Friday, May 8, 2009

የወያኔ መኢሰኖችና የኩዴታዉ አስቂኝ ተዉኔት

የወያኔ መኢሰኖችና የኩዴታዉ አስቂኝ ተዉኔት ጌታቸዉ ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com “ወያነ ትግራይ” በማለት ራሱን የሚጠራ “የታሪክ ነቀዝ”- ግንቦት 7 የተባለዉ (የወያኔ መኢሶን )መንሥትነቴን ለመጣል መፈንቅለ መንግሥት ሊያካሄድብኝ ያቀደዉን ሴራ አከሸፍኩባቸዉ ሲል በራሱ ጋዜጦች ይፋ ማድረጉን ይታወሳል። እዛዉ በዛዉ የዋሸዉን ዉሸት ሳይደርቅ- የተወጠነዉ ሴራ መንፈንቅለ መንግሥት ሳይሆን ባለሥልጣናቶቼን ለመግደል የታቀደ ሴራ ነበር ሲል እንደገና ተመልሶ ራሱ በራሱ ሲያምታታ ተደምጧል። ላማስረጃም ከአባሎቹ በብርበራ ተገኘ ብሎ በእግዝቢት የያዛቸዉ ልዩ ልዩ ጠመንጃዎችና ቦምቦች በራሱ ቴሌቪዥን ለሕዝብ እንዲታይ አድርጓል። ዕድሜ በረዘመ ቁጥር አንድ ድርጅት/መንግሥት/ቡድን… “በፊት” ሲከተላቸዉ ከነበሩት ከተጋለጠበት ተራ ብልጣብልጥ አሰራሩ በሚቀጥለዉ የዉሸት/የቅጥፈት/ያጭበርባሪነት እና የብልጣብልጥነት አሰራሩ ልቀጥልበት ካለም ፣“መንገዱ ስልቱና ዓይነቱን”ቀይሮ የተቀናቃኞቹን የፖለቲካ ፊኛ ማስተንፈስ ማዳከም፣ ማሳጣት(ማጋለጥ-) ሲችል ወያኔ ግን ለ34ዓመታት ሙሉ የተከተለዉ “የዉሸት-መንገድ”ዛሬም ስልቱና ዓይነቱን ሳይቀይር በተለያዩ ተቀናቃኞቹ ላይ በዛዉ በለመደበት የዉሸት ስልቱ ሲወነጅላቸዉ ስናይ እዉነትም የጫካ ሕሊናዉ አሁንም እዛዉ እንደጫጨ መሆኑን አመላካች መረጃ ነዉ። ለብዙ ዓመታት ከበረሃ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ተቀናቃኞቼ ሲዶሉቱብኝ ደረስኩባቸዉ ያለባቸዉን መረጃዎቹ 95%በዉሸት ያቀነባበራቸዉ መረጃዎች ናቸዉ። የጫካ ባሕሪዉ በቅርብ የተከታተሉና ማሕደሮቹን ያነበበ ሁሉ በቀላሉ መገንዘብ ይችላል። ለምሳሌ ህወሓት በጫካ ዘመኑ “ጃሱስ ማንጁስ ዴማ”(ማንጁስ እና ጃሱስ የሚሉ ቃላቶች የዓረብ ቃላቶች ሲሆኑ ወያኔ ቀልቡ በኤርትራ ቡዱኖች “ፕሮፖጋንዳ፣አሰራር አነጋገርና አጻጻፍ” ሰክሮ ስለነበረ ከነሱ ተበድሮ እስካሁን የሚጠቀምባቸዉ ከበርካታዎቹ የዓረብ ቃላቶች ጥቂቶቹ ናቸዉ- ማንጁስ ማለት “ትንሽ ልጅ/አሽከር’ያልጠና’/ኩታራ” ማለት ሲሆን “ጃሱስ” ደግሞ “ሰላይ”ማለት ሆኖ “ዴማ/ዳይማ”ደግሞ ትግራይ ዉስጥ በዓዲግራት አካባቢ/አሲምባ…. እና ዕዳጋሓሙስ የተባሉ ቦታዎችን ያማከለ ተራራማ ቦታ ነዉ- ቦታዉ ከደደቢት ቀጥሎ ወያኔ ለስልጠና ጣቢያ ያዘጋጀበት ቦታ ነበር-የመጀመሪያዉ ጠቅላላ ጉባኤዉ ያደረገበትም እዚህ ነበር)- በማለት ወያኔ የሚጠራዉ የዴማዉ ሰላይ “የ12 ዓመት ወጣት ህጻን ልጅ” ነዉ። ይህ ህጻን (1) በደርግ ተልኮ በስለላ ተግባር ተሰማርቶ የህወሐትታጋዮች ከሚጠቀሙባቸዉ የዉሃ ኩሬዎች መርዝ እንዲጨምር የተላከ ነዉ፤ በማለት እየደበደቡ ‘አዎ ተልኬ ነዉ የመጣሁት በል” እያሉ በማሰቃየት፣- (2) ታጋዮቻችን ወደ ደርግ ዓላማ ለመሳብ በስለላ ተግባር ተሰማርቶ ሲያደራጅ ያዝነዉ በማለት፣ ሸዊት በተባለዉ ታጋይ እና በወያኔዎቹ አባት ስብሓት ነጋ ታጋዮቹ በሙሉ ሲመረመሩ ምንም ማስረጃ ማግኘት ስላልቻሉ ገበሬዉንም በክሎታል በማለት ገበሬዎች እና ቄሶች ሳይቀሩ በሰበቡ የድብደባ ምርመራ ከተካሄደባቸዉ በሗላ ምንም ምንጭ ስላላገኙ በመጨረሻ እንዲረሸን የፈረዱበት “መሓመድ”የተባለዉ ይህ ህጻን እና ሌላዉ ወጣት በሃሰት እንዴት እንደረሸንዋቸዉ ካሁን በፊት በፊታዉራሪ ገዛ ረዳ ቃለ መጠይቅ እንዳስነበብኳችሁ ይታወሳል። ከተማ ገብቶ የመንግሥት ሥልጣን እንደነጠቀም ደ/ር ታየ ወልደሰማያትን ከዉጭ አገር ጉብኘት እንደተመለሰ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ ሲመለስ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ላይ ያያዘዉ ሻንጣ ሲፈተሽ ታጣፊ መሳርያ አገኘንበት በማለት ለ6ዓመት በሃሰት አስሮ እንደለቀቀዉ የምታዉቁት ታሪክ ነዉ። የሓሰት ምስክሮቹም በማናቀዉ ጉዳይ ላይ በሓሰት አንመሰክርም በማለታቸዉ የደረሰባቸዉ ስቃይ በወቅቱ የተለያዩ ጋዜጦች ዘግበዉት እንደነበር ይታወቃል። ሌላዉ ስለ የወያኔ የዉሸት ቀፎነት በዚህ “በኢትዮጵያን ሰማይ- በሎግ” ላይ ያቀረብኩላችሁ የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን የሰጡትን የወያኔ አሰራር እና ሰዉን ፣ድርጅትን እንዴት አድረጎ በሓት እንደሚወነጅል በሰፊዉ ተመልክተናል። ከዚህ ሌላ በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ላይ የደረሰዉ በመንግሥት ግልበጣ የሓሰት ዉንጀላ (በሙት ዓመታቸዉ በዚህ ወር ዝርዝሩ አቀርብላችሗለሁ)-ታሪክ ወያኔ የሓሰት ምስክሮች እንዴት እንዳዘጋጀ የራሱ የወያኔ ታጋይ እና የደህንነት ሰራተኛ የነበረዉ በሗላ ከድቶት ወደ ኤርትራ እጁን በመስጠት ይህ ጉዱ ስላጋለጠዉ እና ለወደፊቱም በምስክርነት እንዳይቀርብ በማለት ስለሰጋ - ወያኔ ተከታትሎ በ2000 ዓ.