Saturday, April 27, 2024

ለስቃያችን ምክንያት የዲሞክራሲ ዕጦት ወይስ በአገር በቀል ገዢዎች በመገዛታችን? ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 4/27/24

 

ለስቃያችን ምክንያት የዲሞክራሲ ዕጦት ወይስ በአገር በቀል ቅኝ ገዢዎች በመገዛታችን?

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

4/27/24

አገራችን በተወላጅ (Native Colonizers) ቅኝ ገዢዎች አስተዳደር እየማቀቀች እንደሆነች በዙ ጊዜ ገልጫለሁ፡፡ ክስተቱ የጀመረው ብ1983 ዓ.ም (1991)  ሲሆን እነሆ 33 አመት ሆኖታል፡፡ ጨለምተኛው ኢትዮጵያዊ ሁር (አብዛኛው) ይህንን አይስማማበትም፡፡ ይልቁኑ አስተባባይ እና ለገዢዎቻችን አጋዥ ሆኖ የገዢዎቹን ዕድሜ ሲያራዝም ብዙ ጊዜ ቆይቷል።

ብዙዎቹ ደግሞ አሁንም ችግራችን “የዲሞከራሲ ዕጦት ነው” እያሉ ሲከራከሩ ዘመናት አለፏቸዋል፡፡በዚህ 33 አመት አገር በቀል ቅኝ ገዢዎች የፈጠሩት ጦርነት አገራችን ተጎድታለች። ጦርነት ላንድ አገር ‘ገዳይ ነቀርሳ’ ነው። ተገድዶ ሚገባበት የነፃነት አምጪ ጦርነት ደግሞ አዳኝ ነው።

ምሁሩና ደንቆሮው “የተጠመቁ ጦርነቶችና ጠማቂዎቹ” በትክክል ሳያውቁዋቸው “ኢትዮጵያ ጦርነት ወዳጅ ነች” እያሉ መድረክ ላይ ሲከራከሩ እንጂ ከአክሱም ፈጻሜ በኋላ የተከሰቱ ‘’ውጭ በቀል” እና “አገር በቀል’’ ጦርነቶች ለምን ቀጣይ እንደሆኑ በዙ መሁራዊ ትንተና አለተደረገም፡፡

ችግር ላይ የጣለን የማያባራ ጦርነት ነው፡፡አዎ። ግን እኮ ሊቀጥል የቻለበት ምክንያትም ከወጭ አገር የመጡብን ጦርነቶች በቀላሉ ስለተመከቱ “ተሸናፊዎቹ” በአዲስ ሜላ መጥተው  በቅኝታቸው (በስልታቸው) የሚጓዙ አገር ውስጥ ያሉ አገራዊ ስሜት የራቃቸው ዜጎች “የፖለቲካና ፤ የሃይማኖት አደፍራሽ ተቀጣሪ ሁራን (አሊቶች) ዲሞከራሲ በሚባል ማሞኝያ ሽፋን እየተቃኙ አገሪቷ ተመስርታ በቆመቺበት ድር ጥረው የያዝዋት አስተማማኝ መልህቆችዋን ከሥር እንዲፈቱና በጦርነት ማዕበል እንድትንገላታ ተባባሪዎች ሆነው በመገኘታቸው ነው፡፡

የኔን ጽሑፍ ሰታነቡ ለረዢም አመታት የምትከታተሉኝ ካላችሁ በ2002 በፈረንጅ አቆጣጠር (ከሃያ አመት በፊት) በሚከተለው ርዕስ ሰፊ ሐተታ ጽፌ ነበር፤

<< በዲሞከራሲ ለመሞቅ ስንሞክር እያበድን የነፃነት ትርጉም እያጣነው ብቸኛዋን አገር ልናጣት ነው>> ብየ  በጣም ሰፊ ትችት ጽፌ ነበር፡፡ ዲሞከራሲ የቅኝ ገዢነት ስሜት ካደረባቸው መሪዎች የሚቀየስ “የአስተዳደር ስጦታ” አይደለም፤ ይልቁኑ “አገር ለመበተን” የሚጠቀሙበት አታላይ ስልት ነው ብየ ሰከራከር ነበር፡፡ ዲሞክራሲ ስለጠላሁ አይደለም። ግን ጊዜው ያንን የሚያስመኝ ሳይሆን ይልቁኑ ወቅቱ የሕልውናችን ፀር ስለሆነ ነው።

በወቅቱ ያሰራጨሁት ጽሑፉ ‘’ትግሬዎች አገሪቱን ሲገዙዋት በነበሩበት ወቅት’’ ስለነበር ትግሬዎቹ (እኔ ትግሬ መሆኔን አትዘንጉልኝ) “ጽሑፌ ትግሬዎች በበላይነት የመሰረቱት መንግስት በአገር በቀል ቅኝ ገዢነት የተቃኘ ነው’’ የሚል ስለነበር፤ በዙዎቹ የያኔ የድረገጾች ባለቤቶች በድንቁርና ስለተሸበቡ (ወይንም በአጉል እወደድ ባይነት)  በዙዎቹ የኔን ጽሑፍ “በራዲካል/ያልተለመደ ድፍረት/አከራሪ አገር ወዳድ...) በሚል ይፈርጁኝ ስለነበር መጣጥፌን ለመለጠፍ አይፈቀዱልኝም ነበርና ጽሑፉን ለማውቃቸው ስዎች በእጅ ሳከፋፍል ነበር፡፡ እና የተቃዋሚዎች ድረገጾች “ታጋችነበረኩ ማለት የቻላል፡፡ ለዚያ ነበር የራሴን Ethiopian Semay የመሰረትኩት፡፡

