Thursday, June 6, 2019

ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች (ክፍል ሁለት) ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ)


ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች (ክፍል ሁለት)
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ)
ይህ ፎቶ የክብራችን መላያ አርማ የሆነቺውን የኢትዮጵያችን ሰንደቃላማ “ዱባይ”  ጥር ወር 2011 (ጃንዋሪ 2019) ውስጥ በተከሄደው የማራቶን ሩጫ ኢትዮጵያዊው “ጌታነህ ታምሬ ሞላ” ሲያሸንፍ ኢትዮጵያውያን ሕጋዊውን ሰንደቃላመችንን በደስታ ሲያውለበልቡ የሚያሳይ አኩሪ የአርበኛነት የልብ ትርታ ያስመዘገበ ትዕይንት ነው (የኢትዮ ሰማይ (እኔ) ካንድ ታዋቂ ኤርትራዊ ነኝ ባይ ድረገጽ አዘጋጅ ጋር በድረገጻቸው ያደረግሁት የትግርኛ ክርክር ለክርክር ከተጠቀምኩበት ፎቶ ማሕደር የተገኘ) 
ይህ ፎቶ የአዝማሪው መስፍን በቀለ እና ሙዚቃውን ያሳተመለት ‘ምነው ሸዋ’ የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት “ወያነ ትግራይ” የሰጣቸው ሕገ ወጡ የኢትዮጵያ ካርታቸውን በየመንደሩ በየፍርስራሽ ግድግዳ ላይ የተለጠፈው የረኞቹ ካርታ በታዳጊ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ሕሊና ውስጥ እንዲቀረጽ ሆን ተብሎ ትውልድ በዚህ ሴራ ተቀርጾ እንዲያድግ የሚያስተምሩብትን መርዛማ የሙዚቀኞቹ  ባንዳዊ ፕሮፓጋንዳ በቪዲዮ ያሰራጩት ፎቶግራፍ ነው። 
በግራ የሚታየው መስፍን በቀለ ነው:: በቀኝ የሚታየው እስከስታ መቺው አብዮት ካሰች “አብዮት ደመቀ” የአብይ አሕመድ ፎቶ ያለበት ከናቲራ ለብሰው ስለ የአፓርታይድ መንግሥት መሪው አብይ አሕመድ “የሰላም መሪ” እያሉ “ለማ መገርሳ አለው ሀሳብ” እያሉ ፋሺስቶችን እያቆለጳጰሱ ሲዘፍኑላቸው የሚያሳይ በዩ-ቱብ የተለጠፈ የመስፍን በቀለ “አብይ የሰላም መሪ” የፕሮፓጋንዳ ቅሌት የሚያሳይ ፎቶ ነው


እንደምን ሰነበታችሁ? ባለፈው ክፍል አንድ ትችት ላይ ፋሺስቱ አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን የመጣበት ስልት በኡሉሚናቲዎቹ መዘውር የተከሰተው የአረቦቹ “ዓረብ ስፕሪንግ አብዮት” በተመሳሳይ መንገድ እንደሆነ ጠቅሻለሁ። የኢትዮጵያው ለየት ያደረገው ግን “የሰው ልጆች ሕሊና በመስለብና በመሰለል እጅግ የተካነ የሕሊና ሰላቢው “አብይ አሕመድ” በኡሉሚናቲዎቹ ዕውቅና እና ድጋፍ ወደ ሥልጣን የመጣ ቢሆንም የሰውየው ረቂቅ ሰላቢነት ‘ምሁራኖችንም ጭምር በመስለቡ’ የኡሉሚናቲዎቹ የጀርባ አመጣጥ መዘውር ለብዙ ምሁራን ሊታያቸው አልቻለም።

