Tuesday, February 15, 2022

የትግራይ ድያቆናትንና የቀሳዉስት ዕምባ (ለማስታወሻዎ) ክፍል 1 ጌታቸዉ ረዳ ETHIOPIAN SEMAY 2/15/22

 

የትግራይ ድያቆናትንና የቀሳዉስት ዕምባ (ለማስታወሻዎ)

ክፍል 1

ጌታቸዉ ረዳ

ETHIOPIAN SEMAY

2/15/22

የትግራይ ድያቆናትንና የቀሳዉስት ዕምባ (ለማስታወሻዎ) የህወሐት ታጋዮች በሰባት ጥይት ደብድበዉ ጫካ ወስደዉ ጣሉኝወይንም The Record That Speaks of Priests and Deacons Abused In Tigray by TPLF Leaders” በሚል ያቀረብኩትን ከ 14 አመት በፊት የለጠፍኩትን ዛሬ መልሼ ላስታውሳችሁ የፈለግኩት አንደኛው ምክንያቴ አዳዲስ ትውልዶች ነገሩን ስለማያውቁት እንዲያውቁት፡ ሁለተኛው እና ዋናው ደግሞ ሰሞኑን የትግራይ ቀሳውስት እና እስልምና መሪዎች ነን የሚሉ ዓባይ ትግራይን (ታላቅዋን ትግራይ) እንመሰርታለን ብለው በትግራይ ናዚዎች ርኦዮት ዓለም ባንዴራ እየተመሩ ኢትዮጵያዊያን አይደለንም ፤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እና እስልምና ተለይተናል በማለት ናዚ ጀርምኖችና የሙሰሎኒ ፋሺስት ጣሊያኖች እንዳደረጉት በትክክለኛው ቅጂ ለማስፈጸም የትግራይ ቀሳውስት ነን የሚሉ “ኮሞፍላጅ ቄሶች እና ሙኡሚን ወያኔዎች” ኢትዮጵያዊነታቸውን ሰርዘው በትግሬነት ዜጋ በይፋ አውጀዋል

ለነዚህ ሰዎች ከኢትዮጵያ መገንጠል ምክንያታቸው አጥጋቢ የሆነ ምንም ምክንያት የላቸውም። ምክንያታቸው “ለ27 አመት” የትግሬ እስላም መሪዎች እና 2 ትግሬ ጳጳሳት ኢትዮጵያን እንዳሻቸው እንዲያስተዳድሩ ፈቅዶላቸው ከትግሬው የወያኔ መንግሥት ጋር ወግነው በመተባባር በተለያዩ ህዳጣን እና አማኒያን ላይ የተለያዩ ብዙ ግፎች ሲፈጽሙ እንደነበረ የተዘገበ ታሪክ ነው።

ዛሬ ከ4 አመት በፊት ከሥልጣናቸው በሕዝብ አመጽ ሲወገዱ ከፖለቲካ ጌቶቻቸው ጋር በማበር ውጭ አገር ያሉትንም ወስጥ አገር ትግራይ ውስጥ ያሉትም የወያኔ ሹመኞች ቀሳውስትና እስላም መሪዎች የወያኔ የመገንጠል ፖለቲካን አጅበው በይፋ ተለይተናል ሲሉ አውጀዋል።

ስለዚህ የተለዩበት ምክንያት አብይ በእምነታችን እና በሕዝባችን ላይ በደል ፈጽሞብናል በማለት እንደምክንያት ቢጠቀሙበትም፤ ዕቅዱ የነበረና ሥልጣን ካጣን አንገነጠላለን የሚለው ድርክቱ ሲጠነሰስ የጠነሰሰው የህወሓት አጀንዳ ነው።

እውነታው ግን ለምእመናን እና ለፈጣሪ ፍጡራን ቢያዝኑ ኖሮ የትግራይ ፋሺሰቶች 17 አመት በጫካ 27 አመት በመንግሥትነት የጨፈጨፉትን ሕዝብ በእሳት የለበለቡትን፤ በእስረኞች ላይ በፖለቲካ የተለዩ ያሰርዋቸው ግበረሰዶም  ሲፈጸም፤ ከሥርዓቱ ጋር ያልተጣጣሙ ቀሳውስት፤ መነኮሳት ሲገደሉ ሲሰቃዩ ሲደበደቡ ፤አንስት መነኮሲቶች የወንድ ጥቃት ሲፈጸምባቸው የት ነበሩ? መልስ የላቸውም። ለብዙ አመት በስርቆት ከስሰው አዋርደው ያሰሩት ሓፍረተ ቢሱ ስየ አብርሃ አንኳ ጫማቸው ተመልሶ እየላሰ ከቄሶቹ ጋር ለግንጣላ ሲልከሰከስ ማየት ፖለቲከኛውም ቄሱም ጠሚጣሚውም፤ ጀለቢያ ለባሹም በወያኔ እየተመሩ ከሰው ባሕሪ ወጥተው ጦርነትን እየደገፉ፤ አገር ሲያፈርሱ እያየን ነው።

የትግራይ ቀሳወስት እና እስላም መሪዎች ሆይ የድርጅታችሁን የወያነ ትግራይ ሰይጣናዊ ገበና ጉዳችሁን ስሙ፤ አልተደረገም ካላቸው እንስማቸው ‘ፈረሱም ሜዳውም ይኸየው”!! ኑ።  ፈጠሪን ከድታችሁ ግፍ ከፈጸሙ ወንጀለኞች ጋር መጎዳኘታችሁ በታሪክም በፈጣሪም ትጠየቃላችሁ ። በዚህ አጋጣሚ  የትግራይ ኦርቶዶክስ ሃለፊ ቄስ ነኝ ብለው የመገንጠል አዋጁን በትግርኛ ያነበቡት ቄስ ብትሰሙዋቸው ቄሱ የሁለት አውላዕሎ (ትግራይ) ተወላጅ እንደሆኑ ብንሰማም የተጻፈበት የትግርኛ ዘይቤ  “ወያኔ”  የእንደርታን እና የራያን ሕዝብ የትግርኛ ለዛ ለማጥፋት የሰራበት “አ ሽ ዓ” ዊ ትግርኛ ስለነበር ቄሱ ለማንበብ ተቸግረው ሲንተባተቡ መስማት እጅግ ያሳዝናል።

የምከክራቸው “አባ ቄሱ ምናለ በራስዎ የትግርኛ ልሳን ዘይቤ ቢጠቀሙ? ወላጆቻችን የተውልንን አካባቢያዊ ልሳን እንዴት ይናቃል? ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ጽፌበታለሁ። ሌላ ቀን እመለስበታለሁ።

ይህ ካልኩ ዘንድ፡

ትግራይ ውስጥ ሲደረግ የነበረው እነ ገብረኪዳን ደስታን አስመልክቶ ቀሳውሰት እና የእስላሞች ሁኔታ በክፍል ሁለት እንመለከታለን። ለዛሬ ግን እነዚ የወያኔ ናዚ አሽከሮች ትግራይ ውስጥ በዲያቆናት፤በቀሳውሰት ህይወት ላይ ምን ይፈጽም ነበር? ብለው እንኳ የመጠየቅ ጥንካሬ የላቸውም። እስኪ ወደ ሗላ ልመስለሳችሁና እነዚህ ቀሳወስት ነን የሚሉ ኢትዮጵያን የከዱ “ከሃዲዎች” ድርጅታቸው ህወሓት በቀሳውስትና በድያቆናት ምን ግፍ ትሰራ እንደነበር አስቲ እናስታውሳቸው።

(ምንጭ፦ ኢትኦጵ መጽሄት- ቅጽ 2 ቁጥር 016 መስከረም 1993 .) ( ከመጽሔቱ በቅጅ ለናንተው አንባቢዎች የቀዳሁት እኔ ጌታቸዉ ረዳ  ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ )

ይህ ታሪክ ኣማርኛ ለማያነቡ የትግርኛ ተናጋሪዎች ተርጉሜ በድረገጼ ስላለ ያንን መመለከት ነው። ለዛሬ አማርኛውን አቀርባለሁ።

 እዉነት ተሸፋፍኖ አይቀርምና፤ ሰሚ አጥተዉ የሚጮህላቸዉ ዜጋ ፍለጋ ለዓመታት የደም ዕምባ ላፈሰሱት የወያኔ ሰለባዎች  በኔ  በኩል በዚህ ዓምድ ዕምባቸዉና እሮሮአቸዉ ለሕዝብ አስተጋባለሁ። ፈራጁ ታሪክ እና በዓይን የሚታይ ጥቃት እንጂ ዘመን የለገሳቸዉ ግራ ተጋብተዉ የዋሁን ማህበረሰብ ግራ የሚያጋቡ አፈጮሌ የሚዲያ  ባለቤቶች  አይደሉም።

ስለዚህም የሕዝባችን ጥቃት ከማስተጋባት ወደ ሗላ ያላልንበት ቃል ኪዳናችንን መሬት ተንተርሰን የመጨረሻዋ እስትንፋሻችንን እየተነፈስንም ቢሆን ትግላችን ይቀጥላል። አገር እና ሕዝብ ያስለቀሱ የባሕር በራችንን ያሳጡንን <<በረሃ እያለን ለፈጸምነዉ ወንጀል አንጠየቅበትም> ብሎ በስልጣን ማን ያህለኝነት የፏለሉት የፈጠራቸው እግዚሃር እንዲምራቸዉ እየተመኘንተበደልን ፍትሕ እንፈለጋለንብለዉ ለጠየቁ የትግራይ ህብረተስብ አባላት መልሳቸዉ ምን እንደነበር ከሚቀጥለዉ የወያኔዎች የገመና ማህደር እንመልከት። የዛሬ የትግራይ ተገንጣይ ቀሳወስቶች ይህንን አንዲመለከቱ እጋብዛቸዋለሁ።

አሁን ወደ ታሪኩ ልዉሰዳችሁ፡

 ኢትኦጵ መጽሄት፦

እንግዳችን ብርሃኔ /ሕይወት ይባላል። ወደ ሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ትግል ዉስጥ እንዲቀላቀል የቀረበለትን ጥሪ ባለመቀበሉና በመቃወሙ፤ በተደጋጋሚ መታሰሩንና በመጨረሻም በአሰቃቂ ሁኔታ በሰባት ጥይት መደብደቡን ይነግረናል። ይህ ወጣት ቤተክርስትያን በማገልገሉም ሳቢያ፤ከፍተኛ ተፅእኖ ተደርጎበት የድቁና መታወቂያዉንም የሕወሐት ታጋዮች ቀድደዉታል። የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ በሐገር ዉስጥ ህክምና የማይድን መሆኑንም የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሰኔ 20 ቀን 1986 አረጋግጧል። ይህንንም ማረጋገጫ የሰጡት ከፍተኛ ህክምና እንደሚያስፈልገዉ ያረጋገጡት / ተመስገን ፍጡር (ቀዳጅ ሐኪም) / ዘሩ /ማርያም (ሜዲካል ዳይሬክተር) ፕሮፌሰር W.Mcquillan (የቀዶ ሕክምና አማካሪ) ናቸዉ።

ይህ 35 ዓመት ወጣት ከዚህ በሗላ ከደረሰበት ጉዳት ለመዳን ዕርዳታ ያደርጉለት ዘንድ የግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን አነጋግሯል።ዳዉተር ኦፍ ቻሪቲከተሰኘ ግበረ-ሰናይ ድርጅት ጥሩ ምላሽ በማግኘት ከዉጭ ሃገር ገንዘብ ቢሰበሰብለትም ገንዘቡ በድርጅት ሓላፊዎች መበላቱንና በሗላም እሱ ሜዳ ላይ መጣሉን ይናገራል።

ወጣቱ በዚህ ጉዳይ ኬንያ ድረስ ሄዷል፤ ወደ ትግራይ ብቅ ብሎም በወቅቱ የነበሩት የትግራይ ክልል ዋና ፀሐፊ / አረጋሽ አዳነን አነጋግሯል። እዚያም አንደር-ግራዉንድ (ከመሬት በታች) ዉስጥ እንዲገባ በማድረግ ለረዢም ሰዓት በጥያቄ እንዳፋጠጡት ይናገራል

ይህ ወጣት ሰዉነቱ ላይ ያለዉ ቁስል እያመረቀዘ እንዳስቸገረዉ ለማየት ችለናል።ይህን ቁስሉን ለማዳንና ከበሽታዉ ለመፈወስ 6 ሚሊዮን 200 ሺህ የኬኒያ ሽልንግ (103 ሺህ ዶላር) እንደሚያስፈልግም / ጆን.. የተባሉ በኬኒያ የሚገኙ ሃኪም ያረጋገጡበትንና // ዲሴምበር 21/98 የተፃፈ ወረቀትም ይዟል።

 ሁሉንም ከእርሱ እንከታተል።>>

ኢትኦጵ -ቅፅ 2 ቁጥር 016 መስከረም 1993 .}-

ጥያቄ፦ስምህ ማን ይባላል?

 ብርሃነ /ሕይወት።

ጥያቄ-  ትዉልድና ዕድገትህ ?

ብርሃነ፦

 ትዉልዴ አድዋ አዉራጃ ሲሆን፤ቀበሌዉ ጣቢያ ኮረም መንደር ደግሞ እንዳ መትከል ስብሃቱ ይባላል።

ጥያቄ- አድዋ አዉራጃ እያለህ የደረሰብህ በደል ምነድ ነዉ?

ብርሃነ፦

ቤተክህነት ተማሪ እያለሁ 1975 . ከአክሱም ጽዮን ድቁና ተቀብየ ስሄድ በወድቅት ሌሊት የማላዉቃቸዉ ሰዎችኢሳ” ወደ ሚባል ወረዳ አስረዉ ወሰዱኝ። በአሁኑ ወቅት ያለዉ ጳጳስ ከደርግ ጋር ሰዉ እንዲገደል ያወጀ ስለሆነ ቅስናንም ሆነ ድቁናን ሊባርክ አይችልም።የሚል ምክንያትም ስጡኝ።

ጥያቄ- ጳጳሱ ማን ነበሩ?

ብረሃነ፦  

ስማቸዉን ዘንግቼዋለሁ በዚያ ሰዓት ስማቸዉ መታወቂያየ ላይ ነበረ።

ጥያቄ-  የትግራይ ተወላጅ ናቸዉ?

 ብርሀነ፡-  

እኔ እንጃአማርኛ ነበር የሚናገሩት።

ጥያቄ-  በተያዝክበት ወቅት ማለትም 1975 . አካባቢዉን የሚያስተዳድረዉ ደርግ አልነበረም እንዴ?

ብረሃነ፦

ከተማዉ ደርግ ነዉ፡በገጠር ወረዳዎችን የሚያስተዳድሩት ወያኔዎች ነበሩ።

ጥያቄ-     ከገጠር ነበር ያያዙህ?   

ብርሃነ፦

 አዎ! ከገጠር ነዉ የያዙኝ። እኔ ስለ እናንተ ዓላማ አላዉቅም፡ ከዚህ በፊትም አላዉቃችሁም። እኚህ ጳጳስ ደግሞ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ / መሪ መሆናቸዉን ብቻ ነዉ የማዉቀዉ እንጂ፤ ጦርነት ያዉጁ አያዉጁ እኔ የማዉቀዉ ነገር የለኝም ፡ስላቸዉ በቅጣት 10 ቀን አስረዉ መታወቂያየን ቀዳደዱት። በሗላም ደርግ ካለበት አካባቢ እንዳልደርስ አስጠንቅቀዉ በዋስ ለቀቁኝ። ሌሎችም ቅስና እና ድቁና የተቀበሉ 50 በላይ የሆኑ ሰዎች ታስረዉ ነበር። እነሱም ከእስራትና ከቅጣት በሗላ መታወቂያቸዉ ተቀምተዋል።

ጥያቄ- የተቀሙት የድቁና መታወቂያቸዉን ነዉ?

ብርሃነ፦

 የድቁና እና የቅስና መታወቂያቸዉ ነበር የተቀሙት።ከዚያ እዚያዉ ቆይተን 1981 / በግድ ወደ ግንባር ዝመቱ አሉን።

 ጥያቄ- በ1975 . እንደተያዛችሁ እንድትዘምቱ አልጠየቅዋችሁም?

