አዝማሪ
መስፍን በቀለን ገልጠን ስናየው
ጌታቸው
ረዳ (Ethio Semay)
10/28/2021
በፎቶግራፉ የተመለከተው ምስል የአብይ አሕመድ እና የሻዕቢያ ፕሮፖጋንዲሰት የሆነው አዝማሪ መስፍን በቀለ ይባላል። ዛሬ ቀን ሚከተለው ዜና አነበብኩ፡ "አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገርን አፈርሳለሁ
ብሎ ከሚመጣ ማንኛውም ኃይል ለመታደግ አይደለም መዝፈን ግንባር ድረስ በመዝመት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ድምጻዊ መስፍን በቀለ ገለጸ።ድምጻዊ መስፍን እንደሚለው፤ በሥራ አጋጣሚ ነዋሪነቱን አሜሪካን አገር ቢያደርግም ከእናት አገር የሚበልጥ የለም ብሎ የቻለውን ሁሉ ሊሰጥ ሁርሶ የወታደሮች ማሠልጠኛ በመገኘት ሠልጣኝ ወታደሮችን በሙዚቃ እንዲበረታቱ ማድረጌ ትንሹ ተግባር ነው ሲልም ገልጿል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት ወታደር ልጅ ነኝ ያለው መስፍን፥ አባቱ ለእናት አገሩ ከ20 አመት በላይ በውትድርና ሙያው ሲያገለግል በካራማራ ቆስሏል፣ ደምቷልም ብሏል።
በወታደር ሕይወት ውስጥ አለማለፌ ያስቆጨኛል የሚለው ድምጻዊ መስፍን ፥አሁን የአባቴን መስዋዕትነት፣ ገድል እኔም መድገም አለብኝ ሲል ገልጿል።" ይላል ዜናው።
መዝመቱ ጥሩ ነው፤ የሚመሰገን ነው፤ የሚበረታታም ነው። ግን ይህ አዝማሪ በተፈጥሮ የተቸረው ልሳኑን በመጠቀም የአምባገነኖች አወዳሽ ሆኖ በመቀጠል ላይ መገኘቱንም ላለመርሳት እንደ እኔ ያሉ የዜጎች አስታዋሾችን ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያን ሉኣላዊ ግዛትን በአስነዋሪ ፕረሮፓጋንዳ
አዳማቂ ሆኖ ሲያሰራጨው ከነበረው ወደ አለፈው ማሕደሩ ከማለፌ በፊት አሁን እንኳ በራሱ ፌስቡኩ ላይ በቅርቡ ስለ አብይ አሕመድ የጻፈውን የሚከተሉት ሦስት የፍቅር (ልብ) ምልክቶች በአረንጓዴ፤ቢጫ እና ቀይ ቀለም የተቀቡ ምልክቶች ያጀበበትን ጽሑፍ ሰንምለከት የሚገርም ነው። ሃቀኛ ኢትዮጵያዊያንን እነ እስክንድር ነጋ አስቴር እና በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ያንገላታ፤ያስገረፈ “ደም የጠማው” አምባገነን ግለሰብ አብይን እንዲህ እያለ አወድሶታል፡
congratulations
“ኢትዮጵያዊነት አሸናፊነት ነው: ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ መልካም የስራ
ዘመን እመኝሎታለሁ!!! የተግባር ሰው !!!
እንኳን ደስ አለሽ ሀገሬ ኢትዮጵያጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የተግባር ሰው !!!