ይባስ ብሎ ሕሊናቸው የተጠለፉ እነዚህ ጋዜጠኞች፤ “ህገ መንግሥቱ መከበር አለበት” የሚሉ እንደ እነ  አንዱአለም አራጌ “አባ ቄሱ” እና ብርሃኑ ነጋ (አምታታው በከተማ) የመሳሰሉ ተቃዋሚዎች (ተፎካካሪዎች የሚል  “ሹመት” አግኝተዋል) እንዲሁም “ምሁራን” ሁሉም ተሰባስበው  ወደ አብይ ዙፋን በመቅረብ “አብይ አሕመድ በርታ እንደግፍሃለን!” እያሉት ነው። እንደ እነ እስክንድር ነጋ የመሰሉ “ትጉሃን ጋዜጠኖች” ሕዝባዊም ሆነ ድርጅታዊ መግለጫ እንዳይሰጡ መታገዳቸውን አላሳሰባቸውም። ይባስ ብለው እነዚህ “ነጭ ባንዴራ አውለብለቢዎች” ሥርዓተ አልባው መንግሥት “የፖለቲካ ዱርየዎችን” በየከተማው አሰማርቶ ያሻቸውን ለማድረግ ሙሉ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ነፃነት በመስጠት እናቶች፤ህጻናትና እርጉዞች ከመኖርያ ቤቶቻቻው በቡልዶዘር እያፈረሱ ወደ በረንዳ እንዲጥሉዋቸው በግልጽ እና በረቀቀ ስልት እየሰራ ድሆችን የማፈናቀል ጥበቡን ሲያደንቁለት አይተናል። ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች በሰላቢው መሪ እንዴት እንደተሰለቡ ከሌሎች አገሮች ተመሳሳይነት ያለውን በማነጻጸር ያንን ለመተንተን ለዛሬ ቀጠሮ ነበረን።
ሆኖም ያንን በሚቀጥለው ሳምንት አዳሪ አድርጌ ለዛሬ ግን ዓይኔን እና ቀልቤን የሳቡ ሁለት አዲስ ክስተቶችን እንመለከታለን።የሚከተሉት ሁለት ክስተቶች ቀልቤን ስበውታል።

(1)-ሙዚቀኛ መስፍን በቀለ እና ምነው ሸዋ ሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት
ለአገር አንድነትና ሉዐላዊ ክብር ሲሉ ወላጆቻችን በተጋድሎ ከጣሊያን ወራሪዎች ያስመለሱትን ሕጋዊ ሉዓላዊ መሬታችንን ከትውልደ ወደ ትውልድ በቀጣይነት ለማስከበር ኤርትራ ምድር ድረስ ሄደው ምጽዋ እና አልጌና የተሰውት ኣእላፋት የኢትዮጵያ ወታደሮች ክብር በሚያዋርድ መልኩ ለኤርትራኖች ይቅርታ ስለመጠየቃቸው ጉዳይ በሚመለከት ለዛሬ የመረጥኩት ርዕስ ነው፦

(2ኛ) ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የተባሉት የሕግ ትምህርት ተባባሪ ፕሮፌሰር (አሰብ ወደ ኢትዮጵያ የምትመራበት የህግ ተስፋ የለም) ኢትዮጵያ ያለወደብ መኖር ትችላለች ስላሉት የተለመደው የኢትዮጵያ ምሁራን የተሸናፊነትና የተስፋ ቆራጭነት አስተምህሮ እንመለከታለን።

በአዝማሪው መስፍን በቀለ እንጀምር።

መስፍን በቀለ የተባለ ሙዚቀኛ የኤርትራን ባንዴራ ለብሶ እየደጋገመ ስለ ኤርትራ ሉዓላዊነት በመቆዘም የምናውቀው ካፈርንባቸው የፖለቲካ ደናቁርት ሙዚቀኞች አንዱ የሆነ ወጣት አዝማሪ እንደ ሌሎቹ  አሳፈሪ አዝማሪዎች በዚያው “ኤርትራ ወለላየ… አበድኩልሽ… ወደድኩሽ” ዕብደት ሳይገታ “የፖለቲካ ማይምነቱን ለመግለጽ” ሲል ልክ በዚህ ወር በፈረንጆች በጁን 2018 “የሰላም መሪ” ብሎ “የአፓርታይድ መሪው” አብይ አሕመድን ያቆለጳጰሰ ሙዚቀኛ እንደሆነ የምታስታውሱት ነው።

በዚያ ባፈርንበት “የሰላም መሪ” “ጭፈራው” ገና ሳይደርቅ ዛሬ ደግሞ “ሰው እንሁን” የሚል አዲስ ሙዚቃ ሰርቶ ኤርትራ ካርታ ከኢትዮጵያ ካርታ ጋር አገናኝቶ በሙዚቃው “ክሊፕ” ውስጥ በመታተሙ ለዚህም በስሕተት ስለሆነ ታላቅ ይቅርታ ይደረግልኝ ሲል ባሳፋሪ መግለጫ የኤርትራ ባንዳዎችን ይቅርታ ጠይቋል።

