ግንቦት 7 እና በቃሊቲ እስር ቤት
የምትገኝ እሩሳሌም ተስፋው ደብዳቤ ጉዳይ
ጌታቸው ረዳ
(Editor- Ethiopian Semay )
ባለፈው ሜይ
18/2016 ‘ግንቦት 7 እና ኦነግ’ የፕሮፓጋንዳ ቆሻሻቸውን የሚጥሉበት
ዘሓበሻ የተባለው ቆሻሻ ድረገጽ ላይ በወያኔ እሰር ቤት ውስጥ የምትገኝ እየሩሳሌም ተስፋው የተባለች ወጣት ግንቦት 7 ጻፈችልኝ
ብሎ የልጅቷን ፎተግራፍና በእጅ ጽሑፍ የተጻፈ ደብዳቤ “የታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው” – እየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት) በሚል
ርዕስ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61148
የተለጠፈው አንብባችሁ ይሆናል።ግንቦት 7
የተባለው በሆቴል ጉሬላዎች“ የሚመራው “ደደብ ድርጅት” ተላከልኝ ብሎ ለሕዝብ የለጠፈው ደብዳቤ ለራሱ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ
ለመጠቀም ሲል ግንቦት 7 ምንነት ያልገባት ጭንቅ ውስጥ የምትገኝ ምስኪን ወጣት ህይወቷ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ማድረጉ ወንጀል
ነው። በሽምቅ ተዋጊ እና ምስጢራዊ ግንኙነት ልምድ የሌላቸው ሰዎች የሚመሩት ግንቦት 7 ከመሪዎቹ እስከ ተራ ኣባሎች ተደጋጋሚ አደጋና የምስጢር ጠለፋ እንደ
ደረሰበት ይታወቃል።
ችግሩ ደብዳቤ ጻፈች የተባለቺው ወጣቷ ሳይሆን ተጠያቂነቱን የሚወስድ የግንቦት 7
መሪዎች በተለይም ሕዝብ ግንኙነት ክፍል የሚሰሩት ደንቆሮ ግለሰቦች መሆን አለባቸው። ይህች ልጅ ግንቦት 7 ምንነት እንደማታውቅ
ከደብዳቤዋ ማንበብ ይቻላል። እንደ ጸሓፊ እንዳለው ‘ቀይ ባሕር ተሻግሮ የሚገኝ አገር ዓረብ አገር እንጂ ኤርትራ አይደለም”፡ ልጅቷም ያን ያህል ኤርትራ የት እንዳለ አወቀች
አላዋቀች ፤ግንቦት 7 ምንነት አወቀች አላወቀች ሳይሆን፤ በችግር ውስጥ/እስር ቤት ውስጥ የሚገኝ እስረኛ እንኳን ደበብዳቤ ቀርቶ ራስንም ለማጥፋት እስከሚደርስ
የሚያስገድድ ፈተና እንሚጋረጥ የታወቀ ነው። በዚህ መከራ ላይ ሆና ጻፈችልኝ የሚለው ምስጢራዊ ደብዳቤ (ይፋ አድርጉትም
ብትላቸው) በምስጢር ከመያዝ ይልቅ ወይንም ስሙን ለጊዜው ለመግለጽ የማንፈልገውን እስረኛ የጻፈልን ደብዳቤ ብሎ ከማተም ይልቅ
“ፎቶግራፏን እና የታሰረችበት እር ቤት ስም” ሳይቀር ከነ የእጅ ጽሑፏ ለሕዝብ ማስነበቡ በወያኔ መርማሪዎች ይበልጥ
ግርፋት፤ስቃይ፤ሞት እና አሰቃቃ ሁኔታዎች እንዲፈጸምባት መንገድ መክፍት መሆኑን የድርጅቱ መሪዎች ማወቅ ነበረባቸው።
ሆኖም፤ ድርጅቱ ከደደብነት ወደ ደደብነት እያደረ የሚዘቅጥ ለፕሮፓጋንዳ እና ለግል
ዝና ብቻ ሲል የኢትዮጵያ ጠላቶችን በማወደስ፤ የወጣቶችም ሆነ የደርጅት መሪዎችን ህይወት አደጋ ላይ በማጋለጥ “ትሬንድ”
