Tuesday, November 18, 2014

ዴምህት “ዓሰብ! ዓሰብ!” የአማራዎች መፈክር ነው አለ፡ ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay ብሎግ አዘጋጅ)ዴምህት ዓሰብ! ዓሰብ! የአማራዎች መፈክር ነው አለ፡
ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay ብሎግ አዘጋጅ)
Novemeber 18/2014
በዚህ ጽሑፍ የተለያዩ ጉዳዮችን አንመለከታለን። መጀመሪያ ይህ ፎቶግራፍ  ይመልከቱ።

ሃብቶም ተኪኤ ይባላል። ኤርትራ ውስጥ በኢሳያስ ጽ/ቤት ልዩ የደህንነትና የጥበቃ አባል የነበረ ነው። አሁን በስደት ኢትዮጵያ ውስጥ ጥገኝነት ጠይቆ ትግራይ ውስጥ ለኤርትራኖች ከተዘጋጁት መጠለያዎች ውስጥ እየኖረ ነው። ይህ የሃብቶም ተኪኤ ፎቶግራፍ የሚያሳየን የኢሳያስ አሽከር በሆነው በጀነራል ተኽላይ ክፈለ (ተኽላይ ማንጁስ) እጅ በምላጭ ምላሱ ከተዘለዘለ በኋላ ነው።


እነኚህ የስቪል ልብስ የሚለብሱ ልዩ የጥበቃ ሃይሎች፤ ኢሳያስን በሩቅ የሚጠብቁ ብቻ ሳይሆኑ፤ ኢሳያስን በቅርበት ሚጠብቁትን ልዩ ኮማንዶዎችንም ጭምር በረቀቀ ስልት እነሱንም የሚከታተሉ ናቸው።  ያለ ምንም ፍተሻ በፈለጉበት ቦታ መግባት ይችላሉ። እነሱ በተኙበት ቴንዳ/ወታደራዊ የመኝታ ክፍል ዘው ብሎ በቀላሉ የሚገባበት አይደለም። ጥብቅ ፈቃድ እና ፍተሻ ይደረጋል። ናይት ክላብ ውስጥ ይገባሉ። እንደ ማንም ሰው ዳንኪራ እየረገጡ ይዝናናሉ። ከስለላ ጽህፈት ቤቶች የሚተላለፍላቸው የውጭ ዜጎች ስም ዝርዝር  እንዲከታተሉዋቸው ሲሰጣቸው በሚገቡበት እና በሚንቀሳቀሱበት ሁሉ በድብቅ ይከታተላሉ። ማንም ሰው ያለ ምንም ጥያቄና ማዘዣ ማሰር ይችላሉ (በቃለ መጠይቁ መሰረት)። 

ለዚህ አሰቃቂ ግፍ ሊደርስበት ያስቻለበት ምክንያት አንድ ወጣት እና አንዲት እርጉዝ ወጣት ሚሊሺያ ድምበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ ለመሸሽ ፈልገው ትብብሩን በሚያሳዝን ልመና  ጠይቀውት፤ ሰውዬው ልቡ ስለተነካ ለእሱ እና ለመሰል ጥቂት ልዩ የኢሳያስ ደህንነት አባሎች የሚሰጥ *የኢሳያስ አፈወርቅ ማህተም እና ፌርማ ያረፈበት ልዩ የይለፍ ደብዳቤ* ቅጅ/ኮፒ ሰጥቷቸው ሊያቆማቸው የሞከረ ሰው ቢኖር ወረቀቱን ያለ ፍተሻ የሚያሳልፈውን ይህ ልዩ የይለፍ ወረቀት ለሚጠይቃቸው ሁሉ እንዲያሳዩ ሰጥቶ ሸኝቷቸው ስለነበር፤ ባጋጣሚ ለመሻገር ባሰቡበት ድምበር ከፍተኛ ሃላፊዎች ስለነበሩ፤ ልጆቹ ተይዘው ወደ ሃላፊዎቹ ሲቀርቡ፤ ጉዳዩ ሲጣራ እርጉዟ ወጣት መታወቂያው ማን እንደሰጣቸው ስለተናዘዘች ፤ ሃብቶም በጀኔራል ተኽላይ ትእዛዝ ተይዞ እጁ እና አግሮቹ በካቴና ታስሮ እስር ቤት እንዲቆይ ካደረገ በኋላ፤እራሱ ተኽላይ ማንጁስ ሃብቶም ወደ ታሰረበት ክፍል ካንድ ወጣት መርማሪ ጋር በመግባት ሐኪሞች ለቀዶ ጥገና የሚጠቀሙበት ብሌድ/ ምላጭ ከኪሱ አውጥቶ ሃብቶም አፉ በሰፊው እንዲከፍት ካዘዘው በኋላ ምላሱን በእጁ ጎልጉሎ በመጐተት ምላሱን ዘለዝሎ/ቆርጦ የተወው ምላሱ ነው ከላይ የምታዩት አሰቃቂ ግፍ። በኢትዮጵያዊ ሳይሆን *ኤርትራዊ በኤርትራዊ* የሚፈጸም የግፍ ማስረጃ ላሳያችሁ የሞከርኩት ይህ ጭካኔ ማስረጃ ኢትዮጵያ በደለችን የሚለው የኤርትራ እና የወያኔዎች ግማታም ውሸት ከእንግዲህ ወዲህ አገራችንን የሚወቅሱበት ሞራልም ብቃቱም እንደሌላቸው ለማሳየት ነው።

