Wednesday, November 22, 2023

ሁለቱ ቴድሮሶች በአቡነ ኤርሚያሰ ያነጣጠሩት ወገንተኛ ትችት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/12/23

 

ሁለቱ ድሮሶች በአቡነ ርሚያሰ ያነጣጠሩት ወገንተኛ ትችት

ታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

11/12/23

አቡነ ኤርሚያስ በወሎ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተወካይ ናቸው። አቡኑ የላሊበላ ወይንም የላስታ ማሕበረሰብ (?) ስብሰባ ተገኝተው የተናገሩት ሃይማኖታዊም ይሁን ማሕበራዊና ፖለቲካዊ ነክ ባንዳንድ ሃያሲያን ሲተቹ ባንዳንዱም ተቀባይነት አግኝተው አለፍ ብሎም የተናገሩት ንግግር ስላልጣማቸው “ይቅርታ እንዲጠይቁ” ጋብዘዋቸው አስተያየታቸው ሰጥተዋል። በዚህ ትችቴ ውስጥ አቡኑ ስለተናገሩት ንግግር የሚያተኩር አይደለም። ምክንያቱም ከመጠን በላይ ትኩረት አግኝቶ መነጋገሪያ ሆኗል። ሳልተች የማላልፈውና ያበሳጨኝ ትዝብት ግን በፎቶግራፉ ላይ የሚታዩት በሁለቱ ቴድሮስች ላይ ነው።

ቴድሮስ ፀጋዬ (ርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ) እና ቴድሮስ አስፋው በሥርዓቱ ተሰድዶ በቅርቡ ወደ ውጭ አገር የተሰደደ ጋዜጠኛ አብረው በአቡኑ ላይ የሰነዘሩት ውርጅብኝ እጅግ ከማስደመም በላይ ወገንተኛነታቸው ፀያፍ መሆኑን ሳልቃወም ላልፋቸው አላልፍም።

ሁለቱ በትግራይ ሁኔታ የሚያላዝኑ ጋዜጠኞች ናቸው። የማላዘናቸው መነሻ ደግሞ በደምብ በሚባል ወያኔዎችና ቱልቱላዎቻቸው የልብ ልብ ሰጥቶአቸዋል። ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁኝ ስለ ትግራዩ ጦርነት ሲነሳ ከነዚህ ሁለት ጋዜጠኞች ብዙ የተራራቀ ልዩነት እንደለኝ ታውቃለካችሁ ብየ እገምታለሁ። ቴድሮስ ፀጋየ እና እኔ የትግራይ ተወላጆች ነን። ቴድሮሰ አስፋው ነገዱን አላውቅም። ጎበዝ ጋዜጠኛ ቢሆንም ከጭንቅላቱ ባለይ ለመፍንዳት የሚሞክር ከወያኔ ቱልትላዎች እኩል በሚያስመስልበት መልኩ በተዘዋዋሪ አዳማቂ ነው።

ያ ባይሆን ኖሮ እነዚህ ሁለት ጋዜጠኞች አማራ የተባሉ ቀሳውስትና ጳጳሳት በተናገሩ ቁጥር እንደ “ደሮ” እያንዳንዷን ቃላት እየለቁሙ ለወራትና ለሰዓታት ለትችት አቅርበው ሲተለትሉዋቸው ስናደምጥ እጅግ ዘረኛ ንግግርና የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ የሚናገሩ የትግራይ ቀሳውስትና ጳጳሳትና ፖለቲከኞች ላይ ሲደርሱ ግን ምላሳቸው የተሸበበ ነው። ጥያቄው ለምን? የወያኔ ትግሬዎች ቱልትላነት ካልሆነ ሌላ መጠሪያ ካለው ላድምጣችሁ።

  “ሃይማኖትና ፖለቲካ” ተዋህደው ፖለቲካው ሃይማኖትን የሚመራው” ሆኖ እያየን ነው። ይህ ግልጽ ነው። በተለየ እና በሚታይ መልኩ “ትግራይ እና ኦሮሚያ” አብያተ ክርስቲያናትና እስልምና ዕምነት ተቋማት ሁሉ በሚዋሹ ቀሳውስትና ሼኮች እየተመሩ ናቸው። ዝርዝር አልገባም (ብዙ ስለተባለለት)። ምዕመኑ “ነገዳውያን ቀሳውስትን” በመከተል የራሱን ሃይማኖቱን በማርከስ ላይ እንደሆነ እያየን ነው።

