ ትግራይ ከአማራ ጋር አትዋሰንም። ከአማራ ጋር እንድትዋሰን ያደረጋት ዋነኛዎቹ ምክንያቶች ሦስት ናቸው። 

1-      ትግሬ ሆኖ በአማራ አስተሳሰብ የተጠመቀ

2-አማራዎች እራሳቸው ታላቅዋ አምሐራ ለመፍጠር ያቀዱት ስትራተጂ በመቀዳጀታቸው ምክንያት

2-      በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱ ትግሬዎች (የትግሬ ገበሬና የአማራ ገበሬ አንድ ናቸው፡ ሁሉም ብሄረሰቦች እኩል ናቸው፤ ህዝብ ከህዝብ አይለይም፤ሁሉም ህዝቦች አንድ ናቸው…ወዘተ) የሚሉ “የአማራ አስተሳሰብ” ተሸክመው በተራ ቁጥር 2 ጋር ከተጠቀሱት አማራዎች ጋር ግምባር በመፍጠር ያጸደቁት ፀረ ትግሬ የሆነ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት ማለትም “ሽጉጥ የምትመስል ትንሽ/ምጢጢዋ ትግራይ በመፍጠር የጥንታዊ ነባርዋ የትግሬን ድምበሮች ቆራርሰው ታላቅዋ አምሓራ በመፍጠር ስለተቀዳጁ ነው።”

በማለት የትግሬው “ናዚትራዊው ቲኦሪሰት” ኪዳነ አመነ እንደ ጀርመናዊው “Alfred Rosenberg” የሌሎች አጎራባች ሕዝብ መኖርያ ቦታዎችን በመውረር (ስፔስ ፍለጋ) መዋዠቅ ያማረው ይህ “ሕልመኛ ተስፋፊ” አማራን በመውቀስና በመዝለፍ “ምጢጢዋ ጭንቅላቱ” ነባሩ የትግራይ ድምበር ከየት እስከየት እንደነበር “ሁሉም የኛ” በሚለው ስግብግብ የናዚትራዎች ባሕሪ በመመራት የናዚ ልክፍት ላሃጩን በየፌስቡኩ ሲያዝረከርክ ተመልክቼው ከመሳቅ ሌላ ምንም ማለት ባይቻልም፡ ያለ አቅሙ የሚስላቸው የሌለ፤ያልነበረ የትግራይ ድምበርና ካርታ ለማሳየት የትግራይ “ነባር” ድምበሮች ስሞች እና አካባቢዎች ከስዕሉ ያቀረብኩት ከመጽሐፈ አከሱም የተገኘ መጽሐፍ በማስረጃ አቀርቤአለሁ።

ከዚያ በፊት ግን ትግሬዎች ለምን የመስፋፋት ፍላጎት እንዳደረባቸው ከሚከተሉት የዛኒ ፍልስፍና ጋር ተመሳሳይነቱን እንመልከት።

ሂትለር በ1933 ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ Lebensraum (ሊበንስራም) በተባለው መርሃግብር የአካባቢ ጎረቤት አገሮችን መሬት በማግበስበስ ላይ ያተኮረ የናዚ ዕቅድ ሲሆን፡ በዚህ መርሃ ግብር “ቦታን የመፈለግና የመውረር ዘመቻ” ብዙ ስራ ተሰርቷል።

መርሃ ግብሩ በአንደኛ የአለም ጦርነት(1914–1918) መጀመሪያ ላይ ሌበንስራም የኢምፔሪያል ጀርመን የጂኦፖለቲካ ግብ ቀዳሚ ቢሆንም ፤ መሬትን (ሰፔስ) የማስፋፋት ዕቅድ እጅግ የተደገፈው ደግሞ (ኤን ኤስ ዲ ኤ ፒ- National Socialist German Workers' Party -) ፓርቲ እና የጀርመን ናዚ ፓርቲ እስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ድረስ ተግባራዊ ሆኖ ሲገፉበት ነበር።

አዶልፍ ሂትለር ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት አዳዲስ የማስፈሪያ ቦታዎችን በቅኝ/በጉልበት/የማስፋፋት መርሃግብሩን የጀርመን ግዛት ወደ መካከለኛው እና ምስራቅ አውሮፓ እንዲስፋፋ የሊበንስራም ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ (1914–1918) መንቀሳቀሱ ይታወሳል። የናዚ አጠቃላይ 'ማስተር ፕላኑ በመሠረታዊ ሥርዓቱ ላይ ሌሎችን ሕዝቦች ከቦታቸው በማስለቀቅ (ወያኔ ለ27 አመት ሲያደርግ እንደነበረውና አሁንም በከፋ መልኩ ለማስፋፋት በወያኔዎቹ “ባይቶና” ፓርቲ እና በመሳሰሉት የትግራይ “የናዚትራ እና የፋሸስትራ አባሎች” እንደታቀደው ሁሉ ጦርነት ከፍቶ በማስራብ ከቦታው እንዲለቁ በማድረግ ነበር።

