Sunday, June 21, 2020

ኢትዮጵያ ከአማራ ከርሰ ምድር ከፈለቀው ከጫካው አምበሳ ከአሳምነው ጽጌ በኋላ ሌላ ወንድ ታገኝ ይሆን? ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay) June 21, 2020


ኢትዮጵያ  ከአማራ ከርሰ ምድር ከፈለቀው ከጫካው አምበሳ ከአሳምነው ጽጌ በላ ሌላ ወንድ ታገኝ ይሆን?
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethio Semay)
June 21, 2020

የኢትዮጵያን ሃቀኛ ጀግኖች እያጣጣላችሁ ከባለተራዎች ጋር ሆናችሁ ነፋስ ወደ ነፈሰው የምትነፍሱ ትንንሽ ጭንቅላቶች ሆይ! ወላጆቻችሁ በመንደር ጋጠወጥ ፖለቲከኞች እየተገፈተሩ ውርደት እንዲቀበሉ ለምን ትፈቅዳላችሁ? መልዕክቴ ከ17 አመት ጀምሮ እስከ 48 አመት ዕድሜ ላለው ለአማራ ወጣት ነው። ለ28 አመት ወላጆቻችሁ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል። አማራ ማሕበረስብ በትግሬዎች እና ኦሮሞዎች እንዲሁም በሶማሌ በሲዳማ እና በመሳሰሉ አክራሪ ቡድኖች ምክንያት “ክብር ከሚነካ ስድብ ጀምሮ እስከ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ተካሂዶበታል፤ በመርዝ ግድያም ጭምር”!!!ከሰሜን ኢትዮጵያ ከምድር ባሕር (ኤርትራ) ጀምሮ እስከ ጫፍ ደቡብ ኦጋዴን ድረስ ካጫፍ እስከጫፍ ግፍ ተፈጽሞበታል። ግፉ ዛሬም ቀጥሏል”። አማራ ወጣት ከመለፍለፍ አልፎ መሬት አርዕድ ነውጥና ተቃውሞ ማሰማት አልቻለም። ለምን? ዛሬስ ምንድነው ችግራችሁ?

ለዚህ እንቅስቃሴ ባይተዋር አይደለሁም፤ ከጥዋቱ እስከ ማታው ነበርኩበት አሁንም አለሁ።  ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም እኔም ሆንክ በጣም እጅግ በጣት የምንቆጠር ኢትዮጵያውያን ለአማራ ሕዝብ ልሳን ሆነን ስንጮህ ጥቂት ነበርን። እንዲያ ሲሆን ብዙ ዘለፋ ተቀብለናል።ሚዲያዎች አፍነውን ነበር (ኢትዮ ሚዲያ፤ ኢሳት፤ ዘሓበሻ፤ ኢትዮ-ፎረም፤ አባይ ሚዲያ…..ወዘተ….)። ልክ እንደ አማራው ማሕበረሰብ እኛም ላይ በ4 መአዝኖች ተከብበን  ድምጻችን ሲታፈን ነበር። 

ግራ በሚያጋባ ሁኔታ “አማራ ነን የሚሉ እራሳቸው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጥቃቱ ተዋናይ ሲሆኑ፤ አንዳንዶቹም “ነገር አታባብሱ ውሸት ነው እንዲህ አልተፈጸመም እያሉ” ጥቃቱ እንዳይገለጽ ሚና ሲኖራቸው፤ ይባስ ብሎ እኔም በትግሬነቴ እየዘለፉ “ከአማራ በላይ አማራ ለመሆን የሚፈልግ” እያሉ እዚህ አሜሪካ ያለው  በሕዝብ ሕሊና በበጎ የማይነሱት ላንዴና ለመጨረሻ ጠውልገው የሟሸሹ፤ አማራ ሆነው ጸረ አማራ የሆኑት የኢሕአፓ ድርጅት ጀሌዎች እና የግንቦት 7 ጀሌዎች ሲዘልፉኝ የነበረውን እስከመቸውም አልረሳውም። 

