Thursday, November 27, 2014

ኤርትራ ያለቀላት የተበላሸች መንደር!ኤርትራ ያለቀላት የተበላሸች መንደር!

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) September, 27/20014
ዓለም በክብር የሚዘክራቸው የኢትዮጵያ ንጉሥ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ

Getachew Reda Editor Ethiopian Semay- Eritrea Licks Its Wounds
በዚህ ጽሑፍ ወያኔዎች ለ22 አመት መልስ ያጡበትና ያሳፈራቸው አንድ አጭር እና ግልጽ ጥያቄ አንመለከታለን። ድሮ በልጅነታችን “እንእኒ” (ሲነበብ ይጥበቅ) የሚባል ዘመን ነበር ሲሉ ወላጆቻችን ያጫውቱናል። እኛም ያንኑ ትረካ ተቀብለን ‘ዝናብ ሲዘንብ’ ጓደኛሞች የሆንን ሁሉ ሁሌም በምንጫወትበት ሞቃታ ስፍራ ሰብሰብ ብለን ተጠጋግተን በብርዱ ላለመጠቃት ተኮማትረን ተቃቅፈን  ስለዘመኑ እውነተኛነት በዓይናችን ያየን ይመስል የራሳችንን ቅጥያ ጨማምረን አጣፍጠን ከፊት ለፊታችን የሚታዩ የድንጋይ ኮረቶች ሁሉ የዛው ዘመን የአምቧሻ ቅሪት መሆኑን በእርግጠኝነት እናወራ ነበር። ዘመኑም “ዘመን እንእኒ” ይባል ነበር። በዛ ዘመን ምን ነበር? ብለን ስንጠይቅ ፤ “ድንጋዩ ሁሉ አምቧሻ ነበር”፤ ማረስ መዝራት፤ መውጣት መውረድ አያስፈልግም ነበር። “ብዘመን እንእኒ ሕምባሻ እንተሎ እምኒ” ድንጋይ ሁሉ አምቧሻ የነበረበት “የእንእኒ ዘመን” አጣፍጠው ወላጆቻችን የነገሩንን እና እኛም ጨማምረን ስለ ዘመኑ መልካምነት እናወራ ነበር።ታዲያ እግዚሃር በሰው ልጆች ስነ ምግባር ተቆጣና አምቧሻው ወደ ድንጋይ ለወጠው ይባላል። ኤርትራኖች ‘ምድሪ ባሕሪ’ ነፃ ስትወጣ ወደ “ዘመን እንእኒ” ተመልሳ ድንጋዩ ሁሉ አምቧሻ ሆኖ አንደሚቀየር ለእናቷ ኢትዮጵያም ከሚትረፈረፈው አምቧሻዋ አንደምታጎርሳት ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸው የኤርትራ ኢኮኖሚስቶች ያልቀባጠሩት ዲስኩር አልነበረም።

አንድ እውቅ የጦቦያ ጸሐፊ (ማን መሆኑን አላስታወስኩትም አሁን) ኤርትራ ነፃ ስትወጣ፤ “ድሮ በጥንት ጊዜ ራሴን ችዬ ‘ኤርትራ’ ስባል የነበርኩኝ  “አገር” ነኝ  ታዲያ ‘ኢትዮጵያ’ የምትባል ከላየ የተፈጠረች የ60 አመት ዕድሜ ያላት አገር በጉልበት አጠቃልላኝ ነው እንጂ አገር ነበርኩኝ፤ አሁን  ግን ነፃ አውጡኝ፡ እያለች እረፍት ስለነሳችን ነፃነቷን ለመስጠት ተዘጋጅተናል እና ኤርትራ የምትባል አገር በፈጠርካት በዚች ዓለም-ምድር ተዘግባ ታውቃት ነበር? ብለው እግዚሐርን ሲጠይቁት “ኤርትራ? ኤርትራ? ኤርትራ ደግሞ ማናት? ብሎ መዝገቡን ሲፈትሽ ማግኘት አልቻለም። አንዲህ የምትባል አገር አላውቅም! ምነው ጊዜን ባታባክኑብኝ” ብሎ እግዚሓርም ራሱ ተገርሞ ነበር ይባላል። ትክክለኛ አባባሉ ባይሆንም በማጠጋጋት (ፓራፍሬዚንግ) አባባል እንዲያ ብሎ ጽፎ ነበር።ኤርትራ ዛሬ 22 አመቷ ነው ነፃ ከወጣች። እገምጠዋለሁ ያለቺው ‘የዘመን እንእኒ ቅዠት” ድንጋይ ብቻ ሆኖባት ፈዝዛ ቀረች። 


ኤርትራ ሁሉም ሞክራዋለች። ጥቁር ገባያ፤ ሌብነት፤ ስም ማጥፋት፤ ውሸት፤ጉራ፤ ወንጀል፤ ጦርነት፤ሽብር፤ስደትና ዕብደት። ከዚህ ወዲያ የሚቀራት መደምደሚያዋ ወደ አመድነት መጓዝ ነው።ከዚያ ጣረ ሞት መዳን ከፈለገች “የቀራት አማራጭ” ኢትዮጵያዊነትዋን “በቁርባን” ተቀብላ ከዘላለማዊው ቅዠት (ደሉዥን) እና ሞት መዳን ነው። ጣሊያኖች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ Ethiopia E Finita !!!! (ኢትዮጵያ አለቀላት) የሚል መፈክር የያዙ ትሬንታ ኳትሮዎች አዲስ አበባን ወርረዋት አንደነበር ጆን ስፔንሰር Unity and territorial integrity (የግዛት ውሁድነት) በሚለው መጽሐፉ ጠቅሰው አንደነበር አንድ ፀሓፊ በጦቢያ መጽሄት ላይ ጠቅሰው ነበር። የተጠቀሰው መፈክር፤ ዛሬ ያለምን ጥርጥር ኤርትራ ካለ ኢትዮጵያ መኖር የማትችል በጉራ ብቻ የተነዳች፤ ደካማ አውራጃዎችን የያዘች፤ ያለቀላት ተበላሸች መንደር ነች። ሰርጓም ሞትዋም በ22 አመት ውስጥ ተጠናቀቀ። ዕጣ ፈንታዋ “ነፃነት” “የኤርትራ መጠለፍ”ን (ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ አገላለጽ) ብላ የገለጸቺውን ነፃነቷን አንደገና “መከለስ” አለባት (ከአመዳም ሕይወት ለመውጣት ስትል!)።ለ22 አመት የተሰጣት  “የኦክሲጅን ስሊንደር” አልቋል! ከዚያ ወዲያ መቀጠል full of difficulties/ ነው። ብልሽት!


