Tuesday, October 29, 2019

የጃዋር ኑሮና ተግባሩ ነፃነት ዘለቀ Posted on Ethio Semay)


የጃዋር ኑሮና ተግባሩ
ነፃነት ዘለቀ (netsanetz28@gmail.com)
Posted on Ethio Semay)
ሰው በወደደው ይቆርባልና በጃዋር ፍቅር ያበዱ ቄሮዎችና ድጋፍ ሰጪ ፖለቲከኞች  እነሱ ብቻ  በሚያውቁት እኛ ግን ከግምት ባለፈ ብዙም በማንረዳው ምክንያት በዚህ የሰይጣን ቁራጭ ጫማ ሥር ተንበርክከው ከርሱ ተርፎ  የሚጣልላቸውን ፍርፋሪ እየለቀሙ ለርሱ ቅን ታዛዥ መሆንን መርጠዋል፤ ነገንና ከነገ ወዲያንም ከነመፈጠራቸው ረስተዋል፡፡ ይህ ጉዞ እስከየት እንደሚወስዳቸው ከአንድዬ በስተቀር እኛም እነሱም አናውቅም፡፡ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ጃዋር እያዘዛቸው እነሱ እየታዘዙ በተለይ ኦርቶዶክስንና ኢትዮጵያን ከያሉበት ድምጥማጣቸውን ማጥፋታቸውን ካለአንዳች መሰልቸት ተያይዘውታል፡፡ እየሸሸ ያለ ዐውሬ ወደኋላው ሲመለስ ሊከሰት የሚችለውን ትዕይንትም የዘነጉ ይመስላሉ፡፡ የፈሪ ዱላ አይጣል ነው ወገኖቼ፡፡ እንደፈሪ ደግሞ  ባለም ላይ ጨካኝ የለም፡፡

1.     የቄሮዎችንና የጃዋርን የግል ኑሮ ስመለከት ልዩነቱ የሰማይና የምድርን ለማለት እንኳን ይከብደኛል፡፡ እንደሰማሁትና ከአንደበቱም “እኔም አቢይም በቪ 8 እንሄዳለን...” እያለ ራሱን በጠ/ሚኒስትር ደረጃ ከተቀመጠ ሰው ጋር ሲያወዳድር እንደሰማሁት ኑሮው እጅግ ቅንጡና ያሉት መኪኖችም ጥይት የማይበሳቸው፣ በ20 ሚሊዮኖች የሚገመቱና ሁሉም ነገር የተሟላላቸው ናቸው፡፡ ይህን ሁሉ ገንዘብ አንዳችም ነገር ሳይሠራ ከየት ሊያገኝ እንደሚችል ማናችንም ከግምት ባለፈ እንረዳለን፡፡ ሌሎች አክቲቪስቶች ደህና ጫማ እንኳን ሳይኖራቸው በነተበ ሸሚዝና ባረጀ ኮት በእግራቸው ሲንከራተቱ ይህ ለኑሮውም ሆነ ለሚያራምደው የሩዋንዳው ሚለ ኮሊንስ ዓይነት ሚዲያ አንድም ዕርዳታ ከማንም ሳይጠይቅ ይህን ሁሉ ገንዘብ ለጥፋት ሲያፈስ የሚጠይቀው የመንግሥት አካልም ሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት አለመኖሩ የጃዋርን ተልእኮ ዕንቆቅልሽ በእጅጉ ያጦዘዋል፡፡ እርሱ በቀጥታና በጀሌዎቹ አማካይነት እያዘዛቸው ሕዝብንና ሀገርን በደቦ እያረዱ ያሉ ምሥኪን ዜጎች ግን ከጭፍን ታዛዥነትና ከድንቁርና በስተቀር ምንም ሀብት የሌላቸው በመጨረሻ ለከፍተኛ ጉዳት የሚዳረጉ ዜጎች ናቸው፡፡ የርሱን ኑሮና የነሱን ድህነት ሳስተያይ የታዘዘብን መቅሰፍት ከሰው ሳይሆን ከላይ ከፈጣሪ መሆኑ ይሰማኛል፡፡ እንጸልይ!

2.    አያቶላ ጃዋር መሀመድ በቅርብ ከአሜሪካ መልስ በ60 ሚሊዮን ብር ቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ የግል መኖሪያ ቤት ገዝቷል፡፡ ይህም የከተማው ወሬ ከሆነ ሰነበተ፡፡ ይታያችሁ - የትኛው አክቲቪስት ነው በዚህ መልክ እየተንቀባረረ በዚያ ላይ ንጹሓን ዜጎችን በማስገደል በዜጎች መሪር ሀዘንና በሀገር መፍረስ ከጌቶቹና ከጌቶቹ ጭፍሮች እየተሸለመ የሚኖር?

