Friday, June 8, 2018

ባድሜ እና ድምጻችን ክፍል ሁለት ጌታቸው ረዳ Ethiopian seamy


News Update:



የአልጄርስ ስምምነት በቀድሞ የኢትዮጵያ /ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና የኤርትራው ፕረዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፊርማ የፀደቀው ታህሳስ 03/1993 . (... 12th December, 2000) መሆኑን ከላይ ካለው የስምምነቱ ሰነድ መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጂ፣ የአልጄርስ ስምምነትን በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቆ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ የታወጀው ህዳር 29/1993 . (... 8th December, 2000) ነው። በመሆኑም የሰላም ስምምነቱ አልጄርስ ላይ ከመፈረሙ አራት (4) ቀናት በፊት የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፅድቆት ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል። የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 55(4) ምክር ቤቱየህግ አስፈፃሚው አካል የሚዋዋላቸውን ዓለም-አቀፍ ስምምነቶች ያፀድቃልየሚል ቢሆንም የአልጄርስ ስምምነት ከመፈረሙ በፊት በምክር ቤቱ ፀድቆ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታውጇል።


ባድሜ እና ድምጻችን ክፍል ሁለት
ጌታቸው ረዳ Ethiopian semay

ባድሜ እና ድምጻችን ክፍል ሁለት
ጌታቸው ረዳ Ethiopian seamy
The two Eritreans conspiring against Ethiopia the third is the Arab enemy of Ethiopia congratulating the two Eritreans for hurting Ethiopia.


ከላይ የሚታየው ፎቶግራፍ ያለ ምንም ተጠያቂነት የሕግ ፍራቻ ሳይኖራቸው የትግራይ ወያኔዎች ባድሜ እና ፀሮና ላይ ለጥይት የማገዱት ኢትዮጵያዊ የደም አምባ ያፈሰሰው ስቃዩ ከንቱ በመቅረቱ አቤቱታው ለፈጣሪ እያቀረበ ነው።ተጠየቂነት የሌለው የ70 ሺሕ ሕዝብ ህይወት እና ቤተሰብ ጭምር ያጠቃለለ ስቃይ እስከዚችው ቀን ድረስ ተጠያቂ የሆኑ የትግሬ መሪዎች እስከዚችው ደቂቃ ድረስ የሉም። ለምን ? መልሱ ግልጽ ነው። አሁንም ስልጣን ላይ ናቸዋ! እነ አብይ እነ ሳሞራ እነ ሰዓረ እርስ በርስ ሲሸላለሙና ሲመጋገሱ የኔ ብጤ ድሃው ጥይት በዓይኑ ገብቶበት ነፃ ያወጣውን የትግራይ መሬት ለኤርትራኖች ሸልመዉታል።

(ከላይ ያሉት ሁለት ኤርትራኖች ከመካከላቸው አረባዊው አልጄሪያዊው የኢትዮጵያ ጠላት ቡታፈሊካ ኢትዮጵያን በማጥቃታቸው እያመሰገናቸው ነው። በዜጎቻችን ደም የነገዱበት የወያነ ትግራይ እና የሻዕቢያ መሪዎች ከነተባባሪዎቻቸው ጊዜው ይረዝማል እንጂ አንድ ኢትዮጵያዊ ወደ መድረክ ሥልጣን ሲመጣ አንድ ቀን ለፍርድ ይቀርባሉ። በእነዚህ ወገኖች ደም ተቀልዶ ነው ዛሬ 17 የትግራይ ገጠሮች ሕዝብ ከቀዬው ተባርሮ ለኤርትራ አንዲሰጥ ወስነናል! ሰላም ያመጣል! እየተባለ ያለው። የዜጋ ስቃይ እና ደም በከንቱ የምትቀልዱ የትግሬ አራዊቶች አንድ ቀን እንደ አለቃችሁ እንደ መለስ ዜናዊ  ሳታስቡት አምላክ ያስወግዳችሗል! )በቅርቡም አንዱ በፈጣሪ ሃይል ይነጠቃል! ቃሌ ነው እመኑኝ!  የትግራይ ሕዝብ ዛሬም መሪዎቹ እንዲያስወግድ ጥሪ አቀርባለሁ። በየገጠሩ ያሉት ተፈናቃዮች “አምቢታቸውን’ ማሰማት መቀጠል አለባቸው።

