Friday, February 3, 2023

ልደቱ አያሌው በቀለ ገርባን ላለማስከፋት የበቀለ ገርባን ዘረኛነት አንድም ቃል ሳያነሳለት “ጋሼ” እያለ ውይይቱን ቋጨው ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 2/3/23

 

ልደቱ አያሌው በቀለ ገርባን ላለማስከፋት የበቀለ ገርባን ዘረኛነት አንድም ቃል ሳያነሳለት “ጋሼ” እያለ ውይይቱን ቋጨው

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

2/3/23

እንዴት አንድ እራሱን በፖለቲካ አለም ያስገባ እውቅ ፖለቲከኛ ሕዝብ የሚያደምጠውን ውይይት ገጥሞ እንዴት ዘረኛውን ላለመንካት ይጠነቀቃል? ናዚን የሚያስንቅ ኦሮሞዊው ናዚ እፊቱ ላይ ተደቅኖ እየተወያየው 30 አመት ስለ እምናውቀውን ስርዓት ማውራት ምን ይባላል? “ኩሽ” ሚዲያ እያለ ራሱን የሚጠራ ወደ ኋላ ተመልካች የሆነ እጅግ የደደበ ጽንፈኛ ጸረ ምኒሊክ እና ጸረ አማራ ፕሮፐጋንዳ የሚነዛ በፋሺሰቶች ቅኝት የሚቃኝ “ቆዛሚ ሚዲያ” ላይ የተጋበዘው ልደቱ አያሌው በቀለ ገርባን የመሰለ ናዚ ኣይነት ጸረ አንድነትና ጸረ ፍቅር ያጋልጠዋል ብየ ስጠብቅ ውይይቱ ሁሉ በቀለ ገርባን ሳያጋልጥ ሁሉም በሚያውቀው ችግር ብቻ እያወራ በቀለ ገርባን ላለማስቀየም ሲል ዘረኛው በቀለ ገርባን እየተጠነቀቀ “ውይቱ ሁሉ “በጋሼ ጋሽየ”  ተጠናቀቀ።

በዛው ሚዲያ ሁለቱም ሲጋበዙ ልደቱ ውይይቱን መጀመር የነበረበት ሂትለር በሚመስለው በራሱ በበቀለ ገርባ አስተሳሰብና አዋጅ ነበረበት። አለመታደል ሆኖ ልደቱም እዚህ ውጭ አገር ባለፉት 27 አመት እንደ ባለፉት እኛን ባሰለቹን “ተሞዳማጅ” ተቃዋሚዎች ልደቱም በቀለ ገርባን ላለማስቀየም አንድም የበቀለ ገርባ ዘረኛነት ሳያጋልጥ “መንግሥት” ወደ እሚባለው እየዘለለ ጊዜው አጠፋ።

ናዚው የደም ጥራት መርማሪው በቀለ ገርባ ካሁን በፊት አዲስ አባባን ለኦሮሞ ባለቤትንት ለማድረግ ከ5 ኦሮሞ ድርጅቶች ጋር ሆኖ ያወጣው ሰነድ ወደ ጎን ልተውና፤ ብግልም LTV ጋዜጠኛ ቤተልሔም ታፈሰ ከምትባለዋ ኦነጋዊ ሴት ጋር ተጋብዞ  አዲስ አበባ” የኦሮሞ ናት፤ በሚል የአብይ አሕመድ “ኦፒዲኦ” እና ሌሎች አራት ኦሮሞዊ ፓርቲዎች ያወጡት አዋጁ ለማብራራት ጠይቃው እንዲህ ይላል፡ “100 ዓመት በፊት አዲስ አበባ የኦሮሞ ነበረች።” ይላል። ጋዜጠኛ  ወሰን ሰገድ /ኪዳን ይህንን የበቀለ ገርባ አባባል ገርሞት አንድ ኦሮሞ አዛውንት ስላነጋገራቸው እንዲህ ይላል፦