/አመል/ የሚጓዝ የከሰረ ቡድን በመሆኑ እየሰራ ያለው ስራ የሚወገዝ ነው። በግል ዝና /ኢጎ/ የሚሰቃዩ የዚህ ድርጅት መሪዎች
እየፈጸሙት ያለውን ደደብነት በልጅቷ ላይ ተጨማሪ ስቃይ ቢደርስባት ወይንም በሕይቷ አደጋ ቢደርስ ቤተሰቦቿ ግንቦት 7ን ተጠያቂ
ማድረግ አለባቸው።
አስቀድሜ እንደገለጽኩት በጭንቅ እና እስር ውስጥ ያለ ሰው የገዛ ህይወቱ ሳይቀር አስከማጥፋት ድረስ የሚመኝበት ጊዜ
አንዳለ በቀይ ሽብርና በወያኔ በረሃ እስር ውስጥ ያለፉ ሰዎች የሚያውቁት ጉዳይ ነው። ልጅቷ በዚህ ሁኔታ ሆና ለድርጅቱ
ስትጽፍ፤ ጭንቀቷን የምታነፍስበት መንገድ መግለጧን ከደብዳቤዋ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል። ይህች ልጅ የአመራ ነገድ ትሁን አትሁን
ባላወቅም ‘ግንቦት 7’ ልክ አንደ ወያኔ “ጸረ አማራ” መሆኑንንም የምታውቅ አይመስለኝም” ካሁን በፊት ያልዘገብኳቸው አዳዲስ
መረጃዎች አሉ፤ እነሱን ለወደፊቱ አቀርብለላችሗለሁ። )”
ልጅቷ፤ “ጀግናው አንዳረጋቸው”….. እስር ቤት አይቼው ነበር…እያለች የምትጠራው
ጸረ አማራና ቅጥረኛ ግለሰብ “ቀይ ባሕር” ልሻገር እያለች የጻፈቺው ደብዳቤ እውን “ለመሄድ የምትመኘውን ምድር ሄዳ
አንዳርጋቸው ጽጌ “በተስፋዬ ገብረአብ አስተዋዋቂነት ጎደና ሓርነት/ኮምቢሽታታቶ፤ ከነ ሰሚራ ሲቀብጥ በነበረበት ጊዜ”
ሄዳ ብታየው ኖሮ እንዲያ ያለ ደብዳቤ ለማጸፍ አትሞክረውም ነበር። የእነ ስንታየሁን ቃለ መጠይቅ ያደመጣችሁ ሰዎች ሰሚራ ከኣንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ምን አይነት ግንኙነት እንደነበራቸው ይፋ እንደሆነ
ታስታውሳላችሁ።ሆኖም የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ተብሏልና ፤ልጅቷ መከራ ውስጥ ሆና ግንቦት 7 ጓዶቿ ጋር ለመቀላቀል መንፈሷ እዛ
እናዳለ ብትጽፍ የሚያስገርመን አይሆንም። እንኳን መከራ ውስጥ ያለ፤ እዚህ ውጭ አገር ተቀምጠው የግንቦት 7 ማንነት በመሪዎቹ
አንደበት በግልጽ እየተነገራቸውም ድርጀቱን የምጠይቅ ድፈርት የላቸውም።
ታሪክ ወደ የዘገበውን ማንበብ አለባችሁ።እነኚህ ግለሰቦች የብዙ ቤተሰብ ኑሮ
እንዲሰናከል ምክንያት ሆነዋል። ብርሃኑ ነጋ አንዳርጋቸው ጽጌ ባልነበረበት (እንግሊዝ አገር እየኖረ ባለበት ሁኔታ) በቅንጅት
አመራርነት/አባልነት እራሱ አስመርጦት (ዲሞክራሲ አልባ ምርጫ) ሲያበቃ፡ ሁለቱም ቅንጅት በማፍረስ የተጫወቱት ሴራ የሚታወቅ
ነው። ቅንጅትን በማፍረስ ዋና ዋና ሚና የተጫወቱ ግለሰቦች ከቀንደኞቹ አንደኞቹ ናቸው። ሌላ ቀርቶ ፕሮፌሰር መስፍን
ወልደማርያምም “ብርሃኑ ነጋ ቅንጅት ለማፍረስ ያቀደው ስልጣን ለኔ ካልተሰጠኝ ሲል ነው” ብለው መስክረዋል ( ቪ ኦ ኤ አማርኛ
ክፍል ተጠየቀው፤ሕንድ ለሕክምና/ለውስብስብ የጭንቅላት/የማጅራት? ለቀዶ ጥገና ሄደው ሳለ። ሳልናገር እንዳልሞት ብየ ይህችን መናገር አለብኝ ብለዋል።)።
አንኳን የዚች ወጣት ህይወት ለመከላከል ቀርቶ ቅንጅት የሚያክል እንኳ ስልጣን እና የግል ዝና ለመስራት ሲል ድርጅቱ እንዲፈርስ
ያልሰራው አሳፋሪ ገበና አልነበረም። የዚች ልጅ ህይወት ለአደጋ በማጋለጥ እራሱ “የፋራ” ፖለቲካ ሲለው የነበረውን “የፋራ”
ፖለቲካ በመስራት አደጋ ላይ ጥሏታል።
በዚህ ግለሰብ የሚመራ ግንቦት 7 የሚያምን ማንኛውም ሰው/ ተከታይ/ አንጨብጫቢ
ወይንም ልምድ የለውም፤ ወይንም በስሜት አንደከበት የሚነዳ ፍጡር ነው። ጭንቅ ያንገላታው፤ ወይንም “ነብሰ ቅትልት/ሱሳይዳል”
ጨዋታ መግባት የሚያምረው ሞኝ ብቻ ነው። ድርጅቱን አምነው ኤርትራ ሄደው በአንዳርጋቸው ጽጌ እውቅና እና ማስፈራራት ለኤርትራ
ደብዳቢዎች ተሰጥተው የደረሰባቸው ግፍ በቃለ መጠይቅ ከነስንታየሁ እና ማስረሻ ያደመጥነው ታሪክ አለ። ይህ ድርጅት የራሱን መሪ
አንዳርጋቸውን አስበልተው፤ አማራሮቹ ዛሬም ውግያ ውስ ሳይካፈሉ፤
ጫካ ውስ ሳይተኙ፤ ውጭ አገር የሙጥኝ ብለው ሲመላላሱ ታያላችሁ።።
ብርሃኑንም በተለያዩ አገሮች እየሾለከ ወደ አሜሪካ እንደሚመጣ ይነገራል። የወያኔ የስለላ መዋቅሮችም ቸል እያሉ አውቀው እንዳላዩ
እያሞኙት ሲሸጋጋር በየት እንደሚሄድ ያውቃሉ፤ የወያኔ ጸባይ የሚያውቅ ሰው የተካነ ልምድ ስላላቸው “አዘነግተው እንደ ጅብ”
“ላጥ” ሊያደርጉት በጥናት ላይ አንዳሉ ሹክ የሚሉ ወሬዎች እየተናፈሱ ነው።አሜሪካኖች ብርሃኑን ቢደግፉትም፤ ሁለቱም
ለአሜሪካኖች አገልጋይነት ይብልጥ እያወዳደሩ ናቸው።፡አንዱ ካፈነገጠ፤ ሌላኛው ወደ ሥልጣን ያመጡታል፡ በረራና ፓስፖርት
ያግዱታል ማለት ነው።
ይህ ቅ ረኛ እና
ደደብ ድርጅት የራሱን ምስጢርና ኮድ መጠበቅ የማይችል ነው። ለምሳሌ በኢሳያስ አፈወርቂ ትዕዛዝ (October 2 ከ2009)
ጀምሮ ለብየርሃኑ ነጋ የተሰጡ የፓስፖርት ቁጥሮች የተለያዩ ቢሆኑም አንደኟው y27129
ሲሆን ድረጅቱ የተጠለለበት ኤርትራ ምድር የስርዓቱ መዛግብትና
ምስጢሮች ለጠላትና ለውስጥ ተቃዋሚ ስለላ የተጋለጡ ናቸው። የሞላ አስገዶም ታሪክ በቅርቡ ያያችሁት ምስጢር ነው። ልምድ
አንደሌላቸው የሚያሳየው ደግሞ፤ የድርጁቱ መሪዎች በሌላቸው አቅም የጠላትን ሃይል ሲንቁ ታደምጣላችሁ።“ወያኔ ሰነፍ ነው፤
ስለላው አይረባም፤ ድምበሩ ክፍት ነው”…….ወዘተ እያለ የድረጅቱ መሪ ደደብነቱን ሲገልጽ የድርጅቱ መሪ ከአመራር አባላት ጋር
ያደረገው በምስጢ የተቀዳ መረጃ በወያኔ የስለላ መረብ መውደቁ ግን ይታወሳል። ቀጠል ያደርግ እና የድርጅቱ ምክትል
መሪ ባሳፋሪ ሁኔታ ባጭር ወቅት በወያኔ እጅ መውደቁ ይታወሳል።
ቀጠል
ይልና እንደገና የግንቦት 7 አለም አቀፍ የደህንነት መዋቅር አባልና ቆየት ብሎም ወደ ኣመራሩ የተቀላቀለ ግለሰብ ባለቤቱ ባንድ