ታዲያ አንድ ወዳጄ አጋጣሚ አገኘሁትና <<ጽሑፍህ አልገባኝም፤አልተሰማማሁበትም>> ሲል ጠየቀኝ፡፡ የተገናኘነው ባጋጣሚ ነበረና ከጊዜ አንጻር ለማስረዳት ባልችልም፣ በተቻለ አጠር አድርጌ ባስረዳውም “አገር በቀል ቅኝ ገዢ የሚባል ከየት አገኝው?” አለኝ፡፡ ከየትም ማግኘት አይጠብቅብኝም፡ የሞቅንበትና የኮራንበት የጀግኖች አገር ኢትዮጵያ አካላትዋ ላይ የተውትን ንቅሳት ምልክቶቿ የመቅረፍ ዘመቻ ሲካሄድባት አይታይህም ወይ? ጣሊያን አነጣሮ በጠላትነት ያጠቃቸው ስቱ ነብሳት” (አማራ፤ኦርቶዶክስና ሰንደቅዓላማ) አሁን ዛሬ ያንኑ በትግራይና በኦሮሞ ቲከኞች እየተደገመ አደለም ወይ? አኩት፡፡ <<አልወዳቸውም ግን ትግሬዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሰለሆኑ በዚያ መታየት የለባቸውም>> ብሎኝ በዚሀ ተለያየን፡፡

ያ ሰው ዛሬ ክ22 አመት በኋላ የግል ፌስቡኩን ስመለከት የአብይ አሕመድ “ዋና ደጋፊ” ሆኖ ስታዘብ  የያኔው ንቃ እንዳልተሻሻለ አይቼው ገረመኝ፡፡

ብዙ ያገራችን ሰዎች በዚህ ተላላነት “ዲሞክራሲ እየሰፈነ ነው” ሰበካ ፤ ወይንም ችግራችን “የዲሞከራሲ እጦት ነው” እያሉ የሃገሪቱ መልህቅ ከስር እንዴት እየተፈታ እንዳለ ማየት አልቻሉም። ዲሞክራሲ ጊዜ ይፈጃል ትዕግስት ያስፈልጋል፡ ሲባሉ ለመሰቃየት ፈቃደኞች ሆነው፤ “ያንን እያምኑ” በአጓጉል ትርጉም ተሞኝተው የተጠመደላቸው ሴራ ሳያዩ እራሳቸው ለስደት አገራቸውንም በማትወጣው ረግረግ እንድትገባ አስተዋጽኦ አደረጉ፡፡

የዲሞክራሲ ጥያቄ እያስቀደሙ የህልውና ጥያቄን በማጣጣል ለ27 አመት ሙሉ ቀጣዩ ትውልድ ማንነቱ እንዲያጣ ሲደረግ ምንም አልታይ አላቸው፡፡ አሁን፤ በቅርቡ ብቻ ፋሺሰቱ አብይ አሕመድ ሥልጣን ላይ ሲወጣ “ጥያቄአችን የህልውና ጥያቄ መሆን አለበት ስለው የነበረው ክርክር” ዛሬ ትንሽ እየገባቸው ሲምጣ ወደ ትክክለኛ መስመር መግባት ጀምረዋል።

ያም ሆኖ ታዋቂ የፖለቲካ መሪዎች ከሚታወቁት ውስጥ ልደቱ አያሌው “ችግራችን የዲሞክራሲ ዕጦት ነው” ፓርላማ በመሳተፍ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ከሚሉት ግምባር ቀደም አስቸጋሪ ሰው ነበር። አሁን የሕልውና ጥያቄ ትንሽ የገባው ቢመስልም ተመልሶ በተዘዋዋሪ መንገድ “ለምሳሌ” የፋኖ የብረት ትግል ለሕልውና እንደሆነ ይቀበልና “ጦርነት ዲሞክራሲ አያመጣም” እያለ እንደገና አሰልቺ ወደ ሆነው “ዲሞክራሲና ሰላማዊ ትግል” ሊያሳምን ይሞክራል። ስላማዊ ሰልፉ ውጤት አላመጣም ሲባል “አልተሞረም” ይላል። እሺ እስኪ ግባና ሞክረው ያለው ሰው ግን አልሰማሁም። 

