Thursday, February 27, 2014


የወያኔ ትግሬዎች በጉንደት፤በጉራዕ፤በዶጋሊ፤….ጦርነቶች የሚዋሹት ውሸት ሲመረመር

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
 መጀመርያ በዚህ የአመቱ ምርጥ ብየ በምጠቅሰው ጥቅስ ልጀምር፦"የመሬት ላራሹ" ጩኸት ውጤቱ "መሬት ለነጋሹ" ሆኗል፤ ለገበሬው የታሰበውን መሬት ወያኔ ወሰደው። የዱሮ ንጉሣዊ ገዢዎቿ ቤተ ሰቦች ስለነበሩ በቊጥራቸው ማነስ ምክንያት እነሱን በማር ግብር ለማጥገብና በሰላም ለመኖር ቀላል ነበረ። የዛሬዎቹ ገዢዎች ብሔረ ሰቦች ስለሆኑ እነሱን ሁሉ በሚሊዮን ዶላር ማጥገብ መራቆትን አስከትሏል።” ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ (ዕርቅና ሰላም፤ የሕይወት ቅመም’ የካቲት 2006 ዓ.ም)

ወየኔዎች ወደ ሥልጣን ከመጡ በሗላ የአገሪቱን ሃብት ባገኙት አቅም እና ዘዴ ሁሉ በማራቆት ብቻ የተወሰኑ ሳይሆኑ የትግራይ ሕብረተሰብ በታሪክ ላይ የሚኖሮው ግንዛቤ የተጣመመ እንዲሆን አድረገውታል።  በርከት ያሉ እንሰሳዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሆን ብለው አጥቂዎቻቸውን ወይንም መሰሎቻቸውን ያታልላሉ። እንሰሳዎቹ በማታለል ዘዴ የሚኖሩበት ምክንያት የተለያዩ ምክንያቶች አሉዋቸው። ለምግብ፤ ወይንም እራሳቸው ከጥቃት ለመከላከል ሊሆን ይችላል።ይሁን እንጂ በተፈጥሮ እራሳቸውን እና ሌሎችን ሆን ብለው ለማታተለል/ለመዋሸት “የተሰሩ ፍጡሮች” ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ያነበብኳቸው አንዳንድ የስነ ልቦና መጻሕፍቶች ይገልጻሉ።
የተለያየ ውሸት የተለያ ምክንያት ቢኖሮውም፡ ዋሾች አድማጭ ፈላጊዎች ናቸው። አታላዮች/ዋሾዎች እንደ እንደተሰጥዎአቸው የማጭበርበር፤ የመዋሸት ወይንም ማራኪ የንግግር ችሎታቸው ይለያያሉ።  የተከታዮቻቸው ብዛትም አንደሚጠቀሙበት የማጭበርበር ስልት ይለያያል። ተራ ዋሾዎች ካደጉበት የውሸት ባሕሪ በመነሳት ሕዝብን የመምራት ፍላጎት እያዳበሩ በሄዱ ቁጥር፤ በመንግሥት፤ በፖለቲካ፤ በሃይማኖት ግብተው መሪነቱን ከያዙ፤ አደገኛ የውሸት ባሕሪያቸው በመጠቀም ሕዝቡን በውሸት ጐዳና በመምራት፤ “ዋሾ ማሕበረሰብን” ይገነባሉ።
እራሱን ያታለለ ማሕበረሰብ “የሕሊና ጎዶሎ/ሃንዲካፕ” ነው።  ሌላ ቀርቶ በየጽሑፎቻችን ላይ የሚታዩ ግድፈቶች/ የቃላት ስህተቶች ልብ ሳንላቸው አልፈን ከታተሙ በሗላ ነው ስህተቶቹ ግልጽ ሆነው የሚታዩን።  የዋህ ሕሊናም በአታላዮች አስተሳሰብ ሲጠለፍ እራሱን መፈተሽ ስለሚያቅተው፤ ከመሪዎቹ የሚነገሩት ሁሉ እውነት ስለሚመስለው፤ እሱም በውሸቱ ዘመቻ እየተካፈለ በሄደ ቁጥር እየዋሸ እንደሆነ አይታወቀውም። በመጠጥ ከሰከረ ይልቅ፤በውሸት የሰከረ ማህበረሰብ አስቸጋሪ  ስለሚሆን (ዲናያል/ክሕደት) እውነታውን ለማስጨበጥ ጊዜ ስለሚፈጅ፤ የእውነት አስተማሪዎች ከዚህ ማሕበረሰብ ጋር ከፍተኛ ግብግብ ይገጥማቸዋል።
ይህ አሳዛኝ ባሕሪ ኢትዮጵያ ውስጥ በባሰ ደረጃ በወያኔዎች ዘመን ተከስቷል። የ ‘ወያኔ ትግሬ’ የውሸት ባሕሪ በታሪካችን፤በባሕላችን፤በአርበኞቻችን እና በሉዓላዊነታችን ክብር ላይ ጥቃት አድርሷል። ጉዳቱ በጣም ከፍተኛ ነው።
ለዚህ ጹሑፍ መነሻ የሆነኝ፤ ሶሞኑን ‘ትግራይ ኦን ላይን’ በተባለው “ፍሎሪዳ” መሰረቱ ያደረገ የወያኔዎች ድረገጽ “Woyane Tigray: 39 Years and Still Standing” በሚል ያስነበበውን መነሻ በማድረግ ነው። (ጸሐፊው ሞቡቱ ሴሰ ሴኰም ሆነ ጋዳፊ ከወያኔ ዕድሜ በላይ እንደገዙ አላወቀም።
“እንደ ጋዳፊ
 መለስን በጥፊ ፤
ሳንፈልጋቸው
ሃያ አመታቸው!”
 ተብሎ የተጨፈረለትን የወያኔ ስርዓት አልሰማም መሰለኝ።)  ርዕሱን በዚሁ ልምልስ  እና ጸሓፊው በበላይ ዘለቀ እና በአሉላ መካካል ያለው ልዩነት ያነጻጸረበትን የውሸት ክስ እንመለከት።ከብርሃነ ካሕሳይ በሚል የተጠቀሰው ርዕሰ የጻፈው ጸሐፊ የዓይጋ ድረገጽ አዘጋጅ ወይንም የትግራይ ኦንላይን አባል አዘጋጅ እንደሆነ ይገመታል።ቢሆንም ባይሆንም ቁም ነገሩን ብቻ እንመልከት።
“…The warrior of Dogali, Gundet and Gura, is not receiving the accolade he rightly deserves simply because he happens to be a Tigrayan. Reverence for Belay Zeleke, who fought the Italians in Gojjam for a brief period, appears to be far greater than the hero of Africa. Unfortunately, the courageous Belay Zeleke was subsequently hanged by Emperor Hailesellaise upon his return from Bath, England, where he had resided after fleeing the country, leaving the people at the mercy of the Italian occupiers.” http://www.tigraionline.com/articles/woyane-tigray-39-years.html   (By Berhane Kahsay
Tigrai Onlne - February 09, 2014)
ይህ ውሸት ተደጋግሞ በወያኔ ትግሬ መሪዎች እና ተኮልኳሊዎቻቸው ተነግሯል። ባለፈው ወር የዶጋሊ በዓል ማክበር ሲገባ፤ ወያኔዎች ሳያከብሩት በዝምታ አልፈውታል። በዚህ የተነሳ ወዳጄ አቶ ብርሃኑ ሰፋ ያለ ቅሬታው ኢ ኢ ዲ ኤን በተባለ ማሕበራዊ መድረክ ለተቃዋሚውም ሆነ ለወያኔዎች ለምን አንዳልተከበረ ቅሬታው ገልጿል። ቅጁም ለእኔ አስተላልፎልኛል። ድሮ ደርግ ምፅዋ ላይ /ዶጋሊ ላይ ስለ አሉላ ያዘጋጀው የሲምፖዚየም ንግግር በመጽሐፍ ተጠርዞ አንዳነብበው ልኮልኝ አንብቤ አንድ ነገር አንዳዘጋጅ ተማጽኖኝ ነበር። ንባቡ ገና ሳልጀምር ወያኔዎች ከላይ የተመለከተው ሚዛን ያልጠበቀ የክስ እሮሮ በራሳቸው ከማድረግ ይልቅ በሌለው ላይ ክስ ሲያወርዱ አንብቤ ነው ይህ ድንገተኛ መልስ ለመጻፍ የተነሳሳሁ።
    ወየኔዎች የውሸት ክስ፤ስም ማጥፋት፤ ክሕደት የድርጅታቸው ባሕርያዊ ቋሚ መለያቸው ነው። በጣም በርከት ያሉ መጽሐፍቶች የአጼ ዮሐንስም ሆነ የራስ አሉላ ታርክ እና ሞገስ ‘አማራ ታሪክ ጸሐፊዎች”’ ብለው ወያኔዎች በሚጠሯቸው የኢትዮጵያ ታሪክ ጻሀፊዎች የጻፏቸው እያንኳሰሱ፤ ዛሬ ወያኔዎች ከ22 አመት ንግሥና በሗላ ገንዘቡ፤ሕትመቱ፤ሳነሱሩ፤ውሸቱ ፤ብዕሩ፤መዛግብቱ፤ዩኒቨርሲቲው እና ምርምር ተቋማቱ በእጃቸው ቁጥጥ ባለበት ዘመን ምንም ሳይጽፉ  በሃያ ሁለት አመት ውስጥ ስለ ዮሐንስ አንድ መጽሐፍ (በትዕቢት የተቆለለ ፤በውሸት የተበረዘ)  የገብረኪዳን መጽሐፍ ብቻ ነው። ወደ ሃውልት ስንገባም፤ ወየኔዎች በአገሪቱ ስም ከውጭ አገር ዕዳ እየተበደሩ ወደ ኪሳቸው ከማግበስበስ እና ልጆቻቸው ወደ ውጭ አገር እየላኩ ከማስተማር እና እራሳቸውም በውድ ገንዘብ እየገዙ ዲግሪ ከማግኘት በስተቀር ለንጉሡም ሆነ ለራስ አሉላ ሃውልት ማሰራት ሲችሉ ወይንም ሕዝቡን አሰባስበው (እርዳታ እንኳ ካስፈለገ) ከማስሰራት ይልቅ እስካሁን ደቂቃ ድረስ ምንም የሰሩላቸው ሃውልት ወይንም መታሰቢያ የለም። ስለ አሉላ ተሰራ የተባለው ሃውልት “የተቀመጡበት ፈረስ የአህያ ምስል በመያዙ፤ሕዝቡ ተቃውሞውን በማሰማት ሌላ የፈረስ ምስል የያዘ ሃውልት እስኪሰራ ድረስ በአቡጀዲ ሸፍነውት አንደነበረ ይታወቃል። አንዳንዶቹ የሚሉት ያህያ ምስል አንዲቀመጡ የተደረገው ሆን ተብሎ በሻዕብያ አፍቃሬ ኤርትራዊያን ወያኔዎች ሴራ ምክክር እንዲቀረጽ አንደተደረገ በሃሜታ መልክ ይሰማል።
በሃያ ሁለት አመት ለአጼ ዮሐንሰም ሆነ ለአሉላ ይህ ነው የሚባል አጥጋቢ መታሰቢያ አንዳልሰሩላቸው የምከራከረው በመረጃ ነው። አማራ አንዲህ አደረገ ፤ያለፉት ጸሐፊዎች የንጉሳችን ታሪክ አልጻፉም፤ ሃውልት አልተሰራላቸውም… እያሉ በውሸት እስካሁን ድረስ የወያኔ ትግሬዎች የትግራይን ሕዝብ ሲያታልሉ 22 አመት አልፏቸው ስለ አሉላም ሆነ ስለ ዮሐንስ የሰሩት አንደም መታሰቢያ አይገኝም። ይልቁንስ ወያኔዎች “ለአሉላ ወይንም ለዮሐንስ” ሃውልት ነፍገው ኤርትራ ምድር ድረስ ሄዶ፤ ምፅዋ እና ሳሕል የኢትዮጵያን ሰራዊት የወጋ በክሕደቱ ዘመን ከጠላት (ሻዕቢያ) ጋር ተሰልፎ የወጋን የራሳቸው ታጋይ ለሆነው “ሓየሎም አርአያ “ (ሐዱሽ አርአያ) ሽሬ አውራጃ ውስጥ ሃውልት አቁመውለታል። ታዲያ “…The warrior of Dogali, Gundet and Gura, is not receiving the accolade he rightly deserves simply because he happens to be a Tigrayan. Reverence for Belay Zeleke, who fought the Italians in Gojjam for a brief period, appears to be far greater than the hero of Africa.” በማለት የወያኔ ቱልቱላዎች በታሪክ ጻሀፊዎች እና ባለፉት ገዢዎች ላይ የትግሬ እና የአማራ አርበኞችን እያነጻጸሩ የሚከስሱት ዘረኛ ክስ ከመክሰስ በፊት ሁሉም ነገር በእጃቸው ባለበት ሃያ ሁለት አመት እራሳቸው ያልሰሩትን ሌሎች አንዲሰሩላቸው መጠበቅ እና መክስስ አስገራሚ ክሰ ነው ?
ለመታሰቢያ የቆሙ ከጣሊያን ወራሪዎች ጋር ተዋግተው በክብር የተሰውት የነ ደጃዝማች አፈወርቅ ፤የነ አቡነ ጴጥሮስ ፤የነ አሉላ፤ የእነ ምኒሊክ ወዘተ መታሰቢያ ሃውልቶች እያፈራረሰ እና እንዲፈርስ ዘመቻ እያካሄደ ያለው የሃያ ሁለት አመት አሳፋሪ ታሪክ የታቀፈው ማን ሆኖ እና ነው ማቆሚያ የሌለው  ሃያ ሁለት አመት “የሕፃናት ልቅሶ እና ክስ” እየተለቀሰ ሌላውን ወገን ተወቃሽ የሚሆነው? ወያኔዎች ትንሽ የአደብ ሓፈረት የሚባል የሕሊና ገዢ እንዴት አንደተለያቸው ይገርመኛል? በሃይለስላሴም ሆነ በደርግ ዘመን ስለ አሉላም ሆነ ስለ ዮሐንሰ ጀብዱ አንዳንጽፍ ተከለከልን ካላችሁ፤ ውጭ አገር ሲኖሩ የነበሩ በርካታ የትግሬ ምሁራን የማን ጎፈሬ ሲያበጥሩ ኖሮው ነው (ከዘውዴ ገ/ስላሴ በቀር) አማራው እንዲጽፍላቸው የጠበቁት እና ተከሳሽ የሚያደርጉት? ያስ ተከድኖ ይብሰል፡ - ሃውልት አልቆመላቸውም፤ ታሪካቸው አልተጻፈም .. ወዘተ… የምትሉት አሰልቺ ልቅሶ ‘ሃያ ሁለት አመት’ ሙሉ ከማልቀስ እና ከመክሰስ ያለፈ ስራ ምን ሰራችሁ? እስኪ ንገሩን? ምን ሃውልት ሰራችሁ? የሐለፎም ሓውልት? የወያኔ ተጋዮች ሃውልት? ለነሱ ከማቆም ይልቅ ለክሳችሁ መነሻ የሆነው የወላጆቻችን ጀግንነት እና ንግሥና አማራዎች ነጠቁን ብላችሁ በረሃ ለመሄድ ከገፋፋችሁ ምክንያት አንዱ ከሆነ የአሉላም ሆነ የዮሃንስ ሃውልት ቅድሚያ ለምን አልሰጣችሁትም? የአሉላ እና የዮሐንስ ገድል ይበልጣል ወይስ አሉላ እና ዮሐንስ ያስከበሩትን ድምበር እና ባሕር ያስደፈሩ እና የዘጉ የወያኔ ታጋዮች ገድል? የአሉላም ሆነ የዮሐንስ ገድል የቀበረ እና በባንዳ ተልዕኮ የተሳተፉትን የጎሳ ታጋዮች ገድል ጎልቶ በበላይነት አንዲታይ እያደረገ ያለው ማን ነው?  ኢትዮጵያዊያኖቹ ዮሐንስ እና አሉላ መታሰቢያ ሳይቆምላቸው፤ ለጎሳ ታጋዮች ለምን ቅድሚያ ተሰጣቸው?   