ብርሃነ፦

ይጠይቁን ነበር፤ ነገር ግን ግዴታ አልነበረብንም። በዘፈን ይቀስቅሱን ነበር። በስብሰባ ያስቸግሩናል። ይቆጡናል እንጂ የጠነከረ ግዴታ አልነበረም። 1981 . ግን ዉጥረቱ ሲበረታባቸዉ ነዉ መሰል ግዴታ ታገሉ አሉን። እኛአንታገልም፤እናንተ ታገሉ፡ እኛ ድሆች ነን፡ ገና ዳቦ እንኳን አልጠገብንምስንላቸዉ፡ማን አጥንቱን ከስክሶ ሊያኖርህ ፈለግክ?” በማለት በተለይምቢሄንየተባለ ታጋይአፈር በእጁ ከመሬት ቆንጥሮ በማፈስ ወዳፍንጫችን አስጠግቶ እንድናሸት አስፈራራን”። በአገራችን መኖር ካልቻልን ተሰድደን እንሄዳለን፡ ይለፍ ብቻ ስጡን ስንል ስትፈልጉበሰማይ ሂዱ እንጂ አይሰጣችሁም”፡ እያሉ ያፌዙብን ነበር።

ታዲያ የት እንድረስ?” ስንላቸዉየራሳችሁ ጉዳይ!ከፈለጋችሁ አገራችሁን ነፃ አዉጡ። ነፃ አናወጣም የምትሉ ከሆነ ግን የዚህችን ምድር በረት አትረግጡም። አሉን።ከማን ነዉ ነፃ የምናወጣት?” ደርግም ኢትዮጵያዊ ነዉ እናንተም ኢትዮጵያዊያን ናችሁ።ስንል <ከበስተጀርባችሁ የሆነ ነገር አላችሁ!> በማለት ማሰር እና መቅጣት ጀመሩን።

ጥያቄ-     ስንት ትሆናላችሁ? ብርሃነ;- 1500 እንሆናለን። ከዚያ ምን ተከተለ?

ብርሃነ-

ወላጆቻችን ታሰሩ። የእርሻ ማስታዎሻችንም ተወረሰ። ቀንደኛ ዓድመኞች ናችሁ በተባልን በተወሰንን ሰዎች ላይ ከባድ ቅጣት ተፈጸመብን። 6 ወር አስከ ዓመት በእስራትና በግርፋት ተቀጥተናል። ክንዶቹ ለረዥም ጊዜ በቀጭን ጅማት ነገር በመታሰራቸዉ ምክንያት ጣቶቹ ደም አስከ ማንጠባጠብ የደረሰ ጓደኛችንም ነበረ።

ጥያቄ- በጅማት ታስሮ እጁ ደም ያንጠባጠበዉን ጓደኛህን ስም ታስታዉሰዋለህ?

ብረሃነ፦

የአንዱ ስም አላስታዉሰዉም። ሰለዳም የሚባል ቀበሌ ነዋሪ ነዉ። ሌላዉ በግርፋት አንድ እጁ እና አንድ እግሩ ሽባ የሆነ ጓደኛየ ሃለቃ ሓዲሽ የባላል። ቢዚያን ወቅት <ሙሹሮችና ካህናት> ሳይቀሩ <በህማማት ጊዜ ከቤተክርስትያን> ተወስደዉ ከሽማግሌዎች በቀር ሁሉም ታፈሶ ተወሰደ። ለመሸሽ የሞከረዉንእንደጅግራ እያሯሯጡ በጥይት ያሳድዱት’ ነበር።

ጥያቄ- ይህ ሁሉ የተፈጸመዉ መቸ ነዉ?

ብርሃነ፦  

የካቲት ወር 1981 . ጀምሮ ማለት ነዉ።

 ጥያቄ-  ትግራይ ነጻ ከወጣች በሗላ ማለት ነዉ?

ብረሃነ፦

አዎ:: ከዚያሰዉ እንደ አዉሬ በአካባቢዉ እየተበተነ በአካባቢዉ በቀን ሰዉ የሚባል አይታይም ነበር። እነሱም ሰዉን እንደጅግራ እያደኑ” ይዉላሉ፤መሬታችንም ለታጋይ ቤተስብ ታድሎ የምንቀምሰዉ የምንልሰዉ አልነበረም።ከቀበሌ ወደ ቀበሌ የሚያስተላልፉ የነሱ ካድሬዎች ካዩን ጥይት ይተኩሱብናል፤ የተኮሱብን ጥይት አልመታንም እንጂ ቁጥር የለዉም።

ከዚያ በሗላ እየተንከራተትንና እየተራብን ቆይተን ህዳር 21/1983 . ገረዳ ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ለአቶ በርሄ እህል ስንሸከምላቸዉ ዉለን፤ቤት ገብተን ገበታዉ ቀርቦ እህል ልንበላ ስንል ቤቱ ተከበበ። የማይታወቁ ታጣቂዎች ናቸዉ። ከተሰበሰበዉ ሰዉ እኔን ጠሩኝና ዉጣ አሉኝ። መጀመሪያ እህል ይብላ እና ዉሰዱት ብለዉ የቤቱ ባለቤት ቢጠይቁም <<አስቸኳይ መልዕክት ስላለን ነዉ፤አሁን ይመለሳል>> ብለዉ ወሰዱኝ።ሌሎችም ከየአቅጣጫዉ ተሰበሰቡ።ወደ 5 እንሆናለን። ሁላችንም በስብሰባ ላይ የምንከራከራቸዉ ነበርን። <<እነዚህ ካልጠፉ ወጣቱ አይታገልም፤በታኞች ናቸዉ፤ከደርግ ለይተን አናያቸዉም>> በማለት ከዚያ በፊት እንዳጠፏቸዉ ወጣቶች እኛንም ለማጥፋት ተዘጋችተዉ እየወሰዱን ሳለ፤ እርስ በርሳችን እንነጋገር ነበር። ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ይሆናል።

ጥያቄ- የት ነበር የሚወስዷችሁ?

 ብርሃነ፦

ጫካ ነዉ፤ እኛ አናዉቀዉም። ኢሳ የሚባል በረሃ ነዉ። ምን ይሻላል? ለመሞት ለመሞት እዚሁ እንሙት እየተባባልን እንደገና ጉዞ ጀመርን። አልፎ አልፎ ነዉ እንጂ እኛን ባንድ ላይ አይወስዱንም ነበር። አንድ እዚህ፤ አንድ ደግሞ ራቅ አድርገዉ ሊወስዱን ከፊት ያለዉን ገፍቼ ሸሸሁ። ቁጥር የሌለዉ ጥይት እላየ ላይ ዘነበ። ፀጉሬ ላይ ትንሽ ነካኝ እንጂ አልመታኝም። አምልጬ ሕግ ያለ መስሎኝ ወደ ዋናዉ አለቃ ሄጀ <የማይታወቁ ታጣቂዎች ሌሊት መጥተዉ በደል አደረሱብኝ፤ በነዚህ ሰዎች ላይ ክትትል ይደረግልኝ፤ከየት እንደመጡ ማን እንደላካቸዉ ይጣራልኝ> ብየ አቤቱታ ሳቀርብ፡ <<እኛ እናጣራዋለን፤ እንከታተላቸዋለን>> ሚል መልስ ሰጡኝ። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለሁ ጥር 23 ቀን 1981 . ሥራ አድሬ ከንጋቱ 12 ሰዓት አካባቢ ወደቤቴ ስሄድ……..

ጥያቄ- ምንድነዉ ስራህ?