ወየኔዎች እና ኤርትራኖች *አማራ/አምሓሩ* ግፍ ፈጽመውብን ነው በረሃ የገባነውና የተነጠልነው እያሉ ሲዘላብዱ አደንቁረውን፤ ጅላጅል ምሁራን ኢትዮጵያዊያንም የነሱን ዲስኩር ተከትለው ስለ ኤርትራ ጥብቅና ቆመው የኢትዮጵያ ሰራዊት በኤርትራዊያን ላይ ግፍ ፈጽሟል እያሉ አገራችን በመጥፎ ገጽታ እንድትታይ የደሰኰሩብንን መጽሐፍቶቻቸው በገፍ ይገኛሉ።  አሁን አማራ አስመራ ውስጥ የለም ፤ አሁን በምላስ ቆራጭነት እየተወገዘ ያለው ማን ነው? ብለን መልስ ፍለጋ ሁለቱንም እየጠየቅን ነው። ምላስ ይበሉበታል እንጂ ግፍ አይናገሩበትም ይባላል። *አማራ! አማራ! በደለን* ዘፈናቸው ለዚህ ግፍ ዳረጋቸው። ጊዜ መስተዋቱ!
 አንድ አይናማው ጀኔራል ተኽላይ ማንጁስ ማለት ይኼ ነው። ተኽላይ የብሔራዎ ውትድርና ጉዳዮች ዋና አዛዥ ነው። በዚህ ላይ የኢሳያስ ልዩ የምሰጢር ባለሟል ነው።የኢሳያስ አፈወርቂ መጠጠኛነት /አልኮሆሊስትነት ማንጁስም አብሮ ይጋራዋል ይባላል።  ኤርትራኖችን ወደ ሲናይ በረሃ ፤ለአረቦች  በመሸጥ የሚጠረጠር ነውም ይባላል።

ይህ የምላስ ቆረጣ ፎቶ ስታዩ እንደኔው ከተገረማችሁ፤ ለአግራሞታችሁ ማስታገሻ ጦቢያ መጽሔት 1985 ዓ.ም መዲና እና ዘለሰኛ በሚል ርዕስ ታትሞ የነበረ አንድ ሁለት ግጥም ልመርቅላችሁ። ገጣሚው ይስፋወሰን ቦጋለ ይባላሉ።

(1)
ወንድም እህት አድርጌአቸው
ኖርኩ ካብቴ ሳካፍላቸው
ውለው አድረው አሙኝ
*ነጻነት* የለንም አሉኝ  
ሌላ ምን እላለሁኝ
ከኔ ተለይተው ያሳየኝ። 

(2)
የጎረቤት ሰዎች የምናውቃቸው
አዲስ ቤት ሰርተው ከመግባታቸው
ማፈራራስ ጀመሩ እየነቃቀሉ
ቤት-ለምቦሣ አንኳን ሳይባሉ።
**************************

በመጀመርያ ከአዘጋጁ መልዕክት፡

ዛሬም በድጋሚ ስለ ገጣሚ እና ባለ ቅኔ ሃይሉ  ገብረዮሃንስ (ጐመራው) አንድ ነገር ብየ ወደ ርዕሴ ልገባ ነው። የጀመርኩትን ዘገባ አንዳይቆራረጥብኝ በማለት የኣርበኛው ጎመራው ሞት በድረገጼ በሰፊው አልዘገብኩትም። ሆኖም ለወደፊቱ በስፋት መዘገቤ ስለማይቀር እና ገላው ቢለየን ሥራውና መንፈሱ ኗሪ በመሆኑ የትም አይሄድም እና በሰፊው እንመለከተዋለን። ኢትዮሚዲያ፤ ዘሓበሻ እና መሰል መንቲያዎቻቸው ስለ ታለቁ ኢትዮጵያዊ  በላቅኔ ጎመራው ሕልፈተ ዜና ሳይዘግቡ መቅረታቸው ኢትዮጵያዊያን አገር ወዳዶች ትዝብታችሁን ልብ አንድትሉ ሳሳስብ። በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ጎመራው ዜና ዕረፍት የዘገቡ ድረገጾች፤ራዲዮኖች በጣም አድርጌ ሳመሰግን፤ ወዳጄ የሙዚቃ ሊቅና መምህር አቶ ዘነበ በቀለ ስለ ጎመራው ዕረፍት ያቀነባባረውን ዜማ እና የህይወት ታሪኩ በዩ-ቱብ ተለጥፏል እና እሱን አንድትመለከቱ አደራ። ወዳጄ አቶ ዘነበ በቀለ የቁርጥ ቀን ልጅ ነህ እና እግዚአብሔር ያክብርህ።  Hailu Gebreyohannes (Gemoraw) - Best Known Poet http://youtu.be/bIVo2i0RstY

