Thursday, March 22, 2018

የወያኔ ትግሬዎች ዕብደት ለመግለጽ አዲስ መዝቀበ ቃላት ያስፈልጋል ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


የወያኔ ትግሬዎች ዕብደት ለመግለጽ አዲስ መዝቀበ ቃላት ያስፈልጋል
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
 
በቅርቡ በጣም ያስደነገጠኝን ነጠላውን የጣለ የወያኔ ትግሬዎች ዕብደት በምን ያህል ፍጥነት አድጎ የትግራይ ታዳጊ ወጣቶችን አመለካከት እንዴት እየበከላቸው እንዳለ አንድ የቅርብ ወዳጄ የላከልኝን ፎቶግራፍ  ከተመለከትኩኝ በኋላ፥ወደ ድረገጽ እንዳልመጣ የወሰንኩትን ውሳኔ እንድሽር አድርጎኛል። ወያኔዎች የመሠረቱት የ17 አመት የጫካው “የትግራይ ፋሺስዝም ፍልስፍና” ዛሬ ዓይን እጅ እና እግር አውጥቶ በትግራይ ታዳጊ ሕጻናት ሕሊና ውስጥ እንዲሰርጽ አድርጎ ‘አገራዊ ማንነታቸውን’ በሰፊዋ ኢትዮጵያ ሳይሆን እንደ ኤርትራኖቹና እንደ ኦሮሞዎቹ በጠባብዋ ትግራይ መልክአምድር ዙርያ ብቻ እንዲንገበገቡ ማድረጉን ይህ የሚተለው ፎቶግራፍ ገላጭ ማስረጃ ነው።

ፖለቲካው ባልገባቸው ምንም በማያውቁ በነዚህ ታዳጊ ወጣቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው የሕሊና ነጠቃ ስንመለከት ወያኔ ዛሬ ፋሺስታዊ መስመሩን እያጠናከረ ወደ ግንጠላ እየሄደ መሆኑን ብዙ ሰዎች እየተረዱት መሄዳቸውን እርግጠኛ ነኝ። ሆኖም ትግሬዎች ቢገነጠሉ የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው በምናሙ ዓለም እንደሚሰበኩት ሳይሆን ከኤርትራኖች ኑሮ በከፋ መልኩ እንደሚኖሩ ዕርግጥ ነው።

እነሱ ብቻ ሳይሆኑ በአካባቢ ፋሺስታዊ ፍቅር የቀወሱት የኦሮሞ ምሁራን ተብየዎችም የቄሮዎቻቸውን ሕሊና በመጥለፍ ‘ኦሮሚያ’ የሚሉት የግንጠላ ዘመቻ ከተሳካላቸው “በአክራሪ ኦሮሞ እስላሞች እና በአክራሪ ኦሮሞ ጴንጤ፤ ኦሮሞ ኦርቶዶክስ እና ፕሮሰተስታንት፤ እንዲሁም በባሌ ሶማሌዎች ውጣ አልወጣም፤ አቁም አላቆምም፤ድምበሬ ነው ድምበርህ ኢይደለም” የመተላለቅ ፍጅት እንደሚከሰት ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለውም። ያኔ የዛሬዎቹ ነፃ አውጪዎች ኑ ቢባሉ ቢሞቱ አይሄዱም። ዛሬም አልሄዱም ለወደፊቱም አይሄዱም። በትገሬዎቹም በኩል እየተመኙት ያለውን ዕብደት ከተሳካላቸውምበተለይ በጠላትነት በፈረጁት እና ብዙ ግፍ በፈጸሙበት በአማራ አካባቢ ሕዝብ መልክአ-ምድር ተከብቦ የሚኖሮው ህይወት ምን እንደሚመስል የፖለቲካ ነብይነትን መሆን አይጠይቅም። የመከራ፤ የንትርክ፤ የብስጭት፤ የጭነቀት፤ የቁጭት፤ የስደት፤ የረሃብ፤ የጉስቁልና የግጭት ህይወት እንደሚገጥማቸው እርግጠኛ ሆኖ መናገር ስህተት አይደለም።

