Tuesday, February 9, 2010

ቆሽቴያቸዉ እያረረ ለሕዝብ ሲሉ በፈገገግታ ጥራሰቸዉን የሚያብለጨልጩ ፖለቲከኞች እንፈልግ

ቆሽቴያቸዉ እያረረ ለሕዝብ ሲሉ በፈገገግታ ጥራሰቸዉን የሚያብለጨልጩ ፖለቲከኞች እንፈል

ለፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ድጋፍ

ከጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com

ቀኑ ሳይመሽ ብርሃኑ ሳይሸሽ በሚል ርዕስ ክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ተቃዋሚዎች በሕዝብ ድምጽ ተደግፈዉ የሚቃወሙትን የወያኔ ትግሬዎች መንግሥት ለማሸነፍ ከፈለጉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድርጅት በተለይም ደግሞ በመድረክ እና በመኢአድ ፓለቲከኞች መሃል እርቅ በማዉረድ የጋራ ስምምነት በመቅረጽ የገቡበት የሰላማዊ ትግል ዉጤታማና በሳላ ፖለቲካ እንዲሆን ከፈለጉ ሕብረት ቢፈጥሩ ጥሩ መልካም ጅማሮ እና ሕዝቡም ለትግሉ የጋራ አትኩሮት እንዲኖረዉ ይረዳል፤ በሚል ለሕብርት ስራ የጠሩትን የአርቆ አሳቢ ጥሪ አንዳንዶቹ ከድንቁርና ወይንም ለፕሮፌሰሩ አልያም ለየደድርጅቶቹ ካላቸዉ ጥላቻ የተነሳ ፣አፍራሽ የሆኑ መልሶች በተለይም በፕሮፌሰሩ ላይ የግል ጥላቻን የሚያንጸባርቁ ከኢትዮጵያዊነት ስነምግባር ዉጪ የዘለፋ ቃላት የሰነዘሩ ግለሰቦች ካነበብኩ በሗላ እንደዚህ ዓይነት ሃገራዊ ጥሪ በቸልተኝነት የሚያዩ ሰዎች ስለ ፕሮፌሰሩ እንጂ ስለ አስተላለፉት ቁም ነገር/መልእክት/ጥሪ አትኩሮት እንዳልሆነ መገንዘብ ችያለሁ፡፡ ሕዝብ እናክብር እያሉ የሚዘላብዱትም ዉሸታቸዉ መሆኑን አመላካች ነዉ።

ፕሮፌሰሩ ስለ እርቅ ስለ የጋራ ጉዳይ በጋራ አዋድዶ/አቀናጅቶ መስራት ተገቢነት እንዲኖረን ጥሪ ሲያስተላልፉ እስካሁን ድረስ የፕሮፌሰሩን ሃሳብ የተቃወሙ ሰዎች ያነበብኩት በሳላ ሳይሆን የቅንጅት አመራሮች ወደ ዲያስጶራ ለጉብኝት (?) ሲመጡ፣ፕሮፌሰሩ ስለ የቅንጅት አመራሮች አቀባበል በሰነዘሩት የግል አመለካከታቸዉ በመነሳት ያኔ የኔን ወገን አልደገፍም እና ዛሬ የኔን ወገን እና እሳቸዉ የደገፉትን ወገን ሰላም መመርያቸዉ አድርገዉ ይወያዩ፣የጋራ ትግል ይመስርቱ፣ ተቀናጅተዉ ለግል ይብቁ የሚሉትን መልከታቸዉ አልደግፈዉም ከሚል ደካማ አቋም ነዉ በብዛት ያነበብኩት:: የፕሮፌሰሩ የያኔ አመለካከት አሁን ካስተላለፉት ምክር በመልክ ቢለያይም በይዘቱ አንድነትን የሚጠይቅ እና የጋራ አሰራርን መመርያ ለምን አላደረጋሁም የሚል ነበር ቅሬታቸዉ ። በስሜት ለሚጋልቡ ዜጎች ለሕሊናቸዉ መዳበርያ ቢረዳ በወቅቱ ፕሮፌሰሩ የነበራቸዉ መልእክት ምን እንዳስተላለፉ ልጥቀስ፡-

( የቅንጅት አመራሮች አቀባበል )

ጌታቸዉ ሃይሌ

“ ቅንጅት በምርጫ ማሸነፍ የሕዝብ መብት ስለተነጠቀ ማኩረፍ እንደ ወንጀል ተቆጥሮበት መሪዎች በሺ የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸዉ ከዓመት በላይ ከተራ ወንጀልኞች ጋር ታስረዉ እንደነበር የሚረሳ አይደለም።……. የመሪዎች መፈታት በተሰማ ጊዜ ለፍትሕ የቆመ ሁሉ ተቃወሚም ሆነ ደጋፊ ደስ ብሎት ነበር። በዚያ ላይ መሪዎቹ ደጋፊዎቻቸዉን ሊገናኙ ወደ አዉሮፓና ወደ አሜሪካ ይመጣሉ ሲባል፣ጀግና ካየን ብዙ ጊዜያችን የሆነዉን ሁሉ ደስታችንን ለመቆጣጠር አቅማችን አልቻለም ነበር። የፈለግነዉ ዓይናቸዉን ማየት ድምፃቸዉን መስማት ብቻ ሳይሆን በደጋፊዎቻቸዉ ማሀል የገባዉን ሰይጣን በአንድነት ሃይላቸዉ እንዲደቁሱት ጭምር ነበር። ይህ ተስፋ ሊፈጸም እንደሚቻል አሁንም ብናምንም እስካሁን አልሆነም፡ የይሆናል ምልክትም ወለል ብሎ አይታይም። ሆኖም ተስፋ አንቆርጥም። መሪዎቹ በፊት በእስር ቤት ባሉበት ጊዜ እነሱ ያቀረቡት የአስታራቂ ሐሳብ ነዉ እየተባለ በተከታታይ ይምጣ የነበረዉ መልክት የተቀደመዉን እየሻረ ተቸግረን ነበር። በሗላ አስታራቂ ልኡካን መጡልን። እነሱም ዕርቅ ሊያመጡ አልቻሉም፡፡

በዚህ ጊዜ አመራሩ ግልጽ የሆነ ስሕተት አድርጓል፤ የአለመግባባቱ መንሥኤዉ አመራሩ በደጋፊዎቹ ላይ መሪዎቹ ስለሾመባቸዉ መሆኑን ለጊዜዉ ልተወዉና፤ እነዚህ ያልተግባቡት የዲያስጰራዉ ደጋፊዎቻቸዉ በቡድን ተከፋፍለዉ ሁሉም የሚፈልጉትን ካላገኙ ለመታረቅ የማይፈልጉ መሆናቸዉን ሲያዩ ቁርጥ ሐሳብ አቅርበዉ በዚያ በመጽናት ፈንታ ያለፈዉን የሚሽር አዲስ ሓሰብ አዲስ ቡድን በመፍጠሩ ቀጠሉበት። ከስሕተትም ስሕተት የሆነዉ ልኡካኑ ያቀረቡት አስታራቂ ቡድንና እራሳቸዉ ልኡካኑ እዚህ እያሉ ገለልተኛ ተቀባይና ያስተናጋጅ ቡድን እነ እገሌን አድርገናል አሉ። ይኸ ራሳቸዉ የላኳቸዉን ልኡካን ገለልተኝነት መካድ ነዉ።በወያኔ እሳት ተፈትኖ ያለፈዉን ዶክር ታየ ወልደ ሰማያትን ከጋበዙት በሗላ ገልለተኝነቱን መካድ ነዉ። ዶክተር ታየ ገለልተኛ ካልሆነ ያየዉን ቢያይ ነዉ እንጂ፣ ወያኔዎች እንደ እንጂኔር ሃሉ ሻዉል እንደ ጠላታቸዉ እንደሚያደርጉት አልጠራጠርም። ጠላት ያደረጉት ለኢትዬጵያ መታገሉን ማን ይክዳል!