ቀጥል አድርጎም እንደገና
“ኢትዮጵያዊ አንድነታችንና እሴታችን: ይበልጥ የሚያብበት ቀጣይ መሪዎቾ እውነተኛ አገልጋይ የሚሆኑባት እና ብሎም ያአፍሪካ ጠበቃ ጭምርነታቸውን የሚያስመሰክሩበት “ታላቅ ቀን” ይሆናል ብዬ አምናለሁ።” ሲል ብዙዎቻችንን አስቀይሞናል።
ዛሬ ወደ ጦር ግምባር እዘምታለሁ አለ ተብሎ በአብይ አሕመድ የዜና ማዕከሎች እየተነገረ ያለው ዜና እኔም እንዳይቀርብኝ እዛ ሄጀ “ልሞዝቅ” ብሎ “በእኔም አይቅርብኝ ስሜት” ካልሆነ በቀር ፤ ሰንደቃላማችንን እየረከሰ ያለን መሪ እያወደሰ ስለ ሰንደቃላማ እና አገራዊ ክብር ምንነት ከእንዲህ ያሉ አዝማሪዎች አንደበት ሲወራ ያማል።
“መሪየ” “የተግባር ሰው” እያለ የሚያሞካሸው በአስነዋሪው መሪው ትዕዛዝ “ጦርነት ተክፍቶባቸው” ቃሊቲ ተወርውረው እየተደበደቡ ያሉ እነ እስክንድር “ቢሰሙ” አጥንታቸው እና ቆዳቸው ምን ያህል እንደሚያማቸው በእነሱ ጫማ ሰውነትና መንፈስ እራሳችሁን አስገቡ እና ላንዴ ገምቱት።
አዝማሪዎች፤ ገጣሚዎች፤ተዋናያን፤ሰዓሊዎች ወዘተ… አገር ሲፈርስ እንዲጠገን፤ መጥፎ መሪ ሲነግሥ ተቀባይነት እንዳይኖሮው የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው። ሆኖም የዘንድሮ ዘፋኞች ግን 30 አመት ሙሉ ጠመንጃ አነግበው ሥልጣን በተቆጣጠሩ ዕብድ ሰዎች የሚተላለፉ አገር አፍራሽ ውሳኔዎች ተቀብለው “ያንን አስፋፍተው እና አቆነጃጅተው” የዋሁን አዲስ ትውልድ እንዲቀበለው አደገኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።
የአገር አፍራሾች ማንነት ታግለው በጽናት የቆሙ እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው። ዛሬ በጥሩ ምሳሌ ተወስዶ በወርቅ ቀለም ሊመዘገብ የሚገባው የማደንቀው የኪነት ሰው አለ። “ቀልድን ተንተርሶ እያሳሳቀ
አምባገነኖችን ዕርቃናቸውን በማጋለጥ እና የማሕበረሰቡንም የደከመ ሕሊና ለማሳየት “ፍራሽ አዳሽ” በሚል ትዕይንታዊ የመድርክ በቀልድ አፍላቂነቱ የታወቀው “ተስፋሁን ከበደ” መቸም ጊዜ ኢትዮጵያ ታሪክ በወርቅ ቀለም መዝግቦ ሲያደምጠው የሚኖር ጥሩ ኢትዮጵያዊ የኪነት ሰው ነው።
በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ የሆነው የተስፈሁን ከበደ
“የመንግስት ምስረታውና የፌስቡክ መዘጋት-ፍራሽ አዳሽ-21-“
የሚለውን አስገራሚ ቀልዱን ያየ ሰው የተስፋሁን ከበደ ኪነታዊ ብቃት “ከደናቁርቱ እነ መስፍን በቀለ አለቅላቂ አዝማሪዎች” ምን ያህል አገራዊ ብቃት በረዢም የርቀት ልዩነት እንደተጓዘ ማየት ትችላላችሁ።
ኢትዮጵያ እንዲህ ያሉ “አስደማሚ” ወጣት የኪነት ሰዎችን ሰትፈጥር በአንጻሩ ደግሞ መላ ቅጥ የሌላቸው እንደ አህያ የሚያናፉ ጮክ ብለው ምድሪቱን የሚያደነቁሩ የአምባገኖች መለከቶችም ስንመለከት እጅግ እንበሳጫለን።
እነዚህ እጅግ ጥቂቶች ሲሆኑ ብዙዎቹ አዝማሪዎች ግን በማያውቁት የፖለቲካ ዋና እየዋኙ አገር በመበጥብጥ ላይ ናቸው። ከነዚህ ከአብይ አሕመድ ምንጣፍ ጎታቾች መካካል አንዱ መስፍን በቀለ መቸውንም ቢሆን “ይቅርታ ካልጠየቀ ይቀር አንለውም።
ይቅርታ የሚጠይቅም አይመስልም። ምክንያቱም እራሱ እንዲህ ሲል ግልጽ አድርጓል፡
"አንተን መደገፌ ሰሕተት ከሆነ እኔ ልክ ልሆን አልፈልግም! አብቹ ፤ካንተ ጎን ለመቆም እልፍ ምክንያቶች አሉኝ!”
