Sunday, April 12, 2009

የትግራይ ተወላጆች ትዝታቸዉና ትዝታችን




የትግራይ ተወላጆች ትዝታቸዉና ትዝታችን
“እዚህ ዉጭ ሀገራት የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆችም በህወሐት ዉስጥ ስለ ታየዉ መከፋፈልም ሆነ ስለ የትግራይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገብሩ አስራት ከስራ መወገድ አስመለክቶ ግራ እየተጋቡ ነዉ። እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችም በጉዳዩ የተቆጡ የጥቆቶቹ ተወካዮች አንዳንዶቹን ተወካዮችን አነጋግረናል”። የቪኦኤዋ ጋዜጠኛ አዳናች ፍስሃየ ነበረች ይሄነን ዘገባ ያስደመጠችን (“የዛሬ 7 ዓመት”)፡ ወቅቱ ትዝ ይላችሓል?ወቅቱ የኢትዮጵያ አምላክ ጠላቶቿ አንድ ባንድ ይበታትናቸዋል ሰንል “ይሳቅብን” የነበረበት ወቅት ነዉ። ያዉም እንደዛሬ ዙርያችን ሁሉ የሸራቶን ጠረፔዛ አሟቂ የነበረዉ ሁሉ ባልታጠረበት ወቅት፣ በጣም .እጅግ በጣም አናሳዎች በነበርንበት፡ ሽዋዉአን ተጋሩ!አማሓሩ፣ ተስፋ የቆረጡ፣ ደርጎችና ነፍጠኞች በምንባልበት ወቅት፣ የወያኔ ጎረምሶች ደረታቸዉ በጠብስና በክትፎ ቅቤ ተደፍኖ፣ የሚሆኑት አጥተዉ “ኤርትራዊት አዶ እዚ ኩሉስ አይሳላኺንዶ” ዘፈን አንግበዉ፣ የሻዕቢያ ባንዴራ ሙትት አድርገዉ እየሳሙ፣ እያዉለበለቡና እየዘለሉ “ምን አባህ!” ሲሉን በነበረበት ወቅት! አይ! አይ! አይ ጊዜ መስተዋቱ! ሁ….ሉ…..ም!!!!!!!! አሳየኸን! አየ ተላላዋ “ገመል” እንሰሳዋ! ልቤን ሰቅዞ የሚይዝ ቃል ቢኖር ይኼኛዉ ቃል ነዉ፡ “ትዝታ!” የፍቅር ትዝታ። መጥፎም ደግም ትዝታዎች አሉዋቸዉ። ሁሉም ባንጀት ዉስጥ ይሰፍራሉ። ያዉም በጣም ከዉስጠኛዉ ክፍል ከጎድጓዳዉ ስፍራ ሁሉም ከሚደብቅ፣ ሳይታዘዝ ሳይታስብ “ብቅ” ይልና በትዝታ ልብን የሚሰቅል የሚያከንፍ በቃጠሎ ልብን የሚያነድድ፡ አይ ትዝታ! የረሳችሁት አንጀት የቋጠረዉ የድሮ ፍቅር ቢኖርባችሁ ቀሰቀስክብን እንዳትሉኝ ትዝታዉን ትቼ ወደ ፖለቲካዉ ትዉስታዉ ልዉሰዳችሁ:፡ እኔ እንደታዘብኩት ፖለቲካም ክፉ ፍቅር ያስይዛል፡ “ካልት”ይሉታል ፈረንጆቹ ። ያነሆልላል፣ ያሳብዳል “መሰዋእቲ””ይሉታል መሰለኝ ‘ተጋደልቲ’!“ሌላን ፍጡር አስከመግደል ራስንም አስከ ሞት መስጠት”-የሚያደርስ ኩፉ የድርጀት ፍቅር። ያዉም የጎሳ እማ ክፉኛ ለክፎ ያስሳብዳል።