Tuesday, July 25, 2023

አከሱማዊው ፓሊዮአንትሮፖሎጂሰቱ ዘርአሰናይ ዓለምሰገድ ጦርነቱ ሁለቴ እንዲያስብ የረዳው ይመስላል፡ ጌታቸው ረዳ (ETHIOPIAN SEMAY) 7/26/23

አከሱማዊው ፓሊዮአንትሮፖሎጂሰቱ ዘርአሰናይ ዓለምሰገድ

ጦርነቱ ሁለቴ እንዲያስብ የረዳው ይመስላል፡

ጌታቸው ረዳ 

(ETHIOPIAN SEMAY)

7/26/23

በፋሺሰቱ ወያኔ “ርዕዮተ ዓለም” ዘግየት ብሎ የተማረከው አክሱማዊው ፕሮፌሰር ዘርአሰናይ  ዓለምሰገድ በሙያው “ፓሊዮአንትሮፖሎጂስት” ነው።

ዘርአሰናይ  2000 (በፈረንጅ) ዓ.ም የሉሲ ልጅ ነች ተብላ የምትጠራው “ሰላም” የሚል ስም የተሰጣት የ3.3 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያላት ሳይንትስቶቹ “የኦስትራሎፒተከስ” ብለው የሚጠሩት ዝርያ ያለው “ቅሪተ አካል” ያገኘ “ፓሊዮአንትሮፖሎጂስት” ነው።

ዘርአሰናይን ካሁን በፊት ሁለቴ ተችቼዋለሁ። ዛሬም ወያኔነቱን ባይለቀውም ጦርነቱ ሁለቴ እንድያስብ ያደረገው ይመስላል።

እንዲህ ይላል።

<< እስካሁን ድረስ ከባድ የሆነ መስዋዕትነት ከፍለናል እና ሳንሞት ሳንቆስል፤ አዲስ አይነት መስዋእትነት መለማመድ አለብን። ከጡሮተኞች ጀምሮ እስከ ወጣቶችና ዲፕሎማቶች የሚሰውበት አካሄድ መለወጥ አለበት። በሙታን እና በአካለስንኩላን የተከበብን መሆናችን እናስተውል። የማንወጣው ተራራ እና የማንሻገረው ወንዝ የሚለው ከተሻገርን በላም የማንፈጥረው ሳይስና ቴክኖሎጂ የለም ማለት አለብን። ደማችን ከዋጀ/ከፈሰሰ/ ሥጋችን ለአሞራ ከሰጠን በላም ሕዝባችን ወደ ከፍታ የሚያሸጋግር ፖለቲካዊና ሳይንሳዊ መንገድ ልንፈጥር ይገባል። ካልሆነ ግን ለዳግም “አንደኛ ፤ሁለተኛ ፤ሦስተኛ፤ አራተኛ እና ለአምስተኛ ኪሳራ እንጋለጣለን።”

ይላል።

የትግራይ ሃገርነት ፤ የናዚዎች ድንፋታና ጦርነት ፤ የጦርነት ፍቅር፤ ጦርነት ለትግሬዎች የጨዋታ ባሕል ነው የሚለው ድንቁርና ትዕቢት ከጦርነቱ ወዲህ ሁለተኛ እንዲያስቡበት ያደረጋቸው ቢመስልም የናዚ መጻሕፍቶች ያነበብን ሁሉ እንደምናውቀው ፋሺዝምና ናዚ ያለውን ጦር እንዲሟሟ ካለደረግክ መልሶ እንደሚያገረሽ ይታወቃል። ይኼው ዛሬም አብይ አሕመድ ሆን  ብሎ ጦሩ ግማሽ ወገቡ ብቻ ተመትቶ ግማሽ ወገቡ እንዲያጋግም እና እንዳይነካ ስላደረገ መሪዎቹ ዛሬም ሃይማኖትን አስታክኮ የመገንጠል ሂደትና ጦርነት ለመጀመር እየጋገሩት ነው። የነ ጌታቸው ረዳ በፌስቲቫሉ ንግግርም ያንኑ ያሳያናል።

