The Amharic version of my commentary regarding the Eritrean oppositions. \
TPLF denied Eritrean Opposition’s request to open office in Ethiopia unless under the umbrella of ethnic organization. ወያኔ በጎሳ ለተደራጁ የሻዕቢያ ተቃዋሚ የኤርትራ ድርጅቶች ጽ/ቤት ሲፈቅድ በጎሳ አንደራጅም ላሉት ግን አልፈቅድም አለ-
ትችት ለኤርትራ የፖልቲካ ድርጅቶች
ጌታቸው ረዳ
www.Ethiopiansemay.blogspot.com
(ኢትዮጵያዊ) ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያ
The above photo from top -down 1- The TPLF man Ato Hubur G/Kidan,the Eritrean political oppositions guardian as director of the "Sanaa-Forum" in Addis Ababa. The next second photograph shows the 13Eeritrean Opposition groups to Isayas pose a Photo aportunity holding the symbol of the TPLF monument in MeKele presented to the group by TPLF Public relation. The third last photo is Ato Tewelde Gebreselassie the chair person to the 13 political groups known as "Kidan" (Alliance) adressing to the conference held in Tigray (Ethiopia).
ቀጥሎ የምታነብቡት ጸሁፍ ከሥስት ቀን በፊት በዚሁ ገጽ በትግርኛ ቀርቦ የነበረዉ የትግርናዉ ሐተታ ወደ አማርኛ ተርጉሜ አማርኛ ለምያነብቡ እንባቢዎች ባጭሩ የቀረበ ሀተታ ነዉ ።ከወደ መጨረሻም ወየኔ በጎሳ ካልተደራጃችሁ ወይንም በጎሳ ለተደራጁ የይሁንታ ቃል ካልሰጣችሁ ጽ/ቤት አይፈቀድላችሁም የተባሉት የኤርትራ ድርጅት ተቃዋሚ መሪዎች የተደረገ ቃለ መጠይቅ ተተርጎሞ ቀርቧል። አንዳንድ የትርጉም ወይንም የቃላት ግድፈቶች/ ስህተተቶች ቢታዩ ከካሊፎረኒያ ወባቂዉ አየር ጋር ትግል ተገጥሞ የተጻፈ ስለሆነ እያረሙ ያንብቡት። መልካም ንባብ።
ይድረስ ትችቴ ለ "ህደግኤ" ለኤርትራ ህዝብ ዲሞክራሲአዊ ግምባር (ኪዳን) { Alliance of Eritrean National Force}
- 1. ደሞክራስያዊ ውድብ ዓፋር ቀይሕ ባሕሪ 2. ግንባር ሃገራዊ ድሕነት ኤርትራ 3. ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ 4. ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ - ሰውራዊ ባይቶ 5. ህዝባዊ ደሞክራስያዊ ግንባር ኤርትራ 6. ደሞክራስያዊ ምንቅስቓስ ሓርነት ኩናማ ኤርትራ 7. ኤርትራዊ ህዝባዊ ምንቅስቓስ 8. ፈደራላዊ ደሞክራስያዊ ምንቅስቓስ ኤርትራ 9. እስላማዊ ሰልፊ ንልምዓትን ፍትሕን 10. ሰልፊ ደሞክራሲ ኤርትራ 11. ሰልፊ ናህዳ ኤርትራ 12. እስላማዊ ጉባኤ ኤርትራ 13. ህዝባዊ ጉባኤ ኤርትራ
ይህ የትችት ደብዳቤ ልልክላችሁ ያስገደደኝ ምክንያት በተለያዩ ወቅቶች በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝቦች መሀል ሊኖር የሚገቡ ግንኙነቶች ለህዝብ ያስተላለፏችሗቸዉ ድርጅታዊ አዋጆችና መግለጫዎች “እናንተ” በኤርትራ ሕዝብ ስም፤”ወያኔ” ደግሞ በትግራይ ሕዝብ ስም (ሲያሻዉም በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ይወስናል)፤ የምታከናዉንዋቸዉ ግንኙነቶች፤ በተለይም በመግለጫችሁ መሰረት የተረዳነዉ፤ ከወያነ እና “ከትግራይ ሕዝብ” (የናንተዉ ቃል ለመጠቀም) ጋር የቆየ ታሪካዊ የዝምድና ግንኘትንን አሳድሰነዋል: የምትሉትን ድርጅታዊ መግለጫችሁ ፤ትግራይንና ኤርትራን ህዝብ፤በድርጅትም በኩል ወያኔ እና እናንተን ብቻ ያቀፈ የተቀረውን የኢትዮጵያ ህዝብ፤ድርጅቶችና ምሁራኖች ግን የናቀ እና ያገለለ ሆኖ ስለተረዳሁት ፡ ይህ ጠባብ ግንኙት ካሁን በፊት ህዝባዊ ግምባር (ሻዕቢያ) ሲጛዝበት የነበረ የተሳሳተ አደገኛ ዝምድና እናንተም ዛሬ ያንኑ ስህተት በመድገም በተንሸዋረረዉ የፖለቲካ ዕይታ እየተጓዛችሁ ስለሆነ ፤ስህቱን ላለመድገም እንድንወያይበትና እንድታርሙት፤ ይረዳችሁ ዘንድ ከወዲሁ ለመጠቆም ነዉ።
በድርጅታዊ መግለጫችሁ በኩል በእንግሊዝኛዉና በዓረብኛ ቋንቋ ካሰራጫችሁት ልጥቀስ እና እንነጋገር።
ልጥቅስ። "...people of Tigray and Eritreaare also remarkably evidenced in other historical events. Indeed, those historical ties were translated to reality when the people of Tigray sent their sons and daughters to Sahil, Eritrea to fight side byside with their Eritrean brothers against the then occupying forces. The commitment, martyrdom, and heroic display of deki Tigray on behalf of Eritrean cause is vivid and historic. The same is true for Eritrean freedom fighters for their gallantry display and martyrdom inside Ethiopia sitting side by side with their Tigrayan comrades." (ዋሕታ/ኢታሊክ ናተይ) <>