ቴድሮስ ጸጋዬን ስንመለከት አማራ ጳጳሳት ወይንም ቀሳወስት ላይ ሲደርስ በራሱ ነገድ ቀሳውስት ላይ ሲደርስ እፅ እንዳጨሰ ሰው አነገቱን ደፍቶ ለመናገር ይደበራል። ትናንት አቡነ ኤርሚያስ ላይ ከቴድሮስ አስፋው ሆነው ሰፊ ፕሮግራም ሰርተው አረፋቸው እስኪደፍቅ ቃላት እስከሚያጥራቸው ድረስ አቡኑን እንደ ወረቀት ሲቀዳድድዋቸው ነበር የዋሉት። ምክንያቱም ተብሎ ቢጠየቅ አማራ በመሆናቸው ወደ እሚል ድምዳሜ እንደርሳለን። ምክንያታዩም ሁለቱም ቴድሮሶች እኔ እስካደመጥኳቸው ድረስ በትግራይ ቀሳውስት ላይ ለዘብተኛዎች ብቻ ሳይሆን ዝምተኛዎች ነበሩ።

ለምሳሌ፤

ካሁን በፊት ቴድሮስ ጸጋየ ያልከነከነው “የባለጌው” የአውስትራሊያው “ጸረ አማራውና ጸረ ኢትዮጵያ የሠረቀ ብርሃን” <<ሂትለራዊና ሁቱ-ኣዊ>> ንግግሮችን በራሱ ሚዲያ ጋብዞት ምን እንደተነጋገሩ እንመልከት፦

አባ ሠረቀ ብርሃን በአደባባይ የተናገረውን ላስታውሳችሁ፡

እንዲህ ይላልለ፦

<< (አማራ የጠራ ዘር) ስሌለው ከዚያም ከዚያም ተጠራቅሞ የመጣ ዘር ስለሆነ አማራ የሚባል ዘር የለም ! ቢኖርማ ያስብ ነበር። ስለዚህም ነው ፤’የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ’ የሚለው። የራሱ የሚባል ዘር የለውም። ከዚህ መጣ ስለማይባል፤ ከትግራይ ከዚያም ከዚያም የተወጣጣ (ስለሆነ) ራሱን ችሎ የመጣ ዘር ስሌለው ‘ሁልጌዜ ሊሸፈን የሚፈልገው ኢትዮጵያ በምትባለው (አገር) ነው’። ለዚህ ነው ሌላ ነገር አይናገርም። ኢትዮጵያዊ ነኝ ብቻ የሚለው።…….

<<………ኦረሞም ኦሮሞኖቱን ይዞ ኢትዮጵያዊ ነው፤ ትግራይም ትግራዋይነቱን ይዞ ኢትዮጵያዊነቱን ይዞ ነው የመጣ፡አማራ ግን አማራነቱን ይዞ ኢትዮጵያዊነት የሚለው ስሌለው፤አማራ የሚባል ዘር ስሌለው፤ ’የሚንጠለጠልበት ዘር ስሌለው’ ኢትዮጵያ በሚለው ተሸፍኖ እየሰራ ስለመጣ “Shame on you! በጣም አፍርባችለሁ።….. >>

<<………..የትግራይ ሕዝብ ሆይ! በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጀነሳይድ እነዚህ አካላት ክደውሃል፡ አማራ ክዶሃል! እመነኝ! እመነኝ! አስረግጬ እነግርሃለሁ። ኢትዮጵያ የምትባል ብትከድህም እግዚአብሔር አልካደህም!”>>

ሲል የወያኔው ማሌሊት ባለጌው ቄስ ሰረቀ በርሃን <<አማራ የፀዳ ዘር ሳይሆን ከዚያም ከዚያም የተጠራቀመ ያደፈ የቆሸሸ ደም “የበታች ዘር (ሎው ካስት)” ነው፤ ሲል በግሃድ ሳይደብቅ በዜና ማሰራጭያ “በትግ’ናዚ” አዋጅ”  ሳይሸማቀቅ አስረግጦ (ሃይላይቱን -አድምቆ) ነግሮናል።

ባለጌው የወያኔ ትግራይ ቄስ እንዲህ ሲል የርዕዮት ሚዲያ ቴድሮሰ ጸጋዬ ወደ ፕሮግራሙ ጋብዞ፤ <<ይቅርታ መጠየቅ ካለበዎት የሚሉበት ነገር ካለ ዕድሉን እነሆ>>፡ በማለት አባ ሠረቀ ብርሃንን ጋብዞ ያለ ምንም “ከባድ ጥያቄና ሊቀርቡ የሚገባቸው ሰረቀ ብርሃን የተናገራቸው የቪዲዮ ሰነዶች ሆን ብሎ የሆነች ትንሽ መናኛ የንግግሩ ክፍል በሴለፎኑ ለአድማጮቹ  በማስሰማት እራሱንም አስገምቶ ሠረቀ ብርሃንን እንደልቡ እንዲጋልብ አድርጓል”  ለድፍረቱ ይቅርታም ሆነ ንስሃ መግባት ቀርቶ “አሁንም ያልኩትን በድፍረት እደግመዋለሁ፡ የሚከራከረኝ ካለ ይምጣ” ሲል ዘረኛ ድንቁርናውን ድፍረቱ ታብዮበታል። ከእያንዳንዱ ውሸት በስተጀርባ ለማታለል መነሳሳትን የሚገፋፋ ታላቅ የጣዖት አምልኮ ትግራይ ውስጥ አለ የምለው ለዚህ ነው። ቴድሮስ ይህ ሁሉ ጉድ አድምጦ <<ይቅርታ መጠየቅ ካለበዎት የሚሉበት ነገር ካለ ዕድሉን እነሆ>>በሚል ሸኘው። ይህ የቴድሮስ ፀጋዬ ወገንተኛ ባሕሪው በሰረቀ ብርሃን ብቻ አልተገታም በአሉላ ሰለሞን (የሩዋንዳው -----የትግሬው ካቡጋ) እንዲሁ ደግሞታል።