አሁን ወደ ጉዳያችን እንግባ።

 አሁንም በድጋሚ የድሮ እና አዳዲስ አንባቢ አድናቂዎቼ አበራታች መልዕክታችሁ እየደረሱኝ ነው። በርካታ ስለሆኑ ጊዜ ወስጄ እመልስላችሗለሁ። በደፈናው እጅግ፤እጅግ አመሰግናለሁ። በዚህ አጋጣሚ ዶክተር ጌታነህም ልክ የሚነካ አበረታች ደብዳቤዎ ደርሶኛል እጅግ  አመሰግናለሁ።

ኢትዮጵያ በጠላት ከተከበበች ዘመናት አልፏታል። የዛሬ ከበባ ከባድ የሚያደርገው በገዛ ልጆችዋ ከድተዋት ደባ እየሸረቡባት  በመሆኑ ከባድ ያደርገዋል። በተቃዋሚ ስም ጠላቶች ተሰግስገው ታጥቀውም ሆነ ሳይታጠቁ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የየራሳቸው መጥረቢያ ይዘው ቆርጠው ሊጥሏት ግዝገዛው ተያይዘውቷል ስል የነበረው ለዚህ ነው። ይህ ግዝገዛ አንዲቆም በተቻለኝ መጠን እነማን አንደሆኑ ለበርካታ አመታት ሳላቋርጥ ተችቻቸዋለሁ። ብዙ ጅሎች አንኔን ተመልሰው እየዘለፉ፤ አንዴ ወያኔ ነህ፤ አንዴ ያልሰጡኝ ስም አልነበረም። ወጣቱ የተሰለበ ስለሆነ፤ በስሜት አጋልበውት ጊዜ ስለወሰደበት አሁን አሁን ቁጥራቸው የማይናቅ ወጠቶች እና ተከታዮቻቻው *ሰከን ብለው* የኔን ምጉት እና የማቀርበው ማስረጃ በመመልከት ልብ ወደ መግዛት አዘንብለው አለቆቻቸውን የመጠራጠር አዝማምያ በየፓልቶኩ እየተደመጠ መሆኑ አንዳንድ መረጃዎች ይደርሱኛል። 

አንዳንድ ጊዜም እራሴ ሳላዳምጥ አልቀረሁም። ብዙ ቢቀራቸውም በቅጥፈት እና በረቀቀ ውሸት የተወጣጠረው ስሜት አሁን የቀነሰ ይመስላል።
ሁሉም በየተራ ጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምን እየሸረቡለት አንደሚገኙ እስከ መጨረሻዋ ትንፋሻችን ድረስ ሽረባቸውን ታሪክ አንዲዘግበው ግዴታችን አንወጣለን ብለን ቃል ገብተን ይኼው ቀጥለናል። ባለፈው ሳምንት በክፍል 1 አንደገለጽኩት ይህ ጽሑፍ የዛው ክፍል ተከታታይ *ዴምህት እና ገብሩ ስብሐት እና ገብሩ ክፍል 2 ነው። ርዕሱ የለወጥኩበት ምክንያት ዴምህትን ለማወቅ ርዕሱን በመመልከት ብቻ በቀላሉ ሊያስረዳ ይችላል ከሚል ነው።

አንዳንድ አንግዳ አንባቢዎቼ ስለሚኖሩ ዴምህት ምን ማለት አንደሆነ ትርጉሙ ልግለጽ።  ዴምህት ትግርኛ ነው። ዴሞክራሲያዊ ምንቅስቓስ ህዝቢ ትግራይ/ የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን/TPDM/Tigray People Dimocratic Movement) ማለት ነው። ዴምህት እያለ ራሱን የሚጠራ አብዛኛው በትግሬ ተወላጆች ተዋጊ ሃይል የተገነባ በኢሳያስ አፈወርቅ የበላይ ተቆጣጣሪነት ብያንስ ለ 13 አመት ኤርትራ ውስጥ የመሸገ ከ45 ሺሕ ተዋጊ ሃይል አንዳለው የሚነገርለት 
ለኤርትራኖች ጠቀሜታ የተገነባ ቅጥረኛ የሽምቅ ተዋጊ ወራዊት ነው።

አቶ ገብሩ አስራት *ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ* በሚል ርዕሱን መሰረት ያደረገ የወያኔን የባንዳ ሚስጥሮችና ውሳኔዎች ምን አንደተደረገ በጻፈው ታሪካዊ መጽሐፍም ሆነ  ባደረጋቸው ቃለ ምልልሶች ያልተደሰተው ይህ ቅጥረኛ የሽምቅ ተዋጊ ቡድን፤ አቶ ገበሩ አስራትን እና ጠቅላላ ወያኔዎችን *ጠላም/ጠላማት* (ከዳተኛ/ከጂዎች) በማለት ዘልፎታል። ይህ ሊል ያስቻለው የመነሾ ምክንያትም እንመለከታለን። ከዚህ አያይዘን የምንመለከተው የዚህ ቅጥረኛ ድርጅት በገብሩ አስራት ላይ ቅሬታ ያንጸባረቀበት ሌላው አስገራሚ መግለጫው ደግሞ፤ ገብሩ  በመጽሐፉም ሆነ በቃለ መጠይቆቹ፤ ሌላ ቢቀር ፤ቢያንስ፤ ቢያንስ፤ የዓሰብ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ሕጋዊነት አለው፤ ብሎ የተከራከረበትን ሰነድ ያወገዘበትን አስገራሚ የትግርኛ ድርጅታዊ መግለጫው እንመለከታለን። 