3.    ጃዋር በዚህን ሁሉ ዐረመኔያዊ ተግባሩ መያዝና ለፍርድ መቅረብ ሲገባው በመንግሥትና በክልል መንግሥት ጥበቃ ሥር ሆኖ የግፍ ግፍ የሕዝብንና የሀገርን ጥሪት እየተቀራመተ ነው - ላኪዎቹ የበጀቱለት በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠረው ዶላር አንሶት መሆኑ ነው፡፡ ለሚያደርሰው ጭፍጨፋ ድጋፍ የሚያደርጉለት በጥላቻ ፖለቲካ የተመረዙ የሱ ቢጤ ደናቁርት “ወንድማችን ጃዋር በመንግሥት ጥበቃ እየተደረገለት ስለሆነ አይዟችሁ፤ ማንም ዝምቡን እንኳን እሽ አይለውም...” በማለት ይህን   ቀንዱ ሀገር ውስጥ ጭራው ግን ውጪ ሀገር ያለ ታላቅ ክፍለ ዘመናዊ ሀገርን የማውደም ዘመቻ በማጧጧፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

4.    ጃዋር ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ተሰሚነቱም ሆነ ሀገርን በመሸጥ ያካበተው ገንዘብ ወደር አይገኝለትም፡፡ ነገር ግን ለተንኮል ሥራው ከሚያውለው ገንዘብ ውጪ ለልማትና ለበጎ አድራጎት ጉዳይ አንዲትም ሣንቲም - ለማስመሰል እንኳን - ሲያወጣ አይታይም - ለነገሩ ሰይጣንን በበጎ ሥራ ተሠማርቶ ለማየት መከጀል ከእባብ ዕንቁላል የዕርግብ ጫጩት እንደመጠበቅ ያለ ጅልነት ነው - ከመነሻው፡፡ እነቢኒያምን - የመቄዶንያውን መሥራች - ተመልከቱ፡፡ የክብር ዶ/ር አበበች ጎበናን ተመልከቱ፡፡ እነሙዳይን ተመልከቱ፡፡ ... መንገዶች በመኪናና በሰው ተሞልተው ተዘጋግተውና ተጨናንቀው ሳይ፣ ድሆች የሚቀምሱትና የሚጠለሉበት አጥተው በየመንገዱ ወድቀው ሳይ፣ የድሆች ሠፈሮች ሽንት ቤት አጥተው ቆሽሸውና ተበለሻሽተው ሳይ፣ ሕጻናት የሚያስተምራቸው አጥተው ከትምህርት ገበታ ተለይተው በየመንገዱ ሲያድሩና ሲንገላወዱ ሳይ፣ አእሩግ በየመንገዱ ሲለምኑ ሳይ፣ ሕዝባችን በርሀብና በውኃ ጥም፣ በድንቁርናና በርዛት ሲሰቃይ ሳይ፣ ... ብዙ መልካም ያልሆኑ የድህነት ገጽታዎቻችንን ስታዘብ ትዝ ከሚሉኝ አንዱ ጃዋር መሀመድ ነው፡፡ የጃዋር በጎ አድራጎት ባፍንጫችን ይውጣ፡፡ ግን “በዚህ ሁሉ ተደራራቢ ችግራችን ላይ እግዜሩስ እንዴት ቢጠላን ይሆን ይህን ጭራቅ ያዘዘብን?” ብዬ እርሱንም አማርራለሁ፤ እርግጥ ነው ከሌላው ዓለም ስለመለየታችን አላውቅም እንጂ ፈጣሪን የሚያስቀይም ብዙ ዕኩይ ተግባር እንዳለብንም አስባለሁ፡፡ ቅጣታችን ግን ከሌሎችም ዕጥፍ ድርብ እንደሚሆን እገምታለሁ፡፡ እንደኛ የተቀጣና የሚቀጣ አለ ብዬ አላምንም፡፡

5.    ጃዋር የኦሮሞ ደም እንደሌለበት በቅርቡ መረጃ ወጥቷል፡፡ እንደጊዜው ፖለቲካ ወደታች ዘቅጠን በደም መክሊት እናስብ ብንል ጃዋር በቋንቋው ብቻ ከሚገናኘው ኦሮሞ ይልቅ በእናቱ በኩል እንደሚገናኝ ለሚነገርለት ለአማራው ይጠጋል፡፡ የዝርያ ቆጠራ ደግሞ በሀገራችን ይበልጡኑ በአባት ስለሚሄድ ይህ ሰው ከኢትዮጵያ ይልቅ ለየመን ይቀርባል፡፡ ስለሆነም የመንን ያፈራረሰ ደም ኢትዮጵያንም ለማፈራረስ ሁኔታዎች ከውጭም ከውስጥም እየተመቻቹለት ነው ማለት ነው፡፡ ዕንቆቅልሽ፡፡

6.   በጥቅሉ ሲታይ ይህን መሰሉ ሰው ከየትም የዘር ሐረግ ቢመጣ ለማስመሰል ካልሆነ በስተቀር ሃይማኖትም ሆነ ባህል፣ ወግና ሥርዓትም ሆነ የሞራል ዕሤቶች ... የሉትም፡፡ የሚታዘዘው ለኅሊናው ሳይሆን ቁሣዊ ድህነትን ከማሸነፍ ረገድ ከየትም ለሚገኝ ገንዘብ ነው፡፡ ተልእኮው የእናቱን ወይም የልጆቹን አንገት ማስቀላት ቢሆንም እንኳን ከመታዘዝ ወደኋላ አይልም፡፡ የሚያናድደውና እጅጉን የሚደንቀው ግን ለዚህ ዓይነቱ የወረደ ስብዕና የሚታዘዝ ሰው መገኘቱ ነው - ሊያውም ዕልፍ አእላፍ ሠራዊተ መንጋ፡፡ (Posted on Ethio Semay)