Saturday, March 24, 2012

ኤርትራዊው ቄስ አባ ይስሐቅ እና ተስፋዬ ገብረ አብ

 ኤርትራዊው ቄስ አባ ይስሐቅ እና ተስፋዬ ገብረ አብ
መልካም ክትትል
የኢትዮጵያን ሰማይ ስሞታ አድምጣችሁ ስለ የእናቷ ጨካኝ ድብደባ ሰለባ የሆነችው የ4 ዓመት ዕድሜዋ ህጻን ልጅ እና የጨካኝ አረመኔዋ ወላጅ  እናቷ “ሃሊማት መሐመድ” ጉዳይ ይፋ ያወጣችሁት ሁሉ አመሰግናለሁ። ዜጐች መከታተል ያለባቸው ጉዳይ ግን የወያኔ ዳኞች ከብዙ ዓመታት በፊት “ኸርሜላ” የተባለችው ወጣት በአሲድ ፊቷን አበላሽቶ እህቷን ሳይቀር ዓይኗን አጥፍቶ መላ ቤተሰብ የረበሸው  ወንጀለኛ ጎረምሳ አንዴ ሲፈቱት አንዴ ሲለቁት እንደነበረው ሁሉ ይህ ወንጀልም እንደዚያ እንዳያበላሹት የዜና ማሰራጫዋች እንደሚከታተሉት ተስፋ እናደርጋለን።በወያኔ ዘመን የሚታየው የፍትህ ሂደት እና የሚደመጠው ዜና ልክ እንደ ስርዓቱ ሁሉ ዘግናኝ ነውና ተከታተሉት። አመሰግናለሁ። ወይ አገሬ!  
ኤርትራዊው ቄስ አባ ይስሐቅ እና ተስፋዬ ገብረ አብ

 
The above Ethiopian elderly father beleives his country Ethiopia and his family are  protected by God not by man as some Atheist want us to beleive.
Dinknesh/Lucy of Ethiopia The First Human and establisher of first country on earth with her own way of life.
“ረሀ ርሃ” ትርጉሙ የመጀመርያ ማለት ሲሆን፡ በእንግሊዝኛ ሲጻፍ LUCY L(ረ) u(ሀ) C(ር) Y(ሃ) (ፈረንጆች ፊደላችን ተውሰው እንዴት እንደ ገለበጡት ተመልከቱት)።
Tesfaye Gebre Ab an  Eritrean Spy, masquereding as Ethiopian giving interview about his anti Amhara book "YeburQa Zemita" to EPLF youth magazine "Meneasey" in Asmara Eritrea.

Important film document for this week from Ethiopian Semay.

You will see how Woyane (the current Ethiopian government) is transferring slaves to the Arab countries legally on this video.Watch it after you read my commentary about the Shabia mercenary Tesfaye GebereAb under the topic ኤርትራዊው ቄስ አባ ይስሐቅ እና ተስፋዬ ገብረ አብ


 ኤርትራዊው ቄስ አባ ይስሐቅ እና ተስፋዬ ገብረ አብ

ጌታቸው ረዳ ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com (408) 561 4836

ኢትዮጵያ የሚለው ስም ሲነሳ በቅናት እርር ድብን የሚሉ የውጭ ወራሪዎች በብዛት ነበሩ። ለምን? የሚል ጠያቂ ሲመጣ መልሱ ብዙ ቢሆንም፤ አብዛኛዎቹ የዓለም አገሮች በሃያላን ወራሪዎች ተጠቅተው አገራቸውን ለወራሪዎቹ አስረክበው በባርነት ሲኖሩ አገራችን ነጻነቷን ጠብቃ መቆየቷ ብቻ ሳይሆን በባርነት ቀንበር ሰር ሲኖሩ ለነበሩት አገሮች ታግላ ጥብቅና ቆማ እራሷን የነጻነት ተምሳሌት ሆና በዓለም መድረክ ስትጠራ መቆየቷ ብዙ ቅናት ያደረባቸው አገሮች ቅስሟን ለመስበር ሴራ እንደሸረቡባት ብዙ ጊዜ የተጻፈ ስለሆነ ብዙ ትንተና አያስፈልገውም።
ሮማን ፕሮቻስካ የተባለው የሃንጋሪ ተወላጅ የጻፈው ኢትዮጵያን የማጥፋት ዘመቻ ጽሑፍ ያነበበ ሰው መልሱ እዛው ያገኘዋል። ነፃነቷን ጠብቃ ስንል መሬቷን አስጠብቃ ኖረች ማለት ብቻ ሳይሆን፤ “ሃይማኖቷን፤ፊደሎቿን፤ጥንታዊ ቅርሶቿን” ተንከባክባ ስለጠበቀችም ነው። ማንነቱን አስጠብቆ፤ በመሬቷ ላይ የሚኖረው ሕዝብ በጦርነት እና በሰላም ማሕበራዊ እና አስተዳደራዊ ሥርዓቱ እንዳይናጋበት በመምራት ቀዳሚ ሚና የተጫወተቺው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት እንደነበረች አንዳንድ አመኬላዎች የሚክዱ ቢኖሩም መረጃው ሊፈቁት አይቻላቸውም እና ሃቁ አፍጦ ይገኛል። ያን ሃቅ እና ቅርስ ለማጥፋት ብዙ ተሸቃጥለውታል፤ዘርፈውታል፤ቀዳድደውታል፤ሰውረውታል፤ሰርቀው ወደ ውጭ አሻግረው ሸጠውታል፤ ዛሬም ጥንትም ጸረ ኢትዩጵያ ትግሉ እንደቀጠለ ነው። ቤተክርስትያን ውስጥ የፖለቲካ ሰዎች እና የውጭ አገር ሰዎች በስውር እየገቡ ምዕመናኖች እንዲበጣበጡ ተደርጓል። ቤተክርስትያኒቱ በወያኔ ሴራ ተጠቅታለች።በውጭ አገር (በተቃዋሚ ስም) በውስጥ ደግሞ ወያኔ ተባበሪዎቻው እሷን ላንዴና ለመጨረሻ ከተምበረከከችበት ለመቅበር ዛሬም በትጋት ይሰራሉ።