የይቅርታው ተባባሪ ዋነኛ ተዋናይ ደግሞ “ምነው ሸዋ” የተባለው የናጠጠ/ ቡርዣዋ የሙዚቃ የንግድ ድርጅት/ በጋራ ሆነው ለባንዳዎቹ ለነ ኢሳያስ አፈወርቂና ጭፍራዎቹ ይቅርታ በመጠየቅ ተባባሪ መሆኑን ዜናዎች ዘግበውታል።

“ሕጋዊውን የሉዓላዊት ኢትዮጵያን ድምበር የሚጻረር” በምትኩ “የመለስ ዜናዊ ጣሊያናዊ የኤርትራ ንድፍ ካርታ” በማክበር “የይቅርታ መግለጫ በማውጣት ባንዳዎቹን ይቅርታ ለመጠየቅ በዩቱብ የተሰራጨውን የጽሑፍ መግለጫ ዜና ስመለከት በጣም ነው የገረመኝ።

ኢትዮጵያ አገራችን “ኤርትራ እና ወደቦቿን” በምን መንገድ እንደተነጠቀች ምንም ዕውቀት እና ምርምር ያላደረጉ የተሰጣቸውን የሚያከብሩ “ከአገር ፍቅር የራቁ” የዜጎችን ዋይታ የማይሰማቸው “አምባገነኖችንና አፓርታይድ መሪዎችን የሚያቆለጳጵሱ አዝማሪዎች” በሕዝቡ ሕሊና እና በሉዓላዊነታችን ከፍተኛ ጉዳይ እያደረሱ እንደሆነ ለብዙ አመታት የታዘብነው ጉዳይ ነው።

እነዚህ ሰዎች የሚያደምጡት በሁለት አፉ የሚዋሻቸውን የአገር መሪዎችን እያደመጡ እንደ አዝማሪነታቸው ያንን “ቡሉ” የተባሉትን እየደገሙ ሕዝብን በማስጨፈር በዙፋን ላይ የተቀመጡትን ተወስካቾ ሃይል እየሆኑ የመምጣታቸው አደጋ እጅግ አሳሳቢ እየሆነብን ነው። አንዳንዶቹ አፓርታይድ መሪዎችን ጫማቸው ስር ተደፍተው ጫማቸውን ስመው “እስከ ዘመነ ፍጻሜዎት በሙሉ ጉልበት አገልግለዎታለሁ” እያሉ የሚገርም የታሪክ አሻራ ጥለው ሲጓዙ ‘ለዛውም “የማፍርበት አይደለም” በማለት አፓርታይድ መሪን ጫማ ስር መውረድ ክብር መሆኑን በተዋበ ቃላት ይገልጹታል።

ሕዝቡ ጠመንጃ በታጠቁ የተለያዩ “እንሰሳት” መሃል ተከብቦ እየተፈናቀለ፤ እየተገደለ፤ እናቶች እና ልጃገረዶች እየተደፈሩ ባሉበት ወቅት ስለ አፓርታይዱ አብይ አሕመድ እና ስለ ኢሳያስ አፈወርቂ “ተክለሰውነት” መዘመር እና ማቆለጳጰስ እንጂ ሉዓላዊ አገርም ይሁን ስለ ህዝብ ብሶት የሚዘምሩ ሙዚቀኞች ዛሬ እገሌ አለ ተብሎ የሚዳሰስ ሙዚቀኛ ያለ አይመስለኝም (ዲ-በቀር)። ሁሉም ሙጥጥ ብለው ተሰባስበው “ዙፋኑን ከብበው” ይጨፍራሉ።

