To change zoom level Press Ctrl and + symbol keys the same time (together) (small size font or minimize page Press Ctrl and - (Minus) symbol.
መልካም አዲስ ዓመት!!!!
እንቅልፍና ምቾት የታደላችሁ ያለፈውን ዓመት በደስታም በምቾትም ያልታደሉትም በሰቀቀን እና በእስራት በግርፋት እና በስደት በሐሳብና በብስጭት ያሳለፋችሁ ወገኖች ሁሉ ሁላችሀም አንኳን ላዲሱ ዓመት አደረሳችሁ። ሃገሬ በታሪክ ማሕደር ልታኖረው የሚረዳት ማበርከት የምችለው ይኼው አዲስ መጽሃፍ አበርክቻለሁ። ከዳንኪራ ምሽት፤ ከቢራና ከጥብስ ቀንሶ መጽሐፍ ገዝቶ የሃገሩን የታሪክ መስተዋት ለማየት ማንበብ የሚፈልግ ሕሊና ካለ ይኼው ሌላው ጥሪ። የወያኔ ገባና ማህደር፡ ደራሲ ጌታቸው ረዳ getachre@aol.com(408) 561 4836 www.ethiopiansemay.blogspot.comGetachew Reda
P. O.Box 2219
San Jsoe, CA 95109
ከጌታቸው ረዳ
Ethiopiansemay.blogspot.com
እንደምን ሰነበታችሁ። ባንዳንድ የግል ምክንያቶች ለተወሰነ ሳምንታት ከመድረኩ ተለይቼ ነበር። እንኳን ደህና ቆያችሁ። ወደ መድረኬ ስመለስ ዋሺንገተን ዲሲ የተካሄደው የተቃዋሚዎች ሰላማዊ ሰልፍ የሚያሳይ በተለጠፈው አውዲዩ ቪዲዮ ነበር ትኩረቴ የጀመርኩት::
ጥቂት ነገሮችን አስተዋልኩኝ። አብዛኛው ተቃዋሚ ሰልፈኛ ወጣት ነው። በፎቶግራፍ የተደገፉ የወያኔ ታሳሪዎች የሚታዩት በቅርቡ ለእስር የተዳረጉት በግምት ወደ ሃያ የሚሆኑ ጋዜጠኞች እና የመሳሰሉ ፎቶግራፎችን ይዘዋል። የቆዩ ታሳሪዎች (የወያኔ ሰለባዎች) ደብዛቸው የጠፉ ኢትዮጵያውያን የሚያውቋቸው አይመስልም፤ ተረስተዋል (ለሽማግሌ ክብር የማይሰጥበት ዘመን ነውና)። ባጭር አማርኛ “ተቃዋሚው ለተወሰነ ወቅት ተጠቅሞ ጥሏቸዋል” (አስታዋሽ እንዳጣ ነባር ሙዚቀኛ ማለት ነው)። ወጣት ሰልፈኛው/ተቃዋሚው የወያኔ ነባር ሰለባዎች ጭራሽኑ የሚያውቃቸውም አይመስልም።
ሁለተኛው የታዘብኩት ነገር፡ ተቃዋሚዎች አንድ ካልሆናችሁ ዞር በሉ እናገላች ኋለን የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። መልእክቱ እውነታና ቁጭት የተቀላቀለበት ቢሆንም ከፖለቲካ እይታ ስመለከተው መልእክቱን ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን መልእክቱን ያስተላለፉ ሰዎች ከቅንጅት/ካንድነት አፍራሾች ከብርሃኑ እና ካንዳርጋቸው የፖለቲካ ሴራ አስተናጋጆችና አሟሟቂዎች ራሳቸውን ማግለልም ይጠበቅባቸዋል። ማህደራቸውንም በማፍረሱ ሽረባ እና እፍ እፍ መስተንግዶ እና ሆሆታ ወቅት ምን ሚና እንደነበራቸው ራሳቸውን መፈተሽ ይኖርባቸዋል
