Friday, November 19, 2021

8557 ከፖለቲካ የጸዱ ትግሬዎችን የሚታደኑበት የነፃ ጥሪ መገናኛ እና የኢሳቱ ግዛው ለገሰ ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY 11/19/2021

 

8557 ከፖለቲካ የጸዱ ትግሬዎችን የሚታደኑበት የነፃ ጥሪ መገናኛ እና የኢሳቱ ግዛው ለገሰ

ጌታቸው ረዳ

ETHIO SEMAY

 11/19/2021


በመጀመሪያ ሰላምታ አላስቀድም። በተረኛው አፓርታይዱ ኢንተርሃሙዌው አሮሙማው መንግሥት  በንጹሃን ቤተሰቦቼ ላይ ባሕርዳር ከተማ ውስጥ እያደረሰባቸው ያለው ጥቃት በሚመለከት “የኢትዮ ሰማይ ድረገጽ ተከታዮቼ” የተለያዩ አበረታች የድጋፍ ኢመይል ላደረጋችሁልኝ እና በሰልክ የደወላችሁልኝ ወንድሞች እና እህቶች እጅግ አመሰግናለሁ። እንድደውልላችሁ ስልክ የተቀዋችሁልኝ፤ ራቅ ያላችሁ ወገኖቼም በጊዜ ጥበት ምክንያት ባለመደወሌ ይቅርታ እያልኩ ስተንፍስ እደውላለሁ።

ይህ ካልኩ ወደ ርእሳችን ልግባ።

 በቅርቡ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ” የሚባል  ቡድን የሚያዘው “በፓርላማ” ህንጻ ውስጥ የሥልክ ጥሪ አስተናጋጅ ቡድን አለ።  ይህ ቡድን ወያኔን በማደን ስም “ንጹሃን ትግሬዎችንም” የማደን ተግባር ለማከናውን  የተመሰረተ የኦሮሙማው አፓርታይድ መንግሥት መዋቅር ነው።

በዚህ መሰረት 8557 በመደወል ማንኛውም ትግሬ ንጹህ ይሁን አይሁን በተሰጠው የስልክ ጥሪ ደውሎ ማስያዝ እንደሚቻል በሕግ ጸድቋል። ይህ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ” የሚባል አዲስ ሳይሆን  አምና ጦርነቱ እንደተጀመረ የተመሰረተ ተቋም ነው። “ሳምረ” በታበለ “የትግሬ ኢንተርሃሙዌ ገዳይ ቡድን” ማይካድራ ውስጥ የተገደሉ ንጹሃን አማራዎች ጭፍጨፋ አጣሪ ሆኖ የተላከ ቡድን ነው። ቡዱኑ በመንግሥት መዋቅር የተደራጀ ስለሆነ ፤እራሱ ቡዱኑ “መንግሥታዊ እንጂ “ “ገለልተኛ ቡድን” አይደለም።

እርግጥ “ሕዝባዊ” ለማስመሰል ለይስሙላ በቅርቡ በአፓርታይዱ ፓርላማ ውስጥ በምርጫ የየገቡ እንዳንድ የአፓርታይዱ ዕድሜ የሚያስቀጥሉ ‘አገር ወዳድ” መሳይ ግን የሥርዓቱ አሟሟቂ የሆኑ አባሎች በአጣሪነት የገቡበት ቡድን እንዳሉ መመሪያ ሲሰጣቸው በቴ/ቪዥን አይተናቸዋል።

ለይስሙላ መሆኑን ባወቅም እንዲሁ እንበል እና የተሰጣቸው መመሪያ ይወጣሉ እንኳ ቢባል ፤ ይህ ቡድን ሥራው በርካታ ስለሆነ ያለ ሃጥያታቸው የታሰሩ በመላ አገሪቱ የተያዙ ሰለባዎች ለማጣራት ጊዜውም አቅሙም የለውም። ምክንያቱም የሚወሰኑት አዲስ አባባ ብቻ ሊሆን ይችላል።ባጫሩ ከተሰጣቸው ግዳጅ ውስጥ አንዱ እንጂ በዛው በታሰሩ ላይ ትኩረት ያደረገ መርማሪዎች አይደለም። ለዚያ ተልእኮ ብቻ እንዲያጣሩ ስላልተደራጁ ፡ንጹሃን አሁንም ፍትህ ሳያገኙ መንገላታቸው እጅግ የከፋ ሊያደርገው ነው።