የወያኔ ውሸት ታሪክን የመበረዝ እና የማጣመም ባሕሪ በምን ዓይነት የአጻጻፍ ዘዴ ቢጻፍ የውሸታቸው ክምር አንዴት መግለጥ እንደሚቻል ሳስበው ይጨንቀኛል። በዶጋሊ፤ጉንደት፤ጉራዕ፤ዓድዋ፤ባድመ፤ዓድዋ… የተደረጉ ጦርነቶች የትግሬዎች የመከላከል ታሪክ እና ጀግንነት ብቻ ነው እያሉ ያለ ምንም ሐፍረት ወይንም ዩልኝታ የሚገልጹት ባሕሪያቸው ሳስበው ለሕሊና ይከብዳል። የዚህ ውሸት ማቆሚያው መቸ እና የት ይሆን?  
የዶጋሊ፤የሳሐቲ፤ወዘተ …. ወዘተ… ብዙ ኢትዮጵያዊያን የተቀላቀሉበት አንዳንዱም በመሪነት የመሩዋቸው ታላላቅ ውግያዎች ውጤት እንጂ የትግሬዎች ብቻ አይደለም። ድሉ እና ሱታፌው የትግሬዎች አንጂ የተቀሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሱታፉ አልነበረም፡ የሚሉት ተዳጋገሚ ውሸታቸው በመጽሐፍም በንግግራቸውም በየስብሰባውም እስኪሰለቸን ድረስ ደጋግመውታል። ሃቁ ግን እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን በተጠቀሱት ጦርነቶች የተሳተፉት ትግሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የተሳተፉበት ውጊያ እና ድል ነበር። መረጃውም ቆየት ብየ አቀርባለሁ። ይህ መረጃ ላንዴ እና ለመጨረሻ ውሸታቸውን የሚያቆም በመሆኑ መረጃውን እንድትጠቀሙበት በጥንቃቄ አስቀምጡት።መረጃውን ከመጥቀሴ በፊት ማለት የምፈልገው ነገር፤ መረጃው ካነበቡት በሗላ አንዳንድ ወያኔዎች፤ “ምንም እንኳ ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ ሰራዊቶች በዶጋሊ፤ በጉራዕ…ወዘተ ይኑሩ እንጂ አብዛኛው ተዋጊ የትግሬ ሰራዊት ስለነበር፤ ድሉ የትግሬ ሰራዊት ነው፡ የሚሉ የወያኔ ጐሰኞች ሊኖሩ ይችላሉ።ለነዚህ የምሰጠው መልስ “ዓድዋ ላይ የተሳተፈው ተዋጊ ሠራዊት፤ አብዛኛው ትግሬዎች ሳይሆኑ የሸዋ የንጉሥ ምኒሊክ ሠራዊቶች ናቸው።  ሌላ ቀርቶ የወያኔ ወዳጅ የሆነው አይሁዳዊው  ‘ኤሪክ ሓጋይ’ “አሉላ” በተባለው መጽሐፉም የትግሬ ሰራዊት እጅግ ጥቂት ስለነበረ አሉላ የሰራው የውግያ አስተዋጽኦ ጎልቶ የሚታይ አልነበረም። ኢሚንት ነው። በማለት መስክሯል። በዚህ ክርክር ከገባን “ከራስ መንገሻ (አሉላ) ሸራዊቶች” ይልቅ ከሌሎች ኢትዮጵያ መንደሮች የመጣ በተለይም ከሸዋ በብዛት የተሳተፈ ሠራዊት ስለነበር፤ የዓድዋ ድል ‘የሸዋ ሠራት ድል’ መሆን አለበት ሊባል ነው ማለት ነው?”
ዋናው የውሸት ቀፎ የሆነው የ ‘ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ’ ድርጅት፤ በድርጅቱ ሁለተኛ ጉባኤ (1975) ያጸደቀው ውሳኔ አንዲህ ይላል “በአገራችን የሰሜን ጦርነቶች በዶጋሊ፤ጉንደት፤ጉራዕ… የተካሄዱ ጦረነቶችና ድሎች የኤርትራ ሕዝቦች እና የትግራይ ሕዝቦች ድል ነው”። ሲል በ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በእነ አምደጽዮን (ከሸዋ እየገሰገሱ) እና በመሳሰሉት የድሮ ነገሥታት ከሩቅ ያገሪቱ ግዛቶች እየተወረወሩ ወደ “ሓማሴን ምድር ወይንም ወደ ባሕረ ምድር” (ኤርትራ) በመሄድ ከቱርኮች እና ከመሳሰሉ ወራሪዎች ተዋግተው ጠላት ድል የመቱትን ሁሉ በመደበቅ፤በአካባቢው የተደረጉ ጦርነቶች የትግሬ ጀግኖች ውጤት እያሉ ሚዛን ያጣ ትምክሕት በማሰራጨት አዲሱን የትግራይ ትውልድም ያንን ውሸት እየተቀበለ በዛው ትምክሕት እየተወጠረ መራመድ ጀምሯል።
አሁን ወደ መረጃዬ ልሂድ።
«----ዘመናዊ የካራቢነር ጠመንጃና መድፍ የጨበጠው የግብፅ ጦር ወደትግራይ አምርቶ የመረብን ወንዝ ተሻገረ።በኅዳር 7 ቀን 1875 ከዚህ ወንዝ አጠገብ ጉንደት ከተባለች ሥፍራ ላይ በንጉሠነገሥት ዮሐንስ 4ኛ የተመራ  የኢትዮጵያ ሠራዊት መንገድ ዘጋበት።ንጉሡ ሠራዊቱን በሁለት ከፍሎ ፤ አንዱን ክፍል ራሱ፤ ሁለተኛውን ክፍል በዚያን ጊዜ የተመሰከረለት ጀግና የነበረው ራስ አሉላ እንዲመራው አደረገ። ሁለቱም የኢትዮጵያ ክፍለ ጦር ከተለያየ አቅጣጫ ደወ ግብፁ ምሽግ ተንቀሳቀሱ። የጉንደት ጦርነት ሙሉ ቀን ፈጀ። ከምሽቱ ላይ ድሉ ለኢትዮጵያውያን ማድላቱ እየለየ መጣ። አብዛኛቹ በጀግንነት የተዋጉ ግብፃውያን ከትግሉ አውድማ ላይ የወደቁ  ሲሆን፣ከነዚህም ውስጥ አራኪል ቤይ እና ሻምበል አረንድሩፕ ያገኛሉ። ከፊሉ ተማረከ፣ አምልጦ ምፅዋ  ሊገባ የቻለው በጣም ጥቂት ነው።
« ከዚህ ውድቀትም በኋላ ከዲቭ እስማኤል በኢትዮጵያ ላይ ቀጣዩን ዘመቻ ለመክፈት ዝግጅት ማድረግ ጀመረ። ለቀጣዩ ጦርነት ካሁኑ የበለጠና የተሻለ ትጥቅ ያለው ሠራዊት ለማዝመት ወሰነ። ላሁኑ ዘመቻ 20,000 ወታደር አዘጋጅቶ  በእጁ የሚገኘውን የተሻለ መሣሪያ ሁሉ አስታጠቀው። እስማኤል ለአዲሱ ዘመቻ በጀርመን አገር በወታደራዊ ሥልጠና የተመረቀውን መኮንን ሙላይ ሐሰን ፓሻን  አዛዥ አድርጎ ሾመው። ከሱም ጋር ሌሎች የግብፅ የጦር መሪዎች አብረውት የዘመቱ ሲሆን፣ ከነዚህም አንዱ ዝነኛው ራቲብ ፓሻ ነበር። በታኅሣሥ ወር 1875 የከዲቩ ጦር ምፅዋ ላይ አርፎ በዝግታ ወደ ማህል ኢትዮጵያ መንቀሳቀስ ጀመረ። በየካቲት 1876 ከመረብ ወንዝ ተጠጋ።
« ለዚህ የግብፅ ወረራ ምላሽ ዮሐንስ 4ኛ በሞሐመዳውያን ላይ ``የመስቀል ዘመቻ`` አዋጅ አስነገረ። ንጉሡ ከጎጃምና ከሸዋ የማጠናከሪያ ኃይል እንዲመጣ አድርጎ ፣ጠቅላላው የሠራዊቱ ቁጥር 60,000 ደርሶ ነበር። ሁለቱ ሠራዊቶች በመጋቢት ወር 1876 ጉራዕ ላይ ተጋጠሙ። ግብፆች ምሽጋቸውን ዙሪያውን በጉድብ ሰንሰለት ስላጠሩት የኢትዮጵያውያኑን ጥቃት ለመከላከል አመችቷቸው ነበር። ከግጥሚያው መጀመሪያ ላይ ስለቀናው ተደፋፍሮ ሙላይ ሐሰን በልምድ የበሰለውና ሽማግሌው ወታደር ራቲቭ ፓሻ ተው እያለው ጠላቱን በግላጭ ገጥሞ እደመስሳለሁ ብሎ ከምሽጉ ወጣ። ይህ ውሳኔ ለግብፆች መጥፊያቸው ሆነ። የኢትዮጵያ ወታደር በቁጥሩ ከወራሪው ጦር እጅግ ከፍ ያለ ነበርና  የውጊያውን ሰልፍ ጥሶ እየተወረወረ ከጠላቱ ምሽግ ውስጥ ገባ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጊያው ወደ መተላለቅ ተለውጦ የግብፅ ጦር በድንጋጤ ተውጦ ፈረጠጠ። ሙላይ ሐሰን ፓሻ ሩጦ ለማምለጥ ሲሞክር ተይዞ ከንጉሡ ፊት ቀረበ። ንጉሡም ድል የሆነበትን ቀን እንዳይረሳው ሲል ከክንዱ ላይ ሁለት መስቀል እንዲተኮስበት አደረገ። በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል የሰላም ውል ከተደረገ በኋላ ከዲቭ እስማኤል ፣ ሙላይ ሐሰን ፓሻና ሌሎችም በጉራይ ጦርነት ላይ ከሱ ጋር የተማረኩትን ከፍተኛ መኮንኖች ማስለቀቂያ ከፍሎ አስፈታቸው።»
(ገጽ 289 እስከ 299፣“የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን፣ጸሐፊዎች፦ አንድርዜይ ባርትኒስኪ እና ዮዓና ምንቴል-ኒየችኮ” ተርጓሚ፦ ዓለማየሁ አበበ 2003)
ስለሆነም በጉራዕ፤በጉንደት፤በስዋኪን፤በዶጋሊ፤በዓድዋ፤በማይጨው፤መመሳሰሉት ጦርነቶች እና በቅርቡም የትግሬው ወያኔ እና የኤርትራው ሻዕቢያ በጫሩት 70,000 የሚገመት ተጠያቂ የሌለው ሕይወት የበላ የጥላቻ ጦርነት ከሁሉም ወይንም ከከፊል የኢትዮጵያ ግዛቶች የሚኖር ሕዝብ የተካፈለበት ጦርነት ነበር። ወያኔዎች በሁለተኛ ጉባኤያቸው የኛ የትግሬዎች ገድል ብቻ ነው ብለው ያሉት በውሸት የተመሰረተ “የትግራይ ጦር ብቻ” የተሳተፈበት ጀግንነት ያሉትን ውሸትም ሆነ፤ የወያኔ ታሪክ ጸሐፊዎች ነን የሚሉን ትምክሕተኞቹ  የትግሬ ብሔረተኞች በመጽሐፍቶቻቸው የሚዋሹት እና የሚመኩባቸው የተጠቀሱት የትግሬ ጦር ውሎ ጀብዱ ሁሉ የትግሬ ብቻ ሳይሆን ጦሩ በዚያን ዘመን ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቀው አገር ይኖሩ የነበሩ ዜጎች በጦርነቱ ተካፋይ እንደነበሩ ከላይ ለመከራከሪያ ያቀረብኩት የመረጃ ሰነድ ማለትም “የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን፣ጸሐፊዎች፦ አንድርዜይ ባርትኒስኪ እና ዮዓና ምንቴል-ኒየችኮ” ተርጓሚ፦ ዓለማየሁ አበበ 2003 ያስረዳል።
የትግሬዎች እና የተጠቀሱት የአካባቢ ተሳታፊዎች የቁጥር ልዩነት ይችላል ወይ? አዎ ምናልባት ሊኖረው ይችላል። ያም በእርግጠኝነት ይህ ነው ማለት ባይቻልም ካራት ወይንም ከሦሰት ክ/ሃገራት የተውጣጡ ተዋጊዎች በቁጥር አነስተኛ ማሕበረሰብ ከነበረው ከትግራይ ጦር ሲነጻጻር ሊበዛ ወይንም እኩል ሊሆንም ይችልም ይሆናል። የጉራዕ/ጉንደት ጦርነት ግን ከጎጃምና ከሸዋ በብዛት የዘመተ መኖሩን በግልጽ ያሳያል። ጎንደርና ወሎ ያልተጠቀሱበት ምክንያት ሁለቱም በንጉሡ ቀጥተኛ ቁጥጥር ሥር የነበሩ በመሆኑ ተሳትፎአቸው ግልጽ ስለሆነ ነው።
አሁን መረጃው ሰጥቻለሁ። የወያኔ ትግሬ ጸሐፍት ጉረኞች በየመጽሕፍቶቻችሁ እና በየቃለ መጠይቃችሁ የምትነዙት አጉል ጉራ እና ታሪክ አደፍራሽነታችሁ ረገብ አንድትሉ በግራ ቀኝ የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች አንብቡ። ለዚህም ነበር አፄ ዮሐንስ ‘የትግሬ ልጅ ሆይ” ሳይሆን ሲሉ የነበሩት ለጦርነት ሲዘጋጁ “የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ” ነበር እያሉ መላውን ግዛታቸው ያለው ሕዝብ ለጦርነት ጥሪ ሲያደርጉ የነበሩት።  ለዚህም ነበር  የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት። ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ ናት፣ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፣ ሦስተኛ ሚስትህ ናት፣ አራተኛ ልጅህ ናት፣ አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሣ።“(አፄ ዮሐንስ ፬ኛ) ሲሉ የነበሩት።

