ከዚህም ከዛም
ክፍል 1- እናዉቅላችሗለን ለሚሉን “ጸሃፍት እና ድረገጸቻቸዉ”
ከጌታቸዉ ረዳ
ሰሞኑን ደግሞ “መድረክ” የተባለ የወያኔ “ነበር” ፕረዚዳንቶች፤”ነበር” ወያኔ ጀኔራሎች እና “ነበር” የወያኔ ሊህቃን መሪዎች በተጠቀሰዉ “መድረክ” በተባለዉ የመገናኛ አዉድ - ወይዘሪት ብርቱካን የምትመራዉ አዲሱ “የተቃዋሚ ድርጅት” እና ተቃዋሚ የተባሉት የወያኔ/ኢሕአዴግ ፓርላሜንታሪያን/አባሎች (እነ መራራ እነ በየነ …) “ተቀላቀለ” የሚል ዜና ሰምተናል። ምን ለምደርግ እንደሆነ “ትንንሽ ነጥቦችን” ለቅምሻ ቢወረዉርልንም መሰረታዊ የመጨረሻ ግቡ **“ወያኔን” በሌላ አነጋገር-“ቡድን-39” ብየ የምጠራዉን ዓረና እና ከመለስ ወያኔ ቡድን ጭምር (ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸዉ እና )” /ወያኔን ለመጣል/ለመለወጥ/ ለማሻሻል ወይንስ ደግሞ --- “የኢትዮ-ሚዲያዉ አዘጋጅ ወንድሜ አቶ አብረሃ በላይ በዌብ ሳይቱ ርዕስ እንደሚነበበዉ “ወያኔ የኢትዮጵያ እና የትግራይ ጠላት ስለሆነ “መጥፋት” አለበት የሚለዉ መሪ አቁዋም ተግባራዊ ለማድረግ? ?
የወንድሜ የአቶ ግርማ ካሳ አንደኛዉንም ወያኔን አትንኩ/አትዝለለፉ ስላሉን አቋማቸዉ እናዉቀዋለንና አዲስ ነገር ሲመጣ ተሎ ከበሮ የመምታት ልምድ ስላላቸዉ ብዙም አልገረመኝም። ከላይ ያለዉ ጥያቄ ግን ፦ለጥያቄዉ መልስ “ከመድረክ- አባሎች” መልስ እንጠብቃለን። መድረክ የተባለዉ አዲስ “እርግብ” አላማዉ ምን ድነዉ? ለመጣል/ለማስወገድ/ለማሻሻል/ለመመሳሰል/ለመጎዳኘት/ለመሞዳሞድ/ለማገዝ/ -ወይስ “ከምርጫዉ በሗላ መረራ ጉዲና ሸዉዶን ፓርላማ ሲገባ እንዳለን “ፓርላማ ዉስጥ ገብቶ “ደሞዝ” ለማግኘት ? መልሱ እንጠብቃለን።
አቶ ግርማግርማን ማንሳቴ ላልቀረ እሳቸዉንም ልጠይቅ። እነገብሩ ካልመጡ ወያኔን መጣል አይቻልም ሲሉን ለመሆኑ እነ ገብሩስ እነ ስየስ ቢሆን በማን እጅ ሆኑ እና ነዉ መለስን ለመጣል የሚችል ታምር ሊኖራቸዉ የሚችል? ራሳቸዉን መከላከል ያልቻሉ ወህኒ የበሰበሱ ምስኪኖች ‘መለስን ይጥላሉ እኛን ነጻ ያወጡናል ስትሉ ይገርመኛል።
ለመሆኑ የሕዝብ ታላቅ ታሪክ ሰሪነቱ እንዴት ረሳችሁት? ካለ ዓረና ሱታፌ፤ካለ ጊዳዳ ካለ ስየ ሱታፌ በምርጫዉ ወቅት ወያኔን መድረሻ አሳጥቶት አልነበረም? መለስ መሬት ጠብባዉ ደብረዘይት ድረስ ተሸሽጎ አልነበረም? ዓረና እና መሰሎቻቸዉ እማ ቅንጅትን ለመምታት “ልዩ ኮሚቴ አዘጋጅተዉ እንደ ነበር ጀኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት (ዑስማን) በደሃይ መጽሄት ነግሮን ነበር። አቶ ግርማ ካሳ ትግረኛ ያነብባሉ የሚል ግምት አለኝ (ካልተሳሳትኩ) አቶ ግርማ ይህነን ምስጢር ለምን ድነዉ የሚሸሽጉን? ወይስ አሁን ምን ክስተት ተፈጠረ እና ነዉ “እነ “ነበር” ፕረዚዳንቶች፤ጀነራሎች፤ ነበር ወያኔ መሪዎች” እንደ ደርግ ወታደሮች እንጠቀምባቸዉ የምትሉን? ለመሆኑ ሁለቱ ክስተቶች “ልዩነታቸዉ ያዉቁታል? የወያኔ ታጋዮች/መሪዎች እና እና የደርግ ጀኔራሎች/ወታደሮች” አመለካከት አንድ ነዉ? እንሸዉዳቸዉ ቢባልስ “ይቻላል?”