ብርሃነ፦

የቤት ስራ፤ቤት በደቦ ስንሰራ ደክሞኝ እዚያ አድሬ ነበር። አባቴ ሞቷል..እናቴ አለች፤ የእናቴ ትንሽ መሬት ነበረችን፡ ቤቴ እንደደረስኩ በረቱን ከፍቼ ለበሬዎቹ ድርቆሽ ልሰጣቸዉ ስል….የማላዉቃቸዉ ሰወች ብትንትን ብለዉ ተኝተዉ አገኘሗቸዉ። ቤቱ ተከቦ ነዉ ያደረዉ። እናንተ እነማን ናችሁ? ስላቸዉ አንዱ እያናገረኝ ሌላኛዉ በሰባት ጥይት መታኝ። በሆዴ እና በአንጀቴ ላይ ደሙ እየተንዠቀዠቀ ሲፈስ እናቴ እንዳታይና እንዳትጮህ ውስጥ ግቢ አሏት። ከዚያ በሗላ <እግሬና እጄን አንጠልጥለዉ ጎትተዉ ጫካ ዉስጥ ጣሉኝ> ሆድ ዕቃየ ተዝረክርኮ ተከፈተ። እንጀቴ ይታያል፡ቅጠላቅጠል አልብሰዉኝ ተሰወሩ።ይህ ሁሉ ሲሆን ከሩቅ ይከታተሉ የነበሩ የአካባቢዉ ሰዎች እነማን እነደሆኑ አይተዋል።

 

ጥያቄ- ስንት ነበሩ?

 

ብርሃነ፦

ወደ 10 ይሆናሉ። ሕዝቡ ተከትሏቸዉ፤ << እነማን ናችሁ? ቁሙ! ነፍስ አጥፍታችሁ አትሄዱም>> ሲላቸዉእየሳቁሄዱ በመጨረሻ ከወደቅኩበት አንስተዉ በሰልፍ ተሸክመዉኝ ዓድዋ አዉራጃ አሰተዳደር ወሰዱኝ።<<የዛሬ ብርሃነ ዕድል ነገ ለኛ ነዉ። ይሄ ልጅ ምን አጠፍቶ ነዉ በወጣትነቱ የተቀጠፈዉ?>> ብሎ ህዝቡ አቤቱታ አቀረበ። በዚህ ወቅት ሕዝቡ መቷል ብሎ ስላመነ ጉድጓዴ ሳይቀር ተቆፍሮ ነበር። ጫካ ወስደዉ እንደጣሉኝ የተነገረኝም በሗላ ነዉ።

ሕዝቡ አሰከረኔን ተሸክሞ <<ደርግን ግፈኛ ትላላችሁ እንጂ ይሄዉና የናንተም ግፍ!>> ሲሏቸዉ 15 ወጣቶች በሲሚንቶ የተሰራ የጣሊያን ጉድጓድ ዉስጥ አስገብተዉ አሰሯቸዉ።

በአጠቃላይ ሕዝቡ 500 (አምስት መቶ) ይሆን ነበር። ወጣቶቹን ካሰሩ በሗላ ህዝቡን በዱላ በታተኑት። እኔንም የሚያዉቁኝ ሰዎች ወደ አክሱም አመጡኝ በአጋጣሚ ነጮች ነበሩ ኦፕራሲዮን ያደረጉልኝ።

ጥያቄ- የት ነዉ ኦፕራሲዮን ያደረጉልህ?

ብርሃነ፦

 አክሱም ሆስፒታል። ሁለት ሰዎች ደም ሰጡኝ። ደም ጨርሼ ነበር። ይሄን ሲነግሩኝ እንጂ እኔ አላዉቅም። 3 ወር ያህል ሕይወቴን አላዉቅም ነበር። የተኛሁበት የጀርባየ ጠባሳ አሁንም አለ። ሕይወቴ መቆጣጠር ስላልቻልኩ መቀሌ ታከምኩ። እዚያም ስላልቻሉ አዲስ አበባ ጥቁር አምበሳ መጣሁ።

ጥያቄ- ጥቁር አምበሳ የመጣኸዉ መቸ ነዉ?

ብርሃ፦

1984 . ሚያዚያ 4 ቀን አዲስ አበባ መጣሁኝ። ጥቁር አምበሳ ሆስፒታልም አስከ መጨረሻ ጥረት አደረጉልኝ። ሕይወቴን ለማዳን በህክምና ብቻ ሳይሆን በተለያየ መልኩ ሲረዱኝ ቆይቶ መጨረሻ ሲያቅተዉ 1986 ሰኔ 16 ዉጪ ድረስ ሄጄ እንድታከም ወስኖ አሰናበተኝ። ከዚያ በሗላ አማራጭ አጣሁኝ። ቀኑ ጨለመብኝ።

ጥያቄ- ከጥቁር አምበሳ ስትወጣ ወዴት ሄድክ? አዲስ አበባ ቤተሰብ አለህ?

ብረሃነ፦

የለኝም። ታዲያ የት አረፍክ? ብርሃነ፦ እዚሁ ሆስፒታል ኮሪደር ላይ ነበር የምተኛዉ

ጥያቄ- ከተሰናበትክ በሗላ?

ብርሃነ፦

 አዎ። ከዚያ ወደ ትግራይ ሄድኩ የማላዉቃቸዉ ሰዎች አዋጥተዉ ቲኬት ቆረጡልኝ ትግራይ ከሄድኩ በሗላ ከብዙ ደጅ ጥናት በሗላ የክልሉ መንግሥት ጸሃፊት / አረጋሽ አዳነን አነጋገርኳት። <ምን ሆንክ> አለችኝ። <በጥይት ተመትቼ> <ማን መታህ?> <የህወሃት አባላት><እንዴ! ምን ብለዉ ይመትሗል? ክሰሳቸዉ።>

<ምን ብየ እከሳቸዋለሁ? ታዉቁት የለም እንዴ ራሳችሁ። እንደ ብርሃነ እንዳትሆኑ እያላችሁ መድረክ ላይ ስበሰባ ላይ ትናገሩ አልነበረም እንዴ? 500 ህዝብ በላይ አቤቱታ ለማቅረብ ሲቀርብ በዱላ አላባበረራችሁትምን? ወንጀለኛ ከሆንኩኝ ግደሉኝ፤ካልሆንኩ ግን አሳክሙኝ። አናዉቅም የምትሉኝ ከሆነ ደግሞ ስንብት ወረቀት ስጡኝና የትም ሃገር አቤት ልበል>> ስላት፡

<የለም ምንግሥት አይመታህም> አለችኝ።<መንግሥቱ ሃይለማርያም አሰቃይቶ የገደለዉ ሰዉ የለም። የእርሱ ወታደሮች ግን ሰዉ ገድለዋል።የህወሐት ወታደሮችም እንደቅጠል ነዉ የቀጠፉን፤የገረፉን።ዕድሜ ልካችንን ሲያሰቃዩን ነዉ የከረሙት። ስለዚህ ለዉጥ የለዉም።ፍርድ ቤት በደርግ ጊዜ ነበረ አሁንም አለ። ያለዉ ፍርድ ቤት ነዉ እንጂ ማሕበራዊ ፍርድ ቤት አይደለም።የመሰላችሁ ፍትህ ስጡኝ> ስላት፡

 

<ግብረሰናይ ድርጅቶች ጠይቅ አለችኝ።> <300 በላይ ግብረሰናይ ድርጅቶችን አነጋግሬመንግሥት ያለ እኛ ፈቃድ ማንንም ሰዉ በግለሰብ ደረጃ እንዳትረዱ የሚል ማስጠንቀቅያ ሰጥተውናልብለውኛል፡ እኔ 60 ሚልዮን ሕዝብ በላይ ስለማልበልጥ ብጠይቃቸዉም መልስ አጥቻለሁ።> ስላት

<ይህንን ነገር እንዴት ልታወቅ ቻልክ?> <ይሄማ ግልጽ የሆነ እኮ ነዉ>ስላት <ይሄማ የፓለቲካ አዝማሚያ ነዉ> ብላ ወዲ ሻምበል የሚባለዉን የፖሊስ አዛዥ ጠራች ።እሱም መጣ።ሌሎችም ተከተሉ።ድምፅ እንኳ ወደማይሰማበትአንደር-ግራዉንድአስገቡኝ።

ጥያቄ- አንደርግራዉንዱ እዚያዉ ምክር ቤት ዉስጥ አካባቢ ነዉ ያለዉ?     

ብርሃነ፦

 አዎ። 800-1130 ድረስ ጎሮሮየ ደርቆ መናገር አስኪያቅተኝ ድረሰ በጥያቄ አፋጠጡቡኝ።

ጥያቄ- የሚጠይቁህ ምን ነበረ?