የዚህ የማያወላዉል ዉጤት ምንድን ሊሆን ይችላል? የቆጡ አወርድ ብላ የብብቷን ጣለችዉ ኢንደሚባለዉ፤ ማለት ለአስተናጋጅነትን የድጋፍ አስተባባሪዎችን አላስተዋወቋቸዉም፤ አላገናኟቸዉም። የቅንጅት ሊቀ መንበር ዋሽንግተን ሲገባ ሊቀበል አልመጣ ከሁሉም ያስደነገጠን ቀደም ብለዉ የመጡ ክብርትና ክቡራን የቅንጂት አመራሮች ሊቀ መንበራቸዉ ክቡር አቶ ሃይሉ ሻዉል ዋሽንግተን ሲገባ ዋሽንግተን እያሉ አልተቀበሉትም።ከብዙ ጭንቅ በሗላ በዉጭ ሀገር ሲገናኙ እንኳን የትግል ጓደኞች የቆሎ ጓደኞችም ይነፋፈቃሉ። ጌጣቸዉ፤ክብራቸዉ፤ድላቸዉ፤ለኢትዬጵያ ሕዝብ ጌጡ፤ክብሩ፤ድሉ አንድነታቸዉን ነፋስ በማያስገባ ሁኔታ ሲያጠብቁ መሆኑ የታወቀ፤ሁሉንም አንድነት ቆመዉ ሊያያቸዉ የፈለገዉን ያንን ሁሉ ተቀባይ ህዝብ አሳቀቁት። ፖለቲከኞች እንኳን እንደዚህ ያለ ሚያስደስት ነገር አግኝተዉ በዉስጣቸዉ ቁሽቴያቸዉ እያረረ ለሕዝብ ሲሉ በፈገግታ ጥርሳቸዉን ያብለጨልጫሉ።

ሕዝብ የቅንጅትን መሪዎች የሚያዉቃቸዉ እንደ ራስ አበበ አረጋይ እንደ በላይ ዘለቀ ለኢትየጵያ በቀዉጢ ቀኗ የደረሰላት አድርጎ ነዉ። ለሀገራችን የደረሱላት ሀገራችንን ክቡር እንዲያጎናጽፏት ሲሆን ሕዝብ በበኩሉ ክብር ያጎናጽፋቸዋል፤ አንዱ መጎናጸፍያ ከቀረ ሌላዉም ይቅርና ዕርቃነ ሥጋችንን እንቆማለን። ሕብረታቸዉን ሳያሳዩን ሲቀሩ የስጋት ስሜት ደቁሱናል፣ ባዶነት ይሰማናል። አያድርስ ነዉ እንጂ ተከፋሉ የሚባል ወሬ ቢነፍስ ከምን እንገባለን? ለወያኔ በምርጫ ያልተፈታንለት በወሬ ልንፈታለት ነዉ እኮ? የሚነፍሰዉን ወሬ ለማሸነፍ እንሞክራለን፤ግን የምናሸንፈዉ ሥራቸዉን ሃይል አድርገን ነዉ።

በዉጭ ሀገር ያሉ የቅንጅት ደጋፊዎች ምንም ቢከፋፈሉ በቅንጅት መሪዎች እና በዶክተር ታየ ላይ መጥፎ ነገር ከአፋቸዉ ወጣል ብየ አልገምትም ነበር። አሁንም ቢሆን የምሰማዉን ፕሮፖጋንዳ የሚያናፍሱት ወያኔዎቹ እንጂ የቅንጅት ደጋፊዎች አይመስለኝም። የቅንጅት ደጋፊዎች ነን የሚሉት ከሆነም ከወያኔ አንለያቸዉም።