ነገሩ እንዲህ ነው! መስፍን በቀለ የተባለው አዝማሪ “ሰው እንሁን” የሚል ዘፈን ትሞ “ምነው ሸዋ” በተባለ “ዩ ቱብ” ተለቅቆ ነበር። ሸክላው እኛ በክፍለሃገርነት እንጂ በሃገርነት አውቅና ያልሰጠናት “ወያኔ-ሰራሽ” የኤርትራን ካርታ ያካተተ “ሕጋዊው” የኢትዮጵያ ካርታ ስለበር፡ ያንን ሕጋዊ የኢትዮጵያ ካርታ “ኤርትራኖችም ሆኑ ደናቁርት ኢትዮጵያውያን/ት” ኤርትራ ሉዓላዊ አገር ስለሆነች አንሳው ብለው አስደንግጠውታል መሰለኝ፤ ወይንም የአገሩን ሉዓላዊነት በአገር በቀል ፋሺሰት አገልጋዮች የተደፈረ መሆኑን ዕውቀት አንሶት ይሁን ወይንም ያንን ቢታተም “ኤርትራኖች” አይገዙልኝም የሚል የገንዘብ ስስት; ም ሆነ በዚህ ጉዳዩ ባልገባኝ ሁኔታ  አሳታሚው “እየተሽቆጠቆጠ ባስቸኳይ” ሸክላውን ‘ከዩ ቱብ’ በማስነሳት “የኢትዮጵያን ሕጋዊ ሉዐላዊ ካርታን በሚጻረር” መልኩ በምትኩ ኤርትራን ካርታ ያላካተተው የዚህ ሴራ ቀራጺዎች የሆኑትን ፋሺሰቶቹ “ወያኔ ትግራይና ሻዕቢያዎች” በመስፍን በቀለ እና በ“ምነው ሸዋ አሳታሚ ድርጅት” የማይገባውን ክብር ተሰጥቶት “ወያኔዎች እና ጣሊያኖች የቀረጹላቸውን ኢ-ሕጋዊ ካርታ” አክብረው በማሳተም እንደገና “ሌላ ሸክላ” እንዲቀረጽ አድርገው ለካርታው ባለቤቶቹ እና ለካርታው ቀራጸዊቹ “ለኤርትራና ለትግራይ ባንዳዎች፡ ይፋ መግለጫ በመስት ይቅርታ” ጠይቀው የማይለቅ ገበና ለታሪክ አስመዝግበዋል።

እነዚህ አዝማሪዎች እና ቱጃሮች የሚኮነኑት በዚህ ጸሓፊ ብቻ ሳይሆን “የኢትዮጵያ ጠበቆች በነበሩት በዋርካዎቹ በእነ ሃይሉ ሻውል፤በነ ሻለቃ አድማሴ እና በእነ ፕሮፌሰር አስራት ድምጽና ነብስ ለዘላለሙ ተረግመው ይኖራሉ።በህይወት የተረፉት ለዚያች ሉዓላዊት ምድር ሲሉ በፋሺስቶች እስር ቤት የማቀቁት የአርበኞቹ የእነ ዶ/ር ታዲዎስ ታንቱ እና የዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት የመሳሰሉ የሚሊዮን አርበኞች ድምፅም ይረግማቸዋል የሚል ግምት አለኝ።

በኤርትራ ምድር ለኢትዮጵያ አንድነት ሲሉ በየተራራውና በየሜዳው በባሕር እና በወንዝ በሚሊዮኖች እና በሺዎች ለረዢም ዘመናት የተዋደቁት ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት በተቀበሩበት ጉራንጉር እና ደማቸው ከምጽዋ የባሕር ውሃ ጋር የተቀላቀለው የአርበኞች ወታደሮቻችን መስዋዕት “ደመ ከልብ” ሆኖ እንዲቀር “መስዋዕታቸውን” ባራከሱባቸው እርኩሶች ላይ ለሃያሉ ፈጣሪቸው “የኤህታ!” እርግማን እንደሚያስተጋቡ አልጠራጠርም። በእርግማናቸው ምሬት ሰበብ “መለስ ዜናዊ እና አባት ነብሱ” ባንድ ወር ውስጥ ሁለቱም ከዘህ ምድር ተቀስፈው ወደ “ኢትዮጵያ ሰማይ” ለፍርድ ተወስደዋል። ማንኛችንም ከሞት ባንተርፍም፤ በእውነት ተራራ ላይ ቆሞ ታሪክ እንዳይረሳ እየተሟገቱ ማለፍ ግን ብፁእነት ነው።

በዚህ ዘመን በተለያዩ የኪነት ዘርፍ የተሰማሩ አዝማሪዎች እና የፊልም ተዋናዮች ያልገባቸው ወይንም አውቀውትም ቢሆን ‘ክብር የነፈጉት’ “የአርበኞቻችን ተጋድሎ” ኢትዮጵያን ከጠላት ለመከላከል በተካሄደው ፍልምያ “በሞሶሎኒ ልጆች (መለስ እና ኢሳያስ) ጨካኝ ወረራ ብዙ ቤተሰቦች ተበትነዋል። ለዛች ውድ ሰንደቅአላማችን እና ሉኣላዊ ምድር ሲሉ በየጉድጓድ እስርቤቶች ማቅቀዋል፤ የሳሕል ተራራ ደን ለማልበስ ሲባል “ወደ ባርነት ተለውጠው” ያለእረፍት እየተገረፉ “እንቅልፍ እንዳይተኙ ታግደው” በቂም እና በጥላቻ በቀል “ምሽግ እና አስፋልት ቁፈራ እንዲሰሩ” ተደርገዋል። በዚህ መልክ ቡዙዎቹ ደብዛቸው የለም። የነዚህ ዜጎች ክብር ወይስ የጠላቶቻቸውን ወራዳ ስራ ማክበር? የትኛው ይመረጣል?  