ይላል አዝማሪው መስፍን በቀለ። ልጁ ምን ያህል በአብቹ ፍቅር መውደቁን ማየት ቀላል ነው።
ማሕደሩን መዝዘን ስንተቸው ፡ “በሾርት ሜሞሪ”- የምትጓዙ “ የማስታወስ ችሎታችሁ ዝግምተኛ የሆናችሁ” ዝግምተኞች “ወደ ዘመቻ አቀናለሁ” ስላለ ትንጫጩ ይሆናል። በበራዦች/በከላሾች ዝምታ የለም::
ይህ አዝማሪ
“ሳብቨርዥን” (subversion) በሚባለው የብረዛ ፕሮፓጋንዳ መሪ ተዋናይ ሆኖ ቆይቷል። ለምሳሌ ከላይ በፎቶግራፍ ያቀረብኩላችሁ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /በጣሊየን”
በ“መለስ ዜናዊ” እና በ“ፋሺሰት ሙሶሊኒ” የተቀነባበረው ከሕግ ውጭ በሃይል የተሰራውን የኢትዮጵያ ካርታ ተብየው በታዳጊ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ሕሊና ውስጥ እንዲቀረጽ ሆን ተብሎ ትውልድ በዚህ ሴራ ተቀርጾ እንዲያድግ የሚያስተምሩበትን መርዛማ የሙዚቀኞቹ
“ባንዳዊ ፕሮፓጋንዳ” በቪዲዮ ያሰራጩት ፎቶግራፍ ስትመለከቱ እኛ ይህንን ሴራ ለምንቃወም እና ለማንቀበል ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ጥቃት ነው።
ይህ የመልክኣምድር የተቀነባበረው ምስል ትኩር ብላችሁ ስትመለከቱ “ህጻናት ታዳጊዎች” በተቆረጠው “ካርታ” ፊት ለፊት ተያይዘው በመቆም በልባቸው እንዲቀረጽ የተደረገ ሴራ ነው። ይህ ያቀነባበረው ደግሞ የመስፍን በቀለ ሙዚቃ አሳታሚ “ምነው ሸዋ” የተባለ ጸረ ኢትዮጵያ አሳታሚ ድርጅት ነው። ለኛ ካርታውን ለማንቀበለው እና እየታጋልነው ላለው
ሴራ መስፍን በቀለ እና “ምነው ሸዋ” አሳታሚ ድርጅት ከሴረኞች የተረከቡትን ስለት ተቀብለው “በልባችን ላይ “ስለት ሰክተውብናል”።
በዚህ ጉዳይ “ነጭ ባንዴራ አውለብላቢዎች (ቁጥር 2)” ላይ በሰፊው ስለጻፍኩት አንብቡ። ሆኖም ባጭሩ ለማስታወስ ያክል ፡ “ሰው እንሁን” በሚለው ሙዚቃው ላይ “የሻዕቢያና የመለስ ዜናዊ
የትግል ውጤት የሆነው “የኤርትራ ካርታ” ከኢትዮጵያ “ቆራጣ መልክኣምድር” ጋር አገናኝቶ ሙሉውን ሕጋዊው የቆየው መልክኣምድራችንን የሚያሳይ ምስል በሙዚቃው “ክሊፕ” ውስጥ በመታተሙ የሻዕቢያው ታዛዥ የሆነው አብይ አሕመድና ሻዕቢያዎች ስለተቆጡዋቸው “ምነው ሻዋ” የሚባለው አሳታሚ (ስዕሉ ላይ ይቅርታ የጠየቀበትን በፌስቡኩ የለጠፈው) በስሕተት ስለሆነ ታላቅ ይቅርታ ይደረግልኝ ሲል “ምነው ሸዋ እና አዝማሪው በጋራ” አሳፋሪ
መግለጫ በማውጣት የኤርትራ ባንዳዎችን ይቅርታ ጠይቋል።
እነዚህ ነጋዴዎች እና የኪነት ሰዎች፤ የማሕበረሰቡን የአዲሱ ትውልድ ሕሊናን በመመረዝ ሕዝቡ አገራዊ “”ቁጭት፤ እልሀ እና ጀግንነቱ” እንዲጥልና “ቁጭት” እንዳይሰማው በመመረዝ “ተሸናፊነትን” በመስበክ በተለያዩ መልኮች “ተንበርካኪነትን”
እንዲቀጥሉ “ባህልን፤ ሰንደቃላማን፤ አገራዊ ክልልን፤ ታሪክን፤ ጽናትን” የፖለቲካው ክርክር በሚያበላሽ መልኩ ከሴረኞች ተረክበው በመስራት ላይ ናቸው።
“የሰላም መሪ”