ከጫካው ዘመናቸው ጀምሮ ለበርካታ አመታት “የአክሱም፤ የሽሬ እና የዓድዋ (አሽዓ)” ወያኔ መሪዎች ከእነሱ የተለዩትን የትግሬ፤ የራያ፤ የዓጋመ፤ የተምቤን፤ የሁለት አውላዕሎ ትግርኛ ተናጋሪ አካባቢ ኗሪዎችንና ታጋዮችን የትግርኛ አነጋገር ዘይቤአቸውን ወደ “አሽዓ” እና “ሓማሴናዊ” ትግርኛ በመለወጥ ያደረጉት ስልት በ3/4ኛው ተሳክቶላቸው ዛሬ እነዚህ አካባቢዎች የራሳቸውን የትግርኛ አጠቃቀም ዘይቤ እየተው እስከ ጥልቁ ቆላማ የገጠር ኗሪዎች ሁሉ ዓሻዓዊና ሓማሴናዊ የትግርኛ አነጋገር ዘይቤ ተናጋሪዎች እየሆኑ ናቸው። ራዲዮኖቹ ፤ቴ/ቪዥን እና ጋዜጦች ለዚህ ዘመቻ ከፍተኛ ሥራ በመስራት ትግራይ ‘እንደ ሶማሌዎቹ” አንድ ዓይነት ያነጋጋር ዘይቤ እንዲጠቀሙ በመቀየስ አንድ ወጥ የሆነ /ሆሞጀኒክ/ “ልሳን እና ደም” “በትግዋይነት ኒው ኦርደር አጀንዳ” የሚመራ ማሕበረሰብ መፍጠር ስለነበር፤ ከሞላ ጎደል እጀታውን (“ከርነል/kernel”) በመቅረጽ በኩል ያቀዱትን ዘመቻ ተሳክቶላቸዋል። (ይህንን እንደ ማስረጃ ለማየት ከተፈለገ የእንደርታ ልጆች እንደ እነ ገብሩ አስራት እና  እንዲሁም “አንድ ክፍለ-ዘመን ሙሉ ሊያጠፉን ሞክረው እቅም በማጣታቸው ስላስተሳካላቸው ”ሰርቫይቭ” አድርገን እዚህ ደርሰናል ባዩ እንደርታዊው ‘ጀኔራል መስፍን አማረ’ እንዲሁም የራያው ዶ/ር አድሃና ሃይለ እና ራያዊው ጀኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይ ፤ የመሰዳሰሉት የእናቶቻቸው የትግርኛ ልሳን ንቀው  ወደ ‘አሻዓዊ’ ልሳን ተናጋሪዎች የመሆናቸውን አባዜ እንደ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል)።