ም ላይ ጋሽ- ባርካ ላይ እንዳስገደለዉ የሚወራዉ “ፍስሃ ሃይለማርያም””-የተባለዉ በሁኔታዉ እራሱ የተሳተፈበት የምርመራ ቅንብር የሰጠዉ ምስክርነት በYou Tube” ቴሌ ቪዥን የቀረበዉ ማስረጃ በማየት የወያኔ ማንነት መገንዘብ ይቻላል። ስለዚህ ወያኔ በዉሸት የፋፋ የዉሸት ቡድን እንደሆነ የሚታወቅ ነዉና ስለ ወያኔ የመፈንቅለ መንግሥት አስቂኙ ተዉኔት እዚህ ትትን ይልቁን እኔ የገረመኝ “ሙሉነህ እዮኤል” የተባለዉ ሌላዉ የግንቦት 7 አመራር አባል ነዉ የሚባልለት ወጣት በዚሁ የሰሞኑ አስቂኝ የመፈንቅለ መንግሥቱ ጋር የተያያዘ ስለ የድርጅት አለቆቹ እነ ብርሃኑ እና “አንዳርጋቸዉ ጽጌ” (በትናቸዉ ጽጌ) የጻፈላቸዉ የአርበኛነት ምስክርነት ገርሞኝ እሱን አንድ ለማለት ነዉ። ከዚህ መፈንቅለ መንገሥት የተባለለት የዉሸት ቅንብር ተያይዞ በር ተከፈተልን በማለት የግንቦት 7-ሰዎች ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ እየተጠቀሙበትም እንደሆነ ግልፅ ነዉ። በግረመንገዳቸዉም የገንዘብ ማሰባሰብያ በር ከፍቶላቸዉ እንደለመዱበት መከረኛዉ የአዉሮጳ እና የዲ.ሲ ስብሰባ 6 እና 7 ሰብሰባዎች እናካሂዳለን በማለት ጥሪ እያስተጋቡ ነዉ። ከዚህ በተያያዘ ሰሞኑ ደግሞ ታክቲኩ ሁሉ አልሰራ ሲል “አርበኛ”-የሚለዉ ቃል- “የሰሞኑ ባለ ተራ ቅመም” ሆኖ “እገሌ አርበኛ” በማለት በየመድረኩ ማንበብ ጀምረናል። ሁለት የወያኔ ተቃዋሚ ነን የሚሉን ጠንካራ ድርጅትን እና በጋራ የመስረሳትን ጅማሮ ያደፈረሱት “የዛኛዉ ጎራ” ታዋቂ ሁለት ሰዎች በተከታታይ ባጋጣሚም ይሁን በተጠና መንገድ የየራሳቸዉ ሰዎች “በአርበኛነት”-በማቆላጰስ ወደ ሚዲያዉ መድረክ አቅርበዋቸዋል። አንደኛዉ እዚህ የተቸሁበት ፕሮፌሰር አለማዮሁ ገብረማርያም ስለ ደ/ር ሃይሉ አርአያ አርበኝነት ሲሆን፣ በተከታታይ ደግሞ “የግንቦት 7”-ሦሰተኛ ሰዉ ነዉ የሚባልለት “ሙሉነህ እዮኤል”የተባለዉ በጸረ አማራነት የታወቀዉ ፣አማራን ለመበተን የኢትዮጵያን አንድነት ለማደፍረስ ለወያኔ አድሮ “የአማራ ሕዝብ ከየት ወደየት” በማጻፍ የታወቀዉ በብዙ ወገኖች “በትናቸዉ ጽጌ” በመባል የሚታወቀዉ “አንዳርጋቸዉ ጽጌ”ን “የአርበኛ ልጅ አርበኛ” በማለት ሲያቆላጵሰዉ አንብበናል። የ80ዓመት አዛዉንት ናቸዉ የሚባሉት የአንዳርጋቸዉ ወላጅ አባት አቶ ጽጌ ሰሞኑን መንግሥቴን ለማወክ ያዝኳቸዉ በማለት ትግራይ ዉስጥ አዛዉንት ወላጆቻችን እና ወንድሞቻችንን ያስር ይደበድብ ይረሽናቸዉ እንደነበረዉ ሁሉ ዛሬም ጉደኛዉ እና ዉሸታሙ ወያኔ እኝህ አዛዉንት ካሰራቸዉ ዜጎች አንዱ ሲሆኑ መሆናቸዉን ከልብ እናዝናለን።ጉዳቱ ካሁን በፊት በኛ በቤተሰቦቻችን እና ወንድሞቻችን ትግራይ ዉስጥ ደርሶብናል እና የሕሊና ቁስሉ እና ከባድነቱ ይገባናል።በዚህም በአንዳርጋቸዉም ሆነ በብርሃኑ ቤተሶበቻቸዉ የሚደርሰዉ እንግልት እንቃወመዋለን። ሆኖም፣-ይህችን ቀዳዳ በመጠቀም “ለወያኔ በማደር ያገሪቱ ሰራዊት ሜዳ ላይ ሲበተን፣ ዜጎቻችን ከኤርትራ ተባርረዉ በባዶ እግራቸዉ ተጉዘዉ አዲስ አበባ መጠለያ አልባ ሆነዉ ሲንከራተቱ አፋቸዉ የከደኑ ብቻ ሳይሆን ለመከራዉ አስተወጽኦ ያደረጉ፣ በሺዎቹ ታፍነዉ እነሱ ባዘጋጁት እስር ሲሰቃዩ ፣ በወቅቱ በስቃዩ ላይ ደስታን የጎነጩ፣ የኢትዮጵያን አንድነት በማፈራረስ ከፍተኛ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳና አስተዋጽኦ በማድረግና በመዲናይቱ ምክትል ከንቲባነት እና በመሳሰሉት ከፍተኛ ስልጣን በመመደብ ወያኔን እና ራሳቸዉን በመንግሥትነት አደላድለዉ ከታወቀዉ የኢትዮጵያ ጠላት ባንዳዉ መለስ እና ታምራት ላይኔ አፍላፍ ገጥመዉ ዊስኪ እና መጽሃፍ ሲዋዋሱና ሲጫለጡ የነበሩት አንዳርጋቸዉ እና ለስየ አብርሃ የመታሰቢያ መጽሀፍ የከተበዉ “ብርሃኑ ነጋን” በአርበኝነት ማቆላጰስ መቼም “ጋኖች አለቁና ምንቸት ጋኖች ሆኑ” ይባል የለ?። ሙሉነህ እዮኤል ሰሞኑን ያንዳርጋቸዉ ጽጌ ወላጅ አባት “በአስቂኙ መፈንቅለ መንግሥቱ”-የተያያዘ በመታሰራቸዉ ወላጅ አባትየዉ “አርበኛ”-ሲላቸዉ ለልጃቸዉ አንዳርጋቸዉን “የአርበኛ ልጅ አርበኛ”-በማለት የወላጅ አባቱን የአርበኛነት ማዕረግ ሲሸልመዉ እኔኑን ደነቀኝ። በተለይ-የመለስ ዜናዊ ወላጅ አባት “አቶ ዜናዊ አስረስን” “ባንዳ” ሲላቸዉ ልጃቸዉ መለስ ዜናዊን “የባንዳ ልጅ “ባንዳ” ብሏቸዋል። ይህ መቸስ በሽታ ነዉ። በሽታ ስላችሁ ሕክምና የማይፈዉሰዉ “የዘረኝነት በሽታ” ማለቴ ነዉ። እንዴት ነዉ ነገሩ ጭልጥ ያለ ነገር!? የአርበኛ ልጅ አርበኛ ይወልዳል ያለ ማነዉ? ብዙ ያርበኞች ልጆች ልጆቻቸዉ “ባንዳ” ሆነዉ አገራቸዉና ታሪካቸዉ ሲያበላሹ ታሪክ የተዘገበ ነዉ። ሙሉነህ እዮኤል ለፕሮፖጋንዳ ስራ ካልሆነ ወይንም የፖለቲካ አለቃዉን አንዳረጋቸዉ ጽጌን ለማስደሰት ካልሆነ ፣እንዳርጋቸዉ ጽጌ በአርበኝነት የሚያስጠራዉ አንድም ማስረጃ አላቀረበልንም። ታድያ እንዴት እንዴት ሲኮን ነዉ ያለ ማስረጃ አርበኛ ብለን አንዳርጋቸዉን የምንጠራለት? ሙሉነህ እዮኤል ወየኔን “ባንዳ” ነዉ ብሎታል፣- ወያኔ ባንዳ መሆኑን ካመነ- እንዴት ሲሆን ነዉ ያርበኛ ልጅ ለወያኔ ለባንዳዉ አድሮ ከሚገባዉ በላይ ወገቡን ለዘረኝነት ብቅል ሰጥቶ ዘረኝነት እንዲበቅልበት ፈቅዶ “የኦሮሞ ትዉልድ ሐረጉ እየመዘዘ -አማርኛ መናገሩን አንጂ አማራ እንዳልሆነ መጽሐፍ ጽፎ እየዘረዘረ አማራንና ኢትዮጵያዊነትን ያጥላላ ግለሰብ ያዉም’ኮ “ኢትዮጵያዊነት-የዘረ-ቢሶች መሸሸጊያ”-በማለት መጽሐፍ የጻፈ ፣ አማራ ሳይሆን “ስለ አማራ ሕብረተሰብ በመጥፎ ጎኑ መጽሐፍ የጻፈ”-መጪዉን ትዉልድ ሊያባላ የሚችል አደገኛ ጽሑፍ የተወልንን ሰዉ በምን ሂሳብ ነዉ በአርበኛነት ሊመደብ የሚችለዉ? የአርበኛ ልጅ በእንደዚህ ያለ ጉደኛ ታሪክ ራሱን ሲነክር አርበኛዉ አባቱ አይቀየሙትም ወይ? ሙሉነህ እዮኤል አማራ ቢሰደብ ባይሰደብ፤ ጉዳዩ አላለዉም፤ አለቃዉ “ኢትዮጵያዊያን ንነ የምንል ሁሉ “ብሔር የሌላቸዉ ዘረ-ቢስ ቢለንም” ሙሉነህ ጉዳይ አላለዉም። የሙሉነህ እዮኤል ሁለተኛዉ ያስገረመኝ ጽሑፉ ደግሞ ወያኔን “አምባ ገነን ቡድን” ማለቱ ነዉ።ለመሆኑ መኢሶን ደርግን “አምባገነን”-እንዲሆን “እንዳርጋቸዉ እና ጓዶኞቹ”” ወያኔንን “አምባገነን” እንዲሆን ዕድሉን የሰጧቸዉ አይደሉምን? ታዲያ ወያኔ አምባ ገነን እንዲሆን በከፍተኛ የፖለቲካ ቦታ ተመድቦ ያገለገለዉ አንዳረጋቸዉ “አርበኛ”-ማለት ዜጎችን አያስቆጣም? ሙሉነህ እዮኤል ወያኔ ትምህርት መቀጠል አለብኝ ካልክ ሂድ ቀጥል በሎ እንደተቀሩት በኬኒያና በባሌ በመከራ ተሸሽገዉ እና ተሰቃይተዉ ሳይሆን “በቦሌ” በክብር የሸኘዉን ወያኔን ምስጋና አይግባዉና እዚህ ድረስ አሸጋግሮ ፈቅዶ የጓደኛዉን የአንዳርጋቸዉ ጽጌን (ጓድ/ጓድ ቁልጵስ) አርበኛነት ማዕረግ ሊያስሰማን መብቃቱ እዉነት ወያኔ “ዉለህ አትግባ” ከማለት ምን ማለት ይቻላል? ሙሉነህ - አስቲ እንደዉ፣ እንደ ብጻዩ/ጓዱ እንደ ብርሃኑ መዋ ድምጹን አጥፍቶ ዉስጥ ለዉስጥ ስራዉ ቢሰራ ምን አለበት? በዚህ ጉዳይ እህቴ “አያልነሽ” በሚጣፍጠዉ አማርኛዋ በሚገባ ገልጻዋለችና ብዙም ለማለት አልፈልግም። ስለ አስቂኙ መፈንቅለ መንገሥቱ ግን አንድ ሁለት ብየ ልዝጋ። ለመሆኑ ብርሃኑ ነጋ በምን ሃሞቱ ነዉ አሜሪካ ተቀምጦ ጦር እያስላከ ወያኔን ለማስወገድ የሚሞክረዉ? ነገሩ ነገር ቢኖረዉም (መፈንቅለ መንግሥት ባይሆንም)-ከብርሃኑ ነጋ የተጠነሰሰ ሴራ እንዳልሆነ ብዙ ሰዉ ይገምታል ።ወያኔ አገዛዙ እየከፋ ስለሄደ በወታደሩም በሲቪሉም ወያኔን በሚችለዉ መንገድ ላለመታዘዝ መሞከሩ አያሌ የማይባል ነዉ። አዲስ ነገርም አይደለም። የብርሃኑ ሃሞት ግን ያየነዉ ነዉ። ድሮ በኢሕአፓ ታሪኩም ሆነ ዛሬ ሴት ልጅቷን ብርቱካንን አጋልጦ ካዲስ አበባ ሸሽቶ በዋሽንግተን -ዲሲ እና በአዉሮፓ በካናዳ የትኩሳቱ መልቀቂያ እና የጉራ መድፈቂያ መድረክ ተዋናይ ከመሆን ሌላ በምን መራራ ሃሞቱ ነዉ እንዲህ ዓይነቱ ስራ የሚሰራዉ? አይሞክርም ሳይሆን ብርሃኑ እና አንዳረጋቸዉ ለእነደዚያ ዓይነት ተልእኮ ዘሎ የሚገባ ሕሊና እና ሃሞት የላቸዉም! እመኑኝ! ከነሱ ይልቅ ሴቲቱ ብርቱካን መቶ በመቶ በወንድነቷ ምረጥ ቢሉኝ አማራጭ ካጣሁ እሷን እምርጥ ነበር። ወያኔ ዋሽቶ መወንጀሉ ላይቀር ዉሸቱን አሳምሮ ቢዋሽ እና የመኢሶኑ የ ዶ/ር ነገደ ጎበዜን የኩባዉና የየመን ሪፑብሊክ አምባሲዎች ትብብር በሌተናል ኮሎነል መንግሥቱ ሃይለማርያም የታቀደዉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ዓይነት ሲደረግ እጅ ከፍንጅ ደረስኩባቸዉ፣ ቢልና ብርሃኑ ነጋ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ወርዶ በደህንነት ጥበቃ ሰራተኛችን በመታየቱ -ለምን እንደመጣ ደህንነት ሰራተኛዉ ቢጠይቀዉ “የእርቅና የሰላም” ድርድር በሚመለከት ስብሰባ ለማድረግ በመንግሥት መጋበዙን ገልጾለት-ሲያበቃ ደህንነቱ ይሄንኑ ለማስታወቅ ወደ አለቃዉ ሄዶ ሲመለስ አጅሬ “ብርሃኑ ነጋ”-ስሙን ለጊዜዉ ለመግለጽ ያልፈለግነዉ በአንዱ በ----------አዉሮጳ አምባሲ አጃቢዎች ታጅቦ በምስጢር በመኪና ተወስዶ መደበቁን ደርሰንበት ደረግ ዶ/ር ነገደ ጎበዜን እንደሸኘዉ እኛም በድርድር አገር እንዲለቅ ሆኗል። ብሎ አሳምሮ ቢዋሽ ምንኛ ታሪኩ ተደማጭነት ባገኘ ነበር። ግን አልቻለበትም! · ብርሃኑም-አንዳርጋቸዉም-ወያኔንና መለስ ዜናዊን አገልገለዋል፣ አክብረዋል፣ አቆላጵሰዋል ዊስኪ ተጫልጠዋል።