“ኤርትራዊው አማረ ተኽለ ዴንቨር ዩኒቨርሲቲ ለዶክተሬት ዲግሪው መመረቂያ የጻፈው የምርምር ወረቀት The creation of the Ethio-Eritrean Federation; a case study in post-war international relations, 1945-1950. ላይ እንዲህ ይላል፤- “ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል አልነበረችም ብለው የሚከራከሩት የአካባቢው ታሪክ የማያውቁ ወይም ሊቀለብሱት የሚፈልጉ የሙሶሎኒ ፋሺስታዊ ፖለቲካ የሚጋሩ ብቻ ናቸው።” ይላል።  አማረ በድሮ ጊዜ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ኢትዮጵያዊነቱን አምኖ ተቀጥሮ ሲሰራ የነበረ፤ በላ ታስሮ ሲፈታ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስራ ለመመለስ ሲሞክር ‘ይህ ሰውዬ አባርሩልኝ’ ብሎ ኮ/ል ጐሹ ወልዴ አንዳይቀጠር የከለከለው ሰው አንደነበር ኤርትራኖች ፅፈውበታል። አማረ ተኽለ የዛሬ አያድርገው እና ያኔ ሕሊናው ሲከተል በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ የኤርትራ አካል አልነበረችም ብለው የሚከራከሩ ሰዎችን “/Neo Fascist ፋሺስት” ናቸው ብሎ ለዲዘርተሼን በጻፈው የመመረቂያው የጥናት ጽሑፍ ነግሮናል። ጊዜ መስተዋቱ! ያኔ የተናገረውን ረስቶ ዛሬ እራሱ ወደ ኒዮ ፋሺስቶቹ በመቀላቀል ‘የኤርትራ ርዕሰ ውሳኔ ኮሚሽነር/አስመራጭ’ በመሆን የውስጥ እና የውጭ የወረበሎች ስብስብ ያዘጋጁትን የወያኔና የሻዕቢያ ሬፈረንደም ባዘጋጁት ሴራ ውስጥ በመሳተፍ እንድትገነጠል ከጣሩት ቀዳሚ ኤርትራዊያኖች አንደኛው ደ/ር አማረ ተኽለ ነበር።


ባለ ሁለት ምላሱ አማረ ተኽለ ወንበዴዎቹ ያዘጋጁትን የግንጣላ ሴራ ስለ ሪፈረንደሙ አንዲህ ይላል፤ “the referendum process as one of the fairest and freest of referendums ever.”  በማለት የኒዮ ፋሺስቶቹ ሬፈረንደም ከማድነቁ በላይ፡ የሻዕቢያ ተቀጣሪ ሆኖ ቱልቱላውን በመንዛት ኤርትራ Eritrea is in the stage of democratic transition በሚል ንኡስ ርዕስ በዲሞክራሲያዊ ሽግግር ድልድይ እንድትራመድ እየመራት ያለው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ አፍሪካ በታሪኳ ያላየቺው ጠንካራ መሪ ነው። There is, as is almost universally agreed by African social scientists, the need for a strong leadership to guide this process. Eritrea is blessed with such a strong leadership whose source of legitimacy is a Rousseauean General will of the population has shaped and shares the vision of the government. It is this leadership that you demonize as authoritarian either out of ignorance or political malice. በማለት የምሁር “ሊጥ”-ነቱን ለ ሲ አይ ኤው የወያኔ አፈ ቃላጤ ለነበረው ፖል ሄንዝ በ March 21 /1999 በባድሜ ጦርነት ጊዜ በጻፈው ጽሑፉ ነግሮናል። አሁን አለማፈር ጠንካራ መሪ ብሎ ሲያሞግሰው የነበረው ኢሳያስን በመቃወም፤ “የኤርትራ ነፃነት” በኢሳያስ ዲክታቶሪያል ባሕሪ እየተረገጠ ነው፤ ሲል ተቃዋሚ ሆኗል። ኤርትራ ያለቀላት የተበላሸች በረዶ ውስጥ ተቀብራ መውጫ ቀዳዳው ጠፍቶባት ያለች መንደር እንደሆነች እኔ ብቻ ሳልሆን፤ ደጋፊዎቿ የሆኑ የውጭ አገር ሰላዮች እና ጸረ ኢትየጵያ ሃይላትም ይህንን እየደገሙት ነው።


ለምሳሌ’- December 2013, Herman Cohen አንዲህ ብሏል።bringing “Eritrea in from the cold” was overdue.” ሲል ሌላው ጸረ ኢትዮጵያ የሆነው ‘አምባሳደር ዴቪድ ሺን-David Shinn’ ደግሞ ገና፤ በጣም ገና፤ ያኔ አዲስ አበባ ውስጥ አምባሳደር ሆኖ ተሹሞ እያለ EEDN በተባለ ዝግ የድረ-ገጽ የወይይት መድረክ ላይ ዴቪድ ሼን ጸረ ኢትዮጵያ ነው ስላልኩኝ እሱን ደግፈው በኔ ላይ ተረባርበው ሲጮብኝ ለነበሩ ኢትዮጵያዊያኖችን ዛሬ እውነተኛ መልኩን በJanuary 13th, እንዲህ ሲል “The idea that Assab belongs to Ethiopia is outdated”ገልጿል።

 

 