ይህ ክፍል በጀመሪያው ክፍል በ6/6/18 ለትግራይ ታጋዮችና ሕዝብ ተቃውሞ እንዲያደርጉ ያስተላለፍኩት ጥሪ. ቀጣይ ክፍል ነው። ባድሜንና ኢሮብን ለኤርትራ ይሰጣል የተባለው ኢ ፍትሓዊ ውሳኔ እና ሴራን አስመልከቼ ያደረግኩት ጥሪ የአጋሜ አውራጃ አርበኛው የኢሮብ ሕዝብ ጥሪየን ተቀብሎ ሕዝባዊ ስብሰባ በማካሄድ “የወያኔዎችን ውሳኔ ውድቅ አድርጎ አንቀበልም ብሏል” ሌሎች ገጠሮችም በግል ተጠይቀው ውሳኔውን አንቀበልም ብለዋል።አንኳን ደስ አለን! ጥሪው እና አንቅስቃሴው ይቀጥላል!! በርቱ!

ወያነ ትግራይም ይህንን ተቃውሞ ስለፈራ እንደ አመሉ መዋሸት ፤መዝረጥረጥ፤ ሕዝብን ማታለል ጀምሯል። አሽከሮቹም አምነውታል። ትናንት ድርጅቱ አወጣው የተባለው የወያኔው ድረገጽ “ዓይጋ-ፎረም” እንደ ዜና ለጥፎታል። ዛሬም የውሸታሙ የስዩም መስፍን የድሮ ማደናገሪያ “ባድሜ ለትግራይ ተሰጠች” ውሸቱን የሚመስል  በዚህ መግለጫ ተደግሟል- እንዲህ ሲል፡-

ህወሓትም በውሳኔዎቹ እንዳለ እንደ ማዕቀፍ በመነጋገር  ዘላቂ መፍትሄ
ለማግኘት በመስራት መሰረታዊ የትግራይን ህዝብ ጥቅም የሚያረጋግጥ መሆኑንም በመግለጫው አንስቷል። ከዚህ አንጻርም ህወሓት የትግራይን ህዝብ ጥቅም በሚያሳጡ ጉዳዮች ላይ እጁን እንደማያስገባ በድጋሚ ማረጋገጥ ይፈልጋል።” (በኢትዮ- ኤርትራ ጉዳይ ላይ የተላለፈው ውሳኔ የሃገራችን ህዝቦች ወንድማማችነት ወደ ነበረበት ለመመለስ ያለመ ነው - ህወሓት) ህወሓት መግለጫ አወጣ የተባለው የተጠቀሰ /ቀን/ቁጥር/ዓ.ም የለውም። 

ይሁን እንጂ መግለጫው ዛሬም እንደለመደው ግልጽነት ያጣ መግለጫ ሰጥቷል። ባገሪቱ የዜና ማሰራጫ ከመንግሥት ተሰጠ የሚለው ዜና ጋር የሚጋጭ መግለጫ ነው።

የ ኢ ቢ ሲ ዜና መግለጫም ሆነ የ ኢ ሕ አ ዴግ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር የሆነው አሕመድ ሽሌ የሚለው እንዲህ ብሏል፡-

 “የ ኢ ሕ አ ዴ ግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና ኢሕአዴግ መንግስት መግለጫ የአልጄሪስ ስምምነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያለምንም ማመንታት ሙሉ በሙሉ ተግባረዊ እንዲሆን እና እንዲፈጸም ተወስናል። ለዚህም ለሁለቱም አገሮች ብሎም ለምስራቅ አፍሪቃ ሰላም አስተዋጽኦ ስላለው ነው።” ብሏል ።

ይኼ ነው የተላለፈው መግለጫ። አይደለም እንዴ? አሁን ግን ወያኔ የሚቀባዥረው የሕዝብን ቁጣ ለማለሳለስ የደበቀው ሌላኛው ምላሱ ይዞ ብቅ በማለት “እንደ ማዕቀፍ በመነጋገር ሲል ሕዝብን ለማደናገር እየሞከረ ነው። አዲስ አበባ የተነገረው ተቃራኒ ነው ትግራይ ውስጥ እየነገረን ያለው ደግም “እንደ ማዕቀፍ በመነጋገር” እያለ ማደናገር ጀምሯል። ማደናገሪያ መዝገበ ቃላት ሲፈልግ አድሮ  ማዕቀፍ” የምትል ማደናገሪያ ይዞ ብቅ አለ። ድሮ “መነጋጋር” የሚል ነበር። አሁን ደግሞ እንደ ማዕቀፍ በመነጋገር”    ይለናል። ያለ ማመንታት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን እና እንዲፈጸም ተወስኗል፡ እያለን በሌላኛው ጉንጩ ደግሞ “እንደ ማዕቀፍ በመነጋገር” እያለ ተቃውሞውን ለማለሳሰለስ ስልት ይዞ መጥቷል።

