Monday, April 20, 2020

የፋሽዝም ማጠንጠኛ የሆነው የትግራይ ብሄረተኛነት በትግራይ ተወላጆች መሃል ጉልህ የሆነ የስነልቦና ለውጥ አስከትሏል ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) 4/20/2020


የፋሽዝም ማጠንጠኛ የሆነው የትግራይ  ብሄረተኛነት በትግራይ ተወላጆች መሃል ጉልህ የሆነ የስነልቦና  ለውጥ አስከትሏል

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
4/20/2020

ይህ ጽሑፍ በመጽሐፌ ላይ የታተመ ሲሆን፤ ይህ ጥቅስ ከመጽሐፌ ጠቅሼ ለናንተው ላቀርብ የፈለግኩበት ምክንያት፤ በጣም ቅርብ የሆነ እና እንደ ወንድሜ ስቆጥረው የነበረው፤ አብሮኝ ወደ ስደትና ወደ አሜሪካም አብሮኝ የተሰደደው፤ብዙ ያሳለፍን የድሮ ወዳጄ እንኳን ለፋሲካው በዓል አደረሰህ ለማለት ደውሎልኝ ከዚያ ወደ ማይቀረው የወያኔና የአገራችን አሁን ያለው ሁኔታ አንስተን ስንወያይ ለበርካታ አመታት ስጠረጥረው የነበረውን አቋሙን በተገጋጋለው ውይይታችን ላይ በድንገት ገንፍሎ ያወጣውን ጋሀድ የሆነውን  “የወያኔ ፖሊሲ ድጋፉን እና ጸረ አጼ ምኒልክ መስመሩን” ከምላሱ ሳደምጥ፤ (ምንም እንኳ የተማረ ሰው ቢሆንም) የግንዛቤ እጥረት ሊኖረው የችል ይሆናል በሚል እሳቤ “በአገራችን የተጻፉ መጽሐፍቶችን እንደ ዋቢ ማስረጃ ላቀርብለት ስሞክር ፤ “አማራዎች የጻፉትን ማንበብ ፍልጎት የለኝም!” በሚል  ከምላሱ አምልጦት ሳይሆን በተጋጋለው ውይይታችን በግሃድ የገለጸልኝ የብዙዎቹ ትግራይ ብሔረተኞችን “ነጸብራቃዊ ተመሳሳይ” ዛሬም እንደገና ባልጠበቅኩት የቅርብ ወዳጄ “አብይ አሕመድ ለትግራይ በጀት ስለከለከለ እኔም የትግራይን መገንጠል እደግፋለሁ፤ ለትግራይ የማትሆን ኢትዮጵያ አመድ ሆና ትበታን”  እኔም በንግግሩ በድንጋጤ ተሰምጬ እንዲህ ያለ የጫጨ አቋሙን በማድመጤ ፤ እኔም ት”ግራይ ስትገነጠል፤ባጀት ከኢትዮጵያ በማትፈልገዋ የበለጸገች በሪፓብሊኪትዋ ትግራይ መስራታችሁ ሰላም እስክትለኝ ድረስ ደህና ሰንብት” ተባብለን የበርካታ አመት ወዳጅነታችን በዚህ በመቋጨቱ፤ ብሐረተኛነት ምን ያህል አደገኛ በሽታ እንደሆነ ለመግለጽ ካሳተምኩት መጽሐፍ ልጥቀስና እናነተም ተማሩበት ። ይኼው።

የትግሬዎች ፖለቲካ “ፋሺዝም እንደሆነ ብዙ ጌዜ የተገለጸ ነው። ብሔረተኛነት ደግሞ ሰብኣዊነትህን የሚነጥቅ ክፉ የመንፈስ በሽታ ነው። ፋሽዝም የተጋነነ የጀግንነትን ስሜት ያጠናክራል፤ የወያኔ ትግሬዎች ዘፈኖች የትግራውያንን ታላቅነት፤ ጀግንነት፤ የልዩ ታሪክ ባለቤትነት፤ የሴቶቻቸው ማህጸን ቅድስናና የጀግና ልጆች ፈጣሪነት እንደዚሁም የታጋይ ገብሩ አስራት ሚስት የውብማር አስፋው በጻፈቺው “እስፊንክስዋም ሞታ ትነሳለች” በሚል መጽሐፍዋ እንዳለችው የትግራዉያን የወያኔ የጽናት ተምሳሌትነት በኩራት ያዜማሉ። 