የጎሳ ፖለቲካ ሲወሳ ትዝታችን የሚያስታዉሰን እዉጭ የሚገኘዉ ምናልባትም 95ከመቶ የትግራይ ተወላጆች “ለወያኔ ትግራይ” አልያም ለጎሳቸዉ ያሳዩት ትኩረት ከፍተኛ ነበር። “የባድመ ጦርነት ምስጋና ገብቶት አይግባዉና” ወያኔዎች ለሁለት ሲሰነጠቁ “እሩቅ እጅግ በጣም አሩቅ”ጥሎዉት የነበረዉን የኢትዮጵያዊት ባስቸኳይ በነብስ አድን ፍለጋ ዉስጥ ገብተዉ “ኢትዮጵያ! አገራችን!” ሲዘምሩ ብዙ ሰዎች ተስፋ አድርገዉ “እንሰሳዋ ገመል”የናዚ ንቅሳትዋን በላጲስ ለማጥፋት ሕሊና ለበሳለች ብለዉ ነበር። እንደተጠበቀዉ ሳይሆን ቀረና-የግመሏ ተከታዮች ትንሽ ሳይቆዩ “ሶሊዳሪቲ ትግራይ” የሚባል ድርጅት መሰረቱ፡ እርስ በርስ ተናከሱና ተበታተኑ። ችግራቸዉን ላለማወቅ ለብተናዉ ምክንያት በመለስና በስብሓት ነጋ ካድሬዎች አሳብበዉ ተበታተኑ፡ የጎሳ በሽታ ል ዕድሜ ደርሶ ሲጓዝ ሀገራዊ ራዕይ ስለሚያጥረዉ ይበተናል። ሲበተን ሁሉም አባሎቹ ኩፉኛ ይደናገጣሉ::ዙርያዉ ሁሉ ጠላት ስለሚመስላቸዉ የፈረሰዉ ለመጠገን እንደገና ይጥራሉ::በዉጭ አገር የትግራይ ተወላጆችም ሆነ በዉስጥ አገር የትግራይ ተወላጆች ዘንድ እየሆነ ያለዉ ትዕይንት ይኼዉ እንደገና አሁንም መልሶ መላልሶ በጎሳ የመሰባሰብ በሽታቸዉ እያገረሸባቸዉ ነዉ። ዛሬም ተምልሰዉ በወያኔ ትግራይ በእነ ገብሩ አስራት ትዝታ ተጠልፈዉ “በዓረና ትግራይ” ለዳግም ግንጠላ ይሁን ኩርፍያ ለብቻቸዉ እንዲጓዙ መንገዱን መልሰዉ እየገነቡት ነዉ:: ይኼ ሞኝነት ይሉታል አንዳንዶቹ፡ እኔ የምለዉ በሽታ ነዉ፡ ጎሰኝነት በጣም ሃይለኛ በሽታ ነዉ ። ከዛ ገትፍፍግ ብሎ መወያየጡ “ኣጆኻ! ኣጆኻ!” ወገንተኝነቱ የተከናነቡበት ብርድልብስ ወርዉሮ መነሳቱ ለአደጋ የሚያጋለጡ ስለሚመስላቸዉ በጎሳ ጠረን ያደፈዉ ብርድልብስ ከገላቸዉ ገፍፍዉ መጣል “ሞት”መስሎ ይታያቸዋል። ከነ ገብሩ እና ከነ አረጋሽ ከነ አዉዓሎም ወልዱ ከነ ስየ አብርሃ ሌላ መለስ ዜናዊን የሚጥል ከቶ ሌላ ሃይል የለም ባዮች ናቸዉ። ታጥቦ ጭቃ ! ባለፈዉ ዓመት በተከታታይ በገንዘባቸዉ አዋጥተዉ እነ ገብሩን አሜሪካ ድረስ እያስመጡ መለስ ዜናዊን ይጥሉታል እያሉ የሚሞኙ ሰዎች አዳዲስ የትግራይ ተወላጆች ሳይሆኑ ያዉ የቆዩት የወያኔ ደጋፊዎች ወይንም በሶሊዳሪቱ (ሁሉም ማለት ሳይሆን)ተደራጅተዉ የቆዩና ወያኔ ሲሰነጠቅ የነገብሩ የነመለስ ደህንነት በእጅጉ ያሳሰባቸዉ፣ ወደ ስልጣናቸዉ እንዲመለሱ ሲሟገቱ የነበሩት ሁላችንም በሚዲያም በአካልም በግልም ያየናቸዉና የምናዉቃቸዉ ናቸዉ:: በጥቅሉ “መሪዎቻችን” ብለዉ ሕዝባዊ ግምባር! ወያኔ ትግራይ! ሲሉ የነበሩ የእነሱ ባንዴራ አዉለብላቢዎችና እስክስታ አዉራጆች/የሚዲያ አገልጋዮቻቸዉ ዛሬም 95 ከመቶዉ ከተወልደና ከመለስ የወያኔ ድርጅት ወጥተዉ ወደ ገብሩና አረጋሽ አዉዓሎም ወደ “ዓረና ወያነ”ገብተዋል። እነማን ናቸዉ ብሎ ለሚጠይቅ የሺዎቹን ተከታዮች ስም ዝርዝር መጥቀሱ ስለሚከብድ ሲሰነጠቁ ሲጮሁላቸዉ የነበሩት ታሪክ ራሱን ይደግማልና ዛሬም ራሳቸዉን በጨዋታቸዉ ለማጫወት ዝግጅታቸዉ በግልጽ እያየነዉ ነዉና ወደ “ትዝታችንና ትዝታቸዉ”ማሕደር ልዉሰዳችሁና አቁዋማቸዉና ለወያኔ መሪዎች የነበራቸዉን ፍቅርና ያ ትዝታ ዛሬም በከፋ መልኩ እንዴት ሕያዉ እያደረጉት እንዳሉ ከማሕደራቸዉ ላስደምየጣችሁ። ወያኔዎች ለሁለት ሲሰነጠቁ የተሰማቸወዉ ድንጋጤ የስሰሙት እሮሮ እና ስሞታ ለዚህ ሳምንት በትግራይ ተወላጆች ስንጀምር ፡ በሚቀጥለዉ ሳምንት ደግሞ ሰፊዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስሰማዉ የደስታ መልክትና ጽሑፍ ፈንጠዚያና ጸሎት በሚቀጥለዉ እትም ይቀርባል። ልዩታቸዉንም አንመለከታለን፤፡ ዛሬም ለነገብሩና ለነ ስየ በፍቅር የመንገብገቡ ቁርሾዉ መቸ አንደጀመረ ማሕደራችን የመዘገበዉን ታሪክ እንመልከት ከሰባት ዓመት በፊት የቪኦኤዋ አዳነች ፍስሃየ የሚቀጠለዉ ዘገባ አቅርባ ነበር_ “ከዚህ ከዋሽንግተን ከቨርጂኒያ ከሜሪላንድ ከኒዉዮርክ ከቦስቶን ከፍላደልፊያና ከአትላንታ የተወከሉ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ ስለሁኔታዉ ከተወያዩ በሗላ አንድ “ኮሚቴ” መመስረታቸዉን፣የኮሚቴዉ አባል የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ገልጿል ። ኮሚቴዉ የተመሰረተዉም የሕዝቡን ድንጋጤና ስሜት ለኢትዮያ መንግሥትና ለሕዝባዊ እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆዩ ድርጅቶች ለትግራዩና ላጠቃላዩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስተላለፍ ነዉ ሲሉ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ አስተላልፈዋል። አስራ አንዶቹ አንጋፋ የህወሓት አባላት የተወገዱት በሕገወጥ መንገድ ነዉ ይላሉ። ይህንን መሰረት በማድረግም የሚከተሉትን ዉሳኔዎች በማብራራት አቶ ሙሉጌታ እንዲህ ይላሉ፦ “በመጀመርያ እነዚህ አስራሁለት የማአከላዊ ኮሚቴ አባላት በተለይም በቅርቡ ማለትም