(በነገራችን ላይ ኢትዮጵያዊያን ኤርትራን የሚፈልጓት ባሕሩን እና መሬቷን እንጂ ሕዝቡን አንፈልገውም ብለው ለዘመናት ተናግረዋል፤ እያሉ ውሸታሞቹ ኤርትራዊያኖች ብዙ አንዳሉ አንብባችኋል። ይህንን በሚመለከት አዲስ አበባ ሲታተም በነበረው ዜጋ መጽሔት በሰፊው ጽፌ ነበር። ጹሑፌም መልስ ለመለስ ዜናዊ ነበር (አቶ መለስ፤ አይዋኒን’ናን!!)። እኛ ኤርትራኖች ወንድሞቻችን ናቸው ስንል፤ በደምም በአጥንትም፤በታሪክም የሚያገናኘን ነገር የለም፡ ባዕዳን ናችሁ፤ ሲሉን፡ እሺ ይሁንላችሁ ፤ባዕድ ነን ካላችሁን የባሕር በሮችና ደሴቶቹ በታሪክም በሕግም ለኛም ይገባናል እና ወደቦቻችን እና ደሴቶቻችን እኩል እንካፈል፡ ስንል  ባሕሩን አንጂ ሕዝቧን አይፈልጉም፤ እያሉ የዋሁን ኤርትራዊ ስለሚያወናብዱት፤ ከእንግዲህ ወዲህ አቶ መለስ ስለ ኤርትራኖች ጉዳይ እየፈተፈትክ አታደንቁረን ፤ በአክሱም/በዓድዋ ትግርኛ “አይ ዋኒን’ናን!!” (ጉዳያችን አይደለም!) ብየ መኖሬን ልብ በሉ። ኢትዮጵያዊን (አማራዎች በእነሱ አገላለፅ) ባሕሩን አንጂ ሕዝቡን አይፈልጉትም የሚሉት ዛሬም እየደገሙት ያለውን ቅጥፈት (መስከረም.ኔት በተባለው የውሸት ቀፎ ድረገጻቸው አሁንም በግልጽ ተጽፎ ታያላችሁ፤ ንጉሡ ያልተናገሩትን፤ያላሉትን ብለዋል እያሉ።)  ልብ እንድትሉት ነው በቅንፍ ያሰገባሁት”)

ገብሩ በቪኦኤ የአማርኛም ሆነ የትግርኛ ክፍለ ጊዜ ባደረገው ቃለ ምልልስ *ከባድሜ ጦርነት በኋላ በአልጄሪስ የተደረጉ ስምምነቶች ተቀባይነት የለውም፡ ምክንያቱም ስምምነቱ ከተደረገ በኋላ ልክ ጣሊያን በ1935 ዓ.ም እንዳደረገው የሰላም ቀጠና መስመር/ባፈር ዞን የተባለው ቀጠና ደፍሮ አፍርሶ ኢትዮጵያን አንደወረረ ሁሉ ፡ ስለ ባድሜና መሰል አካባቢዎች የተደረጉት አልጀሪሳዊ ስምምንቶች በሕግ አይሰራም። ስለዚህም አንደገና ድርድር መደረገ አለበት። ብሏል። አሁን ድርድር ሲደረግ ግን የባድሜ እና ተያያዥ ድምበሮች ብቻ ሳይሆን እኔ ሥልጣን ላይ እያለሁ የተደረገው ኤርትራን ጥቅሞ ኢትዮጵያን የጎዳ የኤርትራ ነጻነት ውሳኔም እንደገና መታየት የግድ አለበት። ብሏል።
  በ19ኛው ክፍለዘመን ጣሊያን ኤርትራ እና ኢትዮጵያ በሚመለከትም፤ ምኒሊክ በሁኔታዎች ተገድደው ያደረጉት ስምምነት፤ ቄሳሩ ጣሊያን በ1935 ዓ.ም ማለፍ የሌለበትን ቀጠና ውሉን ደፍሮ በማፍረስ ኢትዮጵን በመውረሩ የፈረመበት ስምምነት በሕግ ፊት የተጣለ፤የሕግ ሽፋን ስለሌለው፤ ያንን የበሰበሰ የፈረሰ ውል ተንተርሰን ኤርትራን ለመጥቀም ስንል የኢትዮጵያን ጥቅም በከፍተኛ ደረጃ ጎድተን ውሳኔ በመወሰናችን እንደገና ድርድር መደረግ አለበት! ኤርትራኖች አይሆንም ካሉም በሕግ እንከሳለን። ብሏል። ቢያንስ ሕጋዊነቱ የተረጋገጠ ኢትዮጵን የባሕር በር ባለቤትነት ለማድረግ በእንግሊዝ ጊዜ፤ ለተባበሩት መንግሥታት ለፌደረሽኑ መመስረት አስፈላጊነት ምክንያት ሆነው ከቀረቡት አንዱ የዓሰብ/ባሕር ወደብ ባለቤትንት ጉዳይ ኢትዮጵያን የሚመለከታት እንደሆነ በመጥቀስ፤ ይህንን በማስታወስ ዘግተነዋል ያልነውን መዝገብ እንደገና መከፈት አለበት። ሲል ገብሩ የተከራከረበትን አዲሱ ኢትዮጵያዊ/ፍትሃዊ አቋም በትግሬ ሕዝብ ስም በኢትዮጵያ ሰንደቃላማ የአክሱም ሃውልት ለጥፎ ሚንቀሳቀስ ዴምህት የተባለው የሽምቅ ተዋጊ ይህ የገብሩን ሃሳብ በማውገዝ ለኤርትራኖች በመወገን ከኤርትራኖች በላይ ኤርትራዊ በመሆን የሚከተለውን አስገራሚ የቅጥረኛ መግለጫ፤ ኤርትራዊነት በተላበሰ የኤርትራ ትግርኛ ቋንቋ አውጥቷል።
ለታሪክ ዘጋቢዎች አንዲመች በትግርኛ የተጻፈው መግለጫወን አቀርባለሁ። ትርጉሙም ተያይዞ ይቀርባል።

