አሁን
ምን እንደሚያስፈራኝ ታውቃላችሁ?
ይነጋል በላቸው
Ethio
Semay
Happy
Ethiopian Easter
The terrible economic crisis under the leadership of Abi Ahmed
በአብይ አህመድ አመራር ስር አስፈሪው የኢኮኖሚ ቀውስ
5/2/2021
ሰሞኑን ተመላለስኩባችሁ አይደል? ይቅርታ፤ “መቼስ ማልጎደኔ” ይላሉ “እንታይሞ ትገብሮ” ይሉ የነበሩትን የቀድሞ ጌቶቼን የተኩት አዲሶቹ ጌቶቼ፡፡ የሀገራችን ሁኔታ እኮ ዕረፍት አልሰጥ አለ፡፡ ማን እንደሚያስቀናኝ ልንገርህ? “እነገሌ ታረዱ፤ እንትና እምትባል የእነእንቶኔ ከተማ ከነሕዝቧ እንደሲዖል ነደደች፤ አዲስ አበባ በኦነግ ሸኔ ተከበበች፤ አቢይና ሽመልስ አሥር ሚሊዮን ቆንጨራና አምስት ሚሊዮን ስናይፐር በድብቅ አስገቡ….” ስትለው “ምን ይጠበስ(ልህ)?” ለማለት በፈረንጅኛው ጭምር “So what? “ በማለት ሀገር ብትጠበስ ብትገነተር የማይሞቅ የማይበርዳቸው ገልቱዎች ናቸው፡፡ ታድለው ግን፡፡
ከደቂቃዎች
በፊት ከገበያ መምጣቴ ነው፡፡ አሁን በዚች ደቂቃ ደግሞ የቅርጫ በሬ ሊገዙ የሄዱ ጓደኞቼ ለስምንት ሆነን እያንዳንዳችን ያዋጣነው
ብር 4000 (ድምሩ 32000 ብር መሰለኝ!) አልበቃ ብሏቸው ሳይገዙ መመለሳቸውን በስልክ አረዱኝ፡፡ የዛሬ 25 ዓመት የኦህዲድ
ፈጣሪ በሆነው የሕወሓት ዘመነ መንግሥት 32 በሬ የሚገዛ ብር አሁን አንድ በሬም መግዛት አልቻለም፡፡ አቢይ የማፈሪያ አካል አልፈጠረበትም
እንጂ ማፈር ያለበት አሁን ነበር፡፡
የዘንድሮው
በዓል የመንግሥትን አለመኖር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ገበያን ሃይ የሚል የመንግሥት አካል አንድም የለም፡፡ በኪነ ጥበቡ
ውለን እናድራለን፡፡ የዓመት በዓሉ ገበያ አይነሳ፡፡ ቃኝተህ ባዶህን መመለስ ነው፡፡
ዶሮ
ገበያ ውስጥ ከ400 እስከ 1000 ብር ነው - እኔ በአላሙዲን መደብር 350 ብር ሂሣብ ገዛሁ፤ ወረፋውን ግን አትጠይቀኝ፡፡ ጫጩት
ይዞ “ስንት ነው?” ስትለው በኩራት “600” ይልሃል፡፡ ታፍራለህ፡፡ የሕዝቡ የገንዘብ ዕውቀት እየተመነደገ የሰውነትና የአስተሳሰብ
ደረጃ ግን በብርሃን ፍጥነት ቁልቁል እየተሽቀነጠረ ነው፡፡ አንዱን የሰፈር ዱርዬ “ስለሚጠቅመኝ እባክህን አንዴ በጥፊ እንድትመታኝ
ስንት ልክፈልህ?” ብትለው “ከ500 ብር በታች አያዋጣኝም!” እንደሚልህ አትጠራጠር፡፡ “አራት መቶ ልክፈልህ” ብትለው እንኳን፣
ነጋዴዎቹ ሲሉ ሰምቶ “በርሱስ እኔም ከቦታው አላመጣሁትም፤ ገብርኤልን በ485 ነው ከመኪና ያወረድኩት፤ በዚያ ላይ ለሸቃይ የከፈልኩትን
አስበው …” ሊልህ ይችላል - ጥፊውን፡፡
የዕቃውን
ዋጋ ዘርዝሬ አልጨርስልህም፡፡ አንዲት ሃይማኖታዊ ጉዳይ ስላለችብኝ እኔማ ተንገላታሁልህ ወንድማለም፡፡ አሁን ለታ የሁለት ዓመት