ከሻዕብያ ጋር የተደረገዉ ጦርነት…ጀግንነታቸዉ ያስመሰከሩ፣ አገር ወዳድነታቸዉ…በግልጽ ያሳዩ ከመሆናቸዉም በላይ፣ አሁን ታግደዉ ,ከስራ ተባርረዋል። ስለዚህ ሕይወታቸዉ አደጋ ላይ የወደቀ ይመስላል። ችግር ብያጋጥማቸዉ አንድ ነገር ይፈጠራል ብለንም እናምናለን። ችግር ቢገጥማቸዉ ያባረራቸዉ መንግሥት ተጠያቂ እንደሚሆን፡ ከዚያ ቀጥሎ ያስተላለፍነዉ ዉሳኔ ምንድነዉ፦ እነዚህ የተባረሩ አስራሁለቱ ሰዎች ያለ ቅድመ ሁኔታዎች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ፦
ሦስተኛ በድርጅቱ ሕግና በሌሎችም ተጓዳኝ ሕጎች መሰረት የህወሓት ቁጥጥር ኮሚቴ ባሳለፈዉ መሰረት አስቸኳይ ጉባኤ ተጠርቶ ጉዳያቸዉ በጉባኤ እንዲታይ፡-
አራተኛ፦ ጉባኤ አስኪጠራ ድረስ ነጻ ሚድያ እንዲፈቀድላቸዉ፡
አምስተኛ፦አሁን በስልጣን ላይ ያለዉ ክፍል በነዚህ ሰዎች ላይ የሚያካሂደዉ ፕሮፖጋንዳ ስም በማጥፋት፣ በራሳቸወና በቤተሰቦቻቸዉ ላይ ቀጣይ የማባረር እርምጃ ..ባስቸኳይ እንዲያቆም፡
ስድስተኛዉ ዉሳኔ ደግሞ፦ ከኤርትራ ጋር የሚደረገዉ ድርድር በታገዱት በሰላማዊ የቲ-ፒ-ኤል-ኤፍ አባላች ተሳታፊነት መካሄድ ሲገባ አሁን ግን አስራ-ስምነት ብቻ ስለቀሩ ባስራ ስምንቱ ብቻ 2/3ኛ ድምፅ ሳይኖራቸዉ ማለት ነዉ፡ በነሱ ብቻ የሚደረግ ድርድር ተቀባይነት ሊኖረዉ ስለማይችል ድርድሩ ባስቸኳይ እንዲያቆም ነዉ።”” (አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ) ካሉ በሗላ ትላለች አዳነች ፈስሃየ “የትግራይ ክፍል ሀገር ተወላጆችን ወክለዉ የተናገሩተር አቶ ሙሉጌታ በመቀጠል “የህወሓት ካድሬዎችና በተለይም የመከላከያ ሠራዊቱ አገሪቱን ከዚህ ቀዉስ በሰላም እንድትወጣ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸዉ ሳያሳስቡ አላለፉም። ሌሎቹም የኢሕአዴግ አባሎች ያስታራቂነት ሚና እንዲጫወቱ የትግራይ ተወላጆች መጠየቃቸዉ ገልፀዋል።”” አሜሪካ የኢንዲያና ክፍለሃገር አቶ ሃይለማርያም አበበ ደግሞ ከ70 አባላት የሆኑ ኢትዮጵያዊያን አባላት ወክለዉ ተናግረዋል። አቶ ሃይለማርያም አበበ Ethiopian Commentator”የተባለ መጽሄት አዘጋጅ ሲሆኑ በሙያ “Micro Biologist” ናቸዉ። “በዚህ መጽሄት ዙርያ የተሰባሰቡት ሰዎች ባለሞያዎች ሲሆኑ ቡዱኑ የፖለቲካ ስብስብ አይደለም: ያለዉን ሁኔታ ኢንፎርመሺን ለሕዝቡ ለማሳወቅ ሲባል ብቻ የተደራጀ ነዉ” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም አበበ አስምረዉበታል። በዚህ ዙርያ በህወሓት የተፈጠረዉ ችግር የቡዱኑ ስሜት አንጸባርቀዋል።
