Sunday, October 13, 2019

የገዢዎቻችን የጭነት ፈረሶች የመሆን አሳዛኙ የኢትዮጵያውያን ያልተፈወሰው ባሕሪይ ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ (Ethio Semay) 10/14/2019


"የገዢዎቻችን የጭነት ፈረሶች የመሆን አሳዛኙ የኢትዮጵያውያን ያልተፈወሰው ባሕሪይ" 

ጌታቸው ረዳ 
ኢትዮ ሰማይ (Ethio Semay) 10/14/2019


የኖብል ሽልማት ደረት ደላቂዎች ሕሊና አሳሰቢነቱ እንደ አገር እና ሰብኣዊ መብት ስንመዝናቸው ላገራችን ስጋት ተጨማሪ ጭነት የመሆኑ ቀጣይነት ሳስበው የአብይ ትሮይ ፈረስ ሳይሆኑ ግልጽ ጠበቃዎቹ ሆነው ዕልልታቸውን እና ጦራቸውን ቀስረው አገሪቱ  ያሰመረችላቸው ቀይ መስመር አልፈው ቆመዋል። የአብይ አሕመድ እስክስታ ወራጆች ታማኝ በየነ አል ማርያምና ዳንኤል ክብረት ፤ የመለስ ዜናዊ ታማኞች እነ ሚሚ ስብሓቱ እነ ዘርይሁን ተሾመ፤ ትግሬው ‘አዳል ኢሳ” ወዘተ… እያልን ጫማ ሥር ወድቀው ለአገር ሻጮች ፤ለአሳሪዎች እና ገራፊዎች የሚያወነዝፉ እስክስታ ወራጆች ብንዘረዝር የሰዎቹ ስም ዝርዝር ለመጥቀስ ብዙ የጥራዞች ማሕደር ይጠይቃል።

ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ፖለቲካ መሪዎች በዓቢይ አህመድ መስመር ላይ ከወደቁት ሌሎች ጋር ለመጣጣም ትልቅ ይግባኝ እያሳዩ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ የተስፋ ቆራጭነት አምልኮ ያመጣው ባሕሪ ሆኖ  የቁርጥ ቀን ልጆችን የሚደበደቡበት መሣሪያ እየሆኑ ናቸው። 



ስለሆነም በሚገርም ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ምሁራኖች ደረቱን እየደለቀ በባዶ ጫካ ወደ እሚጮህ ጉሬዛ ቀልባቸውን የመስጠት ያህል ባበዶ ምርቃና ደረቱን የሚመታላቸው የአብይ አሕመድ የኖቤል ሽልማት  “ደብዛዛ ደረታቸውን ሲመታላቸው” ዕልልታቸውን የማቅለጡ ባህሪ አስገራሚ እየሆነብኝ ነው። በዚህ አምልኮ ከላይ የጠቀስኳቸው ሰዎች በመሪዎች ላይ ያሳዩት ፍጹም አመልኮ ላሳያችሁ እና ልደምድም።

በፕሮፈሰር መስፍን ወልደማሪያም የሕሊና መዋዠቅ እንጀምር

ፕሮፈሰር መስፍን እንዲህ ይላል፦ 

“እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ሕዝብ ጸሎት ሰማ፤ ዓቢይ አህመድንና ለማ መገርሳን ኮርኩሮ ቀሰቀሰ፤ ቀስቅሶ አሰማራ፤ አሰማርቶ ከውስጥም ከውጭም አቀጣጠለ፤ ትንሣኤ አቆጠቆጠ፤ አረንጓዴ ብቅ አለ፤ የተስፋ ጮራ ፈነጠቀ፤ እሾሁ ጠወለገ፤ ኢትዮጵያ ዓቢይን ይዛ ቦግ አለች፡፡ለማናቸውም ከዓቢይ ጋር በክብር ቆመን ስናጅበው ደስታ ይሰማናል፤ የሚተክዙ የኢትዮጵያ ጠበኞች ናቸው፡፡ዶ/ር ዓቢይ ያበርታህ!” ኢትዮጵያና ዓቢይ (ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማሪያም) ።"ይላል ፕሮፌሰር መስፍን።  

በዚህ አፓርታይድ መሪ ትዕዝዛዝ እስር ቤት ጭለማ ታግተው አብይ በመሸለሙ ምክንያት ታግተው የሚተክዙ እርጉዞች እና ወጣቶችን “የኢትዮጵያ ጠበኞች ናቸው“ እያለ መስፍን የዋዠቀበትን አስነብቦናል። እነሱም ዕልል እንዲሉለት የሚጠብቅ ጽሑፍ!