ከነጻነታችሁ በፊት ምን ትሉን ነበር? “ኣድጊ፤ ኣምሓራይ” (እህያ ፤አማራ) በትዉልድ ቀያችን፤ በእምየ ኤርትራችን እንዳንኖር መብታችንን ረግጦ አገራችንን በቅኝ ግዛት ይዞ ለስደትና ለሞት ለመከራ ዳርጎናል። እህያዉ አማራን ከለምለሚቷ ከምድራችን አባርረን ጠራርገን ከአማራ ቅኝ ግዛትነት ነጻ ያወጣናት ለታ ግን፤በተድላ ካለምንም ሰቀቀን በነጻነት “በኮምብሽታቶ በአስመራ ጻዕዳ” በለምለምዋ ኤርትራችን እናንቧርቃለን፤ አንደንሳለን ፤አንንሸራሸርባታለን ትሉን ነበር። ህጻናትም ዋሾዉ ልሳናችሁ እየተከተሉ ያንኑ ዉሸት ይደግሙት ነበር። እየዘላበደ የዋሾዉ አንደበታችሁ በጣልያኑ በኮምብሽታና ጎዳና መደሰት፤መቧረቅና አስክስታ የማዉረዱ ቀርቶ ያንን ዉሸት እተመገቡ ያደጉት ህጻናት ሳይቀሩ ዛሬ ለሌላ ዙር ለከፋ ስደት መከራና ሞት ዳረጋችሗቸዉ።
ያችነን ነጻነት ስትሏት የነበራችሓትንም እንደ ጥዋት ፀሃይ ወጋገንዋ ታየ። በወያኔ እና በናንተዉ ጥርስ አኝካችሁ አድካመችሁ አልጠግብ ያላችሁትን ፤ዛሬም ከራሱ አልወርድም ያላችሁትን “አህያችሁ” በኮምብሽታቶ ፤በአስመራ ጻዕዳ” ለሽታም አይታይ። በምድሪቱ የለም! እንደተመኛችሁት፤ሰርጋችሁ (የጫጉላ ቤታችሁ) እና ሀዘናችሁ በዛዉ በኮምብሽታቶ በአስመራ ጻዕዳ ሳይሆን በ አምስተርዳም፤በለንደን፤በኒየርክ ባኦክላንድ በሞንትርያል ባሳዉዲ በእምዱርማን፤ በከሰላ ሆኗል። ታድያ “አልቦ-ሰዓት” ሰቀቀን 24 ሰዓት በነጻነት እንንሸራሸራለን እንደንሳለን ያላችዩትን ነጻነት ዘሬ ተመልሳችሁ “ከገዢዎቻችን ከአህዮቹ የባሰ ስርዓት መጣብን!” የሚለዉን መግለጫችሁ ስናነበብ “እንኳን ደስ አላችሁ!” አንዳንላችሁ ወልደን ተዋለደናልና አንደ እናንተዉ ለነገ ሳይባል ሁሉንም እርግፍ አድርጉ የሚዘከዝክ ጨካኝ ሆድ የለንምና “ብቻ…” የባሰ አያምጣ” እንላችሓለን።
እናንተ እንደ ፖለቲካ ተቃዋሚዎች መጠን በወያኔ ታግዛችሁ የኢሳያስን መንግስት ለማስወገድ የምታደርጉትን ጥረት ባይነ ቁራኛ እንከታተለዋለን። አሱን ለማስወገድ በምታደርጉት ጥረትም ተቃዎሞ የለንም። እኛን ያልጨመረ ፖለቲካ በመሆኑ ጉዳያችን አይሆንም። ሆኖም ባንድ በኩል ያሳሰበን ነገር አለ። በዘር እና በጠባብ ድርጅታዊ እይታ ተመርኩዛችሁ የኢትዮጵያን ሰፊ ህዝብ እና ብዙ የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ከቁም ነገር ሳትቆጥሩ ወደ ጎን በመተዉ ከፋሽስቱና ከጎጠኛዉ ወያኔ ብቻ በመሞዳመድ ለምታደርጉት ግንኙነት ግን ሌላ ዙር የግጭት ምንጭ አንዳይሆን አሳስቦናል።
ከላይ የጠቀስኳት እንግሊዝኛ መግለጫችሁ ስንመለከት ኢትያዊያንን አግልሎ በጠመንጃ ሀይል ሥልጣን የተቆጣጠረ ሕግ አልባ ወንጀለኛ እና ለወደፊቱም አገርን በመክዳት በሕግ ፊት ሚጠየቅ የመለስ ዜናዊን ቡድን ያቀፈ እና እንዲሁም የትግራይ ሕዝብ ብቻ የሚያሞግስ የተቀረዉ ሕዝብ ግን “ጸረ የኤርትራ ሕዝብ፤ ቅኝ ገዢ እና ባዕድ” ተደርጎ ያቀረበችሁትን እይታ መታረም አለበት።
ከትግራይ ሕዝብ ጋራ ተዋዋልን፤ተግባባን የምትሉትን ግንኙነት ሩቅ የማያስከድ እና ጠባብ በመሆኑ በሰፊዉ የኢትየጵያ ሕዝብ ቅሬታን እንጂ ወዳጅነትን አያዳብርም የሚል አስተያየት አለኝ። እኔ በምለዉ አቋም ምን ያህል አንደሚለዩ ባላዉቅም፤ የምስረታችሁ በዓል ምክንያት በማድረግ የደስታ መግለጫ የለኩላችሁ ኢትዮጵያዊዉ የኤርትራ ክ/ሀ ተወላጅ ደ/ር ፍስሃጽዮን መንግሥቱ እና ድርጅታቸዉ (አዲስ ተስፋ) ቅሬታየ የሚያጡት አይመስለኝም።
ወደ ሗላ መለስ ብለን ብንመለከት ሻዕብያና ወያነ ሲያደርጉት ነበሩትን አፍላ ፍቅር አልቆ ወደ ከፋ የደም መፋስሰ ጦርነትና ህዝብን ያካተተ ጥላቻ ሊያመጡ የቻሉበት ምክንያትም ፤ጎሰኛ የሆነ ጠባብ ግንኙነት በመከተላቸዉ መሆኑን ማንም አይስተዉም።ስለዚህ በመሞትና በሽረት ላይ “በነብስ ግቢ ነብስ ዉጪ” መሃል እተንገዳገደ ዕድሜዉ እያገባደደ ባለዉ ወያኔን ከማመን ይልቅ፤ “ሻዕቢያ እና ወያኔ” ከሚፈሩት ግንኙነታችሁ ከሰፊዉ ኢትዮያዊ ህዝብና ድርጅቶች፤ ቀና አመለካከት ከያዙ ምሁራኖች፤ ያገር ሽማግሌዎች፤ታሪክ አዋቂዎች በታደርጉ ተተብትቦ አ’ልፈታ ያለዉ መላ-ቅጡ የጠፋዉ የፖለቲካ ክር በአንደነት መፍታት እንደሚቻል ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።( “አንድ የኤርትራ የፖለቲካ ተቃዋሚ መሪ በቃለ መጠይቁ “ኢሳያስ የኢትጵያን የሚረዳ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነዉ” እንዳለዉ፤ ፈጣሪያችሁ ልቦና ሰጥቶአችሁ እናንተም ለበጎ ሥራ ስትነሱና ጤናማ ግንኝነት ስትመሰርቱ -በስመ ኢትዮጵያ አገር ለማፍረስ ከሚጥሩ ጸረ-ኢትዮያ ቡድኖችና ስልጣን ‘ከጠማቸዉ ግለሰቦች ግንኙነት ማድረግ “ታጥቦ ጭቃ” እንዳይሆንባችሁ ትንሽ ጠንቀቅ እያላችሁ መመርምር አስፈላጊ ነዉ)።
በመጨረሻም “እጅ -እጅ” ያለዉ መግለጫችሁ “ወያነ…ወያነ…ወያነ…””የትግራይ ህዝብ- የትግራይ ህዝብ” እያለ በአንድ ዉስን አካባቢ ብቻ ያተኮረ ግንኙነታችሁ ግቡ ኢሳያስን በማዉረድ ያለመ ስለሆነ እናንተ ወያኔን በማቆላመጥ <ደቂ ትግራይ> ስለምትሉዋቸዉና አምላኪዎቻቸዉ ስለ ኤርትራ ህዝባችሁ መጽሄቶቻቸዉ ምን እንደሚሉ ለናሙና ላቅርበላችሁ እና “አማራ፤አህያ፤ ኢትዮጵያ” የምትሏቸዉ በጠላቻ የምትመለከቷቸዉ ቋንቁኛችሁን ከዚህ በታች ያለዉን አገናዘቡ እና “አህያዉ አመራችሁ”ያልጻፈዉን የዘንድሮ ወዳጆቻችሁ ያዉም በቅርቡ እዛዉ ትግራይ ዉስጥ መቀሌ ፤አክሱም ዉስጥ ስትንሸራሸሩ በሐምሌ ወር 2000ዓ/ም የወያኔ መጽሄቶች/”ደቂ ትግራይ” ከሚጻፉላችሁ የጥላቻ ሐረጎች አስኪ እንብቡት።