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እንዳሉት ለአማራው ጥቃት ዋናው ተላላኪ የሆነው እራሱ የአማራ ምሁር ሲሆን በስም ሲጠሩት “ሆዳም አማራ” ነበር ያሉት።  አማራ ንኝ የሚለው ምሁር የወላጆቹን ታሪክ ሲረገጥ አብሮ ሲጨፍር ነበር። ኤርትራን ያልጨመረ በሴራ የተቀነሰው ሉኣላዊ  የኢትዮጵያ መልክአምድር የታተመ ካርታ የአማራ ወጣቶች እንዲቀበሉት ተደርጎ በከናቲራቸው እና በየፌስቡኩ እንዲሁም በየሱቁ በስፖርት በዓላት ቀን በደረታቸው የሚለጥፉት ካርታ ዛሬም ቅቡልነት አግኝቶ ስመለከት እጅግ ሐዘኔታ ይሰማኛል። 

ያ አልበቃ ሲላቸው አዲስ አባባ ውስጥ “ባንዲራው ይኼ ነው!!” እያሉ የሻዕቢያን ባንዴራ እያውለበለቡ አዲስ አባባ እስፖርት በዓላት ላይ በሰላማዊ ሰልፍ እና የጥምቀትና ቅዱስ ዮሐንስ በዓል ክንውን ላይ ሲያውለበልቡ አይተናል።  

እንዲያ እየቆሰልንም እዚህ አሜሪካ የሚኖሩ በየፌስ ቡኩ የተጣዱ አማራ ነን የሚሉ  የኤርትራ ነፃንት እውቅና አልሰጥም ብሎ የተሟገተው አዲስ አበባ የሚኖር አገራዊው ጀግናው “ጋዜጠኛ ታምራት ነገራን” ስብዕናው የሚነካ ስድብ ሳይቀር እየሰደቡ ለሻዕቢያ ወግነው የቆሙ አማራ ነን የሚሉ ወጣቶችም እያየን ነው። የወጣቱ የሕሊና ዝቅጠት እያሽቆለቆለ ሄዶ፤ የአገሩን ታሪክ ጠንቅቆ ባለማወቁ ሄዶ፤ ሄዶ መጨረሻ ላይ “የኢሳያስ አፈውርቅ ፎቶግራፍ” ከመኖርያ ቤቶቻቸው ግድግዳ ላይ ለጥፈው በፌስ ቡክ በቪዲዮ የሚታዩ ትንንሽ ሕሊናዎች ብዛት ባለው ቁጥር በዚህ ትውልድ ለማየት በቅተናል። 

ባጭሩ ለአማራ ውርደት የመጀመሪያው ተጠያቄ አጥቂዎቹ ሳይሆኑ ከአጥቂዎች ጋር ቆመው የሰቆቃው ገመድ አጥባቂ የሆነው ዛሬም ከበሽታው ያልተፈወሰው በኔው አባባል “አለቅላቂ አማራ” በፕሮፌሰር አስራት አባባል ደግሞ  “ሆዳም አማራው” ነው።

ዛሬ  ለ28 አመት የአማራ ወንድ ስንፈልግና ስናፈላልግ በ2012 ዓ.ም  አንድ ብርቱ በላይ ዘለቀና ቴዎድሮስ የሚመስል፤ የወንድ ሚዛን ልክ የለበሰ፤ የአማራ ጠላቶችን ያስደነበረ  እንደ መስቀል ወፍ ብቅ ብሎ ድንገት ስለተሰወረው ትንግርተኛው ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ለምን ተገደለ? አምና ስለ አሳምነው ጽጌ ሰፊ ማብራርያ ጽፌ አሳትሜአቸዋለሁ። ዛሬ ከዚህ ቀጥሎ የማቀርብላችሁ ማስረጃዎች አሳምነው ጽጌ ከመሞቱ በፊት በዘሓበሻ ቀርበው የነበሩ በአሳምነው ጽጌ አንደበት የተነገሩ እውነተኛ አውደዮ/ድምጸ ቃል/ እና በአሳምነው ላይ ሲፈጸሙ የነበሩት ሴራዎችን አቀርብላችኋ  ለሁ።

የአሳምነው ሞት አማራ ካሁን ወዲህ ያያል ተብሎ የማይገመት እጅግ ክብርና በጣም ደፋር የሰው አምበሳ ማጣቱ ሳስበው ድሮ አማራን በሚጠሉ በአክራሪ ትግሬዎች፤ አሁን ደግሞ አማራን በሚጠሉ አክራሪ የኦሮሞዎች መንግሥት እጅ መውደቁን ስመለከት አሳምነውን የሚተካ ወንድ በታጣበት ወቅት የአማራ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን እጅግ ያሳስበኛል።  

