Thursday, April 27, 2017

አሰፋ ጫቦ! ገናናው ብዕርተኛ!
ከጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)
Assefa Chabo 4/26/2017 Posted at Ethiopian Semay

አቶ አሰፋ ጫቦ ወደ እዚያኛው ዓለም አልፈዋል።የተከበሩ አቶ አሰፋ ጫቦ ከዚህ ዓለም በድንገት መለየታቸው በዜና አውታሮች ተለጥፎ ባየሁ ጊዜ የተሰማኝ ድንጋጤ በህይወቴ እንደዚያ ያለ ስሜትና ሓዘን ተስምቶኝ አያውቅም። እጅግ አሳዛኝ መርዶ ነው። በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ እኔ ጌታቸው ረዳ ለቤተሰብ እና ወዳጆቻቸው መጽናናት እንዲሰጣቸው የሓዘን መልዕክት ለማስተላለፍ እወዳለሁ።

ይህ ካልኩኝ በኋላ አንድ ነገር ለማለት እፈልጋለሁ። በአንድ ድርጅት የሓዘን መግለጫ በኩል ስለ እሳቸው የተላለፈ “የሰብአዊ መብት ተሟጋች” ነበሩ’ የሚለው ከህይወት ታሪካቸው ተያይዞ የቀረበ መግለጫ አከራካሪ ስለሆነ፤ አስከሬናቸው በትውልድ አገራቸው ኢትዮጵያ አፈር ከለበሰ በኋላ ለድርጅቱ አዘጋጆች በጥያቄ የምመለስበት ስለሆነ በዚሁ ልለፈው።

ሆኖም ይህ ድንገተኛ ሞት ከማጋጠሙ በፊት በህይወት እያሉ እሳቸው በወያኔ ስርዓት ውስጥ “ኦሞቲክ” የሚበል የደቡብ የጎሳዎች ድርጅት በመምራት በወያኔ የሥልጣን ሽግግሩ ወቅት በተሳተፉበት ወቅት በርካታ አገር ወዳዶች እንደ እነ አሰፋ ማሩ፤ ፕሮፌሰር አስራት እና በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች፤ ህጻናት ሳይቀሩ በቢላዋ፤በገጀራ እየታረዱ፤ከነነብሳቸው ወደ ገደል እየተገፈተሩ ሲጣሉ፤ በርካታ ምሁራንና ዜጎች  በወያኔ ነብሰገዳዮች እየተገደሉ እና እየታደኑ ሲሰወሩ፤ ዝነኛው አገር ወዳድ ፕሮፌሰር ዶክተር አስራት ወልደየስ ስለ አመራው መጨፍጨፍ እና ስለ ኤርትራ መገንጠል በመቃወማቸው ስብእናቸው በቴ/ቪዠን ሲገፈፍ እሳቸው (አቶ አሰፋ ጫቦ) እና የሲዳማ ነፃ አውጪ ድረጀት መሪ የነበረው ሟቹ ወልዳማኑኤል ዱባለ ግምባር በመግጠም  ፕሮፌስ አስራት ያቀረቡትን አቋም በመተቸት፤  ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያው ኢሳያስ አፈወርቅ በተገኘበት አዳራሽ ለኤርትራ ወንበዴዎች ፤አገር ሿጮች፤ነብሰገዳዮች፤ከሃዲ ባንዳዎችን በመደገፍ፤ ምን አቋም አንደያዙ እና ካንደበታቸው ሲወጡ የነበሩ እጅግ አስገራሚ ቃላቶች እና ክርክሮች በማሕደር የተመዘገበ አንደበታቸው መከራከሪያ አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል (ሌሎች ያልገለጽኳቸው ጉዳዮችም ለሟቹ ክብር ስል እዚህ አልጠቅስም)። በዚህ አጋጣሚ ጽሁፎቼን ለማንበብ ከፈለጋችሁ አስፋ ጫቦንስ ከፍተን ብናያቸው? ጌታቸው ረዳ (ኢትዮያጵያን ሰማይ አዘጋጅ)  ወልቃይት.ካም http://welkait.com/?p=7482  ወይንም  ኢትዮ-ጳትረዮትስ.ካም 
http://www.ethiopatriots.com/pdf/አስፋ-ጫቦንስ-ከፍተን-ብናያቸው.pdf