የቅንጅት ጥብቅ ምኞታቸዉ ከሆነ ዉስጥ አንዳንዶቹ የዓመቱን መለወጥ ምክንያት በማድርግ ፤ለመአእድና ለቅንጅት ገንዘብ ስሰበስብ ያደረግሁትን ጥረት እያስታወስሱ፤ገንዘቡ መዘረፉን አምነዉ ሊያስተዛዝኑኝ የሞከሩ ነበሩባቸዉ። የስም ማጥፋቱ መስፋፋት በበዛብኝ፤ አንዱን እንዲህ ብየ ጠየቅሁት ‘ቅር አይበልህ እና አንድ ጥያቄ ልይቅህ፣ እዉነቱን አትደብቀኝ፣ ከተዘረፈዉ የቅንጅት ገንዘ አብዛኛዉ የተደበቀዉ በአንተ የባንክ አካዉንት ነዉ የሚባለዉ እዉነት ነዉ ወይ? ሲደነግጥ የፕሮፖጋንዳ ሃይል እንዴት እንደሆነ የፈለግሁትን ለመንገር ተመቸኝ።

ለቅንጅት ከተሰበሰበዉ ገንዘብ አለግ አንዲት ሳንቲም አልወጣም፤ስም አጥፊዎችን አትመኑ፤ እነሱን በመን ቅንጅታችሁን አትጉ፡፤ ገንዘብ ቢጠፋ እኔ ከከሳቹ አንዱ እኔ እሆን ነበር፣ብጠረጥር እንኳን ይመርመር እል ነበር። አለመጥፋቱን ያመንኩት መዝገብ አይቼና መርምሬ ሳይሆን ከስም አጥፊዎቹ ዉስ የገንዘብ መዝገብ ኦዲት አለመደረጉን በማስረጃ ያሳየን ማንም እንደሌለ ስለማዉቅ ነዉ። እርግጥ መከፋፈል በመጣ ጊዜ ሁሉም በየበኩሉ ገንዘቡን ለመቆጣጠር ተሽቀዳድሟል።እንደ ሰማሁት የሎስ አንጀለስ ገንዘብ አንዱን ክፍል ሲቆጣጠር የላስ ቬጋሱን ሌላዉ ክፍል ተቆጣጥሮታል። የሎስ አንጀለስ ተሰረቀ ብሎ የላስ ቬጋሱን አልተሰረቀም ማለት አይቻልም። እን እዉነቱ ከሆነ ግን የሎስ አንጀለሱም የላስ ቬጋሱም ገንዘብ አልተሰረቀም። አንዱ ከምሥራቅ፣ አንዱ ከምዕራብ ሆነዉ እየተቀባበሉ የተከበረዉን የ ኢትየየጵያዊ ስም የሚያጠፉ በዴሞክራሲና በፍትሕ አያምኑም፣ የኢትየየጵያን ሕዝብም አያከብሩም። አለሁ፤እናከብራለሁ ሲሉ ልናምናቸዉ አይገባም።

ከሁሉም የሚያሳዝነዉ የቅንጅትን ሊቀ መንበር የገንዘብ ዘራፊዎች ደጋፊ ለማድረግ የሚደረገዉ ሙከራ ነዉ። ጀግና ለማሳጣት የሚደረገዉን ሙከራ ሀገር ወገን ወዳድ ሁሉ እዲቃወም በትሕትና በጥብቅ አሳስባለሁ።”