 የኦጋዴን እና ኤርትራ ተገንጣዮችን የሚያበረታታው የዴቪድ ሺንን ‘አናርኪ’ ንግግር ወደ ጎን እንተው እና ኤርትራ ያለ ኢትዮጵያ ‘ብርድልብስ’ መኖር እንደማትችል ካወቁ በሗላ Ambassadors Princeton Lyman, Herman Cohen, David Shinnኤርትራን ከቀዝቃዛው ብርድ እናወጣት ብለው አዲስ ዘመቻ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

 

አሳዘኙ እውነታው ማየት ያቃታቸው ከመሪያቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ሆነው የሕዝባቸውን መከራ ሲያበራክቱ የበሩ ውጭ አገር በድሎት ሚንደላቀቁ ኤርትራዊያን ሊህቃን ናቸው። ኤርትራኖቹ መከራው በኢሳያስ ብቻ አንደተፈጠረ አስመስለው በመውሰድ ኢሳያስ ከተወገደ ኤርትራ ከቆፈኑ/ከብርዱ ማስወጣት ይቻላል፤ የሚል የሞኝ ዘመቻ አሁን ይዘው ቀጥለዋል። ሁሌም ጽሑፎቻቸውን ሳነብብ፤ ያለመማራቸው ይገርሙኛል። ለኤርትራ መሰረታዊ ስቃይ መነሾ “ግንጠላው መሆኑን ሊገባቸው አልቻለም። ማትኰር የነበረባቸው ‘አረቦች፤አንግሊዞች፤አሜሪካኖች እና ጣሊያኖች እንዲሁም እራሳቸው የተጣመሙ የኤርትራ ኤሊቶች ያጣመሙት የኤርትራ ጥያቄ እና ትግሉ ከጅምሩ የተወላገደ መነሾ መሆኑን መረዳት አቅቷቸዋል። ዛሬም ሊሂቃኖቹ ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል ጉዞ፤- ለሃፍረታቸው መሸሺያ ሲሉ ከኢትዮጵያ ጋር ከመወሃድ ኤርትራ ‘ትሙት” ብለው ፈርደውባታል። ሞት የውርደት መሸሻ ዋሻ ነውና፤ ከውርደታቸው ለመሸሽ ሲሉ ሞቷን እያቀላጠፉላት ይገኛሉ። ወዳጄ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሃንየ በቅርቡ “ኤርትራ ሞታለች….” ብሎ በትግርኛ ጽፎ በላከልኝ 46 ገጽ ላይ የኔን አባባል ያረጋግጣል።

 

ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ መኖርም ሆነ በፌደረሽን መኖር አንደሚጎዳቸው የድሮ የባሕር ነጋሽ ተወላጆች በፌደረሸን ጉዳይ አጣሪ ኮሚቴ ሆነው የመጡ የተባበሩት መንግሥታት መልዕክተኞች አስመራ ተገኝተው በነበሩበት ወቅት በአቤቱታ መልክ ገልጸዉ አንደነበረ ታሪክ ዘግቦታል። ኤርትራ እስከ 1889 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ድረስ፤ መረብ ምላሽ/ምድሪ ባሕሪ/ባሕረ ምድር/ባሕሪ ነጋሲ/ባሕረ ነጋሽ እየተባለች ስትጠቀስ የነበረቺው የጥንቷ ኢትዮጵያ አካል የአሁኗ “ኤርትራ” (በፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ አጠራር “የባርነት ስም”) ኗሪዎች ‘ሓንቲ ኢትዮጵያ/አንድ ኢትዮጵያ’ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት!” ብለው በመነሳት “ማሕበር ፍቕሪ ሀገር” ድርጅትን የመሰረቱ ወላጆቻቸው መገንጠሉ ኤርትራን እንደሚጎዳ እና ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተነጥሎ ራሷን ችላ መኖር የማትችልበት ምክንያት ለሕብረቱ ጥያቄ  ምክንያቶቹ ካቀረቡዋቸው ነጥቦች ውስጥ በምጣኔ ሐብቱ እና በቤተሰባዊ ግንኙነት በሚመለከት ከክረስትያኖቹ እና ከእስላም ማሕበረሰብ ተወክለው አቤቱታ አቅራቢዎች በሁለት ነጥቦች የሚከተለውን አቤት ያሉበትን አቤቱታቸውን ታሪክ ዘጋቢዎች በጦቢያ መጽሄት ላይ ያኔ ኤርትራ ነፃ ወጣህ ባለችበት ወር ከዘገቡት ሰነድ ልጥቀስ።

 

እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ በጥሞና አንብቡት፡

                  “እኛ በዛሬው ኑሮአችን ከኢትዮጵያ ተለይተን ለመኖር የማንችል ስለመሆናችን የሚጨበጥ ማስረጃ የምትጠይቁ ሁሉ ይህን የመሰለውን ፍሬ ሊሰጡ የሚችሉ ብዙ ማስረጃዎችን ላቀርብላችሁ ዝግጁ ነኝ። ከሁሉ አስቀድሞ መርማሪው ኮሚሲዮን ባቀረበው ውስጥ እንደተገለጸው እኛ የኤርትራ ሕዝብ ለኑሮአችን በቂ የሆነ እህል በደጋው አገር ለማብቀል የማንችል መሆናችንን አረጋግጠናል። ይህም በመሆኑ ስንዴ ጠፍ እነዚህን የመሳሰሉትን ለኤርትራ ሕዝብ ምግብ የሚያገለግሉት ከኢትዮጵያ መግዛት አለብን። 

 