ቆንጅት ስጦታው የተባለች ጸሐፊ የሰጠችን ዜና ግን “ሰብ ወደብ ላይ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል የጦር ሰፈር ሊገነባ ነው።” June 7, 2018 በሚል ርዕስ


በአቡዳቢ የኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ መወያየታቸውን ተከትሎ በሀገራቱ ዙሪያ አዳዲስ ለውጦችን በማየት ላይ እንገኛለን።  ባድመን ጨምሮ አስራ ሰባት አወዛጋቢ የነበሩትን ወረዳዎች ለኤርትራ ለማስረከብ የተስማማች ሲሆን ኤርትራ በበኩሏ የአሰብ ወደብን ለኢትዮጵያ  በክፍያ እንድትጠቀምበት እንዲሁም የባህር ሀይል ጦር ሰፈር እንድትገነባበት ተስማምተዋል በስምምነቱ መሠረት ባህር ኃይሉ በአከባቢው በሚገኘው ኢምሬት የጦር ኃይል ቁጥጥር እንዲያደርግ ዋስትና ከኤርትራ አግኝቷል።” ሰትል መዘገቧ ይታዋሰል።

የትግራይን ምስኪን ድሃ ሕዝብ እንደ አራዊት ከመኖሪያው በማባረር/ በማስወጣት/ ዓሰብን ለመከራየት በሚል ሕዝብን እንደ መለወጫ ዕቃ አድርገው እንደጓጉ ስንገነዘብ ስለ 17 አወዛጋቢ ገጠሮች ሕዝብ ኗሪዎች  ሳይሆን ትኩረቱ አብይ አና አማካሪዎቹ የሆኑት “ኤርትሮ-ወያኔዎች” ስለ “ኢንቨስትምነት እና ዝና” እየሮጡ እንደሆኑ ከዜናው ልንረዳ ችለናል።  ስለ ሆነም ትግሉ ረዢም እና መራራ ቢሆንም ውሳኔው ሕዝብ ስላላማከረ  ወደ ከፋ ግጭት አንደሚያመራ ዛሬም ደግመን እያስጠነቀቅን ነው።

በዚህ ትችት ሁለት ታዋቂ ሰዎችን እተቻለሁ። ፕሮፌሰር ታደሰ መድሃንየ የተባለ የአጋመ አውራጃ ተወላጅ ሲሆን ሌላው ስዩም ተሾመ የተባለ አምቦ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ስለ ባድሜ የሰጡትን መወገዝ ያለበት አስተያየታቸውን እንመለከታለን።

እንደሚታወሰው  በ “ወያኔ-ኦፒዲኤው” ሌ/ኮለኔል አብይ አሕመድ የተመራ ባድሜን ለኤርትራ አሳልፎ ስለመስጠት አስመልከቶ ብዙ ዜጎች አልተደሰቱበትም ፤ ጥቂት የወያነ አቃጣሪዎች ግን ወድደውታል/
ተቀብለውታል። የወደዱትም “አለቆቻቸው “ሰላም ያመጣል ብለው ሲሉዋቸው” እነሱም እንደ ገደል ማሚቶ ማስተጋባት ነውና ውሳኔውን ተቀብለውታል።ይህ የሁለት ሴረኞች (ወያኔ/ሻዕቢያ) ስምምነት አስመለክቶ ከመጀመሪያውኑ በኤርትራዊው መለስ ዜናዊ የተመራው “የአልጄሪስ ስምምነት ሴራ ”ሕግ የጣሰ እና ሕጋዊነት እንደሌላው” ብዙ የሕግ ባለሞያዎች ተችተውበታል።