ትግሬዎች ለህልውናችን ያስፈልገናል ብለው የጎረቤት ነባር ሕዝቦችን በማስለቀቅ እንዳደረጉት ሁሉ ጀርመን ለህልውናዋ አስፈላጊ የሆነውን (ስፔስ/መሬት) እንደምትፈልግ እና አብዛኛዎቹ የመካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ ተወላጆች በቋሚነት መወገድ አለባቸው (ወይ ወደ ሳይቤሪያ በጅምላ በመጋዝ ፣ በማጥፋት ወይም በባርነት) የፖላንድ ፣ ዩክሬንኛ ፣ ሩሲያኛ ፣ ቼክኛን ጨምሮ እና ሌሎች የስላቭ ብሔራት “አሪያን” እንዳልሆኑ በማድረግ ቦታቸውን መንጠቅ የሚለውን ዕቅድ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የናዚ መንግሥት እነዚህን መሬቶች በጀርመን ቅኝ ገዥዎች በሌበንስራም ስም እንደገና በጀርመኖች እንዲሞሉ የማድረግ ሙከራ አድርጓል።

ትግሬዎች በወልቃይትና በመሳሰሉ የወሎ ግዛቶች ወርረው ነባሩን ሕዝብ አማርኛ እንዳይናገር በማድረግ አብዛኛዎቹንም በመግደልና በማስወጣት፤ሴቶችንም በትግሬዎች እየታመጹ ትግሬዎች እንዲባዙ በማድረግ እና አማራ በሚበሉት መሩቶችም “ሴቶች የአማራ ትውልዶች እንዳይልዱ በወሊድ መቆጣጠሪያ መርዞችን ወደ ማህጸናቸው በማስገባትና በመውጋት የአማራ ዘር በሚሊዮኖች አንደተሰወረ (በወያነ ፓርላማም ጭምር ባመነው ዘገባ) እንዲሁም ብዙ ሺሕ ታጋዮቻቸው በሃይል በተነጠቁ ለም መሬቶችና ከተሞች አስፍረው እንዲበለጽጉ እንዳደረጉት ሁሉ  ጀርመንም “በሊበንስራም አቅድ” የጀርን ዝርያዎች (ኖርዲኮች) ያለምንም ስጋት በምቾት ለመኖርና ለመመገብ ለራሳቸው የእርሻ ትርፍ እንዲያገኙ ሞክሯል።

ይህ የሂትለር ስልታዊ ስግብግነት መርሃግብር የአለም የበላይነትን ለመቀዳጀት “ቦታዎችን/ስፔስ” በማግበስበስ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በተያዙ ቦታዎች “በዘር” የላቀ የጀርመን ማህበረሰብ ለማሳደግ ሲባል “በሊበንስራም ዘመቻ የተነጠቁ አገሮችና ጎረቤቶች ውስጥ”፣ “አሪያን ያልሆኑ ዘሮች” የጀርመን ማሕበረሰብ አካል እንደሆኑ የሚታሰቡ ቦታዎችን አርያን ዝርያ ያልሆኑትን እየለቀሙ ማባረር ወይም የአካል የንብረት ውድመት እንዲደርሳበቸው በማድረግ (ወያኔዎች በጉልበት በያዝዋቸው ቦታዎች እንደተደረገው) በዓለም ውስጥ racially superior society አርያን ዝርያዎች ልቀው ብብዛትና በሃያልነት እንዲወጡ የሚረዳ የነዛዎችና የፋሺሰት ጣሊያኖች “የቦታ ፍለጋና መስፋፋት” መርሃ ግብር ታቅዶ በተግባር እንደዋለ ታሪክ ይነግረናል።

ሲጠቃለል የመርሃግብሩ ሁለት ገጽታዎች የሚከተሉት ናቸው።

 ( 1) ናዚዎች በሚይዙት ቦታዎች ሁሉ ትላልቅ የግብርና እና ኢንዳስትረያል ንጠረ ዕቃዎችን ለጀርመን ህዝብ ፍጆታ ማዋል፡ናዚዎችና/ፋሺስቶች በሚይዝዋቸው ቦታዎች የዘር ማጽዳት በማድረግ የተደላደለ ኑሮ ለአርያን ዘሮች መፍጠር።