እንደዚሁም ደግሞ የእስላሞች ሊግ ቃል አቀባይ ባደረገው መግለጫ የሚከተለውን ተናገረ፦

                   “ የኤርትራ መሬታችን ጤፍ የማያፈራ መሆኑን በኢትዮጵያ ሰሜን የሚገኘው የትግራይ ክፍል አንደዚሁ በመሬት በኩል ድሀ ሆኖ ለኤርትራ ምንም ዓይነት ጥቅም የማይሰጥ በመሆኑ በየአመቱ በብዙ ሺሕ ሕዝብ የሚቆጠሩት ሕዝባችን ከብቶቻቸውን እየያዙ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ጐንደር አውራጃዎች ተሻግረው ከብቶቻቸውን ያበላሉ። በዚህ ሁኔታ የትግራይ መሬት በምሥራቅ ኤርትራ ክፍል ላሉት በቆላ ውስጥ ለሚኖሩት ሕዝቦች ከብት የሚያግጡበት ሥፍራ ሲሆን፤ ጐንደር ደግሞ በምዕራብ አውራጃ ለሚኖሩት የሚበዙት እስላሞች ለሆኑት ሕዝቦች ከብት ማሰማርያ ሆኖ ይገኛል።

 

ስለዚህም በምሥራቅና በምዕራብ ኤርትራ (በምፅዋ እና እሱንም በመሳሰለው አውራጃ) ላሉት ክርስትያኖች እስላሞች ለኑሮአቸውን ከኢትዮጵያ ውስጥ አድርገዋል። እነሱም ከኤርትራ ውስጥ ለመኖር ቢፈልጉ ኖሮ በረሃብ ባለቁ ነበር።

 

  ለሕዝቧ ኑሮ አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ዓይነት ምግብና እህል ከኢትዮጵያ በመግዛት ብቻ የምትደገፈው ኤርትራ ከጥቂት ጨው በስተቀር ወደ ውጭ የምትሸጣቸው ሌላ ዕቃ የላትም። ይህም በመሆኑ ያገር ውስጥና የውጭ አገር ንግዳችን የሚበዛው ክፍል በትራንዚት ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ የንግድ ዕቃና ለኤርትራ ሕይወት የሚያስፈልግ ምግብ ብቻ ሆኖ ይገኛል። ይህን የመሰለው ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርገው ንግድ ቢቋረጥ የምፅዋ ወደብና መላውም ኤርትራ ንግዶች ሥራቸውን ያቆማሉ። ከእነዚህም ከኤኮኖሚ ማስረጃዎች በስተቀር ይበልጥ ጠቃሚነት ያለውና ከአእምሮአችንም ምንጊዜም የማይለየው ከሦስት ሺሕ ዘመን በፊት ጀምሮ ቅድመ አያቶቻችን አንድ የኢትጵያ ሕዝብ ክፍል ሆነው የነበሩበት መሰረተታዊ ጉዳይ ቀርቦ ይገኛል። የጋራ ጥንታዊነታችን የልምዶቻችን የቋንቋዎቻችን ፤የሃይማኖቶቻችንና የጥቅማጥቅሞቻችን መተሳሰር በጣም ጥልቅ ከመሆናቸው የተነሳ ግልጽና ተገቢ በሆነ አኳሗን በሚያጠግቡ ለመግለጽ ምቹዎች ናቸው።” 

 

በማለት በምጣኔ ሃብቱ ረገድ የሚደረስባቸው መከራ ከላይ የተነበዩት ፍራቻ ትክክል ሆኖ ይኼው በዓይናችን እያየነው ነው። ቀጥሎ ቤተሰባዊ ትስስር ሚደርሰው የሚከተለው አቤቱታቸው ደግሞ ኤርትራ ከኢትዮጵያ የመዋሃድ ጉዳይ ዋል እደር ማይባልበት መሆኑን እና ተሎ እንዲፋጠን ሁለት መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ ኤርትራኖች በተመሳሳይ መልክ ጥያቄአቸውን አቅርበዋል። ያካተቱት ዝርዝር ሐተታ ረዢም በመሆኑ፤ የመጀመሪያዋን ብቻ ልጥቀስ፦ አንዲህ ይላል፤-

 

“እኛ በኢትዮጵያ ውስጥ የምንኖር ሁለት መቶ ሺህ የምንሆን ኤርትራውያን በኤርትራ ውስጥ የሚኖር ወንድሞችና ዘመዶች አሉን። የእነሱንም ችግር ብዙ ከመሆኑ በስተቀር በዚያ ክፍል በሚገኘው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ውስጥ አለመጠን ተጨቁነው ይኖራሉ። የሚበዙት የተማሩት ኤርትራውያን ከኤርትራ እየተሰደዱ ባሁኑ ጊዜ በእናት አገራቸው (ኢትዮጵያ) ውስጥ በነፃነትና በመልካም የኑሮ ደረጃ ተደስተው የሚኖሩ መሆናቸውን እዚህ ላይ ማንሳት አስፈላጊ ነው። በጣም የሚያሳዝነው ካገራችን መለየታችን ብቻ ሳይሆን ከወሰን ባሻገር ያሉት ወንድሞቻችንና ዘመዶቻችን በችግርና በጭቆና ውስጥ እንዲኖሩ ማወቃችን ነው። ስለዚህ የኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል ጉዳይ በተቻለ ፍጥነት አንድ ውሳኔ አንዲያገኝ ልመናችንን እናቀርባለን።”  ሲሉ እነሱም በበኩላቸው ጥያቄአቸው ለኰሚሽኑ በደብዳቤ ገልጸዋል።

 

የትገሬ ባንዳዎች ኢትዮጵያን የባሕር ወደብ አልባ ለማድረግ ለኤርትራኖች ወግነው የተጠቀሙባቸው የቅን ግዛት ካርታዎች እና ውሎች በዛሬው ዘመን ውድቅ መሆናቸውን ለማየት የተለያዩ ካርታዎችን እንመልከት እና ውይይታችንን እንደምድም።

 

ሦስት ካርታዎችን እንመልት

 

የሚከተሉት 3 ታሪካዊ የተለያዩ የኢትዮጵያ መልክአ ምድሮችን እንመለከታለን። ይህ መልክአ ምደር/ማፕ የፕሮፌሰር ንጉሳይ አየለ የምርምር ውጤቶች ስለሆኑ አስቀድሜ ለሳቸው ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በእነዚህ መልክዓ ምድሮች የምንመለከተው ቁም ነገር ጣሊያን ከአፄ  ምንሊክ ጋር ያደረገው የድምበር ውል በማፍረስ እራሱ ያዘጋጀው ከ1888 እስከ1928  ኢትዮጵያን ያዋሃደ የመጀመሪያው የኮሎኒ/የወረራ መልክዓ ምድር /ካርቶግራፊን እንመለከታለን። ከዚአ ለ 5 አመት ግራ እና ቀኝ በጀግኖች እየተዋከ ቆይቶ በ1933 ዓ.ም ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ ተባረረ። 

