Monday, March 16, 2009

የ“ህወሓቶች” አርአያ ደጃዝማች ገበረስላሴ

የ“ህወሓቶች” አርአያ ደጃዝማች ገበረስላሴ ከታሪክ ሠነድ ጌታቸዉ ረዳ
ኣብዛኛዉን ጊዜ ኢትዮጵያን ያጠቃት ሃይል “የዉጭዉ ወራሪ” ሳይሆን “ከዉስጥ ሆኖ ለጠላት ያደረ፤ እንደ መለስ ዜናዊ ዓይነቱ የቅኝ አዙር ገዢዎች አጎብዳጅ፤ ለዓለማዊ ስልጣኑ ያደረ ዜጋ ነዉ”። በፈረንጆች እና በዓረቦች የሚንቀሳቀሰዉ “ህወሓት” የተባለዉ የባንዳዎችና የዘመናችን የመኳንንት ስብስብ ኢትዮጵያን በማፍረስ ላይ ግምባር ቀደም ሚና የሚጫወተዉ ለብዙ ኣመታት ህወሓት ከተመሰረተበት ጀምሮ በበላይነት እየመራ ያለዉ “የዓድዋዉ ቡድን” እንደ ሆነዉ ሁሉ፤ በጣሊያን ጊዜም በባንዳነት ጣሊያንን ያገለገሉ ምርጥ የዓድዋ ፤የአክሱም እና የእንደርታ መኳንንቶች እንደነበሩበት ታሪክ ያስረዳል። ለዛሬ ከታሪክ ሠነድ መርጬ የማቀርብላችሁ ከትግራይ መኳንንት አንዱ ደጃዝማች ገብረሥላሴ ይሆናሉ።በወቅቱ ኢትዮጵያን ለመዉረር ያኮበኮበዉ አስመራ ይኖር ለነበረዉ ለፋሽስቶቹ ወኪል “ለኮማ ንዳቶረ ማርቲኒ” የጻፉት ደብዳቤ መጬዉ ትዉልድ እንዳይረሳቸዉና ዛሬ ያለነዉ ተቃዋሚ ክፍሎችም ባንዳዎች “በክፉ ቀን” ምን ያህል “ርቀት ተጉዘዉ አገራቸዉን ለግል ጥቅም መሸጥ እንደሚችሉ” ለማሳየት ነዉ። መለስ ዜናዊ ኤርትራን ሲያስገነጥል ከአስገንጣዮች እና ከተገንጣዮች ልቆ ያስሰማዉ የነበረዉ “ለሻዕቢያ/ለ ኤርትራ ፍቅር” ዉክልና ልብ ብላችሁ ብታጤኑት፤ በዛም ምክንያት ‘በብዙ ኢትዮጵያዉያን/ት አገር ወዳዶች ዘንድ ሁሉ እንደተጠላዉ ሁሉ። ደጃዝማች ገብረሥላሴም በደብዳቤአቸዉ የሚሉት ለጣሊያን ፍቅር የተነሳ “የኢትዮጵያ ሞኳንንት ሁሉ ለምን ጣሊያን ወደደ ብለዉ ሁሉም ጠሉኝ፡ ለማጥፋትም ተመኙኝ…” ይላሉ። ደብዳቤዉ እንዲህ ይነበባል። አንዳንድ ቦታዎች በቅንፍ የምታዩት በቅንፍ ከኔ የተጨመረ ቃላት ምን ለማለት አንደሆነ በግድፈት የተዉት ቃላት ወይንም በያኔዉ አነጋገር እና በዛሬዉ አባባል ለማሳየት ነዉ። “ይድረስ ተክቡር ወልዑል ወዳጄ ኮሚንዳቶራ ማርቲኒ። ጌታየ ሆይ አሁን በረሃ ለበረሃ ስዞር እርስዎ የኮሎኒያ መንግሥታ (መንግሥት) ሆኑ ሲሉ ብሰማ አዘኔ ቀለለኝ ተስፋየም እንደገና በረታ። እኔ ተዋጋት (ተዋግቼ) የደረሱበትና ፊትም ድል ማድረጌ ሗላም ድል ከመሆን የደረስኩበት ነገር በኢጣሊያ ፍቅር የተነሳ ነዉ። በኢጣሊያ ፍቅር የተነሳ ባይሆን ግን እርስዎ እንደሚያዉቁት ሹመቱና ማረጌ (ትልቅ) ነበረ። ከኢትዮጵያ ሁሉ መኳንንት በኔ የማይቀና አልነበረም። ሓላ ግን ለምን ኢጣሊያን ወደደ ብለዉ ሁሉም ጠሉኝ። ለማጥፋት