ፕሮፌሰር ዘርሰናይ ታዲያ በሙያው ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘ ሊቅ ቢሆንም እንደ ማንኛቸውም የናዚ ጀርመን ፈላስፋዎች፤የፊዚክስ፤የሕክማና እና የአንትሮፖሎጂ ሊቃውንት ሁሉ ዘርአሰናይም ትግራይ ውስጥ በወየነ ትግራይ ድርጅት የበቀለው “ናዚያዊ የፋሺዝም ርዕየት” አካል ሆኖ የተጠረነፈ “ዛሬም የመንጋው” አካል ነው።

 የትግሬ እና የናዚ ብሔረተኛነት አንድ የሚያደርጋቸው ባሕርይ  (ኢንቴንስ ናሺናሊዝም) “ንዳዳዊ ብሔረተኛነት” እና ያ ንዳድ ወደ ብዙሃኑ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ በመንጋ የተጠመቀ ማሕበረሰብ የመቀናጀቱ ሂደት ከጀርመኖቹ ጋር አንድ ያደርጋቸዋል።

በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ማሕበረሰብ የሚባል ድርጅት ወያኔ ከተመሰረተ ጀምሮ ለፋሺሰቱ ድርጅት ቀኝ እጅ ሆኖ የሰው ሃይል፤ የገንዘብ እና የቁሳቁስ (ራዲዮ መገናኛ ወታደራዊ ልብስ፤ ጫማ ወዘተ…) በሱዳን በኩል ወደ ትግራይ ጫካ በማስገባት የትግሉ ግማሽ አካል ሆኖ የቆየና ፤ ዛሬም “የሃገረ ትግራይ ምስረታ” ዋናው አንቀሳቃሽ ክፍልነው። ታዲያ ይህ ድርጅት ያዘጋጀው የ49ኛው አመት ድግስ ላይ ተገኝቶ ከተናጋሪዎቹ አንዱ ነበር።

የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ዶ/ር ዘርአሰናይ  ዓለምሰገድ እንደተለመደው “ንዳዳዊው ብሔረተኛነቱን” ከፍ በማድረግ እንኳን አደረሰን ይል እና አንደተለመደው የአክሱም ሥልጣኔ የትግሬው ብቻ እንደሆነ የሚቦተልከው ውሸት (እንደ ካሁኑ በፊት ባይሆንም) በገደምዳሜ ሲነካካው ሰምተናል። ምንም እንኳ በሙያው የሚመጥን ሰው ቢሆንም አክሱም የትግሬዎች ብቻ ነበር የሚለው በማስረጃ እንዲያሳምነን እኔም ሆንኩ አቻምየለህ ታምሩ በትችቶቻችን ብንጠይቀውም እስካሁን ድረስ ሊያቀርብ አልቻለም።

ዶ/ር ዘርአሰናይ ዓለምሰገድ የፋሺሰቱ ድርጅት አወዳሽና ደጋፊ መሆኑን ለመትጠራጠሩ ሰዎች ካላችሁ ከጦርነቱ በፊት በትግሬዎች ስብሰባ ላይ የተናገረው ካሁን በፊት ባቀረብኩት ትችቶቼ መግለጼ ይታወሳል። ላስታውሳችሁ።

 ከትግርኛ ወደ አማርኛ ምን እንዳለ ላስነብባችሁ፡-

“ዛሬ በትግራይ ውስጥ በ2.7 ሚሊዮን ህዝብ የተመረጠ ፓርቲ/መንግስት እንዳለ መቀበል አለብን! ይህ ያለ ምንም ክርክር አክብረን መቀበል አለበን። ይህንን መንግሥት ለመመስረት ከምርጫው በፊትም ሆነ በኋላ ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሏል”