ከላይ ያየነው ፎቶግራፍ የወያኔ ፋሺስቶች “አዲስ ሰውን የመፍጠር ዘመቻቸው ለማሳካት በምልክት፤በሙዚቃ፤በባዓላት የሚደረጉ ግጥሞች ጭፈራዎች የሚያስተላልፉት አዲስ ትግራዋይነት ትምህርት በመቅረጽ የተሳካላቸው ሌላው የክስተት ምልክት ነው። በዚህ የወያኔዎች “አዲስ ሰው የመፍጠር” የፋሺስት ፍልስፍና መርሃ ግብር መሠረት ታዳጊ የትግራይ ወጣቶች ዓይናቸው በትግራይ መልክኣ-ምድር ብቻ ተወስኖ እንዲቀር በማድረግ ፤ እንደ አንድ የአገር ዜጋ ከሌሎች በጋራ የሚጋሩዋቸውን አገራዊ መለክአ-ምድርም ፤ ሰንደቃላማም ሆነ ስነ ልቦና እንዲረሱት በማድረግ “ከጎሳቸው እና ከክልላቸው ውጭ” ያለውን ዜጋም ሆነ ‘መልክኣ-ምድር” እንደራሳቸው እንዳይቆጥሩት ሲደርግ ፤ የሚያስከትለው ጉዳት የመጀመሪያ ተጠቂዎች “የትግራይ ትግርኚ አቀንቃኞች እነ ዳዊት ከበደ፤ እነ ገብረኪዳን ደስታ እነ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም፤ስብሓት ነጋ እና በጣት የሚቆጠሩ ወያኔ መሪዎችና ሊሂቃን ሳይሆኑ” ፤ መጪው ትውልድ አገር እንዳይኖሮው ዛሬ መሰረት የተጣለው የወያኔዎች የአካባቢ የጥላቻና የግጭት ‘ፖሊሲ’ የእጅ አዙር ተጠቂ የሆነው በመላዋ ኢትዮጵያ ከጫፍ እስከጫፍ ተንሰራፍቶ ያለው በየክፍለሃገራቱ የሚኖሩ ድህም ሃብታምም የትግራይ ተወላጅ ዕጣ ፈንታው በየቀኑ በነፃነት ያለስጋት የመኖር ዕድሉ ምን ያህል አስጊ ሁኔታ ላይ እየመጣ እንዳለ ይህንን ጽሑፍ ለምታነብቡ ግልጽ ነው።

ይህ እውነታ ደግሞ እኔ የምለው ብቻ ሳይሆን፤ ፋሺስቶቹ እነ ገብረኪዳን ደስታ በመጽሐፋቸው ለቀየሱት ፋሺስታዊ የጥላቻ አስተዳዳር፤ የትግራይ ሕዝብም ሆነ የትግራይ ትግልና መስዋእትነት ለጥቃት እንደሚጋለጥ (“የትግራይ ህዝብና የትምክህተኞች ሴራ ከትናንት እስከ ዛሬ” (1999ዓም) ገብረኪዳን ገጽ 10) ግልጽ አድርጎታል።ገብረኪዳን ብቻ ሳይሆን የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ሳይኖሮው ጠላት እንዲባዛበት ያደረገው መለስ ዜናዊም ጭምር እንዲህ በማለት ቅራኔ እንደሚኖር ግልጽ ያደረገበትን እናስታውሳለን። እንዲህ ይላል፡ “….ስለሆነም እነዚህ ታሪካዊ ጠላቶቻችን አሁን እኛን በዲሞክራሲና በመልካም አስተዳደር ዕጦት ቢወቅሱን የሚያስገርም አይደለም። የትግራይ ህዝብ ታግሎ የጣላቸው ደመኛ ጠላቶች እንደገና ዛሬ መልሰው ለማምጣት ቢሞኩሩም ህዝቡ በጠላቶቹ ላይ ምንም ዓይነት ብዥታ ስሌለው ጠንክሮ ይታገላቸዋል እንጂ አይደነጋገርም።ሲል መቀሌ አደባባይ ላይ ለተሰበሰበው ህዝብ ተናግሮአል። (መለስ ዜናዊ በየካቲት ወር 2002 ዓም በተከበረው 35 አመት የድርጅቱ ምስረታ በዓል-) “ፋሺዝም  የአክራሪ ብሄረተኛነት የተጋነነ መገለጫ” ከሚለው ከዶክተር አሰፋ ነጋሽ የተገኘ)። በወያኔ መጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የሚቃወማቸው ሁሉ “ደመኛ ጠላት እና በጦርንት የተሸነፈ ነው።” ይህ ደመኛ ጠላት የሚባለው አብረዋቸው ሲያታገሉና ሲያቦኩ የነበሩትን እነ ገብሩ አስራትን እነ ስየ አበርሃን እነ አረጋሽ አዳነን፤እነ አስገደን ያጠቃልላል። ፋሺስቶች ፖለቲካ አያውቁም; የሚያወቁት በመግደልና በመገዳደል በማሸነፍና በመሸነፍ ብቻ ያለውን ዓለም ብቻ ነው የሚያዩት።ለዚህ ነው ዛሬ የትግራይ ሕዝብ በያለበት እየታደነ የመኖር ህልውናው ተገድቦ ክፍለሃገሮችን እየለቀቀ ወደ ትግራይ መጓዝ ጀምሯል እየተባለ ዜና መደመጥ የተጀመረው።