አሳምነው በህይወት እያለ ለምን በአምባቸው ተገመገመ?  ገዱ አንዳርጋቸው ወደ አዲስ አባባ ሄዶ “ቀነኒሳ ሆቴል ለ15 ቀን ተቀምጦ የሥራ ስንብት ለምንስ ጠየቀ”? የሚሉት አስፈላጊ አንኳር ጥያቄዎችን እንመልከት።

የአሳምነውን ቃል እንደዋዛ ለረሳችሁት ሁሉ በድጋሚ ላስታውሳችሁ። እያንዳንዷን ቃል ሕጋዊነትዋን ጠንቅቃችሁ ተረድዋት። እንዲህ ይላል፤

ለመረጋጋት እና እንደ አማራ ለመቆም በምናደርገው ትግል  ውስጥ የሃይማኖት አባቶች ወጣቶች ሴቶች የፀጥታ ሃይሎች አንድነታችንን የሚፈታተን ነገር ሲመጣ በንቃት መታገል አለብን፡ መሞት አለብን! ።” (አሳምነው ጽጌ)

ይህ ንግግር ሕጋዊ ነው። ተግባራዊም አድርጎታል።፡በምንም መለኪያ ሕግን ሞራልን የሚጻረር ንግግር አይደለም። ይህ ሕጋዊ ንግግር ያስደነበራቸው በአብይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞ መንግሥት እና በትግሬዎች መንግሥት የተቀናጀ “ገዳይ ቡድን” አሰማርቶ አሳምነውን ለማሰር ወደ ባሕርዳር ሲከንፍ በአልሞት ባይ ተጋዳዩ አሳምነው ጽጌ እጅ የወደቁ ወላዋዮችን ጨምሮ እራሱንም ወደ የማይቀረው ዓለም ይዞ የሄደ ክስተት ተከሰተ።

እንግዲህ አስታውሱ፡ “ለአፓርታይዱ ክልል” አዲስ አስተዳዳሪ ሆኖ የተሾመው “ዶ/ር አምባቸው መኮንን” እና አሳምነው ጽጌ መግባባት እንዳልነበራቸው በወቅቱ ሲወራ እንደነበር እናስታውሳለን። ጀኔራሉ (አሳምነው) ከመሞቱ በፊት የዘሓበሻው ሽክሹክታው ፕሮግራም እንዲህ ብሎ ዜናውን አስደምጦን ነበር።ነበረ የተበሰለውም እዚህ ልግለጽ፡

"በውስጥ አዋቂዎች አነጋግረን እንዳገኘነው መረጃ በዶ/ር አምባቸው እና በብ/ጄ አሳምነው ጽጌ መካከል ምንም ችግር ባይኖርም ዶ/ር አምባቸው ግን ብ/ጄ/አሳምነው ጽጌን ከሰሜን ሸዋ እና ከከሚሴው ጥቃት በሗላ ቁጭ አድርገው ገምግመዋቸዋል፤ ተብሏል። ለምን ገመገሙዋቸው? ይላል ዘሐበሻ (ግምገማ የተባለው በዘሓበሻ ዘገባ በተቃራኒው ወደ መደምደሚያ አቀርባለሁ)

…ነገሩን ከሥር እንመልከተው፡ ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ የደህንነትና የሰላም ግንባታ ቢሮ ሓላፊ ሆነው እንደተሾሙ በርካታ አመርቂ ሥራዎችን መስራታቸው እሙን ነው።በተለይ በተሾሙበት ወቅት በሰሜን ጎንደር እና ዓፋር ክልል ባቲ አካባቢ ታጣቂዎች ችግር በፈጠሩበት ወቅት፤ ከነዚህ ሁሉ በስተጀርባ በተለይም የህወሓት እጅ እንዳለበት በግልጽ በሚዲያ (በዜና የማሰራጫዎ ማእከሎች) በመናገር ይታወቃሉ። በተለይም በሰሜን ጎንደር ገንዳ ውሃ በነበረው ግጭት ታጣቂዎቹ በገበሬዎች ላይ ሲቶኩሱ “ፀረ አየር” መቃወሚያ መሳሪያ ታጥቀው እንደነበር መግለጻቸው ይታወሳል። “በወቅቱ በሰሜን ጎንደር በነበረው ግጭት ከመከላከያ ጋር በቅርበት እየሰራችሁ ነው ወይ?” ተብለው በጋዜጠኞች ሲጠየቁ “ከመከላከያው ጋር በላይኛው ደረጃ እየተሰራ መሆኑን አላውቅም” ማለታቸውን በወቅቱ ፓርቲያቸው ውስጥ ያሉ ወገኖች እና እንዲሁም መከላከያዎችን አስደንግጦ ነበር።
አሳምነው እንዲህ ብለው ነበር”

“በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ ይህንን ክልል የጦርነት አውድማ እና የችግር ቀጠና አድርጎ እኛ እንደ አማራ አንድ ላይ ቆመን እንደ አማራ አስበን፤ለኢትዮጵያ ወይንም ለአገር የምናበረክተው አስተዋጽኦ እንዳናደርግ እንደሆነ መታወቅ አለበት። ይህንን አስቡበት።” ሲል ተናግረው ነበር፡

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሥልጣን ለይ በነበሩበት ጊዜ ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ለጋዜጠኞች ሲሰጥዋቸው በነበሩ ምላሾች ደስተኛ አልነበሩም። በዚህ ጉዳይም ብ/ጄ አሳምነው ንግግራቸውን እንድያስተካክሉ ተነግሯቸው ነበር ። በሚፈጠሩ ግጭቶች ላይም ምንም ማጣረት ሳይደደረግ በሌሎች ላይ በጋዜጣ መግለጫም ሆነ በጋዜጣዊ ቃለ መጠይቅ ጣት መቀሰር እንዲያቆሙ እና ፖለቲካዊ በሆነ መንገድ ብቻ መግለጫዎች እንዲሰጡ ተነገሮአቸው እንደነበር ሹክ ብለውናል።” ብሎ ነበር የዘሓበሻ ዜና።
ልብ በሉ፤ ገዱ አንዳርጋቸው የተባለው የአብይ አሽከር አሳምነው ጋር የነበረው አለመጣጣም አንድ በሉ። ከዚህ በታች ያለውን ተመልከቱ።

በወቅቱ በተለይም  በጎንደር ግጭት ሲፈጠር አሳምነው ጽጌ መግለጫ ሲሰጡ የነበረውን ቀርቶ የአማራ ፖሊስ ኮሞሽነር ዘላለም ልጃለም መግለጫ እንዲሰጡ በእነ ገዱ አንዳርጋቸው ተደርጎ እንደነበርና በዚህ የተነሳ ገዱ አንዳርጋቸው ከነ አሳምነው ጋር አለመስማማት ተፈጥሮ ነበር። በኋላ ግን የአሳምነው ሃይል  እያየለ መጣ። ገዱ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ወደ አዲስ አባባ በመጡበት ወቅት በቀነኒሳ ሆቴል ሲቀመጡ የሥልጣን መልቀቂያቸው ምክንያቶች አንዱ “የጎበዝ አለቆች አስቸገሩኝ ፤ እነ አሳምነው ጽጌ አላሰራም አሉኝ” የሚል ነበር።
ገዱ ይህንን ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ 15 ቀን ቢሰጣቸውም አሻፈረኝ ብለው ሥልጣናቸውን ለቀዋል። 

ገዱ ሥልጣን ከለቀቁ በኋላና ዶ/ር አምባቸው ክልሉን መምራት ከጀመሩ በኋላ አሳምነው ጽጌን ተክቶ በአሳምነው ቦታ መግለጫ እንዲሰጡ በእነ ገዱ አንዳርጋቸው ተሰይመው የነበሩት የፖሊስ ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለምን ተክተው በምትካቸው የግንቦት 7 አመራር አባል የነበሩት የመቶአለቃ አበረ አዳሙ ከስዊድን አገር መጥተው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር  ሆነው ተሾሙ። እሳቸው ከተሾሙ ወዲህ በክልሉ ስለሚከሰቱ ግጭቶች ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጡ የሰላም እና የመረጋጋት ም/ሃላፉ የሆኑት ኮ/ል አለበል አማረ ናቸው።” ይላል ዘሓበሻ።