ብለዋል።

ይህንን የፋሺሰት ድርጅት ለመመስረት የትግራይ ሕዝብ ብዙ መስዋዕትነት እንደከፈለ አስረግጦ ይነግረናል። ስለሆነም ያለ ምንም እንካ ስላንትያ ፋሺዝም አክብሮ መቀበል የግድ መሆኑን ነግሮናል።

በመቀጠልም፤

 በትግርኛ እንዲህ ይላል፡

 “ኣብ ትግራይን ትግራዋይነትን ንዕሰል”

<<ወደ ትግራይ እና ትግራዋይነት ብቻ እንትመም>>

ይላል።

እዚህ ላይ ማትኮር ያለብን የዘርአ ሰናይ ንግግር የሂትለርና ተከታይ ምሁራኖቹ  ሲሉት የነበረውን ነው ዘርአሰናይ የደገመው። እነሱ የሚሉት ብሔራዊ አንድነታችን የተመሠረተው “የግለሰብ ደም መሰባሰብ (ዘር) ማሕበረሰቡ ደም በመገንባት ወደ ጋራነት እንዲተሙ ያደርጋል (ያቆራኛቸዋል)። እንደ ዘርአሰናይ እና እንደ ናዚዎቹ አባባል  አንድ ዓይነት “የኖርዲክ ዝርያ ወደ ጀርመን ኖርዲክነት ካልተመመ”  ትግሬውም <<ወደ ትግራይና ወደ ትግራዋነት ብቻ ካልተመመ>> “ ከሌላ ደም ጋር መትመም የዘር መጠላለፍን ያስከትላል” የሚል የዘር ጥራት ፍላጎታቸውን አንድ ያደርጋቸዋል።

“ትግሬ ወደ ትግራይ እና ትግሬነት ካልተመመ” የመለያየትና የነገዱ ተወላጆች መበላሸት መንስኤ ምክንያት ነው በሚለው “በደም ሃይጂን” ትኩረት ያደረገ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ነው”። በእነ ዘርአሰናይ እና በናዚ ምሁራን እምነት ሁል ጊዜ የሚመራቸው አንድ ነገር ነው፡ እርሱም በጀርመንነት እና በትግራዋይነት ብቻ ላይ ያነጣጠረ እምነት እና በመሪ ድርጅቶቻቸው በደም እና በመስዋዕትነት የተመሰረቱት “የራይክ” እና “የወየነ ትግራይ” መንግሥት ያለ ምንም ማንገራገር መቀበል ነው ይላሉ።

ከላይ ያየነው የዘርአሰናይ ንግግር ማለትም “ይህንን መንግሥት ለመመስረት ከምርጫው በፊትም ሆነ በኋላ ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሏል” የሚለው እና <<ወደ ትግራይ እና ትግራዋይነት ብቻ እንትመም>> የሚለው ንግግሩ ለመሪ ድርጅቱ ለወያኔ መገዛት እምነቱን በግልጽ ነግሮናል።

ፕሮፌሰር ዘርአሰናይ የትውልድ ሐረጉ አክሱም ቢሆንም ያደገው ኤርትራ እንደሆነ ይነገራል። ታዲያ ብዙዎቹ ኤርትራ ያደጉ ትግሬዎች ለኢትዮጵያ እና አማራ ያላቸው ጥላቻ መረን የለቀቀ ነው።

ካሁን በፊት ዘረሰናይ እንዲህ ሲል ወያኔ ያስተማረው ንግግር ደግሞታል፡

<< ‘በዚህ በደማቅ የትግራይ ታሪካችንና ባህላዊ ቅርሳችን ምክንያት በሰሜንም ሆነ በደቡብ ያሉ ጎረቤቶቻችን ይቀኑብናል፤ የእኛ ነው ብለው ሊነጥቁን ይፈልጋሉ።>> ብሏል።