እነሆ፦
ከወያኔዎቹ አንዱ ነዉ። ጉዕሽ ወ/ገብርኤል ይባላል።ኗሪነቱ ጀርመን አገር። ጉዕሽ -“ደሃይ” እየተባለ የሚታወቅ ትግራይ ዉስጥ መቀሌ ከተማ የሚታተመዉ ወርሓዊ የወያኔዎች መጽሄት በመጀመሪዉ የሽፋኑ ገጽ ከመጽሄቱ 4 ቋሚ አምደኞቹ አነዱ እንደሆነ ይነበባል።
ጸሃፊዉ፤ በደሃይ መጽሄት በመጋቢት/ሚያዚያ 2000ዓ.ም ዕትሙ ላይ <ቅንጅት ሓንካሪ> (“በጥባጩ ቅንጅት”- የፖለቲካ ይዞታቸዉና የከሸፈዉ ዉጤታቸዉ- ደሃይ መጽሄት ገጽ 13 መጋቢት/ሚያዚያ 2000ዓ.ም www.dehaytigray.com ) በሚል ርዕስ ለትግራይ ሕዝብና ለትግርኛ አንባቢዎቹ “ጉግ ማንጉጎቹ መጡብህ፤ ጠንቀቅ በል፤ ሊጨፈልቁህ ነዉ፤ መብትህ ሊነጥቁህ መጡ፤ ያላረሱትን፤ ያልለፉበትን ሰብል ለማፈስ የቋመጡ የተለፋበት የሚነጥቁ፤ በዉርስ በተዋረድ የተረከቡትን ባህሪያቸዉ….ዛሬም…….ሊዉጡህ ነዉና…ወዘተ..ወዘተ…በማለት ህዘብን በማስፈራራት ግራ ተጋብቶ የመለስ ዜናዊን ስልጣን ላይ ለማራዘም ሆን ተብሎ ወየኔዎች በምስጢር በቅንጅት ስም የዉሸት ማህተም/ዓርማ አትመዉ መለስ ዜናዊ የፈለሰፈዉ “የኢንተር ሃሙዌዉ” አጋጪ ቅስቀሳ በነዚህ ጸሃፊዎች እንደ እውነት ተደርጎ ተወስዶ በነ ጉዑሽ ወ/ገብሪኤል ለፕሮፖጋንዳ ሥራ ሲዉል እንብባችሁት ይሆናል (ይህ ጸረ ቅንጅት የኢንተርሃሙዌ ቅስቀሳም ሃቅ መስሏችሁ ከናንተም መሃል ለዋያኔ ድጋፍ በራድዮናቸዉ ግልባጩን ያስተጋቡ ነበሩ (“ድምጺ ደሊና” የተባለዉ አስማሪኖ.ካም በተባለዉ ድረገጽን ያስተዉሷል- በዚህ ላይ እኔም “በኢሜይል” አስተዳደሩ ለምን የኤርትራ ተቃዋሚ ድርጅት ራድዮኖች በእንደዚህ ዓይነት ቅሌት ቅስቀሳ መግባት እንደተፈለገ ቅሬታየን አሰምቼ ነበር)።
ዛሬም፤በዛዉ ወር እና በዛዉ መጽሄት የደሃይ መጽሄት አምደኛዉ ጉዑሽ ወ/ገብሩኤል ስለ ኤርትራ አረጋዊያን/አባቶች አንዲህ ይላል።
<<…ሆኖም ጨዋ፤ መካሪ፤ አረጋዊ ከየት ይምጣ?ያልተፈጠረባቸዉ? አሻግረን ከማዶ የምናየዉየኤርትራዉያን የአረጋዊያኖቻቸዉ ለፍቅርና ለወንድማማችነት፤ ለአንድነት፤ ለጥንካሬ የወንድማዊነት ጉርብትና አገሽበት፤ ለሽምግልና ለዕርቅ፤ለፍቅርናናኝ መስህብና ምልክት አንዲሆን የተፈጠረ ሳይሆን፡ ሽበታቸዉ ለጌጥ ብቻ የበቀለ፤ ዉቃቢ የራቀዉ ፤ጨዋነት ያልተላበሰ ፤ሰው ሰራሽ ቀለም ነዉ።>> {ጉዑሽ ወ/ገብርኤል (ጀረመን) ኤርትራ ዓገብ በሃላይ አልቦ ሃገር- ፡ደሃይ መጽሄት መጀመርያ ዓመት- መጋቢት/ሚያዝያ 2000ዓ/ም
www.dehaytigray.com] {<<…….ግና ወረጃን ማዓዳይን ሽማግለ ካበይ ይምጻእ? አቲ ኣማዕዲኻ ዝረኤ /ሽበት ኤርትራዊያን ንሽምግልናን ንዕርቅን ንሰናይ ጉርብትናን ንፍቕሪን ዝተፈጥረ ዘይኮነስ ንጌይጺ ዝኸዉን ሰዉ ሰራሽ ዝዓይነቱ ዘይዉርዙይ ቀለም’ዩ>> {ጉዑሽ ወ/ገብርኤል (ጀርመን) (ኤርትራ ዐገብ በሃላይ ኣልቦ ሃገር- ደሃይ መጽሄት -ቀዳማይ ዓመት መጋቢት/ሚያዚያ 2000 ዓ.ም}
እነኚህ እና የመሳሰሉት የወያኔ “ማሃይማንና-ጎጠኞች” ናቸዉ ደስ ሲላቸዉ ባንዴራዎቻቸሁን እያዉለበለቡ “ኤርትራዊት አዶ እዚ ኩሉ ኣይሳላኺንዶ” ሲሉ ደስ ካላላቸዉም ከላይ ያስነበቡን ዘረኛ ጹሁፋቸዉ ላልተማረዉና ለተማረዉ ሕዝባቸዉ በመጽሄቶቻቸዉ የሚነዙትን ቅስቀሳ ለናሙና ያነበብነዉ ነዉ።
እነዚህ ናቸዉ ዛሬ እናንተ “ደቂ ትግራይ” እያለችሁ ብረት ለታጠቁት ዘመነኞች በማቆላመጥ ሌለዉን ህዝብና ተቃዋሚ ድርጅቶች አግልላችሁ ሽር ጉድ የተያያዛችት። ለማንኛዉም ቀና ልቦና ሰጥቶአችሁ የምንለግሰዉን አስተያየት በጥሞና እንደምትምለከቱት ተስፋ አደርጋለሁ።
ከዚህ በታች የምታነብቡት ቃለ መጠይቅ ኢትዮጵያ ድረስ ሄደዉ አዲስ አበባ እንደገቡ የቅኝ ገዢዎች ቅጥረኛዉ ወያኔ ዛሬ ደግሞ ከጌቶቾቹ አዲስ መመርያ ተስጥቶታል መሰል ኤርትራንም በጎሳ ለማደራጀት እንደተቀሩት ጛዶቻችሁ በጎሳ ካልተደራጃችሁ ወይንም በጎሳ ተደራጁትን ካላቀፋችሁ እንደተቀሩት የምትጠይቁትን ጽ/ቤት ለመክፈት አይፈቀድላችሁም ፤ ፡ሽመልባ ወደ ተባለዉ የኤርትራ ስደተኞች መጠለያም ሄዳችሁ ለመጎብኘትም ቢሆን አይፈቀድላችሁም፡ በማለት ከላይ የተመለከትናቸዉ ትግራይ አክሱም ዉስጥ ጉባኤ በማደርግ የጋራ ሕብረት/ኪዳን መሠረቱ የተባሉትን 13ቱን ቡድኖች በመቃወም ለዜና ዘጋቢዎቻቸዉ የሰጡትን የኤርትራ አንድነት የአርነት ግምባር የተባሉት የአመራር አባሎች የሰጡትን ቃለ መጠይቅና ቅሬታ፤ ትግርኛ ለማታነቡ ወገኖች በኢትዮጵያ ምድር ዉስጥ ምን እሰተፈጸመ እንዳለ እና የኢትዮጵያ ጠላቶች አገሪቱን ምንኛ መቀለጃ እና መናሃሪያ እንዳደረጉዋት ላስነብባችሁ። “አቶ ረዘነ ሃበተ እና- አቶ መሓመድኑር ዑስማን” ሁለቱም ከ ዩናይትድ ኤርትርያን ናሽናል ፍሮንት ማለት “ግምበር ሃገራዊ ሓርነት ኤርትራ” “ግ.ሃ.ሓ.ኤ”) (የኤርትራ አንድነት የአርነት ግምባር) ሊቀመንበር እና የድርጅቱ የዉጭ ጉዳይ ተጠሪ ፦ጉደኛዉ “መለስ ዜናዊ”- “ሰንዓ-ፎረም” የሚባል ድርጅት መስርቶ የእናት አገሩን የኤርትራ ጉዳይ በቅርብ ለመከታተል እና የወደፊት መጠለያዉ እንድትሆነዉ አያዘጋጃት ያለቺዉን የመጪዋ መለስ እና የስብሓት ኤርትራ በወኪላቸዉ በወያኔዉ በሕቡር ገ/ኪዳን በኩል ምንኛ ተጽእኖ እንደተደረገባቸዉ ያሰሙት እረሮ አንዃር አንኳሩን እነሆ።-
ጥያቄ
<< ወደ ኢትዮጵያ እንደገባችሁ የስራ ጉብኝታችሁ በየትኛዉ ጀመራችሁ?