ክቡራትን ኩብራንን ደገፍቲ ቃልስና ኣብ ዉሽጢ ሃገርን ወጻኢ እትነብሩ፡
 

ኣብ ዉሽጢ ኢትዮጲያ ኣንጻር ጠላማት መራሕቲ ወያነ ዝጉሃሃር ዘሎ ብፍላይ ድማ ብግንቦት 7 ዝምራሕ ኣዝዩ እንዳንሃረ ዝቅጽል ዘሎ ሓያል ህዝባዊ ቃልሲ ከምኡ እዉን እቲ ኣብ መንጎ ግንቦት 7 ዴምህትን ዝተኸተመ ናይ ወትሃደራዊ ስምምዕ ንጠላማት መራሕቲ ወያነ ኩቱር ራዕዲ ፈጢሩሎም ከምዘሎ ብግብሪ እንዕዘቦ ዘለና ጉዳይ እዩ።

እታ ብጭንቀት ዝተሓመሰት ጸባብ ናይ ጠላማት መራሕቲ ወያነ ሓንጎል ንህዝቢ ኣምሓራ ንምትላል ሓንሳብ "ዓሰብ ናይ ኢትዮጲያ እያ" ሓንሳብ ድማ "ናይ ኤርትራ ሕቶ መግዛእታዊ ኣይነበረን" "ወያነ ቀደም ተጋጊና ኢና" ክብሉ ኣብ መራኸቢ ብዙሓን ተጠሊዖም ይግዕርሩ ኣለዉ። "ሑኑቅ እንታይ የዉጽእ? ዓፍራ" ከምዝብሃል ጠላማት መራሕቲ ወያነ እታ ህዝቢ ኢትዮጲያ ዝተትዓ ገመድ ኣብ ክሳዶም ኣትያ ምስተሾቅረረት ግድን እዩ ከም እኒ ኣይተ ገብሩ ኣስራትን ኣይተ ስብሓት ነጋን ክዓፍሩ።”
https://www.facebook.com/demhit.wellelo?fref=ts

“የተከበራችሁ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር ምትገኙ የትግላችን ደጋፊዎች ሆይ!

በኢትዮጵያ ውስጥ በካሃዲዎቹ ወያኔዎች ላይ እየተፋፋመ ያለው የተቃዋውሞ ድምፅ፤ በተለይ ደግሞ በግንቦት 7 እየተመራ ያለው እየተቀጣጠለ ያለው የህዝብ ትግል እና እንዲሁም የግንቦት 7 እና የዴምህት ማህተም ያረፈበት ወታደራዊ የጋርዮሽ ስምምንት ለካሃዲዎቹ የወያኔ መሪዎች ብርቱ ፍርሐት እያሳደረበት እንዳለ እየታዘብነው ያለው ጉዳይ ነው።

\ያቺ በጭንቀት እየታመሰች ያለቺው የካሃዲዎቹ የወያኔ መሪዎች ጠባብ ሕሊና፤ የአማራን ሕዝብ ለማታለል ሲሉ አንዴ"ዓሰብ  ኢትዮጲያ ነች" አንዴ ደግሞ " ኤርትራ ጥያቄ  የቅኝ/ባዕድ ግዛት አልነበረም፤ ውሳኔአችን ስሕተተኛ ነው" እያሉ በብዙሐን የመገናኛ መድረኮች ጮክ ብለው እያጓሩ ተደምጠዋል።     

የታነቀ ሰው በአፉ ምን ያወጣል ቢሉ *ዓረፋ* አንደሚባለው ከሃዲዎቹ የወያነ መሪዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ የገመደላቸው የማነቂያ ገመድ አንግታቸው ላይ ስትጠልቅ የግድ እነ አቶ ገብሩ ኣስራት አረፋ መድፈቃቸው አይቀሬ ስለሆነ ዓረፋ መድፈቃቸው የግድ ነው።”
https://www.facebook.com/demhit.wellelo?fref=ts