ይህ ሁሉ የሚያመለክተው ከጫካ ጀምረው አማራን የሚዘልፍ ስድብ በዘፈን በትያትር መልክ እየተዘጋጀ ሕዝቡ “ጠላት እና ደመኛ” ብለው በሰየሙት “የአማራ ማሕበረሰብ” በመጥፎ ዓይን እንዲታይ በመቅረጽ ላቀዱት የግንጣላ ዘመቻቸው አሰልፈውት ይኼው ዛሬ ብዙዎቹ የትግራይ ወጣቶችና ሴቶች እህቶቻችን በአካባቢያዊ አስተሳሰብ ተጋርደው ሰፊውን ዜግነት ኢትዮጵያዊ መልክአምድር ረስተው ወንዶች የወያኔ ባንዴራ ተሸክመው ሲጨፍሩ፤ ሴቶች ደግሞ የሚለብሱት ዙርያ እና መጫሚያ፤ እንዲሁም ቁንድላቸው በወያኔ ባንዴራ ቀለም ተሰርተው ሲጨፍሩ ያየ ተመልካች እውን እነዚህ ሰዎች አገራዊ ሰንደቃላማ ያላቸው የኢትዮጵያ “ትግሬዎች” ናቸው ወይስ “የተገነጠሉት ኤርትራኖች?” እስከማለት ደርሷል።

ይህ ሁሉ ዕብደት የሚያሳየው ባህሪ ገሃድ እየሆነ መሸማቀቅን ትተው አጀንዳቸው በግልጽ ማሳወቅ ጀምረዋል። ሰሞኑ ጌታቸው ረዳ የተባለው ወያኔ ባለሥልጣን ወደ ውጭ አገር መጥቶ “አጋአዚ” በሚል ፋሽስታዊ የሆነ “ሃይማኖታዊ እና ትግራዊ/ኤርትራዊ የግንጠላ አጀንዳ አቀንቃኝ የሆነው አጋአዚ የሚባል ቀኝ አክራሪ ቡድን ማነጋገሩን ሰው ነግሮኛል”። የወያኔ ትግሬ ጸሐፊዎችም በየሚዲያው የትምክሕቱና የግንጠላው አባዜ ለግንጠላው ዝግጁነታቸውም በቅርቡ ግልጽ እያደረጉት ነው። “Opportunities for Tigari in Post Esayass Eritrea (By Berhane Kahsay Tigrai Online, March 16, 2018) በሚል የተጻፈ፤ ብዙ ኤርትራ ምሁራን እና እኔኑም እራሴን ጭምር ያስገረመ ጽሑፍ አስነብበውናል። በጸሐፊው በስተጀርባ ያለው የግንጣላ እና ማን አሕለኝነት ሕልም እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ዋናው ትኩረቱ እየነገረን ያለው፡ ትግራይ ስትገነጠል ኢሳያስ አፈወርቂ የሌለባት “ደካማ ኤርትራ” በወያኔዎች እጅ ስለምትወድቅ “ኤርትራን የትግራይ የቅኝ ግዥ ለማድረግ” በሩ ክፍት ነው ሲል አስገራሚ ዓይን ያወጣ አጀንዳ ነግሮናል። 