ይህ ቡድን ከሰብኣዊ መብት ጠበቃ ተብየዎች አብሮ ይሰራል አይሰታም የታወቀ ነገር የለም።

አሁንም የዚህ ድርጅት ዋና ትኩረት የሰብአዊ መብት ሥራ ሳይሆን “የማፈን፤የማሰር” ትኩረት ያደረገ ነው። አሰራሩ በጀርመን እና በሩዋንዳ እንደተደረገው “ጎረቤቶች” በጡቆማው እንዲተባበሩ መብት ተሰ ጥቶአቸዋል። ይህስ ባልከፋ፤ ክፋቱ ግን በትግሬ ጥላቻ የሰከሩ “ኢንተርሃሙዌ” ግለሰቦችና ፖሊሶች ያሻቸውን ለማድረግ ዕድል የከፈተ አደገኛ ዘመቻ ነው። ይህንን አዋጅ ከወጣ ወዲህ ከሥራቸው ከቤታቸው ከህጻናት ልጆቻቸው የተለዩ ከተከራዩት ቤት እንዲወጡ ተገፍትረው የወጡ፤ የተፈናቀሉ፤ የተደበደቡ ፤የተገደሉ፤ንብረታቸው የተዘረፉ፤ ማጎርያ ውስጥ በበሽታ የታመሙ ያልታከሙ፤ ምግብ የሚያመጣላቸው ያጡ… ብዙ ስቃይ እየደረሰ አፋጣኝ ውሳኔ አልተሰጠም። በተለይ አዲስ አባባ ውጭ ያሉ ትግሬዎች የከፋ በደል እየተፈጸመባቸው ነው። ባሕርዳር ዋናው ማሳያ ነው።

የአፓርታይዱ ኢትርሃሙዌው ፖሊስ የማገጠ ነው። ሥርዓቱ ፍትህ ይሰጣል ብለው በድጋፍ ከቆሙት ካድሬዎች  አንዱ በፌስቡክ ድረገጹ ላይ ስለ ተጨማለቀው ፖሊስ አሰራር እንዲህ ይላል።

“የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ሆድ መሙያ የገንዘብ ምንጭ ሆኖለታል! አዲስ አበባ ፖሊስ ሀገርን በገንዘብ እየለወጠ ነው!” ይላል።

በዚህ መልክ እንዴት ፍትሕ ሊመጣ ይቻላል የሚል ጥያቄ ቢጠየቅ መልስ ሊያኝለት አይቻልም።

ዘመዶቻችን ለወራቶች አሁንም ታጉረው ያለ ምንም ፍትህ ታስረው እየተሰቃዩ ናቸው። ይህ ድርጊት የሚደግፉና የሚደስቱበት በጣም በርካታ በውጭ አገር እና በውስጥ አገር ያሉ ተባባሪዎችን አደራጅቷል።

ከጋዜጠኞች፤ ከተማሪዎች፤ ከሰራተኞች እስከ ተራ ዱርየ “በየግል ምክንያቱ” ተነሳስቶ የዚህ ዘመቻ አላማ አዳማቂና አበረታች ሆኗል። የወያኔ ደጋፊ ላይ እርምጃ የሚወሰደው አስታክከው በገፍ በትግሬነታቸው ብቻ ምንም የሌላቸው ወደ ማጎርያ እስር ቤት መውሰዳቸው ዕልል ብለው የሚደግፉ በርካታ ኢንተርሃሙዎች በየፌስቡኩ ተበራክቷል። ይህ ደግሞ ለአገሪቱ መፍረስ “ረሴፒ” ዋናው አቀላጣፊ ነዳጅ ነው።

ትናንት ምን እንደገፋኝ አላውቅም መከታተል ካቆምኩኝ አመታት የሆነኝን “ኢሳት” የተባለው አደገኛ “የኢንተርሃሙዌ  ሚዲያ” ድንገት ገብቼ ሳደምጥ ግዘው ለገሰ የተባለ አንድ በዕደሜ” የጠና የጣቢያው “ባልደረባ” ስለ አበበች አዳኔ አድናቆቱን ሲገልጽ እንዲህ ሲል ሰማሁት፤

“በብሔር ምክንያት የታሰረ የለም! ኦሮሞም አማራም ትግሬም ታስሯል። ነገር ግን እየታሰረ ያለው ለአሸባሪው “ህ.ወ.ሐ.ት” ዕርዳታ የሚሰጡ ብቻ ናቸው እየታሰሩ ያሉት።ስለዚህ ወ/ሮ አዳነች ያሉትን አድናቆቴን ለመግለጽ እወዳለሁ ፤ወ/ሮ አዳነች ለሌሎች መሪዎቻችንም ምሳሌ ናቸው።”

በማለት አስገራሚ የሆነ ፤ከዕድሜው ጋር የማይሄድ አገልጋይነት ከዚህ ሰው ንግግር የሚነግረን ነገር በጣም በርካታ ነው።

“ማልካም ኤክስ” የተባለ የጥቁሮች መብት ተሟጋች እንዲህ ያሉትን ሰዎች በሚከተለው መልክ ይገልጻቸዋል፡

“ሁለት ዓይነት ኔግሮ (ጥቁር) አለ። አሮጌው ዓይነት እና አዲሱ ዓይነት። አብዛኞቻችሁ የድሮውን አይነት ኔግሮ እንደምታስታውሱት በባርነት ጊዜ ስለ እርሱ በታሪክ ውስጥ ስታነብቡ "አንክል ቶም/ አጎት ቶም" (አጎቴ ቶም) ተብሎ ነበር የሚጠራው። በዛው ወቅት ቆየት ብሎ በባርነቱ ዘመን ሁለት  ዓይነት ኔግሮዎች ነበሩ። “የሃውስ ኔግሮ”  “የቤት ኔግሮ” እና “የእርሻ ሜዳው ኔግሮ”።

የቤት ኔግሮው አብዛኛውን ጊዜ የሚኖረው ከጌታው አጠገብ ነው። እንደ ጌታው ይለብሳል፤ ጌታውን የጣለለት ልብስ ይለብሳል። ጠረጴዛው ላይ ጠግቦ የተወውን የጌታውን ምግብ ይመገባል። አዳሩም መኖርያውም በጌታው ቤት ውስጥ - ምናልባት በመሬት ውስጥ ወይም በሰገነቱ በጌታው ቤት ውስጥ ይኖራል።

 ጌታው እራስ ምታት ሲታመም  ከጌታው ጋር አብሮ  እራስ ምታት እንደየዛው ስለጌታው ይታመማል።  የጌታው ህመም ህመሙ ነበር። እና እሱ ራሱ ከመታመም ይልቅ ስለጌታው መታመም በጣም ይጨነቃል። የጌታው ቤት ሲቃጠል ጌታው ከሚችለው በላይ እርሱ  ሲጨነቅ ይታያል።

እርሻ ሜዳ ላይ የሚውሉ ብዛት ያላቸው  “ኔግሮዎች” ግን ጌታቸው በታመመ ጊዜ ተሎ እንዲሞት ይጸልያሉ። የጌታቸው ቤት በእሳት መቃጠል ሲያዩ ሃይለኛ ነፋስ እንዲመጣና እንዲያቃጣጥለው ይጸልያሉ።

ዛሬም የሃያኛው ክፍለ ዘመን ዓይነት የቤት ኔግሮ አለ። የሃያኛው ክፍለ ዘመን ‘አጎት ቶም’ ይኼኘውም ልክ እንደ “አጎት ቶም” ከ100 እና 200 ዓመታት በፊት እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ያው “አጎት ቶም” ነው። ልዩነታቸው ይኼኛው “ዘመናዊ” ነው። የትናንቱ ‘አጎት ቶም’ በራሱ ላይ “መሀረብ” ይጠመጥም ነበር። ይህኛው ‘አጎት ቶም/አንክል ቶም’ ግን “ ራሱ ላይ ዘመናይ ቆብ ያጠልቃል፤ ሱፍ ይለብሳል ፤ ክራባት ያደርጋል’’።