እንግዲህ በዚህ መግለጫ አራት ነግሮች ተጠቅሰዋል፤ እንመልከታቸው። የቅኝ ግዛት፤ጠላማት (ካሃዲዎች)፤ዓሰብ እና አማራ። መጨረሻ የተጠቀሱ ሁለት ነገሮች አበይት ጉዳዮች ስለሆኑ በሰፊው ስለምንመለከታቸው፤ ጠላም/ጠላማት (ነጠላ/ብዙሃን) የሚሉትን ቃላቶች ከምን የተነሳ ባሕሪ አንደሆነ ምንጫቸውንም ማን እንደሆነ እንመልከት።

ጠላማት ማለት ከሃዲዎች ማለት ነው። ይህ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ በመጽሐፍ፤በመጽሄት፤ጋዜጣ እና ራዲዮን በግጥም መደመጥ የተጀመረበት በባድመ የጦርነት ፍጥጫ ወቅት ነው። ምንጮቹ ኤርትራዊያኖች ናቸው (በኋላም ወያኔ ካድሬ ምሁራን “ጥልመት” (ክህደት) የሚል ኤርትራኖች በትግራይ ሕዝብ የፈጸሙት ወንጀል (ኢነተር ሃሙዌ አይነት ወንጀል) መጽሐፍ በመጻፍ እና ነፃነታችሁ በእኛ ሱሪ እና ፈቃጅነት አግኝታችሁ ስታበቁ፤ አሁን አላደረጋችሁልንም ብላችሁ ከዳችሁን በማለት ወያኔዎችም “ጥልመት” (ክሕደት) በማለት ጽፈዋል)። ኤርትራኖችም ይህ ጠላማት የሚል እሮሮአቸው በትያትር፤በዘፈን፤ በግጥም፤ በጽሑፍ በስዕል ፤በየስብሰባው ሰፊ ሽፋን አግኝቶ እያንዳንዱ ኤርትራዊ (አብዛኛው) ከሻዕቢያ ፕሮፓጋንዳ ክፍል የተደነቀረለትን ይህ ቃል “ጠላማት ወያነ !…. ጠላማት ወያነ !…” በማለት የአፍ መክፈቻቸው ቀዳሚ የስደብ ቃል ሆኖ አገልግሏቸው ነበር።


ለምን ከሃዲዎች አንዳልዋቸው፤ ሁላችሁም የምትገምቱት ነው። *ኤርትራ የግላችን ኢትዮጵያ የጋራችን* የሚለው መፈክራቸው በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የተመኙትን ሰፊ ስርቆት እና የታይዋን ሕልም ድንገት ሳያስቡበት ባጭሩ ስለተቀጨባቸው፤ የተዋዋለወነውን የጋራ ስርቆት እኛኑን አባርራችሁ እንዴት ለብቻችሁ ትዘርፋላችሁ፤በማለት የቁጣ እና የቁጭት ስድብ ያንጸባረቁበት ቃል ነው። የተዋዋልከው ሲከዳህ *ውል አፍራሽ/ከሃዲ* ብለን አንደምንለው፤ ትግርኛውም ፡ለነጠላ ከሃዲ ለብዙሃን ጠላማት ይላል። ይህ ቃል በሻዕቢያ ደጋፊዎች ዘንድ አሁንም ወያኔን በሚመለከት ሲተቹ  ካፋቸው የማይርቅ የአፍቸው መክፈቻ ስድብ ነው። ዴምህት ይህ በሻዕቢያ የዜና እና ማስታወቂያ ክፍል ተዘጋጅቶለት በስሙ እንዲተላለፍ የተደረገው መግለጫም ቃሉ ሲጠቀምበት ከማን አንደመነጨ እኛ ትግሬዎች ተጠቃሚው እና አመንጪው ማን እንደሆነ በደምብ ስለምናውቀው ነው ልገልጽላችሁ የፈለግኩት።    
ሌላው በመግለጫው የምንመለከተው፡ ዴምህት የተባለው ይህ ድርጅት በብርሃኑ ነጋም ሆነ በዚህ ደርጅት መግለጫ ድርጅቱ ከግንቦት 7 ጋር የጋራ ወታደራዊና ፖለቲካዊ  ስምምነት አንዳደረጉ ገልጸውልናል። ወታደራዊ ስምምነቱ ስትመለከቱት ግንቦት 7 ከሻዕቢያ ጋር የጋራ ወታደራዊም ፖለቲካዊም ስምምነት ፈርሟል ማለት ነው። ወታደራዊ ስምምነት ያለው የጋራ የሆነ ፖለቲካዊ ስትራተጂም አለው ማለት ነው። ሻዕቢያ የሚወጋው ወያኔን ብቻ ሳይሆን የባሕር በር ለኢትዮጵያ ወግኖ ሽምቅ ጦር ተዋጊ የመሰረተና ኤርትራን ወደ ድርድር ለማስገባት ጦርነት የከፈተ ድርጅት ሁሉ ሻዕቢያና ግንቦት 7 በጋራ ሊወጉት ነው ማለት ነው። ምክንያቱም ዴምህት ከዚህ ቀጥሎ የምናየው ዓሰብን የሚጠይቁ አማራዎች ብቻ ናቸው ብሎ ደምድሟል።
ዓሰብን የሚጠይቅ ደግሞ የኤርትራ ጠላት የሆነ ኢትዮጵያዊ ነው ብለው አስቀምጠውታል። ስለሆነም ፤ ዓሰብን ለኢትዮጵያ ባለቤትንት የሚጠይቅ ሁሉ ቀዳሚ ጠላት ነው ብለውናል።እነሱ ደግሞ አማራዎች የሚባሉ ናቸው ብሏል።  ዓሰብን በሚጠይቁ በአማራዎች ላይ ከኤርትራ ጋር ሆነን ስለ ኤርትራ ሉዓላዊነት እንመክታቸዋለን ማለቱ ነው።