ተመኙኝ። ኢጣሊያ የትሪፖሊን ጦርነት በጀመረች ጊዜ ራስ ስብሐት ባሻ ብዙቅ ሁሉ (ባሻ ብዙቅ እያሉ ያሉት ባንዳ ሁሉ ማለታቸዉ ነዉ) ወደ ትሪፖሊ ሄዷልና ይሂን (ይኼኔ) ጊዜ ኢጣሊያን እንዋጋና አገራችንን አስከ ምጽዋ ድረስ መልሰን እንያዝ ብሎ ላዲስ አበባ መንግሥት መከረ። ከዚህ ወዲያ ያበሻ መንግሥት ከራስ ስብሐትና ከደጃች ስዩም ጋራ ሁነህ ኢጣልያን በድንግት ገስግሰህ ዉጋዉና አገራችንን አስለቅቅ፡ እሄን ያደረክ እንደሆነ ኢጣልያ ይዞት የነበረዉን ሁሉ አገር ራስ አሰኝተን ለአንተ እንሰጥሃለን አሉኝ። እኔ ግን አይሆንም እንዋረዳለን ከኢጣልያ አንጣላ ደግሞም ምንም ተከፍሎ ጥቂት ወደ ትሪፖሊ ቢሄድ አሁን ያለዉ የጣሊያ ጦር እልቅ የለዉም ብየ አስፈርቸ (አስፈራርቼ) አስቀረሁ። በዚህ ነገር ሁሉ አቅማማሁ፡ ይልቁንም ራስ ስብሐትና ደጃች ስዩም ለኢጣሊያ አግዞ ነዉ ብለዉ አሳጡኝ። ጠላቴም ባዛ፡ ከዚህ ቀጥለዉ እኔ የጣሊያን ምክር ሰምቶ ሰራዊቱ ሁሉ ወዳገሩ አሰናብቶ ጥቂት ራሴን ሁኜ ወደ አዲስ አበባ እሄዳለሁ ስል ሰራዊቱን ማሰናበቱን አይተዉ አደጋ ጥለዉ ወጉኝ። ነገር ግን በፊት ድል አድርጌ የጣልያን ብርቱ ጠላት ራስ ስብሃትን ገደልሁ። ያስመራ መንግሥት ጥቂት አይዞህ ብሎኝ ቢሆን የጣልያን ጠላት ሁሉ አጠፋዉ ነበርሁ። ድል ታደረግሁ በሗላ ድል መሆኔ ግን እኔ ስለሷ ስዋጋ ኢጣልያ ዝም በማለቷ ነዉ። ኢጣልያ ዝም ስትል ሲያይ ጊዜ፤ለኔ ሊያግዝ ምሎ የነበረዉ ሁሉ የድፍን ትግሬ መኳንንት ፈርቶ ከዳኝ። አሁን አንዲህ በርሃብና በጥማት እየተቆላሁ በረሃ ለበረሃ እንከራተታለሁ። አንድ ነገር ብቻ ደስ ያለን ምሽቴና ሁለት ልዦቸ (ልጆቼ) ከጣልያ እጅ ሁነዉ በደግ ስለተቀመጡልኝ ነዉ አሁን የታመነ ብዙ ጦር አለኝ። ያገዛችሁኝ እንደሆነ እያደረ ይበዛል። ያላገዛችሁኝ እንደሆነ እያደረ ይጠፋል እንጂ አይበዛም። እርስዎ ትልቁ ወዳጄ ምንሰትር ሁነዉ በርግጥ እንዲያስቡልኝና እንዳያስጠቁን አዉቀዋለሁ። የሚቸግርዎ እንዳለ አዉቃለሁ። በርስዎ ሃይል በርስዎ አጋዥ ኢጣልያ አይዞህ ያለኝ እንደሆነ ድፍን ትግሬ ተጸለምት አስከ ስቆጣ አስከ አሸንጌ ያለ ሁሉ መኳንንት እንዲያግዘኝ የታወቀ ነዉ። ነገር ግን መቼም በጥቅምትና በህዳር ጠርነት ላይቀራችሁ ነዉና እሄን ጌዜ ጀምራችሁ አግዙኝ ብየ ብልከ ከሮማ ፈቃድ አልመጣልኝም ብለዉ ምላሽ መለስዩልኝ። አሁንም ጌታየ ወዳጅ ተስፋየ ሁሉ ከርስዎ ላይ ነዉና አደራ አይዞህ ብለዉ ተሎ ይላኩልኝ። መድሃኔ ዓለም ጤናና እድሜ ይስጥልኝ ብየ እጅ እነሳለሁ። ደጃዝማች ገብረስላሴ የጥንት ወዳጅዎ አሁንም የሚያምንዎ።”