በዚህ አጀንዳ እየነገረን ያለው 165 ሺሕ ኤርትራውያን ስደተኞች (ሙዚቀኞች ምሁራን ወታደሮች…) በነፃ እንዲንቀሳቀሱ እና በቀጥታ የኢትዮጵያ ዜግነት በመስጠት ዜጎች እንዲሆኑ እና መጪው የትግራይ ትግርኚ (ኦርቶዶክስ ክርስትያን አጋአዚያን) እቅድ እውን ለማድረግ “አከለጉዛይ እና ሠራየ” የሆኑትን ኢሳያስን ስለማይወዱ እነሱን ማሰባሰብ ነው ይላል (ዜግንት ለመስጠት ትግሬዎች ሥልጣን ስላላቸው መልእክቱ በቀጥታ ለማን አህለኝነቶቹ ለወያኔ መሪዎች የተላለፈ ነው)።

በውስጠ ሴራ አነጋገርም የትግራይ አጋአዚ አጀንዳ ለመቅረጽም የሚከተለው ሃሳብ በማጉላት እንዲህ ይላል።

Eritrean Muslims in order to make them receptive to Ethiopia’s (ትግሬዎች ማለቱ ነው) presence in their country when Esayass is finished. Eritrean regions bordering Tigrai such as Akele Guzay and Serai have strong affinity with their kin south of the boundary and would welcome back Ethiopia(ትግሬዎችን ማለቱ ነው) with open arms.ኢሳያስ ሲወገድ ‘አከለጉዛይ እና ሠራየ’ ከመረብ በታች ለሚገኙት ትግሬዎች በደም እና በአጥንት የተሳሰሩ ስለሆኑ እጃቸውን ዘርግተው እኛን ትግሬዎች እንዲቀበሉን ማድረግ ነው ይላል። ሓማሴኖች ግን ትግሬዎች ስለሚጠሉ (ስለሚንቁ ቢባል ቀላል መሰለኝ) አያምኑንም ይላል። ስለሆነም በዚህ ምክንያት ቀስ በቀስ እስክንስባቸው ድረስ መጀመሪያ አጎራባቾቹን ብቻ ነው ማተኮር ያለብን ይላል (አጋአዚ ንቅናቄም ያተኮረው በነዚህ አካባቢዎች ነው)። 

“Once the current Eritrean leader is out of the way…… በዚህ መልክ ኢሳያስ ሲወገድ….. የትግራይ ታላለቅ ኩባንያዎች፤ ስሜንቶዎች እና የራያ ቢራ ፋብሪካ ሳይቀር የኤርትራን ኢኮኖሚ በትግሬው የህንፃ እና የመንገድ ስራዎች ከፍተኛ ጉልበት ያለው “የሱር” ኩባንያ እና ባጠቃላይ በኣእላፍ ቢሊዮን ዶላር አሴት የሚያንቀሳቅሰው “ኤፈርት” ሚባለው ትግሬዎቹ ትልቁ ኩባንያ በማስገባት በምጣኔ ሐብት የጠወለገቺው እና የተዳከመቺው ኤርትራን በቁጥጥር ስር አድርጎ ኤርትራን መቆጣጠር (የቅኝ ግዛት ማድረግ) ይቻላል ይላል። ስለዚህ When an opportunity knocks at your door, grab it with both hands. “አዱኒያ/ ሎተሪ/ የበርህ መዝግያ ሲያንኳኳ በሁለት እጅህን ዘርግተህ ተቀበለው”። በማለት ኤርትራን (ከተቻለ በትግራይ ትግርኚ አጋአዚ ሥር ማስገባት) ካልሆነ ደግሞ ተዳክማ እየጠበቀችን ያለቺው ኤርትራ መላውን የኢትዮጵያን ምጣኔ ሃብት በመበዝበዝ ያደጉትን የትግሬዎች ታላላቅ ኩባንያዎችን አስገብተን ኤርትራን መቆጣጠር ነው። ሲል ይፋ የሆነው የሰሞኑ የትግራይ ኦንላይን አምደኛ ነግሮናል። መቸም እዛ ድረግጽ ላይ የሚለጠፈው ጉድ አጅግ የሚገርም ነው። ታስታውሳላችሁ “እኛ ትግሬዎች ማንንም ማሸነፍ የሚያስችል ከተፈጥሮአችን የተሰጠ ከሌሎቹ ኢትዮጵያውያን የተለየ የጀግንነት “ዲ ኤን ኤ” ያለን ሰዎች ነን” ብሎ የጻፈ ጸሓፊ እዛው ድረገጽ መለጠፉን ታስታውሳላችሁ? ካላነበባችሁ የተባለው ይኼው ነው።