(2)-የሊበንስራም ሁለተኛው መርሃ ግብር ደግሞ የሌሎች ሕዝቦችን ቦታዎች “የኛ ነበሩ” በሚል ትርክት በወረራ ቦታዎችን በመያዝ በዛው ቦታ የነበሩ “እንዲጅነስ” “ነባር ተወላጅ ሕዝቦችን” በደምና (በዘራቸው) አርያን ያልሆኑትን እየለቀሙ ማጽዳት ወይንም ከቦታው በማባረር፡ በሚያዙ ቦታዎች ሁሉ አርያኖችን እንዲባዙ በማድረግ የአርያን ዘር እንዲባዙና ሃያልነታቸው በዓለም መጥቆ እንዲወጣ ማድርግ ላይ የተመሰረተ ዕቅድ ነበር። በዚያም አስታክኮ ናዚዎች Nordicism (ኖርዲክ)  (ጀርመኒክ) በቆሸሹ ዘሮች እየተዋጠ ከምድረገጽ እየጠፋ ያለ የዓለም ምርጥ ዘር በመጥፋ ያለው የሚሉት ናዚዎች እና ትግሬዎች “በጉርዲ” (በቆሻሻ ዘሮች በተለይ አማራ ጋር የተዳቀሉ ትግሬዎች “ትግራዋይነትን” እያቆሸሱት ስለሆኑ  ከጉርዲ(ከገለባ) የጸዳ ትግራዋይነት “የተባለ “አዲስ  የትግራይ ሃይማኖት በመፍጠር  እንደሚንቀሳቀሱት ሁሉ ዛሬ ኪዳነ አመነ የተባለ ከሰውነት ውጭ በአልሰጠነ አራዊት ሕሊና በደመነብስ እየተመራ ወላጆቹ ወያኔዎች ያስተማሩትን የጥላቻና የማስፋፋት መዝሙር በማስተጋባት የሕዝብ እልቂት ለማምጣት እየሰበከበት ያለው በታሪክ ያልነበረ ነባር የትግራይ ድምበርና ግዛት በምናቡ እየፈጠረ “ጸረ አማራ” ዘመቻ በማወጅ “የሕዝብ እልቂት” መምጣት እንዳለበት በአዲስ ካርታው ይሰብካል።

ከነጭራሹ “ጎጃም ጎንደር ሽዋ እና ወሎ እንጂ “አማራ” የሚባል ዘር የለም “አማራ” ብሎ የፈጠረው “ወያኔ’ እንጂ አማራ የሚባል ሥፍራ/ማሕበረሰብ በታሪክ ተሰምቶ አይታወቅም፡ በማለት የወያኔ አፓርታይድ ክልል በማድነቅ ‘አማራ” የተፈጠረው በ27 አመት ውስጥ ነው፤ ያውም በ“ወያኔ ዘመን ይላል። ስለዚህ አመራ ከትግሬ ጋር ተካልሎ አያውቅም ይላል በሌሎቹ ትርክቶቹ።

በጣም የሚገርመው በተራ ቁጥር 2 የተጠቀሰው የኪዳነ አመነ ምክንያት እንዲህ የሚለውን እንመልከት፤

“በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱ ትግሬዎች (የትግሬ ገበሬና የአማራ ገበሬ አንድ ናቸው፡ ሁሉም ብሄረሰቦች እኩል ናቸው፤ ህዝብ ከህዝብ አይለይም፤ሁሉም ህዝቦች አንድ ናቸወ…ወዘተ) የሚሉ የአማራ አስተሳሰብ የተሸከሙ ትግሬዎች..” የሚለውን ስትመለከቱ የዚህ ልጅ ሕሊና የናዚ መርሆ አራማጅ መሆኑን የምታዩት “አማራዎች ሰው ሰው ነው ሁሉም ህዝብ በሰው ልጅ ህዝብነቱ እንጂ በጎሳና በዘሩ መለየት አይገባም” የሚለው የአማራዎች  የሰው ሰውነት ማሳያ መልካም የአንደነት ተግባር ፍጹም በመጻረር እኛ በተራ አንድ ቁጥር የጠቀሰንን ትግሬዎች “ሰው በሰውነቱ እንጂ በጎሳውና በዘሩ ለይቶ መደራጀት፤ ትግሬ ከትግሬ አማራ ከአማራ ብቻ መጋባት በተፈጥሮ ሕግ የሰው ልጅ ተግባር አይደለም” እንደ ኢትዮጵያ አብረን መኖር የምንል የትግራይ ሰዎችን ኮንኖናል።

