Tuesday, February 7, 2023

“ለምን ለምን ሞተ!” የሚል ጠያቂ ወጣት በሌለበት አገር ወራሪዎች ማፍረሳቸውን ይቀጥላሉ አንቀላፊውም ማንቀላፋቱን የቀጠለ ይመስላል! ጌታቸው ረዳ 2/7/23 Ethiopian Semay

 “ለምን ለምን ሞተ!”  የሚል ጠያቂ ወጣት በሌለበት አገር ወራሪዎች ማፍረሳቸውን ይቀጥላሉ  አንቀላፊውም ማንቀላፋቱን የቀጠለ ይመስላል!

ጌታቸው ረዳ

2/7/23

Ethiopian Semay

ካሁን በፊት የኦሮሞዎች ሦስተኛ ዙር ወረራ የሚል ጽሑፍ መጻፌን ታስታውሳላችሁ። በዛው ጽሑፍ ትግሬዎችም አብሬ በውስጥ ቀኝ አገዛዝነት (ኢንተርናል ኮሎናይዘሽን) ጠቅሻቸዋለሁ። ሰሞኑን በሃይማኖት አስታክኮ የተከሰተው ኦሮሙማው ሃይማኖታዊ ፖለቲካ እየሆነ ያለው ከዚያ ከጻፍኩት ቅጥያ የቀጠለ ነው።

ስም በመለወጥ ግርማ የተላበሱ የመሰላቸው “ኦሮሞ” በሉን የሚሉ የደርግ ኦነጋዊ ምሁራን “በኦሮሞ” መጠሪያነት ተሰይመው 3/4 የኢትዮጵያ መሬት የማይገባቸው የመሬት ስፋት ይዞታ በባለቤትነት ይዘው “አማራን” በመግደልና በማስወጣት “ኦፓርታይዳዊ ክልል” እንዲመሰርቱ የፈቀደላቸው ወያነ እንደነበር ይታወቃል።

በማንኛቸውንም የታሪክ ማሕደርና ዘመን ተሰምቶ የማይታወቅ “ኦሮሚያ” የሚባል “አካባቢ” ሲጠነሰስ ወናው መነሻው አገር የመመስረት ዕቅድ ነበር። እነሆ ያንን  ለማስፈጸም አዲስ አባባን ለመሰልቀጥና በኦሮሞ “ ክልል “ አስገብቶ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ዜጋ ሁሉ ከከተማው በማስወጣት (ይም በዶዩክዩታቸው ጽፈውታል)ኦሮሞ ብቻ በማስኖር  የኦሮሚያ ዋና ከተማ ለማድረግ ነበር። ያም እያደረጉ ነው።

ዛሬ ደግሞ ለ30 አመት የቀጠለው ጸረ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ዘመቻውን በመቀጠል በሺ ዘመናት ዕድሜ ያስቆጠሩ አብያተ ክርስትያናትን በጽንፈኞቻቸው እያሰማሩ በማቃጠልና በማፍረስ 27 አመት ሙሉ ሲሰሩበት ቆይተዋል።

ታስታውሱ እንደሆን ብዙ እስላሞች ወደ ቤተክሕነት አስገብተው የቤተክርስትና መጻሕፍት አጥንተው ክርሰትያኖች መስለው በመግባት ድያቆናት ከሆኑ በሗላ ‘ክርስትያናትን” ወደ እስልምና ለመለወጥ እንዲያመቻቸው “ወደ እስልምና ገብተናል” እያሉ የክርስትናን መጽሕፍተ ሲዘልፉና በራዲዮና ቴ/ቪዥን “ዲያቆን እገሌ ቄስ እገሌ” እስልምናን ተቀብለዋል እያሉ ፖለቲካ ሲሰሩ መቆየታቸው ታውቃችሁ።

ዛሬ ደግሞ  ለፖለቲካ እንዲያመቻቸው ቄስ መስለው የገቡ የኦሮሞን ሕዝብ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚሰብኩ “ኦነጋዊ ቄሶች” በየቦታው በይፋ አብያተ ክርሰትያናትን በመውረር አማራ እና ኦርቶዶክስ አስወጥቶ “ኦሮማዊ ኦርቶዶክስ” ለማድረግ እየጣሩ ይገኛሉ። በዚህም ብዙ የሰው ህይት ጠፍቷል።