ወያኔዎች በኢትዮጵያ ምድር ያደረጉትን ፋሺስታዊ ትምክሕት እና አካባቢዎችን በቁጥጥር ስር የማድረግ ባህሪያቸው ገሃድ እየሆነ እየመጣ ያለው ‘በመከራ እየተንገላታች ያለቺውን ኤርትራ’ በምን ብልሃት ገብተው ኤርትራን ቅኝ ማድረግ እንደሚችሉ የመግለጽ አባዜ የሚያሳየን መረጃ  የትምክሕቱ መጠን መለኪያው “ማለፉን” ነው። ሌሎች ደካሞች፤ እኛ የማንሸነፍ ባለ ዝናዎች፤ የምድር አንበሶች እና አድራጊ ፈጣሪዎች፤ አዋቂዎች፤ እኛ ትግሬዎች ዕርዱን ሳንል ብቻችን ዓድዋ ላይ ከጣሊያንን አሸነፍን’ ድረሱልን ሳንል እኛ ትግሬዎች ብቻችን ባድሜ ላይ ከሻዕቢያ ጦርነት ገጥመን ድል የተቀዳጀን ብቸኛ የባሕር ዑንቅ ልጆች …የሚለው የፋሺስት ጠባይ እየተደመጠ ያለው፤ ከላይ ያየነው እና ከታች የምናነብበው የትግሬዎች “ከንቱ የትምክሕት” ባህሪ ተመሳሳይነቱ መነሻው የፋሺስቶች ዕብደት ነጋሪ ምልክት ነው። ለዚህ ነው የትግሬዎች ዕብደት ለመግለጽ አዲስ መዝቀበ ቃላት ያስፈልጋል፡ የምለው።

አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ) ከዚህ በታች አያይዤ ያቀረብኩላችሁን ጉድ አንብቡና የዕብደቱ መጠን የት እንደደረሰ ፍንጭ ይሰጣችል።

ሳሙኤል ተስፋይ ማለት ማን እንደሀነ ባይታወቅም ከዚህ በታች ያለው የለጠፈው ይህ ከታች የሚታየው ሰው ይመስለኛል። ሙሉውን ቀጥሎ እንዲህ ይነበባል።

6 uur · 

ትግራይ ከማንም በላይ እብልጠን የምንወዳት ያል ምክንያት እደልም ተጋሩ ነን በልን የምንመካ ያል ምክንያት እደልም
1) የኢትዮጵያ የስልጣነ መሰረት ትግራይ
2) የኢትዮጵያ ክርስትና መሰረት ትግራይ
3)
እስልምና ለመጀመርያ ግዜ የተቀበለችው ትግራይ
4) የኢትዮጵያ ብሎም የኣፍርካ የመጀመርያ ፈላስፋ ትግራይ
5) የቤተክርስትያን ዜማን በማዘም በኣፍርካ ብሎም በኣለም መሰረት ትግራይ
6) ጥቁሮቹ ለመጀመርያ ነጭን ስያሸንፉ በትግራይ እየተመሩ
7) በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ግዜ ትምህርት የተጀመረበት ትግራይ 
8 ) በኢትዮጵያ የራሱን ኣለባበስ የራሱን የምግብ ኣሰራር የጀመረው ትግራይ
9) ኢትዮጵያ ለመጀመርያ የካቶሊክ ሃይማኖት የተቀበለው ትግራይ
10) የኣፍርካ የመጀመርያ ጀነራል ትግራይ
11) ለመጀመርያ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ኣላማ እንድትኖራት ከነ ትርጉሙ የሰሩት ትግራይ
12) የዛሬ የሃገራችን ኢትዮጵያ የምል ስም ኢቶጵ ከምል የግል ስም የመጣ ከትግራይ
13) የመጀመርያ የኢትዮጵያ ኣምባሳደር ከትግራይ (በፈረንሳይ ሃገር)
14) ለኢትዮጵያ ሃገር በጠቅላላ 5ሚሊዮን በላይ ህዝቦቹ መስዋእት በማድረግ በሃገር ታርክና ድል ትልቅ ቦታ ያለው ትግራይ
15) በነገስታት 500 ኣመት በፊት ያለው ታርክ እንኳን ብንመለከት ሁሉም ልባሉ ይችላል ዘራቸው ከትግራይ ነው፡ ፋስለደስ ከዛም መሳፊት ራስ ጉግሳ፡ ንጉስ ሚካኤል፡ ደጇት ውቤ፡ ጣይቱ የወሎም ብሎም የጎንደሩ ነገስታት ከትግራይ እንደሆኑ ታርክ ይናገራል
16) የቅርቡ እንኳን ብንመለከት ሃፀይ /ስላሴ ኣያታቸው ከተምቤን ትግራይ ናቸው ( የወላጃቹ ርስት ተብሎ ተምቤን ላይ መሬት እምደመበራቸው ይታወቃል)
17) ሃገራችን ከጠላት ወረራ ለመከላከል በተደረገው ፍልምያ ሁሉ የትግራይ ተወላጆች ወሳኝ ተራ ነበራቸው፡ ኢትዮጵያ ለግራኝ ኣህመድ፡ለቱርክ፡ ለጣልያንን ለማህድስት ለመመከት በተደረጉ ሁሉ የትግራይ ህዝብ ከማንም በላይ ብዙ መስዋእት ከፍሎዋል። 
18) ኣንድ ግዜ የትግራይ ልጅ ወደ ማሀል ኢትዮጵያ ይሄድና ከየት ነህ ይሉታል የዛ ንጉስ የነበሩት ኣቶ ወልደኣብ ወልደ ማርያም፡ እሱም እኔ ትግራዋይ ነኝ ብሎ መለሰላቸው፡ ንጉሱም "ኣይ ትግራዋይ ንናይ ባዕሉን ንናይ እንዳማቱን ንኩሉ መዋታት" ኣሉት፡ ትርጉሙ፡ ( ኣይ ትግራዋይ ለራሱም ለሌላውም ለሁሉም ምሞት) ኣሉት ይባላል። 
19) የሃፀይ /ስላሴ መንግስት እንድወድቅ ትልቅ ጫና ያሳደረና የኣዲስ ኣበባ ተማርዎች መሪ የነበረው ጥላሁን ይግዛው ትግራይ
20) ህወሓትና የህወሓት መስራቶች ትግራይ
21) ደርግን ለመጣል ኣዲስቷ ኢትዮ ለመመስረት የበላይነት ትግራይ
22) world class mind የተባለው ኢትዮጵያ በኣለም ያሳወቃት ትግራይ
23) የኤርትራ መሪ ከነ ኣማካርዎቹ ትግራይ
24) የኤርትራ ዋና ባለ ሃብት ትግራይ
25) መጀመርያ ነጭን በማሸነፍ ታርክ የሰሩ ትግራይ
26) ሴት ታጋዮቹ ወደ ትግል ለመጀመርያ የተቀላቀሉት ትግራይ
27) የኣድዋ ድል ዋናው ታርኩና ብዙ መስዋእት የከፈለው
28) ትግራይ ነው የኣለም የጤና ጀነራል ዳርክተርና ኢትዮጵያ ከፍ ኣድርጎ ያሳየ ትግራይ
29) ኣባይ የደፈረ ጀግና ከትግራይ 


ብዙ ብዙ ብዙ ምጨመር ኣለ እኔ ዋናዎቹ ብቻ ነው ያነሳሁት ጨምሩበት ..... ትግራይ ኣያልቅም