በዚህ 33 አመት ተቃዋሚዎች (አንዳንዱን በቆራጥነት የታገሉ አርበኞችን አይመለከትም) የትግሬው መለስ ዜናዊና የኦሮሞው አብይ አሕመድ አድናቂዎች ሆነውም ሆነ፤ እነዚህ ቅኝ ገዢዎች በሚያሰምሩላቸው የመታገያ አቅጣጫ እየተከተሉ ገዢዎቹን በሰላማዊ መንገድ እንጠላለን እያሉ የነበሩት <<ሕብርተሰቡ ኩፉኛ ሲበከል>> ማየት አልቻሉም። ማሕበረስቡ ባሕሉን ጥሎ በቀላል ተታላይ፤ዘራፊ፤ገዳይ፤ሐሰተኛ፤ስግብግብ፤አገር ጠል፤ ገበርሰዶማዊ፤ ደፋሪ፤ የአህያ፤ የውሻ ፤ የሰው ሥጋ በይና የሰው ደም ጠጪ ሆኖ በአራዊታዊ ባሕ ዕርቃኑ እየተራመደ ነው፡፡ባሳዛኝ ተት ሃይማኖቶች የነዚህ ተጋሪዎች ሆነው “አፍቃሬ ንዋይ” እና “ዝሙተኞች” የሆኑ ሞራል-ቢስ ሰዎች ሚመርዋቸው ተቋማት ሆነው ማየት አልቻሉም፡፡

ይህ ሁሉ ሲፍጸም አማልክቶቿ የት ሄዱ? የሚል ጥያቄ ሳይጭር የሚቀር አይመስለኝም። በዙዎች ላይስማሙ ሆናል፡፡ የዚያች አገር ማህፅን አማልክቶችን ስትወ የኖረችና አሁንም ጥቂቶች ቢሆኑም “ወልዳች”። ዘመን መቁጠር ከተጀመረ ጀምሮ ለረዢም ዕድሜ አጥቂዎች እንዳያጠቅዋት” በየማአዝናቱ ቆመው ተከላክለውላታል (ሲጠብቋት “ነበር” ብል ይሻላል)፡፡ ዛ ራሳቸው ክፉኛ ተከበዋል፡፡

ከመቸውም ዘመን በከፋ መልኩ ተጠቅተዋል፡ለዘመናት ዘ ሲቆሙ አመድ ላይ ተኝተው ድጋይ ተነተርሰው ያቆዩንን አገር መልኳ ሁሉ ደብዝዟል፡ አካላትዋ ተቆራርጧል። እነሱ የምስል ጆቻቸውና ልጅ ለጆቻቸው የቀረነው ጠቂቶች በመሆናችን በዙሃ ምሃ ግበተ “በሙጃዎ’ ተወን በመረታችን “ኢትዮጵያ” የሚለው ምጻቸን እየታፈነበን ቸግናል፡፡

በመታፈኑም፡ በሸዋ፤ በወሎ ፤ በጎጃምና በጎንደር በምጥ ተወልደው ብቅ ያሉት አማልክት ተዋጊዎችዋ “የዲሞከራሲ ችግር ሳይሆን የሕልውና ጥያቄ ግምባር ቀደም ጥያቄ አድርገው ከቅኝ ተገዢዎቻችን ኢትዮጵያንና ሰንደቃላማዋን ነፃ ሊያወጡን ችቦ አቀጣጥለዋል።” ስለሆነም የዕልልታ ድመፅ ይገባቸዋል

<< ጢስ አባይ ራሰህን ከገደል ላይ ጥለህ የተቃጠለውን የምታጠፋ፤ የሞቀውን የምታበርድ ዓባይ “ግዮን” ራስህ በብስጭት ነድደህ ተቃጠልክና ‘ጭስ፤ በጭስ’ ሆንክ!>> እንዳሉት የፀፀት መጽሐፍ ደራሲ ሟቹ አቶ ለይኩን ብርሃኑ። ይሄው ጥቂት አማልክማሹ በጫካ ገማሹ በእስር፤ማሹ “በመጻፍ” ስደት አገር ሆኖም ቀስቃሸና ሞጋች ሑፎችን ንግግሮችን በማድረግ፤ እንዲሁም እየታገሉ ሰላሉ፤ስለ ተገድሉብን አርበኞቻችንና ሰለ ገድላቸው፤ ሰለ ታፈኑና ሰለ ታስሩ አንስትና ተባዕት ታጋዮቻችን ለዓለም ጀሮ በማዳረስ ላሉና ሃይለኛ አገር ቅር  ስሜት ጀታቸው እየጨ የራሳቸውን አንጀት ሳያሱ የኛን የዜጎች በማራስ ላይ ላሉ በልጆችዋ ለተበደለቺው ላልታደለቺው ቅድስት አገርና አማልክት ልጆችዋ ስላምና ድል ለነሱ ይሁን።

 መልካሙን ሳምንት እመኝላችለሁ እያልኩኝ እናት አገራችሁ በመታመምዋ ለተጎሳቆላችሁ የኢትዮጵያ ልጆች በዚህ የቪዲዮ መልዕክት ልሰናበታችሁ

Temeche Nigus Hageren Amobign ሀገሬን አሞብኝ New Ethiopian Music 2021 Official Video 720p

https://youtu.be/ymGmfU8BjeI?si=AJKOWZyd5Wsj-zFO

 

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)