ወያኔዎች የትግራይ ወያኔ ብሄረተኞች ከንጉሥ ዮሐንስ “የኢትዮጵያዊነት” ትርጉም ምን ማለት አንደሆነ ሊማሩት አልፈቀዱም። አለማፈራቸው ዛሬ ደግሞ ይባስ ብለው “ማንነት” ትግራዋይነት አንጂ “ኢትዮጵያ” የሚባል ማንነት የለንም መላት ጀምረዋል። ንጉሥ ዮሐንስ እያሉን ያሉት ግን “ኢትዮጵያ ማንነትህ ናት”  -ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ ናት፣ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፣ ሦስተኛ ሚስትህ ናት፣ አራተኛ ልጅህ ናት፣ አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሣ።” ሲሉ በወርቃማው ‘ኢትጵያዊ ማነንት’ ትርጉማቸው ተርጉመውልን ቢሄዱም “የወያኔ ባንዳዎች” ወደ ቁልቁል ወደ መንደራቸው በመሸማቀቅ “ትግራዋይነት” አንጂ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንንት የለም፤ በማለት ወደ “ትግሬነት” ወደ “ኤርትራዊነት” ማንነት ወደ እሚሉት ደደቢታዊ እና ናቕፋዊ የግንጠላ አዝማሚያ እና መንደርተኛነትን አጥብቀው ማማንዠክ ይዘዋል።