አሁን ስልጣን ላይ ያለው የኦሮሞ እና የትግሬ ፓርቲ ቡድን በማያገባው እየገባ ሲፈተፍት ግጭት መፍጠሩ አይቀሬ ነው። ከወያኔ ወደ ወያኔ የሚርመጠመጥ “ኮሰመቲክ/ጥገናዊ” ቅብ እየቀባ ተሸናፊው ተቃዋሚ እልል እያሰኘ እስከ ወገብ አንገታቸው እያስደነሳቸው ነው። በመንፈስም በአካልም የተሸነፈ ተቃዋሚ መነሻቸው ቢገባኝም፤ በታሪክ ፊት ግን አሽቃባጮቹ ተቃዋሚዎች አፈርኩላቸው (ረሳሁት ይቅርታ አዲስ ሰም አላቸው ‘ተፎካካሪዎች”  ማለቴ ነው።) ግራም ቀኝ ነፈሰ አብይ  የአማራ እናቶች (ለሴቶች እናቶች አስባለሁ ይላል በአፉ!!) እያየተፈናቀሉ እያለቀሱ እየተደበደቡ ስላሉት እናት አማራዎች ለማስቆም ያደረገው አንድም ነገር አላየሁም። የዘር ማጽዳት ዘመቻ አስቸኳይ አዋጅ አውጆ ማስቆም ያልቻለ መሪ እና ቡድን ለኔ መንግሥት ብየ አልቀበለውም! ኮስመቲከ/ጥገናዊ ስርዓት ሕጋዊነት ስለሌለው አሽቃባጭ ሁሉ ማንቋለጣችሁን አቁሙ!።

ባራክ ኦቦማ መሳዩ ሌ/ኮለኔል አብይ አሕመድ በኤርትራኖቹ የሚመራው ህወሓት ተገፋፍቶ እንኳን ባድሜ የሰጠውን ቀርቶ በመለስ ዜናዊ ለኢሳያስ የተሰጠው ቀይ ባሕርን አሳልፎ የሰጠውን ስምምነት እንኳ ሕጋዊነት እንደሌለው እና ወኪሎቹም ሕጋዊ እንደልሆኑ እና ሆን ብለው ኢትዮጵያን ለመጉዳት የተነሱ በጉልበት ስልጣን ይዘው ‘ለሌላ’ ወገን በማዳላታቸው ሕጋዊነት ስለሌላቸው “ሕጋዊ መንግስት” ቦታውን ሲረከብ በተባበሩት መንግስታት ሕግ መሰረት ሊያፈርሰው እንደሚችል ፕሮፌሰር ቶካላ ወ/ሓጎስ የተባበሩት ሕግ ጠቅሰው ገልጸውታል። ያንን በዝርዝር ለመረዳት

“..the decision of the Boundary Commission, is invalid and should never be the basis of any relationship between Ethiopia and “Eritrea” at any future time.” (Ethiopia and “Eritrea” - Antagonists in Perpetuity: Cohen, Shinn, and witless Diasporas to the Rescue?) Tecola W. Hagos*) አንብቡት።አሁን ያለው ሽር ጉድ በሕግ ፊት ምንም ዋገ የለውም።

በዚህ መልክ ወያኔዎች ባድመን እና 17 የትግራይ ገጠሮችን አሳልፎ ለኢሳያስ መስጠት አዲስ አደለም። በሲአይኤም በወያኔም የተደረገ ሻጥር ነው። ዛሬም ባድመ ይሰጥ ሲባል አሜሪካዊው ጃፓናዊው “ሰላዩ” ያማሜቶ በሁለቱም ከተሞች ሄዶ አስፈራርቶ ባድሜን ለኤርትራ እንዲሰጥ ውሳኔ እንዲያሳልፍ አድርጓል። በኤርትራኖች የተደገፈው ቪዥን ኢትዮጵያ የተባለውንም እነ ካሳ ከበደ “ሽንጤን ገትሬ” ስለ ኢሳያስ ለኢትዮጵያ በጎ አሳቢነት እከራከራለሁ የሚሉትንም ጀሮ ጠቢዎች  በሕዝብ ላይ በተቀነባበረ የተለያዩ ማዕዘኖች አንዱ ዜራ ስለሆነ በሰላም ስም ከተለያዩ ማዕዝናት የሚወረውሩት ቀስቶች ለዚህ አብቆቶናል።

አሁን የአልጄሪሱ ስምምነት አውን ለማድረግ ቀስ በቀስ በር ለመክፈት የጀመረው እንዲህ በሚል ነበር፦ Herman Cohen Time to Bring Eritrea in from the Cold”] በሚል ርዕስ እና  David Shinn የተባለው የኦጋዴን ነፃ አውጪ ወዳጅ ደግሞ እንዲህ ይላል  [“Time to Bring Eritrea in from the Cold (But It’s Harder than It Sounds)”] for normalization of relationship between Ethiopia and Eritrea” ይላል።