ጉዳይ ከውጭ አገር ወደ አዲሰ አበባ ሄዳ ወያኔ ደርሶባት የግንቦት 7 ኣበላትና ምስጢር ዝርግፍ አድርጎ እንዲሰጥ ካልሆነ ግን ባለቤቱ
እንደማትለቀቅና እስር ቤት አንደምትበሰብስ ለባለቤቷ ስልክ ደውለው ይነግሩታል። ባለቤቷ አስቸጋሪ ሁኔታ መውደቋን በማወቁ፤ ሰውየው
ከ እስከ ያለውን የድረጅቱን ምስጢር ሙልጭ አድርጎ ለወያኔ አስረክቦ ባለቤቱን ያስፈታል። በዚህ ሁኔታ አንዳለ ድንገት የመካካለኛው
ምስራቅ የግንቦት 7 ሰብሳቢ የነበረው አባል ጋብቻ ለማካሄድ ወደ አገር ቤት ሲሄድ፤ የመጀመሪያው ሰለባ የሆነው ይህ ግለሰብ ነበር።
እንደደረሰ በቀጥታ ከአውሮፕላን ማረፊያ ይዘው ወደ እስር አስገቡት። የግንቦት 7 የደሕንነት አመራር ምስጢሩን አሳልፎ ከሰጠ በኋላ
ምንድ ነው ያደረገው? ለግንቦት 7 ሥራ አስፈጻሚ አባላት እንዲህ እንዲህ ያለ ችግር ተፈጥሮብኛል እና፤ የማውቀውን ያክል ለወያኔ
አሳልፌ ሰጥቼ ሚሰቴን አስፈትቻለሁና ይህንን ጉዳይ እናንተ ማወቅ ስለሚገባችሁ ይህ እንድታውቁት ብሎ ለሚቀርባቸው የሥራ አስፈጻሚ አባላት ይነግራቸዋል።
ታዲያ
ግንቦት 7 ደደብ እና ቡድነተኛ ስለሆነ፤ በቅርብ ለሚያውቃቸው ሰዎች ብቻ ይህንን ምስጢር ይነግሩና ሌሎዩ የተጋለጡ አባሎችመጋለጣቸውን
እንዳያወቁ ይደረጋል።ይህንን የማያውቅ አባል ወደ ኢትዮጵያ ሲሄድ ወይንም አገር ውስጥ የነበረ አባል በተለያዩ ጊዚያቶች በጠላት
እጅ እንዲወድቁ ተደርገዋል። የታሰሩም፤የተገደሉም፤የተሰደዱም እንዳሉ በወቅቱ ከግንቦት 7 ራሳቸውን ያገለሉ አማራሮችና የድርጅቱ
ተዋጊ ሃይሎች የነበሩ አባሎቹ ገልጸውታል። ይህ ድርጅት በጣም አደገኛ እና የድርጅት ምስጢራዊ ጥበቃ የብቃት ልምድ የሚጎድለው ብቻ
ሳይሆን ፤አባላቱንም ሆነ አማራሩን ለአደጋ የሚጋለጥ ደደብ ድርጅት መሆኑን ብዙ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል።
ከዚህ
ተነስተን ይህች ወጣት ጻፈቺው የተባለው ደብዳቤ ለግል ድርጅቱ በሚስጢር ከመያዝ ይልቅ ‘ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲል ይህች ወጣት ለባሰ
መካራ እንድትጋለጥ አድርጓል። ይህች ልጅ ለሚደርስባት ተጨማሪ አደጋ ግንቦት 7 ተጠያቂ ነው። ድርጅቱ የሚመሩ ግለሰቦች የጀርባ
ታሪክ ስትመለከቱ እነ ብርሃኑ ናቸው። ጰርፓራ ፈሪዎችና ተሎ የሚጎነበሱ፤ ሸሽት እንጂ መጋፈጥ የማይወዱ፤ሌላ ወጣት እያጋፈጡ እንሱ
ባልዋሉበት ወንጀል አዎ ሰርተናል ብለው ፈርመው ከእስር የሚወጡ፤ ወጣቱን የሚያጋፍጡ ሃፍረት ትርጉም የማይገባቸው ግለሰቦች ናቸው።
የብርሃኑን ታሪክ የአንዳርጋቸውን ኑዛዜ ልብ ይለዋል።
ለምሳሌ የቅንጅት ጊዜ ታስታውሳላችሁ።
እስኪ
አንዳንድ ጸሃፊዎች ብርሃኑን ያጋለጡበትን ማሕደር እንፈትሽ፤
የቅንጅት አመራሮች ጥቅምት 18 ቀን ገበሬውን ማጭድ አትዋዋስ፣
የቤት እመቤቶችን ሰፌድ አትቀባበሉ፣ የተቸገረ ኢህAዴግ ብታገኙ አትመጽውቱ ብለው በመማማል ለጋዜጦች መረጃውን “ሊክ” አደረጉ፡፡