ይኸ ነበር በወቅቱ አስደናቂ እና በክብር መዝገብ ተመዝግቦ ለታሪክ መከራከያ መጠበቅ ያለበት የተከበረ አመለካከት የሰነዘሩት። በዛች መልዕክታቸዉ ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች አንዲትም ዓረፍተ ነገር ወደ ቆሻሻ የምትጣል ወይንም በንቀት የምትጣል ወይንም በዉሸት የተሰነዘረ አባባል ማግኘት አይቻልም። የተጠቀሰዉ አመለካከታቸዉ በኢንተርኔት ከተለጠፈ ቀን እና ዓመተ ምሕረት ጀምሮ አስካሁን ድረስ ነጥብ በነጥብ አቅርቦ ያጣጣለዉ ወይንም ዉድቅ ያደረገ ተቃራኒ ጽሁፍ ፈልጌ አላገኘሁም። ጉዳዩ እከታተለዉ ስለነበር እመኑኝ። ፕሮፌሰሩ ያቀረቡት በሃቅ የተመረኮዘ አስተያየት ከሌለዉ ወገን በተቃራኒ ቀርቦ አመለካከታቸዉን ያሸነፈ የለም። ህ ታሪከ በመሆኑ ያኔም ትናነትም ዛሬም ለወደፊቱም የሚመክት ሰዉ እንደሌለ በእርግጠኝነት ለነገር እችላለሁ። ያኔ ሲናፈስ የነበረዉ ዉዥምብር እጅግ አሳፋሪ እና ጮርቃ አስተሳሰብ የበዛበት በስሜት የሚጋልብ መያዣ የታጣበት አልባ ፕሮፓጋንዳ እና ሙግት በመኖሩ ይኸዉ ለዚህ ለዛሬዉ ፍርክስክስ አድርሶናል። ያኔ ቅንጅት ተበጥብጦ ሲከፈል ፤ክፍፍሉ በዛ አላበቃም፤ በብርሃኑ እና በብርቱካን መሃል፤ በኢንጂኔር ግዛቸዉ እና በፕሮፌሰር መስፍን መሃል አስገራሚ የሆነ ልዩነት ተፈጥሮ ተለያይተዉ አንዳንዱ ድብድብ ጸብ ዉስጥ ገብተዉ አሳፋሪ ተዉኔት ዉስጥ ገብተዉ እናያቸዋለን።

ዛሬ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ በተቃዋሚመ መሃል ዕርቅ ይዉረድ ማለታቸዉ እንደ ጉድ የሚያዩ አሳፋሪ ጉደኞች ማየት ፖለቲካዉ ምን ያህል እንደዘቀጠ አመላካች መንገድ ሆኖናል። እዉነቱን ልንገራችሁ፤- እኔ ስለ ብርቱካን ጮርቃ አስተሳስብ ብዙ ማለት በቻልኩ ግን አንዳንዶቹ አርበኛቸዉ ስለሆነች እሷንም ሆነ እነሱ ላለማስቀየም ያለ አግባብ ከታሰረችበት አስክትወጣ ድረስ መጠበቁ እና ሽንፈቷን ጮርቃ አስተሳሰቧን ወደ ሗላ መተቸበመመምረጥ ተቃዋሚዉ ይህ ዉረደት እና ድክመት እንዴት እና በማን ምክንያት እዚህ ደረጃ ሊደርስ እንደቻለ እሷንም ጨምሮ ላለመተቸት ለበጎ ቀን አቆይቸዋለሁ/አቆይተነዋል። የታሰረ ሰዉ መተቸት በሃገራችን የተለመደ ስላልሆነ መታገሱ ጥሩ ነዉ በሚል።