“ባሁኑ ጌዜ በኢትዮጵያ የተፈጠረዉ ችግር የኛ ሜምበሮች ተሰባስበን አቋም ወስደናል። ይህም ምንድነዉ የነዚህ አስራሁለቱ በተመለከተ በእዉነቱ የእነ አቶ መለስ ዜናዊ ቡድን የህወሓትን ሕግ ጥሰዉ እንዳገድዋቸዉ ሙሉ በሙሉ እናምናለን። እንዲሁም እዚህ ያሉት የትግራይ ተወላጆች በሙሉ (በእነ አቶ መለስ የተወሰደዉ እርምጃ) መቶ በመቶ ከሕግ ዉጭ መሆኑን ያምናል። እርምጃዉ ከሕግ ዉጭ መሆኑን ያምናል። እኛም እናምናለን፡በዘህ ትልቅ፣ትልቅ ቁጣና ንዴት ተሰምቷቸዋል።ስለዚህ የተባረሩት ሰዎች ወደ ስራቸዉ ባስቸኳይ እንዲመለሱ በብዙ ከተሞች የሚኖሩ ትግራይ ተወላጆች ለአቶ መለስ ዜናዊ የቅሬታ ደብዳቤ አስተላልፈዋል፡ ለዚህ አስካሁን ድረስ የተሰጠ ምላሽ የለም ። በጣም በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነዉ።”” አዳነች ፍስሃየ ትቀጥልና “አቶ ሃይለማርያም አበበ አያይዘዉም “በህወሓት ሕግ መሰረት የትግራይ ምክር ቤት መሰብሰብ የሚችለዉ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ገብሩ አስራት ናቸዉ:: አሁን ግን የትግራይ ምክርቤት ባቶ መለስ ተጽዕኖ ራሱ ስበሰባ ጠርቶ ፕረዚዳንቱን ማዉረዱ ራሱ ተገቢ አይደለም። ካሉ በሗላ “ዲሞክረሲን በመርገጥ ዲሞክራሲን ማምጣት አይቻልም” ብለዋል።..በመጨረሻም አቶ ሃይለማርያም “ዉጭ ያለን ኢትዮጵያዊያን አገራችን አደጋ ላይ ወድቃለች የሚል እምነት ስላለን ሕዝቡ ያልተበረዘና ተገቢ የሆነ ኢንፎርመሺን ለማግኘት የራዲዮ ስርጭት ለመክፈት እየተዘጋጀን ነዉ ብለዋል:” : ስትል የቪኦኤዋ አዳነች ፍስሃየ የህወሓትን መሰንጠቅ አስመልክቶ ከመቀሌ እና ከዉጭ የሚኖሩ የትግራይ ክፍልሃገር ተወላጆች የተጠናቀረዉን ዘገባ እላይ የተዘገበዉ ዓይነት ለነገብሩ የድጋፍና የደህንነት መቆርቆር ስሜት ለዛሬዉ የዓረና የፍቅር እርሾ መነሻዉ ያኔ ያስተላለፏቸዉ ዉሳኔዎች እንደነበሩ ልብ ልንለዉ ይገባል። በነገራችን ላይ ሃይለማርያም አበበ አዳነች አንደገለጸችዉ በሙያ Micro Biologist ሲሆን ደጀን ራዲዮ ተብሎ የሚታወቀዉ ራዲዮ አዘጋጅ የነበረ ነዉ። አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ደግሞ ድሮ መቀሌ በድረጉ ጊዜ የምርት-ካድሬ የነበረ እና ባሁኑ ሰዓት የሕግ ጠበቃ ባለሙያ ነዉ:: እንግዲህ እንዲህ ካልን ዘንዳ ያ ሁሉ ልቅሶና “አገር አደጋ ላይ ወድቃለች” እሮሮአቸዉ ለእነ ገብሩ ታዝኖላቸዉ እንደሆነ የምናዉቀዉ እንጂ አገር አደጋ ላይ የወደቀችዉ ሲሰነጠቁ ሳይሆን አገሪቱ በተቆጣጠሩዋት ወቅት እንደነበር ደጋግመን በጮህንበት ወቅት የነበረ ቢሆንም “ጨኸን ጮኸን እንዳልጮኽን ሆንን” ያለዉ ቅዱሱ መጽሐፍ ሆኖ ባስገራሚ ሁኔታ አገሪቱን ለአደጋ የጋረጥዋት ጋሬጣዎች “ሲቧጨቁ” ከዉጭ ሆነዉ “አገር ምድሩ አዳጋ ላይ ወደቀ” ብሎ መጮች ታሪክ የማይረሳዉ ማሕደር ቢሆንም:- ፍጹም ሰዉ የለምና ከስሕተት ተምሮ ስሕተትን አርሞ እንደገና ለቀና መንፈስ ተነሳስቶ ጋሬጣዎቹ በሓላፊነት ከመጠየቅ ይልቅ ዛሬም እነ ገብሩን ስልጣን ላይ ለማስቀመጥ ከ7 ዓመት በፊት በጉባኤ ያስተላለፉት ላለመፋታት ዉሳኔ እዉን ለማድረግ ቃል ኪዳን ገብተዉ ነበርና ያነኑ እዉን ለማድረግ ተከታታይ ቴሌ ኮንፈረንሶች በደብቅም በግልጽም ይጧጧፋል። በግሌ እንኚህ ሰዎች ያልተባበረ ሕብረታቸዉ አስተባብሬ ሁላችንም በኢትዮጵያዊነት መስመር እንጂ በብሔረሰብ ሰልፍ ተሰልፎ አላስፈላጊ መበታተንና የዘር መጎነታተል እንደቆየዉ 33 ዓመት እንዳይቀጥል የተቻለኝን ያህል ለማድረግ በየስቴቱ በስልከም በኢሜይልም በማነጋጋር ሞክሬ አልሆን ብሎኝ በትዝብት ትቼአቸዉ ዛሬም ያንኑ አንቀጽ 39 አስከ “መገንጠል” የነገብሩ የወያነ ትግራይ የፍቅር ትዝታ አልለቅ ብሏቸዉ “እምቢ ካላችሁ እንገነጠላለን” ከሚሉን ከነ ገብሩ ከነ ሰዉ በላዉ አዉዓሎም (ዲያብሎስ ይሉታል በቅጽል ስሙ የህወሓት አስረኞች} ከነ አረጋሽ አዳነ ( ዲያቆን ገብረሕይወትን በአረመኔዉ “ወዲ-ሻምበል” መቀሌ ጽ/ቤቷ ስር አንደር ግራዉንድ አስገብታ ያስመረመረቺዉ) እያወዳደሱ ለነሱ መከላከሉ ቀጥለዉበታል። ታሪክ ነዉና እኛም የመጨረሻ ትግሉ ከነማን እንደሚሆን በታሪክ ዓይን በጎሪጥ እየተከታተለነዉ እንገኛለን። ኢትዮጵያዊነት ለ33 ዓመት ጎልብቶ ከታሰረበት ኬላ እየሰበረ በመዉጣት አሸናፊነቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደመቀ መጥቷል፡ ብሄረተኞች ከጎሳቸዉ እና ለጎሳቸዉ አስከመገንጠል ሲያቅዱ እኛም የጊዜ ጉዳይ እንጂ “ኢትዮጵያዊነት” የመጨረሻዋ ተራራ በመዝለቅ ያሸናፊነቱን የችቦ መብራት ይዞ በታሪክ ፊት በከራት ይቆማል! ጌታቸዉ ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com