ስለሆነም ግንቦት 7 እና ዴምህት በጋራ ወታደራዊ ስምምነታቸው መሰረት አማራውን ይወጋሉ ማለት ነው። ምከንያቱም ዴምህት በኢሳያስ የሚንቀሳቀስ ልዩ ወታደር መሆኑን ተደጋግሞ ተነግሯል። ስለዚህም ድሮ ወያኔ እና ኤርትራ ወታደራዊ ስምምነት እንዳደረጉት ሁሉ፤ ዴምህት ከግንቦት 7 ያ ደግሞ ከዴምህት የሚፈልጉት የሚለዋወጡት ነገር አለ። ይህ ደግሞ ያለ ኢሳያስ የሚደረግ ልውውጥ የለም። በተዘዋዋሪ ግንቦት 7 ከሻዕቢያ ጋር ወታደራዊ ሰምምነት ፈርሟል ማለት ነው። በመግለጫው መሰረት ስምምነቱ ደግሞ ዓሰብን የሚጠይቀው “የአማራ ሕብረተሰብ” ላለማስደሰት እና ዓሰብ የኤርትራ ነው ብሎ ኤርትራኖችን “ማስደሰት” ቀዳሚ ትግላቸው መሆኑን ነው የዴምህት/ቲፒዲኤም መግለጫ ግልጽ ያደረገልን።    


እዚህ ላይ መዘንጋት የሌለበት የዴምህት ወታደራዊ ሰምምንት ያለ ኢሳያስ ሙሉ ፈቃድ እና አውቅና እንደማይደረግ ማውቅ አለባችሁ። እንኳን ወታደራዊ ስምምንት ቀርቶ ፤የዴምህት መግለጫ ሳንሱር ተደርጐ ብቻ ሳይሆን ቀጥታ የሚጻፈው በሻዕቢያ በኩል የተመደቡ ዴምህትን የሚቆጣጠሩት የባላይ ሃላፊዎች የሆኑ ሻዕቢያዎች ናቸው። ለዚህ ደግሞ አበባ የተባለችው ኤርትራዊት ጋዜጠኛ ወደ ኢትዮጵያ እጇን በሰጠችበት ወቅት፤ ኦነጐችም ሆኑ የመሳሰሉት ሁሉ ዜና ፤ፕሮፓጋንዳ፤ ድርጅታዊ መግለጫዎችን በሙሉ የሚረቀቁት፤  አንዲሰራጭ የሚፈቅዱት ኤርትራዊያኖች አንደሆኑ አበባም ሆነች አሁን አውስትራሊያ/ አንግሊዝ አገር ጥገኛ ሆኖ የሚኖር በቅርቡ ስለ ተስፋዬ ገበረአብ መሰሪነት በዘሐበሻ እና ኢትዬ-ሚዲያ እያስነበበን ያለው *ሰናይ* የተባለው ጋዜጠኛ በሚገባ ያውቃል። እሱን ቃለ መጠይቅ ብታደርጉት ሰፊውን ታሪክ ይነግራችል። ስለሆነም ግንቦት 7 እና ዴምህት ወታደራዊ ሰምምነታቸው ዓሰብን ከጠየቀ ተዋጊ ሃይል ግምባር ገጥመው ሊወጉት ነው ማለት ነው። ይህ ግልጽ ነው። የኤርትራኖችም ሆነ የወያኔዎች የሰለችን አማራውን አንደ ጨው ማጣፈጫቸው የትም የሚደነቅሩት “አማራ የተባለ ሕብረተሰብ” ዛሬም ዓሰብን የሚጠይቅ *አማራ* ብቻ እንደሆነ ደጋግመው አሁንም በዴምህት በኩል ገልጸውልናል። ወይ አማራ ጅሉ ምን ይሻልህ ይሆን?! አማራ አማራ አማራ አማራ ..አሁንም ከላይ የተቀመጡት ወያኔዎች ይሁኑ እንጂ ቢሮክራሲው የሚያካሂዱት አማራዎች ናቸው “ስልጣን ያለው” አማራ ነውም ብለው እኮ ሲነግሩን ወያኔዎች ባንድ መግለጫቸው አንብቤአለሁ። አይገርምም? ምን ቢደረግ ይሻላል!?   