 የትግራይ ኦን ላይን ውሸታሞች በአማራ ሕብረተሰብ እና አርበኞች ላይ ያላቸው የጥላቻ መንፈስ ከኤርትራዊያኖቹ የባሰ ጥልቅ እንደሆነ ልብ ያለው በበሰለ ሕሊና የተከታተላቸው ታዛቢ የሚመሰክረው ቢሆንም ዛሬም ከሃያ ሁለት አመት በሓላም ጥላቸው እና ትንኰሳው ስላልበረደላቸው፤ በትግሬው አሉላ እና በአማራው በላይ ዘለቀ (አማራ እና ትግሬ የሚለው በሽታቸው ሲያወዳድሩ) መካከል ልዩነት ፈጥረው “አማራዎች” የአሉላን ክብር እንድያንስ አድርገዋል፡ እያሉ የአማራ ጸሐፊዎችን የሚከስሱት ውሸት እራሳቸው በራስ አሉላ ላይ እያደረጉት ያሉት ደባ እንዳይጋለጥ የሚያደርጉት ተንኰል ነው። የሚከተለውን ጉድ አንብቡ፤

 

“Tigrai Rep. officially disowns the indomitable lion of Dogali, Ras Alulaበሚል ርዕስ ወንድማችን ጌታሁን በቀለ የዘገበውን እንመልከት።
 
The Horn Times Newsletter, Dec 2, 2012
By Getahune Bekele
“ The great Abyssinian chief Ras Alula is at present a person of much interest to the Italians, and the Reforma is publishing a sketch of his life, in the course of which it is stated that he is the son of Abyssinian peasants.”
The Paul mall Gazette, April 12, 1887
“Ras Alula developed great military skill, and for many years was regarded as one of the greatest Abyssinian Generals.”
The New York Times, Feb 27, 1879
Eritrean born top TPLF warlord Bereket Simeon is currently on a new mission alongside another anti-Ethiopian hireling Sibehat Nega, an Ignoramus who regards Ethiopia’s rich history as an offence that should be erased.
Few days after the ruling minority junta announced the pending removal of statues of martyred bishop Abune Petros and emperor Menilik, Tigraye republic officially disowned her own anti- colonial war hero, Ras Alula Engida by removing the obelisk which commemorates the battle of Dogali from the only school named after him in his home province of Tigraye, Tembein zone of Abi-Adie town.
According to the Horn Times Tigrai zone reporters, the up graded and modernized high school was renamed “Meles Zenawi comprehensive high school” on November 21, 2012.
Speaking at the ceremony, TPLF cc member commander Yetbarek Aleneh told the visibly unhappy crowd that “ those who call  themselves opposition parties  must worship Ras Alula in Addis Ababa or Asmara…or even in Washington Dc, where they live as fugitives…not here in Tigraye. We have created a new Tigrai with the blood of our children, not with Alula’s blood.”
However, after the ceremony, a miner scuffle broke out between armed TPLF security personnel and the residents of Abi-Adie town who strongly objected to the name change and threatened to burn down the school. Several arrests were made  near the town of Mekele, the capital of Tigrai and became a household name when he ambushed an Italian battalion of 500 men, led by Colonel Tommaso De Cristofori, in Dogali near the port city of Massawa, present day Eritrea, on 26 January 1887 and killed almost all the invaders in just few hours of fierce battle.
His huge statue topped with a red star was erected in Dogali during the communist rule in Ethiopia and January 26 used to be a national holy day before TPLF came to power in May 1991.
Nevertheless, Ras Alulas’ monument was blasted by EPLF, Eritrean People’s Liberation Front (shabia) commander Petros Solomon in 1989 in the presence of the late fuehrer Meles Zenaw’s father, Ato Zenawi Asres, a traitor who fought alongside the Italians during the second Italo-Abyssinian war.
To the 500 Italians killed by the patriots, the massive monument erected in their honor is still standing in Rome’s famous Piazza Dei Cinquecento while TPLF warlords, who descended from families of traitors, try to destroy Ethiopia’s own war memorials.
Furthermore, despite the juntas vile attempt to eradicate history, in the pristine smoggy ravines of the north, the golden belt of Ethiopian patriotism, shepherds are singing about the heroics of this gallant soul called Ras Alula Aba-Nega…as they did for generations…”  (ጌታሁን በቀለ The Horn Times Newsletter, Dec 2, 2012)
ይህ ጉድ ተሸክመው ነው ሌላወን እየከሰሱ ለወንጀላቸው ሽፋን ለማድረግ የሚጥሩት። ከላይ አንደተመለከቱት፤ ተምቤን አውራጃ ውስጥ በራስ አሉላ የተሰየመውን ት/ቤት በወያኔው መሪ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲጠራ የተደረገው ሴራ ነው። ዶጋሊ ላይ ደርግ ለክብራቸው ያስሰራው የመታሰቢያ ሃውልትም በሻዕቢያዎች ሲፈርስ ወያኔዎች ምንም የተቃውሞ ቃል አላቀረቡም፤ ሲናገሩም ተደምጠው አይታወቁም። ይባስ ብለው ታሪካቸው እና ስማቸው እየደመሰሱ የራሳቸውን ወንጀል ለሌላ መለጠፋቸው እጅግ የሚገርሙ ጎዶች ናቸው።
ከዚህ በታች የማቀርብላችሁ ፎቶግራፍ፤ ዶጋሊ ላይ (ምፅዋ አጠገብ) ለራስ አሉላ መታሰቢያ ሃውልት የደርግ መንግሥት ያስሰራው የጀግኖች ሃውልት ሻዕቢያዎች ካፈረሱት በሗላ ሲሆን (ሃውልቱ በቦምብ ጋይቶ ወደ ሜዳነት ተለውጦ የጣሊያን እና የሻዕቢያ ሰራዊቶች የየራሳቸው ሰንደቃላማ ባንድነት እየሰቀሉ ኤርትራ ባንዳዎች አብረው ከጣሊያኖች ጋር ሲዋጉ አሉላ ስለደመሰሳቸው የክብር መዘክር አብረው ሲዘክሩ ነው (በጣም አሳፋሪዎች!!)  ፎቶግራፉም ይኼው። በትልቁ ለማየት ስትፈልጉ ማጉልያውን ተጠቀሙ።
ከዚህ በታች የሚታየው ፎቶግራፍ ደግሞ የደርግ መንግሥት ያሰሰራውን የአሉላ ሃውልት አፍርሰው የጣሊያን እና የባንዳዎቻቸውን መታሰቢያ አንደገና አሰርተው የተከሉት አዲስ ሃውልት ነው።
ከዚህ በታች የምጠቅሳቸው የወያኔ ታሪክ ጸሐፍት ለአማራ ያላቸው ጥላቻ ብርቱ ሲሆን ታሪክንም እያዛቡ የዘገቡ የወያኔ ካድሬዎች ናቸው።
ዶ/ር (መምህር) ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም
የምታዩት ፎቶ ዶ/ር (መምህር) ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ነው። የትምህርት ቤት ጓደኛዬ የነበረ ነው። በዕድሜ ይበልጠኛል። አክሱማዊው ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ድሮ የኢሕአፓ ታጋይ የነበረ ነው። አሁን ጭልጥ ብሎ ወደ ጎሰኞቹ ወደ ወያኔዎች በመግባት ቀንደኛ ገጣሚ እና የውሸት አሳማሪ የታረክ ምሁር ሆኗል።
 
ከላይ የሚታው ሙሉወርቅ ኪደነማርያም ነው። የሚኖረውም ትግራይ ውስጥ  ነው። ሙሉወርቅ እንዲህ ያለ ጎሰኛ ይወጣዋል ብዬ ገምቼም አለውቅም። ደህና የነበሩ ወጣቶች ስያድጉ ምን መርዝ ቀምሰው በጎሰኛነት ልክፍት አንደሚያብዱ አላውቅም። ዛሬ ወያኔዎች ከሚመኩባቸው በርከት ያሉ ውሸታሞች መካካል ምናልባትም ሟቹ ደ/ር ክንፈ አብርሃምን የተካ የታሪክ ምሁር በመሆን፤ በንጉሥ ምኒሊክ እና በአማራ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የሚያስተጋባ ጎሰኛ በመሆን ተዋጥቶለታል። ሙሉወርቅ መቀሌ ውስጥ የሚገኘው “Queen Sheba” ኮለጅ ዲን ነው። (ፋሺስቶቹ ኩዊን ሸባ/ የሚለው አንግሊዝኛ ቋንቋ ‘ንግሥት’ የሚለው ‘አማርኛ’ ወይንም ‘ንግሥቲ’ የሚለው ‘ትግርኛ’ ስላስጠላቸው ቋንቋችን ተነጠቅን ብለው በረሃ ገብተው ሲዋሹ ዛሬ የባስ ብለው ትግርኛውንም ጭምር በእንግሊዘኛ ተኩት። አሳፋሪ ትውልድ!)


ገብረኪዳን ደስታ “እምቢ አንጻር ወረርቲ” (በወራሪዎች ላይ እምቢታ) ብሎ በጻፈው ምጽሐፍ ፈላጭ ቆራጭ በነበሩት ግፈኞቹ “የትግራይ መሳፍንት እና የጉልተኞች ዲሞክራሲ” ድንቅነት እና በጐነት ለማሳየት እና ለማስተዋወቅ በተጻፈው የውሸት ክምር ተመርኩዞ “ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም” አስተያየቱን አንዲሰጥ ተጠይቆ፤ ስለ አፄ ዮሐንስ እና ስለ ምኒሊክ፤ ስለ ‘አማራ’ ጻሀፊዎች ብዙ ዘላብዷል።   


አስቀድሜ አንደተናገርኩት ሙሉወርቅ ጎሰኛ እና አማራ የሚጠላ መሆኑን እኔን ለመቀበል የሚያዳግታቸው ሰዎች ስላሉ በሌላ ሰው አንደበት መረጃየን ላቅርብ። አብርሃ ደስታ ይባላል። አብዛኞዎቻችሁ ይህ ወጣት በመጥፎም በደግም ጽሑፉ የምታውቁት ነው። የጻፈ ሁሉ ደራሲ ነው? በሚል ርዕስ መጣጥፉ ስለ ሙሉወረቅ ኪዳነ መርያም  እንዲህ ይላል።

አዲስ አበባዎች ሰለማዊ ሰልፉ ሲቀውጡት እኔ ደግሞ ከጓደኞቼ ጋር ... የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በመቐለ ከተማ ቅርንጫፍ ስለመክፈቱ ተጋብዘን እየተነጋገርን ነበር። የአዲስ አበባ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁ ደስ ብሎኛል።

እኔ ግን ስለ ማህበሩ ዉሎ ትንሽ ላካፍላቹ። ምክንያቱም ካደረግነው ዉይይት አንድ 'ደስ የሚል' ነገር ስላገኘሁ ነው። የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር በመቐለ ቅርንጫፍ የሚከፍትበት ዝግጅት ጥሩ ነበር። ብዙ ሙሁራን ደራሲያን ታድመው ንግግር አድርገዋል።

ግን በደራሲያኑና በሙሁራኑ ንግግር ቅር ያሰኘኝ ነገር ነበረ። ከክብር እንግዶቹ ሁሌ 'ሊቃውንት' ተብለው የሚቀርቡ / ሰለሞን ዕንቋይ፣ መምህር ገብረኪዳን ደስታና መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ነበሩ። ከኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር የተላኩ አራት ደራሲያንም ነበሩ። ንግግር አድርገዋል።

ከኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር የተወከሉ አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው ግን ትግርኛም ይሰማሉ። የአብዛኞቹ ንግግር አልተመቸኝም። ሲበዛ ግብዝ ነበሩ። የሚናገሩት የልባቸው እንዳልሆነ በቀላሉ መገመት ይቻላል። ጥረታቸው ለግዜው እኛ የትግራይ ተወላጆችን ማስደሰት ነበር። በትክክል ግን ማስደሰት ሳይሆን መመፃደቅ ነበር። ትግራይ ሰማይ ሰቀሏት። ከነሱ አንድ ግን ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጠና አስደሰተኝ። ሌሎቹ ግን 'የእውነት ደራሲያን ናቸው?' ብዬ ራሴ እንድጠይቅ አድርገውኛል። ግብዝ ደራሲ አልወድም።
የኛዎቹም ተናገሩ። / ሰለሞን ብዙ አላባላሹም። አጠር ያለ ግሩም አስተያየት ሰጡ። መምህር ሙሉወርቅ ለመጀመርያ ግዜ (እኔ እስከሰማሁት ድረስ) 'አማርኛ ማወቅ ጥሩ ነው' ብሎ ተናገረ። ገረመኝ፤ አናደደኝም። ግብዝ መሆኑ ነው። 'አማርኛ ተናጋሪዎች ከመሃከላችን ስላሉና እነሱ ለማስደሰት ስለፈለገ ነው?' ብዬ ታዘብኩት፤ ምክንያቱም አቋሙ ከዚህ በፊት አውቀዋለሁ። ትንሽ ቆይቶ ግን ወደ ተለመደው የፖለቲካ መዘባረቁ ገባ። ተረጋጋሁ። ምክንያቱም ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተመልሷል። እንደወትሮው ለሸዋ ታሪክ ፀሃፊዎች መውቀስ ጀመረ። »
 እኔ ደግሞ ግራ ሲገባኝ 'ሁሉም ፀሓፊ ደራሲ ነው እንዴ? ለምንድነው የታሪክ ተመራማሪዎች እንደ ደራሲያን አድርገን የምንቆጥራቸው? ድርሰት ጥበብ ነው፣ መፃፍ መቻል ግን ክህሎት ነው።' ብዬ ጠየቅኩ። (የጻፈ ሁሉ ደራሲ ነው? አብርሃ ደስታ)
ከላይ በአበርሃ ደስታ አንደተገለጸው ሙሉ ወርቅ ኪዳነማርያም ማለት ይህ ነው።
ሙሉወርቅ የዚህ ትምክህተኛ ቡድን አገልጋይ ሆኖ ሳዳምጥ በጣም ነው የገረመኝ። ዮሐንስ አዳራሽ መኝታ ክፍላቸው ውስጥ በተደረገው የገብረኪዳን ደስታ መጽሐፍ ድጋፍ አንደለፈፈው ትግሬዎች በብዙ የታሪክ ሰነዶች ድሮም ይሁን አሁን እንኳ በቅርቡ በባድሜ ጦርነትም ይሁን በዓድዋ፤በማይጨው ጦረነቶች ሁሉ ትግሬዎች ባካባቢያቸው የተከሰቱ ጦርነቶች ብቻቸውን አልገጠሙዋቸውም። እንኳን እና ድሮ በርሃብ፤በተላላፊ በሽታ፤በወባ፤ እና ባስቸጋሪ ክረምት የሰው ሃይል እና የስንቅ ምንጭ በሚያስፈልግበት ወቅት ብቻቸውን ሊዋጉ ቀርቶ፤ አሁን ሁሉም በእጃቸው ባደረጉበት ጦሩም ፤ሃብቱም፤ስልጣኑም፤ አይሮፕላኑም፤መድሃኒቱም፤ፋብሪካው እና ማጓጓዣው በቁጥጥራቸው ባደረጉበት ወቅት አንኳ ‘ሻዕቢያን’ ከባድመ፤ከዓሊተና፤ከዛላምበሳ.፤ከባዳ…. መግፋት አቅቷቸው ለሁለት ዓመት የትግራይ ድንበር ተወርሮ፤ ያካባቢው ድምበር ኗሪዎቹ ተፈናቅለው፤ መኖርያ ቤቶቻቸው  እየተቃጠሉ ፤ኗሪዎች እየተገረፉ እና እየተጠለፉ፤ ጫካው እየተመነጠረ፤ ድንጋዩ እየተፈነቀለ “የሻዕቢያ”  ምሽግ ማጠናከሪያ ሆኖ ሁለት አመት ሲቆይ “እርዱን” ተብሎ ነው የድሮ ሰራዊት ሳይቀር እየተለመነ ተመልሶ በመታጠቅ ‘ሻዕቢያን” ድባቅ የመታው እና እስከ ባረንቱ፤ተሰነይ እና ሰንዓፈ ገብቶ ያራወጠው። ይህ የዓምና ታሪክ ነው፡ አንዴት ልንረሳው አንችላለን?  ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ፡እነ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም “በሰሜን የተደረጉ ጦርነቶች በሙሉ በትግሬዎች የተካሄደ የትግሬዎች ጀግንነት ነው እያለ ሕዝቡን በጀብደኝነት ሲያሰክሩ ማድመጥ እህግ አስገራሚ ክሰተት ነው። አለማፈር!
አታኽለቲ ሓጎስ
በትግርኛ እንዲህ ይላል። “ተጋሩ  ንኢትዮያ መዋእቲ  ዝኾ ኑንን ዘድ ንዋን እየ ገይ ረ ዝ ወ ስዳ። (ትግሬዎች ኢትዮጵያን ለማዳን ቤዛ የሆኑ ናቸው)።(ቃለ መጠይቅ - ውራይ መጽሄት)
አታኽልቲ ሐጎስ ማለት ‘ሃቅ ሃቁን ለህጻናት’ እና “ደቂቀ ምኒሊክ፤ አይንታሓማመ” እና የመሳሰሉ ጎሰኛ እና ዘረኛ መጽሐፍ የጻፈ የወያኔ ደራሲና ገጣሚ እንዲሁም ሰዓሊ ነው።” እሱም አብሮ አደጌ ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ ትግሬዎች (ወያኔን አይጨምርም) በማንኛወም ውግያ ሲሳተፉ በኢትዮጵያዊነታቸው እንጂ “ኢትዮጵያ የተባለች አገራቸው ከጠላት ለመከላከል ቤዛ የሆኑ አንጂ ‘ኢትዮጵያ የተባለች ባዕድ አገር’ ለማዳን የተሰው አይደሉም። የወያኔ ደራሲያን ችግር፤ “ትግራይ እና ኢትዮጵያ” ለያይተው የማየት በሸታቸው የጠነከረ ስለሆነ ማንኛውም ጦርነት ሲካሄድ  “ኢትዮጵያ የምትባሉ ፍጡሮች ፈጣሪዎቻችሁም አዳኞቻችሁም እኛ ነን።” የሚል የትምክሕት አበዜ ሲያስተጋቡ ፣የስካራቸው ውሸት መጠን የለውም። ለዚህም ነው መላ ኢትዮጵያ እና መላው የኢትዮጵያ አካባቢ ሕዝብ የተካፈለበት የአክሱም ስልጣኔ የትግሬዎች ብቻ አድርገው በማጽፍ እና በመሳል በውሸት የሚስሉት፤፡ ይህንን የወያኔ ትግሬ ንብረትና ታሪክ አድርገው የሚያቀርቡት የሌሎችን አስተዋጽኦ እና ክብር የሚጋፋ አስጸያፊ ምሰል አንደናሙና ተመለክቱት።

መምህር ገብረኪዳን ደስታ
ሚኒልክ ወደ ትግራይ የመጣው  ትግሬ ከጠገበ እና አንድ ከሆነ አይገዛምወይም አይቻልምየሚል እምነት ነበረዉ። በተጨማሪም የትግራይ ህዝብብዙ ብርአለው፤ተብሎ ስለሚታመን ገበሬውንእየዘረፉሃብት ማካበትና ሕዝቡንማደሕየትም” “እንደ ስልትየተያዘ በመሆኑ አስፈላጊ ነበር። አጼ ምኒልክ ወደ ትግራይ ያደረጉት ዘመቻም እነዚህንሁለት ነጥቦችለማሳካትና ተግባራዊ ለማድረግ ነዉምመህር ገብረኪዳን ደስታ (የትግራይ ሕዝብ እና የትምክሕተኞች ሴራ ከትናንት አስከ ዛሬ ገጽ 103) ምንጭ “ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” ከሚል መጽሐፍ፤- ደራሲ ጌታቸው ረዳ።

ይህ ፎቶግራፍ ወደ ግራ በኩል የሚታየው ሽማግሌው መምህር ገብረኪዳን ደስታ ነው። ወደ ቀኝ በኩል ያለው ወጣት “ዮሃንስ” (ጆን እያሉ ወያኔዎች የሚጠሩት) የተባለው የትግራይ ሰው ለወያኔ የቆመ ጋዜጠኛ  ነው።


መቸም ሕሊና ላለው ሰው ምኒሊክ ወደ ትግራይ መጥተው የትግራይን ሕዝብ ከጠላት ወረራ እንዲያድኑት የተማጸነው ማን አንደሆነ የታሪክ ሰነዶች ያነበባችሁ የምትስቱት አይደለም። ሚኒሊክ ወደ ትግራይ ዓድዋ የዘመቱት ገብረኪዳን ደስታ እና የገብረኪዳን አስተማሪዎች የነበሩ በሚኒለክ ዘመን የኖሩ እነ ደብተራ ፍስሃ አብየ እዝጊ አንደሚሉት “ምኒልክ ወደ ትግራይ ያደረጉት ዘመቻ እነዚህንሁለት ነጥቦችለማሳካትና ተግባራዊ ለማድረግ ነዉ” የሚለው ውንጀላ ምንኛ እውነትን የሚረግጥ ክህደት መሆኑን ብዙ ትንተና የሚያስፈልገው ስላልሆነ ለናንተ ፍረድ እተወዋለሁ። ምኒልክ ጥሪውን ተቀብለው ጣልያን ባይመቱት፤ እናቶቻችን ብዙ የጣሊያን ዲቃላ ባፈሩልን ነበር።እናት አያቶቻችን በሰላቶ ጎረምሶች በተደፈሩ ነበር። ወንድ አያቶቻችንም የጣሊያን ጀርዲን (ጋርደን) ውሃ አጠጪ እና ዘበኛ፤ ወይንም እንቁላል ጠባሽ በሆኑ ነበር። በኤርትራ የደረሰ ውርደት ሁሉ በትግራይ ማሕበረሰብ በደረሰ ነበር። እድሜ ለምኒሊክ አንዳንል፤ ወያኔዎች ያ ሁሉ ውለታ እረስተው ‘ምኒሊክ ለብር ዘረፋ እና ትግራይን አደህይቶ ለመግዛት” አንዲያመቸው ነው ወደ ትግራይ ዓድዋ የመጣው ማለት ከባድ ወንጀል ነው። የሚኒልክ ደግነት እና በጎ ስራ ሰሪነት አንዲሁም የትግሬ መኳንንት ጎርበጣ ባሕሪ እና አርስ በርስ መጠላለፍ እና መገዳደል ባሕሪ የዘመኑ ምሁር የነበሩት የትግሬው ተወላጅ “ነጋድራስ ገ/ሕይውት ባይከዳኝ ” ስለ ምኒሊክ የጻፉትን በጎነት እና መልካም ስራ ማንበብ ነው። አሳዛኙ ግን ነጋድራስ ስለ ምኒሊክ ደካማ ጎን የጻፉትን እያጐሉ ፤ስለ በጎ ምግባራቸው እና ለትግራይ እና ስለ ኢትዮጵያ ያደረጉት አስተዋፅኦ የጻፉላቸውን እየደበቁ ወያኔዎች የገብረህይወት ባይከዳኝን ብዕር ሲያበላሹ ማየት በጣም ያሳዝናል። በዚህ ላይ ሌላ ቀን እመለስበታለሁ።

