Tuesday, July 21, 2020

ይድረስ ለጀርመን ድምፅ ያማርኛ አገልግሎት ቦን/ጀርመን 21.07.2020


ይድረስ ለጀርመን ድምፅ ያማርኛ አገልግሎት
ቦን/ጀርመን
21.07.2020          
በሐምሌ 12 ቀን 2012 . ዕለተ እሁድ እንወያይ ሳምንታዊ ዝግጅት ሦስት ሰዎችን አቅርባችሁ በአቶ ነጋሽ መሐመድ አዋዋይነት የተደረገዉን ሰምተን ምላሹ ይኽዉ።

የጀርመን ድምፅ ራዲዮ ተብየዉ ከሁሉ በተቀዳሚ አንድን  ፀረ ዐማራ ለዘር ማጥፋትና ማፅዳት ግልጽ የጥላቻ ቅስቀሳ ዋና አቀንቃኝ የሆነዉን ራሱን ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኒ ብሎ የሚጠራዉን፣ 16ኛዉ ሁለተኛ አጋማሽ (1665) ከግራኝ አሕመድ ጅሃዳዊ ወረራና ፍጅት በኍላ በተከተለዉ የጋላ ነገድ ወረራና በሸዋ ምድር መጤ ሠፋሪ ሆኖ ከቀረዉ የጋላ ቱላማ ጎሣ ዉላጅ የአቢቹ  ዘርያ ነኝ ያለዉ ዓይኑን በጨዉ አጥቦ ጥንታዊት በራራ እንዶጥና የቀዳማዊ አጤ ዳዊት(1382-1411) መናገሻ በነበረችዉ ሥፍራ ገናና ሰመ ጥሩዎች በሆኑት እቴጌ ጣይቱ ብጡልና ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ዳግም በተመሠረተችዉና አዲስ አበባ ብለው በሰየሟት መዲናችንና ዙሪያ የአቢቹ ወረሞ ጎሣ ብቸኛ መኖሪያ ነበር ብሎ እራሱን የኦሮሞ ነጻ አዉጭ ግንባር (ኦነግ) የሚለዉ ያልታጠቁ ሰርቶ አደር ገበሬዎችን ነጋዴዎችንና ሠራተኞችን ዐማራ ኢትዮጵያዊ እስላምና ክርስቲያን በመሆነናቸዉ ብቻ ለይቶ ነፍጠኛ እያለ ፈርጆ በአሰቃቂና አረመኔያዊ ድርጊት የፈጀና የሚፈጅ፣ ያፈናቀለና የሚያፈናቅል የወንጀለኞች ቡድን የፈጠራ ትርክትንና ፀረ ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳ በቅጥረኝነት ልክ እንደ ሻዕቢያ እና ትሕነግ ወያኔ ሲያደርጉት እንደነበረዉ ለኦነጉ ብርሃነ መስቀል እንዲያነብንብ የጀርመን ድምፅ ራዲዮ ነፃ መድረክ ሆኖታል። 

ምን የጀርመን ድምፅ ብቻ ያሜሪካኑም ቪኦኤ የተሰኘዉ ለብርሃነ መስቀል አበበ የዉሽት በሬዉ ላም ወለድ ትረካ እንዲያናፋ ሰለሞን አባተ የተባለዉ ድንብርብር ተከታታይ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግለት ተደምጧል። ወደ ዋናዉ ቁም ነገር ተመልሰን የነጋሽ አሕመድን ቅሌቱና ወንጀሉ ለብርሃነ መስቀል አበብ ዐማራን በስም ለይቶ፣ ነፍጠኛ በሚል ምልከታዉ፣ የጥላቻ ቅስቀሳ በማነሳሳት በጀርመን ድምፅ ራዲዮ በስፋት እንዲያሰራጭ አስችሎታል። ብርሃነ መስቀል በሚረጨዉ የፈጠራ ወሬ ማለትም አዲስ አበባና ዙሪያዋ የአቢቹ ጎሣ መኖሪያ ነበር እያለ አዲስ አበባን በአረመኔ የቄሮ መንጋ ለማስጨፍጨፍ፣ ለማዉደም በጀርመን ድምፅ ራዲዮ መርዙን ረጭቷል።