ፋሽዝም በትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ባስከተለው የስነምግባር፤ የአመለካከት ለውጥ ምክንያት ስትመለከቱ፤ ለምሳሌ ያህል ከሰባት መቶ ሺህ በላይ (ይላል አንዳንድ ጥናት) የትግራይ ተወላጆች በኃይል ተከዜን ተሻግረው የወልቃይትን፤ የጸገዴን፤ የጠለምትን ወዘተ መሬት ሲነጥቁ አመለካከቱ በፋሽስት አመለካካት የተቀረጸው የዛሬው የትግራይ ትውልድ ይህንን የሌላውን መሬት ነጥቆ በስግብግብነት ለትግሬነት ብቻ በማጠቃለል የመውሰዱን ድርጊት እንደ ሕገ ወጥና -ሞራላዊ ድርጊት አልቆጠረውም። እንዲያውም ይህንን ህገወጥና ነውረኛ ድርጊት እንደ ጀግንነት ስራ ቆጥሮውት ይፎክርበታል። ወልቃይት ውስጥ ወያኔዎች ሕብ ሰብስበው የስኬዱት ይህንን ዘረኛ ሙዚቃ በዩቱብ አድምጡ ።
https://www.youtube.com/watch?v=hScfnfaqLOY
 
ከትግርኛ ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁ፡ ሁለቱ ዘፋኞች እየተቀባበሉ ያዜሙትን ፍሬ ነገር እንዲህ ይላል

 ጠላቶቻችን በቅናትምራቃቸው እንደ ራበው ውሻ ያንጠባጥባሉ”፤ እኛ አልፎልናል፤ ድል አድርገናል፤ ተደስተናል፤ እኛ  ያሰብነውን  ፈጽመናል፤ ጠላቶቻችን ግን ፈዝዘው  ቀርተዋል/ይፍዘዙ!!  እያሉ ይዘፍናሉ፤ ይፎክራሉ።ሕዝቡም አብሮ በሙዚቃው ተውጦ ጦዟል፡
ደጋግሞም እንዲህ እያሉ ይዘፍናሉ--

"ወልቃይት አገሬ እሷን ነበር የምመኛት፤ ዛሬ በትግል (በጉልበት) አግኝቻታለሁ። ትግራይ አገሬ፤ ቆንጂት አገሬ፤ ጠላቶችሽ ፈዝዘው ይቅሩ፤ አንቺ ነሽ ሞራሌ፤ አንቺ ነሽ ወኔዬ። የትግራይ ልጅ፤ የወያኔ ልጅ በማንነቱ የማይደራደር፤ በምንነቱ የማይሳሳት….በጥፍሩ ጥሮ ግሮ ሃብት የሚያፈራ/የሚያለማ። በጥፍሩ ጥረቱን አሳይቶ ባሸናፊነት የወጣ የትግሬ ልጅ። ዘራፍ አለ በወልቃይት፤ በደጀና በቃብቲያእሰይ ይበል የትግሬ ልጅ ባለ ድርብ ዋልታ። እሷ(ወልቃይት)ነበረች በትግል  ወቅት  ስመኛት  የነበረች፤ አሁን አግኝቻታለሁ። የምንመኛትን ወልቃይትን አንለቃትም፤ በል የወያኔ ጎበዝ፤ እና የወያኔ መስመር ተከታይ! ቦታ የለንም ለትምክሕተኞች። እሷን ለትምክሕተኞች አንለቅም። ጣፋጭ ፍሬ የተሸከመውን ወይም ያረገዘውን ዛፍ አንሰጥም። የወልቃይትን ለም መሬት ለትምክሕተኞች (ለአማራ) አንለቅም። አራስ ላማችንን፤ ፍሬ ያላት ዛፋችን ለአማራዎች አንሰጥም፤ (ለአማራ) ትምክህተኛ ኃይል አንሰጥም"  የሚለው ስንኝና ሙዚቃ የሚያመለክተን በአክራሪ ብሄረተኞች እየተገለጸ ያለው ፋሺስታዊ ልሳን ከላይ የጠየቀስኩትን በጸያፍ ቃላቶች የታጀበ የትግራውያን ፉከራ ምንን ያመለክታል?