እንደርታዊዉ ተወላጅ የወያኔው ዘፋኝ ኪዳነማርያም ረዳ
 ንአብነት ማይ ጨዉ ዓድዋ እንተዘከርና፤
ተምቤን ዓቢይ ዓዲ ሽረ እንዳባጉና፤
 ኩይናት ምስ ገበሩ እቶም ወለድና፤ ጸላኢ ደምሲሶም ታሪኽ ሓደጉልና።
 ጨቆንትና አምሓሩ ምስ ታሪኽ ፀሓፍቶም ንዓና ዓብሊሎም ታሪኽና ጎቢጦም አለዉ ይምክሑ ብደም ወለድና፤
ንቃለስ ተጋሩ ክንመልስ ቅያና
  ትርጉም፦ ሓቀኛ ታሪክ ተደብቆ አይቀርም ለምሳሌ የማይጨዉን፤ የዓድዋን፤የሽረእንዳባጉናን ታሪክ ስንመረምር ወራሪዎችን ድባቅ በምመታት ትግሬ ወላጆቻችን አኩሪ ታሪክ ትተዉልን አልፈዋል። ይሁን እንጂ፤አባቶቻችን ብብዙ ዓዉደ ዉግያዎች ደማቸዉን አፍስሰዉ ያስመዘገቡትን ታሪክ “(ጨቆንትና አምሓሩ ምስታሪኽ ፀሓፍቶም”) “ጨቋኞቻችን አማሮች እና ታሪክ ጸሃፊዎቻቸዉበአሁኑ ወቅት እየተኮፈሱበት ነዉ። ታሪካችንን ቀብረዉ በአባቶቻችን ደም/ታሪክ እየተመኩበት ናቸዉ እና የትግራይ ተወላጆች የሆንን በሙላ ታሪካችነን ለማሳደስ በፅናት መታገል አለብን!” ይል ነበር፤ ተደርሶ የተሰጠው በረሃ ላይ እያለ የወያኔ ሙዚቀኛ የነበረው ዘፋኝ ኪዳነ ማርያም ረዳ።  ምንጭ (ይድረስ ለጎጠኛው መምህር፤- ደራሲ ጌታቸው ረዳ።)
 ይህ እጅግ ወደ ታች የዘቀጠ ዘረኛነት እና ውሸት ሰፊ ትንተና የሚያስፈልገው አይመስለኝም። እያንዳንዱ አንባቢ በቀላሉ የሚፈርደው ነው። ሆኖም ወላጆቻችን በጦርነት የመሸሽ ታሪክ፤ ምንም ወንጀል፤ ምንም የባንዳ ስራ እንዳልተሳተፉ አድርጎ የሚያቀርብ ጀብደኝነት የአማራ አዋቂዎች አንደሚሉት “አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል…” ነው እና ይህንን ታሪክ አስኪ አብረን አንመልከት እና ፍርዱን ሰጥተን አንሰናበት።አቡነ ጴጥሮስ አገሬን እና ሃይማኖቴን ለፋሺስት ሕዝብ አጎንብሶ አንዲሰግድ አልፈቅድም ብለው፤የድለላ ገንዘብ እና ማዕረግ ይሰጠዎታል ቢባሉም “ግንባሬ ለጥየት” ብለው በአምላካቸው ጽናት ተሞርኩዘው መስዋዕት ሲሆኑ ወላጆቻችን ቀሳውስተ አክሱም እና ዓዲግራት እንዲሁም ዓድዋ… ዘምባባ እያውለበለቡ እንደክርስቶስ “ንሴብሖ” የሚለው ውደሳ እያስተጋቡ ለፋሺስቶች ሲሰግዱ ተመዝገቧል። ይህ የወላጆቻችን ታሪክስ ለማን ልንሰጠው ነው? አማራዎች በኛ ታሪክ እየኮሩ በባዶ ታሪካቸው እየፎረከሩ ነው እየተባለ በአማራ ላይ የተዘፈነው ዘፈን ነውር አይደለም ወይ? ታሪክ እንፍራ አንጂ! አማራዎች እና ትግሬዎች እኮ ያንድ እናት እና ልጅ ወንድማማቾች ናቸው። ከሁለቱም አብራኮች የወጣን ትግሬዎች እኮ ነን። አስኪ ይህንን ቪዲዮ/ፊልም ተመልከቱት እና ራሳችንን እንፈትሽ። ሁሉም ጎሳ የራሱ መጥፎ ታሪክ እና ደካመ ጎን አስመዝግቧል። አንዴት እኛ ትግሬዎች ብቻ ጀግንነት ብቻ የሰራን እንጂ ደካመ ጎን የለንም ብለን ሌላውነ ከዳተኛ እያልን በድርቅና አንከሳለን። ገብረኪዳን ደስታ በትግርኛው ቃለ ጠይቁ “ትግራዋይ እማ ነፀላኢኡ አይነብርከኽን/አይሰግድን፤ንጥልያን፤ ንድረቡሽ ተምበርኪኺ አይፈልጥን” ሲለን (ትርጉሙ “ትግሬ በታሪኩ ለጠላት ተምበርክኮ ፤ተጎንብሶ ሰግዶ አያውቅም። ለማንኛውም ጣሊያን ይሁን ድርቡሽ ሰግዶ እጁን ሰጥቶ በታሪካችን የታየበት የተመዘገበበት ወቅት ከቶ የለም!”  የተንበረከኩ የሰገዱ ሌሎች ናቸው። ሲለን ይህ ከዚህ በታች ያለው ፊልም እሰኪ ተመልከቱ እና የገብረኪዳን ውሸትና እውነት እናመሳክረው።
 Tigray (AGAME) Ethiopians WORSHIPING Italian Colonialist in
 Le bellezze di Axum, antica capitale etiopica.
La popolazione indigena offre i propri servigi alle truppe coloniali
Il Vicerè Graziani in visita a Adigrat e Decamerè
 በሚቀጥለው ክፍል 2 ጽሑፌ ገብረ ኪዳን ደስታ አጼ ዮሐንስ ትግራይ ውስጥ ከዓፋር ማሕበረሰብ የነበራቸው ግንኙነት በሰላም በመከባበር አንደነበረ በውሸት የገለጸው፤የተዛባ ታሪክ በሰፊው እተነትነዋለሁ። ሚኒልክ እና ቴዎድሮስ አንጂ ዮሐንስ በሃይል አላስገበሩም የሚለው ቅዠት፤ ከስሑል ሚካል ጀምሮ እስከ አጼ ዮሐንሰ ድረስ ከዓፋሮች ጋር የተደረገው ጦርነት፤ዝርፍያ የሴት ጥልፊያ (ዓፋሮች አንደሚከስሱት ከሆነ ንጉሱ ልጃቸው አርአያስላሴ የተወለደው ከሔርቶው የዓፋር ጎሳ መሪው ከ ‘ያኩሚ ሲረ ዓሊ’ ልጅ ከዴቶ ሲረ ዓሊ የተወለደው ልጅ አርአያስላሴ እናቱ ዴቶ አባቱ ደጃዝማች ካሳ (ዮሐንስ) በሽፍተነት ጊዜያቸው አንዴት በጉልበት አንደጠለፏት እና አርአያን አንዴት እንደወለዱት በዓፋሮች የተጻፈ ሙግት አቀርባለሁ። እንዲሁም በትግሬ ገዢዎች እና ዓፋር ባላባቶች የተደረገ ረዢም የደም መፋሰስ ውጊያ እስካሁን ድረስ መብረድ ለምን አንዳልቻለ እንመለከታለን። ወያኔዎች የራሳቸውን ነገሥታት ጛዳ እየደበቁ  የሌሎቹን ጎሳዎች ነገሥታት እና መሳፍንቶች ወንጀል ሲቦረቡሩ “አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል…….” ነውና ሳንወድ የራሳችንን ጉድ ቦርቡሬ ማሳየት ሃላፊነት ስላለብኝ፤ በሚቀጥለው ክፍል ሁለት አንመለከታለን።
ወያኔዎች የፋሺስት ሃዋርያዎች ናቸው!
 በመጨረሻም ወያኔ የፋሺስት ሐዋርያዎች/ደቀመዝሙሮች ናቸው ለምን ትላቸዋለህ;፡የወያኔ ስራ እና የሙሶሎኒ ስራ ይለያያል እያሉ ሲሞጉትኝ ለነበሩ ሰዎች በአንድ የማከብረው ውድ ወዳጄ የተላከልኝን ካነበበው መጽሐፍ አጭር መረጃ ላስነብባችሁ እና ልሰናበት። ከታች የምታዩት ሰነድ፤ንግግር፤ተግባር፤ፖሊሲ፤ትዕዛዝ እና ንገግር፤ መለስ ዜናዊ እና ግበረ አበሮቹ በኑሮ ምክንያት ከአማራ ቀዬአቸው ለቀው ወደ ደቡቡ አገራቸው በመጓዝ በሚኖሩ አማራዎች የወሰዱት እርምጃ ድሮ ሙሶሎኑ እና ረዳቶቹ የቀየሱት ፖሊሲ አንደነበረ እና ያ ስራ ወያኔዎች አንዴት ተግባራዊ አንዳደረጉት ለማነጻጸር ይረዳችሁ ዘንድ ይኼው አንብቡት። 
 
ወያኔዎች የፋሺስት ሙሶሎኒ ደቀ መዝሙሮች ናቸው የምንለውም ለዚህ ነው።


 በመጨረሻም - ልዩ ማሳሰቢያ
በዚህ አጋጣሚ ብዙ ሰዎች የሚከተሉት መጽሐፈት አንዳላነበብዋቸው ይነግሩኛል። ደቂቀ እስጢፋኖስ፤ ይድረስ ለጎጠኛው መምህር፤ የወያኔ ገበና ማሕደር እና በትግርኛ ሓይካማ የሚል መጽሐፍ ላላነበባችሁ ዜጎች በተመለከተው አድራሻ ጠይቆ ማግኘት ይቻላላል። በጣም የሚያሳዝነው ጉዳይ ወያኔዎች የውሸት ደራሲያኖቻቸው እስከ አሜሪካ ድረስ እያስመጡ ወጪውን ሁሉ እየሸፈኑ መጻሐፋቶቻቸውን በመግዛት በማሰራጨት ለመጪው ትውልድ አንዲሳሳትበት በከፍተኛ ደረጃ ሲንቀሳቀሱ፤ “ተቃዋሚ” ነን የምንል ማሕበረሰቦች ግን ደራሲዎች ጊዜአቸው ሰውተው ፈታኝ ሕሊና ታግለው የጻፉዋቸው መጽሐፍት ላለመግዛት ወይንም አንባቢ ላለማግኘት ብዙ ሲጥሩ አንብቤአለሁ። ጉዳቱ ለደራሲው የመንካት ሞራል እና ለወደፊቱም አንዳይጽፍ አንዳይታገል የሚገፋፋ ቢሆንም፤  በዋናነት ግን፤ መጪው ትውልድ የመታገያ ሰነድ አንዲያጣ ማድረግ መሆኑን ያወቁት አልመሰለኝም። የሽንፈታችን ብዛት ሳስበው መጠን የለውም።አመሰግናለሁ።ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)   getachre@aol.com  visit www.ethiopiansemay.blogspot.com ወይንም Ethiopian Semay ብላችሁ ጉገል ማድረግ ትችላላችሁ። አመሰግናለሁ።