ሁሉንም የድል እና የታሪክ ቅርሶችና  ጥበቦች የእኛ ነው” በሚል እብሪትና እብደትስጥ የገባው ፕሮፌሰር ዘረሰናይ  ዓለምሰገድ  በሚሊዮን የሚቆጠሩትና ይህንን ድርጅት በጭፍንነትና በጀሌነት የሚከተሉ ተከታዮቹ አክራሪ ብሄረተኛነትና በሚፈጠ<<በደማቅ የትግራይ ታሪካችንና ባህላዊ ቅርሳችን ምክንያት በሰሜንም ሆነ በደቡብ ያሉ ጎረቤቶቻችን ይቀኑብናል፤ የእኛ ነው ብለው ሊነጥቁን ይፈልጋሉ>> የሚለው ዕብደት ውስጥ ከገቡ ዘመናት ተቆጥሯል። በዘፈናቸውም አድምጠናል። ዘርአሰናይ እንደ አንድ የመሬትና የሰው ልጆች የዘር ጥናት ተመራማሪ እንዲህ ያለ የናዚና የፋሺሰት ደንቆሮ እምነት ውስጥ መግባቱ ይደንቃል ይገርማል።

 “ትግራይ ውስጥ ያሉ አሁን ያሉትም ሆኑ ጥንት የተፈለሰፉ የመነጋገርያና የጽሕፈት ፊደሎች፤ መጻሕፍቶች፤ዘውዶች፤ ገንዘቦች፤ ቅዳሴዎች፤ ቅርሶችም ሆኑ ቤተ እምነቶች በግምባታው ላይ የሚታወቁና ያልታወቁ ነገዶች (የውጭ ዘሮች ሳይቀር) የተካፈሉበት የአክሱም ዘመን ሥልጣኔ << የትግሬዎች ብቻ ነው>>   የሚል ድንቁርና ስቆ ከማለፍ ምን ማለት ይቻላል።

በዚህ ፌሰቲቫል ደግሞ ሓፈረት ሳይሰማው 27 አመት የትግሬዎች

መንግሥት ሰላምና ልማት ሲያመጣ ትንሽ የዲሞክራሲ ጉድለት እንደነበረው ነግሮናል።

ሰላምና ልማት ነበር የሚለው ትግሬዎች የተንደላቀቁበትን ሰላምና ሃብት ክምችትን ነው። ዛሬ ዘረሰናይ የሚደግፈው የፋሺሰት ቡድን ለ27 ዓመታት በኢትዮጵያ ዘረኛ የአፓርታይድ ሥርዓት አስፍኖ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ያጨለመ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን በተለይ ከትግራይ በታች ባሉት የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሞት፤ ለመፈናቀል፤ ለስደት፤ ለመከራና ለሃዘን የዳረገ መሆኑን አይቀበልም። ስለሆነም ነው በዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ከመሩት አንዱ የሆነው ጌታቸው ረዳን በዚህ ፌስቲቫል አዳራሽ ከመንበሩ ተነስቶ በሞቀ ጭብጨባ ተቀብሎ አቅፎ አክብሮ ሲቀበለውና ሲክበው ላመየት የበቃን።

የትግሬ ወጣት ምሁራን ወደ መንጋነት የመጠርነፋቸው ድምዳሜ ፤ ልክ እንደ ናዚ ወጣቶች እምነት "ወደ ህዝባዊው ንቅናቄ (ወደ መንጋነት የተቀላቀልነው) ከነጻነት ለመላቀቅ ነፃ ለመሆን ነው>> እንደሚሉት ሁሉ የትግራይ ወጣት ምሁራንም ግለሰባዊ ነፃነታቸውን መንጋው ለሚመራው “ቡድን” አስረክበዋል። ከላይ ያየናቸው የፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ ንግግሮች ሁሉ መንጋውን ለ49 አመት ሲመራው የነበረው ቡድን የተናገረውን ነው ሲደግመው የሰማነው።

 ሰናይ ሳምንት ይሁንላችሁ!

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)