ፊዳለችን በመጠቃት ላይ ነው፤ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በመጠቃት ላይ ነው፤አማራው በመጠቃት ላይ ነው፤ደምበራችንም በቅጥረኞች ተጠቅቷል። ይህ እሮሮ አሁን ብቻ ሳይሆን ከጥንት ጀምሮ የሸረቡት የቅጥረኞች ታሪክ ስንመለከት ወላጆቻችንም እንደዚሁ በትግል አልፈው ተንከባክበው ለኛ ሲያስረክቡን አገር በቀላሉ የኖሩበት አልነበረም። ለምሳሌ “ትቤ አክሱም መኑ አንተ?” (1951 ዓ.ም ) የተባለው መጽሐፍ ደራሲ ክቡር አቶ አስረስ የኔሰው “ካቶሊኮች” “አረቦች” “ጣሊያኖች” እና የመሳሰሉት የኢትዮጵያን ታሪክ፤ቋንቋ… ለመበረዝ (ከአክሱም ታሪክ ጀምሮ) የተደረገው ሴራ፤ ለምሳሌ “አባ ጋስፓሪን ገብረማርያም” የተባሉ ኤርትራዊ ካቶሊክ ስለ ታሪካችን (ፊደል፤ሃይማኖት፤ታሪክ..) አበላሽተው መጽሀፍ ከጸፉ ወዲህ አቶ አስረስ እላይ የተጠቀሰው በጣም ሃይለኛ (ፓወር ፉል) መጽሀፍ የመልስ ምት ጽፈው ለወጣቶች ሲያስጠነቅቁ እንዲህ ብለውእንደነበር ላስታውሳችሁ እሻለሁ።
“…ስንኳንስ ዛሬ በኢትዩጵያ ግዛት ውስጥ የሚገኙትንና ከውጭ እንኳ ከጥንት ግዛቶቿ የጥንት ጽሑፎችን እየመረመረ የሚያመጣ ሰው ኖሮ ቢሆን የጥንታዊ ነጻነታችን መታወቂያ ያልነውን ፊደላችንን አባ ጋስፓሪን ለመንጠቅ ባልከጀላቸው ነበር። የኢትዮጵያ ወጣቶች ሆይ ይህን ሁሉ መዘዝ ያመጣብን ከውስጣችን የሚገኙ በእለት እንጀራ፤በዳቦና በሻይ እየተገዙ ምስጢራችንን እያወጡ ከዚሀም ቀደም ሰዎቻችንን ያስጨረሱ፤አሁንም ለወደፊቱ አሳባቸው አላማቋረጡን  ይሀ ታሪክ የተባለው የፖለቲካ መጽሐፍ መሆኑን እወቁ (የሓርርን ግዛት አንስተው ሲየወሱ ነው)። ….የእነ አባ ጋስፓሪን አባቶች ከአባ ቤርሙዴዝ ጀምሮ እስከ ዛሬ ያሉትን ኢትዮጵያ ያልወለደቻቸው ልጆች አዝላ ትኖራለች። ታዝለው ከመኖራቸውም የተነሳ መታዘላቸውን ምክንያት በማድረግ የሚያስቡላትን አሳብ ደግ በማስመሰል ምርምር ተይዟል።” ብለው ነበር።
እነሆ ዛሬ ከጀርባዋ ታዝለው የኖሩ ኤርትራዊያኖች እነ መቶ አለቃ ተስፋዬ ገብረአብ እና መሰል ሻዕቢያዎች “መታዘላቸውን ምክንያት በማድረግ” ኢትዮጵያን ከድተው አማራውን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት እና ከግድያ የተረፈውም ከተወለደበት አገሩ ወጥቶ ወደ ስደት እንዲፈልስ ራሱን እንዲያቀረቅር ምክንያት የሆነው እንዳይበቃው ዛሬ ደግሞ ተስፋዬ ገብረ አብ የተባለ የወያኔ እና የሻዕቢያ  አገልጋይ ሌላ የሴራ መላ/ዘዴ አልቆበት ‘ኢትዮጵያ ወታደር እንጂ አምላክ አያድናትም” በማለት “ኢትዮጵያ ታበጽሕ ኢደዊሃ ሃበ እግዚአብሔር” ብሎ መጽሐፍ ቅዱሳችንን መዝግቦ ያቆየልንን የወላጆቻችን እምነት ማንቋሸሹን ቀጥሎበታል። ቃል በቃሉ እንዲህ ይላል”
 “…ኢትዮጵያ ጥንታዊ ብቻ ሳትሆን፣ በእግዚአብሄር እጅ የተሰራችና በአለም የመጀመሪያዋ አገር ናት። በእግዚአብሄር ጥበቃም ለዘልአለም እንደምትኖርና ዳግም ሃያል እንደምትሆን ማንም ጥርጥር አይግባው። ኢትዮጵያ አልፋ፣ ኢትዮጵያ ኦሜጋ ናት። በዚህ ዘልአለማዊ ጉዞ ውስጥ ደግሞ፣ አገሪቷን ከጥፋት የሚታደጓት መላእክት የመኖራቸውን ያክል፣ የእባቡን ድርሻ የሚወጡም ሞልተዋል…”
ይህ ከላይ ያለው አባባል የሰፈረው ኢትዮ ሚዲያ የተባለው ድረገፅ “ተስፋዬ ገብረ እባብ” በሚል ርእስ እኔን ባወገዘበት መጣጥፉ ነበር።….መለስ አገሪቱን ሸጦ እየጨረሰ አብርሃ በላይ ደግሞ… “አታስቡ ኢትዮጵያን የሚጠብቁ መላእክት አሉ” ይለናል። “ኢትዮጵያ በእግዚአብሄር እጅ የተሰራች” የሚለው ሙገሳም ለዚህ ዘመን አይሆንም። ጊዜውን ጨርሶ የተጣለ አባባል ነው። አገራት የሚሰሩት በሰዎች ነው። “ኢትዮጵያ በአለም የመጀመሪያዋ አገር” የሚለውም መሰረት የለውም። በየትኛው ጥናት ነው ይሄ የተረጋገጠው? ይሄ ሁሉ ማዘናጊያ ነው። ዜጎች አገራቸውን በወታደራዊ ሃይልና በፖለቲካ ማስጠበቅ አለባቸው።” (Monday, March 5, 2012  ኢትዮጵያን ማን ይጠብቃት? ወታደር ወይስ መላእክት? ተስፋዬ ገብረ አብ)