ልክ እንደ ጌታው ይለብሳል። ተመሳሳይ የቋንቋና ዘይቤን ይናገራል። ያውም ከጌታው በተሻለ ሁኔታ ለመናገር ይሞክራል። በተመሳሳይ ዘዬ፣ በተመሳሳይ መዝገበ ቃላት ይናገራል።

“የነሱ” ሰራዊት ስትል  “ሠራዊታችን” ይላል። እነሱን ለማመለካከት “እነሱ” ስትል "እኛ" ይላል። "የእኛ ፕሬዝደንት" "መንግስታችን" "የእኛ ሴኔት" "የእኛ ኮንግረሰሮች" "የእኛ ይሄ እና “የኛ" ምናምን እያለ ቢኳትትም መጨረሻ ላይ እንኳን በዚያ "የእኛ" ውስጥ “መቀመጫ አያገኘም”። ይላል “ማልኮም ኤክስ” በ1963 እ.ኤ.አ. ሚችጋን ለተማሪዎች ከተናገረው ንግግር እንግሊዝኛውን መረዳት የማትችሉ አንባቢን እንደሚመች ቀንጭቤ በራሴ ያስተካከልኩት ንግግር ነው። ቪዲዮው ግን ለጥፌዋለሁ።

በሚገርም ተመሳሳይነት እንደ የኢንተርሃሙዌ ቀስቃሽ የሩዋንዳው “RTLM” ራዲዮ አዘጋጅ የነበረው “ካቡጋ” (የኢሳት ካቡጋ መሳይ መኮንን ኢትዮጵያዊያን የሆኑ ትግሬዎች ልክ እንደ  “አሜሪካዊያን በጃፓኖች” አሜሪካ  የወሰደቺው ዘረኛ ሁሉም ጃፓን ሰብስቦ የማጎር ወንጀል በትግሬዎች ላይ እንዲፈጸም በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ያወጀውን አስገራሚ ጥሪ እየገረመን፤  ትናንት ደግሞ የዚህ ጣቢያ አባል የሆነ አቶ ግዛው ለገሰ የተባለው  በትግሬነቱ የታሰረ ትግሬ የለም ሲል እጀግ ነበር የደነገጥኩት። እንዲህ ያሉ ፍጡራን አገራችን ውስጥ ተበራክተዋል። “ሞራል ድካደንት” የሚባለው “የሞራል መበስበስ” ፍጥነቱ እጅግ ዘግናኝ ነው። ይህ ሰው አበበች አዳኔ በትግሬነቱ የታሰረ የለም ስትል እርሱም ልክ “ማልካም ኤክስ” እንዳለው ግዘው ለገሰም ያለ ምንም ሐፍርት “የጌታውን ቃል ደገመው”።

ለዚህ ነው በመጽሐፌ ውስጥ “ሳብቨርዥን” በሚለው ምዕራፍ ውስጥ የጠቀስኳቸው የግንቦት 7 አባላት እና የመሳሰሉ ምሁራን እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወያኔን ተክቶ በሚመጣው አዲስ ሥርዓት ውስጥ ተዋናይ በመሆን እንዲህ ያሉ ሰዎች ለአገሪቱ መፍረስ ከፍተኛ እጅ እንደሚኖራቸው የገለጽኩት።

በመጽሐፌም ውስጥም ይሁን አሲምባ ከተባለ ፓልቶክ ላይ ከ 7 አመት በፊት የሰጠሁት  ቃለ መጠይቅ ማድመጥ አሁን እየተደረገ ያለው ድርጊት እና ተዋናዮቹ ለአገሪቱ “ክራይሲስ” አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሚሆን የገለጽኩት ለዚህ ነበር። ቃለ መጠይቁ እየፈለግኩት ስለሆነ ሳገኘው እዚህ እለጥፈዋለሁ።

ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY