ኦነግ ዐቢይ አሕመድ የወያኔ ሎሌ በነበረበት ወቅት የውስጥ አርበኛው እንደነበር አረጋገጠ!
እነ ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ያሳሰረ ዐብይ አሕመድ ነበር
አቻምየለህ ታምሩ (ኢትዮ ሰማይ -Posted at Ethio Semay)
ከወራት በፊት [ እ.ኤ.አ. ሜይ 2 ቀን 2019 ዓ.ም.] ከውስጠ አዋቂ ያገኘሁትን የታመነ መረጃ እዚህ ፌስቡክ መንደር አትሜው ነበር። ያተምሁት መረጃ ዐቢይ አሕመድ የወያኔ የጃሚንግና የስልክ ጠለፋ አዛዥ በነበረበት ወቅት በወያኔ ላይ ስዒረ መንግሥት ያሰቡትንና ይከታተላቸው ከነበሩ ሁለት ቡድኖች መካከል ለኦሮሞዎቹ ለእነ ከማል ገልቹ ቡድን ሚስጥራዊ መረጃ አሾልኮ በመስጠት ወደ ኤርትራ እንዲያመልጡ ሲያደርግ የአማሮቹን የነ ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ቡድን ግን እሱ ራሱ የተካፈለበትን ኦፕሬሽን አካሂዶ ሰዎቹ እንዲያዙና ለወያኔ ለእርድ እንዲቀርቡ ያደረገ መሆኑን የሚገልጽ ነበር።
አዎ! ዐቢይ አሕመድ የፋሽስት ወያኔ የጃሚንግና የስልክ ጠለፋ አዛዥ በነበረበት ወቅት ኦነጎች እነ ከማል ገልቹን መረጃ አሾልኮ ሰጥቶ ወደ ኤርትራ እንዲሸሹ ሲያደርግ በተመሳሳይ ወቅት ይከታተላቸው የነበሩትን እነ ጀኔራል አሳምነውና ጀኔራል ተፈራ ማሞን ግን « ነፍጠኞች መንግሥት ለመገልበጥ ተነስተዋል» በማለት ጠለፍሁት ያለውን የስልክ ልውውጣቸውን ለነ መለስ አሳልፎ ሰጥቶ እሱ ራሱ በቀጥታ ተሳታፊ በሆነበት ኦፕሬሽን አማሮቹ ጀኔራሎች በቁጥጥር ስር ውለው የወያኔ ችሎት የእድሜ ልክ ፍርደኛ በመሆን ላለፉት አስር ዓመታት በወያኔ ስቃይ ቤቶች ፍዳቸውን እንዲበሉ አድርጓል።
ኦነግ ትላንት ባወጣው መግለጫ ደግሞ «ዐቢይ አሕመድ በትግሉ ወቅት አብረውኝ ይታገሉ ነበር» በማለት የወያኔ የጃሚንግና የስልክ ጠለፋ ኃላፊ በነበረበት ወቅት እነ ከማል ገልቹ እንዲያመልጡ ሚስጥር ካሾከከበት ተግባሩ በተጨማሪ ለኦነግ መረጃ ያቀብል የነበረ የውስጥ አርበኛው እንደነበር ገልጿል። በተለይም በወለጋ የኦነግ ጦር መሪ የነበረው ለገሰ ወጊ በወያኔ ጦር ከመገደሉ በፊት እንዲገደል በቤተ ወያኔ መወሰኑን ዐቢይ አሕመድ መረጃውን ለኦነግ በሚስጥ አሹልኮ እንደነበር ኦነግ በመግለጫው አውስቷል።
የኔ ጉዳይ ዐቢይ ለምን የፋሽስት ወያኔ የጃሚንግና የስልክ ጠለፋ አዛዥ በነበረበት ለኦነጋውያን ሚስጥር አሾልኮ ሰጠ፤ አልያም የኦነግ የውስጥ አርበኛ ለምን ሆነ የሚል አይደለም። የኔ ጉዳይ «ኢትዮጵያን እወዳለሁ» የሚለውን ዐቢይ አሕመድ አገር ለመመስረት የሚታገሉት እነ ከማል ገልቹ መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሲዘጋጁ የተደረሰባቸው መሆኑን እንዳይገደሉ ሚስጥራዊ መረጃ ሰጥቶ ካገር እንዳስወጣና «ኦሮምያ» የሚባል አገር ለመመስረት ይታገል የነበረው ለገሰ ወጊ እንዳይገደል የወያኔ ሚስጥር አሳልፎ የሰጠውን ሰውዬ «ኢትዮጵያ እናታችን ናት» ያሉትን አማሮቹን እነ ጀኔራል ተፈራንና ጀኔራል አሳምነውን ግን ሚስጥራቸውን አሳልፎ በመስጠት ለወያኔ እርድ እንዲቀርቡ ማድረጉን የሚያዩና የሚሰሙ ሰዎች «ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ ሟች ነው» እያሉ ካፈርሁ አይመልሰኝ ብለው አሁንም ድረስ «አፈ ቅቤ ሆዴ ጩቤ» መሆኑን አለመገንዘባቸው ነው።
ሲያመልኩት የሚውሉ ሰዎች ዝቅጠት ነው።
«በኢትዮጵያ ኅልውና የሚመጣ ካለ እስክብሪቶ ሳይሆን ክላሽ ተሸክሜ ለመዋጋት ዝግጁ ነኝ» እያለ የሚደሰኩረው ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ማተባቸውን የቆረጡት ኦነጋውያን ጉዳት እንዳይደርስባቸው ጠቃሚ ሚስጥር በማሾለክ ከወያኔ ጥቃት ሲታደግ የኖረውና ኢትዮጵያ ወይም ሞት ያሉትን አማሮችን እነ ጀኔራል ተፈራ ማሞና ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ግን ሚስጥራቸው አሳልፎ በመስጠትና ቤታቸው ድረስ ኦፕሬሽ መርቶ ለወያኔ ለእርድ ያቀረባቸውን ጉድ ነው «ለኢትዮጵያ ሟች» ነው እያሉ ሲጃጃሉ የሚውሉት!
(Posted at Ethio Semay)