ዉድ አንባቢዎች ሆይ፡ “ዋች ዶግ” (ታዛቢ) የሚባሉ ክፍሎች በፖለቲካዉ ዓለም እንዳሉ የምታዉቁት ነዉ። ታዲያ በኛዉ ማሕበረሰብ አልተለመደም እና “የዋች ዶግ- የታዛቢ” ጭሆት እና ስራ ስንሰራ “አፍራሾች” የኤርትራ
ዜጎች ስለሆናችሁ ወደ ኤርትራችሁ ሂዱ ከኢትዮጵያ ዉጡልን ይሉናል። የማንባለዉ የለም።
አብሶ እማ ለእኔ እና ለወንድሜ አቶ እያሱ አለማዮህ “የትዝብት ስራችነን በጦቆምን እና በጻፍን በጮህን ቁጥር” ጭራሽኑ “ኤርትራዉያኖች አድርገዉን ከኢትዮጵያ ዉጡልን፤ዜግነታችሁ ኢትዮጵያዊ አይደለም እያሉን ነዉ። ይሄ ደግሞ አሲምባ ከተባለዉ የህዋ ሰሌዳ (ለኔ በተለይ) እና ሰሞኑን ደግሞ አቡጊዳ ከተባለዉ የህዋ ሰሌዳ የዉይይት መድረከ ሃሳባችንን በለገስን ቁጥር “ዜግነታችን” ጭራሽኑ ተገፍፈን መድረኩ ሆን ተብሎ ለሚዘልፉን ለዘረኞች እየተፈቀደ “ባዙሪት” ደም ፍላታቸዉን ለመወጣት እየተወጡ ታዝበናል።
በሁለቱም መድረኮች ተመሳሳይ “መፈክር” በድረ ገጾቻቸዉ ተለጥፎ ተለይቶ ይነበባል። “አሲምባ ዳት ኦርግ” ልጀምር፦ አሲምባ የተባለዉ መድረክ ስታነቡ “የሚከተለዉን ታነባላችሁ- “እምቢኝ ለአንጃዎች!ለሆዳሞች! ለበታኞች!እምቢኝ እመቢኝ ለወያኔዎች! ለዘረኞች! ለጎጠንነት! ወዘተ…”ይላል። ታዲያ ወደ የዉይይት መድረካቸዉ ገብታችሁ ስትፈትሹ “ዘረኞችን፤ጎጠኞችን፤ጸረ ኢትዮያ አስተያየቶችን ፤የብልግና ቃላቶች የሚጽፉ ሰዎችን አረጋዉያን ቤተሰቦቻችንን የሚዘልፉ ቃላቶችን የሚጽፉ ግለሰዎች ሲያስተናግዱ ደግሞ ታነባላችሁ። አስቀድሜ ለህዝብ ይፋ ስላደረግኩት አሁን መድገሙ ያሰለቻል እና ወደ አቡጊዳ ድረ-ገጽ እንለፍ።
ወደ አቡጊዳ ወደ ተባለዉ ድረ ገጽ ስትግቡ ደግሞ ልክ እንደ አሲምባዉ “መፈክሩ” ከላይ አሸበርቆ ይነበባል “የአደራ ዕዳ” ይላል - ከ ወደ ዉይይቱ መድረክ ስትገቡ ደግሞ አንድ ዘበኛ እንዲህ ሲል ከበሩ አፋፍ ላይ የተለጠፈ መፈክር ያስነብባችሗል - “ህወሓት እና ሻዕቢያ መድረካችን ላይ አስጸያፊ ቃላቶችን በመጻፍ ስላስቸገሩ ሁሉንም አስተያየት ሳንሱር ለማድረግ ተገደናል። አስተያየትዎ ከተገመገመ በሗላ እንለጥፈዋለን። ከይቅርታ ጋር።(አቡጊዳ) ይላል፡፤
ታዲያ ሻዕቢያ እና ህወሓት ብቻ እንጂ ኦነጎችን ወይንም “ኢትዮጵያዉያን” አስጸያፊ ቃላቶችን አይጽፉም የሚል አቋም በመያዝ የሚከተለዉ አስጸያፊ ብቻ ሳይሆን “ዘረኛ” ጽሁፍ እራሳቸዉ ገምግመዉ “የይለፍ” ፈቃድ አትመዉ እንዲለጠፍ ፈቅደዋል። የሚከተለዉ እንዲህ ሲል ስለ እኔ እና ስለ አቶ እያሱ አለማዮሁ “ወደ ኤርትራችሁ ሂዱ” የሚል በአቡጊዳ ሳንሱር ፈቃድ የተለጠፈዉ -ልጥቀስ GUYs, leave alone the lost Getachew Reda. Is Getachew Reda Berhane Meskel Reda’s brother? Getachew