መልስ-
አዲስ አበባ የገባንበት ዕለት አርብ ስለነበር፡እንደዚሁም ረዢም ጉዞ መንገድ ስለተጛዝን የድካም ስሜት ተጽዕኖ ስለበረን፡ ለሚመለከታቸዉ ያገሪቱ ባለስልጣኖች ወዲያዉኑ እንደመጣን ልንገናኛቸዉ አልቻልንም ።በዛም ቅዳሜ እና እሁድ የመንግት መሥርያቤቶች ዝግ ስለሚሆኑ እስከ ዛው ድረስ ግን ካንዳንድ የተለያዩ የኤርትራ ተቃዋሚ የአመራር አባላት ጋር አንዳንድ ሃሳቦችን አንለዋወጥ ብለን ሃሳቦችን ተለዋወጥን። ዕሁድ ከሰዓት በሗላ በ11 ሰ ዓት አካባቢ፡የመንግሥት ባለስልጣኖች ይፈልጓችሗል የሚል መረጃ ደረሰን። እኛም በበኩላችን ያረፍንበት ሆቴል እና አድራሻ ለሚመለከታቸዉ ደዉለን ነገርናቸዉ። ያኔዉ ዕለተ እሁድ በ12 ሰዓት አካባቢ ከሰዓት በሗላ ፡ ኣቶ ተኸስተ የሚባል የሰንዓ ፎረም ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ወደ አረፍንበት ሆቴል በመምጣት ተገናኘን።
ከሰላምታ ልዉዉጥ በሗላ ኣቶ ተኸስተም የመጣበት ምክንያት ሲገልጽ “ወደ ኢትዮጵያ የገባችሁበት ምክንያት ጆሮየ አስኪደነቁር ድረስ በተደጋጋሚ ከ6 ተለያዩ የኪዳኑ (የህብረቱ) አባሎች ስልክ ደውለዉ ‘ህብረታችነን ለማፍረስ ነዉ ወደዚህ የመጡት’ በማለት ስላወኩኝ ይህንን አቤቱታ ልነግራችሁ ነዉ መጣሁት። በተጨማሪም ህብረቱ እጅግ የተሳካ ጉባኤ አድረጎ የተዋጣለት የጋራ መድረክ መመስረቱን ደስ ብሎናል”። በማለት ስለ ኪዳን ያለዉን አዎንታዊ/በጎ አመለካከት የግሉን ገለጸልን።
እኛም “የደረሱህ አቤቱታዎችን መሠረት በማድረግ ይህንኑ ቅሬታ ለማሰማትና ለመወያየት እኛዉ ዘነድ መምጣትህ ተገቢ ነዉ። በበኩላችን ግን እኛ እዚህ ስንመጣ ድንገት አልመጣንም ወይንም አመነንም ዓላማ ለማፍረስ አልመጣንም።ከመምጣታችን በፊት ዋሽንግተን ዲሲ. ከሚገኘዉ ወኪላችሁ ጋር ተገቢዉን የፖለቲካ ዉይይት አድርገን ነበር የመጣንበት።ስለዚህ የነሱን የ6ቱን ድርጅቶች አቤቱታ ለማሰማት ነዉ የመጣሁት ከማለት እንግዶች እንደመሆናችን መጠን ረጋ ብለህ የመጣንበትን የኛ መነሻም ማጥናትም ተገባ ነበር። ግን ያ ስላላየን፤ከጠበቅነዉ በላይ ቅሬታ የተሰማን መሆኑን ገለጽንለት።
እሱም ስለ ሕብረቱ ያለዉን አስተያየትና አቋም ገለጸልን።የሱን አስተያየት ካዳመጥን በሗላ፡ በበኩላችን፤- እኛ እንደ “ግንባር ሃገራዊ ሓድነት ኤርትራ /ግ.ሃ.ሓ.ኤ/” ድርጅት መጠን ፡ ኪዳን/ሕብረቱ የኤርትራን ሕዘብ ችግር ሊፈታ ብቃት ይሁን ሞራል ፤ከሁሉም በላይ ደግሞ ድፕሎማቲካዊም ሆነ፤ የፖለቲካና የ’ስትራተጂ ብቃት የለዉም የሚለዉ መከራከሪያ ፖሊሲያችን የድርጅታችን ጽኑ ዕምነት መሆኑን አበክረን ገለጽንለት። ቀጥለንም ከኪዳን/ከህብረቱ ጋር ተወህደን በጋራ ለመስራት ፍቃደኞች አንዳልሆንን ግልጽ አደረግንለት።
ኣቶ ተኸስተ ም በበኩሉ፡ ከኪዳን ጋር የማይሰራ ድርጅት አንረዳም፡ ይኹን እንጂ አትንቀሳቀሱም፡ የፖለቲካ ስራዎች አትሰሩም አንላችሁም። ማንኛዉም ኤርትራዊ ህ.ግ.ደ.ፍ ን ለማስወገድ መታገል ይችላል። ይህም የመንግሥታችን ፖሊሲ ነዉ በማለት መልስ ሰጠን። በበኩላችን ከ ኪዳን/ከህብረቱ ጋር ተዋህደን አንሰራም ስንል በመሰረቱ ሰንዓ ፎረም ፐይሮል መዝገብ ዉስጥ አንገባም ማለታችን እንደሆነ በግልጽ አስቀመጥንለት።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ዉስጥ ድርጅታዊ ሥራ ለማከናወን እንዲያመቸን ድርጅታችንን የሚወክል ህጋዊ ጽ’ቤት ለማቋቋም እንዲፈቀድልን ብቻ ለመጠየቅ ነዉ የኛ አመጣጥ እንጂ ከኪዳንም የመተሳሰር ጉዳይ ወይም የመሳሰሉት ሁነታዎች ለመፈጸም ለመነጋገርም ሆነ የ ማንንም እጅ ለማየትና ለመንሳት አልመጣንም። በማለት ያመጣጣችን ጉዳይ ይበልጥ ግልጽ እንዲሆንለት አብራራንለት። አቶ ተኸስተም ቀጠሮ ስላለኝ ልተዋችሁ ነኝ ሌላ ጊዜ እንገናኝ፡ በማለት ተሰናበተን።
ጥያቄ-
የናንተን መምጣት በመቃወም አቤቱታቸዉን አስሰሙ የተባሉት 6ቱ ተቃዋሚ ድርጅቶች በቁጥር ብቻ ነዉ ወይስ በስምም እነማን መሆናቸዉን ተነግሮአችሗል? ከሚመለከታቸዉ ባለስልጣኖችስ ቀጣዩ ግንኙነታችሁ ምን ይመስል ነበር?