በነጋታው ጥቅምት 19 ቀን 1998 ዓ.ም ዳ/ር ብርሃኑ የነፍስ ሲያውጁበት በነበረው የቀስተ ዳመና ደብዳቤና ማህተም አማካኝነት
“አኛ ቀስተ-ደመናዎች የለንበትም” አለ፡፡ አብሮ አቡኩቶ ጋገራው ላይ አኔ የለሁበትም የብርሃኑ ነጋ ባሕሪ ነበር።
በረከት ሰምኦን “ኢትዮጵያ ፎረም ፎር ፖለቲካል ሲቪሊቲ” በሚባለው የወያኔ አሽከሮች የወያኔን ወለል የሚወለውሉበት ሀገረ አሜሪካ በሚገኘው የውይይት መድረክ ላይ ቀርቦ ያለውን ቃል በቃል ላስቀምጥ “ዶ/ር ብርሃኑ ብዙ ጊዜ የሚያነሳልኝ ነገር እኔ መቼም ይሄ ሂደት አስፈርቶኛል፡፡ አንተ ጋ ነው የምመጣው፡፡ አንተ ታድነኛለህ… የማይለኝ ጊዜ አልነበረም”፡፡ ሲል የብርሃኑ ፐርፓሪ ፈሪ ባሕሪ ገልጾልናል። እዚህ መግለጹ አስናዋሪ ሆኖብን እንጂ
ከሸራተን ተይዞ ወደ ላንድወሮቨር እየተገፋ በጥፊ ሲነትሩት ያዩ የድርጊቱ ተካፋዮች ለቅርብ ሰዎች ያጯወቷቸው የታየው አሳፋሪ ነገር
“ተከድኖ ይብሰል” ነው።
እስኪ
ሌላው የብርሃኑ ትዝታዎችና ማሕደር እናስታውስ። መቸም አስታዋሽ ሲያጣ ነገር እየተራሳ እነ ብርሃኑ ነጋ “ነፃ አውጪዎች፤ቆራጦች….ጀግኖች.ማንዴላዎች”
እየተባለ እየተፏጨላቸው ሲንጨበጨብላቸው አድምጠናል። ብርሃኑ ግን ማሕደሩ ያንን አያሳይም።
ምሳሌ
ልስጥ ፤
እጅግ በጣም የሚያሳፍረውና
ለሕሊና የሚከብደው ነገር ደግሞ ሌላው የዶ/ር ብርሃኑ የእስር ቤት የአራዳ ፖለቲካ ነው። ይላሉ አንድ ጸሃፊ፤-
“እኔ የቀሰቀስኩበትም ሆነ ያነሳሳሁበት ጊዜ የለም፡፡ መታሰር አይገባኝም፡፡ አልፎ ተርፎም የቅንጅቱም ሥራ አስፈፃሚ አይደለሁም፡፡ ጥቅምት 22
የተሰበሰበው የቅንጅት ላእላይ ምክር ቤት የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ወስኖ በወ/ት ብርቱካን ፊርማ መግለጫው ሲበተን አሞኝ አልተገኘሁም፡፡
ስለዚህ ኢህአዴግ አኔን ለማሰር የሚያስችል በቂ ምክንያት የለውም፡፡ እኔን ያሳሰረኝ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነው፡፡ ወደፊት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቦታ መያዝ የምችለው እኔ መሆኔን ስለሚያውቅ ነው” የሚል ነበር፡፡
በተለያየ አካባቢ አጋጣሚና በተደጋጋሚ ይህንን አስር ቤት ውስጥ ሲያነሳው የነበረው “አልነበርኩበትም” ክሕደት በዓላማ አንድነት የተሳሳሩ የትግል አጋሮቹ ጋር በጋራ በወሰዱት አቋም ምክንያት መታሰሩን ጥያቄ የሚያነሳ ከሃዲና ሽሽታም ግለሰብ ነው፡፡ አሁንም ከነ ተስፋዬ ገብረአብ
ጋር አስመራ ውስጥ እየተሽሞነሞነ ወርቅ ፍለጋ የተሰማሩ ድሃ ወጠቶችን ከሻዕቢያ ጋር እየተነጋጋረ
ከትግራይ ድምብር እያሳፈሰ ለማጋፈጥ እንጂ እሱ ጦር ሜዳ ሄዶ
አንደማይዋጋ ከማህደሩ ማንነት የምናውቀው ግለሰብ ነው። በዚህ ወር ደግሞ (?) ለማቀፍ በየሦስት ወሩ አሜሪካ ሲመላለስ በእግረመንገዱም