 

ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ጣሊያን በሠራው ካርቶግራፊ እና እራሱ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ አንድ ግዛት መሆናቸውን የሰራውን እና ውሉን አፍርሶ የሰራውን መልክዓ ምድር ተከትለው ሕዝቡን በማማከር እና ከላይ ባስነበብኳችሁ የኤርትራ ጥያቄና ፍላጎት እሳቸውም ጠቅልለው ሕጋዊ መልክዓ መሬታቸውን እስከ 1966 ዓ.ም ድረስ አስተዳደሩ።

 

ከዚያ ደረግ ከ1966 እስከ 1991 ዓ.ም ድረስ የተረከበውን ሕጋዊ መልክዓ ምድር ሲያስተዳድር ቆይቶ በዚያ በ 17 አመት ውስጥ ውስጣዊ የድምበር አስተዳዳር ለውጥ አደረጎ ዓሰብን እና ሌሎችን በራስ ገዝ ‘ጀሪ መንደሪ’ (ሪዲሰትሪክቲንግ) ሕግ በመከተል አስተዳደሩ ወደ ወሎ አዛውሮታል።

 

 የመረብን ወንዝ ጥሼ ወደ ኢትዮጵያ ወደ ትግራይ ድምበር ከገባሁ በጣሊያን እና በምንልክ የተደረገው ዉል አይጸናም ብሎ የፈረመበትን ዉል ድምበር ጥሶ በ1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን ለሁለተኛ ጊዜ በሁለት አቅጣጫዎች ኢትዮጵያን ወርሮ የኮሎኒ አዲስ መልክዓ ምድር የሰራበትን ብቻ ሳይሆን፤ እኔ በሆነ ምክንያት ኤርትራን ለቅቄ ስወጣ፤ ኤርትራ ለሕጋዊ ባለቤቷ ለኢትዮጵያ አስረክባለሁ፡ ያለውን ዉል ሁሉ ማጤን ያስፈልጋል። 

 

ከአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ እስከ ደርግ ጊዜ በወላጆቻቸው አስተዳዳር ሥር በአጥንታቸውና በደማቸው ተከብሮ የቆየው የባሕር ነጋሽ ምድር ዛሬ ‘ራሳቸውን ‘ወያኔ’ ብለው የሚጠሩ ትግራይ ውስጥ የበቀሉ ባንዳዎቹ የኤርትራ ጉዳይ የኮሎኒ ጥያቄ ነው፡ በቅኝ ግዛት የያዘቻት ደግሞ ኢትዮጵያ ነች፡ ስለሆነም መለክዓ ምድሩን ለማካለል በኮሎኒ/በቅኝ ግዛት ደምብ እና ካርታ ተደራድረን ኤርትራን ጉዳይ እንፈታለን ያሉትንም ቢሆን “የኮሎኒ” ሕግም ቢሆን አልተከተሉም። አሁን አሁን ከአልጄሪስ ስምምነት ወዲህ ብዙ የወያኔ መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው የነበሩ ስምምነቱ የወያኔ መሪዎች እንጂ የሕዝብ ውሳኔ እንዳልነበረ ሁለት ያታወቁ የትግራይ ተወላጆች እንዲህ ይገልጹታል፡-

 


“Before anything else, the people living in the region called “Eritrea” are, Tigreans. The idea of “Tigreans” and “Eritreans” as separate peoples, was never ours. See editorial (December 1993) Ethiopian Commentator, Haile Mariam Abebe.).


ሻዕቢያዎች እየነገሩን ያሉት ኤርትራ ነፃ የወጣቺው በሕግ ሳይሆን በጉልበታችን ነው። ብለዋል። በትግሬ ምሁራን የሚገለጸው እውነታው ግን አንዲህ ነው፦


“When the EPLF was pinned down by Mengistu’s army in Nakfa, the Tigrean fighters arrived for its rescue twice. During the “Red Star Campaign” of 1982, for instance, Tigreans fought in Nakfa on the Eritrean side, for nine months. Furthermore, without the supreme sacrifice of the Tigreans, the demand for Eritrean independence would have been little more than a bargaining chip for a negotiated settlement.”  ( Alem Abbay (1993) “An Unappreciated Gift Horse in the Mouth”, The Ethiopian Times, March/April 1,
No. 2)  


አለም ዓባይ ከላይ የነገረን፤ “….ሻዕቢያ በመንግስቱ (ኢትዮጵያ) ወታደር ናቕፋ ላይ ተገፍቶ ትንፋሽ አጥሮት ከተራሮቹ ግድግዳ ተጣብቆ ሞቱን ሲያጣጥር  የወያኔ ትግሬ ተዋጊዎች ወደ ናቕፎ ገስግሰው ቶሎ ደርሰውለት ከፍተኛ መስዋዕት ከፍለው ከደርግ ሃይለኛ ብትር ባያድኑት ኖሮ የሻዕቢያ መጨረሻ ዕድል ከኢትዮጵያ ጋር በደርድር ይቋጨው ነበር።” እንዳለው ሁሉ ፤ እውነትም ሻዕቢያ ዓሰብን ለመስጠት ዝግጅነቱን ለደርግ መግለጹ ይታወሳል።