የአንድ ህዝብ ወይም ጎሳ ተወላጆች የአክራሪ ብሄረተኛነት መገለጫ በሆነው የፋሽስት ስርዓት እብደት ውስጥ ጭልጥ ብለው ሲገቡ እንደዚህ ከላይ በጠቀስኩት መልክ ይሉኝታንና ነውርን በማያውቅ መልክ በእብሪት ይደነፋሉ፤ ይፎክራሉ። ወዳጄ ዶ/ር አሰፋ በመጽፌ ውስጥ የጠቀስኩት በጦርነቱና በአብዮቱ ምከልንያት ትግራይ ውስጥ የተጸነሰው ፋሺዝም ምን እንደሚመስል እንዲህ ይላል።

በጦርነቱና በአብዮቱ ምክንያት ትግራይ ውስጥ የተጸነሰው ፋሺዝም


የጣሊያን ፋሽዝም አውሮፓን አውዳሚ የነበረውን የአንደኛው የዓለም ጦርነት ታኮ ስልጣን ላይ እንደ ተቆናጠጠ ሁሉ የትግራይ ፋሽዝም ኢትዮጵያን አውዳሚ ከነበረው የአስራ  ሰባት ዓመታት ጸረ-ደርግ ትግልና ኢትዮጵያን የቀዝቃዛው ጦርነት ዋና መራኮቻ ካደረገው የካፒታሊስቱ (የምዕራቡ) ጎራና የሶሻሊስቱ (የምስራቅ አውሮፓ) ጎራ ፉክክር ዋነኛ አትራፊ ሆኖ በግንቦት ሃያ ቀን 1983 . ስልጣን ተቆናጧል። በዚህም ምክንያት ይህ የወያኔ ብቸኛ የስልጣን ባለቤት መሆን የትግራይን ህዝብ በኢትዮጵያ መቃብር ላይ የምትገነባው የአዲሲቷ የበለጸገች ትግራይ ባለቤት ከማድረጉም በላይ የትግራይ ተወላጆች ከትግራይ በታች ያለውን የኢትዮጵያን ሃብት በብቸኝነት እንዲዘርፉና ታይቶ የማይታወቅ የሃብት ባለቤት እንዲሆኑ አስችሎአቸዋል። የትግራይ ተወላጆች የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ተቀላቅሎ በታሪካቸው አይተውት የማያውቁት ፍስሃና ልማት ያመጣላቸውን መንግስት የሚጥሉበት ምክንያት የለም ብዬ ከሃያ ስድስት ዓመታት በላይ ስንሟገት የነበርነውን ጥቂት ኢትዮጵያውያን እንደ ጥላቻ ሰባኪ ሲያዩኝ ቆይቶአል። እላችሁላሁኝ የትግራይ ህዝብ የወያኔን የፋሽስት ስርዓት እስከ ወደቀበት የመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ አብሮት ይዋጋል፤ ይዋደቃልም። ከወያኔ መውደቅም በኋላ የትግራይ ህዝብ ካለ አግባብ ወያኔ እየዘረፈ ትግራይን የገነባበት ሂደት እንዲመለስ ጠመንጃውን ይዞ ተተኪውን የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነት ይገጥማል። ይህንን ዛሬም በድጋሚ ከዛሬ ሃያ ስድስት ዓመታት ጀምሮ እናገር እንደነበረው ካለጥርጥር በጥላቻ ሳይሆን በእውቀት ላይ የተመሰረተን ጥናት ተንተርሼ  በእርግጠኛነት  እናገራለሁኝ። ጭፍን አምባገነንነትን የሚያራምድ ወይኔን የመሰለ ፋሽስታዊ የፓለቲካ ስርዓት ተከታዮቹን በማያቋርጥ አብዮታዊ እንቅስቃሴና በማያቋርጥ ፋሽስታዊ ፕሮፓጋንዳና ትምህርት ጠምዶ በማደንዘዝ ይገዛል።  የሚለው የዶከትር አሰፋ ነጋሽ ጥናት ዛሬ የብዙ አመት በሆነው የትግራይ ተወላጅ ወዳጄ ሲንጸባረቅ ማድመጤ እውነትም ፋሺዝም/አክራሪ ብሔረተኛነት አደገኛነቱ በቅርብ ሰው እንደገና ማየቴ ፋሲካ በማልረሳው ትዝታ አክበሬ ዋለኩኝ።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)