አዳዲስ ታሳሪዎች ወደ እስር ቤት ሲወረወሩ ውጭ ያለው ተቃዋሚ ቡድንተኛ እና ወገንተኛ እንደመሆኑ መጠን “ሸሪከኛነት” መለያው ስለሆነ ለጊዜው በነሱ መታሰር ተጠቅሞ ለተወሱ ወቅቶች ከጮኸ በኋላ ይረሳቸዋል። ሌላ አዲስ ብቅ ሲል ወደ እሱ ያዘነብላል እሱን ወደ ሰማይ ከሰቀሉት በ ኋላ እንደገና የሱ ወቅት ሲያበቃ ወደ ሌላ ብቅ ብቅ ወደ ሚል ወረታቸውን ያን-ጸባርቃሉ። አንዳንዱ እዛው እንዲታሰሩ እንዲቆዩለት ይመኛል።ለምሳሌ የብርቱካን መዲቅሳ መታሰር እና እስከ ህልፈት እንድትቆይ በይፋ ሲመኝ የነበረው ተክሌ ወ/ሚካል የተባለው ካናዳ የሚኖር ወጣትና የካረንት አፈየርስ/ኢካድ ፎረም አርታኢ እሷ ከመፈታቷ በፉት የጻፈውን ታስታውሳላችሁ። ለምን ሲባል፤ ታሳሪ ከሌለ የሚጮኹበት መነሻ ስለሚያጡ የነሱ ምቾት በውጭ አገር በመኖር ተጠብቆ ታሳሪዎቹ ግን እሰር ቤት በመበስበስ የማስጮኽያ መገልገያ ምክንያት ይጠቀሙባቸዋል ማለት ነው።
በጣም የገረመኝ ግን የሚከተለው ነው። ሪፖረቱን ሳዳምጥ አንድ ቴድሮስ መንክር (ካልተሳሳትኩ) የሚባል በእድሜ ጎልማሳ የሆነተከቃዋሚ ሰልፈኞች አንዱ “የኢሳት ቲቪ/አዲስ ድምፅ” ጋዜጠኛ አቶ አበበ ገላው ለቃለ መጠይቅ አቅርቦ ሲጠይቀው ወጣቱ ለዚህ ሁሉ ብልሽት የ40 ዓመት ፖለቲከኞች እንደሆኑ እና እነዚህ ፖለቲከኞች ባኢድሜ ሽማግሌዎች ስለሆኑ መድረኩ/ትግሉ ለወጣቱ ትውልድ መልቀቅ ይኖርባቸዋል ሲል በምሬት ይገልጻል።
ይህ ወጣት ከልቡ እንዳለሆነ እገምታለሁ። ምክንያቱም ይህ በጎልማሳ ዕድሜ የሚገኝ ወጣት “ቃታ ፍልቀቃ” ነባር ታጋዮችን ከመዝለፍ መጀመርያ የራሱን ጉልበት እና ሕሊና በመፈተሽ ዳቦ ፍለጋ ከመሯሯጥ ይልቅ እንደ አርባ ዓመቶቹ ፖለቲከኞች ቃታ ፍልቀቃ በመግባት አገሪቷን በቃታ አፍኖ እየገዛት ነው፤ ጋዜጠኞቻችን እያሰረ ነው ብሎ ሻንጣ ወገቡ ላይ አነግቦ በሰንደቃላማ ያሸበረቀ ቆብ አጥልቆ ፈረንጅ -ጽ/ቤቶች ቆሞ አርባ አመት ፖለቲከኞች እና ሽማግሌዎችን መድረኩን ልቀቁ እያሉ ከመጮህ፤ ራስን በቃታ ፍልቀቃ መፈተን እና ዳቦ ፍለጋውንም አቁሞ ሽማግሌዎችን ከመዝለፍ ተቆጥቦ የራስን ድክመት በሽማግሌ ፖለቲከኞች በማላከክ ነባር ፖለቲከኞችን መሸፈኛ ምክንይት ከማድረግ ፤የናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ ጩኸት ባህል መራቅ ረገቢ ነው። ለወጣት ፖለቲከኞች አስረክቡ ብሎ ነባር ፖለቲከኞችን ከመዝለፍና ላንድነቱ ለብጥብጡ ላልመስማማቱ ሽማግሌዎች ናቸው የሚበጠብጡን ብሎ ከመቀባጠር ይልቅ እንደ እነ ልደቱ አያሌው እና አንዷለም አራጌ የመሳሰሉ ወጣቶች ለምን አልተስማሙም ብሎ ራስን መፈተሽ ተገቢ ነው።በተለይ ደግሞ ወጣቱ ዳቦ ማሯራጡን አቁሞ ቃታ ፍልቀቃ ገብቶ ራሱን ካልፈተሸ ሽማግሌዎች ለወጣቶቹ የሚያስረክቡት ፖለቲካ የለም። ዳቦ ፍለጋ እና ቃታ ፈልቅቆ ጠላትን ማንበርከክ የተለያዩ ባሕሪዎች ስለሆኑ “የ አርባ አመት ሽማግሌ ፖለቲከኞች” አደናቀፉን/አተራመሱን/ስልጣን አንለቅም አሉን… የሚለው የቅጥፈት ምክንያት ተሎ አቁማችሁ “የፒሳ እና የዳቦ” ገመጣ” የሆድ ሱስ አቁማችሁ እንደ ወጣቶቹ በቃታ ፍልቀቃ እራሳችሁን መፈተሽ ይጠበቅባችኃል። በዳቦ ማሯሯጥ ሩጫ የተጠመደ ወጣት ሽማግሌዎች ላይ የማላከክ ጩኸት ብቃቱም ሞራሉም መብቱም የለውም። “ቢ ኤስ” ይላሉ ፈረንጆቹ! እውነትም “ቢ ኤስ!” ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ www.ethiopiansemay.blogspot.com