ወያኔዎች የኰሎኒ የግዛት ማፕ ብለው ወደ ዓለም መድረክ ለድርድር (ለሴረው) ሲቀርቡ ይዘውት የመጡት ማፕ “የኰሎያሊስትዋ ጣሊያን እንጂ” “የኰሎኒያሊስትዋ ኢትዮጵያ” አይደለም። ምክንያቱ ምንድ ነው? ቢባል፤ የመጨረሻዋ ኢትዮጵያ ኮሎኒያሊስት ነች ሲሉ የደሰኮሩበትን ሁለቱ ‘ወንበዴዎች’ በግብር ለመተርጎም የኢትዮጵያን ኮሎኒያል ካርታ ይዘው ከሄዱ ከታች የሚታየው 3ኛው ካርታ ሕጋዊ ሊሆን ነው። ያ ደግሞ ዓሰብን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገባ መሆኑን በደምብ ስለሚያውቁ እና ስጋት ስላደረባቸው፤ በለመዱት ዓመጽ እና ቅጥፈት ከውጭ ኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተመካክረው “ኢትዮጵያ” የት ትደርሳለች “ኢትዮጵያን አምበርክከናታል” ስለዚህ የበሰበሰ ጣሊያን ማፕ ብቻ ይዘን አንቅረብ ብለው ኤርትራን አስገነጠሉ።

 

በጣም የሚገርመው ደግሞ ከጣሊያን ካርታዎችም ቢሆን መርጠው (ፒክ ኤንድ ቹዝ) ነው ለግንጠላ የሚያመቻቸውን የበሰበሰውን የድሮ ማፕ የተጠቀሙበት።እንደነገርኳችሁ በማፕ የሚገዙ ቢሆኑ ኖሮ ጣሊያን የሰራው ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ያዋሃደው የ1928 እስከ 1933 ዓ.ም የመጨረሻውን ውሉን አፍርሶ የሰራውን አዲሱን የጣሊን ቅኝ ማፕ ሊጠቀሙበት በቻሉ ነበር። ሆኖም ገብሩ አስራት በመጽሐፉ አንደገለጸው በባንዳው ወየኔ አመራር ውስጥ ከኤርትራኖች በላይ ኤርትራኖች ሆነው ኤርትራኖችን ለመጥቀም ከነሱ ጋር ወግነው አገራቸውን ኢትዮጵያ ፍትሕ በተጻረረ ሁኔታ ኤርትራን አስገንጥለው 90 ሚሊዮን ሕዝብ ያለ ባሕር ወደብ አስቀርተው በጠላት አንደትከበብ አድርገው የፈርንሳይ ጥገኛ የሆነቺውን ከጅቡቲ እና ስርዓት ከፈረሰባት (ፈይልድ ስቴት) ከሶማሊዋ የሐርጌሳ የወደብ ተከራይ ቴናንት/ጥገኛ አደርገዋታል።

ሦስቱ ካርታዎች

ወያኔዎች ለኤርትራ ጥብቅና ቆመው የባሕር በር ለኢትዮጵያ ሲዘጉ፤ የተጠቀሙባቸው ወጋ ቢስ የሆኑ “የፈረሱ የቅኝ ግዛት መከራከሪያ ውሎች” ብለው የሚሞጉቱባቸው በምኒልክ እና በጣሊያን ፋሺስት መካካል ተደረጉ የተባሉ ሦስቱ ዉሎች የ1900/19002/1908(እኤአ) ውሎች ናቸው። እነዚህ ውሎች ዋጋ ቢስ ናቸው አንቀበላቸውም ብልን የምንሞግትባቸው ምክንያቶች በሚከተሉት ነጥቦች ምክንያቶች ነው። በቀላሉ አንዲገባችሁ ባጭሩ ላስረዳ፤-

 

1)    የMay, 1889 (ኤዘአ)ውጫሌ ውል እየተባለ የሚጠቀሰው ምኒሊክ ለመሳሪያ እና ለገንዘብ ልውጥ ኤርትራን ለጣሊያን ሸጧት የሚባለው ውል የያዘ እና ኢትዮጵያ የጣሊያን ቅኝ ነች የሚለው በጣሊያን ቋንቋ የተጻፈው ከአማርኛው ትርጉም እና ውል የሚጻረር በመሆኑ ምኒልክ ውሉ እንዲስተካከል በትዕግስት እየጠየቁ አንዲስተካከል ቢጠይቁም ጣሊያን አልለውጠውም በማለቱ ምንሊክ በ1893 (ኤ ዘ አ) በግልጽ አወጁ፡ ዋጋ አንዴሌለው ለጣሊያን እና ለዓለም አስታወቁ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ካልገዛሁ ብሎ በ1888 ድምበር ጥሶ (ኢዘ አ) ዓድዋ ላይ ጦርነት ከፍቶ ውርደቱን ተከናንቦ እጁን ሰጠ። ከዚያ በፊት የነበሩት ውሎች በሙሉ ፈረሱ።ለጊዜው ለሁለቱ ተዋጊዎች ደምበር ሆነው የሚያገለግሉ ሦስት ወንዞችን መረብ፤በለሳ እና ሙና እንደ ድምብር አጥር ሆነው ተወሰኑ።

 

 