እነሱ ስራቸውን እየሰሩ ነው፡ ሲሰሩም ቆይተዋል። ዕንቅልፉን መተኛት ያልጠገበው ኦርቶዶክስ ክርስትያን ተከታይ ወጣት እኔ እንደማየው በጉልበት ከወራሪው ነጥቆ ፍትሕ እጁ ውስጥ ከማስገባት ይልቅ ወደ ሰማይ አንጋጦ ለ30 አመት ሲያደርገው የነበረው መጃጃል አሁንም ቀጥሎበታል። (በቁጥር ጥቂት የሆኑት መስዋእት የሆኑትን ጀግኖች አልነካሁም፤ እያልኩ ያለሁት ስለ ሚሊዮን አንቀላፊውን ነው)

ከማንኛቸውንም ምእመን የምሰማው ‘ከሃይማኖቴ የሚበልጥብኝ የለም” የሚል  ሲነገርና ጥቁር ልብስ ለብሶ ከመምበርከክ ያለፈ’ ወራሪውን መንግሥት አርዕድ በሆነ የሥራ ማቆምና የምርት የባንክ የአየር፤ የጭነትና የታክሲ መኪና ማዕቀቦችን ፤ቤት መቀመጥን፤ ሲያስፍልግም ቤመንግሥቱን ከብቦ ዛየሮችና ባንግላዴሾች እንዳደረጉት ወራሪውን መንግሥት አስጨንቆ ከሚማግጥበት ሥልጣን ማውረድ ወይንም የሚቀርቡለት ክሶች እንዲያደምጥና ተግባራዊ እንዲያደረግቻው ማስገደድ አልቻሉም።

 ይባስ ብሎ ወራሪው መንግሥት ከሳሽ ሆኖ የተገላቢጦሽ እንደገና ለሁለተኛ ዙር ጥቃት ለመፈጸም ኦሮሞ ወታደሮቹን አሰማርቶ ተነስቷል።

አሁን ጥያቄው በመንግሥት ታጣቂዎች የተገደሉ ቀሳውስትና ምዕመናን “ለምን ለምን ሞቱ?!” የሚለው መሬት አንቀጥቅጥ ነውጥ ለማድረግ ዝግጁ ናቸው ወይስ ጥቁር ልብስ በመልበስ ብቻ ወይንም ወደ ሰማይ ማንጋጠጡን ይቀጥሉባታል? ይህንን በማለቴ አንዳንድ ወገኖች ደስ ላይላቸው ይችላል፡ (ባይገርማችሁ በወጣትነቴ መንግሥቶችን በተለያዩ ወቅቶች በድፍረት ተቃውሜ በብዙ ስቃይ አልፌአለሁ፤ አሁንም እዳው እየከፈልኩ ነው።)_ ሆኖም ወደ ሰማይ እያንጋጠጡ ማታበቸውን ካንገታቸው ለ30 አመት ሲበጥሱላቸው እያዩ ወደ ሰማይ ማንጋጠጡ ምንም ፍትሕ አላስገኘላቸውም።

 ሰንደቃላማቸው በወራሪዎቹ ክብርዋን አጥታለች። የአርበኞች ሃውልትና ቅርሶች ሲፈራርሱ አሁንም ወደ ሰማይ፤ ሌላ ቀርቶ አስክንድር ነጋ ሲታሰር ሲፈታ ፤መሰል ጓዶቹም ሲታሰሩ ሲፈቱ አንስት ወንዶችና ታጋይ አርበኞች ፍዳቸውን ስያዩ ፤ በአመጽ ከዕስር አስፈትቶ መሬት አርዕድ የሆነ አመጽ ከማስነሳትና ወደ ተሻጋሪ እርከን ጎትትቶ የአገሪቱን ስቃይ ከማስቆምና የወራሪዎቹን ጉልበት በጉልበት መልስ ከመስጠት ይልቅ ለ 5 አመት ያየነው ባሕሪ  ዛሬም ወደ ሰማይ ማንጋጠጥ  ነው።