Al Mariam (Abiymania)

Abiy Ahmed “911 Search and Rescue” prime minister ጠ / ሚ/ ዶ / ር ዐቢይ አህመድ የ “911 የአደጋ ፈጥኖ ደራሽ ነው” እያለ ሲሰብክ አንብበናል፡፡
እንዲህ ይላል።

“If Ethiopians are wrongfully imprisoned, abused and tortured in their own country, who you gonna call. Abiy Ahmed! To me, he is “911 Search and Rescue” prime minister. ለእኔ “911 ፍለጋ እና አዳኝ” ጠቅላይ ሚኒስትር ነው ፡
ኢትዮጵያውያን  በገዛ አገራቸው ውስጥ በስህተት ከታሰሩ ፣ ከተጎዱ እና ከተሰቃዩ መጀመሪያ የሚጠሩት ማንን ነው?  ዶ / ር አብይ አህመድ!  በሥርዓቱ ላይ እያለ ምንም እስርና ስቃይ አይረደርስበትም፤ በዙህ እርግጠኛ ነኝ። ምክንያቱም ዶ/ ር አብይ አመድ ስትታሰር እና ስትሰቃይ ፈጥኖ ደራሽ እና አዳኝ ነው! ለእኔ “911 ለአደጋ ፈጥኖ ደራሽ ነው።” ይላል (ፕሮፌሰር አለማዮህ ገብረማርያም/አል-ማርያም ጠበቃ እና የሕግ አስተማሪ)

ታማኝ በየነ

 ከአል ማርያም ጋር ሆኖ በጋራ ባወጣው “ኢትዮጵያውያኖች፣ ያገኘነዉን ታላቅ ሰጦታ እንዳናጣ  ዓይናችንን ከፍተን መጠበቅ አለብን!” 
በሚለው
ከእንግሊዝኛ ነፃነት ለሀገሬ በተባለ ተርጓሚ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በታተመው ውስጥ ታማኝ እንዲህ ይላል።

“የአሉባልታ መሳሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን እና የመንግስታቸውን ሕጋዊ ቅቡልነት ለማሳጣት እና ወገን እና ሀገር ወዳዱ መሪ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሰላማዊ የለውጥ ሂደት አንጸባራቂ ኮከብ በመሆን የተጎናጸፉትን ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ አመኔታ ለመሸርሸር እና ለማጥፋት ሲባል ሆን ተብሎ ታስቦበት፣ በስሌት እና በታቀደ መልኩ እየተካሄደ ያለ መሰረተ ቢስ ዘመቻ እንደሆነ እናምናለን፡፡

“...ሀገሪቱ ወደ ሕግ አልባነት ስርዓት ተቀይራለች፤ ሕገ መንግስቱ እየተጣሰ ነው” እያሉ በነጋ በጠባ ሽንጣቸውን ገትረው የቅጥፈት ስዕል ለመሳል የሚያደርጉትን ከንቱ መንፈራገጥ እና ባዶ ጩኸት በአርምሞ እና በቁጭት እየተመለከትነው እንገኛለን፡፡ ይህም በሕይወት እና በሞት መካከል የሚደረግ ከንቱ መንጠራወዝ ካልሆነ በስተቀር ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ ነው ከሚለው የአበው ብሂል የሚያልፍ አይሆንም፡፡…ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዓይኖቻቸውን ካገኘነው ስጦታ ላይ እንዲያተኩሩ እንጠይቃለን፡፡እንደመር፣ አንቀነስ፣….” በማለት ታማኝ አልማርያም ጋር ሆኖ ስለ ዓብይ ቆሞ የውሸት ስጦታ እንዳናታ እያለ ዲያስፖራውን እና አገር ውስት ያለውን ሲያጃጅል ረው አንዳይበቃ:-