በጎሳ ገብቶ አማራው እንድያልቅ መጽሐፍ ጽፎ ህጻናት እና እናቶች እንዲያልቁ ሰበብ ሆኗል። በዚህ ስራው በማስረጃ እየተሰነደ ጥገኝነት ለሰጠው አገር እና ለሰብአዊ ነክ ጉዳይ መስርያቤቶች እንዲቀርብላቸው እና እንዲያውቁት ዝግጅት እንዲደረግ እንዴትስ ሰነዶች መሰብሰብ እንዳለባቸው በውይይት ላይ ያሉ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ። በውጭ ያሉ ተቃዋሚዎች ነን የሚሉን ሰዎች እንደ ወትሮአቸው ካልተከላከሉለትና ትግሉን ከነሱ ጋር እንዲሆን ካልለወጡት ብርታቱን ይስጣቸወሁ፤ ግፉበት እላለሁ።
ይህ ጉደኛ ሻዕቢያ በ“የቡርቃ ዝምታ” መጽሐፉ ላይ አጼ ምኒልክን እና አማራውን “በነፍጠኛውና በአሳማው አጤ ምኒልክ ትእዛዝ በሕዝብ አናት ላይ የተተከሉ በዝባዦች ናቸው” ያለውን አልበቃ ብሎት።  የመንደርዋ ባላባት አባ ዋቆ አንድ ቀን አመፅ አንደሚያነሳና የቡርቃ ገበሬዎች ዝምታ ፈንድቶ አማሮች አንደሚጨፈለቁ/እንደሚጨፈጨፉ የቀሰቀሰውን የእልቂት ሴራ አልበቃ ብሎት። ትንበያው እውን ለማድረግ ጭፍጨፋው በዓይኑ ለማየት እንዲፋጠንለት በመጠየቅ “የኦሮሞ ሕዝብ ዛሬ ጨረቃ ወጥታልሃለች ለምን ዝም ትላለህ? ዝምታው አይበቃህም ወይ? አማራውን የምትመነጥርበት ወቅት አሁን ነው!” ሲል የተማጸነው አና ወንጀሉ ተሳክቶለት አፎይ ያለውን እረፍት እንዳይበቃው፤ አውሮጳ ከመጣ ጀምሮ ደግሞ በአጼ ምኒልክ ቤተሰብ እና ክብር ላይ ያልተቋረጠ ዘመቻ መጀመሩን አልበቃ ብሎት፡ ሰሞኑ ደግሞ በተዋህዶ ኦርቶዶክስ መጽሐፍ እና እምነታችን ላይ የሻዕቢያው ውስጣዊ ስራው እኛኑን ክርስትያኖች ማጥቃቱን ቀጥሎበታል።
በዚህም ፕሮፓጋንዳውን ለማሰራጨት እየተባበሩት ያሉትን ሕዝብ እንዲጨፈጨፍ መጽሐፍ የጻፉ ፤የዘር እልቂት ጥፋት ግድያ እንዲፈጸም ያዘዙ የገደሉና ያስገደሉ ወንጀለኞችን እንደ ተቃዋሚ ተቀብለው (አንዳንዱም መሪዎቻቸው አድረገው እየጋበዟቸው ነው) በማስጠጋት ብርታት እየሰጧቸው ያሉትን “የፈሪ መንጋ” ስብስብ ተቃዋሚ ተባባሪዎቻቸው በታሪካችን ተጠያቂዎች ናቸው።

ለማንኛውም ጊዜው የኢትዮጵያ ጠላቶች የበረቱበት ወቅት ነውና  እንደ ተስፋዬ ገብረአብ  የመሳሰሉ የበሉበትን ሳህን የሚሰብሩ ሻዕቢያዎች ኢትዮጵያን ለማጥፋት አማራውን፤ መታወቂያ ፊደላችንን፤የዘመን መቁጠሪያ ዘዴአችንን እና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ለማጥፋት ከእነ ቤርሙዳዝ ፤ከእነ አባ ማስያስ (ካቶሊክ) እነ ኢዋርሶን እና ኤሪክሰን የተባሉ የስዊድን ፕሮተስታንቶች ትግራይ ውስጥ ሰርገው በመግባት ተዋህዶን ለማፍረስ የተደረገው ጥረት (ይህንን በተመለከተ አዲስ መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ ነኝ)፤ እና በቅርቡ አስራኤሎች ከመንግስቱ ሃይለማርያም (ደርግ) እና ከመለስ ዜናዊ (ወያኔና ሻዕቢያ) ተመሳጥረው በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖቹን “እስራኤሎች” ናችሁ ተብለው በገንዘብ በባርነት እንዴት እንደተሸጡ እና እዛው እንደገቡ ምን እየገጠማቸው እንደሆነ የምታውቁት ነው። ወደ አረብ አገሮች በግልጽ በቪዛ የሚሸጡ የዘመናችን ሴት እህቶቻችን “ባርያዎች፤የቤት ገረዶች”(ከላይ የተለጠፈው የፊልም ታሪክ ይመልከቱ)። ስለ አረቦች ጸረ ኢትዮጵያ ጉንጎና ሴራ ብዙ ትንታኔ አያስፈልግም፤ ከአክሱም ዘመነ መንግስት እስከ ቅጥረኛው ግራኝ መሐመድ ጀምሮ እስከ ወያኔ ዘመን ድረስ በክረስትያኖች እና ገዳማት እየደረሰ ያለው ትኩስ ዜና መዘርዘር አላሰፈለገኝም።

የታምራት ላይኔ ጴንጤ ሃይማኖት ድርጅት በኢትዩጵያ ህጻናት እና ወጣቶች ሕሊና ላይ ሰርስሮ በመግባት ወዴት እየለወጣቸው እንደሆነ እዚህ በራሴ ድረገጽ  በቀኝ  የተለጠፈውን video መመልከት በቂ ማስረጃ ይሆናችሗል ተመልከተቱት። ይህ ጥቃት የቆየ የጥንት ቅጥያ የጥቃት ዘመቻ ነው።
ተስፋዬ ገብረ አብ ኢትዮጵያዊ ካባና ቋንቋ ለብሶ ዛሬ ስለ ወያኔ ብቻ እና ስለ ኢትዮጵያ የተዋህዶ ቤተክረስትያን አምነት እና ተከታዮቿ አናት ላይ በእሳት የጋለ የብረት አሎሎ መወርወር መብቴ የተጠበቀ ሲሆን “ባለቤቴና ልጆቼ” ስለ ሚኖሩባት ስለ ኤርትራ እና ስለ ሻዕቢያ ላለመጻፍ ግን የሚያስገድደኝ የጋዜጠኛነት ሞራልና እና ግዴታ የለብኝም፤ሲል ሳያፍር ስለ ሻዕቢያነቱ በግልጽ ሲሞግት አንብበነዋል። ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቃት ብለው ለሚሉ አማኞቿ “ጊዜ ያለፈባቸው አማኞች፤ያረጀ፤ የተጣለ እምነት” ሲል ጥቃቱን ሰንዝሯል።   