ብርሃነ፦

የደረሰብህ ነገር ተንትነህ በሙሉ ንገረን፤ያየሀዉ ነገር ሁሉ ተናገር፤ሙሉ መብት ሰጥተንሃል አሉኝ። እኔ በመጀመሪያ የቤተክህነት ተማሪ ነበርኩ።ወላጆቼ ቤተክርስትያንን እንድታገለግል ለቤተክርስትያን ሰጥተንሃል አሉኝ። እኔ በመጀመሪያ ደረጃ የቤተ ክህነት ተማሪ ነበርኩ።ድቁናየ ስቀበል ደግሞ ታጋይ ሐጎስ የሚባል የወረዳ አስተዳዳርየድቁና የምስክር ወረቀቴን ቀደደዉ።ቀጥለዉ ታገል ተባልኩ። እኔ አልታገልም ሰርቼ ነዉ የምበላዉ ስላቸዉ፡የለም መታገል አለብህአሉኝ። መጨረሻ ወጣቱን በታኝ ነህ! አሳዳሚ ነህ!> አሉኝ።የበተንኩት ሰዉ የለም።ብርሃነ እንዳትታገል ብሎኛል የሚል ሰዉ ካለ አምጡት አልኳቸዉ።

 

መጨረሻም ወጣቱን ማፈን ጀመሩ። ማፈን ማባረር ሲጀምሩ እኛም የምንገባበት ቦታ አጣን።ተረበሽን፤ የት እንሂድ? ገሚሶቹ ወጣቶች ወላጆቼ በእኔ ሰበብ ከሚሰቃዩ አኔ ልሙት እያለ ወደ ትግል ግምባር ሄዶ ሞቷል።እላዩ ላይሳር በቅሎበታል’።የተቀረንም ሰዉነታችን በጥይት ተበሳስቷል።እሳት ጨብጦ፤ፈንጅ ረግጦ ለስልጣን ያደረሳችሁ ወጣት በየፌርማታዉ ወድቋል፡ግማሶቻችንም ጠፍተናል።

ለምሳሌ ያህል ይግዛዉ ጣሰዉ - ከማይጓጓ ፍቱሕ /ሕይወት - ከማይዳዕሮ አለቃ ሐጎስ- ከማይደዕሮ /እግዚአብሔር= ከደዕሮ ሸዊቶ ዓለምሰገድ ይግዛዉ -ከዳዕሮሸዊቶ አረፋይኔ ከገረዓ፤ አበበ ገብረአብ - ከገረዓ ሲጠቀሱ ከነዚሁ አንዱ አኔ ነኝ።

ጥያቄ- እነዚህ የተገደሉ ናቸዉ?

ብርሃነ፦

ታፈነዉ ተወስደዉ የጠፉ፤አድራሻቸዉ የጠፋ ናቸዉ።

ጥያቄ- አሁንም የት አንዳሉ አይታወቅም?

ብርሃነ፦

የሉም! በቃ!....ለአብነት ያህል ከነዚህ ሰዎች አንዱ እኔ ነኝ። ጊዜ ከሰጣችሁኝ በመቶ ሚቆጠሩ ሰዎች አዉቃለሁ አልኳቸዉ። በመጨረሻ <መሬት ተወስዶብኛል ብለሃል ማን ነዉ የወሰደዉ?> አሉኝ። አኔ እዚህ ሆኜ መሬቴ ተወስዷል፡መሬት የለኝም።የሚል መልስ ሰጠሗቸዉ። <በምን ትደዳራለህ> አሉኝ፤ <ለምኜ ዕድሜ ለሕዝቤ> የሚል መልስ ሰጠሗቸዉ። <በል አሁን የምትፈልገዉ ምንድነዉ? ደረሰብኝ የምትለዉ በደልስ ምንድነዉ?> አሉኝ <<እኛ የትግራይ ተወላጆች በሦስት ፓርቲ ብዙ ችግር ደርሶብናል።ከኢትዮጵያ ሕዝብ በተለየ ሁኔታ የትግራይ ህዝብ በደረግ በሻዕቢያ በህወሐት ተበድሏል። እንደዚህ ሆኖ እያለ የደርግ ባለስልጣኖች ለፈጸሙት ግፍ በፍረድ ቤት ሲጠየቁ እኛስ ለምን መፍትሔ ለምን አይሰጡንም? ለምሳሌ ለደርግ ባለስልጣናት በጀት መድባችሁ ጠበቃ አቁማችሁ /ቤት እንዲቀርቡ አድርጋችሗል።በህወሐት እና ፡በሻዕቢያ በኩል በደል የደረሰብን ሰዎችስ ምን እንሁን? እኛም እኮ ሰዎች ነን።ቅጠል አይደለንም።መፍትሔ ለምን አይሰጠንም?>>ብየ መልስ ሰጠሗቸዉ።

እንዲያዉም የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገብሩ አስራት <<በትግላችን ወቅት ያጋጠሙን አንዳንድ ችግሮች በአሁኑ ሰዓት ሊያስጠይቁን አይችሉም።>> የሚል መለስ በመድረክ ላይ ተናገረ።

ጥያቄ- በስብሰባ ላይ ነዉ?

ብርሃነ፦

በስብሰባ ላይ የተናገረዉና በቴሌቪዥን የቀረበ ነዉ ፤መልስ የሰጠዉ። እኔ የተናገርኩት እና ሌሎችም ቤተሰቦቻችን አምጡልን፡ሞተዉም እንደሆነ ንገሩን ብለዉ አቤቱታ በማቅረባቸዉ ነዉ።

ጥያቄ- ከእነ ወዲ ሻምበል ጋር በእንዴት ተለያያችሁ?

ብረሃነ፦

መጨረሻ ላይ አሁን የት ነዉ ምትኖረዉ አሉኝ? እኔም አቅጣጫ ቀይሬ እዚህ ቦታ ነዉ የምኖረዉ አልኳቸዉ። ተከትለዉ ሊይዙኝ ነዉ የፈለጉት።

ጥያቄ- እዚያዉ ትግራይ ዉስጥ ነዉ ያልከዉ?

ብረሃነ፦

አዎ።መቀሌ ዉስጥ የሀሰት አድራሻ ነግርያቸዉ፤ ከከተማ ወጥቼ ቲኬት አስቆርጨ /አበባ መጣሁ። /አበባ እንደመጣሁ ድርጅቶች ዉጭ ልከዉ እንዲያሳክሙኝ ጠየቅኩ።

ጥያቄ- የዉጭ ድርጅቶችን ነዉ?

ብረሃነ፦

አዎዳዉተር ኦፍ ቻሪቲወደ ሚባለዉ ድርጅት ሄጀሲሰተር ካትሲል ካሲንየምትባል አነጋግሬያት አልቀበልም ብላኝ ነበር።ዶክሜነቴን ካየች በሗላ ግን ተቀብላ ፈቃደኛ ከሆንክ ዉጭ ገንዘብ አሰባስቤ ለንደን ወስጄ ላሳክምህ አለችኝ። እኔም ፈቃደኛ ሆኜ ያለኝን ዶክሜንት እና ፎቶግራፌን ጭምር ሰጠሗት። እርግጠኛ አይደለሁም ገነዘቡ ሲገኝ እነግርሃለሁ አለችኝ።

እሺ ብየ ስጠብቅ 1988 . ነሐሴ አካባቢሲስተር እዉነቱየምትባል የሷጸሃፊእና አሷ ሆነዉ <ገንዘቡ ተገኝቶልሃል ዉጭ ትሄዳለህ፤አሁን አሁን ፎርሙን ትሞላለህ > አሉኝ። እሺ ብየ ፎረሙን ሞላሁ።የምታዘጋጀዉ ነገር ካለ አዘገጅ አለችኝ። ተዘጋጀሁ። በዝግጅት ላይ እያለሁ ነሐሴ መጨረሻ ታመመምኩ። ምኒሊክ ሆስፒታል ተኛሁ።

ጥያቄ- ከምኒሊክ ሆስፒታል ተኝተህ ከወጣህ በሗላ ከሲሰር ካትሲል አልተገናኘህም?