<< ትግራይና ኢትዮጵያ ምን እና ምን ናቸው? ከዚህ በህዋላስ ወዴት?” በሚል ርዕስ አሉላ ሰለሞን ካሁን በፊት ያወጃቸው የጥላቻ አዋጆቹን አስመልክቶ ወደ ፕሮግራሙ ጋብዞት እንዲያብራራ ጠይቆት አሉላ ለጥያቄው ሲመልስ አዋጆቹን እያጣመመ እንዳሻው ሲመልሳቸው ቴድሮሰ ሆን ብሎ አሉላ በጽሑፍና በድምፅ ያወጃቸው 10ቱ የአሉላ የዘር ቅስቀሳ አዋጅ “ወንጀል” መሆናቸውን እያወቀ ቴድሮስ ከ10ሩ ውስጥ ነጠላ አዋጅዋን ብቻ መዝዞ እንዲያብራራለት ጠይቆት አሉላ እንዲያ እያወላገደ አንዳንዴም እንደ ጀግንነት ቆጥሮት ዘረኛ አዋጁ “ግቡን የመታ ስኬታማ” እንደሆነ በደስታ ሲገልጽለት ቴድሮስ ፀጋየ አሉላን አጥብቆ ላላመጠየቅ እንዲህ ያለ ወንጀል በቸልታ ዝም ብሎ እንዲያላግጥ ለቅቆታል።

ጸረ አማራ ፕሮፓጋንዲስቶች ወደ ቴድሮስ ሚዲያ ሲቀርቡ ቴዎድሮስ ያለወትሮው እንደ ንብ ሲናደፍ የነበረው ምጡቅ ምላሱ “ሆን ብሎ” ሲሸብበው በተደጋጋሚ አይቻለሁ። እንደፈለጉት ሲጋልቡ እያደመጠ ዝም ብሎ “የፈለጉትን ሲያቦኩ” ይለቃቸዋል። እንደ ቴድሮስ የመሰለ የጥያቄና መልስ ልምድ ያለው “ሕግ የተማረ ሰው” እንዲህ ወርዶ ሳየው ምንም እንኳ በተለያየ ጎራ ብንሰለፍም እንዲያ ያለ ምጡቅ ሕሊና ጠውልጎ በትግራይ አክራሪ እቡይነት ተሸብቦ ሳየው አዘንኩኝ።

ቴድሮስ ጸጋዬ የአሉላ ሰለሞንም ሆነ ሠረቀ ብርሃን የቀሰቀሱት ዘረኛ አዋጅ በተነገሩ የዘረኞቹ ነጥቦች ተስማምቶት ካልሆነ በስተቀር ቴድሮስ ባለው የሕግ ዕውቀት አሉላንም ሆነ ባለጌው ቄስ ሠረቀ ብርሃንን  የሚወጥርበት መሟገቻ ፍሬ ነገር ያጣል ብሎ መገመት የዋህነት ነው።

 አሉላ ሰለሞን የደረሳቸው 10ቱ የጥላቻ መመሪያዎች ፈረንጀቹ እንደሚሉት ሕብረተሰባዊ ኑሮን የሚያደፈረስ “የሞት ቲኬት” የሚሉት ነው። ይህ አደገኛ ጥሪ ያወጀው የትግሬው “ ሐሰን ንገዜ” (የሩዋንዳው መንትያ) አሉላ ሰለሞን በሚገርም ሁኔታ ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋዬ አቅልሎ ማየቱ አንድ ቀን በዚህ ርዕስ ሰዎች አንስተው በታሪክ ይወያዩበታል።