የአቢቹን ጎሣ በተመለከተ ሐቁ ግን ሌላ ነዉ። ይህ ጎሣ የሚኖረዉ ባማራዉ ምድር በወግዳ ነዉ። ያቢቹ ዋና ጠላት ገላን የተባለዉ ከአዋሽ ወንዝ በሰተሰሜን ከወጨጫ ተራራ በመለስ ከእንጠጦ ተራራ በስተደቡብ ከየረር ተራራ በሰተምዕራብ ባላዉ አካባቢ የሚኖረዉ። በሸዋ ከግራኝ አሕመድ ወረራና ከተከተለዉም የጋላ ወረራና ቇሚ ሠፈራ ሳቢያ ተለያይቶና ተነጥሎ የቆየዉን በጋላ ጎሣ የተያዘዉን ያማራዉን ምድር ለማስመልስ ያጤ ልብነ ድንግል ተወላጆች እነ ያዕቆብ፣ ነጋሢ፣ መርድ አዝማች ስብስቴ፣ አብዬ፣ አምሃ ኢየሱስ፣ አስፋ ወሰን፣ ራስ ወሰን ሰገድ፣ ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ፣ ኃይለ መለኮት ተከታታይ ዘመቻ አድርገዋል። የሸዋዉ ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ እስከ ጉራጌ እና አባይ ወንዝ በመለስ ያለዉን አገር አስመልሰዉ አቅንተዋል። በዛሬዉ አዲስ አበባ በጥንቱ በራራ የአቢቹ ጎሣ ስፋሪ በጭራሽ አልነበረም። ለዚህም ዋናዉ ሰነድ የእንግሊዝ ንግሥት ቪክቶሪያ መልክተኛ መሪ የነበረዉ ሻምበል ዊሊያም ሃሪስ ያይን ምስክር ሆኖ ያዘጋጀዉን መጽሐፍ መመልከት ነዉ። ከዚህም ሌላ አፍቃሪ ጋላ የነበረዉ የጀርመኑ የወንጌል ሚሲዮን ተብዬዉ ሰላይ ዮሓን ሉድቪኽ ክራፍ ከሰሜን ኢትዮጵያ ሲባረር በታጁራ በኩል ወደ ሸዋ ገብቶ ሁለት ዓመታት ቆይቶ ሸዋን ዋና ማዕከሉ አድርጎ አእዋሚ ጋሎችን ሁሉንም የፕሮቴስታንት ክርስትናን ሰብኮ ከሸዋ በስተደቡብ ያለዉን አገር ልክ እንደነ ታንጋኒካ፣ ካመሩን፣ ቶጎና ናሚቢያ ያፍሪቃ ጀርመን ቅኝግዛት መስፈሪያ ለማሰደርግ አቅዶ ባዘጋጀዉ ትረካ አቢቹ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንደማይኖር ያረጋግጣል።

ሌላዉ የነጋሽ አሕመድ በጣም አሳፋሪ ቀልባጣነት "ኢትዮጵያ እንዴት ትፍረስ?" እያለ ማሟረቱ ነዉ። በእዉነትና ብርግጠኛነት እንላችኍላን እናት ሀገር ኢትዮጵያ አትፈርስም። ሊያፈርሷት የሞከሩ ጠላቶቿ ሁሉ ፈርሰዉ ትቢያ ሆነዋል፣ ይሆናሉ።

 የጥላቻ ቅስቀሳ የሚያነሳሱ፣ የሚያደራጁ፣ የአንድን ማኅበረሰብ ለይተውና ምልከታ ሰጥተዉ፣ ሰባዊ ክብሩን አዋርደዉ ለዘር ፍጅት(Genocide) እና  ዘር ማፅዳት (Ethnic cleansing ) ዘመቻ ከሚያደርጉና ካደረጉት ጋራ በግልጽና በስዉር የሚተባበሩትን ሁሉ በጥብቅ እንቃወማለን። እነዚህ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን::
ኢትዮጵያ በልጆቿ መስዋዕትነት በነፃነት ትኖራለች!!!!

ቶሚ ገሞራው       

 የዉብዳር ዘለቀ/ዶክተር             
 ገለበዉ ሰንጎጎ          
ገብሬ ጉልቱ /ዶክተር
ሞገስ  ገብረ እግዚአብሔር 
21.07.2020