Sunday, May 6, 2018

ኣብይ ሆይ! የት አለህ? ብለው ይጠሩሃል የመተከል አማራ ተፈናቃዮች! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


ኣብይ ሆይ! የት አለህ? ብለው ይጠሩሃል የመተከል አማራ ተፈናቃዮች!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
ጎንደር ባሕርዳር ላይ መጥተህ አማራዎችን “አማራ አማራ” የምትሉት ነገር ትቼ..የኢትዮጵያን ነገር እንዲህ እያንገበገባችሁ መልሳችሁ አማራ አማራ ስትሉ ታፈርሱታላችሁ!”  ብለህ ወቅሰሃቸዋል። ይኼው ጥቃታችንን አስቁምልን ባሉህ ሳምንት ባልሞላ አማራ በመሆናቸው ብቻ ከመተከል (ቤንሻንጉል) አካባቢ ከገዛ ድንግል መሬታቸው ከኢትዮጵያ መሬት ከተባረሩ አንድ ወር ሆኗቸዋል።

 ዘገባውን ከነስም ዝርዝራቸው እና የመሬት ባለቤትንት ከነ ቤተሰብ ብዛት፤ ለማየት እንዲሁም ከተባረሩ ወዲህ ባሕር ዳር ከተማ ሄደው ‘ስንፍጭ አማራ’ ብለው ለሚሳደቡ አማራ ተብየ የወያኔ ብአዴኖች እየደረሰባቸው ያለው ስቃይና የዜግነት ረገጣ አቤት ለማለት ሲሄዱ ‘ብእዴን እና ኮማንድ ፖስት” የተባለው የጀርን የጎስታ መንትያ ከተጠለሉበት ቤተክርስትያን እየተጎተቱ መጠለያ እንዲያጡ እየተደረጉ መሆናቸውን መረጃው ካልደረሰህ በምሁሩ ወጣት አቻምየለህ የተዘገበውን
    ከመተከል የተፈናቃይ አባወራዎች ጥፋት አማራ መሆናቸው ብቻ ነው! (አቻምየለህ      ታምሩ) May 5, 2018” http://welkait.com/?p=14163 የሚለውን ዘገባ ተመልከት።

“አማራ አማራ” የምትሉት ነገር ትቼ..የኢትዮጵያን ነገር እንዲህ እያንገበገባችሁ መልሳችሁ አማራ አማራ ስትሉ ታፈርሱታላችሁ!” ያልካቸው አቤት ባዮች በወቅቱ አንተ እንድያ ብለህ ለመለስክላቸው የጠየቁህም ይህንኑ የመበራሩ የዘር ማጥፋቱ ጥቃት ለ27 አመት በቀጣይነት እንደተፈጸመባቸው እና ያንን እንድታቆምላቸው ነበር ‘ስሞታቸውን ሲያስሰሙህ’ የነበሩት።
አለመታደል ሆኖ አንተም በእዛው ጠባብ ውንጀላ ወንጅለሃቸው ይኼው ዛሬም አንተ እየገዛሃት ባለህባት ‘ኢትዮጵያ ምድር’ አማራ ስለሆኑ ከመተከል እየተባረሩ ነው። ይበልጥ አሳዛኝ ያደረገው ደገሞ ‘በወያኔ እና በብእዴን ጎስታ ወታደሮች’ ከተጠለሉበት ቤተክርስትያን እየተጎተቱ ግማሹም የት እንደደረሱ እንዳልታወቀ እየተዘገበ ከሆነ ያንተ ቅድሚያ ምንድ ነው? ስለገደልናችሁም ይቅርታ ያልከውስ ይቅርታህ ዛሬም ባንተ ወቅት ‘እየቀጠለ’ መሆኑን አላወቅኩም ልትል ነው? እህል ውሃ ለማድረስ ለተሯሯጡ ዜጎቻቸው ሁሉ እየታሰሩና እየተዋከቡ ነው። ለምን? እኮ ለምን? 