ወይንም Ethiopian Semay facebook ወይንም Ethiopiaan seamy blogspot.com

ብላችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። የመጨረሻው ትችቴ ማርች 20/2017 ነው። ለዚህ ጽሑፍም ሆነ ለመጀመሪያው ትችቴ መልስ መስጠት አልፈለጉም ነበር። በድንገት ከመለየታቸው በፊት፤ ሌሎች ርዕሶችን በሚመለከት ሲጽፉ እንደነበር አይቻለሁ እና፤ መልስ መስጠትም የሚችሉበት የመከራከሪያና የማምለጪያ መስኮቶቹ ዝግ ስለነበሩ፤ መልስ አልነበራቸውም። በዚህም አከብራቸዋለሁ ። (ለኢሕአፓንም ሌላ ተመሳሳይ ጉዳይ ጠይቄው መልስ ስላለስጠኝ  ኢሕአፓም አፉን ስለዘጋ፤ አክብሮት እሰጠዋለሁ ማለት ግን አይደለም፡ ጉዳዩ ለየቅል ነውና) ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በድንገተኛ ሞት ከዚህ ዓለም ተለዩን። በጣም ነበር ከውስጥ አንጀቴ እጅግ ያዘንኩት። በወቅቴ የተሰማኝን ድንገተኛ ሓዘን ለመግለጽ ቃላት አላገኘሁም።

ምከንየታዩም እሳቸው፤ የኋላኋላ ጸረ ኢሳያስ / ከዚያም ጸረ ኦነግ፤ ጸረ ወያኔ፤ ብርቱ ብዕርተኛ ፤ሲጽፉ ለዛቸው የሚጥም፤ልዩ የብዕር ስልተኛ ነበሩ። ከዚያ ባለፈ ግን ጽ/ቤቱ ዋሺንግተን ያደረገው ከኣንድ ተቋም ክቡር አቶ አሰፋ ጫቦን “የሰብአዊ መብት ተሟጋች” ነበሩ ያለውን በኔ በኩል አልቀበለውም። አቶ አሰፋ ከዚህ ዓለም በሞት ከመለየታቸው በፊት እንደ እነ ጸሀፊው ጸጋዬ ገ/መድህን (ሙሉጌታ ሉሌ) እና የመሳሰሉት ከግንቦት 7 ጋር (ባጭሩ ኤርትራ ከሚያሰለጥናቸው ጋንጎች ጋር) አልተሻሹም፤አልቆሸሹም። እንደ እነ ሙሉጌታ ሉሌ ለጸረ አማራው እና ለጸረ ምኒሊክ ለነ የግንቦት 7ቱ ኤፍሬም ማዴቦ “አምባ አላቀረሩም”፤ ኤፍሬም ማዴቦን ጀግናዬ አላሉትም። ስለሆነም በዚህ በዚህ  ለአቶ አሰፋ ልዩ ከበሬታ አለኝ።  በሓዘን ላይ ሆነ እንጂ በጣም የሚገርመኝ እዚህ ውጭ አገር ያሉ የፖለቲካ አክቲቪስቶች እና ፖለቲከኞች ጋዜጠኞች ‘በወያኔ (እንዲሁም በደርግ) ለታሰረ ሁሉ “ጀግናዬ”/ጀግና/ እያሉ አንዳንዶቹን ሲያሞካሹ አይቻለሁ; ያስገርመኛል፤ የደርጉን አንተወው እና የወያኔን እስረኞች ብንመለ፤ከት ታምራት ላይኔም፤ ስየ አብርሃምም፤ ብስራት አማረም፤ አንዳርጋቸው ጽጌም፤ ጁነዲን ሰዶ ወዘተ ሰንቶቹ የስለላ እና የመረጃ አቀባይ የነበረ፤ በአንድነታቸወን ላይ ሲያሰር እና ሕግ ሲያጸድቅ የነበረ፤ ናዚያዊ ጸረ አማራ መጽሐፍ የጻፈ ሁሉ በወያኔ ታስረው ተሰቃይተዋል፡ ስለሆነም እነሱም በጥቅሉ ወደ ጀግና መንደር እየደባለቁ ሲሞካሽዋቸው አይተናል። ለዚህም ነበር ብርሃኑ ነጋ “ጎህ ሲቀድ” በሚለው ስለራሱ (ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት) በጻፈው መጽሐፍ ላይ፤ የወያኔን ካርታ ከመለጠፉ አልፎ መጽሐፉን ለስየ አብርሃ ነበር ማስታወሻነቱ እንዲሆንለት የገለጸው። (የተስፋየ ገብረ አብ መጽሐፍ መቅድም ጻሀፊው እና አሻሻጩ “ብርሃኑ ነጋም በሌለቹ “ጀግና” ተብሏል። የዘመኑ ጀግና እጀግ  ያስገርማል። አርበኛነት በ$500.00 ዶላርም መግዛት የተቻለበት ዘመን መጥተናል።