ኢሳያስን ከበሮዶው ክፍል እናስወጣው የሚሉን ሰላዮቹ እነ ኮኸን፤ሼን ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ “ሁለቱም ስርዓቶች’ ሳይለወጡ “ሕዝብ ለሕዝብ እያሉ” “የእውቀታቸው ማሳያ ባዛር/ አዳራሽ” በማድረግ እነ መድሃንየ ታደሰ እና የመሳሰሉ የዚሁ የባዕዳን እጅ ያለበት ሴራ እየሞረዱት እንደሆነ ከሚናገሩት ንግግር መገመት ይቻላል። በዚህ መልክ በተለያዩ ቦታዎች ባድሜ ከመሰጠቱ በፊት ሕዝቡ አዲሱን ለጆሮ የማይጥም ነጎድጓድ እንዲለማመደው የማለሳለስ ስራ ተሰርቷል ማለት ነው።

ኤርትራን ነፃ ለማውጣት እና ባሕሮቻችን ጥርቅም አድርጎ ለኢትዮጵያ ለመዝጋት የታገለው የትግሬው ወያነ ትግራይ ነው።ዛሬም ባድሜ ሰጥቻለሁ የሚለው ያው ወያነ ትግራይ ነው (ወየነ ኤርትራ ቢሉት ጥሩ ነበር ከተግባራቸው ጋር አብሮ ስለሚሄድ)። ሕዝብ ለሕብ ምን ምናመን የሚባል ሕዝብ መቸውኑ ወስኖ አያውቅም በጥሉም በወዳጅነቱም የለበትም; ሑሉም በስርዐት መሪዎች የተከሰቱ ጣጣዎች ናቸው። ስርዐቶቹን ሳታፈርስ ሕዝብ ብታነጋግር ባታነጋግር ለውጥ የለውም።ሕዝብ ለሕዝብ ብሎ ነገር ፖለቲካው ሳይፈታ የሚደረግ ውይይት ትርፉ ለሊሂቃን የመጫወቻ አዳራሽ እና መዝናኛ ሆኖ  ነው የሚቀረው።

አሳፋሪ ያደረገው እንቆቁልሽ ግን የወላጆቻቸውን ርስትና ድምበር እንዲከበር የፈሰሰበትን የደም መሬት ረግጠው ለክተው ከኤርትራኖች ጋር ወግነው እልል እያሉ ዛሬም በማዕቀፍ/በመነጋገር.በምንተስ በምንት እያሉ ለወያኔዎች የሚያንጨበጭቡ ትግሬዎችን ዛሬም ይገርሙኛል። እነ መለስ የትግራይ ሕዝብ ተከታይ እና ድጋፍ ባያገኙ ባሕርን ወደብን የሚያክል ትልቅ ጉዳይ አሳልፈው ዛሬ ለዓረቦች አይሮፕላን እና የሮኬት ማስወንጨፊያ እንዲሆን ያለ ምንም ስጋት አይፈጽሙትም ነበር።

ወደ ትልቁ ምሁር ወደ ትግሬው ፕሮፌሰር መድሃንየ ታደሰ ከመሄዳችን በፊት አምቦ ዩኒቨርሲቲ በተባለው ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምር ስዩም ተሾመ የተባለ ስለ እኔ እና መሰሎቼ የጻፈውን እንመልከት እና ወደ መድሃኔ እናልፋለን።

ስዩም ተሾመ ማለት ካሁን በፊት የወያኔ አምላኪ የሆነው የሰሜን አሜሪካ የወያኔ ትግሬዎች ሊቀመንብር የሆነው ሰለሞን አሉላ የተባለው በፌስ ቡኩ መምህር ስዩም ተሾመ ላይ “እርምጃ ይወሰድበት” እያለ የወያኔ መሪዎችን ሲወተውት እንደነበረ ራሱ ስዩም ተሾመ ይህንን አስመልክቶ አፈትልኮ የወጣ መረጃ፦ “ስዩም ተሾመን ጨምሮ ሁለት ፀሃፊዎችን ለመግደል ታቅዷል!” ጥቅምት 30, 2017 Seyoum Teshome Amazing Story, ነፃነት, Democracy በሚል ርዕስ ያስነበበን ነው።
ከከፍተኛ የደህንነት ኃላፊዎች አፈትልኮ ወጣየተባለው መረጃ ለመጀመሪያ ግዜ የደረሰኝ ባለፈው ሳምንት ሲሆን የስልክ ቃለ ምልልስ ይህን ማያያዣ (Link) በመጫን ማዳመጥ ይቻላል። በማለት ሰፋ ባለ ሃተታ ከሰጠ በሗላ
ከላይ ከተጠቀሰው ግለሰብ በተጨማሪ፣ ለደህንነት ሰዎች ቅርበት ያላቸው ሌሎች ጓደኞቼስዩም ተሾመ መወገድ አለበትየሚለው ውሳኔ መተላለፉን እንደሰሙ በመጠቆም ስጋታቸውን ገልፀውልኛል።

ይህን ከመስማቴ በፊት፣ ትላንት ጠዋት ብዙ የፌስቡክ ጏደኞቼ ከአሉላ_ሰለሞን ገፅ ላይ የተወሰደ ምስል ልከውልኝ ነበር። ከታች እንደሚታየው አቶ አሉላ ሰለሞን እኔ እንድታሰር በይፋ ጥሪ አቅርቧል። ውስጥ አዋቂውከአሉላ ሰለሞን ጋር እንዴት ስዩም ተሾመ ይወገድ ትላለህብሎ ለረጅም ሰዓት እንደተከራከረው በመግለፅ ከፅሁፉ በስተጀርባ ያለውን እውነታ፣ በተለይ የአቶ አሉላ ሰለሞን የፖለቲካ አቋም በግልፅ ያሳያል፡፡ በዚህ መሠረት፣ አቶ አሉላ ሰለሞን እንደ እኔ የተለየ አቋምና አመለካከት የሚያራምዱ ግለሰቦችን ያለምንም ጥፋትና ማስረጃ እንዲታሰሩ በይፋ ጥሪ ከማቅረብ ጀምሮ ያለፍርድመገደል አለባቸውብሎ እንደሚከራከር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም ህግ በሰፈነበት አሜሪካን ሀገር ተቀምጦ በኢትዮጲያኖች ላይ የሽብር ወንጀል እንዲፈፀም ጥሪና ቅስቀሳ እያደረገ እንደመሆኑ በህግ ሊጠየቅ ይገባል።….


በማለት አሉላ ሰለሞን በኔ ላይ እርምጃ እንዲወሰድብኝ የሚከተለውን መንግሥት ወትውቷል።”  ሲል ስዩም ተሾመ ስጋቱን የገለጸ ነው።
 ይህንን በሰፊው የገለጽኩላችሁ የተለያየ አስተያየት ስላለው አንድ ዜጋ እንዲወገድ የሚወተውቱ ትግሬዎች እንዳሉ እና ወያኔዎችም የፈለጉት ውሳኔ ሲያሰልፉ እንደዚህ ያሉት ተከታዮችም ውሳኔውን እንዲያከብሩት ያላቸው የጋራ እከከኝ ልከክህ ሰምምነት ነው። በነገራችን ላይ አሉላ ሰለሞን የተባለው ወጣት ቪ ኦ ኤ ትግርኛ ላይ ቀርቦ የባድሜን አና የመሳሰሉትን ለኤርትራ መሰጠቱ ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ደግፏል (ከነሱ ዓይነቶቹም የሚጠበቅ ባህሪ ነው)።
ወደ ስዩም ተሾም እንመለስ፡

 ባጭሩ ስዩም ተሾመ ማለት የአህያ ቄራ በኢትዮጵያ እንዲቋቋም ደግፎ የተከረታከረ ሰው ነው። እኔ አይደለሁም ካለም ማስተባባያ መስጠት ይችላል። ቆሻሻ በልቶ ተርቦ ከመሞት አህያ በልቶ መኖር በምን እድላችን የሚል ዓይነት ክርክር ያቀረበ በጣም አስገራሚ ሰው ነው።

ዛሬ ደግሞ
እነ እንቶኔ የድንጋይ ፍትፍት የሞላትን ባድመሄደች፥ ቀረችእያሉ ይቃዣሉ፡፡ሲል ወርፎናል። መሬቱም የድንጋይ ፍትፍት ብሎታል። ስላላየው እና ስላላወቀው አልይዝበትም። ሆኖም የድንጋይ ፍትፍትም ይሁን ለም ወይንም ወርቅ እና ዱር እኛን ያሳሰበን ዓለም ሲፈጠር እዛው የኖሮው ሕዝባችን ውጣ ተብሎ ወይንም ዜግነትህን ቀይር ተብሎ አዲስ ዜግነት ወይንም አዲስ ህይወት እና መፈናቀል እንዲደርስበት ለማየት ውስጣችን ስለማይቀበለው ነው እንጂ አንተ እንደምትለው “ፍትፍት ድንጋዩን” አይደለም። ምሁራኖቹ እነ ስዩም ተሾመ ከሩቅ ከተማ ሆነው ባንዲት ሹል ብዕር ስለ ድንጋይ ፍትፍት ክምር እንጂ ስለ እዛው ያለው ኗሪ ፍጡር መፈናቀል አልታያቸውም። ሆኖም እነዚህ ምሁራን ምን ያድርጉ? _ እየበደሉን ያሉት የኛዎቹ ከሃዲ ባንዳዎች ናቸው ለዘሂህ ሁሉ ትችት እና ስድብ እያጋለጡን ያሉት።

እንዲህ ያሉ ምሁራን በምን መንገድ ቢተቹ ይሻላቸዋል የሚል ጥያቄ ብናቀርብ የሚመቻቸው ትችት የለም። ሰድበናቸዋል፤ አስተምረናቸዋል፤ ሰህተታቸውን ነግረናቸዋል….መታመር አይችሉም። እውነት ከሆነ ካለይ እንዳነበብኩት- አንዴ የኦነግ ባንዴራ ሕጋዊነት ይሰብካሉ አንዴ ደግሞ  እገሌ አርበኛ ነጻ አውጪ ጀግና ይላሉ….የማይዘባርቁት ጉድ የለም።

ስለ እነዚህ በቁማቸው ስለበከቱትና ስለ በሰበሱት ምሁራኖቻችን ብዙ ብለናል። በተለይ ዩኒቨርሲ ውስጥ እናስተምራለን የሚሉ የዘመኑ ወጣት ምሁራን የባሰባቸው የበሰበሱ ናቸው። ዛሬም ታጥቦ ጭቃ ናቸው። አንዳርጋቸው ጽጌን የነጻነት አርበኛ ፤የሰው ልጆች መብት አክባሪ ጀግና….. እያሉ አንዳንዶቹ “ኔልሰን ማንዴላ” ሲሉት አንዳንዶቹ እንደ ቤተክርትያን እግሩ ላይ ወድቀው እየተሳለሙ ወደ “እምየ ምኒሊክነት” ለውጠውታል። በየ ዩኒቨርሲቲው የሚያስተምሩት ስለ ሕዝብ መፈናቀል ሳይሆን ስለተሰዋው 70 ሺሕ ኢትዮጵያዊ ስለ ህጋዊ እና ሕገ ወጥ አልጀሪስ ስምምነት ሳይሆን የሚያስተምሩት እነ እንቶኔ የድንጋይ ፍትፍት የሞላትን ባድመሄደች፥ ቀረችእያሉ ይቃዣሉ፡፡እያሉ በየተቋማቱ ወጣቱን ሲያጥቡት ይውላሉ። እነኚህ ናቸው የኛ ምሁራን።

አሁን ወደ መድሃንየ ታደሰ።

መድሃነ ታደሰ የምስራቅ አፍሪቃ (ቀንድ) የፖቲካ ተንታኝ ነው። ይህ ወጣት ምሁርነቱ አያጠራጥርም። ግን እንዲህ ያሉ ምሁራን ደግሞ ባይማሩ ይሻል ነበር። መድሃኔ ባለፈው በወያኔ (EBC) TV ቀርቦ የሰጠው ቃለ መጠይቅ በውሉ መሰረት ባድሜ መስጠት “በአካባቢው የቆመው የኢትዮጵያ የምጣኔ ሓብት ዕድገት ለማንሰራራት ይረዳል። ሰላም በሁለቱም አገሮች ይመጣል….” ወዘተ ወዘተ…..እያለ ሲሰብክ አድምጬው እንደዚህ ዓይነቶቹ ምሁራን ለአገራችን ምንም የማይረቡ እንደሆኑ ነው ከነበረኝ እምነት መልሶ ነው የጨመረብኝ።