<<ይህ ምላሻቸው ገረመኝ፡፡ መገረም ብቻ አይደለም፡፡ 5 ስድስት ዓመት በፊት የገጠመኝን ትልቅ ቁምነገር አስታወሰኝ፡፡ ያኔ ወደ ኦሮሚያ ክልል ገጠር የመሄድ ዕድል አግኝቼ ነበር፡፡ እዚያ ካገኘኋች የኦሮሞ አባቶች መሃል በአንደበተ ርቱዕታቸው ያስገረሙኝን አዛውንት ጠጋ ብዬ ጠየቅኳቸው፡፡ ኦሮሚያ ስለሚባለው ክልልና ስለኦሮሞ ብሔር አሰፋፈር ቃል በቃል ባይሆንምክልል የሚባለውን እርሳውየሚል ዓይነት መልስ ነበር የሰጡኝ፡፡ እናምሉከ መሌ ብየ እንቀቡየሚል ተረት ነገሩኝ፡፡እግር እንጂ ሀገር የለኝምማለት ነው ትርጉሙ፡፡እግሬ የደረሰበት ሁሉ አገሬ ነውአሉ እጅግ የረቀቀና የሚያስደምም ማብራሪያ ሰጡኝ፡፡ፈጣሪ ለሰው ልጅ ድንበር አልከለለም፤ ወሰን አላበጀምየሚል አንደምታ የለው ነበር ማብራሪያቸው፡፡በእኚህ አዛውንት ጥልቅ ማብራሪያ የተነሳ (ኦሮምኛ ቋንቋ ባልችልም) አባባላቸውን ልረሳው አልቻልኩም፡፡ አንድ ቀን፣ ከዕለታት አንድ ቀን አባባላቸው በውስጤ ሲብላላ ከርሞ ግጥምመልክ ፈንድቶ ወጣ፡፡ሉከ መሌ ብየ እንቀቡየሚል ግጥም ፃፍኩ፡፡

ከዚያ ጊዜ ወዲህ ኦሮሞ፣ በተለይም የኦሮሞ አዛውንቶች ጥልቅ አሳቢዎች እንጂጠባብአለመሆናቸውን አስባለሁ፡፡ በሰውነት ደረጃ እንጂ በብሔር ማዕቀፍ እንደማይሰቡ፣ ምድር በሙሉ የሰው ልጅ እንጂየእከሌወይምየእኔየማይሉ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ ከዚህ ትልቅ ነገድ የወጡ የዘመኑ ፖለቲከኞች ናቸው እንግዲህ ከክልልም ወርደውአዲስ አበባንበጠባብ አጥር ውስጥ ለመቀንበብ የሚከጅሉት፡፡ ለዚያውም በማያሳምን መልኩ፡፡ አቶ በቀለ “….አዲስ አበባ ዓመት ከመቶ በፊት የኦሮሞ ነበረችነው ያሉት፡፡ ከዚያ በፊትስ? … የሚል ጥያቄ ቢከተል ምላሻቸው ምን ሊሆን  እንደሚችል እንጃ፡፡እኚያ አዛውንት ግንፈጣሪ ለሰው ልጅ ድንበር አልከለለም፤ እግሬ የረገጠበት ሁሉ ሀገሬ ነውነው ያሉት፡፡ ሌላውም ሰው የተባለ ሰው እግሩ የረገጠው (እሳቸው የሚኖረበት ኦሮሚያ ክልልም ቢሆን) ሃገሩ ነው ማለታቸው ነው፡፡ አቤት ርቀታቸው…..!፡>> ይላል ጋዜጠኛ ወሰን ሰገድ /ኪዳን።

በብልጽግናው ሽመልስ አዱኛ አባባል ወለጋ በሚባል ቦታ መሽጎ << ነብሰጡሮችን የሚያርድ “አታቪሰቱና” ገብረ ሰዶማዊውና የሰው ስጋ አርዶ የሚበላ >>  ኦነግ የተባለው አደገኛ ስብስብ ደጋፊ የሆነው የበቀለ ገርባ ደጋፊነት በሚመለከት “ልደቱ አያሌው” የበቀለ ታሪክ እያወቀም ቢሆን  አንዲትም ቃል አላነሳለትም። ለምን? የልደቱና የበቀለ ገርባ ውይይት “እርባናው” ምንድነው?

በቀለ ገርባ አዲስ እስታንዳርድ ከተባለመ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ እናስታውስና ወደ ከፋው ዘረኛነቱን እንገባለን”። እንዲህ ይላል

I don’t believe in the idea of the unionists….’

‘For example people complain that we are not able to work in the regions because we don’t know the language. In the first place you are there because you want to sell your knowledge, your skill and your service, is that not? If I went to Tigray to sell my knowledge, my skill or to sell my expertise then I have to interact with the people who want to be served in the language they understand. Nobody is disallowed to work there. But the only thing is serve these people in the language they understand.’ “

ይላል። በቀለ ገርባ አማርኛና አማሮች ኦሮሞ ካልተናገሩ ግብይት ንፈግዋቸው የሚል በቀለ ገርባ አጋራዊ የመገናኛ ቋንቋ ሆነውን አማርኛ ይጥፋ ካለ በላ ሕዝቡና ሃኪሙ በምን ቋንቋ  ይገነጋገር?