ወደ በኤርትራ ሂሳብ በኩል የሚተላለፍ ወደ ናቅፋ የሚለወጥ ዶላር ለቃቀሞ ለመሄድ እንደገና መጥቷል።
ስለሆነም
የዶ/ር ብርሃኑ የ የለሁበትም ክሀደት ሁሌም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው አለምአቀፍ ማህበረሰብ የድረሱልኝ ጥሪ እንደሆነ ለመገመት አያዳገትም፡፡ ዛሬ ግንቦት 7“በኮሌክቲቩ ሊደር ሽፕ” (ትርጉሙ ምንም ይሁን ምን) የሚመራ ነው ቅንጅትም አንዲሁ “በኮሌክቲቩ ሊደር ሽፕ” ሂደት አምናለሁ የሚለው ዶ/ር ብርሃኑ መድረክ ላይ መውጣት፣ መደስኮርና ውሳኔ መስጠት ሲሆን በጋራ፤ ተጠያቂነትና
መታሰር ሲመጣ በተናጠል ማለቱን፤ የታወቀ ማሕደሩ ነው፡፡
ጸሓፊው
አንዲህ ይላሉ
“ብርሃኑ
በቅንጅት ወቅት አገሪቷን ነፃ ለመውጣት ይህንን ስርዓት ከመጋፈጥና በተከታታይ ሰልፍ ከማንቀጥቀጥ ውጪ አማራጭ የለም፤ በማለት ሕዝቡን ለብጥብጥና ለእርስ በርስ ትርምስ ካደረገ በኋላ ማፈግፈግ ዶ/ር ብርሃኑ አሜሪካ በየፖልቶኩና መድረኩ እንደሚለፈልፈው የአራዳ ፖለቲካ ይሆን? ሞትና እስሩን ለፉራ፤ ስልጣኑንና መድረኩን ለኛ አይነት፡፡” ይላሉ ጸሃፊው።
የህስ ማሕደር ትዝ ይላችኋል? በብርሃኑ ነጋ
የለሁበትም ማሕደር ልቋጭ፡
ሚስጢሩን ያጋለጠው የብርሃኑ የቅርብ ትውውቅ የነበራቸው ጸሓፊ
ናቸው።የቅንጅት አመራሮች በብዛት በወያኔ ጎስታፖዎች እየተደበሰቡ ወደ እስር ሲገፈተሩ፤አንዳንዶቹም በየቤታቸውና በየመስርያቤታቸው
ታግተው ባሉበት ሁኔታ በነጋታው ዶ/ር ብርሃኑ ከተጠለለበት የአና ጎሜዝ የሸራተን ክፍል ወጥቶ ወደ እንግሊዝ ኤምባቢ ያመራል፡፡ብርሃኑ
ነጋ፤ ከእንግሊዝ ኤምባሲ ይደውልና ለአንድ የቅንጅት ከፍተኛ አመራር ከተማው ያለበትን ሁኔታ ይጠይቃል፤ በደረሰው መረጃ መሠረት
የመንግሥት ታጣቂዎች በከባድ መኪና ተጭነው ወደ ቅንጅት ቢሮ እየገሰገሱ በመሆኑ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጠይቀው በማከታተል እኔ
እዚሁ (እንግሊዝ ኤምባሲ) ልቀር ነው ይላሉ፡፡ በዚህ ወቅት የቅንጅት አባሎች በገፍ እየታሰሩና እየተደበደቡ ነው፡፡ የቅንጅት አመራር
እንዲያድናቸውም በተማጽኖ ላይ ናቸው፡፡ ስልክ የተደወለላቸው የቅንጅት አመራር የብርሃኑ ጥያቄ ተገርመው ውሳኔው የራሳቸው መሆኑን
በመግለጽ አግባብ የሚሆነው ግን እጣ ፈንታቸውን ከሕዝብና ከአመሪራቸው ጋር ቢያደርጉ መሆኑን ይገልፁላቸዋል፡፡
እኚህ የቅንጅቱ አመራር ብርሃኑ ነጋ ያንን የጭንቅ ቀን የትና
እንዴት እንዳሳለፉት ባያውቁም የኢህአፓ ከፍተኛ አመራር የነበረው “የዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ሹፌር ነበርኩ” የሚለን ዶ/ር ብርሃኑ
ነጋ ከዶ/ር ተስፋዬ ስብእና ምንም ያልተማረ መሆኑን ሲገልጹ “ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ የተሰውት ደርግም የኢ.ህ.አ.ፓ አባላት የተገኙበት