መጀመሪያ ነገር ኢሳያስን ባድሜን ለመውረር ያነሳሳው ‘ባድሜ’ ስለፈለገ አይደለም። እራሱ መድሃንየም እንዲህ ሲል ጽፎታል፡

“የኤርትራን ታሪክና ፖለቲካ ነጣጥሎ ማየቱ ግጭቱን አስመልክቶ በወቅቱ ለተፈጠረው ውዥምብር ምክንያት ነው ብሎ ጸሐፊው ያምናል።” (መድሀኔ ታደሰ የኢትዮጵያ ኤርትራ ጦርነት የግጭቱ መነሻና መድረሻ- ገጽ 5)
ይቀጥልና
“ የትግረኛ ተናጋሪዎች ሁኔታ ኤርትራዊ (የተሳሳተ) ማንነትን ኤርትራዊ ብሔረተኘነትን እና የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ተፈጠሮና የፖለቲካ ባህሪይን (የኤርትራ ውስጥ ችግር በአግባቡ ካልተመረመረ የጦርነቱን ኢኮኖሚያዊ አንደምታ እንካን መረዳት ያስቸግራል። ገጽ7 …….(መስመር የተጨመረ)

ኤርትራውያን በክልሉ የሚኖራቸውን ሚና በተመለከተ የያዙት ጭፍን ፍላጎት ነው።… የኤርትራ መሪዎች በተደጋጋሚ ‘ለአፍሪካ አህጉር አመራር የመስጠት ፕሮጀክት አላቸው…..ኤርትራ ልዩ ናት የሚለው ልክፍት በኤርትራ የውጭ ፖሊሲ ውስጥ በግልፅ መታየቱም አያስገርምም። ገጽ 142-43) የተሳሳተ የኤርትራውያን የራስ ምስል ብዙዎቹ ኤርትራውያን በፖለቲካ፤በርዕዮተ ዓለምና በባህል ወዘተ እንዳያድጉ አድረጓቸዋል (ገጽ131) መድሃኒየ ታደሰ (ዘኒ ከማሁ)

እንዲህ ከሆነ፤
ይህ የተሳሳተና የተጋነነ የኤርትራውያን የራስ ምስል ዛሬም እቦታው ላይ እያለ ኢትዮጵያን ተሻግሮ አፍሪካን በሞላ የሚሸፍን ፕሮጀክት አለን ብለው በሚያምኑ ኤርትራውያን ስልጣን ላይ ሳይነሱ እንዴት ሰላም ሊመጣ እንደሚችል መደሃኒየ ሳይነግረን የአልጄሪሱ ኢ ሕጋዊና - ኢ ፍትሐዊ ውሳኔ መቀበል “ለሁለቱም አገሮች ሰላም ያስገኛል” ሲለን ቀደም ብሎ እራሱ የጻፈውን 360 ዲግሪ በተቃራኒ ታጥፎ ሌላ ፖለቲካ ስብከት ውስጥ ይሰብከናል። ኤርትራኖቹ ሲ ኣይ ኤው ‘ኮፕላን’ የአፍሪካ እስራሎች ናችሁ ስላላቸው አምነውት በዛው የቀጠሉት የኤርትራ መሪዎች እነዚህ የመሳሰሉ ‘ተረታ ተረቶች በማጠራቀም’ ለኤርትራውያን የተሳሳተ የራስ ምስል መጠናከርና ቀጣይነት እንዲኖሮው እስከዛሬ በተረት ተረታቸው እየቃዡ ባለበት ሁኔታ “ሰላም ይመጣል ‘ ብሎ መስበክ መፈተሽ ያለበት ውሰጠ ሴራ እንዳለ እጠረጥራለሁ።

መድሀኔ ታደሰ በመቀጠል አንዲህ ይላል፡
“ይህ ቢስማርካዊ ሚናም የኤርትራን አመራር የተሳሳተ የራስ ምስል ማግዘፍ ትንሻን አገር እና ድሃይቷን አገር በምስራቅ አፍሪቃ ወደ እምትገኝ “የራምቦ”  አገር ለወጥ በድፍረት ተነሳ” (ገጽ 146 ዘኒ ከማሁ) እንግዲህ እነዚህ አምነቶች እቦታቸው ላይ እያሉ መድሃኔ ታደሰ ሻዕቢያ ከድሮው መስመሩ እንዳልተዛነፈ እያወቀ ኢሳያስ ያሳየው የባህሪ ለውጥ ሳያሳየን ባድሜን እና 17 የትግራይ ገጠሮች ለኤርትራ አሳልፎ መስጠትን ሕዝብን ማፈናቀል “ሰላም” ያስገኛል ብሎ የሚለን ስብከት የከሰረ መስመር መሆኑን በስፋት እንነጋገርበታለን፦
ይቀጥላል
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)