ብርሃነ፦

ለምሳሌ ያህል ሲሰተር ጤናየ በአካል ጉዳዩን ታዉቀዋለች። / ሙሉጌታ እና / ሥዩም የሚባሉ ባሉበትሲሰተር ካትሲል” <እኔ ከሁለት ሳምንት በሗላ ወደ ዉጭ አልከዋለሁ።ጊዜያዊ ዕርዳታ አድረጉለት ገንዘብ አሰባስቤለታለሁ> ትላቸዋለች። እነሱም የዉጭ ዜጋ ሆነሽ እንደዚህ ካደረግሽ እኛ የኛ ወገናችን ሆኖ ዕርዳታ የማናደርግለት ምንም ምክንያት የለም። አሏት። ከዛ አስወጥታ ቤቷ ድረስ ወሰደችኝ። ቤቷ ከወሰደችኝ በሗላ

ጥያቄ-እራሷ ቤት?

ብርሃነ፦

 አዎ። መኖሪያ ቤቷ ከወሰደችኝ በሗላ፤ሲሰትር ጆኣንየምትባል ሃኪም ነበረች። እገሬም መንቀሳቀስ አይችልም ነበር፡ በጣም ደክሜአለሁ። ከሆስፒታል የታዘዘልኝ መርፌ ነበርና <ልዉጋህ መሬት ዉረድ ከአልጋ > አለችኝ።አሁንሴንት ሜሪነዉ የምትሰራዉ። አስክትነግሪኝ ድረስ አልቆይም ወርጄ እወጋ ነበር፤ነገር ግን አቅም የለኝም ሁሌም አልጋ ላይ ነዉ ተኝቼ የምወጋዉ> ስላት፤እግሬን ጎትታ መሬት ላይ ወረወረችኝ።ደም ፈሰሰኝ።አለቀስኩ።

 በሗላ የትግራይ ኢሮብ አካባቢ ተወላጅ የሆነችሲሰተር ሳባየምትባል የሰጠችኝ መልስ << ብርሃነ! ይህ እኮ የካቶሊክ ድርጅት ነዉ፡ ለምን ቅድስት ማርያም ሄደህ አትለምንም?>> አለችኝ። ከዚያም ለሲስተር ካትሲል <<የካቶሊክ እማኞች እያሉ ይሄ እንዴት ይሄዳል? የተሰበሰበለት ገንዘብ በካቶሊክ ድርጅት እንጂ በኦርቶዶክስ ድርጅት አይደለም፤ሊሄድ አይችልም>> ብላ ተቃዉሞ አቀረበች። በወቅቱ ለእኔ ይነገረኝ የነበረዉ ግን ገንዘቡ እንደመጣ ከሁለት ሳምንት በሗላ እንደምሄድ ነበር የተነገረኝ።>>

ጥያቄ- ሲስተር ሳባ የተቃወመችህ ኦርቶዶክስ ስለሆንክ ነዉ ወይስ ከህወሐት ጋር ግንኙነት ኖሯት ኖሯል ይሆን?

 ብርሃነ፦

ያን ጊዜ በህወሐት እንደተመታሁ አያዉቁም ነበር። እንዲያዉም ግልፅ አድርጌ አልናገርም ነበር።

ጥያቄ-ከዚያስ ምን ተከተለ?

ብረሃነ፦

በሰኔ ወር 1990 . ፈረንጇ አዲስ ወረቀት አምጣልኝ እና እሞክራለሁ ስላለችኝ ሆስፒታል ከጤና ጥበቃም ጭምር አስፅፌ ሰጠሗት። ማስረጃዉን ስሰጣት ክረምቱን ዉጭ ነዉ የምቆየው ገንዘብ አሰባስቤ እመጣለሁ አዚሁ እየሰራህ ቆየኝ>> አለችኝ። ተመልሳ ስትመጣ <<ትንሽ ገንዘብ አግኝቼአለሁ እና እንዳልከዉ ኬኒያ ብትሄድ ምን ያህል ያድኑኛል ብለህ ታምናለህ? >> አለችኝ። እኔም <<እርግጠኛ አይደለሁም፤ ነገር ግን ወደዚያዉ የሚመላለሱ ነጋዴ ዎች ስላሉ ከነሱ ጋር ልመካከር።>> አልኳት። እንግዲያዉስ ተነጋገርና በአጭሩ ቀን መልሱን ስጠኝ>> አለችኝ።

ነጋዴዎቹ የሕክምና ማስረጃየን ኬንያ ከወሰዱ በሗላ <ኬኒያ ደርሰን ለዶክተሮች አሳየነዉ፡ የሕክምናዉን ወጪ ግምቱን እንጂ ከወዲህ ይህን ያህል ይፈጃል ማለት አንችልም፡የራጁ ዉጤት ስለሌለም ለመገመት ያዳግተናል፤እንደሚታየዉ ጉዳቱ ከባድ በመሆኑ 15ሺህ ዶላር በታች አይበቃዉም>> መባላቸዉን ገለጹልኝ።

ይህንኑ አምጥቼ፤ በአማርኛ ተጽፎ የነበረ፤ በእንግሊዝኛ አስተርጉሜ ሰጠሗት።<<በል ተዘጋጅ፤ አሁን ትሄዳለህ፡ፓስፖርት አዉጣ>> አለችኝ።ፓስፖርት ካወጣሁ በሗላ ወደ ናይሮቢ ከመሄዴ በፊት ገንዘቡ ይሰጠኝ ችግር ሊያጋጥመኝ ይችላል እና ትላልቅ ሰዎች ስላሉ ገንዘቡን ለነሱ ስጪሊኝ>> ስላት <<የለም እዚህ አልሰጥም ከኢንግላንድ ቀጥታ ከአባ ሚካኤል 15 ሺህ ዶላር ተቀብለህ ታክመህ ትመጣለህ።ካነሰህ ከዚያ ደዉለህ ንገረኝ>> ብላ አድረሻ ሰጠችኝ።

ጥያቄ-ኣባ ሚካኤል ደግሞ መናቸዉ?

ብረሃነ፦

 የአባታቸዉን ስም አላቅም፡ ፈረንጅ ናቸዉ።ካቶሊክ።አድራሻቸዉ ጽፋ ሰጠችኝ።ያለ ተቀባይ ቀጥ ብየ ሄድኩ። ከዚያ ስደርስ ችግር መጉላላት ደርሶብኛል።እግዚአብሔር ጥሎ አልጣለኝም ከዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ትብብርና ዕርዳታ አድርገዉልናል። በገንዘብም በሌላም።ከእኝህ ሰዉ ጋር ያገናኙኝም አነሱ ናቸዉ።በሗላ ግን የተጠቀሰዉገንዘብ አላገኘሁም።

ጥያቄ- ሰዉየዉን ስታገኛቸዉ የለም አልሁ?

ብርሃነ፦

 ትንሽ ገንዘብ ነዉ ያለዉ አሉኝ።<ምን ያህል አለ?> ስላቸዉ <2ሺህ> አሉኝ። 2ሺህ ዶላር በናይሮቢ ደረጃ ለቀለብ እንኳን አይበቃም ብየ ለሲስተር ክርስቲና አዲስ አበባ ደወልኩላት። በኬንያ የታወቀ ሆስፒታል ስንት ዶላር እንደሚያስከፍሉ ተመርምረህ ወይም ግምቱን ላክልኝ ወይም ይዘህ አለችኝ፡ እኔም ኬንያ ዉስጥአጋርካን’ በሚባል ሆስፒታል / ጆን የሚባል ሃኪም 1 ሳመንት መርምሮኝ ዋጋዉን አሳወቅኳት።ሁሉን ነገር ካየ በሗላ 4 ወር ትተኛለህ፤ሦስት ዓይነት ኦፐራሲዮን ታደርጋለህ እግርህም ይድናል። እንደነበረዉ ይሆናል። ለአጠቃላዩ ወጪ 6ሚሊዮን 200 ሺህ የኬንያ ሽልንግ ወይም 103 ሺህ ዶላር ትከፍላለህ አለኝ።ይህንኑ መልስ ለሲሰተር ካሰቲል ሰጠሗት።

ሲስተር የሄን ጊዜ ፈነጠዘች። <3ጊዜ ዘለለች> <እንዳለ ፈረንጅ በሙሉ የግምቱን ወረቀት ሲያይ አጨበጨበ>

ጥያቄ- ለምን?  