የኔን አስተያት ልጨምርበት፡ ወሬ አፈንፋኞቹ ከሚሴ ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት  የተሳሳቱት አሉባልታ ነገር አለ። አሳምነውን የሚወነጅሉበት ፤ በእነ ጌታቸው አሰፋ እየሰለጠነ የነበረው ሰሜን ሸዋ አካባቢዎች በኦነግ እስላማዊና “ኢንተርሃሙዌ’ አክራሪ ኦሮሞዎች ከ5 ወራት በፊት ከሚሴ ላይ ጥቃት ከመድረሱ በፊት የአማራ ክልል አካባቢዎች በተለይ የሰሜን አማራ ክልል አካባቢ፤ በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሰው በወያኔው ጌታቸው አሰፋ የኋላ ድጋፍ ሰጪ የሚያንቀሳቅሰው ሃይል አሰማርቶ እስከ ላውንቸር ተኳሾች ድረስ እያሰለጠነ እንደሚገኝ እና አሰልጣኞቹም የትግርኛ ተናጋሪዎች እንደሆኑ የሚያሳይ በሰነድ በአንድ የደህንነትና የሰላም መረጋጋት ቡድን የቀረበው ለደህንንቱ ሃላፊዎች ቀርቦ “ተቃጥሎ ቆሻሻ መጣያ ተጥሏል”  ብሎ አምባቸው መኮንን አሳምነውን ገምግሞት ነበር እያሉ በውሸት ያልሆነውን ወሬ “እንደ ውሻ አፍንጫ” እያፈናፈኑ (ምናልባትም እንደ ማፈሪያው ብ/ጄ/ል ተፈራ ማሞ የመሳሰሉ ሴረኞች ሲያፈንፈኑት የነበረውን ውሸት ሊሆን ይችላል) ሲነገር እንደነበር ይታወሳል። እንደምታውቁት አሳምነው ከማንኛቸውም የክልሉ ባለሥልጣን ከታች እስከ ላይ ድረስ እና እንዲሁም የደህንነትና የሰላም መረጋጋት አባሎች በበለጠ የአማራ ጥቃት የማይፈልግ እና “ጸረ ኦነግና ጸረ ወያኔ” መኖሩን እየታወቀ እንዲህ ያለ ዘገባ አሳምነውን ለማሳጣት፤ አሳምነው ሆን ብሎ “ዘገባውን አፍኖት ነበር” ብለው እየዋሹ ስትሰሙ እንዲህ ብለው የሚዋሹት እነማን ቡድኖች እንደሆኑ በቀላሉ  የአሳምነው ጽናት እና የሌሎቹ ጽናት ገምግማችሁ በቀላሉ ልትደርሱበት ትችላላችሁ። ጀግና ሁሌም ምሳር ይበዛበታል። እኛ ሁሉ 28 አመት ወያኔን ስንታገል የወያኔ አርበኞች ሲሉን አልነበረም? አሳምነውም ላይ የደረሰው እንደዚያ ነው።

እኔ የጨነቀኝ ‘ኢትዮጵያ ከአማራ ከርሰ ምድር ከፈለቀው ከጫካው አምበሳ ከአሳምነው ጽጌ በኋላ ሌላ ወንድ ታገኝ ይሆን? የሚለው ጥያቄ ሳቀርብ “አሳ ነባሪ” ተብሎ የውስጥ አርበኛ መጠሪያ ስም በኢሳያስ  አፈወርቅ ዕውቅና የስለላ ስም ተሰጥቶት የነበረው አብይ አሕመድ ያኔ አስመራ ውስጥ ከነበረው የኦነግ አመራር  ከኮለኔል ገመቹ ጋር ምስጢሮችን በስልክ ወደ አስመራ እየደወለ (እራሱ ኮ/ል ገመቹ  እንነጋገር ነበር ብሎ ተናግሯል- ኦነግን በገንዘብም ጭምር ይረዳቸው ነበር) ምስጢሮችን ሲያስተላልፍ የነበረው “ባንዳው አብይ አሕመድ” (አሳ ነባሪ) ዛሬ ሥልጣን ላይ ወጥቶ አብን የተባለው የወጣት ቡድን መሪዎችን እየተጎተቱ ወደ እስር ሲገቡ ባሕርዳርም መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የመሳሰሉ እየተገፉ ወደ እስር ሲገቡ ወጣቱ ይህንን እያየ ምንም አመጽ ባለማስናሳቱ ስታዘብ አሁን ያለው ወጣት እውን የአማራ “ከርሰ ምድር” የወለደቺው ከጫካው አምበሳ ከአሳምነው ጽጌ በኋላ ሌላ ወንድ ታገኝ ይሆን? የሚል ጥያቄ ጭሮብኛል። ዝም! በቃ ዝም! በቃ እንዲህ መቀለጃ ሆናችሁ ልትቀጥሉ ነው?፡የተረጨባችሁ አደንዛዥ ውሃ ምን ይሆን? ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ Ethiopian Semay)