አሉላ አፍጥጦ ሳያፍር እንዲህ ያለውን ቴድሮስን ያላስገረመው የሰለሞን አባባል ላስታውሳችሁ፤

<< የተጋባችሁ ካላችሁ ተፋቱ፤ ያልተጋባችሁ ካላችሁም አትጋቡ የሚሉ አስተያየቶች ብዙ ለቅስቀሳ ውለው ተመለክቻለሁ። “ጋብቻ”  የምተለዋ ቃል፤ ሰዎች አትኩረዋል፤ ጓደኝነትም ጭምር አንስቻለሁ። ቴድሮስ ቤተሰቦችህ ጭምር ሲሰቃዩ ቤተሰቦችህ ያሉበትን ሁኔታ የማይጠይቅ ጓደኛ ነው ብሎ ተደላድሎ የሚቀጥል ሰው ካለ ልታሳዩኝ ይገባል። ከዚህ ሰው ጋር ወዳጅነት መቀጠል አያስፈልገኝም የማለት መብት አለህ።” እያለ እራሱን ከወንጀል ነጻ ለማድረግ ሲመጻደቅና ሰለሞን ሁሉንም እንዳሻው ለብዙ ደቂቃዎች እንዲዘባርቅ ዝም ብሎ ሲለቀው  ነበር

በታወጀባቸው አማራ ማሕበረሰቦች ህይወትና ጋብቻ ግን ችግር ፈጥሬ ይሆናል የሚል ልብህ ውስጥ አለ ወይ? ብሎ አልጠየቀውም ፤ ቴድሮስ ያሳሰበው በዚህ ተንተርሶ በትግሬዎች ላይ የደረሰው ችግር ብቻ ነበር ትኩረቱና ልቡ! ያውም አዋጁ “ስሕተት” በሚል ቀላል ስሕተት አድርጎ  መሳሉ ይገርማል።

ቴድሮስ ሰለሞንን እንዳሻው እንዲዘባርቅ ከለቀቀው በላ እንዲህ ሲል ደመደመው፤

<<ማድረግ  ከሞራላዊ ከማሕበራዊ ዕይታ አንጻር ነው ጥያቄው የነተነሳው እና ባጭሩ ንገረኝ እና ወደ ሌላ ርዕስ እንገባለን። >> የሚል ረዢም ጊዜ እንዲዘላብድ የለቀቀው አልበቃ ብሎት ባጭሩ ንገረኝ እና ወደ ሌላ ርዕስ እንገባለን። ብሎ ደመደመው።

እንደምታውቁት ቴድሮስ ጸጋዬ ዳኒኤል ክብረት እንዲህ አለ ፤ሞገስ እንዲህ አለ፤ አቡነ ኤርሚያስ እንዲህ አሉ ፤ሚሊሺያው ጳጳስ እንዲህ አሉ፤ እገሌ እንዲህ ጻፈ፤ እገሊት እንዲህ ተናገረች እያለ እየተነተነ ጠረጴዛን የሚደበድብ በንዴት የሚንጨረጨር ሰው ነው። በትግራይ ሰው የተጻፉት ስለ 10ቱ ቃላት የጥላቻ ሕጎች በሚመለከት እና በባለጌው ቄስ ሠረቀ ብርሃን የተነገሩት ንግግሮች ግን መንጨርጨሩንስ ተውት ማታለላቸውን እንዳያሰናክልባቸው በጥንቃቄ ነበር የያዛቸው።

ይህ ሁሉ የቴድሮሰ ፀጋዬ ወገንተኛነት (ፓርቲዛን) ዛሬም ቀጥሎበት አቡነ ኤርሚያስ ጋር ሲደርስ ግን ሌላ አባሪና አጋዥ ጋዜጠኛ ቴድሮስ አስፋውን ጋብዞ አቡኑን እስኪበቃቸው ድረስ ሲሰድቧቸውና ሲያሳንስዋቸው ዋሉ። ሠረቀ ብርሃንንም ሆነ አሉላ ሰለሞን ወይንም “ታላቅዋ ኢትዮጵያ” የሚል ተረት ተረት ቅዠት የሚቃዡ አሉ፡  ታላቅዋ ኢትዮጵያ የሚለው ትልቅነት የትግራይ እንጂ እንደሚቃዡት አይደለም”>> ብሎ የተኩራራው የወያኔው ጌታቸው ረዳ ጋር ሲደርስ ግን እንኳን አጋዥ ጋዜጠኛ ጋብዞ ሊተቻቸው ጭራሽኑ እነሱንም ጋብዞ የባሰውኑ እንዲያቦኩ ዕድል እንደሰጣቸውና እንዳከበራቸው እናውቃለን።  ሚስኪኑ አቡኑ አሳዘኑኝ፤ የዘረኛነት ቃል እንኳ አልወጣቸውም ፤ግን ልክ እንደ የፖለቲካ ተንታኝ ተቆጥረው ሚዲያው ሁሉ አረፋውን ሲደፍቅባቸው ነበር የዋለው ያደረው። ይህ ወገንተኛነት ወይንስ ሚዛናዊ ጋዜጠኛነት ትችት?

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)