ሕጻን ጢል አድርጎ ተሸክሟት የሚሄድ ብጥሌ ኬሻ ከሰል “350 ብር ገዛሁ” ብትለኝ ክብርት ባለቤቴ ወ/ሮ መሽኛሽወርቅ ለአንድ ሣምንት
ቡና ማፍያ ለማትሆን ያ ሁሉ ገንዘብ መውጣቱ ደሜን አንተከተከው፡፡ ለአንድ ኪሎ ድቃቂ የበዛበት ገብስ ቆሎ ደግሞ 100 ብር! ይቺ
ፅዋ ወጣች በለኛ! በእርሻው ላይ እንዳለ ከሩቅ ተጣርተው የእናታቸውን ሞት ያረዱት አንዱ ባላገር “የሆነስ ሆነና ከፈኑን ማነው
የሚገዛው?” ብሎ ሲጠይቃቸው ወንድሞቹም መልሰው “ያው ባንተው ነዋ!” ሲሉት “ከረመች በለኛ” እንዳለው አረም ላይ የነበረ ገበሬ
መሆኔ ነው እኔም፡፡
ወዳስፈራኝ
ነገር ልሂድ ይልቁንስ፡፡ የሚያስፈራኝ ትልቁ ነገር የገንዘብ ዋጋ መጋሸብ የመንግሥትን አቅም በቀጥታ የሚጠቁም ነው፡፡ መንግሥት
ነኝ የሚል አካል ፖለቲካውን ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚውንም በአግባቡ መቆጣጠር አለበት፡፡ ኢኮኖሚው የሕዝብ ሕይወት መሠረት ነው፡፡ አሁን
ያለው የአቢይ መንግሥት ግን ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ውጪ ሌላው ነገር ሁሉ ከእጁ የወጣ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ አንጻር ውለን የምናድረው
ከፍ ሲል እንዳልኩት በኪነ ጥበቡ እንጂ በመንግሥት ጥበቃ እንዳልሆነ ሰሞነኛ ሀገራዊ ጉዳዮች በተለይ አፍ አውጥተው እየተናገሩ ናቸው፡፡
ዝናሽ ታያቸው ገበያ የምትወጣ አይመስለኝም፤ ስለዚህም አቢይ በተዛዋሪም ቢሆን ገበያውን የማወቅ ዕድል ላይኖረው ነው፡፡ ማወቅ ግን
ነበረበት፤ ምክንያቱም እየገዛ ያለው ካለ እህል ውኃ የማይኖሩ ምድራዊ ፍጡራንን እንጂ መብላትና መጠጣት ሳያስፈልጋቸው በፀጋ የሚኖሩ
የገነት መንፈሣውያንን አይደለምና፡፡ ሰውዬው የዳይሜንሽን ፊስቱላ ሳይገጥመው አልቀረም፡፡ Creatures that live in
the third dimension, i.e planet Earth, need to get food and water in order to
survive, unlike other beings out of this dimension. Abiy is not a spirit,
though he may eventually claim to be so and neither is he a god or God. መንታላውና ተቅበዝባዡ
አቢቹ ሥልጣኑ ላይ ውሎ ማደሩን እንጂ፣ ያቺን የሚቃዥባትን ኦሮሙማ በባሌም በቦሌም ማሳካቱን እንጂ ስለተጨባጩ ዓለም - ስለወቅቱ
ሀገራዊ ሁኔታ የሚያስብበት ጊዜም ሆነ ፍላጎት የለውም፡፡ ይህ ህመም በመሆኑ ህክምና ያሻዋል፡፡
ጀርመን
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ስትወድቅ ደች ማርኳም አብሮ ተዘረረና ወጣቶች ቤታቸውን የሚያሳምሩት ቱባ ቱባ የገንዘብ ኖቶቻቸውን