ይህ የሚያሳየን ምንድነው ስንል ከላይ የጠቀስኩት የናዚው ሊሂቅ “Alfred Rosenberg” አይሁዶች ሰው  ሳይሆኑ ከአርያን/ከኖርዲክ ሕዝብ እንደ ሰው ወይንም እንደ ሕዝብ መጠራት አይቻልም” ባይ ሲሆን ከኖርዲክ ዝርያ ወይንም እንደ ኪዳነ አመነ (ከትግራይ ውጭ ያለው ሕዝብ እኩል እንደ ትግራይ “ሰው” ሰው ማለት አይቻልም”ይላል። “Total alienation እና “Total humiliation” ነው እንደ ናዚዎቹ የኪዳነ አመነ ሰበካ።

ኪዳነ አመነ የሚሰብከው ይህ አዲስ ካርታ እውን ለማድረግ የሚሰብከው “በጦርነት” ነው።ይህ የናዚትራዎች ቅዠት የሚቀበል ስለሌለ “ጦርነት” እንደ ቦታ ስገኚያ እና ከተሰመሩ አዲስ ካርታዎች “አማራን ማጽጂያ/ማጥፊያ” እንደ ጥሩ አጋጣሚ ይመለከተዋል።

“Alfred Rosenberg ናዚ ከተሸነፈ በሗላ በፍተሻ በጠረጴዛው ውስጥ የተገኘው የእጅ ጽሑፉ እንደህ ይላል።

 I welcome the war. It is necessary to exterminate directly all those racially inferior germs of Jewry and its bastards as a final solution to the problem unsolved for ever two thousand years …”  “ (Alfred Rosenberg- by Fritz Nova P-120 published 1986)  (ጦርነቱን በደስታ እቀበላለሁ። ለሁለት ሺህ ዓመታት ላልተፈታው ችግር የመጨረሻ መፍትሄ ሆኖ እነዚያን በዘር ዝቅተኛ የሆኑ የአይሁድ “ጀርሞችን/ትል/” እና መናኛ ፍጡራን ሁሉ በቀጥታ ለማጥፋት ጦርነት አስፈላጊነት ነው…።” (Alfred Rosenberg- ደራሲ Fritz Nova ገጽ-120 ሕትመት 1986)

እንግዲህ የትግራይ ነባር ደቡባዊና ምዕራባዊ የትግራይ መሬትና ድምበር ብሎ የፈጠረው ካርታ “ድል ለታሪካዊና ሕጋዊ መሬታችን!” “ድል ለታላቅዋ ትግራይ!” በማለት የደመደመው ካርታ “በድል” ሊተገብረው የሚችለው መንገድ በጦርነት እንጂ በምንም ሕጋዊም ሆነ ታሪካዊ ማስረጃ ሊያረጋግጠው አይቻለውም።በቅርቡም እየተካሄደው ያለው ጦርነትም የታቀደው እንደማያዛልቅ እያየነው ነው።

ለዚህ ነው “የናዚትራ ጦር” መሪዎች ትግራይን ለመገንጠል “ግንጠላን” እንደ ወንጀል መሸፈኛ እና መሸሰጊያ ዋሻ እየተጠቀሙበት ያለው።

እንደምታዩት ይህ ካርታ ነባር ሳይሆን በ1914 ዓ.ም (በ2022 AD) በኪዳነ አመነ እና የመሳሰሉ “የናዚትራ እና የፋሽትራ” የትግራይ ናዚዎችና የትግራይ ፋሺሰት በድኖች ወጣቱን በማስፈጀት  ዕድሚያቸውን ለማራዘም ፤ለወንጀላቸው መሸሸጊያና ከሕግ ሰንሰለት ማስመለጪያ (መደራደሪያ) የሚጠቀሙበት  ስልት ነው።

አዲሱ የመሬት ካርታ የማግበስበስ ዘመቻ በታላቅዋ ትግራዋይነት ድምፅ የሚጮህ የትግራይ “ናዚትራ” ርእየተ ዓለም ‘የናዚ ጀርመን “ሊበንስራም” ቀጥተኛ የመስፋፋት ቅጂ ነው።   

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (ETHIOPIAN SEMAY)