ሃይለ ፊዳ እና ጓዶኞቹም ሌተናል ኮሎኔል መንግሥቱን አገልገለዋል፣ አክብረዋል፣ አቆላጵሰዋል ዊስኪም ተጫልጠዋል። ስለዚህ እነ ብርሃኑ ነጋ እና አንዳረጋቸዉ “ግንቦት 7”ብለዉ ራሳቸዉን ቢጠሩም ሰዎቹ “የወያኔ-መኢሰኖች”ናቸዉና ከጓዳቸዉ ከበረከት ስሞን ጋር ሲማከሩ፣ ሲለሳለሱ እና ሲያቅማሙ የግንቦቱን ሕዝባዊ እሮሮ አክሸፉት (የቤት መቀመጥ አድማዉን ልብ ይለዋል)። ከወያኔ መኢሰኖች ብዙም አልጠበቅንም ትናንትም ዛሬም ነገም ። የደርጉ የሃይለ ፊዳ መኢሰኖችና እና የወያኔዎቹ የአንዳርጋቸዉ/ብርሃኑ “የወያኔ መኢሰኖች”-ልዩነታቸዉ የደረጎቹ መ ኢሰኖች ሃገራዊ አንድነት እንዳይላላ የታገሉ ኢትዮጵያዊነትን ያስቀደሙ ከዘረኝነት የጸዱ ሲሆኑ፣ የደርግን መነግሥት በጥበብ ለመጣል ደርግን የተደባለቁ ጊዜዉን ያላገናዘቡ ፖለቲከኞችና የደርግን ዙፋን የገነቡ ሲሆኑ”። የእነ ብርሃኑ ነጋ እና አንዳረጋቸዉ “የወያኔ-መኢሰኖች” ግን አማራን የሚጠሉ ዘረኞች፣ ለወያኔ ያደሩ ፣ ካለ ወያኔ በቀር በራሳቸዉ ህልዉና እና ፖሊሲ መቆም ያልቻሉ፣ ጥገኞችና፣ አገር ሲፈርስ ሮጠዉ አገር ገብተዉ ኩት… ኩት.. እያሉ የወያኔ አለቆችን ባሽከርነት እየተከተሉ “ባንዳዎች” ብለን ከምንጠራቸዉ የወያኔ መሳፍንት አለቆች ጋር ዊስኪ ሲያንቃርሩ “ፎቶ መነሳት” እንደኩራት የሚቆጥሩት “አሳፈሪዎች”፣ የባሕር በሮቻችን ሲዘጉብን ኡኡ ስንል ያማራ ትምክህተኞች እሮሮ እያሉ “ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ”-ሆነዉ የወያኔን ዉሳኔ ተቀብለዉ ያስተጋቡ ናቸዉ ። · ዋ! ዋ! ያዉም እኮ ፣ “የአርበኝነት የምስክር ወረቀት” በ$500 ዶላር እንሸጣለን በማለት በታሪክ ያልተሰማ. ያልተደረገ “ምጻእተ ዓለም / ጉድ!” አርበኝነትን ማዕረግ ችርቻሮ ገበያ ንግድ ዉስጥ የገቡ እኮ ናቸዉ!እናንት ወንድሞቼ/እህቶቼ፣-በኢሕአፓ አባሎችና ደጋፊዎቻቸዉ ጥረት.፣ መስተንገዶነት፣ ጽ/ቤት ቅርንጫፎቻቸዉ በአዉሮጳም በአሜሪካም ክፍት አድርገዉ እነ ሃይሉ አርአያም እነ ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዉልም እነ ልደቱ አያሌዉን አሰባስበዉ አስከ ቅንጅት ሕብረት ድረስ እንዲጎለብሱ እና ተበታትነን የነበርነዉን ህብረተሰቦች ጸረ ወያኔ ቆመን እንድንታገል ከጅምሩ የተተከለዉ የሕብረት ችግኝ ዉሃ አየርና እና ማዳበርያ ሆነዉ በማሳደግ፣ በማጠናከር ያደረጉት በታሪክ የማይረሱ ሸጋዎቹ “ኢሕአፓዎች” ከማመስገን ይልቅ (የብርሃኑ መዋ እና የአንዳርጋቸዉ ሴራ እንዳለ ሆኖ) ብርሃኑ ነጋ ከእስር እንደተፈታ ዉጭ አገር መጥቶ ዋሽንገተን ዲሲ አዳራሽ ገብቶ ከአፍዓበት የመጣ አርበኛ ይመስል “አበባ እና ዘምባባ ሲጎነጎንለት”-የመጀመርያ ዲስኩሩ ዘለፋ የጀመረዉ በወያኔ ሳይሆን “በኢሕአፓ”-ላይ ነበር ያነጣጠረዉ (ስልጡንና የፋራ ፖለቲካ በማለት-የስድቡ የሽርደዳዉ ጉንጉን ምን ይል እና ለማን ይዘልፍ እንደነበር የምናዉቀዉ እናዉቀዋለን)። በዚህ ዘዴ ነበር “የብተና ስራቸዉ የጀመሩት” ። · ቀጥሎ በወያኔ እና በኢሕአፓ ላይ እያደባለቀ ተደጋጋሚ የብተና ፕሮፖጋንዳዉ እና ስድቡ እንዳጦፈዉ በኢንጅነር ሃይሉ ላይ በተቀነባበሩ ዘረኞች በየመድረኩ እና በየሚድያዉ አስሰልፎ ጅላጅል ብርቱካንን ፊት-ፊት በማስቀደም እሱ ከሗላ ምን ማለት እንዳለባት እያጣደፈ ሕብረቱን በትኖ ሲያበቃ፣--ልጅቷንም ጥሎ አሜሪካኖች ገንዘብና ቀለብ ሰጥተዉት ሳትሰራ ሳትለፋ “ተራራ ላይ ወጥተህ ቁጭ ብለህ ተፈላስፍ” ብለዉኛል ብሎ እዚህ “ፋራዎች”-ከሚለን የፖለቲካ አዛዉንቶች ጋር ቀረ። የምስኪኒቷ ድርጅትም አስዋን ለእስር ዳርገዉ ኢንጅነር ሃይሉን አምባገነን ባሉበት አፋቸዉ ዛሬም በፕሮፌሰር መስፍን አፍ እርስ በረስሳቸዉ “አምባገነንነት እና ስርዓተ አልበኝነት ማን ያዘኛልነት እና ገለልኝነት” አዲሱን ፓርቲዋን ዉጦታል እያሉ በገዛ ብዕራቸዉ እየነገሩን ነዉ! · አንግዲህ ይህ ሁሉ አፍራሽ ተግባርና ባሕሪ ባጭር ጊዜ ዉስጥ ተጋግሎ የነበረዉ የሕዝቡ ወኔ እና ሕብረት ላይ “ቀዝቃዘ ዉሃ ሲቸልሱበት”ያረርነዉን እንዳይበቃ መላልሰዉ የሚጽፉት ፕሮፖጋንዳ እና ጉራ “ቁጣችንን የሚያበረድ ሆኖ አላገኘሁትም!”አሁንም አሁንም ጉራቸዉ ሰንጢ የማይበጣዉ ሆኖ አሜሪካ እና አዉሮጳ በመዞር እየተንገዋለሉ እነ አንዳርጋቸዉን “አርበኞች” በሉልን ሲሉን- በ እውነት እላችሗለሁ በመንገስቱ ሃይለማርያም ፊት ቆመዉ አንድ “ቄሱ”-እንዳሉት የዚህ ዕብጠት ትርጉም “እኔ- እየጠበበኝ መጥቷል”። በቻ ለማንኛዉም በወሎየዉ በሸኽ ጅበሪል ምርቃን/ሀድራ “አላህ ይሁናችሁ አላህ ይሁነና” ከማለት ምን ማለት ይቻላል?

የወያኔ መኢሰኖችና የኩዴታዉ አስቂኝ ተዉኔት

የወያኔ መኢሰኖችና የኩዴታዉ አስቂኝ ተዉኔ
“ወያነ ትግራይ” በማለት ራሱን የሚጠራ “የታሪክ ነቀዝ”- ግንቦት 7 የተባለዉ (የወያኔ መኢሶን ) መንሥትነቴን ለመጣል መፈንቅለ መንግሥት ሊያካሄድብኝ ያቀደዉን ሴራ አከሸፍኩባቸዉ ሲል በራሱ ጋዜጦች ይፋ ማድረጉን ይታወሳል። እዛዉ በዛዉ የዋሸዉን ዉሸት ሳይደርቅ- የተወጠነዉ ሴራ መንፈንቅለ መንግሥት ሳይሆን ባለሥልጣናቶቼን ለመግደል የታቀደ ሴራ ነበር ሲል እንደገና ተመልሶ ራሱ በራሱ ሲያምታታ ተደምጧል። ላማስረጃም ከአባሎቹ በብርበራ ተገኘ ብሎ በእግዝቢት የያዛቸዉ ልዩ ልዩ ጠመንጃዎችና ቦምቦች በራሱ ቴሌቪዥን ለሕዝብ እንዲታይ አድርጓል። ዕድሜ በረዘመ ቁጥር አንድ ድርጅት/መንግሥት/ቡድን…“በፊት”-ሲከተላቸዉ ከነበሩት ከተጋለጠበት ተራ ብልጣብልጥ አሰራሩ-በሚቀጥለዉ የዉሸት/የቅጥፈት/ያጭበርባሪነት እና የብልጣብልጥነት አሰራሩ ልቀጥልበት ካለም ፣ “መንገዱ ስልቱና ዓይነቱን”-ቀይሮ የተቀናቃኞቹን የፖለቲካ ፊኛ ማስተንፈስ ማዳከም፣ ማሳጣት(ማጋለጥ-) ሲችል ወያኔ ግን ለ34 ዓመታት ሙሉ የተከተለዉ “የዉሸት-መንገድ”-ዛሬም ስልቱና ዓይነቱን ሳይቀይር በተለያዩ ተቀናቃኞቹ ላይ በዛዉ በለመደበት የዉሸት ስልቱ ሲወነጅላቸዉ ስናይ እዉነትም የጫካ ሕሊናዉ አሁንም እዛዉ እንደጫጨ መሆኑን አመላካች መረጃ ነዉ። ለብዙ ዓመታት ከበረሃ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ተቀናቃኞቼ ሲዶሉቱብኝ ደረስኩባቸዉ ያለባቸዉን መረጃዎቹ 95%በዉሸት ያቀነባበራቸዉ መረጃዎች ናቸዉ። የጫካ ባሕሪዉ በቅርብ የተከታተሉና ማሕደሮቹን ያነበበ ሁሉ በቀላሉ መገንዘብ ይችላል። ለምሳሌ ህወሓት በጫካ ዘመኑ “ጃሱስ ማንጁስ ዴማ”(ማንጁስ እና ጃሱስ የሚሉ ቃላቶች የዓረብ ቃላቶች ሲሆኑ ወያኔ ቀልቡ በኤርትራ ቡዱኖች “ፕሮፖጋንዳ፣አሰራር አነጋገርና አጻጻፍ”-ሰክሮ ስለነበረ ከነሱ ተበድሮ እስካሁን የሚጠቀምባቸዉ ከበርካታዎቹ የዓረብ ቃላቶች ጥቂቶቹ ናቸዉ- ማንጁስ ማለት “ትንሽ ልጅ/አሽከር’ያልጠና’/ኩታራ” ማለት ሲሆን “ጃሱስ” ደግሞ “ሰላይ” ማለት ሆኖ “ዴማ/ዳይማ”-- ትግራይ ዉስጥ በዓዲግራት አካባቢ/አሲምባ….እና ዕዳጋሓሙስ የተባሉ ቦታዎችን ያማከለ ተራራማ ቦታ ነዉ-ቦታዉ ከደደቢት ቀጥሎ ወያኔ ለስልጠና ጣቢያ ያዘጋጀበት ቦታ ነበር-የመጀመሪያዉ ጠቅላላ ጉባኤዉ ያደረገበትም እዚህ ነበር)-በማለት ወያኔ የሚጠራዉ የዴማዉ ሰላይ “የ12 ዓመት ወጣት ህጻን ልጅ” ነዉ። ይህ ህጻን (1) በደርግ ተልኮ በስለላ ተግባር ተሰማርቶ የህወሐትታጋዮች ከሚጠቀሙባቸዉ የዉሃ ኩሬዎች መርዝ እንዲጨምር የተላከ ነዉ፤ በማለት እየደበደቡ ‘አዎ ተልኬ ነዉ የመጣሁት በል” እያሉ በማሰቃየት፣- (2) ታጋዮቻችን ወደ ደርግ ዓላማ ለመሳብ በስለላ ተግባር ተሰማርቶ ሲያደራጅ ያዝነዉ በማለት፣ ሸዊት በተባለዉ ታጋይ እና በወያኔዎቹ አባት ስብሓት ነጋ ታጋዮቹ በሙሉ ሲመረመሩ ምንም ማስረጃ ማግኘት ስላልቻሉ ገበሬዉንም በክሎታል በማለት ገበሬዎች እና ቄሶች ሳይቀሩ በሰበቡ የድብደባ ምርመራ ከተካሄደባቸዉ በሗላ ምንም ምንጭ ስላላገኙ በመጨረሻ እንዲረሸን የፈረዱበት “መሓመድ” የተባለዉ ይህ ህጻን እና ሌላዉ ወጣት በሃሰት እንዴት እንደረሸንዋቸዉ ካሁን በፊት በፊታዉራሪ ገዛ ረዳ ቃለ መጠይቅ እንዳስነበብኳችሁ ይታወሳል። ከተማ ገብቶ የመንግሥት ሥልጣን እንደነጠቀም ደ/ር ታየ ወልደሰማያትን ከዉጭ አገር ጉብኘት እንደተመለሰ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ ሲመለስ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ላይ ያያዘዉ ሻንጣ ሲፈተሽ ታጣፊ መሳርያ አገኘንበት በማለት ለ6 ዓመት በሃሰት አስሮ እንደለቀቀዉ የምታዉቁት ታሪክ ነዉ። የሓሰት ምስክሮቹም በማናቀዉ ጉዳይ ላይ በሓሰት አንመሰክርም በማለታቸዉ የደረሰባቸዉ ስቃይ በወቅቱ የተለያዩ ጋዜጦች ዘግበዉት እንደነበር ይታወቃል። ሌላዉ ስለ የወያኔ የዉሸት ቀፎነት በዚህ “በኢትዮጵያን ሰማይ-በሎግ-”ላይ ያቀረብኩላችሁ የመቶ አለቃ አበረ አዳሙ መኮንን የሰጡትን የወያኔ አሰራር እና ሰዉን ፣ድርጅትን እንዴት አድረጎ በሓት እንደሚወነጅል በሰፊዉ ተመልክተናል። ከዚህ ሌላ በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ላይ የደረሰዉ በመንግሥት ግልበጣ የሓሰት ዉንጀላ (በሙት ዓመታቸዉ በዚህ ወር ዝርዝሩ አቀርብላችሗለሁ) ታሪክ ወያኔ የሓሰት ምስክሮች እንዴት እንዳዘጋጀ የራሱ የወያኔ ታጋይ እና የደህንነት ሰራተኛ የነበረዉ በሗላ ከድቶት ወደ ኤርትራ እጁን በመስጠት ይህ ጉዱ ስላጋለጠዉ እና ለወደፊቱም በምስክርነት እንዳይቀርብ በማለት ስለሰጋ -ወያኔ ተከታትሎ በ2000 ዓ.ም ላይ ጋሽ- ባርካ ላይ እንዳስገደለዉ የሚወራዉ “ፍስሃ ሃይለማርያም””-የተባለዉ በሁኔታዉ እራሱ የተሳተፈበት የምርመራ ቅንብር የሰጠዉ ምስክርነት በYou Tube” ቴሌ ቪዥን የቀረበዉ ማስረጃ በማየት የወያኔ ማንነት መገንዘብ ይቻላል። ስለዚህ ወያኔ በዉሸት የፋፋ የዉሸት ቡድን እንደሆነ የሚታወቅ ነዉና ስለ ወያኔ የመፈንቅለ መንግሥት አስቂኙ ተዉኔት እዚህ ትትን ይልቁን እኔ የገረመኝ “ሙሉነህ እዮኤል” የተባለዉ ሌላዉ የግንቦት 7 አመራር አባል ነዉ የሚባልለት ወጣት በዚሁ የሰሞኑ አስቂኝ የመፈንቅለ መንግሥቱ ጋር የተያያዘ ስለ የድርጅት አለቆቹ እነ ብርሃኑ እና “አንዳርጋቸዉ ጽጌ” (በትናቸዉ ጽጌ) የጻፈላቸዉ የአርበኛነት ምስክርነት ገርሞኝ እሱን አንድ ለማለት ነዉ። ከዚህ መፈንቅለ መንግሥት የተባለለት የዉሸት ቅንብር ተያይዞ በር ተከፈተልን በማለት የግንቦት 7 ሰዎች ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ እየተጠቀሙበትም እንደሆነ ግልፅ ነዉ። በግረመንገዳቸዉም የገንዘብ ማሰባሰብያ በር ከፍቶላቸዉ እንደለመዱበት መከረኛዉ የአዉሮጳ እና የዲ.ሲ ስብሰባ 6 እና 7 ሰብሰባዎች እናካሂዳለን በማለት ጥሪ እያስተጋቡ ነዉ። ከዚህ በተያያዘ ሰሞኑ ደግሞ ታክቲኩ ሁሉ አልሰራ ሲል “አርበኛ” የሚለዉ ቃል- “የሰሞኑ ባለ ተራ ቅመም” ሆኖ “እገሌ አርበኛ” በማለት በየመድረኩ ማንበብ ጀምረናል። ሁለት የወያኔ ተቃዋሚ ነን የሚሉን ጠንካራ ድርጅትን እና በጋራ የመስረሳትን ጅማሮ ያደፈረሱት “የዛኛዉ ጎራ”ታዋቂ ሁለት ሰዎች በተከታታይ ባጋጣሚም ይሁን በተጠና መንገድ የየራሳቸዉ ሰዎች “በአርበኛነት” በማቆላጰስ ወደ ሚዲያዉ መድረክ አቅርበዋቸዋል። አንደኛዉ እዚህ የተቸሁበት ፕሮፌሰር አለማዮሁ ገብረማርያም ስለ ደ/ር ሃይሉ አርአያ አርበኝነት ሲሆን፣ በተከታታይ ደግሞ “የግንቦት 7” ሦሰተኛ ሰዉ ነዉ የሚባልለት “ሙሉነህ እዮኤል” የተባለዉ በጸረ አማራነት የታወቀዉ ፣አማራን ለመበተን የኢትዮጵያን አንድነት ለማደፍረስ ለወያኔ አድሮ “የአማራ ሕዝብ ከየት ወደየት” በማጻፍ የታወቀዉ በብዙ ወገኖች “በትናቸዉ ጽጌ” በመባል የሚታወቀዉ “አንዳርጋቸዉ ጽጌ”ን “የአርበኛ ልጅ አርበኛ” በማለት ሲያቆላጵሰዉ አንብበናል። የ80ዓመት አዛዉንት ናቸዉ የሚባሉት የአንዳርጋቸዉ ወላጅ አባት አቶ ጽጌ ሰሞኑን መንግሥቴን ለማወክ ያዝኳቸዉ በማለት ትግራይ ዉስጥ አዛዉንት ወላጆቻችን እና ወንድሞቻችንን ያስር ይደበድብ ይረሽናቸዉ እንደነበረዉ ሁሉ ዛሬም ጉደኛዉ እና ዉሸታሙ ወያኔ እኝህ አዛዉንት ካሰራቸዉ ዜጎች አንዱ ሲሆኑ መሆናቸዉን ከልብ እናዝናለን።ጉዳቱ ካሁን በፊት በኛ በቤተሰቦቻችን እና ወንድሞቻችን ትግራይ ዉስጥ ደርሶብናል እና የሕሊና ቁስሉ እና ከባድነቱ ይገባናል።በዚህም በአንዳርጋቸዉም ሆነ በብርሃኑ ቤተሶበቻቸዉ የሚደርሰዉ እንግልት እንቃወመዋለን። ሆኖም፣-ይህችን ቀዳዳ በመጠቀም “ለወያኔ በማደር ያገሪቱ ሰራዊት ሜዳ ላይ ሲበተን፣ ዜጎቻችን ከኤርትራ ተባርረዉ በባዶ እግራቸዉ ተጉዘዉ አዲስ አበባ መጠለያ አልባ ሆነዉ ሲንከራተቱ አፋቸዉ የከደኑ ብቻ ሳይሆን ለመከራዉ አስተወጽኦ ያደረጉ፣ በሺዎቹ ታፍነዉ እነሱ ባዘጋጁት እስር ሲሰቃዩ ፣ በወቅቱ በስቃዩ ላይ ደስታን የጎነጩ፣ የኢትዮጵያን አንድነት በማፈራረስ ከፍተኛ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳና አስተዋጽኦ በማድረግና በመዲናይቱ ምክትል ከንቲባነት እና በመሳሰሉት ከፍተኛ ስልጣን በመመደብ ወያኔን እና ራሳቸዉን በመንግሥትነት አደላድለዉ ከታወቀዉ የኢትዮጵያ ጠላት ባንዳዉ መለስ እና ታምራት ላይኔ አፍላፍ ገጥመዉ ዊስኪ እና መጽሃፍ ሲዋዋሱና ሲጫለጡ የነበሩት አንዳርጋቸዉ እና ለስየ አብርሃ የመታሰቢያ መጽሀፍ የከተበዉ “ብርሃኑ ነጋን” በአርበኝነት ማቆላጰስ መቼም “ጋኖች አለቁና ምንቸት ጋኖች ሆኑ” ይባል የለ?። ሙሉነህ እዮኤል ሰሞኑን ያንዳርጋቸዉ ጽጌ ወላጅ አባት “በአስቂኙ መፈንቅለ መንግሥቱ”-የተያያዘ በመታሰራቸዉ ወላጅ አባትየዉ “አርበኛ”-ሲላቸዉ ለልጃቸዉ አንዳርጋቸዉን “የአርበኛ ልጅ አርበኛ”-በማለት የወላጅ አባቱን የአርበኛነት ማዕረግ ሲሸልመዉ እኔኑን ደነቀኝ። በተለይ-የመለስ ዜናዊ ወላጅ አባት “አቶ ዜናዊ አስረስን” “ባንዳ” ሲላቸዉ ልጃቸዉ መለስ ዜናዊን “የባንዳ ልጅ “ባንዳ” ብሏቸዋል። ይህ መቸስ በሽታ ነዉ። በሽታ ስላችሁ ሕክምና የማይፈዉሰዉ “የዘረኝነት በሽታ” ማለቴ ነዉ። እንዴት ነዉ ነገሩ ጭልጥ ያለ ነገር!?-የአርበኛ ልጅ አርበኛ ይወልዳል ያለ ማነዉ? ብዙ ያርበኞች ልጆች ልጆቻቸዉ “ባንዳ” ሆነዉ አገራቸዉና ታሪካቸዉ ሲያበላሹ ታሪክ የተዘገበ ነዉ። ሙሉነህ እዮኤል ለፕሮፖጋንዳ ስራ ካልሆነ ወይንም የፖለቲካ አለቃዉን አንዳረጋቸዉ ጽጌን ለማስደሰት ካልሆነ ፣እንዳርጋቸዉ ጽጌ በአርበኝነት የሚያስጠራዉ አንድም ማስረጃ አላቀረበልንም። ታድያ እንዴት እንዴት ሲኮን ነዉ ያለ ማስረጃ አርበኛ ብለን አንዳርጋቸዉን የምንጠራለት? ሙሉነህ እዮኤል ወየኔን “ባንዳ” ነዉ ብሎታል፣- ወያኔ ባንዳ መሆኑን ካመነ- እንዴት ሲሆን ነዉ ያርበኛ ልጅ ለወያኔ ለባንዳዉ አድሮ ከሚገባዉ በላይ ወገቡን ለዘረኝነት ብቅል ሰጥቶ ዘረኝነት እንዲበቅልበት ፈቅዶ “የኦሮሞ ትዉልድ ሐረጉ እየመዘዘ - አማርኛ መናገሩን አንጂ አማራ እንዳልሆነ መጽሐፍ ጽፎ እየዘረዘረ አማራንና ኢትዮጵያዊነትን ያጥላላ ግለሰብ ያዉም’ኮ “ኢትዮጵያዊነት- የዘረ-ቢሶች መሸሸጊያ” በማለት መጽሐፍ የጻፈ ፣ አማራ ሳይሆን “ስለ አማራ ሕብረተሰብ በመጥፎ ጎኑ መጽሐፍ የጻፈ” መጪዉን ትዉልድ ሊያባላ የሚችል አደገኛ ጽሑፍ የተወልንን ሰዉ በምን ሂሳብ ነዉ በአርበኛነት ሊመደብ የሚችለዉ? የአርበኛ ልጅ በእንደዚህ ያለ ጉደኛ ታሪክ ራሱን ሲነክር አርበኛዉ አባቱ አይቀየሙትም ወይ?-ሙሉነህ እዮኤል አማራ ቢሰደብ ባይሰደብ፤ ጉዳዩ አላለዉም፤ አለቃዉ “ኢትዮጵያዊያን ንነ የምንል ሁሉ “ብሔር የሌላቸዉ ዘረ-ቢስ ቢለንም” ሙሉነህ ጉዳይ አላለዉም። የሙሉነህ እዮኤል ሁለተኛዉ ያስገረመኝ ጽሑፉ ደግሞ ወያኔን “አምባ ገነን ቡድን”-ማለቱ ነዉ።ለመሆኑ መኢሶን ደርግን “አምባገነን”-እንዲሆን “እንዳርጋቸዉ እና ጓዶኞቹ”” ወያኔንን “አምባገነን” እንዲሆን ዕድሉን የሰጧቸዉ አይደሉምን?-ታዲያ ወያኔ አምባ ገነን እንዲሆን በከፍተኛ የፖለቲካ ቦታ ተመድቦ ያገለገለዉ አንዳረጋቸዉ “አርበኛ” ማለት ዜጎችን አያስቆጣም? ሙሉነህ እዮኤል ወያኔ ትምህርት መቀጠል አለብኝ ካልክ ሂድ ቀጥል በሎ እንደተቀሩት በኬኒያና በባሌ በመከራ ተሸሽገዉ እና ተሰቃይተዉ ሳይሆን “በቦሌ”በክብር የሸኘዉን ወያኔን ምስጋና አይግባዉና እዚህ ድረስ አሸጋግሮ ፈቅዶ የጓደኛዉን የአንዳርጋቸዉ ጽጌን (ጓድ/ጓድ ቁልጵስ) አርበኛነት ማዕረግ ሊያስሰማን መብቃቱ እዉነት ወያኔ “ዉለህ አትግባ” ከማለት ምን ማለት ይቻላል? ሙሉነህ - አስቲ እንደዉ፣ እንደ ብጻዩ/ጓዱ እንደ ብርሃኑ መዋ ድምጹን አጥፍቶ ዉስጥ ለዉስጥ ስራዉ ቢሰራ ምን አለበት? በዚህ ጉዳይ እህቴ “አያልነሽ” በሚጣፍጠዉ አማርኛዋ በሚገባ ገልጻዋለችና ብዙም ለማለት አልፈልግም። ስለ አስቂኙ መፈንቅለ መንገሥቱ ግን አንድ ሁለት ብየ ልዝጋ። ለመሆኑ ብርሃኑ ነጋ በምን ሃሞቱ ነዉ አሜሪካ ተቀምጦ ጦር እያስላከ ወያኔን ለማስወገድ የሚሞክረዉ? ነገሩ ነገር ቢኖረዉም (መፈንቅለ መንግሥት ባይሆንም) ከብርሃኑ ነጋ የተጠነሰሰ ሴራ እንዳልሆነ ብዙ ሰዉ ይገምታል ።ወያኔ አገዛዙ እየከፋ ስለሄደ በወታደሩም በሲቪሉም ወያኔን በሚችለዉ መንገድ ላለመታዘዝ መሞከሩ አያሌ የማይባል ነዉ። አዲስ ነገርም አይደለም። የብርሃኑ ሃሞት ግን ያየነዉ ነዉ። ድሮ በኢሕአፓ ታሪኩም ሆነ ዛሬ ሴት ልጅቷን ብርቱካንን አጋልጦ ካዲስ አበባ ሸሽቶ በዋሽንግተን -ዲሲ እና በአዉሮፓ በካናዳ የትኩሳቱ መልቀቂያ እና የጉራ መድፈቂያ መድረክ ተዋናይ ከመሆን ሌላ በምን መራራ ሃሞቱ ነዉ እንዲህ ዓይነቱ ስራ የሚሰራዉ? አይሞክርም ሳይሆን ብርሃኑ እና አንዳረጋቸዉ ለእነደዚያ ዓይነት ተልእኮ ዘሎ የሚገባ ሕሊና እና ሃሞት የላቸዉም! እመኑኝ! ከነሱ ይልቅ ሴቲቱ ብርቱካን መቶ በመቶ በወንድነቷ ምረጥ ቢሉኝ አማራጭ ካጣሁ እሷን እምርጥ ነበር። ወያኔ ዋሽቶ መወንጀሉ ላይቀር ዉሸቱን አሳምሮ ቢዋሽ እና የመኢሶኑ የ ዶ/ር ነገደ ጎበዜን የኩባዉና የየመን ሪፑብሊክ አምባሲዎች ትብብር በሌተናል ኮሎነል መንግሥቱ ሃይለማርያም የታቀደዉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ዓይነት ሲደረግ እጅ ከፍንጅ ደረስኩባቸዉ፣ ቢልና ብርሃኑ ነጋ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ወርዶ በደህንነት ጥበቃ ሰራተኛችን በመታየቱ -ለምን እንደመጣ ደህንነት ሰራተኛዉ ቢጠይቀዉ “የእርቅና የሰላም” ድርድር በሚመለከት ስብሰባ ለማድረግ በመንግሥት መጋበዙን ገልጾለት-ሲያበቃ ደህንነቱ ይሄንኑ ለማስታወቅ ወደ አለቃዉ ሄዶ ሲመለስ አጅሬ “ብርሃኑ ነጋ”-ስሙን ለጊዜዉ ለመግለጽ ያልፈለግነዉ በአንዱ በ----------አዉሮጳ አምባሲ አጃቢዎች ታጅቦ በምስጢር በመኪና ተወስዶ መደበቁን ደርሰንበት ደረግ ዶ/ር ነገደ ጎበዜን እንደሸኘዉ እኛም በድርድር አገር እንዲለቅ ሆኗል። ብሎ አሳምሮ ቢዋሽ ምንኛ ታሪኩ ተደማጭነት ባገኘ ነበር። ግን አልቻለበትም! · ብርሃኑም አንዳርጋቸዉም ወያኔንና መለስ ዜናዊን አገልገለዋል፣ አክብረዋል፣ አቆላጵሰዋል ዊስኪ ተጫልጠዋል።ሃይለ ፊዳ እና ጓዶኞቹም ሌተናል ኮሎኔል መንግሥቱን አገልገለዋል፣ አክብረዋል፣ አቆላጵሰዋል ዊስኪም ተጫልጠዋል። ስለዚህ እነ ብርሃኑ ነጋ እና አንዳረጋቸዉ “ግንቦት 7” ብለዉ ራሳቸዉን ቢጠሩም ሰዎቹ “የወያኔ-መኢሰኖች”-ናቸዉና ከጓዳቸዉ ከበረከት ስሞን ጋር ሲማከሩ፣ ሲለሳለሱ እና ሲያቅማሙ የግንቦቱን ሕዝባዊ እሮሮ አክሸፉት (የቤት መቀመጥ አድማዉን ልብ ይለዋል)። ከወያኔ መኢሰኖች ብዙም አልጠበቅንም ትናንትም ዛሬም ነገም ። የደርጉ የሃይለ ፊዳ መኢሰኖችና እና የወያኔዎቹ የአንዳርጋቸዉ/ብርሃኑ “የወያኔ መኢሰኖች”ልዩነታቸዉ የደረጎቹ መ ኢሰኖች ሃገራዊ አንድነት እንዳይላላ የታገሉ ኢትዮጵያዊነትን ያስቀደሙ ከዘረኝነት የጸዱ ሲሆኑ፣ የደርግን መነግሥት በጥበብ ለመጣል ደርግን የተደባለቁ ጊዜዉን ያላገናዘቡ ፖለቲከኞችና የደርግን ዙፋን የገነቡ ሲሆኑ”። የእነ ብርሃኑ ነጋ እና አንዳረጋቸዉ “የወያኔ-መኢሰኖች”ግን አማራን የሚጠሉ ዘረኞች፣ ለወያኔ ያደሩ ፣ ካለ ወያኔ በቀር በራሳቸዉ ህልዉና እና ፖሊሲ መቆም ያልቻሉ፣ ጥገኞችና፣ አገር ሲፈርስ ሮጠዉ አገር ገብተዉ ኩት…ኩት..እያሉ የወያኔ አለቆችን ባሽከርነት እየተከተሉ “ባንዳዎች”ብለን ከምንጠራቸዉ የወያኔ መሳፍንት አለቆች ጋር ዊስኪ ሲያንቃርሩ “ፎቶ መነሳት”እንደኩራት የሚቆጥሩት “አሳፈሪዎች”፣ የባሕር በሮቻችን ሲዘጉብን ኡኡ ስንል ያማራ ትምክህተኞች እሮሮ እያሉ “ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ” ሆነዉ የወያኔን ዉሳኔ ተቀብለዉ ያስተጋቡ ናቸዉ ። · ዋ! ዋ! ያዉም እኮ ፣ “የአርበኝነት የምስክር ወረቀት” በ$500 ዶላር እንሸጣለን በማለት በታሪክ ያልተሰማ.-ያልተደረገ “ምጻእተ ዓለም /ጉድ!”አርበኝነትን ማዕረግ ችርቻሮ ገበያ ንግድ ዉስጥ የገቡ እኮ ናቸዉ!እናንት ወንድሞቼ/እህቶቼ፣- በኢሕአፓ አባሎችና ደጋፊዎቻቸዉ ጥረት.፣ መስተንገዶነት፣ ጽ/ቤት ቅርንጫፎቻቸዉ በአዉሮጳም በአሜሪካም ክፍት አድርገዉ እነ ሃይሉ አርአያም እነ ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዉልም እነ ልደቱ አያሌዉን አሰባስበዉ አስከ ቅንጅት ሕብረት ድረስ እንዲጎለብሱ እና ተበታትነን የነበርነዉን ህብረተሰቦች ጸረ ወያኔ ቆመን እንድንታገል ከጅምሩ የተተከለዉ የሕብረት ችግኝ ዉሃ አየርና እና ማዳበርያ ሆነዉ በማሳደግ፣ በማጠናከር ያደረጉት በታሪክ የማይረሱ ሸጋዎቹ “ኢሕአፓዎች” ከማመስገን ይልቅ (የብርሃኑ መዋ እና የአንዳርጋቸዉ ሴራ እንዳለ ሆኖ) ብርሃኑ ነጋ ከእስር እንደተፈታ ዉጭ አገር መጥቶ ዋሽንገተን ዲሲ አዳራሽ ገብቶ ከአፍዓበት የመጣ አርበኛ ይመስል “አበባ እና ዘምባባ ሲጎነጎንለት”-የመጀመርያ ዲስኩሩ ዘለፋ የጀመረዉ በወያኔ ሳይሆን “በኢሕአፓ” ላይ ነበር ያነጣጠረዉ (ስልጡንና የፋራ ፖለቲካ በማለት-የስድቡ የሽርደዳዉ ጉንጉን ምን ይል እና ለማን ይዘልፍ እንደነበር የምናዉቀዉ እናዉቀዋለን)። በዚህ ዘዴ ነበር “የብተና ስራቸዉ የጀመሩት” ። · ቀጥሎ በወያኔ እና በኢሕአፓ ላይ እያደባለቀ ተደጋጋሚ የብተና ፕሮፖጋንዳዉ እና ስድቡ እንዳጦፈዉ በኢንጅነር ሃይሉ ላይ በተቀነባበሩ ዘረኞች በየመድረኩ እና በየሚድያዉ አስሰልፎ ጅላጅል ብርቱካንን ፊት-ፊት በማስቀደም እሱ ከሗላ ምን ማለት እንዳለባት እያጣደፈ ሕብረቱን በትኖ ሲያበቃ፣-ልጅቷንም ጥሎ አሜሪካኖች ገንዘብና ቀለብ ሰጥተዉት ሳትሰራ ሳትለፋ “ተራራ ላይ ወጥተህ ቁጭ ብለህ ተፈላስፍ”-ብለዉኛል ብሎ እዚህ “ፋራዎች-ከሚለን የፖለቲካ አዛዉንቶች ጋር ቀረ። የምስኪኒቷ ድርጅትም አስዋን ለእስር ዳርገዉ ኢንጅነር ሃይሉን አምባገነን ባሉበት አፋቸዉ ዛሬም በፕሮፌሰር መስፍን አፍ እርስ በረስሳቸዉ “አምባገነንነት እና ስርዓተ አልበኝነት ማን ያዘኛልነት እና ገለልኝነት” አዲሱን ፓርቲዋን ዉጦታል እያሉ በገዛ ብዕራቸዉ እየነገሩን ነዉ! · አንግዲህ ይህ ሁሉ አፍራሽ ተግባርና ባሕሪ ባጭር ጊዜ ዉስጥ ተጋግሎ የነበረዉ የሕዝቡ ወኔ እና ሕብረት ላይ “ቀዝቃዘ ዉሃ ሲቸልሱበት” ያረርነዉን እንዳይበቃ መላልሰዉ የሚጽፉት ፕሮፖጋንዳ እና-ጉራ“ቁጣችንን የሚያበረድ ሆኖ አላገኘሁትም!”-አሁንም አሁንም ጉራቸዉ ሰንጢ የማይበጣዉ ሆኖ አሜሪካ እና አዉሮጳ በመዞር እየተንገዋለሉ እነ አንዳርጋቸዉን “አርበኞች” በሉልን ሲሉን- በ እውነት እላችሗለሁ በመንገስቱ ሃይለማርያም ፊት ቆመዉ አንድ “ቄሱ” እንዳሉት የዚህ ዕብጠት ትርጉም “እኔ- እየጠበበኝ መጥቷል”። በቻ ለማንኛዉም በወሎየዉ በሸኽ ጅበሪል ምርቃን/ሀድራ “አላህ ይሁናችሁ አላህ ይሁነና” ከማለት ምን ማለት ይቻላል?