የሚለውን አሳፋሪ ዘፈኑን እንዳለ ሆኖ የቀድሞ ሠራዊት አባል ልጅ ነኝ የሚለን ይህ አዝማሪ “ለሻዕቢያ ባንዴራ” አለቅላቂነቱን ከመጠን በላይ “ተደጋግሞ” ይቅርታ ሳይጠይቅ ያሳያው ፕሮፓጋንዳ ስንምለከት ያውም “የደርግ ካርታ” እያሉ “አብደው” ከሚያብዱት ዕብዶች ጋር አብዶ ስመለከተው፤ ልጁ “ከወታደር ልጅ የተወለደ አይመስልም”። ወላጁ የተሰውለት ብሔራዊ ክብር ለሻዕቢያ አጎብድዶ ስናይ “አሳዛኝ ትውልድ”መድረሳችን የሚገርም ነው። ችግሩ እንዲህ ያሉትን አዝማሪዎች ሙዚቃቸውን እየገዙ የሚያጅብዋቸው መኖራቸውንም የሕዝባችን ንቃተ ሕሊና ደረጃ ምን ላይ እንዳለ ይነግረናል።
ጽሑፌን በሚከተለው የማይረሳ እውነታ ልቋጭ።
ዛሬ በኢትዮ 360 ዩቱብ ቴ/ቪ ወይይት 10/26/21 (በፈረንጅአቆጣጠር) ሃብታሙ፤ ኤፍሬም እና ብሩክ ሲወያዩ፡ የሰማሁት አስገራሚ እውነታ ;
በሃብታሙ አያሌው የአዲስ አባባ ሕዝብ “በፖለቲካው ሱታፌ መደንዘዝ”
በወያኔ ዘመን አጫወቱኝ ያላውን የአንድ አዛውንት አባት ማስተዋል እንዲህ አሉኝ ይላል
መጀመሪያ ሃብታሙ ከታች ለተጠቀሰው መደምደሚያ መነሾ የሆነውን እንዲህ ይላል።
“አዲስ አበባ ላይ አስታውሳለሁ አንድ
ትልቅ ሰው ናቸው እና ነገሩ ያኔ ትግል በነበረበት ጊዜ ነው። ሕዝቡ ምን ነካው? ሰልፍ ለመውጣት፤ምብቱ እንዲጠይቅ ለማድረግ ፤እኛ የህይወት መስዋእትነት የሚያስጠይቅ ጉዳይ ከፍለን ‘ሁለት ቀን ሦስት ቀን ቀድመን አዲስ አበባ ከተሞች ሁሉ ዞረን ቀስቅሰን እጁን ይዘን ነግረን እኮ ነው የምናስወጣው፦ ሕዝብ እምቢ ብሎ እራሱ መውጣት ነበረበት፤መሪ መውለድ ነበረበት፡ ሕዝቡ ምን ሆኖ ነው እንዲህ የሆነው? ብለን ተወያየን፤ ሰልፍ የሚወጣም ከሆነ በሩቅ ሆኖ ኮፍያ አድርጎ መነጽር አድርጎ በሩቅ “ይተኮሳል? አይተኮስም?” እያለ በማዶ የሚያማትር ነው የነበረው (አሁንማ እርሳው)።....
....አንድ የፓርቲ አባል የነበረ ሰው ነበር: መንግሥት ለሰልፉ ፈቃድ ከሰጠ “ድብደባ እስራት” አይኖርምና “ክራባት አድርጎ” ሮጦ ከፊት ይሰለፋል፤ መንግሥት ይህንን ሰልፍ አልፈቀድኩም ካለ፤ እኛ ደግሞ ማነው ፈቃድ ያደረግህ ብለን እንወጣለን ብለን በወጣንበት ቀን አርሱ ወይ “አሞኛል ብሎ ይተኛል፤ወይንም ናዝሬት ነኝ አዋሳ ነኝ ያለሁት ይልሃል። እና ይህ ሁሉ መከታና ግፍ በሕዝቡ ላይ እየደረሰ ሕዝቡ እንዴት አይነሳም? ምን ነካው ብለን ካንድ ትልቅ ሰው ናቸው ስንነጋገር፡ ምን አሉኝ መሰለህ፤ ...
“… ስማ አሁን ሕዝቡ ‘ወንድ ወንዱን’ ነገ ቀበሌ መጥተህ ተሰልፈህ “ሽንት መሽኒያህ ይቆረጣል” ብሎ መንግሥት ቢወስን ፡ ‘እንዴት ነው የምትቆርጠው? ምን መብት ቢኖርህ ነው? ብሎ የሚጠየቅ ሰው ሳይሆን የሚኖር የሚመስለኝ “እባካችሁ ሥራ አለብኝና እንዳይረድፍብኝ ተሎ ቁረጡኝና ልሂድ ብሎ የሚል ሕዝብ ነው ያለው ይመስለኛል” ብለው አጫወቱኝ። ያለውን አስገራሚና እውነታ ባለው አባባል ጽሑፌን ልደምድም።
ሼር አድርጉ ሌላውን አንቁበት!
በሰላም እንሰንብት!
ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)