Reda is another Eyasu Alemayohu from Eritrea. Both are hidden snakes to poison Ethiopia’s unity and Ethiopians in support to their Eritreans in Menlik’s Palace. Getachew Reda will continue with his destructive and divisible against all oppositions parties except on his Eritreawi Eyassu’s EPRP. UDJ stands for Ethiopia’s unity, democracy and freedom of Ethiopians and belongs to Ethiopians not to Eritreans. The Eyassu Trojan Horse Getachew Reda must take off his hand from our country Ethiopia peacefully. Getachew was very busy hand from our country with his divisible articles when Ethiopians were created AFD. And we know now how this man has involved in destroying of CUPD and KIL along with Meto Aleka’s son in law (Eyaassu). Who knows may be millions dollars is behind the door. So Getachew must be leave our Ethiopian’s issues for Ethipians, other wise you will face Ethiopians. Your country (Eritrea) is separated from Ethiopia. You have done all what you could for it’s separation.” End of quote. ዉድ አንባቢዎች ይህ እና ይህንን የመሳሰሉት የዜጎችን መብት የሚነጥቁ ዋልጌዎች በተጠቀሰዉ “ዌብ ሳይት” አዘጋጆች ተነብቦ ፤ተገምግሞ “የስደብዋቸዉ፤ዝለፏቸዉ፤ኢትዮያጵያዊያን አይደሉም ብላችሁ ለዓለም ንገሩ፡ በማለት “ ድረገጻቸዉ ከሚለጥፈዉ መፈክር “በተቃራኒ” ጽሁፉን ገምግመዉ በእዉቅናቸዉ ሲለጠፍ ታዝበናል። ትግላችን ከወያኔ ብቻ ሳይሆን እኛን መስለዉ የዘረኝነትን ጽሁፍ አንብበዉ ገምግመዉ ይለጠፍ በማለት የሚለጥፉ የድረ-ገጽ ባለቤቶችን ለኢትዮጵያዉያን በመንገር ለታሪክ እንድትመዘግቧቸዉ ይሄዉ አቤቱታችነን ከማስተላለፍ አንቆጠብም።
ይህንን ስንል ደግሞ “ትግሉ እናቆማለን ማለት እንዳልሆነ እነዚህ ተባባሪዎቻቸዉ እንዲያዉቁልን ደጋግምን ለማሳሰብ እንወዳለን።
2ኛዉ ክፍል ለአቶ ግርማ ካሰ የሰጠሁትን መልስ አንብቡ።