እንዲረሸኑ ሲያውጅ እራሳቸውን ማዳን ሲችሉ አባሎቻቸውን ከአዲስ አበባ ለማሸስ ሲንቀሳቀሱ፤ ዶ/ር ብርሃኑ ግን ራሳቸውን ለማዳን
ይፍጨረጨሩ ነበር” ብለዋል፡፡
ይህ ሁሉ ታሪክ
ሚያሳየን የግንቦት 7 መሪዎች (ብርሃኑም፤ አንዳርጋቸውም…..) ጭራሽኑ ዛሬ መታመን የሌለባቸው ምክንያት ታሪካቸው የተጨማለቀ፤ሽሽት
የሚያበዙ፤ ታሪካቸው የጠቆረ፤ ታላላቅ ኢትዮጵያዊያኖችና ተማሪዎች ሲገደሉ ፤ ከመለስ ዜናዊና ከታምራት ጋር ዊስኪ ሲጨልጡ የነበሩ፤ ዛሬ ደግሞ ወጣቱን ለመከራ እያጋፈጡ እነሱ ወደ አሜሪካ
እየተመላላሱ ሲሽሞነሞኑ፤ ታጋዩ በረሃ ድምበር ውስጥ የ ሻዕቢያ ድመበር ጠባቂና ሟሽላ ቆራጭ አድርጎ መፈላፈስ ፤ተዋግተናል እያሉ
“መረጃ የሌለው፤ በፎቶ ያልተደገፈ 20 የወያኔ ወታደር ገድለናል፤ እንደዚህ ያለ ቁጥር አቁሰለናል እያሉ ቪዲዮ የለ፤ፎቶ የለ፤
ምንም መረጃ በሌለበት፤ ሁለቱም ወስላቶች (ወያኔዎችና ግንቦት 7) ትንንሿን ተራ ሽፍታ የሚቶኩሶውን የቶክስ ልውጥን ትልቅ ድራማ/ትያትር
ሲሰሩ ማድመጥ አጅግ ይገርምል።
ብርሃኑ ነጋ እንደ
ፖለቲካኛ ሀቀኛ ሰው አድርገው የሚያዩ ደደብ ምሁራን ሲያንጨበጭቡ
በዩቱብ ስመለከት “ምራቄን ልተፋባቸው ይዳዳኛል”። ይህ ከሃዲ ዛሬ የሚታለቡትን ላሞቹን
ለማለብ በቅርቡ ከአስመራ እየበረረ ይመጣል የሚል ማስታወቂያ ተለጥፏል። ቅንጅትን ያፈረሰ ይህ ከሃዲ በምኑ ታሪኩና የጀርባ ማሕደሩ
ነፃ አውጪ ሊሆን አንደሚችል ተካታዮቹ ይገርሙኛል።
ብርሃኑ ማን ነው?
ትዝ ይላችሗል የቅንጅት መራሮች ጥቅምት 18 ቀን ገበሬውን ማጭድ አትዋዋስ፣ የቤት እመቤቶችን ሰፌድ አትቀባበሉ፣ የተቸገረ የኢህአዴግ ደጋፊ ብታገኙ አትመጽውቱ ብለው በመማማል ያሳለፉትን ለጋዜጦች መረጃውን “ሊክ” አደረገ፡፡
በነጋታው ጥቅምት 19 ቀን 1998 ዓ.ም ብርሃኑ ነጋ ሲያውጅበት በነበረው የቀስተ ዳመና ደብዳቤና ማሕተም አማካኝነት “ኛ ቀስተ-ደመናዎች የለንበትም” አለ፡፡ ሃሳቡን አላምንበትም የትም አያደርስም ማለት የነበረ ነው። አብሮ አቡኩቶ ጋገራው ላይ እኔ የለሁበትም የብርሃኑ ፈሪነትን
ያመላክታል።
ብርሃኑ ነጋ የወያኔን ጫማ ለመሳለም ሲል የዶ/ር ተስፋይ ደበሳይ ሾፌር ሆኖ ኢሕአፓን
ያገለገለበተትን ፓረርቲ ነካሽ፤ ሳደቢና ረጋሚ ነው። ወያኔ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ የዘረጋውን የፖለቲካ ሥርዓት ለመቀላቀል ወደር የለሽ ተጋድሎ አድርገዋል። ታማኝነቱን ለማረጋገጥ በፋና ሬዲዮ ጣቢያ ላይ ቀርቦ “የተበላ ኡቁብ” እያለ የቀድሞ ድርጅቱን አህአፓ ላይ ተከታታይነት ያለው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አካሂደዋል። አሳፋሪ የፖለቲካ አቃጣሪ ሆኖ ነበር ሽር ጉድ ሲል የነበረው!
ጸሀፊውን እንደገና ልጥቀስና ልደምድም፦
“ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ታምራት ላይኔ እስር ቤት እስከወረዱበት ጊዜ
ድረስ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከኢህአዴግን የሚያሞካሹ ጽሑፎችን ባገኙት መድረክ
ከማቅረብ አልፈው፣ ከአዲስ Aበባ ዩኒቨርስቲ “በፀረ-ዲሞክራሲያዊነት” ተፈርጀው
የተባረሩ ምሁራንን (ዛሬ የትግል አጋሮቻቸውን) ተክተው የትምህርት ሥርዓቱ
የተፈጠረበትን ቀውስ በማርገብ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ ለኢህአዴግ የነበራቸው አፍላ ፍቅር በርዶ በመካከላቸው
የነበረው ግንኙነት የተቋረጠው ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ቢሆንም፣ ዶ/ር ብርሃኑ
እንደሚሉት “በፖለቲካ መስመር በተፈጠረ ልዩነት” እንዳልነበረ ሕያው ምስክሮች
ይገለጻሉ፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ በለመዱት የገሃዱ ዓለም ቲያትራቸው እየታገዙ በከፍተኛ
መተጣጠፍና ቅልጥፍና በንድ በኩል የሥልጣን መሰላሉን እየተቆናጠጡ፣ በሌላ
እጃቸው በሕገ-ወጥ መንገድ ንብረት በማጋበስ ድርጅታቸውን እያነቀዙ መሆኑን
የተረዳው ኢህአዴግ ፊት ይነሳቸው የጀመረው በንቅዘት ተጠልፈው የሥልጣን
መሰላሉ ያዳለጣቸው አቶ ታምራት ላይኔ ከኃላፊነታቸው ሲነሱ ነበር፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ ኢህአዴግ ጫካ ውስጥ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ከድርጅቱ ከፍተኛ
ታጋዮች ጋር አሜሪካ በምስጢር ይገናኘ እንደነበረ አቶ ጌታቸው ጀቤሳ “ዝንብ
ካድሬ፣ ውሻ ፖሊስ፣ አዝማሪ ጋዜጠኛ” በሚለው ጽሑፋቸው የገለጹት ቢሆንም፤
ኢህዴግ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ለጀመሩት አዲስ ግንኙነት መስመሩን የጠረጉት
አቶ ታምራት ላይኔ መሆናቸው ይታወቃል፡፡” ይላሉ።
“ዶ/ር በርሃኑ በአቶ ታምራት ላይኔ Aማካኝነት ከኢህአዴግ እቅፍ ውስጥ
መግባት ብቻ ሳይሆን አዲስ ላቋቋሙት ሪል ስቴትና በቤተሰቦቻቸው ስም በወቅቱ
ሊገነቡዋቸው ላቀዱት ሕንፃዎች የሚውል መሬት በነፃ እንዲያገኙ ረድተዋቸዋል፡፡
የፓርቲያቸው (ቀስተ ደመና) መስራችና ግንባር ቀደም አባል ወ/ሮ ንግሥት
በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ እንደገለጹት “ማንም ሰው ለዶ/ር ብርሃኑ የሥልጣን ጥም
ወይም ማጋበስ ለሚፈልጉት ንብረት መወጣጫ በመሆን ካላገለገለ የቀድሞ ወዳጅነቱ የቱንም ያህል የጠበቀ ቢሆን የመልካም ጊዜ ግንኙነታቸውን ለቅጽበት ታክል ማስታወስ የማይፈልጉ ሰው ናቸው፡፡” ብላዋለች
“ለዚህም ይመስለኛል የራሳቸውን ታሪክ ከልጅነት እስከ እውቀት “የነፃነት
ጎህ” በሚለው መፅሐፋቸው ላይ ከአቶ ታምራት ላይኔ ጋር የነበራቸውን የረጅም
ጊዜ አጋርነት አንድም ቦታ ሳይጠቅሱ የቀሩት፡፡ ዶ/ር ብርሃኑ ሥልጣንና ንብረት የሚገኝበት መንገድ ከፊታቸው እስከታያቸው እውነታው ሆነ ከሞራላቸው ጋር የሚጋጩ ግለሰብ መሆናቸውን ይህ ምሳሌ የሚገልፀው ነው፡፡” ይላሉ ጸሐፊው።
የግንቦት 7 ዋናው መሪና አሽቃባጮቼ ሌሎችን ለመከራ እያጋፈጡ
የአራዳ ፖለቲካ እና ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እየተጠቀሙ የሰዎችን ህይወት ወደ አደጋ መግፋት አዲስ ነገር አይደለም። ስለሆነም ነው የዚህ ወጣት ፎቶግራፍና የእጅ ጽሑፍ በይፋ
ለወያኔ በማቀበል ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩባት ማየት አሳዛኝ ነው። በልጅቷ ላይ የከፋ መከራ እንዲደርስባት እያደረገው ያለው ሥራ መወገዝ
አለበት።፡ልጅቷ በጭንቀትና ተስፋ መቁረጥ የጻፈቺውን ደብዳቤ ምክንያት እስር እያለች አደጋ ቢደርስባት የዚች ልጅ ቤተሰብ ግንቦት 7ን በሃላፊነት መጠየቅ አለባቸው፡ እስኪ በዚህ ወር ሊመጣ ነው ተብሎ ላሞቹን ለማለብ
ሲመጣ ምን አንደሚቦተልክ ደግሞ እንደገና እንጠብቅ፡፤
አመሰግናለሁ ጌታቸው ርዳ ((Editor- Ethiopian Semay ) getachre@aol.com