አንድ እጅግ የታዘብኩት ነገር አለ። እሱም አቶ አሰፋ የተሳሳቱት (ምክንያታቸው ባልታወቀ ምክንያት እና ምንም ተቀባይነት በሌለው ምክንያት “ምጽአተ አማራ የሚለው መጽሐፍ እና የሞረሽ ሲቪክ ድርጅት መሪው ክቡር አቶ ተክሌ የሻውንም የመዝለፋቸው እንቆቁልሽ) እንዳለ ሆኖ፤ ለሟቹ ለክቡር አቶ አሰፋ ጫቦ ልዩ አክብሮት የምሰጣቸው ምክንያት፤ ብዙ ታላላቅ ጸሐፊዎች ፤ጋዜጠኞች፤ምሁራን ለኢሳያስ ግብር ሲያድሩ፤ ከተሰቀሉበት አስከባሪ ማዕረግ እራሳቸው በቅሌታቸው ወደ አፈር አውርደው ሲጥሉት እና ሲያዋረዱ፤ ለኤርትራ ወንበዴዎች ልዩ ሙገሳ ሲያቀርቡ፤ ከጐሰኛ  ቡድኖች ጋር ሕብረት በመፍጠር ልዩ ፕሮፓጋንዳ ለተግንጣዮች እና አማራን ለጨፈጨፉ እና ላስጨፈጨፉ ወንጀለኛ የተግንጣይ መሪዎች ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩ፤አልፎም “በእነሱ ጫማ ስር ገብተን ጫማቸውን አንድንለካላቸው” ሲገፋፉን፤ እና በርካታ ‘አጋሰስ ምሁራን”  ለግንቦት 7 እና ለኦነግ ጎሰኛነት አክብሮታዊ  ትኩረት በመስጠት እንደ እነ ጌታቸው በጋሻው፤ ፕሮፌሰር መሳይ፤ ሻለቃ ዳዊት ወልደግዮርጊስ፤ አምባሳደር ካሳ ከበደ….ወዘተ…..ወጣቱን ሲያጃጅሉት፤  አቶ አሰፋ ጫቦ ግን በዚው ጭቃ አላደፉም። ለዚህም ነው አክብሮት የምሰጣቸው እና ሓዘን የተሰማኝ። እግዚአብሔር ነብሳቸውን ይማር! ለቅርብ ቤተሰብ እና ለወዳጅ ዘመድ የኢትዮጵያ አምላከ እግዚአብሔር መጽናናት ይስጣቸው!
ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) getachre@aol.com