ኢሳት ከተባለው ጋር ቃለ መጠይቅ ሲያደርግም እንዲህ ብሎ ነበር፦

<< የኦሮሞ ህዝብ በአንድ ብሄር ስር ተጽኖ ተደርጎብን፤ ተገደን ነበር። አማራው ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል >>

ሔዋን ማንደፍሮ የተባለች ጸሐፊም በቀለ ገርባ ከእስር ተፈትቶ ሲወጣ አማራ ኦሮሞን ይቅርታ  ሊጠየቅ ይገባል ሲል ሰምታው ብላ ነበር፦

<< እንዴት ሰው ይህን ያክል ግፍ ቀምሶ ሲወጣ ከዘር ባልወረደ ሃሳብ ተመልሶ ብቅ ይላል??? ስር ቤት አንደ ሰው እንዲያስቡ የሚያረግ ተስፈ ነበረኝ። ይች ሃገር የማናት ብለው ራሳቸውን ጠይቀው ለየት ያለ መልስና አቋም ይዘው ቢወጡ ምን በኮራንባቸው ነበር። መልሰው አዛው ነክረውናል።>>  ብላለች።

አሁን ወደ ከፋው የበቀለ ገርባ የናዚ ባህሪያትን እንመለክትና ልደቱ አያሌው ይህንን የበቀለ ገርባ ባሕሪ እያወቀ “በጋሼ፤ጓሽዬ” ውይይቱን ለምን ደመደመው? 

በቀለ ገርባ “ኦሮሚያ ኔት ወርክ” ከተባለው ጋር ኦሮሞ ሕዝብ ሰብስቦ እንዲህ አለ፡ ተርጓሚው “ዘውዱ ታደሰ” በቀለ እንዲህ ይላል፡-

                   ኦሮሞ ሕዝብ ደሞዝ እንኳ ሲቀበል አንድ ፤ ሁለት እያለ ገንዘቡን እንዳይቆጥር። በክልላችን ብዙ ብሔር ብሔረሰብ አለ፤ ነገር ግን እኛ በክልላችን ኦሮምኛ ብቻ ከተናገርን እንዲሁም በትምህርት ቤት ከኦሮምኛ ውጪ ሌላ ቋንቋ እንዳይማሩ ወይንም እንዳይናገሩ ካደረግን ኦሮምኛ ብቻ የሚናገር ሰው እናበዛለን።በኦሮሚያ ክልል የሚኖር የሌላ ብሔር ነጋዴ ካለ ዕቃ ልትገዛ ስትሄድ በኦሮምኛ “ስንት ነው?” ስትለው በሌላ ቋንቋ ካናገረህ ደህና ሁን ብለህ ሂድ! ነገም ድገመውና በኦሮምኛ ዋጋውን ጠይቀው፤አሁንም በሌላ ቋንቋ ከመለሰልህ ሳትገዛ ተመለስ።እንዲህ ሦስት አራት ቀን ስተደጋግመው ወይ “ክልሉን ለቅቆ ይወጣል” አልያም “የኛ ሰው የሆነው አስተረጓሚ ቀጥሮ ንግድ ቤቱን በቋንቋችን አነጋግሮን” እንገበያያለን።……

……..ከሁሉም አሁን ልጆች እያበላሸን ያለው፡  አባት ኦሮሞ ይሆን እና እናት አማራ ወይንም ትግሬ ወይንም ወላይታ ጋር እየተጋባን ነው ትልቅ ችግር እያስገባን ያለው።በዚህ ምክንያት ልጆቹ ቋንቋቸውን ሳያውቁ እያደጉብን ነው። ሰብሰባ ላይ በሌላ ቋንቋ መነገር የለበትም። ይህ ለቋንቋችን ዕድገት ይጎዳል።ፍንፍኔ ውስጥም ሆነ ሌላ ቦታ ሆቴል ውስጥ ማስተናገድና መስተንገድ ያለብን በቋንቋችን ነው።መናሃርያ ውስጥ ታክሲ ውስጥ በቋንቋችን ማስተናገድ አለብን።    

በመቀጠል በቀለ ገርባ አዲስ አበባ ውስጥ “ስለ ኦሮሞ ቋንቋና ባህል እድገትበኦሮሞ ባህል ማእከል የተካሄደ የፓነል ውይይት  08/07/2011 (March 2019) ተካሂዶ ነበር። ዋና አላማውም የኦሮሞን ቋንቋና ባህልአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ” ማሳደግን ዐቢይ ዓላማው አድርጎ የተቋቋመው የኦሮሞ ቋንቋና ባህል ቦርድ፣ ምሁራንና የማህበረሰቡን ልዩ ልዩ አካላት ያሳተፈ የፓነል ውይይት  ከተጋበዙት የመድረኩ ዋና ተናጋሪ መካካል በቀለ ገርባ ነበር።

 እንዲህ ብሎ ነበር፡

<< ከአማራ፣ ከትግሬ፣ ከጉራጌ፣ ከሶማሌ፣ ከከምባታ፣ ከአፋር፣ .. ከወላይታ ጋር ጋብቻ  እያደረግን ነው ትልቅ ችግር የሆነብን >>ከሶስት ወይም ከአራት ዓመታት በፊትና አሁን ያለውን ብንወስድ፣ የኦሮሞን ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ቁጥር አሁን አዲስ አበባ ውስጥ ለውጥ አለ ወይስ የለም? “ለውጥ አለ” (የአድማጮች መልስ)፡፡ በየሄድንበት ሁሉ የኦሮሞን ቋንቋ ነው አይደል የምንሰማው አሁን? ለምን ይመስላችኋል? የቋንቋው ደረጃ (ስታተስ) ስለተለወጠ ነው፡፡ ደረጃው ነው የተለወጠው፡፡ ደረጃው ደግሞ አንድምበስልጣን የሚመጣ ነው፤ በፖለቲካ ስልጣን”፡፡ የፖለቲካ ስልጣን! አሁን ያሉት ይጥቀሙንም፣ አይጥቀሙንም፣ ምንም ይሁኑ ምንኦሮሞ መሆናቸውን” ብቻ ሰዎች ያውቃሉ፡፡ እናምሰዎቹ እንዲህ ናቸው፤ይላሉ፡፡ አሁን ይህ ቋንቋ ይፈለጋል፤ ገበያ አለው፡፡ ነገ ከሌለን [ስልጣን] እዚህ ቦታ ላይ አይኖርም፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት በታክሲ ስትሄዱ፣ ወይም ሌላ መኪና ስትሳፈሩ፣ ወይም አውሮፕላን ውስጥ ስትገቡ ከአንድ ቋንቋ በስተቀር የሚዘፈን የለም፡፡ ናዝሬት ብትሄዱ፣ ጎባ ብትሄዱ፣ ነቀምት ብትሄዱ፣ ሻሸመኔ ብትሄዱ፣ አዲስ አበባ ብትመጡ፣ አንድ ቋንቋ ብቻ ነው የሚዘፈነው ታክሲ ውስጥ፣ገገው፣ ገገውይላል፡፡ አሁን ሁኔታ የለም፤ ብዛት የለውም፡፡ አቅም ነው፤ አቅም ስለተለወጠ ነው፡፡ አቅም ሲለወጥ ቋንቋችንም እየተለወጠ ይሄዳል፡፡ ስልጣን እያገኘ ይሄዳል፤ ጉልበት እያገኘ ይሄዳል፡፡ የፖለቲካ ስልጣን የምንፈልገው ለዚህ ነው፡፡ መጥፋት አንፈልግም፡፡ ቋንቋችን እንዲጠፋ አንፈልግም፡፡ ስለዚህ ስልጣን መያዝ የቋንቋችንን ደረጃ ይለውጣል፡፡ ወደ ላይ ከፍ ያደርገዋል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አሁን ላስረዳችሁ እንደሞከርኩት፣ ከጥቂት ዓመታት በፊት ባካሄድኩት ጥናት የሚመስል ነገር እንደተረዳሁት፣ እናንተም ከህዝብ ቆጠራ ሰነድ ማግኘት እንደምትችሉት፣ ኦሮሚያ ውስጥ ያሉ የወላይታ ሰዎችና ኦሮሚያ ውስጥ ያሉ የትግራይ ሰዎች ቁጥር እኩል ነው፡፡ እኩል ነው፡፡ ሆኖም የወላይታ ዘፈን አትሰሙም፡፡ ድምጻቸው አይሰማም፡፡ የሉም፡፡ የሌሎቹን ግን እንሰማለን፡፡ ይሄ ለምን/እንዴት ሊሆን ቻለ? ኤኮኖሚ ነው፤ የገንዘብ አቅም ነው ያለው፤ የፖለቲካ አቅም ነው ያለው፡፡ የኤኮኖሚ አቅም የሚኖረን ከሆነ ቋንቋችን ይጠነክራል፡፡ የፖለቲካ ጉልበት (ስልጣን) ካለን ቋንቋችን ይጠነክራል፡፡ ያለበለዚያ የኛ ቁጥር ይህን ያህል ነው፣ እኛ ይህን ያህል ሚሊዮን ነን፣ እንዲህ ሆነን፣ እንዲያ ሆነን ብንል ዋጋ የለውም፡፡ ማድረግ በሚገባን ነገር ላይ በርትተን መስራት ከሁላችን የሚጠበቅ ነው ማለት ነው፡፡