2)    ምኒሊክ ሰራዊታቸው ይዘው ወደ ኤርትራ መዝለቁ ፤ጣሊያን ተዋጊ ትኩስ ሃይል፤ስንቅና መሳሪያ በባሕር እየተላከለት አንደሆነ እና በተጨማሪም እዚህ ለመጥቀስ የማያመቹ ሰፊ የሆኑ የመሃል፤የደቡብ እና የምስራቅ ኢትዮጵያ ግዛት ክፍሎች ዝርዝር ትንተናዎች የሚሹ ሰፋፊ ያልተጠቀሱ ምክንያቶችም ጭምር ጦርነቱን መግፋት አደጋ አንዳለው በመገመታቸው ሰራዊታቸው ከድሉ በሗላ በደስታ ወደ እየ መንደራችን አንመለሳለን ብሎ መፍረስ በመጀመሩ እና በከብትና በሰውሕይወት ረሃብ እና በሽታ ትግራይ ውስጥ ግብቶ ብዙ ሰው ስላለቀ (የስንቅ ችግር) እና በመሳሰሉ ሁኔታው አመች ስላልነበረ ኤርትራ በጣሊያን እጅ ልትቆይ ወሰኑ። ኤርትራ ሲቆይ ድምብር እንዳያልፍ ተፈራረመ።ኤርትራ ለቆ ሲወጣም “ኤርትራ” ለባለቤቷ ለኢትዮጵያ አንደምታስረክብ በ1896 እና የ1900 (ኤአ) ውል ገባ። ኤርትራ ለማንም መንግሰት /ሃይል/ተዋዋይ አሳልፋ ለመስጠት ወይንም መሸጥ አንደማትችል ፈርማለች። (በሗላ ቃሉን አጥፎ ኤርትራ ለእንግሊዝ ሰጥቶ ወጣ፤ ወይንም አንግሊዝ በጉልቷ ነጠቀች)።የተጠቀሱት ስመምነቶች አስመልክተው ታላቁ የታሪክ ምሁር ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ የሙሉት “It should be emphasized that the treaties of 1902 and 1908 under which Eritrea claims the disputed territories are essentially flawed. These territories belong indisputably to Ethiopia and until Italy, in its attempt to provoke another war with Ethiopia annexed them in 1929 by force, they were administered by Ethiopia. What makes even more difficult the settlement of conflict between the two countries according to the colonial treaties is the fact that the geographical map of Eritrea has constantly changed during and after those treaties as the following instances highlight: 

Even under Italian rule, considerable part of Eritrea was under the sovereignty of Ethiopia. This includes the huge expanse of land under the control of Dabre Bizen and its dependencies (daughter monasteries) that were directly administered by the imperial Ethiopian government. If Eritrea insists that the border should be marked according to the above-mentioned colonial treaties, it is within Ethiopia's power to claim back these territories and those forcibly annexed by Zolli in 1928 and 1929. In both ways, Eritrea is bound to lose substantial mass of its land. Moreover, the control of Dabre Bizen and its dependencies will give Ethiopia a safe gateway to the important port of Massawa. Understandably, this will have serious consequences for Eritrea as an independent state. ጣሊያን ኤርትራን እያስተዳደራት እያለም ቢሆን ኤርትራ ውስጥ የሚገኘው ደብረቢዘን ገዳም ሳይቀር በኢትዮጵያ ኣስተዳደርና ንብረት ነበር (በውጫሌ ውስጥ ተጠቅሷል)


http://www.ethiopianreview.com/2001/Article_HaileMLareboAPRJUN_2001.html


3)   ጣሊያን ለሁለተኛ ጊዜ አልደፍርም ያለበትን የድምበር ውል አንደገና ጥሶ በመረብ እና በኦጋዴን ገብቶ በ1928 (ኢዘአ) ኢትዮጵያን ወረረ። ለ5 አመት ሲዋከብ ቆይቶ ተሸንፎ ወጣ። ከዚህ በፊት የነበሩ ውሎች ሁሉ ፈረሱ። 

 

4)  ከዚያ በሗላ በእንግሊዝ ተንኮል ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መዋሃድ ሲኖርባት ከሃያላኑ አንዱ በመኖሩ ኤርትራን እና ትግራይን ገንጥሎ ለማስተዳዳር አንዲመቸው ፍላጎት ስላደረበት  ኤርትራ ውስጥ እቆያለሁ ብሎ ተንኮል ሰራ። በዚህ ጭቅጭቅ ተነሳ። ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በሗላ 4 ሐያላን መንግስታት ሲባሉ የነበሩት የመሰረቱት የኤርትራ እና ኢትዮጵያ ጉዳይ መርማሪ አካል በደረሰበት ጥናት መሰረት፤ የተባበሩት መንግሥታት ማሕበር ጉባኤ ኤርትራ በንጉሡ የዘውድ አስተዳደር ሥር ሆና ፤የራስ ገዝ’ መብት ተሰጥቷት ለ10 አመት ከቆየች በሗላ ወደ ኢትዮጵያ ትዋሃድ ብሎ ውሳኔ ሰጠ። በ1900/1902/1908 የነበሩ ዉሎች እንደገና “ለሦስተኛ ጊዜ” በዚህ ባዲሱ ሕይወት እና አስተዳደራዊ ለውጥ ተሻረ።


5)  በ1944 ዓ.ም (ኢዘ አ) ኤርትራ እላይ እንደተመለከታችሁት መሰረት በሕዝቡ ተወካዮች ኤርትራ ከኢትዮጵያ ሙሉ ውሕደት አደረገች። በዚህ ለአራተኛ ጊዜ የቆዩ ዉሎች በሙሉ ፈረሱ።

 


6)  ዓሰብ ከዋነኛው የኤርትራ ማሕበረሰብ በ400 ኪ.ሜትር ርቀት ርቃ ትገኛለች። ለብዙ አመታት መላትም እስከ ደርግ ፍጻሜ ድረስ ከኤርትራ ይልቅ ምጣኔ ሐብታዊ (ንግድ) እና ማሕበራዊ ግንኙነት ከኤርትራ ይልቅ ከኢትዮጵያ ጋር ነበር። ዓሰብ ለደሴ 70ኪ/ሜ ትርቃለች። የወደብ መጠቀሙ መብት እና ሂሳቡን በሕግ ምረኩዝ ስታሰሉት “ወያኔዎች” ባሕር ወደብ ለኛ መከልከላቸው ትግራይ ትግርኚ መደብ ሊጠብቁት የፈለጉት ሴራ፤ ወይንም በሥልጣን ያሉ ትግሬዎች ወደ ኤርትራ የሚያደሉት የሁለት ደም ዲቃላዎች ሆነው ይበልጥ ለኤርትራ በማዳላታቸው ነው። ከሁለቱ አንዱ። 

 