 “ዘረኛው ማን ነው ኢትዩጵያዊያን ፍረዱ” የተባለ መጽሐፍ ደራሲ  አቶ ይትባረክ ግደይ የተባሉ ጸሐፊ ኢትዮጵያ የሚባል አገር የሚታወቀው አሁን በምንሊክ ዘመን ነው፤በሰው እጅ የተሰራ አገር ነው፤ ለሚሉት እና “ኢትዮጵያ ታበጽሕ ኢደዊሃ ሃበ እግዚአብሔር” የሚለውን የሚሳለቁበት ለእንደ እነ ከሃዲው እና “ኤቲየስት/በወላዲ እና በተወላዲ ሃያልነት፤ታምረኛነትና ጥበብ የማያምን እንደ ተስፋዬ ገብረ አብ የመሳሰሉ የሶቭየት እና የቻይና ልበወለድ ጸሐፊዎች ኮቴ የሚከተሉ ኤርትራዊያን ሻዕቢያዎች፤ ለአስተማሪዎቻቸው ለእነ አባ ጋስፓሪኒ ገብረማርያም እና  እንዲሁም “ዶክተር በሉኝ” አባ ይስሓቅ ገብረየሱስ ለተባለው ከሃዲ የቄስ ተጋዳላይ ኤርትራዊ መኖክሴ “አምላክ የሚጠብቃት ኢትዮጵያ የምትባል አገር በታሪክ አትታወቅም” ሲል ለጻፈው መልስ ሲሰጡ እንዲህ ብለው ነበር፡
“ኢትዩጵያ ሁሉ ልብ በል! ኢትዮጵያ የምንባል እኛ ነን እንጂ እንናተ አይደላችሁም ብለው ፍርድ ቤት የከሰሱን የሉም። ስለዚህ ከመጽሐፍ ቅዱስ፤ከነቢያት በላይ በዓለም ምን ማስረጃ ሊገኝ? መጽሐፍ ቅዱስ ኢትዩጵያን ወክሎ ዳኝነቱን ከሰጠ፤ነቢያት ከመሰከሩ ምን ሊኮን?” ሲሉ መልስ እና ጥያቄ ጠይቀው ነበር። እነ ተስፋዬ ገብረ አብ ግን “ምጽሐፍ ቅዱሳችሁ እና ነቢያት ስለ አገራችሁ የጻፉትን መጽሐፍቶቻችሁን አልቀበለውም፤ መሳቂያ ነው፤’ጊዜ ያለፈበት፤የተጣለ እምነት ነው” በማለት “ኢትዮጵያ ወታደር እንጂ አምላክ አያድናትም” በማለት በተዋህዶ “እምነታችን” እና ፅናታችን ላይ አዲስ የጥቃት ዘለፋ እና ዘመቻ ጀምሯል ። ኢትዮጵያን እያሰጠቁ ያሉት ባሁኑ ወቅት በውጭ አገር እየኖሩ በተቃዋሚነት ተሰልፈው ቴሌቪዝን እና ራዲዮን ኢንተርኔት አቋቁመው “ነብስ የገደሉ እና እንዲጨፈጨፉ ምክንያት እና ቅስቀሳ ያደረጉ” ድርጅቶች እና ግለሰቦች” አቅፈው ኢትዮጵያዊያን እና ነገሥታቶቻችን እንዲዘለፉ እንደገና  እንዲሰድቡን እንዲያስተምሩን፤ እንዲመሩን እና እንደገና እንዲጨፈጭፉን የሰሩት የዘር ማጥፋት ወንጀል ለሕዝብ ይፋ እንዳይሆን የተቻላቸው ያህል በመሸፈን ትብብራቸውን ስላልነፈጓቸው እንሆ ተስፋዬ ገብረ አብ የተባለው ጸረ አማራ ሻዕቢያ ደግሞ ዛሬም

 “ኢትዮጵያ በእግዚአብሄር እጅ የተሰራች” የሚለው ሙገሳም ለዚህ ዘመን አይሆንም። ጊዜውን ጨርሶ የተጣለ አባባል ነው።”

ሲል የአያቶቹ የእነ አባ ይስሐቅ ጸረ ኢትዮጵያ እና ጸረ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እምነቱ ታሪክ በመከተል ይህ ይፋ የሆነ ዘለፋ እና ጥቃት በወላጆቻችን አምነት እና ታሪክ ሰንዝሮብናል።

 የተሰፋዬ ገብረ አብ የዘለፋ አጻጻፍ ያልተረዳው የዋህ አንባቢ አባ ጋስፓሪኒ ገብረማርያም የተባሉ ኤርትራዊ የካቶሊክ መነኩሴ የጻፉት መጽሐፍ ካላነበባችሁ የተስፋዬን ኢትዮጵያዊ ተቆርቋሪነት አስመሳይ የሽፋን ብዕር ሊረዳችሁ አይችልም።ለዚህም ነው አቶ አስረስ የኔሰው ለአባ ጋስፓሪኒ ገብረማርያም እና የመሳሰሉ ኢትዮጵያዊ አሞጋሽ መስለው ጸረ ኢትዮጵያ ቅስቀሳ የሚነዙ ቅጥረኞችና ካሃዲዎች ማሩን ከእሬቱ እየለዩ ለሕዝብ መረጃውን እንዲያነበው ትተውልን የሄዱት።
ተስፋዬ ገብረ አብም ማሩን ጣል ያደርግ እና እሬቱን በሰፊው ይቀባዋል። እህሳ ምነው ጐመዘዘ ሲሉት? ይሄው ማሩን አልቀመሳቸሁትምሳ! ለማት እንዲመቸው አንድ ሦስት መስመር ማር ጣል አድርጎ ወደ ተልእኮው ይገባል። “አንድ ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ለተራቡ ሕዝቦች እግዚአብሐር ለአለሙ ሁሉ አንድ በግ ሰደደ” ሲል መጽሐፉ ቅዱስ  ተስፋየየ ገብረ አብ ቃሉን በቃል ብቻ ተርጉሞ ወላጆቻችን እና መጽሐፍ ቅዱሱን “ ባንድ በግ የሚያምኑ ሞኞች” እንደሚለን ጥርጥር የለንም። “ኢትዮጵያ ታበጽሕ ኢደዊሃ’ ለሚለው አባባልም ጠመንጃ ከታጠቁ የሰው ወታደሮች ከታምረኛው አምላክ ጋር እያወዳደረ ለመፈላሰፍ በመሞከር ‘ዘመኑ ያለፈበት” “የተጣለ” በማለት መጽሐፍ ቅዱሳችንን አጠጥሎታል። 
ይህ ጥቃት በሻዕቢያ እና ወያኔ ጀሌዎች በዓለም አቀፍ ሃያላን አገሮች የስለላ መሳሪያዎች ተደግፈው ኮሚኒሰት ደርግን በመጣል ሌሎች የምዕራብ ተቀጣሪ ኮሚኒስቶችን በመተካት በኢትዮጵያ ሃይማኖት እና ታሪክ፤በክብሯና በድመበሯ ላይ ጥቃት እንዲደርስብን የተጫወቱት ሚና መርሳት የለባችሁም። አንዴ ላስታውሳችሁ እና ወደ ተስፋዬ ገብረ አብ እመለሳለሁ።

ካሁን በፊት  የኢትዮጵያ ክፍለሃገሮች ተብለዉ ሲታወቁ በነበሩት በኤርትራ እና በትግራይ ክ/ሃገር የተመሰረቱት ሁለት የሽምቅ ተዋጊ ሃይሎችን ለመረዳትና አካቢውን ለመቆጣጠር ሲባል  የቀይ ባሕር አዋሳኝና እና አካባቢዉ “5ኛ መርከብ” ተብሎ በሚጠራው ማዕከሉ በዲያጎ ጋርሲያ ያደረገዉ “በሪር አድሚራል ጆን ላት አሌክስ” እዝ ስር ሲመራ የነበረዉ የአሜሪካዉ የባሕር ሃይል  እና CIA  በአካባቢዉ የሰፈረዉ “ቀይ ነብር” በመባል የሚጠራው የኬጂቢ የሶቭየት የስለላ ሃይልን ለመቀናቀን ሲል ኤርትራ ዉስጥ ለኤርትራ ሐርነት ህዝባዊ ግምባርን የስለላ መረጃ በማቅረብ አፍዓበት ላይ ሰፍሮ የነበረዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት እንዲጠቃ ሲያደርግ፦በትግራይም ለህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የስለላ መረጃ በማቀበል፤ እንዳባጉና (ሽሬ አዉራጃ-ትግራይ ዉስጥ) ላይ ሰፍሮ ዘመናዊ መሣሪያ ታጥቆ በነበረው በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጥቃት እንዲፈጽሙ አንደረዷቸው በዚህ በራሴ ድረገጽ/ብሎግ ካሁን በፊት ዘግቤው እንደነበር የሚታወስ ነው።

በደርግ የሚመራው ለኢትዮጵያ ተዋጊ ሰራዊቶች “የመጨረሻ በር የሚቆልፍ” ስትራተጂ በApril 16/1989 የአሜሪካን ፕረዚዳንት በነበረው ጸረ ኢትዩጵያው ጂሚ ካርተር ሰብሳቢነት መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወረቅ ለሁለተኛ ጊዜ ሱዳን ውስጥ በመሪድያን ሆቴል ተገናኝተዉ፡የጋራ ወታደራዊ ዕቅድ እንደነደፉ ገልጫለሁ። በዛ ወቅት በሕዝባዊ ግምባርን የወከለ እጅግ ምስጢራዊ በሆነ ምደባ አንድ (ግለሰብ) ብቻ ሚስጥራዊ የስለላ መረጃዎችን የሚያከናዉን ሲመረጥ፦  ወታደራዊ ስትራተጂ፤ ስለላ እና መረጃ አስመልክቶ በመጀመሪያ ስብሰባዉን የመራዉ ከህዝባዊ ግመባር ጴጥሮስ ሰለሞን (አሁን በኢሳያስ እስር ቤት ሚስቱሲ ጋር ታስሯል)እንደነበርና ቀጥሎ ከትግራይ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ድግሞ ሓየሎም፤ጻድቃን፤ ክንፈ ገብረመድህን እና መሰል አጋሮቻቸው …።  ኢትዩጵያን የማጥፋት ዘመቻ እንዴት እንደተቀነባበረ መዘገቤንም ታስታወሳላችሁ፤
በቅርቡ የወያኔ የስለላ ዋና ሐላፊ የነበረው ብስራት አማረ በጻፈው “ፍኖተ ገድል” መጽሐፍ ላይ በሽሬ ውስጥ ጀግናው ጀኔራል አርአያ ዘርአይ በበርከታ የወያኔ ሰላዮች (ፒ አይ) ተከብበው የእለት ተለት እንቅሰቃሴያቸው ሲከታተሉዋቸው እና ወታደራዊ ምስጢሮችን ሳይታወቃቸው ሲመዘብሩዋቸው እንደነበረ ገልጿል። ይባስ ብሎ እዛው መጀመሪያ  ሽሬ ውስጥ የ17ኛው ክ/ጦር ኮሚሳር የነበሩት ኰሎኔል ጨመዳ  የተባሉት በሗላ ባዲስ አበባ የኢትዮጵያ ምድር የፖለቲካ ኮሚሽነር የነበሩት  የወያኔ (ፒ አይ) ታማኝ ስላይ አባል ሆነው ያገለገሉ እንደነበር እና ባሕር ዳር ውስጥ የ603ኛ ሰራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ የነበሩት ኰሎኔል መንግሥቴ እና የመሳሰሉት፤የወታደራዊ መዋቅሩ እና የወታደሩ እንቅስቃሴ አሳልፈው ለወያኔዎች መረጃ ያስተላልፉ እንደነበር በገጽ 279 ገልጾታል። (ወያኔ እና ሻዕቢያዎች አንዴት ለድል እንደበቁ  ይህ መረጃ በቂ ማስተማሪያ ነው)
ይህ ሁሉ ሽረባ እና ከበባ ሲደረግ የውስጥ  ጠላቶች ወገን መስለው ከውጭ ጠላት ጋር ሲተባበሩ እንደነበር በቀላሉ ከዚህ እንድትማሩ በሚል ነው ይህንን ያስታወስኳችሁ።     

ይህን የሲ. አይ ኤ መረብ  ትናንትም ሆነ  ዛሬ እንዳልለቀቀን ማወቅ ይኖርባችሗል (ተክሌ የተባለው የግንቦት 7 አቀንቃኝ እና በቅርቡ ደግሞ  ወደ ኢሳት ቲቪ እግሩን በማቅናት ጋጠኛ መሆን እየቀባጠረ ያለው ይህ ወጣት፤ “ሲ ኣይ ኤ ቅብጥርጥስ የምትሉት ያረጀ ያፈጀ ታሪክ አሁን የለም” ፤ “አዳራሽ ውስጥ የኦነግ ባንዴራ ካልተሰቀለ  የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ  ቢሰቀል ባይሰቀል ምንም ትርጉም አይሰጠኝም” ያለንን በወየኔ ሕሊና ሲሰበክ ያደገ ጉደኛውን ልጅ አትርሱ)። ስለሆነም በጨቅላ ዕድሜያቸው አምላክ የለም ተብሎ የህወሓትና የሻዕቢያ ኰሚኒስታዊ ቀለም እያጠመቀ/እያጠለቀ የክህደት ጽሑፍ ሲለማመድ ያደገ የተስፋዬ ገብረ አብ ብዕር የኢትዮጵያን የተዋህዶ ሃይማኖት ታምረኛው አምላክና ምእመናኖች የማንኳሰስ ዘመቻ ከአያቶቹ ከኤርትራ ሻዕቢያዎች የወረሰው ብዕር ዛሬም እየገፋበት ነው ።
ኤርትራኖች  ኢትዮጵያ እንዳልሆኑ ለዓለም ለመንገር የራሳቸው የዘመን መቁጠሪያ ቀይረው የገዢዎቻቸው የአውሮጳ ዘመን አቆጣጠር ተጠቅመዋል። የማንነተቸው መለያ የሆነው ግዕዙ ፊደልም እንዲሰረዝ እና እንደ ኦሮሞዎቹ እና አውሮጳ ሰዎች በላቲን ፊደል እንዲጽፉ “በጉባኤያቸው ላይ ሃሳብ ቀርቦ አንዳንዶቹ በስንት ንትርክ ሃሳቡን ተቃውመው “ግዕዙን” እየተጠቀሙ ነው። በጣም የሚገርመው ጉደኛው ገበናቸው ግን ኤርትራኖች ስለ ሃይማኖታችን ስለ አገራችን ታሪክ እና ማንነታችን እምነት ብቻ ሳይሆን ጥቃታቸውን ያነጣጠሩት ስለምንመገበው “ጤፍ” ሳይቀር በመጽሐፍ መልክ ጽፈው አሳፋሪ ባህሪያቸውን ለትውልድ ትተው የማለፋቸው ትንሽ እንኳ  የማይሰቀጥጣቸው አንዳልሆነ የተስፋዬ ገብረ አብ የጽሑፍ አርበኛ የሆነው ቅሌታሙ ኤርትራዊው “ቄስ ተጋዳላይ አባ ይስሐቅ ገ/የሱስ” የጻፈውን “ፍረዱ” የተባለው የትግርኛ መጽሐፉ አቶ ይትባረክ ግደይ  የጻፉትን መልስ በአማርኛ አስነብባችለሁ።  
አባ ይስሐቅ የተባለው ቄስ አፍቃሬ ሻኢቢያ እና በርካታ መጽሐፍቶች በጣሊያንኛ እና በትግርኛ ሃይማኖፐታዊ፤ፖለቲካዊ እና የታሪክ መጽሐፍቶችን ጽፏል። አሉላ አባ ነጋ ስም ሲጠራ ጌቶቹን ጣሊያኖችን ስለደመሰሱለት አንደ በሽታ ያደርገውና ይጥለዋል። እጅግ ይጠላቸዋል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵ ዊነት የሚባል ነገር እጅግ ያንገሸግሸዋል።ይህንን የሚተለው ጉድ አንብቡ እና ልሰናበታችሁ። የአክሱም ታሪክ ኤርትራኖች የመሰረቱት ነው ይላል። ካልሆነ አክሱም የትግሬዎች ነው ከተባለ ግን “ተረት ተረት ነው። የሚመገቡትም ጤፍ በኤርትራዊ ጀግና ሰው እንዴት እንደተፈጠረና “ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ እንዴት እንደሚያንገሸግሸው ያለው ጥላቻ ሳይደብቅ በራሱ በትግርኛ መጽሐፉ እንዲህ ይላል። (አንዳንድ ቦታዎች ላይ አጻጻፉ የግንቦት 7ቱ እና የወያኔ አሽከር የነበረው ጸረ አማራው መጽሐፍ ጻሐፊ አንዳርጋቸው ጽጌ አጻጻፍ ጋር ይመሳሰላል)።
“ምሕረት የሌለውና መድሃኒት ያልተገኘለት ኢትዮጵያ የሚለው ተፀውኦ ስም እንደ ባህል ሆኖ የሚወረስ ሁሉንም የአበሻ ልጅ ለካፊ በሽታ ነው። ይህ በሽታ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ዘወትር የሚነገር “ኢትዩጵያ፤ኢትዮጵያዊያን” የሚለው ሀላፊነት የጎደለው አጠራር ወይም አባባል የፀሐፊዎች ልብ ወለድ ታሪክ ነው። በሽታው ሐሰትን ያፈቅራል፤ተረት ተረትን ተፈላስፎ ታሪክ ነው ብሎ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን በታሪክ የሌሉ ሰዎችንም እየጨመረ ታሪክ መፍጠራቸው ያስገርማል።
        ምኒልክ፤ሳባ፤ማክዳ፤ህንዳኬ ወዘተ… የተባሉና ኢትዮጵያ ውስጥ  ለተፈጠሩ ነገስታትን መፈጠር የቻሉ የሀሰት ደራሲያን ናቸው። የህ እየተከታተለ የመጣው በሽታ እና “ቀታሌ ነፍስ” ሐቀኛና እውነተኛ ታርክንና ማንነትን ወይም ንፁህ ዜግነትን የሚያሳጣ፤የራስክን ታሪክ እንዳታውቅ ዓይኖችህን ሸፍኖ በራስ እንዳትተማመን የሚያደርግና ወደ  ላ የሚጎትት ላ ቀር፤ዘመኑ ያለፈበት ባህል እና እምነት የመጣ የእኛ ብቻ ሳይሆን የመላ አፍሪቃ ቀንድ በሽታ ነው።
…የኢትዮጵያ ታሪክ የሚሉት በወቅቱ ሲወረር፤ሲመዘበር፤ሲጨቆንና ሲቀጠቀጥ የነበረው ኤርትራዊ ግን ሰጥ ለጥ ብሎ ለአማሮች እንዲገዛላቸው ጥርጊያ መንገድ ሲያመቻችላቸው ነበር።…በተለይ ደግሞ የሃለቃ ታየ ፅሑፍ ከተረት ተረት አልፎ የሐሰት አሉባልታ ይዘትም አለበት።በሌላ በኩል በዋናነት የተረት ተረት ወሬ ስታወራ ይምትታየው ክብረ ነገሥት የምትባለው የኢትኦጵ  መጽሐፍ ነች።
በአበሻ ምድር እንደ አንድ አምላክ የሚታይ ሀይለኛ ትልቅ ዘንዶ ነበረ። አንዲት ቆንጆ ለአቅመ አዳም የደረሰች ልጃገረድ የንጉሥ ልጅ ነበረች። ከአንድ መደባይ (መደባይ ታብር ለማታውቁት ሰዎች፤ አክሱም ውስጥ አንድ የገጠር ስም ነው (ወያኔዎች ዛሬ  ለኤርትራኖቹ ሸልመዋቸው ካልሆኑ እኔ እስከነበርኩበት ጊዜ ከአክሱም ከተማ ወደ ሰሜን በኩል የሚገኝ ከአክሱም ወረዳዎች አንዱ የነበረ ነው።ጌታቸው ረዳ) ከተባለው ሕዝብ የተፈጠረች ነበረች።
ከእለታት አንድ ቀን ይህች ልጃገረድ እርቃነ ሥጋዋን ወጥታ ፀሐይ ስትሞቅ አንድ ጐረምሳ (የንጉሥ ልጅ) አያትና ክብረ ንፅህናዋን ደፈራት። ጐረምሳው ይህንን ተግባር ሲፈፅም በአካባቢው የነበረው ዘንዶ አተኩሮ ይመለከት ነበርና እሱም የተፈጥሮ ስሜቱን ከውሀው ላይ ረጨ። አመፀኛውም የንጉሡ ልጅ ተግባሩን ከፈፀመ በሗላ ልጅቷን እዛው ጥሏት ሄደ። እሷም የገጠማትን ከባድ አደጋ ተቀብላ ዘንዶው የተፈጥሮ ስሜቱን ወደ ረጨበት የምንጭ ውሃ በመሄድ የተራከሰችበትን ለማፅዳት ስትል ደጋግማ ታጠበችና ከንጉሡ ልጅ እና ከዘንዶው አረገዘች።
መከረኛዋ ወጣት ልጅ ከሕብረተሰቡ ጋር አብራ ለመኖር ስላልቻለች የበረሃ ኑሮዋን ተያያዘችዉ። የተረገዘ ሳይወለድ አይቀርምና አንድ ዘንዶና አንዲት ሴት ልጅ (ሰው) ወለደች)። እሷ ግን ዘንዶውን እንደወለደች ወዲያውኑ ሞተች። የተወለዱት ሴት ልጅ እና ዘንዶ ግን በተወለዱበት በረሃ ላይ ማደግ ጀመሩ። የአካባቢው እረኞች አዩዋቸውና ለወላጆቻቸው ነግረው የአካባቢው ሰው ተሰብስቦ ተመለከታቸው። ልጅቷ ዘንዶውን ገድላ ከሕብረተሰቡ ጋር እንድትቀላቀል መከሯት። እሷ ግን ወንድሜን የእናቴን ልጅ አልገድልም አለች። ዘንዶውም “አጋብስ” እየተባለ ይጠራ ነበር። አጋብስ አደገ። ቁመቱም 70 ክንድ ሆነ።የጥርሱ ብዛትም 70 ሆኑ። ይህ አጠቃላይ ፍጥረቱ አፀያፊና የሚዘገንን ፍጡር፤ ሰውን እያደነ መዋጥ ጀመረ። አጋብስን የሚያሸንፍ አቅም ያለው “ወንድ” ጠፋ። በዚህ ጊዜ ከልጅቷ ጋር ተባብሮ መፍትሄ ማግኘት እንደሚሻል ሕዝቡ አመነ። በመጨረሻ ልጅቷ በቋንቋው አነጋገረችውና ከስንት ልመና በላ (አስር በሬዎች፤አስር ላሞች፤አምሳ በጐች፤ አምሳ ፍየሎች፤አንድ ጋን ማር፤ አንድ ጋን ወተት፤ አንዲት ወጣት ልጃገረድ) በየቀኑ ግብር የሚሰጡት ከሆነ ተስማምቶ እንደሚኖር በጉልበቱ እንደማይጠቀም ቃል ገባላቸው። በዚህ ዓይነት ሕዝቡ ግብር እየከፈለ አራት መቶ ዓመት ኖረ።የሚሰጡትን ልጃገረዶችም በተቆጣ ጊዜ ይውጣቸው ነበር።
እጅግ በጣም ብርቱ ሕዝብ የነበረው የመደባይ ነዋሪ በዚህ ክፉ አውሬ እየተገዛ ቆየና አንድ “ገብጋቦ” የተባለ “የሐማሴን ተወላጅ” (እዚህ ላይ ልብ በሉ፤ ከትግራይ/መደባይ “ወንድ” ታጥቶ ዘንዶውን የሚያሸንፍ ወንድ ኤርትራዊ ሰው ተላከላቸው ማለቱ ነው) ወደ መደባይ መጣና የመደባይ ሕዝብ ከእርሱ ጋር በአንድ ነገር ላይ ተስማማ። እሱም ከአጋቦሳ ነፃ ካወጣቸው  ዕድሜ ልኩን የልጅ ልጅም ጭምር በአጋቦሳ ምትክ ተተክቶ ሊገዛቸው ተስማሙ። ከዚህ በሗላ ሓማሴናዊው ገብጋቦ ዘንዶው ባለበት ዙርያ ትልልቅ ግንድና ሰባት ግመል አድርጎ ዙርያውን በአንዷ ላይ እሳት ለኩሶ በአራቱ ማዕዘንም አቀጣጠለ። ዘንዶ ማምለጥ አልቻለምና እዚያው ተቃጠለ። በመጨረሻም ገብጋቦ በመጥረቢያ ራሱን ፈነከተውና፤አረፈ፤ሞተ።
በመሬት የተረጨው የአጋቦስ ደም (የዞንዶው ደም) ዝናብ ሲዘንብ ERAGROSTIS ABISINIA/ጤፍ ወደ ተባለ የአዝርእት ዘር ተለውጦ ለሕዝበ ኢትዮጵያ ምግብ ተብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀለ። “ወቀተልኮ ለከይሲ ወወሃብክሙ ሲሣዮሙ ለሕዝበ ኢትዮጵያ”፡ ይህ “የዘንዶ ደም ነጠብጣብ” ጤፍ የተባለ አዲስ  የተረገመ  ዘር ለኢትዮጵያዊያን ቀለብ ተብሎ የተፈጠረ እስካሁን ድረስ ይመገቡታል።  “ዘንዶን ከገደልክ በላ ገብጋቦ ልጅቷን -(የዘንዶውን እህት) አግብቶ በመንገሥ የመጀመሪያ አክሱማዊ ስርው ንግሥነት በሀገረ አበሻ እንደ መሰረተ ሞተና አክሱም ላይ ተቀበረ፡ ልጅቱም የልጅ ልጆቹም የአክሱም ነገስታት ሆነው ቀጠሉ። በሰባተኛው ትውልድ አንዱ የአያቱን ስም በመውሰድ አጋቦስ ይባል ነበር።” ይላል፡ የአባ ታጋይ ይስሐቅ መጽሐፍ ጉደኛ ነው።
እናንተ አበሻ እንጂ “ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት” የሚባል በሽታ ያሳምመኛል; በጣም ኩፉ በሽታ ነው። እናንተ ኢትዮጵያ አይደላችሁም፤ ይህ ስም በአፍሪካ ቀንድ መድሃኒት የሌለው በሽታ ነው ይለናል።
የትግራይ ተወላጅ የሆኑት አቶ ይትባረክ ግደይ የዛ ኤርትራዊ መነኩሴ መጽሐፍ ካነበቡ በላ ገርሟቸው እንዲህ አሉ፦=” ኤርትራዊያኖች ለእውነት ስትሉ ፍረዱ። ትላንት የቀንና የማታ ቀለቡ የነበረውና በርካሽ እየገዛ ሲዝቀው እና ሲሽቀዳደምበት የኖረውን ነጭና ቀይ የኢትዮጵያ ጤፍ ከዘንዶ ደም ነጠብጣብ የበቀለና የተረገመ ዘር፤ ለኢትዮጵያዊያን ቀለብ ተብሎ የተፈጠረ ነው ይለዋል ምንም ሃፍረት ሳይሰማው።
አባ ይስሐቅ እንዲህ ይበሉ እንጂ፤ ዛሬም ቢሆን አይገኝም እንጂ ከተገኘ በጁቡቲ እና በየመን በሱዳን ዞሮ በገጠር ድምበሮችም ዙርያ በኮንትሮባንድ ወደ ሰለጠነቺው ወደ አባ ይስሐቅ አገር ኤርትራ እየተሻገረ ኩንታሉን አሁን 13,000 ናቕፋ አየገዛ ለእርዳታ ከሚሰጠው ፊኖ እና ሟሽላ እንዳታልቅበት ተጠንቅቆ በቁጠባ እየደባለቀ እንደሚኮመኩመው ሁሉም የሚያውቀው ዜና ነው። ኤርትራ ነኝ ብሎ ራሱን የሚጠራ የመረብ ምላሽ ሕዝብ ይቸገራል እንጂ የሻዕቢያው ታጋይ መኖክሴ ፀሐፊ መጽሐፉን እየሸጠ “ከዘንዶ ደም” የበቀለ ነው ብሎ የሚያንኳስሰው ለኢትዮጵያውያን የተሰጠ የምግብ ዘር ሳይጠየፈው እያፈላለገ በድሎት እየኖረ መመገቡ መቸ ይቀራል! ብለዋል።
ዛሬም የዛ በጣሊያኖች ፕሮፓጋንዳ ያሰከረው አባ ይሳሐቅ ገብረየሱስ ተማሪ የሆነው ሻዕቢያ ሰላይ ተስፋየ ግበረ አብም የንቀቱ ንቀት  ይውጣላችሁ ብሎን “““ኢትዮጵያ በእግዚአብሄር እጅ የተሰራች” የሚለው ሙገሳም ለዚህ ዘመን አይሆንም። ጊዜውን ጨርሶ የተጣለ አባባል ነው።”  ሲል የኢትዮጵያ አምላክ ታምራዊ ሃይል እና መለኮታዊ ጥበቡን በማጣጣል  በመንፈሳዊ እምነታችንና ተዋህዶ ቤተክርስትያናችን ላይ አዲስ ጥቃት ሰንዝሮብናል።
ኢትዩጵያውያን በያላችሁበት ዓለም ይህ የሻዕቢያ ሰላይ ፤ አንድነታችንን ለማፍረስ ሳይታክት ለብዙ አመት እስካሁን ድረስ እየሰራ ስለሆነ፤ ይህንን ሰው የሚያስጠጉ ሰዎች እና ተቃዋሚዎች እና ሚዲያዎች ተባባሪዎቹ ሆነው ሲገኙ ያለማመንታት እነሱንም በግልጽ ማውገዝ ማጋለጥ መቃወም አለባችሁ። ከለየለት ጠላት ይልቅ እኛን መስለው ከሚያጠቁን እና ከሚያስጠቁን የኛ ሰዎች መጠንቀቅ አለብን። Ethiopia Shall soon Stretch forth her hands unto her God የሚለው  የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ኢትዮጵያን ሬቪው የተባለው የታወቀው የሻዕቢያው አፍቃሪና አፈቀላጤ “ኤልያስ  ክፍሌ” በድረገጹ ላይ Mon Feb 20, 2012 1:40 pm ”Ethiopia Shall soon stretch forth her hands unto Eritrea” ተብሎ እንዲነበብ ፈቅዶ ተለጥፎ እየተነበበ ነው። ኢትዮጵያውያን ሆይ! እናንተን መስለው ገብተው ያገራችሁን ክብር እና እምነታችሁን እንዲራከስ የሚፈቅዱ ተቀጣሪዎች እጅጉ እንድትጠነቀቁ እንደ ወዱ ኢትዮጵያዊው ሊቅ እንደ “አቶ አስረስ የኔሰው” ሳየሰለቸኝ የውስጥ ሴረኞችንና ሰላዮችን እንድንቋቋማቸው አሁንም በድጋሜ ጥሪየን አቀርባለሁ።በትዕግሰት ስላለነበባችሁኝ አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳwww.ethiopiansemay.blogspot.com  getachre@aol.com