ብዙዎቹ አዝማሪዎች በሚለቁት ዘፈን ምን ጠባሳ ጥለው እንደሚሄዱ የገባቸው አይመስሉም። “ሉኣለዊነት ለማስከበር’ የጭፈራ ያህል እንደ ቀላል ነገር መስሎ ያዩታል። የስንት ዜጋ ህይወት እንደጠየቀ ለማወቅ ፍላጎት አላሳዩም። እነዚህ ባለጊዜዎቹ አዝማሪዎች እና የፊልም ተዋናዮችና አዘጋጆች “ውጭ አገር ካለው ሃገራዊ ዜጋም ሆነ አንገቱን አቅርቅሮ ጊዜ እየጠበቀ ካለው አገር ውስጥ የሚኖረው የአገሩን መሬትና የባሕር ብር መደፈሩን የቆጨው ኢትዮጵያዊ የልብ ትርታ” የሚለዩበት መንገድ ብዙ ነው። ይህንን ለማሳየት ከላይ የጠቀስኩት ቀን እና አመተምህረት በዱባይ ማራቶን ላይ ከፍ ብሎ የተውለበለበው “ሕጋዊው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ካርታ” መመለክት በቂ ግንዛቤ ሊሰጠን ይችላል።

“የመስፍን በቀለ እና የምነው ሸዋ የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት” ኤርትራኖችን ይቅርታ የመጠየቃቸው ቅሌት “ዱባይ ላይ በቆራጥ የአርበኞች ልጆች” የተውለበለበው “ሕጋዊ የኢትዮጵያ ካርታ የታየው ፎቶግራፍና ቪዲዮ” በሁለት ተቃራኒ “ካምፕ’ የቆሙ ናቸው። በዛው ልክ የነ መስፍን በቀለ እና የምነው ሸዋ አጋር የሆነው “ለንደን ውስጥ የሚገኘው “የአብይ አሕመድ ኤምባሲ” በዱባይ የተውለበለበው ሕጋዊው ካርታችን በዜና የተሰራጨውን ፎቶ “በጽ/ት ቤቱ የዜና ማሰራጫ ማእከል ስለለጠፈው” በየ ዓለማቱ የተበተኑት “የሞሰሎኒ ልጆች” ቅጽበታዊ “ኡኡታ” ወደ ኤምባሲው በማስተጋባታቸው ምክንያት“ ኤምባሲው በጽ/ቤቱ በኩል “ለኤርትራውያን እና ለትግራይ ኦን ላይን ትግራይ ትግርኚ “የአጋዚያን ልጆች” በሚያስደስት መልኩ የይቅርታ መግለጫ ማውጣቱ የሚታወስ ነው።የመስፍን በቀለ እና የምነው ሸዋ ቅሌት ከዚያው የለንደኑ የኤምባሲው ቅሌት በግብርና በአቁዋም አንድ ያደርጋቸዋል።

በነገራችን ላይ “የትግራይ ትግርኚ/አጋዚያን” እና “ሰብ ሕድሪ” ተገንጣይ የፋሺሰት  ርዕዮት አቀንቃኞች “በትግራይ ኦን ላይን” ድረገፅ ላይ ከኤርትራኖች በባሰ መልኩ “የደርግ ካርታ” እያሉ “አብደው” እንደነበር ማስታወሱ ተገቢ ነው። እባካችሁ ከያኒያን ባልገባችሁ ጥልቅ ፖለቲካ እየተበከላችሁ መስዋዕት በተከፈለበት የደም መሬት ላይ ከመቀለድ እና ትተናት ለምንሄድ ዓለም በታሪክ ማሕደር ጠባሳ እያስመዘገባችሁ ከምታልፉ፤ “ተፈጥሮ በለገሰቻችሁ ድምፅ  ተሰልፋችሁ አርፋችሁ ስለ ፍቅር፤ ስለ እነሰሳ፤ ስለ ተራራ፤ስለ ቡና ስለ እርሻ፤ ስለ ገበሬና ስለ ክብረ በዓል እየገጠማችሁ ብታዜሙ ይመረጣል።የመጣውን ሁሉ አርጋጅ ከመሆን ተቆጠቡ! ይህንን በሚመለከት እዚህ ላቁምና ወደ እሚቀጥለው እንለፍ።