ይህ ሁሉ ሸክም ተሸክመን ዛሬ ፕሮፌሰሩ በቀና ሀገራዊ ተቆርቋሪነት ተነሳስተዉ እርቅ ይወረድ ቢሉ ይደገፋል እንጂ ለምን ተብሎ ስድብ ይጠብቃቸዋል? ድሮ ተችተዉናል የሚሉ ሰዎች ካሉ እና እንዳሉም ስላለነብበኩኝ የኸዉና እሳቸዉ በቅንጅት የመጀመርያ ንትርክ ምን እንደታዘቡ ለታሪክ ያስቀመትኩትን ጽሁፋቸዉ አቅርቤአለሁ። የሰዉ ክብር እና ስም በከንቱ ከማጥላላት ልቅ ከዚህ በመነሳት እኔ አሞግታለሁ የሚል ካለ በስሜት ከመፈንጨት እና ጮርቃ ግልብ ከመጋለብ ይኸዉ ሜዳዉ ይኸዉ ፈረሱና አለንጋዉ እሳቸዉ ባቀረቡት የድሮ ጽዩፋቸዉ ልተች የሚል ካለ ጋብዣለሁ። ግን እርግጠኛ ነኝ ነጥብ በነጥብ ያቀረቡት የዛሬም ሆነ የድሮ አሳባቸዉን ከድሮ የቅንጅት አመራርም ሆነ ( የዛሬዎቹ ግንቦት 7 ይሁን ከመድረክ አመራሮች ) እና አባሎች በብቃት የሚሞግት የለም። (ወያኔዎች እና አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ፕሮፌሰሩ ትግራይን ይጠላሉ ሲሉ እሳቸዉ በጻፉት/ባስተላለፉት መልእክት አንዲትም ነጥብ በጸረ ትግሬነት ያጋለጠ የትግራኢ ሕዝብ ተወካይ/ተቆርቋሪ አፈኛ ጠበቃ ነኝ የሚል አንድም ሰዉ እስካሁን ማግኘት አልቻልኩም። ሁሉም ያነበብኳቸዉ መልሶች በራሳቸዉ እንደሚመቻቸዉ የሚተረጎሟቸዉ ትርጎሞች እና በዉሸት እንደሚዘላብዱት እንጂ በነጥብ እየጠቀሱ አላቀረቡልንም። ልክ ብርቱካን መዲቅሳ መኔሶታ/አሜሪካ ሆና ስለ በድሪ አደም (የወያኔ ፍረድ ቤት እንኳ ጸረ ትግሬ ንግግር መልእክት አላስተላለፈም ብሎ በነጻ የለቀቀዉን ጉዳይ) እና ስለቅንጅት ጸረ ትግሬነት ለትግራይ ሕዝብ ይቅርታ በመጠየቅ “በዉሸት እንደዘላበደችዉ” ማለት ነዉ!)።

ይሄንን ስለተቃወምኩ ፤Tigrayan Wanted For CUD! One found Getachew Reda በማለት በማስታወቅያ መልክ ማለትም በካርቱን ኢሳያስ አፅብሃ የተባለዉ የለየለት ዘረኛ እና ጎጠኛ ግለሰብ “በዓይጋ ፎረም” ድረገጹ ላይ የለጠፈዉን ታስታዉሳላችሁ።

ፕሮፌሰር ዶክተር ጌታቸዉ ሃይሌ ብሔራዊ እርቅ አድርጎ ሀገርን ከጥፋት ማዳን አለብን የሚሉትን መልክት መደገፍ ካልሆነም ደግሞ የማይሰራበት ምክንያት በመረጃ አስደግፎ መከራከር ያለ ነዉ ፤ ግን “ስድብ” ለምን ተብሎ? መሪዎቹ ካላወቁበት ዜጎች በዚህ መንገድ ተራመዱ የማለት መብት እኮ ዲሞክራሲ የምትሉት የሚደግፈዉ አንዱ አካል እኮ ነዉ! ይህ መብት ካላወቃችሁ መድረክ የሚባለዉ ድርጅት እንዴት ሲኮን ዲሞክራሲያዊ ነዉ እያላችሁ ሕዝብ እንዲመርጠዉ በደጋፍ ትቆማላችሁ? እስከመቸ ድረስ በስሜት ተጋልቦ ሊደረስ የሚፈለገዉን አድራሻ መድረስ ይቻለናል? የፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ ቀጥተኛ መልእክት እንደገባኝ ከሆነ ቆሽቴያቸዉ እያረረ ለሕዝብ ሲሉ በፈገገግታ ጥራሰቸዉን የሚያብለጨልጩ ፖለቲከኞች እንፈልግ/እናበረታታ” ነዉ። ይኸ ለምን ያስሰድባል? / / ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com