በቀለ ገርባ በዛው ስብሰባ ልክ ሽምልስ አዱኛ እንደተናገረው አማርኛን ለማስወገድ ሌሎች ክልልኦች ኦሮምኛ አሳስገናል እንዳለው በቀለ ገርባም የሚከተለው ብሏል።

  << ቋንቋችን ወደሚቀጥለው ክፍለ ዘመን እንዲሻገር የምንፈልግ ከሆነ፣ ብዛታችንን፣ ዲሞግራፊያችንን መጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ዛሬ በማንጠቅምባቸው ቦታዎች (ጉዳዮች) ውስጥ ሁሉ ሰብረን ልንጠቀምበት ይገባናል፡፡ ነገ ዛሬ ከምንጠቀምበት ድንበር አሻግረን ልንጠቅምበት ያስፈልገናል>> ። ብሏል።

ስለዚህ ይልና በመጨረሻ 

<<ከራስ ማህበረሰብ ውጭ የሚፈጸም ጋብቻ፣አንድን ቋንቋ ከሚገድሉ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው ብለናል።ለአንድ ሰው የስራ መስክ ከፈታችሁ ወይስ አልከፈታችሁም ዝም ብለን እየተነሳን ብንጮህ፣ ይህቺ ሰውዬ ቋንቋችንን አትናገርም፣ ምንምን እያልን፣ቤቱን ማስዘጋት ነበር”፣ ማናምን ከምንል፣ ምን እዚያ አደረሰን፣ ምንስ አስዘጋን፣ ገንዘባችን ኪሳችን ውስጥ ነው ያለው፣ መግዛት ከሚገባን ቦታ ሄደን አንገዛም? እሱእራሱን ይዘጋው የለም እንዴ?” ስለዚህ በብልሃት መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ስለ ቋንቋችን ጉዳይ፣ በጥንካሬ፣ በብልሃት፣ በእውቀት ተመርተን ስራ መስራት ይኖርብናል፡፡ … >> (በቀለ ገርባ)

ልደቱ ሊደፍረው ያልፈለገው ነገር፤ << ጋሼ በቀለ ነገዶች በራሳቸው ቋንቋ ይጠቀሙ መብታቸው ነው ብለሃል፤ ትክክል ብለሃል >> ይላል ልደቱ። ገራሚው ልደቱ አያሌው  ግን በቀለ ገርባን ሊነግረው የሚገባው ነገር የሰው ልጆች መስተጋብርና ውህደት በሚጻረር የናዚ አስተሳሰብ “<<ከራስ ማህበረሰብ ውጭ የሚፈጸም ጋብቻ ኦሮምኛን ስለሚያጠፋ ኦሮሞ ካልሆኑ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ጋር ጋብቻ እንዳትፈጽሙ.. ብለሃል፡ በንግግርህ ብዙ ሰው እንደለያየ እገምታለሁ ፤ ይህ በሕግ የሚያስጠይቅ ቢሆንም ለጊዜው ግን ይቅርታ አልጠየቅክም ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መጠየቅ አለብህ ብሎ ከመመለስ ይልቅ “ጋሼ በቀለ ትክክል ብለሃል፡ ጋሽየ ጋሼ ውስጥ ገብቶ ሲዳክር ነበር።

ቋንቋን ለማሳደግ በሚል ሽፋን የሰው ልጅ የተፈጥሮ ሕግጋትን በሚጻረር መልኩ <<ከራስ ማህበረሰብ ውጭ የሚፈጸም ጋብቻ ኦሮምኛን ስለሚያጠፋ ኦሮሞ ካልሆኑ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ጋር ጋብቻ እንዳትፈጽሙ ልጆችም እንዳትወልዱ እያለ በግሃድ የሚሰብክ ጸረ የሰው ልጆች አንድነትና ውህደት የሚሰብክ ናዚዊ በቀለ ገርባ በልደቱ ቅልስልነትና ጓሼ ጋሽዬ” ባይነት በቀላሉ ሲታለፍ “ዘረኞችን” ማን ያጋልጣቸው? ዛሬስ ልቤ ሁሉ እየተቃጠለ ለማን ፖለቲከኛ አቤት እንደምል እየጨነቀኝ መጥቷል።

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

ልዩ ቆይታ ከአንጋፋ ፖለቲከኞች ጋር

https://www.youtube.com/live/mB10xu2P_Zg?feature=share