መልስ
እነማን እንደሆኑ በስም አልተነገረንም፡ ብቻ ተቃዉሞ እንዳሰሙ እና መምጣታችንን አንዳላስደሰታቸዉ ነበር የተነገረን። እኛን ለመቃወምም አቅማቸዉ በፈቀደ ሁሉ እንደሚጥሩ ግልጽ ሆኖልን ነበር። በተግባርም አየነዉ። የዉሸት እና የማምታታት ስራዎች ዳብሮ ቆይቶን አይተናል። በ5/19/2008 ሰኞ ዕለት ጥዋት፡ የሰንዓ ፎረም ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ሕቡር ገብረኪዳንን ተሌፎን ደዉለን ምምጣታችንን ስንገልጸለት፤ በጣም እጅግ በጣም በንዴት ነድዶ የቁጣ ዶፍ አወረደብን። እንኳን አንደ አንድ የጽ/ቤት ዳይሬክተር ፡ እንደ ተራ ሰውም የተለመደዉ ቀና የሆነ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የትሕትና ባህል ማሳየት አልቻለም።
አቶ ሕቡር ያሳየን ገጸ ባሕሪ ከግሉ የመነጨ አንጂ ከመንግሰሥት ነዉ የሚል ዕምነት የለንም።ስለሆነም ሐላፊነታችነን ግልጽ ለማድረግ የመጣንበት ተልእኮ/ዓላማ በጽሁፍ ማቅረብ አስፈላጊ ሆኖ ሰላገኘነዉ፤ በጽሁፍ ገለጽንለት ።
እንደዚያም ሞክረን፤ አቶ ሕቡር ልያነጋግረንም ሆነ ሊመልስልን አልፈለገም።በሌላ በኩል ግን በርከት ያሉ ኤርትራዊያን እየመጡ የሰንዓ ፎረም ሐላፊዎች እናንተን እንዳናነጋግር ትዛዝ አስተላልፈዉልናል።እያሉ ይነግሩን ነበር።
ጥያቄ ለአቶ ሕቡር በጻፋችሁት ደብዳቤ መሰረት እንደተረዳነዉ፤ ሁለት የተለያዩ የጉብኝታችሁ ምክንያቶች ነበር የገለጻችሁት። ቀዳሚዉ ነገር ግ.ሃ.ሓ.ኤን የሚወክል ጸ/ቤት ጽሕፈት ለማቋቋምና ፖሊሲያችሁና ትግላችሁ ለማስተዋወቅ እና ልላዉ ደግሞ ወደ ሽመልባ መጠለያ ሄዳችሁ ስለ ስደተኞቹ ሁኔታ ዘገባ ይዛችሁ እንድትመለሱና የAmerican Eritrean Organization for Justice Democracy and Development ለሚባል ለNGO ማህበር ለማቅረብ ነዉ። ሁለቱንም ለማከናወን ምን ቀጣይ ጥረት ገጠማችሁ?
መልስ
አስራሁለት ቀናትያክል መልስ ለማግኘት ስንጠባበቅ የተለየ ለዉጥ ስላላየን ወደ ሁለተኛዉ ተልእኮአችን ለማከናወን ይረዳን ዘንድ ከሚመለከታቸዉ ክፈሎች ንገግግር ለማድረግ ወደ Administration for Refugee and Returnee Affairs (ARRA) በመሄድ የሕግ እና የፕሮቴክሽን መምርያ ሓላፊ፡ አቶ ሃይስላሴ ገብረማርያምን አነጋገርን። ከ AEOJDD የተሰጠን ደብዳቤ ም አስረከብነዉ። ። ኣቶ ሃይለስላሴ ገብረማርያም በጣም ትሑት እና የበሰለ ባለ ሞያ ፡ ሐላፊነቱና ተገቢ ስራዉን በሚገባ የሚያዉቅ ሆኖ አገኘነዉ። ባጠቃላይ ስለ ኤርትራ ስደተኞች ጉዳይ ሰፊ ማብራርያ ሰጠን።ይኹን እንጂ ወደ ሽመልባ ለመጓዝ የመንግስት ፈቃድ ሊያስፈልጋችሁ ነዉ፡ አለን።እንዴት? አልነዉ። አሱም ፡ የዚህ አገር ጸጥታ ለመጠበቅ በተለይም ኤርትራዊያን የፖለቲካ ክንዋኔ ሲያደርጉ መንግሥት ማወቅና ማሳወቅ ግዴታ ስለሚል መንግሰሥት ፈቃድ ሊያስፈልጋችሁ ነዉ፡ አለን።
ቀጥሎም ፤ ከሰንዓ- ፎረም ሃላፊዎች’ሳ አስካሁን ድረስ ምን ተነጋገራችሁ አለን? በበኩላችን ምንም መለስ አላገኘንም፡ ምንም ያደረግነዉ ነገር የለም፡ አዚህ እንዳለን ያዉቃሉ፤ በሕጋዊ አመጣጥ መጥተን እዚህ እንዳለንም ነግረናቸዋል። ብለን ከመለስንለት በሗላ እንግዳዉስ ወደ ነሱ ደዉየ መልሱን እነግራችሗለሁ አለን። በበኩላችን እሺ አልነዉ።
ኣቶ ሃይለስላሴ ገብረማርያም፡ ከሁለት ሰዓት ቆይታ በሗላ ቴሌፎን ደዉሎ፡ ወደ ሽመልባ ለመሄድ ፈቃድ እንደተከለከልን ነገረን። ያኔ ተልኦኳችን እንዳይሳካ ከዉስጥ መሰናክሎች እንደተደረጉብን ግልጽ ሆነልን፡
ሆኖም በእኛ ዕምነት በሰንዓ-ፎረም በኩል የተደረገልን ተጽዕኖ ከግል የነሳ መሆኑን ነዉ የምናምነዉ እንጂ ከመንግሥት እንዳልሆነ ጽኑ ዕምነታችን ነዉ ። የሆኖ ሆኖ ለኛ ግልጽ ባልሆነ ምክንያትና ያልጠበቅነዉ አንድ የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ባልደረባ የሆነ ግለሰብ አነጋገረን። ግለሰቡ፤ ቀና ሰዉ ነበር። ያካባቢዉ ሁኔታ በደምብ ጠንቅቆ የሚያቅ በመሆኑ ጠለቅ ያለ መግለጫ ስለሚታዩት ክስተቶች ገለጸልን። እኛም በጥሞና አዳመጥነዉ። መጨረሻም፡ለመሆኑ ከሰንዓ ፎረም ጽ/ቤት አባሎች ጋርስ ስለጉዳያችሁ ተነጋግራችሓል? አለን። እኛም ሁኔታዉን ገለጽንለት።ለማንኛዉም ከሕቡር ጋር ሆነን ጉዳዩን እንመለከተዋለን። አለን። እንደተባለዉ ሁኔታዉን በጥሞና ስንጠባበቅ ከቆየን በሗላ ሕቡር የነገረዉን የሚገርም ነገር በስልክ ደዉሎ የሚቀጥለዉን ነገረን።
”ከኪዳኑ/የህብረቱ አመራሮች ጋር ለመስራት ፈጸሞ ፈቃደኞች አይደሉም።እኛን ያሰማራን የአሜሪካ ሲ.አይ.ኤ ስለሆነ በቀን ለያንዳንዱ ታጋይ $300.00 እየከፈልን ማታገል እንችላለን።በማለት ፐሮፖጋንዳ እያናፈሱ መሆናቸዉን መረጃ ስለያዝን፡በበኩላችን አስኪ የት እንደሚደርሱ እናያለን ብለን በጥሞና እየተከታተልናቸዉ ነን፡ ብሎ ነግሮኛል እና ያመጣሁላችሁ መልስ ይሄ ነዉ”። በማለት ነግሮን በዚህ ተሰናበተን።
ባጠቃላይ ሁኔታዉ ስንመለከተዉ ሕቡር ያላልነዉን አሉባልታ መናኛ ወሬ እንደ እዉነት ቆጥሮ እኛን ዋጋ ለማሳጣት ያደረገዉ ሙከራ በእዉነቱ እኛ ከጠበቅነዉ በታች እጅግ ወርዶ ስላገኘዉ ፤ሃለፊነት የጎደለዉ አነጋገር ብቻ ሳይሆን ነዉር መሆኑንም ለመግለጽ እንሻለን። አቶ ሕቡርን በደብዳቤ በቴሌፎን ስለ አላማችን ስለጉብኝታችን ተልእኮ ምክንያት ገልጸንለት ስናበቃ ፤ምንም መልስ አልሰጠንም። ያ እንዳይበቃ ስማችንን ሳይቀር አጎደፈዉ።ከሕብረት ድርጅቶቹ ጋር የማበር፤የመስራት አለመስራት መብታችን ለኛ መተዉት አለበት።ካሁን በፊት ከሕብረቱ ጋር እንዳንሰራ እንቅፋት የሆኑትን ነገሮች ዘርዝረናል። በይፋ ድርጅታዊ መግለጫም አዉጥተናል።ስለዚህ ከነሱ ጋር ለመስራት ፈቃደኞች አይደለንም።በዚህ የተነሳ የዶፍ ቁጣዉን በ ላያችን ላይ ማዉረዱ ተገቢ አልነበረም። ይህ ታዛቢ የሚፈርደዉ ጉዳይ ነዉና በዚህ እንተወዉ።
ጥያቄ ሌላስ ምን ችግር ገጥሟችሁ ነበር?
መልስ
መነሻዉ ምንም ይሁን ምን የኛን ስም ለማጉደፍ ያልተሞከረ ነገር አልነበረም።ከሕብረቱ አመራር አንዳንዶቹ ከኛ ጋር ለመስራት ምንም ችግር እንደሌላቸዉና ፖሊሲያችንም አንደሚያከብሩት በጎን እየመጡ ገልጸዉልናል።ሆኖም ለመልካም ዉጤት ከህብረቱ ጋር ሆነን አብረን ብንሰራ ሃሳባቸዉንም ሰንዝረዋል።በበኩላችን ግን የኤርትራ ችግር መፍትሄዉ አንድነትን የሚያጠነክር የፖለቲካ ስትራተጂ በጋራ መታነጽ አለበት። ሕብረቱ እየተከተለዉ ያለዉ ስልትና የፖለቲካ ሰትራተጂ “ህግደፍን”/ሻዕቢያን ከስልጣን የሚያስወግድ ብቃት የለዉም።ዓለማዉ የአገር አንድነት ግምት ዉስጥ ያስገባ ሳይሆን፡ ጠባብ የጎሳ ዝንባሌ ከአገር ጥቅም እና እንድነት በፊት የሚያስቀድም ነዉ። በጠባብ ብሄረተኛነት ስሜት ተወጥረዉ ያገሪቷን አንድነትና ታሪክ ካለማገናዘብ እየተጓዙ የምናያቸዉ የኤርትራትራ ተቃዋሚ ድርጅቶች የህዝቡን ችግር ይፈታሉ ብለን አምነን እንደማናዉቅ ደጋግመን አቋማችንን አስታዉቀናል። ሆኖም ፍሬ ቢያስገኝም ባያስገኝም መኖር አለበት ነዉ የሚሉት።የጎሰኝነት ሃይል አቅፎ እየተጓዘ ያለዉ የሕብረቱ አንዳንድ አባሎች ከጎን ከእኛዉ ዘንድ በመገናኘት በብሄር መደራጀቱ አልወደድደነዉም እያሉ ቅሬታቸዉን ይገልጹልናል።በሌላ በኩል ደግሞ የሕብረቱ ጠበቆች ሆነዉ ሲጮሁ እኛን የሚያጎድፍ ዘመቻ ሲያደርጉ እንታዘባቸዋለን።
ጥያቄ ሕብረቱ አንደ አንድ ሃይል ሆኖ ነዉ እየተጓዘ ያለዉ የሚለዉን እናንተ እንዴት ትመለከቱታላችሁ?
መልስ፤ -
ካሁን በፊት ስለ ሕብረቱ ያስቀመጥነዉ አቋማችን እንደተጠበቀ ሆኖ፤የትጥቅ ትግል እንዳይካሄድ እንቅፋት እንዲሆን ነዉ ተመሰረተዉ። እነኚህ የጎሳ ድርጅቶች ናቸዉ፡ ማለትም የኩናማ ሕዝብ የዓፋር ህዝብ ነፃ ለማዉጣት እንታገላለን የሚሉት፡ጎሳቸዉን ብቻ ነፃ በማዉጣት ያተኮረ የታጠቀ ተዋጊ ሠራዊት ብቻ ነዉ ያላቸዉ እንጂ፤በአገር ደረጃ የኤርትራን ሕዝቦች ለአንድነት አታግሎ ነፃ የሚያወጣ ተዋጊ ሠራዊት የላቸዉም።ስለሆነም ሕብረቱ “ህግደፍን”(ሻዕቢያን) የሚያስወግድ የታጠቀ ተዋጊ ማስሰለፍ አይችልም።ሕብረቱ የዜና፤የዉጭ ጉዳይ፤ማህበራዊ፤የምጣኔ ጉዳይ ክፍሎች የመሳሰሉት ጉዳዮችን የሚያከናዉኑ ጸ/ቤቶች አሉት፡ ነገር ግን ወታደራዊ ክንፍ ወይንም ወታደራዊ ጉዳይ ጽ/ ቤት የሚል አካል አልገነባም፡የለዉም። ስለዚህም ዓይነተኛዉ መንስኤ የጎሳ ወታደራዊዉ ክንፍ አገራዊ የአንድነት ራዕይ ካለዉ ተዋጊ ሠራዊት ጋር ለጋራ ዓላማ አብሮ ባንድነት ተሰልፎ ጠላትን በጋራ መዋጋት አይችልም። የማይጣጣሙ ዕይታዎች፤ግቦች፤ዓላማዎች ስላሉዋቸዉ።ስለዚህ ኪዳን/ሕብረቱ በተቀመጠለት ቻርተር እጨዋታዉ ሜዳ ላይ እጫወታለሁ ብሎ ወታደራዊ ክንፍ ይኑረን ብሎ ወደ ዉሳኔ ከሄደ ዕድሉ የመበታተን ዕጣ እንደሚሆን ስለሚያዉቅ አንድ የጋራ የታጠቀ ሠራዊት ይኑረን የሚል ከአፉ አይወጣዉም።
ጥያቄ፡
የብሔር ጥያቄ ኤርትራ ዉስጥ መቸ ነዉ የተጀመረዉ? እዉን የብሔር ችቆና ሚሉት ነገር አለ?አለ ከተባለስ፤ ካሉን ብዙ ብሄረሰቦች እንዴት ኩናማ፤ የዓፋር ብሄረሰቦች ነፃ አዉጪ ብቻ ሊመሰረቱ በቁ?