ብርሃነ፦

በዚህ ሰነድ ከብዙ ሃገሮች ገንዘብ ስለሚሰበስቡ።..በካናዳ፤ በአሜሪካ፤ በእንግሊዝና በሌሎችም አገሮች ለሚገኙ በጎ አድራጊዎች ወረቀቱን እበትናለሁ። በዚህ ሰነድ ገንዘብ ሲመጣ ተመልሰህ ትሄዳለህ ትለኛለች።

እሺ ብየ በመጠባበቅ ላይ እያለሁም ጋሽምየጉዞ ወኪል’ ልካ ገንዘብ ጨምረን ስለምንልከዉ ተመልሶ ለሕክምና ስለሚሄድ ከቲኬቱ ከሚመለሰዉ ገንዘብ መልሱት ብላ እዚያዉ አስቀሩት። ከታህሳስ አስከ ሚያዚያ ሲያመላልሱ አቆይተዉኝአለርት’ ሆስፒታል እንሂድ አሉኝ።

<< አለርት ሆስፒታል ስጋ ደዌ ህክምና ነዉ ያለዉ፤የኔን በሽታ አይመለከትም፡ ባለሞያወቹ ጥቁር አምበሳ / ነዉ ያሉት ስለዚህ አልሄድም> ብል፡ <እገሌ ከሚባልደ/ ጋር ተስማምተናል።> አሉኝ።

ምንድነዉ ምትስማሙት 5 ዓመት ሙሉ መለመኛ ሆኜ ተቀምጫለሁ። ከዚህ በሗላ መለመኛ ሆኜ መቀጠል አልፈልግም። ያገኘሁት ፋይዳ የለም። ስለዚህ ባላችሁት መሰረት ላኩኝ፡ አንልክም የምትሉ ከሆነ ግን በስሜ የተዋጣዉን ገንዘብ ስጡኝ፡ የትም አገር ሄጄ ታክሜ እድናለሁ> ስላቸዉ ሲስተሯ ተደበቀች።

በሗላ ባሕር ዳር ሄዳ መሸሸግዋን አወቅኩ። ባሕር ዳር ሄጀ ለፓሊስ ኮሚሽኑ እንዲህ ያለች ሴትዮ አለች ተባበሩኝ አልኳቸዉ። ያለችበትን ንገረን እንተባበርሃለን አሉኝ። እኔን ስታይ ትደበቃለች ብየ በሌላ ሰዉ ሳስጠይቅ እንዲህ የምትባል እዚህ የለችም አሉኝ። ከባህር-ዛፍ ዉስጥ ተደብቄ ቆየሁና መኪና ይዛ ስትወጣ ያዝኳት። ሕግ ቦታ እንሂድ ገንዘቤን ስጪኝ። ስላት፡

<<ተዉ አታጋልጠኝ፡ እኔ ሲሰትር ሜሪ ለምትባል አዉስትራሊያዊትና ለሲስተር ትብለጽ አስረክቤ ነዉ የመጣሁት፡ 1 (አንድ) ቀን ብቻ ስጠኝና አስጨርስልሃለሁ።>> አለች። ችግር የለም፡ አልኳት።በሗላ ግን ተመልሳ ወደ አዲስ አበባ ጠፍታ ሄደች።

 አግኝቻት ነበር፡ ጠፋች አልኩ።ለፖሊሶች።ፖሊሶች ለአየር መንገድ ስልክ ደወሉ። በጥዋቱ በረራ እንደመጣች አረጋገጡ። ከባሕር ዳር መጥቼሴንት ሜሪአዲስ አበባ ከተማ አገኘሗት። ሳገኛት <<በይ አሁን ! ! እላለሁ! መፍተሄ ስጪኝ፡>> ስላት፡

<<አዲስ አበባ የመጣሁት እኮ ስላንተ ጉዳይ ለመነጋገር ነዉ። የባንክ ደብተር ከፍተህ እኔ ጋር >> አለችኝ። እዉነት መስሎኝ ይህንን ሰኔ 20ቀን 1991 . ከተነጋገርን በሓላ ሰኔ 22 ደብተር ከፍቼ ወደ ሴንትሜሪ ስሄድ ጽሁፍ አዘጋጅታ ድርጅቱን ሰራተኞችና ሌሎችም የማይታወቁ ሰዎች ይዛአንደር-ግራዉንድዉስጥ አስገብታ፤መስኮትና በር ተቆልፎ በቀኝና በግራ እጄን ይዘዉ በማላምንበት ወረቀት ፈርም አሉኝ። በማላዉቀዉ ጉዳይ አልፈርምም አልኩ።

ጥያቄ- ምንድነዉ የምትፈርመዉ?

ብርሃነ፦

ሕክምና አልፈልግም፤ምናምን የሚል ይዘት ነበረዉ።

 ጥያቄ-

አላነበብከዉም?

ብርሃነ፦

 ትንሽ ነዉ ያየሁት አላነበብኩትም።3ገጽ ነዉ የተጻፈዉ።በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ። እምቢ ስላቸዉ ጊዜ ሰራተኞቹ ለመኑኝ። <<የሰዉ እንጀራ አትዝጋ፡ ለምን አትፈርምም? የሰጠችህ ገንዘብ አለ።አሉኝ። ልወጣ ስል ከለከሉኝ።በየት ልዉጣ?! በሩ ተቆልፏል።

ከዉስጥ ሌላ ክፍል አለ፦ ፊታቸዉ እንዳይታይ ኦፐሬሽን እንደሚያከናዉን / ዓይናቸዉ ብቻ የሚታይ ሰዎች ጨምብል አጥልቀው ጩቤ እና መሳሪያ ይዘዉ ደረቴ ላይ ደገኑብኝ። ካሁን በሗላ ወይ ለጋዜጠኛ አልያም ለፖሊስ ከተናገርክ ወዮልህ! ትፈርማለህአትፈርምም? የማን ገንዘብ ልትበላ ነዉ?ካንገራገርክ እዚሁ እንደፋሃለን!>> አሉኝ።

የነሱን ዘዴ ስላወቅኩ ገድለዉ በቆሻሻ መኪና ሊጥሉኝ እንደፈለጉ ግምት ስላደረብኝ ችግራችሁ ይሄ ከሆነማ አምጡ፡ እፈርምላችሗለሁ።>> ብየ ፈርሜ 5 ሳንቲም ሳልይዝ ወጣሁ። ሁሉንም ለፖሊስ ጣቢያ፤ለጠቅላይ / ቢሮ ለፍትሕ /ርና ለዉጭ ጉዳይ / በአስቸኳይ አሳወቅኩ።

ጥያቄ- ማመልከቻ ነዉ?

 ብረሃነ፦

 ማመልከቻ ባስቸኳይ በፖስታና በተለያዩ መንገዶች 70 ብር በላይ አዉጥቼ ላክሁ። የተሰጠኝ መልስ ግን የለም። የዉጭ ጉዳይ / ከስንት ጊዜ በሗላ እንዲጣራ ብሎ ለፌደራል ፓሊስ አስታወቀ። መጨረሻ የማይረባ ገንዘብ ሰጥተዉ አሰናበቱኝ።

ጥያቄ-ማን?

ብርሃነ፦

 እነሱ።

ጥያቄ- እነሱ እነ ማን?

 ብርሃነ፦

 እነ ሲሰተር ክርሰቲኒ፡

ጥያቄ- ምን ያህል ላኩልህ?

ብርሃነ፦

 ወደ አስር ሺህ ብር ገደማ ላኩልኝ።በዛችዉ ስታከም ቆየሁ። መንግሥትም ዞር ብሎ አላየኝም። አስካሁን ድረስ በዛች ገንዘብ ነበር ቆየሁት። አሁን ግን የምቀምሰዉ እንኳ ቸግሮኛል።

 

ጥያቄ- ጠ// ቢሮ አመልክተህስ ምንም ምላሽ አልመጣም?

 

ብርሃነ፦

ከሦስት ወር በሗላ ከፍትሕ / እና ከአደጋ መከላከል ጠይቅ የሚል መልስ ነዉ የተሰጠኝ።

ጥያቄ- በፖሊስ በኩልስ?