   (2ኛ) የሕግ ትምህርት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ (አሰብ ወደ ኢትዮጵያ የምትመራበት የሕግ ተስፋ የለም ስላለው ጉዳይ በሚመለከት፤መልስ ልስጥ ንባቡን ስትጨርሱ

“አሰብ ወደ ኢትዮጵያ የምትመራበት የህግ ተስፋ የለም” ለተባለው ቃለ መጠይቁን በስዕለ ድምፅ ለማድመጥና ለመመልከት ይህን ተጫኑ።

ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ “አሰብ ወደ ኢትዮጵያ የምትመራበት የሕግ ተስፋ የለም” ለሚለው የደካሞች እና የተሸናፊ ምሁራን ስነ ልቦና ሰፊ ትችት ስለሚያስከትል፤በሚቀጥለው ባጭሩ እንመለከተዋለን። ሰሞኑን በቪዲዮ የተሰራጨው የምሁሩ አቁዋም ብዙዎቹን ኤርትራውያንን ያስፈነደቀ እና እስክስታ ያስመታቸው የዶ/ሩ አባባል ለኛ ን አስቀያሚ (ናስቲ) ሲሆን በዋናነት ግን ደስታው ለኤርትራኖች እና እንዲሁም በወያኔው ሜ/ጀ ተኽለብርሃን የሚቀነቀነው “ለአጋኣዚያኖቹ ለትግራይ ትግርኚ” አቀንቃኞች ተድላ እና ኩራት ያስተላለፈ መልዕክት ነው።

በርዕሱ የተጠቀሰው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ በተጨማሪም ዶክተሩ የወያኔው የመለስ ዜናዊን መስመር በመከተል “ኢትዮጵያ ያለ ባሕር ወደብ መኖር ትችላለች” የሚለው የወያኔዎች ፕሮፓጋንዳ በመቀበል ዶክተሩም ያንን አቁዋም ማራመዱ የሚገርም ነው። “ዓሰብ ወደ ኢትዮጵያ የምትመራበት የህግ ተስፋ የለም” ትንታኔው በመጪው ወጣት ትውልድ ሕሊና እና ሉዓላዊ ግንዛቤ የሚያደርሰው ጫና እና ሕግን የጣሰ ክርክር፤ ያውም የሕግ ምሁር ሆኖ “ሕግን ያላጣቀሰ” ተስፋ ቆራጪነት መስመሩን በሚመለከት ሰፊ ውይት የሚጋብዝ መስመር ነው።

ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ብርቱ አገር ወዳድ አርበኛ ኢትዮጵያዊ መሆኑን እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምሕር ሆኖ የ27 አመቶቹ የትግሬ ባንዳዎችም ሆኑ አሁን ሥልጣን ላይ የተቆናጠጠው ‘ኦሮሞአዊ አፓርታይዱ መሪ” አብይ አሕመድን “አክራሪ የነገድ አቀንቃኝነት ፖለቲካ” በሚገባና በበቂ አስገራሚ ድንቅ ችሎታው የሚሞግት ምርጥ ሊቅ መሆኑን የማምንበት ብሆንም፤ ልዩነታችን “በዓሰብም ሆነ በወደቦቻችን እንዲሁም ስለ ኤርትራ ኢ-ሕጋዊ ግንጠላ የሚንጸባረቅ አመለካከት የዶክተሩ እይታ እንደ ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ለ27 አመት የተሸከሙት የተሸናፊነትና ተስፋ ቆራጭነት ያስከተለው የስነ ልቦና ሽንፈት እንደሆነ ለማወቅ የስነ ሕሊና ተመራማሪ መሆንን አይጠይቅም። ያውም የሕግ ምሁራን ሆነው ምክንያታቸውን ሳይጠቅሱ ለምን ሸብረክ እንደሚሉ ይብልጥኑ ይገርመኛል።