ግድግዳ ላይ በመለጠፍ ነበር፡፡ የዚያድባሬ ሶማሊያ ከመውደቋ በፊት ሽልንጓ ነው ቀድሞ የተፈጠፈጠው፡፡ ዚምባብዌ በኢኮኖሚ ስትንደባለል
አንድ ኪሎ አፕል ለመግዛት በሚሊዮን የሚቆጠር የዚምባብዌ ዶላር በሻንጣ ወይ በኮሮጆ ይዞ መሄድ ያስፈልግ ነበር፡፡ በጥቅሉ የመንግሥትን
መውደቅ ቀድሞ ወይም ተከትሎ አሊያም ጎን ለጎን የሚመጣው የገንዘብ መውደቅ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡ የኛስ ዕዳው ገብስ ነው፡፡
ባንበላስ? ቱ! አንድ ቀን ባይበላ ይሞታል? መንግሥት ተብዬው ግን ወዮለት! የኑሮ ውድነት ለመንግሥት ውድቀት መጥፎ ምልኪ ነው፡፡
ዕንቁላል 7 ብር፣ ቅቤ 600 ብር፣ ዘይት 120 ብር፣ … ምን አለፋህ … በስሙኒ ደሞዝ የሽህ ብር ኑሮ እንድንኖር ነው እየተገደድን
ያለነው፡፡ ያለው ግን እንደቀልድ ነው የሚመዘርጠው፡፡ ሌባውና ሙሰኛው፣ ስንጥቅ አትራፊ ነጋዴውና ትላልቅ ደሞዝተኛውማ …ኧረ ተወኝ
ወንድሜ፡፡ ማለፉ አይቀርም ያኔ እናወራዋለን - ከማዕበሉ ከተረፍን አይደል ለዚያውስ? እየመጣ ያለው ጦርነትና ርሀብ “ምነው በናቴ
ማሕጸን ውስጥ ውኃ ባደረግኸኝ” የሚያስብል ነው፡፡ ይህ አደጋ ግን ለብዙዎች ሊታይ አልቻለም፤ ሕዝቡ ምን ዓይነት ረቂቅ መነፅር
አድርጎ ይሆን?
ዋናውና
ትልቁ የሚያስፈራኝ ነገር ደሞ “ገንዘብ ተይዞስ የሚገዛው ነገር ከጠፋ ወዴት ይደረሳል?” የሚለው ነው፡፡ አዎ፣ እነዚህ አቢይና
ሽመልስ የሚባሉ የታችኛው መንግሥት (The Netherworld) ባልደረቦች የገደሉትን ገድለው ቀሪውን አምራች የማኅበረሰብ ክፍል
እያፈናቀሉ በገዛ ሀገሩ ስደተኛና በመጠለያ ኗሪ ስላደረጉት እህልና ሌሎች የምግብ ሸቀጦች በገበያው እንደዱሮው ሊኖሩ አይችሉም፡፡
ዕጥረት አለ አሁንም፡፡ የአቅርቦት ዕጥረትና ድንቁርና ሲደመሩ የኑሮ ውድነቱ ወገብ ሰባሪ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ብር የሌለን ሰዎች
እንቅርና መቶ ሽህ ብርም ይዘህ አንድም ኩንታል ጤፍ ልትገዛ የማትችል ከሆነ ብርና የመጸዳጃ ወረቀት በዋጋ ተስተካከሉ ማለት ነው፡፡
ያኔ ብርና ዶላር በትሬንታ ኳትሮ ከነሬሞርኬው (ተሳቢው) ጭነህ “የዳቦ ያለህ!” ብትል ላታገኝ ትችላለህ - የሚበላውን ዳቦ ነው
የምልህ አንተ ደ’ሞ፡፡
ይሄውልህ
“ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው” ሲሉ ሰምተሃል አይደል? አዎ፣ በኔም መጣጥፍ ውስጥ ባንተም ሕይወት ውስጥ - ልብ እያልነው ልብ ሳንለውም
እየተቀላለድን እዚህ ደረስን፤ ግን ግን አቢይና ሽመልስ ከላያችን የሚነሱበት መለኮታዊና ሰብኣዊ ጥምረት ካልተፈጠረ በተለይ አገር
ውስጥ ያለን ዜጎች ተያይዘን ማለቃችን ነው፡፡