Thursday, January 14, 2021

 


የፋሽዝም ማጠንጠኛ የሆነው የትግራይ  ብሄረተኛነት በትግራይ ተወላጆች መሃል ጉልህ የሆነ የስነልቦና ለውጥ አስከትሏል!

በዚህ ሰነድ ትግሬዎች በወልቃይት ጎንደሬዎች ላይ ምን ሲሉ ነበር? መልሱን ከታች ታዩታላችሁ።

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

4/20/2020 እንደገና 1/14/2021 ታትሞ የቀረበ

ይህ ጽሑፍ በመጽሐፌ ላይ የታተመ ሲሆን፤ ይህ ጥቅስ ከመጽሐፌ ጠቅሼ ለናንተው ላቀርብ የፈለግኩበት ምክንያት፤ በጣም ቅርብ የሆነ እና እንደ ወንድሜ ስቆጥረው የነበረው፤ አብሮኝ ወደ ስደትና ወደ አሜሪካም አብሮኝ የተሰደደው፤ብዙ ያሳለፍን የድሮ ወዳጄ እንኳን ለፋሲካው በዓል አደረሰህ ለማለት ደውሎልኝ ከዚያ ወደ ማይቀረው የወያኔና የአገራችን አሁን ያለው ሁኔታ አንስተን ስንወያይ ለበርካታ አመታት ስጠረጥረው የነበረውን አቋሙን በተጋጋለው ውይይታችን ላይ በድንገት ገንፍሎ ያወጣውን ጋሀድ የሆነውን  የወያኔ ፖሊሲ ድጋፉን እና ጸረ አጼ ምኒልክ መስመሩንከምላሱ ሳደምጥ፤ (ምንም እንኳ የተማረ ሰው ቢሆንም) የግንዛቤ እጥረት ሊኖረው የችል ይሆናል በሚል እሳቤበአገራችን የተጻፉ መጽሐፍቶችን እንደ ዋቢ ማስረጃ ላቀርብለት ስሞክር አማራዎች የጻፉትን ማንበብ ፍልጎት የለኝም!” በሚል  ከምላሱ አምልጦት ሳይሆን በተጋጋለው ውይይታችን በግሃድ የገለጸልኝ የብዙዎቹ ትግራይ ብሔረተኞችንነጸብራቃዊ ተመሳሳይነትዛሬም እንደገና ባልጠበቅኩት የቅርብ ወዳጄአብይ አሕመድ ለትግራይ በጀት ስለከለከለ እኔም የትግራይን መገንጠል እደግፋለሁ፤ ለትግራይ የማትሆን ኢትዮጵያ አመድ ሆና ትበታንሲለኝ፤ ይህንን የቆየውን ጽሑፌ ለማቅረብ ፈለግኩ።

 እኔም በንግግሩ በድንጋጤ ተሰምጬ እንዲህ ያለ የጫጨ አቋሙን በማድመጤ እኔም ግራይ ስትገነጠል፤ ባጀት ከኢትዮጵያ በማትፈልገዋ የበለጸገች በሪፓብሊኪትዋ ትግራይ መስራታችሁ ሰላም እስክትለኝ ድረስ ደህና ሰንብትተባብለን የበርካታ አመት ወዳጅነታችን በዚህ በመቋጨቱ፤ ብሐረተኛነት ምን ያህል አደገኛ በሽታ እንደሆነ ለመግለጽ ካሳተምኩት መጽሐፍ ልጥቀስና እናነተም ተማሩበት ይኼው።

የትግሬዎች ፖለቲካፋሺዝም እንደሆነ አምስተርዳም ኗሪ በሆነው በምሁሩ ዶክተር አሰፋ ነጋሽ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያዊ ምሁር ስለ የትግራይ ፋሺዝም እና ኦሮሞ ፖለቲከኞች ፋሺዝም መሆኑን በብቸኛው በወዳጄ ዶከተር አሰፋ ብቻ የቀረበ ሰነድ እና ከዚያም ብዙዎቹ እየተቀባበሉ የነቁበት የዶክተሩ ሰነድ እየተቀባበሉ ኢትዮጵያዊያን ምሁራኖች ተምረውበታል።

ብሔረተኛነት ማለት ደግሞ ሰብኣዊነትህን የሚነጥቅ ክፉ የመንፈስ በሽታ ነው።ፋሽዝም የተጋነነ የጀግንነትን ስሜት ያጠናክራልይላል ዶክተር አሰፋ ነጋሽ። የወያኔ ትግሬዎች ዘፈኖች የትግራውያንን ታላቅነት፤ ጀግንነት፤ የልዩ ታሪክ ባለቤትነት፤ የሴቶቻቸውን ማህጸን ቅድስናና የጀግና ልጆች ፈጣሪነት እንደዚሁም የታጋይ ገብሩ አስራት ሚስት የውብማር አስፋው በጻፈቺውእስፈንክስዋም ሞታ ትነሳለችበሚል መጽሐፍዋ እንዳለችው የትግራዉያን የወያኔ የጽናት ተምሳሌትነት በኩራት ያዜማሉ። 