 ሰሞኑንም አብይ አሕመድ ሕዝብ የተዋደቀበትን ድምበር አሳልፎ ለጠላት ዝግጅነቱን በራሱ ፓርላማ ቀርቦ ስላረጋገጠ፤ የኖብል ተሸላሚ በመሆኑ ደስታው ወሰን እንደሌለው “እንኳን ደስ ያለዎት” ሲል ዕልለታውን አስደምጦናል። ይህ ከንቱ ዕልልታ እስር ቤት ላሉ ጋዜጠኞች እና የነፃነት ተጋዮች እንዲሁም ለዳር ድምበራችን ሲሉ ለተዋደቁ አርበኞች ክሕደትና ንቀቱን ከማሳየቱ አልፎ ኦሮሞች ዘንድ ሄዶ ኢትዮጵያ ውስጥ የኦዴፓ ጀሌዎች ያስለበሱት የኦነግ ልብስ ብድር ለመመለስ ይሆን ዘንድ ለመሪያቸው ለአብይ መመለሱን ማረጋገጫ ነው። ባንዳ ማለት ከዚህ ሌላ ካለ ንገሩን።

መጨረሻ መሳረጊያ፤

እንዲህ ዓይነቱ መሪዎችን የማምለክ ባሕሪ የመለስ ጀሌዎችም ሲያደርጉት ነበር። አንድ ምሳሌ ልስጥ:

አዳል ኢሳው ይባላል። ሎስ አንጀለስ ዩኒቨረሲቲ ለከፍተኛ ትምሕርት ሲከታተል የነበረ ነው። ድሮ የብአዴን ዋና ሰው ነበር። ቆይቶም ሎስ አንጀለስ ሆኖ ዓይጋ ድርገጽ ላይ የወያኔ ፕሮፐጋንዳ ሲነዛ የነበረ የትግሬ ምሁር ነው። እንዲህ ያለውን ላስታውሳችሁና ልደምድም፦

 “I am again a born believer & my religion is Meles Zenawi (Adal Isaw September 2, 2012)   በሚለው ጽሑፉ እንዲህ ይላል፦

 “I believe Meles Zenawi was born for reasons other than the ordinary ones that you and I were born for”  “I have a reason to revert back to the religion that I have abandoned early in life. Things were trite and nothing was out of the ordinary then, and, I had to walk away from my religion as a result. But now, and after many years of abandoning my religious belief, I am a born-again believer and my religion is Meles Zenawi.” ……”I believe in Meles Zenawi and he is my religion from now on till the end of my time”….

“አምናለሁ ፣ አቶ መለስ ዜናዊ የተወለዱት እርሱ እና እኛ የተወለድነው ከተለመዱት ምክንያቶች ውጪ ነው” ነገሮች ነገሩ ምቹ ነበሩ እናም በዚያን ጊዜ ከተለመደው ውጭ ምንም አልነበረም ፣ በዚህ የተነሳም ከሃይማኖቴ ራቅኩ፡፡ አሁን ግን ሃይማኖታዊ እምነቴን ለቅቄ ከወጣሁ በኋላ እኔ እንደገና የተወለደ አማኝ ነኝ ፣ ሃይማኖቴም መለስ ዜናዊ ነው ፡፡ ”

“Indeed; Meles Zenawi is my religion for he is a rarity—a gift from the Goddess of Ethiopia. And hence, he is the religion that I have now”. (Adal Isaw September 2, 2012   adalisaw@yahoo.com)
“በእርግጥም; መለስ ዜናዊ ሀይማኖቴ ነው ፣ እሱ የማይገኝ መስከርም ወፍ/ሉል ነው - የኢትዮጵያ አምላክ (ስጦታ)፡፡ እናም ፣ አሁን እኔ ያለኝ ሃይማኖት መለስ ነው::” (አዳል ኢሳው መስከረም 2 ቀን 2004 ዓ.ም.)ይላል።

ስለሆንመ ነው ዛሬም የገዢዎቻችን የጭነት ፈረሶች የመሆን አሳዛኙ የኢትዮጵያውያን ያልተፈወሰው ባሕሪይ ተጠናክሮ በዓብይ ኦሮሞ አፓርታይድ ዘምንም አወንዛፊነትና አምላኪነት ቀጥሏል። አምናም ዛሬም የሚታየው ፈውስ የታጣለት የምሁራን አጎብዳጅ ባሕሪ አንድ ቦታ ላይ ካልተገታ አገራችን ከአምባ ገነኖች ብትር ነፃ አትወጣም።
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ  ሰማይ)