የዶከተር ደረጀ ዘለቀ ሦስተኛው እና ያስገረመኝ የመለስ ዜናዊ አይነቱ ፕሮፓጋንዳ ያንጸባረቀው ደግሞ እንዲህ ማለቱን አስገርሞኛል፡ “ዓሰብ ዓሰብ የሚሉ ጦርነት ውስጥ እራሳቸውን አያስገቡም” ይላል። ዓሰብ ዓሰብ የምንል ዜጎች ጦርነት ውስጥ መሳተፋችን እና አለመሳተፋችን እንዴት ሊለየን ይቻለዋል? በሺዎች በቁጭት እየበገኑ ያሉ ውታደሮች እና ወታደራዊ አዛዦች በዚህ የስም ማጠልሸትና ማንኳሰስ ተገቢ ነው? እንዲህ ያለ የምሁራን ሕሊና የዜጎችን ሓሞት ለመግደል በጠላቶች የተዘረጋውን ፕሮፓጋንዳ እየተቀበሉ ማስተጋባታቸው መነሻው አልገባ እያለኝ ደግሜ ደጋግሜ ሳስበው ይብልጥኑ የተማሩት “ቀለም” ምን እንደሆነ አልገባህ ብሎኛል።

ቢሆን ይሁን እንበል እና ሁሉም ዜጋ  ወደ ጦርነት መግባት አለበት እንዴ? ጦርነት እኮ ‘ጥይት መተኮስ” ብቻ አይደለም። የብዕር ጦራችንን ለማክሸፍ የብዕር ጥይት ሚተኩሱትን እንደ እነ ዶ/ር ደረጀ አይነቶቹን“ ዓሰብ ወደ ኢትዮጵያ የምትመራበት የህግ ተስፋ የለም” በሚሉት ተሟጋቾቻችንም ሆነ በጸረ ኢትዮጵያ ጠላትነታቸው የታወቁት በእነ ሞሶሎኒ ልጆች ላይም ብዕራችንን ማሾልም እኮ የጦርነቱ አካል ነው። ብዕር እኮ ኢፍትሓዊ ፍርድ እና አምባገነን ስርዓትን የመለወጥ ሃይል አለው። ብዕር እኮ ፈሪን ሳይቀር ብረት ታጥቆ ከጠላት ጋር እንዲፋለም የማድረግ ስልት አለው። ብዕር እኮ የጠላትን የሓሞት ከረጢት የመጭመቅ ጉልበት አለው። ያ እማ ባይሆን ከጦርነት በፊት እና በጦርነት ወቅት ተጋች አገር ወዳድ ጋዜጠኛ  ጸሓፊና አዝማሪ ለምን ያስፈልግ ነበር? አገር እኮ የተገነባቺው በጦርነት ስልት ብቻ ሳይሆን በጸሐፊዎች የክርክር ሙግት ጭመርም ነው።

ይህንን የምሁራን ተሎ ተስፋ ቆራጭነት እና ተሸናፊነት ምክንያቱ በትልቅ መፈተሽ ያስፈልጋል። ለሺዎቹ ዘመናት የቆየ ሉኣላዊ ድምበር እና ሕዝብ እንዲህ በፍጥነት ሊወድቅ የቻለበት ምክንያት ምንድነው? የሚለው ጥያቄ ዜጎች ሊነጋገሩበት የሚገባ ወቅታዊ ጉዳይ ነው። ውድቀቱም ሆነ ተሸናፊነት እና ተስፋ ቆራጭነት ምንጮቹ ምሁራን ወይስ ተራው ዜጋ? አንባቢዎቼ በዚህ ርዕስ ተወያዩበት እና ለዛሬው ግን በሚቀጥለው እስክንውያይ ዓሰብን እና ኤርትራን በሚመለከት ከጥቂት አመታት በፊት በሚከተለው በዶ/ር ያዕቆብ ኃ /ማርያም የሕግ ምዕዳንና ትዝብት በሰጡት ጽሑፍ ጠቅሼ-ልሰናበታችሁ፦

እንዲህ-ይላሉ፦

“የአገር ሕልውናን እስከመፈታተን ሊደርሱ ከሚችሉ ከዋነኛ የአገር እሴቶች አንዱ የባህር በር አለመኖር ነው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ሁኔታ፡፡ በማይጨው ጦርነት ለሽንፈታችን ምክንያት ከሆኑ ከዋነኛ ምክንያቶች አንዱ ኢትዮጵያ የገዛችው የጦር መሳሪያ በጅቡቲ በኩል ወደ አገር እንዳይገባ ፈረንሳይ መከልከልዋ እንደነበር መዘንጋት የለብንም፡፡” ካሉ በላ፤ በመቀጠልም