 የሚደርስላቸው መንግሥት የለም። ስለሆንመ “ኣብይ ሆይ! የት አለህ? ብለው በኛ ጩኸት በኩል ይጠሩሃል!” ሱዳን? ጁቡቲ? አዲስ አበባ? ወይስ ኢትዮጵያ? ወዴት ብለን እናግኘህ? እያሉ ዕርዳታህን በቶሎ እንዲደርስላቸው እየተጣሩህ ነው።  

የዲያስፖራ ሊቃውንቶች በየፓልቶኩ እና በየድረገጾች “ለአብይ ጊዜ እንስጥ” እያሉ ነው። እነዚህ ወገኖች ርቀው የሚኖሩ፤ በምቾት ላይ ናቸው እና የመተከል አማራዎች ስቃይ እና የዘር ጥቃት አላመማቸውምና  “ፋታ ! ፋታ! ስጡት” እያሉ ጥብቅና ገብተውልሃል። መታደል ይሉታል ይኸው ነው! ግን እኮ ‘እነዚህ አማራዎች እየኖሩት ያሉት” ወከባ እና ስቃይ “ፋታ” አይሰጥም! አይደለም እንዴ?

አብይ ሆይ! እስኪ ይህንን ልጠይቅህና ትችቴን ላቁም።

አብረውህ ቤተመንግሥት ቪላ ውስጥ በክብር እና በምቾት እየኖሩ፤ በአጥቂዎች እንዳይጠቁ “በልዩ ኮማንዶ” እየተጠበቁ ያሉት ልጆችህ እና ውድ ባለቤትህ ‘የመተከል አማራ ልጆች በየጫካው እና በየቤተክርስትያኖች አጥር ግቢ እንኳ ለመጠለል ተከልክለው ‘በብእዴን ጎስታፖ’ ወታደሮች እየተጐተቱ እንደ እንሰሳ መድረሻ ያጡ ‘እህል ውሃ’ በተነፈጉ አማራ ተፈናቃዪች መካከል አንደኞቹ ቢሆኑ ኖሮ እና አንተ ሥልጣን ላይ ባትኖር ፤ ምን ይሰማህ ነበር? አንተም እንደ እነሱ የመንግሥት ያለህ ትጮህ ነበር። አይደለም እንዴ?

አንተ ሱዳንም ጁቡቲም ተጠምደሃል እና በምትክህ እስኪ ‘ክብርት ቀዳማይ እመቤት ፓስተርዋ ባለቤትህ” ወደ ባሕርዳር ልከህ እስኪ የመንፈሳዊው ሥራዋ ትስራ ዘንድ ላካት እና ጎስታፖዎቹን አውግዛ አማራዎቹን ከስቃይ እና ከመዋከብ ታቁምላቸው።ጎስታፖዎቹ ለተዋህዶው በተክርትያን መሪው ‘አቡነ አብርሃምን’ እየተተናኮሉዋቸው ነው እና እስኪ ክብርት ባለቤትህን ላክላቸው እና ምናልባት ለፕሮተስታንት ፓስተር ቢያዳምጡ ላክላቸውና ወከባውን እና ሌላው ቢቀር ቤተክርትያን ግቢ ውስጥ እንኳ እንዲጠለሉ በዚህ ወገናዊ አስተዋጽኦ አድርግላቸው? ከዚህ መንገድ ሌላ በምን አሳምነን እንጠይቅህ?

እውነት፤እውነት እላለሁ፡ ዲሞክራሲህ በቀረላቸውና ቤተክርስትያን ግቢ እንዲጠለሉ አስፈቅድላቸው! ለመሞት ትንፏሹ ‘በውጪ ነብስ - ግቢ ነብስ’ እያጣጣረ ያለውን ሰው እንዳይድን ዶክተሩ የያዛትን ቡና እስኪ እስኪጨርስ ‘ፋታ’ ስጡት ይባላል እንዴ ወገኖች? ትንሽ ጨከን አላላችሁም የአብይ ዲያስፖራዎች?! 27 አመት በአንድ ነገድ ላይ ይህ ሁሉ ጭካኔ እና ወንጀል ሲፈጸም ትንሽ አይቆረቁራችሁም እንዴ?
ጌታቸው ረዳ (Ethiopioan Semay)