አቶ ግርማ ካሳ በወያኔ ተገደሉብን የምትሉ ሰዎች አደብ አድርጉ ፤ሕግ እስክናቋቁምላችሁ እነ ገብሩ እነ ስየ እነ አዉዓሎም እነ እነ የወያኔ ፕረዚዳነቶች እና ሊህቃኖች እና ጀኔራሎች እና ባቶ ግርማ ካሳ ድርጅት በመተባበር እያሰብንላችሁ ነዉ እና እስከዛዩ አፋችሁን ክደኑ “አደብ! አደብ!” እያሉን በዛዉ ድረገጽ ዉይይት መድረክ አንብበናቸዋል።
ወንድሜ አቶ ግርማ ካሳ “በዓረና/በወያኔ” የተሰቃየበዎት/የተነጠቀበዎት ወንድም ዘመድ ወዳጅ፤ጎረቤት ጓደኛና የትግል ጓደኛ ላይኖረዎት ይችላል እና የቤተሰብ ሃዘን አልተሰማዎትም። "እንዴታ አለኝ እንጂ" ነገር ግን በሗላ እንተሳሰብ "በገደሉብን፤ በነጠቁብን፤አገር በሸጡት፤አገር ባዋረዱት" ሰዎች እጅ በእነ ገብሩ በእነ በእነ..በእነ "ነጻ"-እንወጣለን የሚሉትን ፖለቲካዎ "ለመሞኘት እና ለማሞኘት" መብትዎ ነዉ እና አከብረዋለሁ። ነገር ግን ካሁን በፊት "ወያኔን መዝለፍ፤ አፋኝ፤ገዳይ፤ባንዳ፤ ጨቋኝ ...ማለቱን "መቆም አለበት!"የሚል ትዕዛዝዎ ሲያስተላልፉልን "ሞኝነትዎን አከበርን። ሞኝነትዎን ግን መልሰን "እባክዎ ወደ እኛ ጅላጅል ፖለቲካዎን አያስተላልፉት? ወደያ ይጣሉት" ስንለዎት "ተቆጥተዉን ነበር" ግን ትንሽ ሳይቆዩ ከሕልምዎ "ባነኑ እና" ወደ ልብዎት ሲመለሱ "እኔስ መስሎኝ ነበር" ብለዉ ደግሞ ሞኝነትዎን" አስተካከሉ እና ወደ ልብዎ ገቡ። ያ ያስታዉሱታል የሚል እምነት አለኝ። አሁንም ወያኔ በተጠጋዎት ቁጥር “ተስፋ፤ተስፋ ተስፋ” የሚል መፈክር እያሰሙን ነዉ “መልካም ተስፋ ለሁላችን”
እኔ የሚገርመኝ አሁንም አርስዎ እነ ስየ እነ ገብሩ የትግራይን ህዝብ ወደ እኛ እያስገቡልን ነዉ እያሉን ነዉ ። ስልትዎን አደንቅለዎታለሁ "ዉጤቱ ሳይ" በበለጠ አድናቆቴን እለግስለዎታለሁ። ያስ ባልከፋ ነገር ግን ቤተሰቦቻችን ያዉም በሺዎቹ የትግራይ ዜጎች አሁን እርስዎ ነጠላዎን "አወንዝፈዉ" "ሽር ጉድ በሚሉላቸዉ ነብሰ ገዳዮች እና አገር አስገንጣዮች" እጅ ቤተሰብ እና ጓደኛ ያለቀባቸዉ የትግራይ ሰዎች እና የተቀሩት ኢትዮጵያዉያን ጩኸት "ሲያጣጥሉ" ሕግ “ሲቋቋም ገድለዉ በድለዉ ከሆኑ እንተሳሰባልን” በማለት ፍረደ ገምድልነትዎን አስሰምተዉናል። እኛ የእርስዎ ተባበሪነት ማጣት እንጂ
እዚሁ ሲመጡ ከስሰን ፍረድ ማግኘት ይቻል ነበር ነገር ግን ለዚህ አልታደልንም። የሕግ ሰዎች ምናልባት እያነበቡኝ ከሆነ ምን እያልኩ እንደ ሆነ ከገባቸዉ ሃለፊነታቸዉ በተግባር ያሳዩን፡እዚሁ አገር- “አሁኑኑ!!
ግርማ ካሳ "ጅልነትዎ አሁን ሳይሆን፤ ለወያኔ ማዘንዎ መከላከልዎ አሁን ሳይሆን" የቆየበዎት በሽታ ስለሆነ አስከዚያዉ ግን ፡ነብሰገዳዮችን የማጋለጥ፤ባንዳዎችን የመኮነን፤ስረዎቻችን አና ማሕደሮቻቸዉን የመጻፍ መብታችንን እባክዎን በሚከላከልሉዋቸዉ በወያኔ አምላክ ስም አይንፈጉን" ገዝቸዎታለሁ!