መለስ-
የጎሳ ድርጅቶች ወደ መጨረሻዉ ሰዓት ነበር የተመሠረቱት።መጀመሪያ “ደምሓኩኤ” (የኩናማ) ቀጥሎ የቀይ ባሕር ዓፋር ብሔራዊ ግምባር ተመሠረተ። ከዚያ ደምሓኤ (ሰ.ደ.ግ.ኤ) ህዲግኤ (ሳግም) ኢትዮጵያ ዉስጥ በርከት ላሉ ዓመታት ከ ኢሕአዴግ ጋር ስትራተጂ ግንኙነት ያካሂዱ እንደነበር እንመለከታለን። ስለዚህ የአመሰራረታቸዉ ዘመን ካዛ በላይ ላያስፈልግ ነዉ። እዉን የብሔረሰብ ችቆና ኤርትራ ዉስጥ አለ? ለሚለዉ ጥያቄ የኢሳያስ ፋሽስታዊ ስርዓት የፈጠረዉ ወይንም ተመሳሳይ ጭቆናዎች ነበሩ ወይንም አሉ የሚል በድርጅታችን አቋም አለ ብለን አናምንም። ዋናዉ ችግር ደግሞ የጎሳ ሰራዊትና ለአገር አንድነት የሚቆም ሠራዊት አብሮ በአንድ ሊጓዝ አይችልም፡ዓላማቸዉ ደግሞ የጎሳ ሠራዊትና የአንድነት ሃይሎች አብረዉ ሊያያይዛቸዉ የሚያስችላቸዉ የጋራ ክር የለም። የኢሳያስ ሥርዓት ሁሉንም በእኩል እየረገጠ ያለ ሥርዓት እንጂ፡ለእገሌ ሕዝብ ወዳጅ ለእገሌ ሕዝብ ደግሞ ጠላት ነዉ የሚባል ነገር የለዉም።
እዉነቱን ለመናገር በህግደፍ አስተዳደር የሚጠቀም ካለ እሱን ሚደግፍ ግለሰብ ይሁን ሃየማኖት ወይም ድርጅት ይጠቀማል፤ አሱን የማይደግፍ ደግሞ ማንም ይሁን ማ የሚታየዉ በጠላትነት ነዉ። ስለዚህ በብሄር ደረጃ እገሌ ከእገሊት ብሔረስብ የተሻለ ጥቅም እና የኑሮ መሻሻል እና ደህንነት አለዉ የምንልብት ጭብጥ ማስረጃ የለንም። ለምን የኩናማ እና የዓፋር ብሄር ብቻ በብሄር ደረጃ ተደራጁ? ለሚለዉ ጥያቄ እነሱ ራሳቸዉም ሊመልሱት አይችሉም። አስቀድመን እንደገለጽነዉ እወነትነት አለዉ ብለን ስለማናምን ምክንአቶቻችንም ግልጽ አድርገናል። ምክንያቱም ስለሌላቸዉ ለምን በዛ ጎዳና እንዲደራጁ እንደመረጡ መልስዩን ለማግኘት ብዙ አንጓዝበትም ፡ ግልጽ ነገር ነዉ።የሳሆና የብሌን ብሄረሰቦችን ለማደራጀት ጥረት ተደርጎ ላይ ታች ተብሎ ሳይሳካላቸዉ ትርፉ ድካም ብቻ ሆኖ ቀርቷል፡-
በቅርቡ እኛ ኢትዮጵያ ዉስጥ እያለን አዲስ የሳሆ ብሄራዊ ድርጅት ምስረታ ይፋ እንደሆነ በኣዋጅ ሰምተናል።ይህ አዲስ ክስተት ደግሞ የሳሆ ጀግና ህዝብ ታሪክና አርበኛነት የሚያጎድፍ እንጂ ለሳሆ ሕዝብ መብትም ሆነ አለኝታነት ያልቆመ መሆኑን በድፍረት የምናስቀምጠዉ ሚዛን ነዉ። ታጋይ የሳሆ ህዝብ አባሎች ከኛዉ ጋር አብረዉን ለአንድነት እየታገሉ እና ነዉ።
የኢትዮጵያና የኤርትራ ሁኔታ የተለያየ ነዉ። ኢትዮጵያ መስፍናዊ ስርዓት በተስፋፋበት የአንድ ሕዝብ ልዕልና እና የአንድ ሃይማኖት የበላይነት የተስፋፈበት አገር መኖሩን በተጨባጭ የምናቀው ነዉ።(አስተያየት - ከጌታቸዉ ረዳ- ሰዉየዉ ያንድ ሕዝብ የበላይነት ነበር እያለን ያለዉ አማራዉን ሕዝበ ማለቱ ነዉ “የታሪክ ማይምነቱን” እንዳለ እያለፋችሁ ሌላዉን ፍሬ ነገር አንብቡ)።
ከኢትዮጵያ መንግሥት ብዙ ነገር መማር እንደምንችልና እንደተማርንም እናምናለን። ሆኖም ከኛ ሁኔታ ጋር የማይሄድ የፖለቲካ አሰራር ቀድተን መጠቀም ግን ተገቢ አይደለም። ኢትዮያን ለመምስል የብሄር ጥያቄ ፡ ሱዳንን ለመምሰል የእስላማዊ መንግስት ልናቋቁም ኣይግባንም ብለን ብጹኑ እናምናለን።
ጥያቄ፦
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ተቃዋሚ ሃይሎች ያለዉን ግንኙነት እንዴት ታየዋለህ? ? ግ.ሃ.ሓ.ኤ ስ ምን ዓይነት ዝመድና ሊኖረዉ ይገባል ብለህ ታምናለህ?
መልስ-
ባጠቃላይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ተቃዋሚ ሃይሎች መሃል ግልጽ የሆነ ዝምድና /ግንኙነት አለ ለማለት አያስደፍርም፡ግንኙነቱ “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ” ከሚሉት ዓይነት ስትራተጂ አያልፍም። በኛ በኩል እንደ “ግ.ሃ.ሓ.ኤ” አቋም በኤርትራ ተቃዋሚ ሐይሎችና በ ኢትዮጵያ መንግሥት መሃል የጠነከረ ስትራተጂያዊ ግንኙነት መኖር ይገባዋል እንላለን። የፈሺስቱ ኢሳያስ ስርዓት ከኢትዮጵያ እስትራተጂካዊ ጠላቶች የጠበቀ ግንኙነት በማድረግ ኢትዮጵያን ለመበታተን ታጥቆ እየሰራ ባለበት ወቅት፡የኢትዮጵያ መንግሥት ህ.ግ.ደ.ፍን(ሻዕቢያን) ለማስወገድ የጠራ ስትራተጂካዊ መስመር ይዞ ግንኙነት ለማድረግ ያልፈለገበት ምክንያት አስካሁን ድረስ ለኛ ግልጽ ያልሆነልን ጉዳይ ነዉ።
በስመ እስትራተጂካዊ ዝምድና ምስረታ ካጋጠመን ሁሉ ግንኙነት መመስረት ማለት አይደለም።መንታ የሆነ ስትራተጂ መኖር የለበትም። ብእምነታችን እንደ ግ.ሃ.ሓ.ኤ ድርጅት በማንናኛዉም ጊዜ ከኢትዮጵያ እስትራተጂ ጠላቶች ጋር ማንኛዉንም ግንኙነት ሆነ አድላዊ ግንኙነት አናደርግም። የኢትዮጵያ ዕድገት፤ስልጣኔ ደህንነት ለኛ እንደ ስትራተጂካዊ ጠቀሜታ ነዉ የምንመለከተዉ። …….ይህ የፖለቲካ አቋማችን እየገለጸ ያለዉ ሁለቱንም ሕዝቦች ሰላምና መተሳሰብ አንዲኖር ያለመ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። ፋሺሽት ኢሰያስን ለማስወገድ የሁለቱንም አገሮች ጠቀሜታ እና እኩል የመመካከር ግንኙነትን ያተኮረ መሆን አለበት አንጂ የኤርትራ ተቃዋሚ ሃይሎች ለመከታተል የተቋቋመ “ሰንዓ-ፎረም” በመባል የሚታወቅ ተቋም በምንም መልኩ የሁለቱንም አገር ህዝቦች ዝመድናያላገናዘበ በመሆኑ ብቃት የለዉም።
የሚደረጉ ግንኙነቶች ፍትሃዊ ግንኙነት እንዲኖረዉ በሁለቱም በኩል ሲታመንበት ነዉ። ሰንዓ-ፎረም አሁን ካለዉ ከሚጠራበት ስም ጀምሮ በተቋሙ ላይ የዓይነት ለዉጥ ሊደረግበት ይገባል ብለን እናምናለን።
ሱዳንም ሆኑ የመን፤ ፋሺሽቱ ኢሳያስ ይወገድ ኣይወገድ የሆነ ይሁን ፖለቲካዊ ጠቀሜታ የላቸዉም።ጉዳአቸዉ አይደለም። በሰንዓ- ፎረም ሚሰባስብ ቡድን ሌላ የማይታወቅ አጀንዳ ኖሮት ካልሆነ በቀር እኛኑን ብዙ አያጓጓንም።ለሚያጓጓቸዉ እና ለሚመለከታቸዉ እንተወዋለን። በኛ በኩል ስለ የኤርትራ ተቃዋሚዎችን ጉዳይ በሚመለከት ግን ሰንዓ- ፎረም የፈረሰ ስለሆነ ትርጉም አይሰጠንም። ስለሆነም፤ትርጉም የለዉም። የሰንዓ ፎረም ተቋም ሃለፊዎች የኤርትራን ተቃዉሞ ለማዳከም ከ ህ.ግ.ደ.ፍ (ሻዕቢያ) ጋር እጅና ጓንቲ ሆኖዉ እየሰሩ መሆናቸዉን በጋሃድ እየተገበሩትና እየገለጹት ስላሉ ለማንም ብሩህ ነዉ ብለን ነዉ ምናምነዉ። ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ ተቃዋሚዎችን ጉዳይ በሚመለከት የጠራ የፖለቲካ ፖሊሲ ነድፎ ግልጽ በሆነ መንገድ አበክሮ እንዲይዘዉ በዚህ አጋጣሚ እንገልጻለን። የፋሺሽቱ ኢሰያስ ሥልጣን ላይ መቆየት አሳሳቢነቱ ለኤርትራዉያን ብቻ ተደርጎ መመልከቱ ስህተት ነዉ እንላለን።
ጥያቄ-
ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለዉን ችግርና ግንኙነት ለመፍታት ምን አቅዳችሗል?
መልስ-
የግዜ ጥያቄ መሆኑን ብቻ ነው እንጂ ዉለን አድረን ግ.ሃ.ሓ.ኤ በኢትየጵያ ዉስጥ ጽ/ቤት አቋቁመን ትግላችን እንደምናንቀሳቅስ ዕምነታችን ነዉ። የተፈጠረዉ ዉዝግብ ከጊዜ ጋር ይፈታል። በሕብረቱ ላይ በአስቀመጥነዉ የግምገማ አቋማችን ምክንያት በ ኢትዮጵያ ዉስጥ የመንቀሳቀስ መብታችን መታገዳችን ተገቢ አይደለም። እንደገለጽነዉ የሰንዓ-ፎረም ተቋም ዳይሬክተር ከሕብረቱ ጋር ካለዉ የጠበቀ ግንኙነት ምክንያት ታገድን እንጂ በመንግሥት ፖሊሲ ደረጃ እንዳልሆነ እንዲታወቅ ደግመን ለማሳወቅ እንፈልጋለን።
ስሕተተኞች ናችሁ የሚል የሕብረቱ አባል ካለ በተግባር ስሕተተኞች መሆናችን ያሳዩን። በሰላማዊ መንገድ ህግደፍ (ኢሳያስን) እናሸንፈዋለን ብሎ በአቋም መጽናት እራሱ “ህግደፍ” በራሱ ይለወጣል ማለት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም።ህ.ግ.ደ.ፍ በቅራኔ በሃይል ትግል ካልሆነ በምንም ተኣምር ማስወገድ አይቻልም።የሕብረቱ አባሎች በሰላም የሚፈታ ነገር እንደሌላ በደምብ ይረዱታል። አንዴ በሰላም አንዴ በሃይል እነገጥመዋለን ይላሉ። የሰላም ትግል የሚሉትንም ግልጽ አላደረጉትም፡ እንዴትና የት ተሁኖ ነዉ ሰላማዊ ትግል የሚካሄደዉ? በሃይል እንታገለዋለን የሚሉት አቋማቸዉም ቢሆን ወታደራዊ ስራዎችን ለማንቀሳቀስ እንዴት 13 ዓይነት ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ ታጋዮችን አሰማርቶ እና 13 ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ተይዞ ሊሆን ይችላል? አይሆንም!
የኤርትራን ሕዝብ ለማዳን ከሆነ ዓለማችን አንድ ወጥ የሆነ አገራዊ ሠራዊት መስርቶ ማንቀሳቀስ ብቻ ነዉ ነባራዊዉ ሁኔታ እየጠራን ያለዉ። ከዚ ዉጭ ሌላ ነገር መከተል ከንቱ ሕልም መከተል እንጂ “ህግደፍ”ን በትጥቅ አልባ ትግል አስወግዳለሁ ማለት ዘበት ነዉ።
አመሰግናለሁ።እኔም አመሰግናለሁ 8/12/2008 {የሃግሓኤ ዜና ወኪል}. ትርጉም ጌታቸዉ ረዳ ሳንሆዘ ካሊፎርኒያ www.ethiopiansemay.blogspot.co