 አረቦች “አላህ ወ አክበር!” ብለው ቤን አዚዝን ሙባረክን ወዘተ… ገርስሰውታል። ኢትዮጵያዊያን በኦሮሞ ፖሊሶች ማተባቸው ሲበጠስ ማተባቸውን አስረክበው አጎንብሰው በሰላም ወደ ቤት ከመሄድ ያሳዩት አንድም የረባ ግብግብ አላሳዩም። ይህ ትህኪት የታዘበው አርበኛው እስክንድር ነጋ አንቀላፊው ወደ ሰማይ ማንጋጠጡን ብቻ አድርጎ መቀጠሉን ሲያይ ጥሎላቸው ጠፋ። ልምራችሁ የሚል አርበኛን ተስፋ አስቆርጦ አሁን ኦሮሞዎቹ የልብ ልብ አግኝተው ማተብ ከመበጠስ ወደ ቤተክርሰትያን ንብረት መውረስ ተሸጋግረው ምእመናኑን በጥይት መረሸን ጀምረዋል። ጣልያን ዞሮ በየት መጣ!

ቁማርተኛው አብይ አሕመድ ኢትዮጵያን ሕዝብ “ሾርት መሞሪያም” ይልና ያ አልበቃ ሲለው አማራውንና ሕዝቡን ጅል፤ ጅላጅል ጅላንፎ ሲል ወርፎታል። የሚገባው ነው ይላል ወዳጄ ዳግማዊ ጉዱ ካሳ።        

እንዲህ ይላል

“እዚህ ላይ ሳስበው አቢይ ጅል ያለው አማራን መሆን አለበት፡፡ አማራ ጅል ካልሆነ ባቀናት ሀገሩ ማንም እየመጣ እንዲህ ሲጫወትበት ቆም ብሎ ማሰብና ዘሩን ከዕልቂት ሀብት ንብረቱን ከውድመት ለመታደግ መነጋገር ነበረበት፡፡ አማራ ጅል ካልሆነ - ለቃሉ ይቅርታ ይደረግልኝና - ከስድስት ሚሊዮን ሕዝብ የተውጣጡ ጥቂት ወያኔዎችና ከሃያ ሚሊዮን ገደማ ሕዝብ የተውጣጡ እፍኝ የማይሉ ኦነግ/ኦህዲድ ቄሮዎች በነፍሰ ሥጋው ሲጫወቱበት ፈዝዞ ባላያቸው ነበር፡፡ አፍዝ አደንግዝም እኮ ዓይነት አለው፡፡ አማራ ምን እንደነካው ማወቅ ይቸግራል፡፡ በብዛትም፣ በዕውቀትም፣ በታሪክም ከማንም የማይተናነስ ሕዝብ ሆኖ ሲያበቃ ማንም ጩልሌ አራት ኪሎ እየገባ ሲጫወትበት ነፍዞ ዝም ብሏል፡፡”

 በማለት አግራሞቱ ግልጸ ነበር።

 አሁንም ወደ 90 ሚሊዮን የሚሆነው የኦርቶዶክስ አማኝ አማራን ከነካው “አዚም” የወጣ አልመሰለኝም። ቁማርተኛን ለመብላት የሚጣሉልህን የተከሰቱ ካርዶችን ነጥቀህ ቶሎ አስተካክለህ ወደ ጠረጴዛው ካልጣልክለት ተሸናፊ ነህ! እየሆነ ያለው ታሪክ ራሱን ይደግማል የሚባለው እንዲህ ያለ “አዚማም” ትዕይንትን ነው።

ዛሬም “አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ ኢትዮጵያ ያንተ አይደለችም ወይ” እና “ለምን ለምን ሞተ!” የሚል ጠያቂ ወጣት በሌለበት አገር ወራሪዎች ማፍረሳቸው ይቀጥላሉ፡ አንቀላፊውም ማንቀላፋቱን ይጥላል። አትነሳም ወይ! የሚለው የኔ ቅስቀሳ ሰምቶ ካልተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝቡ የማመጽና የቁጣ ቀን እንደ ፍርድቤት ቀጠሮ እየጎተተ በሄደ ቁጥር ትኩሳቱ እያዛለ ሕዝቡ በወራሪዎቹና በወራሪው መንግሥት መዳፍ ሥር ገብቶ ለዳግም ተጠቂነት የመግባት ዕድሉ እየሰፋ የመጣ ይመስለኛል።

ጽሑፉን ተቀባበሉት!!

አመሰግናለሁ!

ጌታቸው ረዳ