“ኢትዮጵያ ምትገኝበት አደገኛ አካባቢ ሲሆን ጂኦፖለቲካውና ሃይማኖት ከስሌት ሲገባ የባህር በር በተለይም የኢትዮጵያ የአሰብ ባለቤትነት ጥያቄ ከሸቀጥ ማስተላለፍ በዘለለ የሕልውና ጥያቄ ሆኖአል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ወሳኝነት እንዳለው እያወቁ “አሰብ አሰብ የምትሉት ምንድን ነው” እያሉ ይህንን ትልቅ ሕዝብን ያስጨነቀና እንቅልፍ የነሳ ጉዳይ ሲያጥላሉ ተደምጠዋል፡፡ በዚህ ላይ ብዙ ማለት ቢቻልም በተቃዋሚዎች መሃከል ሌላ አዲስ የጭቅጭቅ ርእስ ላለመክፈት ሲባል ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትዝብት እንተወዋለን፡፡ ጥቅሙን ከሕዝብ በላይ የሚያውቅ የለምና።” 

 በማለት ደ/ር ያዕቆብ ግሩም ትንተና ቢሰጡም

ያው እሳቸውም በተደጋጋሚ ስለ ዓሰብ ሲተነትኑ ታጥቦ ጭቃ ውስጥ የገቡበት ጥቂት ጊዜዎች አሉ።

ለምሳሌ በእዚህ ጽሑፍቸው መጨረሻ የተጠቀሰው “በዚህ ላይ ብዙ ማለት ቢቻልም በተቃዋሚዎች መሃከል ሌላ አዲስ የጭቅጭቅ ርእስ ላለመክፈት ሲባል ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትዝብት እንተወዋለን።” የሚሉትን አባባል ስትመለከቱት ከእርሳቸው ጀምሮ ብዙ ምሁራን የወደቁበት አባባል ይህ አባባል ነው። “ተቃዋሚዎች መካካል ሌላ አዲስ የጭቅጭቅ ርዕስ ላለመክፈት ሲባል የሉዐላዊን ጉዳይ ለሕዝብ እንተወው” በማለት እነኚሕ ዓለም አቀፍ የሕግ ሙያ ያላቸው ምሁራን የሕዝቡን አቅምና ትምሕርት እያወቁት በከፋ መልኩ ኑሮ እና አፓርታይድ ላንገላታው ምንም ለማያውቀው ከኑሮው ጋር እየታገለ ያለው ምስኪን ሕዝብ “የባሕርን ወደብን የሚመስል ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ” ሕዝቡ “እራሱ ይፍታው” እያሉ “ተፈትነው የወደቁት አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ተብየዎች” አንዳይጫቃጨቁበት ተብሎ በማሰብ ጊዜ በመውሰድ የባሰ ጦስ ውስጥ አስገብተውን ዛሬ ይኼው እነ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀም ቢሆን “(ጊዜው እየረዘመ ስለሄደ ይመስለኛል?) ዓሰብን በሕግም በሃይልም ለማስመለስ ተስፋ የለውም’ እያሉ መጪውን ትውልድ ያለ ባሕር ወደብ በመሬት ታጥሮ ለዓረቦች እና ለመሳሰሉ አክራሪ ጎረቤት አገሮች መጫወቻ እንዲሆን በሉዓላዊነት ያለው ግንዛቤ የትውልድ ሕሊና ሞራል እንዲዘቅጥ ምሁራንም ከያኒዎችም ፈርደውበታል።

ይህንን የተመለከተ  ከበረሃ በመጡ “በለስ በቀናቸው” ውስጠኛ ጠላቶቻችን የተፈጥሮ ሕጋዊ ወደቦችዋንም ሆነ ሰፋፊ ለም መሬቶችዋን “በወረራ ስትነጠቅ” ያየ አንድ ኢትዮጵያዊ ገጣሚ “ምፅዐት ዐማራ” በሚል መጽሐፍ የተዘገበውን እንዲህ ሲል በገጠመው ስንኝ ጽሑፌን ልደምድም፦

“ከጫካ ሰው ጋራ ቁማር ተጫውቼ
ወና ወጥቻለሁ አገር ተበልቼ
እኔም ስጠባበቅ ምርት እህሌን ላፍሰው
ከጫካ የወጣ ዝንጀሮ ጨረሰው”

ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች  ክፍል 3 ይቀጥላል………
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ Ethiopians semay