7)   ወያኔዎች አልጀሪስ ሄደው ባቋቋሙት ፈራጅ አካል በ1902/በ1905/1908/ ጠሊያን የሰራው ካርታ እና ስምምነት አንፈረዳለን ሲሉ በሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ “ይግባኝ” ማለት እንደማይቻል የተፈራረሙበት ምክንያትም ከዚያ በሗላ የተሰሩ ካርታዎኦች እና ውሎች ካቀረቡ “ይዘውት የሄዱት ውሉ” የበሰበሰ፤የማይሰራ መሆኑን አስቀድመው ስላወቁ፤ “ይግባኝ” የሚያግድ ስምመንት ሆን ብለው መፈራረማቸውለ፤ግልፅ ሴራ ነው። ለወደፊቱም በሕጉ መሰረት “አንድ የመንግስት ተወካይ/አካል/ ሆን ብሎ የአገሩን ጥቅም የሚጎዳ ስምምነት ከፈረመ ስምምነቱ አንደገና አንደሚመረመር የተባበሩት መ/ሕግ ይጠቅሳል።                                   

 

አሁን፤ ለማስረጃ ያቀረብኳቸው 3 የተለያዩ መልክዓ ምድሮችን እነሆ ተመልከቱ እና ወያኔዎች በሴራ እንዴት አንደጐዱን ይኼው ተመልከቱ።  

Map 1. Ethiopia During Fascist Italy's Occupation (1936-41).

Map 2. Ethiopia between 1952-1987.

Map 3. The 1987 Border Regime of Ethiopia  (1987-91).

   በዚህ መረጃ መሰረት ኮሎኒዎች ነን ከተባልን የመጨረሻው የኮሎኒ ማፕ የቀረጸው እና የመጨረሻው ኮሎኒያሊስት ማን ነው? የሚለው ጥያቄ እናቅርብ። ኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ ባዕድ ነች በለውናል። በኮሎኒያሊሰት ማፕ እንዳኛለን ካሉ እኛ የሰጠናቸውን የመጨረሻዎቹ ቅኝ ገዢዎች የምንባለው የሰራንላቸው የኮሎኒ ማፕ ለምን ይዘው ለድርድሩ አልተጠቀሙበትም? የ1964 የካይሮ ውሳኔም ተገንጣዩ የመጨረሻው ቅኝ ገዢ የሰጠው መሬት/ቅርጽ ይዞ ይሄዳል ይላል። መጨረሻ ቅኝ ብለው ወያኔዎች የሰየሙንም እኛ ከሆንን፤ ኢትዮጵያዊያን ቢሆኑ ኖሮ የኛን ካርታ ይዘው መከራከር ነበረባቸው።  መልስ የሚያሻው ጥያቄ ነው። 


ባንዳዎቹ በእውነተኛ ክርክር ጎሮራቸው ስለታነቁ ለዚህ ጥያቄ እስካሁን ድረስ መልስ ሲሰጡበት የሰማነው መልሳቸው “ኢትዮጵያ ያለ ወደብ 22 አመት ኖራለች ስለዚህ አያስፈልገንም” ወይንም ፤ በስብሐት ነጋ መልስ መሰረት “ዓሰብ ሳይሆን ጅቡቲ ነው ለኛ ለኢትዮጵያ የሚረባው” (ዓሰብን አትጠይቁ ወደ ትግራይ- ለትግራይ ትግርኛ መርሃ ግብሩ ስለሚጠቃለል ማለቱ ነው። ወያኔ “ዓሰብ” በትግራይ ክልል ያካተተ ካርታ ሰርቶ እንደነበረም ታውቃላችሁ።) የመሳሰሉ የማሃይሞችና ተረብተኞች መልስ ከመስጠት በቀር ለጥያቄአችን ቀጥተኛ መልስ ሊመለሱልን አልቻሉም። 22 አመት ያለወደብ ከጅቡቲ ወደብ እየተከራዬን ኑረናል፤ ስለዚህ ያለ ወደብ መኖር ይቻላል፤ የሚለው “መልስ ሲያጡ የሚመልሱት መልስ” የውዳቂዎች መልስ ነው።  ለነገሩ ኑሮ አይባልም አንጂ ኤርትራም  እኮ 22 አመት ወደቧ ባዶ ሆኖ ኖራለች። ጥያቄአችን አጭር፤ቀጥተኛና ግልጽ ነው!!!  22 አመት ዳክረው መልስ ያጡበት ጥያቄ አሁንም እንዲመልሱልን እንጠይቃቸዋለን። 


ወያኔዎች የኤርትራን ጉዳይ መፍትሄ ለማግኘት በኮሎኒያሊሰት ማፕ እንዳኛለን ካሉ ለምን እኛ የሰጠናቸውን የመጨረሻዎቹ ቅኝ ገዢዎች የምንባለው የሰራንላቸው የኮሎኒ ማፕ ይዘው ለድርድሩ አልተጠቀሙበትም? ጥያቄአችን አጭር እና ቀጥተኛ ነው። ለመረዳት አያስቸግርም።
ይህንን ለመመለስ 22 አመት ፈጀባቸው- አሁንም መልስ የላቸውም፤ ዛሬም ለጥያቄችን መለስ እየጠበቅን ነው። ወይ ኢትዮጵያ የኤርትራ ቅኝ ገዢ አልነበረችም በሉን ወይንም ነች ካላችሁ ደግሞ ጥያቄአችንን መልሱ። ካልሆነ ክርክራችሁ አንጅት የሚያሳርር ‘የፖለቲካ ጨዋታ ነው’። ፕሮፈሰር ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ አንዳሉት 

“…the time gap that exists between these treaties and the Eritrean independence is so vast, and the change in status that Eritrea underwent during this same period is so intricate as to make any appeal to colonial treaties and OAU charter of no use beyond political gimmickry.”  

(Colonial Treaties in the Context of the Current Ethio-Eritrean Border Dispute and Settlement  4th International Conference of Ethiopian Studies, November 6-10, 2000, at the Institute of Ethiopian Studies, Addis Abeba University. Ethiopian Review Ethiopian Review, April 2001)   

 
ኤርትራ የደፈረሰች፤ ያለቀላት፤ የተበላሸች መንደር የኢትዮጵያውያን ብርቱ ክንድ እየጠበቃት ነው። ምርጫው የራሷ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) Ethiopian Semay getachre@aol.com