ፋሽዝም በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ባስከተለው የስነምግባር፤ የአመለካከት ለውጥ ምክንያት ስትመለከቱ፤ ለምሳሌ ያህል ከሰባት መቶ ሺህ በላይ (ይላል አንዳንድ ጥናት) የትግራይ ተወላጆች በኃይል ተከዜን ተሻግረው የወልቃይትን፤ የጸገዴን፤ የጠለምትን ወዘተ መሬት ሲነጥቁ በፋሽስት አመለካካት የተቀረጸው የዛሬው የትግራይ ትውልድ(ለምሳሌ የዓረናው እንደ እነአብርሃ ደስታእና የአክራሪው ወያኔ እንቁላል የሆነው የባይቶና በፋሺሰታዊ ስነ ልቦና የተቀረጸው ዓባይ ትግራይ መሪ ወጣት የሆነውክብሮም በርሀበማን አለብኝነት የሌላውን መሬት ነጥቆ በስግብግብነት ለትግሬነት ብቻ በማጠቃለል የመውሰዱን ድርጊት እንደ ሕገ ወጥና -ሞራላዊ ድርጊት አልይቆጥሩትም። እንዲያውም ይህንን ሕገወጥና ነውረኛ ድርጊት እንደ ጀግንነት ስራ ቆጥሮውት ይፎክርበታል። ለምሳሌ ወልቃይት ውስጥ ወያኔዎች ሕዝብ ሰብስበው ያስጨፈሩትን ይህንን ዘረኛ ሙዚቃ በዩቱብ አድምጡ የኔን ጽሑፍ ካነበቡ በሗላ ግን ትምክህተኛው ሙዚቃቸው ስላጋለጥኩባቸ ይህ ከታች ያለው የቪዲዮ አድራሻ ሆን ብለው ከዩቱብ አስነስተውታል።

https://www.youtube.com/watch?v=hScfnfaqLOY

  በዚህ ቪዴዩ ሙዚቃ ወልቃይት ውስጥ በብዙ ሺሕ ሕዝብ ሰብስበው የጨፈሩበት ይህ ቪዲዮከትግርኛ ወደ አማርኛልተርጉምላችሁ፡ ሁለቱ ዘፋኞች እየተቀባበሉ ያዜሙትን ፍሬ ነገር እንዲህ ይላል።ዛሬ እና ከጥቂት ወራት በፊት የነበረውን የወያኔዎች ተምክሕት እና ዛሬ በጦርነቱ ተሸንፈው በሚያሳፍርና በሚያሳዝን ሁኔታ እንዴት እንደተንበረከኩ ታይቷል። ለውርደታቸው መነሻ የሚከተለው ትምክሕት ነበር። እነሆ!

ጠላቶቻችን በቅናትምራቃቸው እንደ ራበው ውሻ   ያንጠባጥባሉ

እኛ አልፎልናል፤

ድል አድርገናል፤

ተደስተናል፤

እኛ  ያሰብነውን  ፈጽመናል፤

 ጠላቶቻችን ግን ፈዝዘው  ቀርተዋል/ይፍዘዙ!!  እያሉ ይዘፍናሉ፤ ይፎክራሉ።ሕዝቡም አብሮ በሙዚቃው ተውጦ ጦዟል፡

ደጋግሞም እንዲህ እያሉ ይዘፍናሉ--

ወልቃይት አገሬ እሷን ነበር የምመኛት፤

ዛሬ በጉልበቴ አገኘሗት

ትግራይ አገሬ

ውቢትዋ አገሬ

ጠላቶችሽ ፈዝዘው ይቅሩ፤

አንቺ ነሽ ሞራሌ፤

አንቺ ነሽ ወኔዬ፤ አንቺ ነሽ ክብሬ

የትግራይ ልጅ፤

የወያኔ ልጅ”’

በማንነቱ የማይደራደር፤

በማንነቱ የማይሳሳት….

በጥፍሩ ጥሮ ግሮ ሃብት የሚያፈራ

በጥፍሩ ጥረቱን አሳይቶ ባሸናፊነት የወጣ

የትግራይ ልጅ! ዘራፍ አለ በወልቃይት!

በደጀና በቃብቲያእሰይ ይበል የትግሬ ልጅ!

ባለ ድርብ ዋልታ።

እሷ ነበር ወልቃይት

በትግል  ወቅት የነበረች ስመኛት

አሁን አገኘሗት!

የምንመኛትን የኛዋ ወልቃይትን

ከቶ አንለቃትም

! በል የወያኔ ጎበዝ፤ እና የወያኔ ተከታይ ተረከዝ፤

ቦታ የለንም በላቸው ለትምክሕተኞች።

እሷን ለትምክሕተኞች አንለቅም።

ጣፋጭ ፍሬ የተሸከመውን

ያረገዘውን ዛፍ አንሰጥም።

 የወልቃይትን ለም መሬት ለትምክሕተኞች (ለአማራ) አንለቅም። አራስ ላማችንን፤

ፍሬ ያላት ዛፋችን

 ለትምክሕት አማራዎች አንለቅም።

 ለትምክህተኛ ኃይል አንሰጥም

 የሚለው ስንኝና ሙዚቃ የሚያመለክተን በአክራሪ ብሄረተኞች እየተገለጸ ያለው ፋሺስታዊ ልሳን ከላይ የጠየቀስኩትን በጸያፍ ቃላቶች የታጀበ የትግራውያን ፉከራ እንዲህ ይደመጥ ነበር።

የወልቃይት የጎንደር ተወላጆች ወልቃይትን ለማስመለስ ብዙ መስዋዕት ከፍለው ነበር። ፋሲስቱ አብይ አሕመድ ዛሬ የራሱን ፓርቲ ልኮ ወልቃይትና የራያ አካባቢ የትግራይ ነው ብሎ የአማራዎች ጽዋ አቆሽሾታል። የወልቃይት በጠቅላላ የጎንደሬዎች ተጋድሎ ከመንግሥት ታጣቂዎች እና ከወያኔ ታጣቂዎች እየተፋለሙ ያስመዘገቡት የቆየ ቪዲዮ እጋብዛችሗለሁ። መልካም ቆይታ።

ሰላም እንሰንብት

ጌታቸው ረዳ!!