 

ብርሃነ፦

ፖሊስ እና ፍትሕ ብንጠይቃቸዉ አቃቤ ሕግ የዉጭ ዜጋ ለመያዝ ማን ፈቀደላችሁ? ብሎ ይከሰናል! ስለዚህ ዓቃቤ ህግ የጻፈልን እናጠራለን ብለዉኝ ነበር። ፌደራል ፖሊስ በተደጋጋሚ አቤቱታ አቅርቤ ለፍትሕ / ደብዳቤ ጻፈልኝ። ይሄ ድርጅት በመንግሥት ተመዝግቧል ወይስ አልተመዘገበም? ባስቸኳይ መልስ ስጡን ብሎ ጻፈ። ደብዳቤዉን አላየሁትም፡እንደዚያ የሚል ደብዳቤ ተጽፏል አሉኝ። ፍትሕ / አቶ መስፍን ጋር ሂድ አሉኝ።

ጥያቄ-መስፍን ግርማ የፍትሕ / የነበሩት?

 ብረሃነ፦

 አሳቸዉ ጋር ስቀርብ አቶ መስፍን <<ይሄ ድርጅት የዉጭ ዜጎች ስለሆኑ በዉጭ ስለሚያስጠይቀን ልንጠይቃቸዉ አንችልም >> ሲሉ መለስሉኝ።

ጥያቄ-ከዚያ በሗላ አልጠየቅክም?

ብርሃነ፦

 ከዚያ በሗላ ተስፋ ቆረጥኩ። ልጠይቅም አልችልም።ብጠይቅም ተሰፋ አልነበረኝም። ሁሉንም ቦታ አቤት ብያለሁ።ከዚያ ወዲያ የት አቤት ልበል?

ጥያቄ-አሁን አንተን የሚረዳህ ማን ነዉ?

ብርሃነ፦

 እንዲሁ አንዳንድ በሁኔታየ ያዘኑልኝ፤የሆዴን የሚያዉቁ ሰዎች በይበልጥ የአዲስ አበባ ዶክተሮች ይረዱኝ ነበር። በአብዛኛዉ ደግሞ አንድ ዶክተር የተባበሩኝ ነበር። ለቤት ክራይም ይከፍሉልኝ ነበር። እሳቸዉ ከዚህ ከተቀየሩ በሗላ ግን በሕክምናዉም፤በመድሃኒቱም በጣም ጨልሞብኛል።

ጥያቄ-ተከራይተህ ነዉ የምትኖረዉ?

 

 ብርሃነ፦

ተከራይቼ ነዉ።ከፈረምኩ በሗላ ከነበርኩበት አካባቢ እየመጡ አላስቀምጥ አሉኝ። እየደወሉ እቤት እየመጡ ብርሃነ አለ ወይ እያሉ ሲያሰቸግሩኝ የግድ ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ።

ጥያቄ-አሁን የት ነዉ ያለኸዉ?

 ብርሃነ፦

 እየከፈልኩ ወይንም ከማቃቸዉ ሰዎች ካገኘሁ ከነሱ ዘንድ አድራለሁ

ጥያቄ- እንጂ ቋሚ ቤት የለህማ?

ብረሃነ፦

 ቃሚ ቦታ የለኝም።

ጥያቄ- አሁን ወላጅ እናትህ ዓድዋ ናቸዉ?

 

ብርሃነ፦

 ጥቁር አምበሳ ሆስፒታል እያለሁ ነች ከዚህ ዓለም ተለየችኝ።

ጥያቄ-  እህት እና ወንድሞችህስ?

ብርሃነ፦

 በዚህ የተነሳ የት እንዳለ እንኳ አላዉቅም። ሸራሮ አሉ ይባላል፡ ማን ወደ እዛ እንደወሰዳቸዉ አላቅም።

ጥያቄ- እንደምትነግረን ሥር የሰደደ በደል ደርሶብሃል። በደሉም ማብቂያ አጥቷል። እንደምናየዉ በሰዉነትህ ላይ ያለዉ ቁስል እጅግ እጅግ ያሰቅቃል። ሽታዉም እንዲሁ። አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም መንግሥት ምን እንዲያደርግልህ ነዉ ምትፈልገዉ?

ብረሃነ፦

እካሁን የቆየሁት በኢትዮጵያ ህዝብ እና በኢትዮጵያ ዶክተሮች ድጋፍ ነዉ። 9 (ዘጠኝ) ዓመት ላቆየኝ ለሰፊዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ። አሁንም ቢሆን ሰፊዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በመንግሥት እና በዉጭ ድርጅቶች የደረሰብኝን ግፍ ግምት ዉስጥ አስገብቶ ችግሬን እንዲከታተልልኝ እፈልጋለሁ።

በሁለተኛ ደረጃም፤ በዘህ እሸት የወጣትነት ዘመኔ ካለሁበት አሠቃቂ ስቃይ እና አስከፊ በሽታ እንድላቀቅ ይረዳኝ ዘንድ በተቻለ መጠን እዲተባበረኝ በትህትና እጠይቃለሁ።

ጥያቄ-

ዋናዉ በሽታህ ያለዉ እግርህ ላይ የሚታየዉ ነዉ? ወይስ ሌላ ነዉ?

ብርሃነ፡-

አንጀቴ ደም እና መግል ያለማቋረጥ ሆዴ ዉስጥ እየፈሰሰ ነዉ። (ቁስሉን እያሳየ) ይሄ በገሃድ ሚታይ እና በባለሞተኞችም የተረጋገጠ ነዉ። ካሉት በታች፤ከሞቱት በላይ ሆኜ ሕይወቴ በቋፍ ላይ ነች። 24 ሰዓት በስቃይ በችግር እተጠበስኩ (በምሬት እያለቀሰ) ነዉ ያለሁት።//-/

ኢትኦጵ፦ አመሰግናለሁ አቶ ብረሃነ።

ማሳሰቢያ ከላይ የቀረበዉ ቃለ መጠይቅ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን በመጽሄታቸዉ አትመዉ ለታሪክ ማሕደር የተዉልንን የኢትኦጵ መጽሄት አዘጋጆች ከፍተኛ ምስጋናየን አቀርባለሁ።የትግራይ ነፃ አዉጪ ድርጅት መሪዎችበትግራይ ዲያቆናት እና ካህናት እንዲሁም ወጣቶች ላይ በስብእናቸዉ ያደረሷቸዉ የመብት ረገጣ ወንጀሎች ሳይጠየቁበት ዓይናቸዉን በጨዉ አጥበዉ ዛሬም በዉሸት ዓለም!” እናሞኛችሁ ሲሉን፤ የትግራይ ህዝብ ዕምባ ከጉዳይ ሳይቆጥሩ ከነኚህ እርኩሶች ጋር እንተሻሽ የሚሉንን ዉጭ አገር የሚኖሩ እና ውስጥ አገር ያለ ቀሳውስት ነን ባዮች አብረዋቸው የሚዶሉቱ ምእመናን ተብየዎችና ሚዲያዎቻቸው ባጠቃላይ በሃይማኖት ስር ተሸሽገው የግንጠላ ፖለቲካ በማራመድ አዋጅ እያወጁ የሚፎልሉትንየሃይማኖት ነጋዴዎች ” “የፖለቲካ ሽርሙጥናቸዉንእንዲያቆሙ መጠቆም የዜጎች ሃለፊነት መሆኑን ከወዲሁ አደራ እላለሁ።

የዜጎች ደም፤ እምባ፤ኡ ዛሬም ከምድር በታች እና ከምድር በላይ ይጮሃል።ፍትህ ማግኘት ይኖርበታል። ፍትሕ ጠየቃችሁ ብለዉ የሚጠሉን ካሉ፤እኛን ሳይሆን የጠሉት ፍትሕን ነዉ። ጌታቸዉ ረዳ ሳንሆዘ ካሊፎርኒያ www.Ethiopiansemay.blogspot.com

(ምንጭ፦ ኢትኦጵ መጽሄት- ቅጽ 2 ቁጥር 016 መስከረም 1993 .) ( ጌታቸዉ ረዳ