ይህ በእኛ በትግሬዎች ስም የሚሸቅጥ ቅጥረኛ ስብስብ፤ *ዓሰብ!ዓሰብ!* የሚሉ ፈካሪዎች አማራዎች ስለሆኑ ዓሰብ ለኢትዮጵያ መሰጠት አለባት ብለው የሚሉ አማራዎች ብቻ ናቸው ብሎናል ዴምህት የጌቶቹን ልሳን ሲያስተጋባ ። ሰው መስማት እምቢ ብሎኝ እንጂ እኔ ይህ ድርጀት ቅጥረኛ ነው ካልኩ ቆይቷል። ኢሳት የተባለው የግንቦት 7 ቴሌቪዥን ጣቢያ ኢትዮጵያዊ አድርጎ ሲቀባጥር ፤ መሪውን አስሬ እየጋበዘ ሲያሺፍብን ነብር። ስለ ግንቦት 7 እና ስለ ይህ ኤርትራ ባንዳ ሰራዊት አንድነት የጋራ ስምምነት እንደ ብርቅ ቆጥሮት የዋህ አድማጮችን ሲያታልል ከረመ። ተስፋዬ ገብረአብንና ጃዋርን በፖለቲካ ተንታኝነት ሲያጎለብቱብን መክረማቸው የሚታወስ ነው። አሁን ይኼው ሳይደባብቅ ተስፋዬ ገብረአብ ጊዜው ቆጥሮ እንደተጋለጠ፤ ዴምህትም የአያቶቹ የነ ኢሳያስ እና የትግሬ ልሂቃን ብሔረተኞች በአማራ ላይ የነበራቸው የቆየ ጥላቻ ወደ ዴምህት ተላልፎ ይኼው እነ ስብሓት እነ ስዩም መስፍን እነ መለስ ዜናዊ ሲነግሩን የነበረውን  ዓሰብ የአማራዎች/የነፍጠኞች ጥያቄ እንጂ የኢትዮጵያዊያን ጥያቄ አይደለም በማለት ኤርትራዊያኖች እና ወያኔዎች የሚሉትን ቃል በቃል  ዴምህትም ቃል በቃሉ ሳይቀንስ ሳይጨምር ያችንኑ ደግሞላችል። አሁን እኔን ከመውቀስ ተቆጠቡ። ስነግራችሁ የነበረውን ነው በማስረጃ ደግሜ ዛሬ ያሳያችችሁ። ገና ስለ እነ ብርሃኑ ነጋ ድርጅት ሌላ ጉድ ለወደፊቱ ታነባላችሁ። 

ወያኔ ለመጣል ለምን ሰይጣን ጋር አንፈራረምም ብሎ ብርሃኑ ነጋም ሆነ አንዳርጋቸው ጽጌ ሲነግሯችሁ “ስታንጨበጭቡ” የነበራችሁ ተቃዋሚዎች የአማራ ጥላቻ ከሌላችሁ በቀር ካሁን ወዲህ እነ ብርሃኑ ነጋም ሆነ አርበኞች ምናምን፤ምናምን የሚባሉት “አማራን ከሚጠላ” ዴምህት የጋራ ፓለቲካዊም ወታደራዊም ስምምነት አድርገናል ሲሏችሁ እጃችሁ እስኪቃጠል ድረስ ካንጨበጨባችሁ በሽታው የኛ ሳይሆን የናንተ ነው። ጉዳት ከደረሰ በላ ከንፈር መምጠጥ እርባና የለውም።

ለዚህ ነበር በድርጅታዊ መግለጫ “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” ስላለ ብቻ “ኢትዮጵያዊ” ነው እያላችሁ ተሎ ዝው አትበሉ፤ አትሞኙ፤ ረጋ በሉ ስል የነበረው። እነ ጋዜጠኛ ተመስገንም ሆነ እነ ፕ”ሮፌሰር መሳይ ባለፈው ክፍል አንድ ጽሁፌ ምን ያህል ጅላጅሎች/የዋሆች (ይቅርታ - ቃላት በማጣት ነው) አንደሆኑ ለማሳየት የሞከርኩት። በኤርትራ በኩል የሚመጣ ነጻነት፤ወታደራዊ ዕርዳታ ያለ ሪሞርክዮ/ተጐታች አይመጣም ብለን ነግረናል። ወያኔን በነፍጥ ለመግጠም ከፈለጋችሁ፤ አገር ውስጥ አንደማንኛውም ሽፍታ ሸፍቶ እምቢ ብሎ ገጠሩን ማስከትለ ይቻላል; “ሞት ላይቀር” አንደ አንዳርጋቸው ታግታችሁ ሳትታኮሱ (ወይ ሳዮናይድ መርዝ ለመከላከያ ሳትይዙ) ከመሞት ፡ አብሮ ካንተው ጋር ዱሩ፤ድንጋዩም፤ሰውም አራዊቱም ከሚተኛ ጋር ተታኩሶ መሞት ሕዝቡ የእምቢተኛነት ባሕሪ ያስጀምራል። ። አስፈላጊው ድፍረት ብቻ ነው። ሌላ ቀርቶ አዲስ አበባ ሆኖ በፈቀድም ባለፈቃደም ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጎ ወያኔንም በህዝባዊ አመጽ ማፍረስ ይቻላል። የጎደለው ፡ወኔ ብቻ ነው፤ ደፍረት! ከሽብርተኘው ኤርትራ ውጡ! አንድ ቀን ሻዕቢያ ከወያኔ ጋር ሲደራደር ሜዳ ለይ አንደሚበትናችሁ፤ መደራደሪያ ካርድ አንደሚያደርጋችሁ ምን አለ በሉኝ!

ትንሽ ስለ ስብሐት ነጋ

ክፍል ሦሰት ኤርትራ ሕጋዊ ኢትዮጵያዊ ምድር መሆኑን በቀላል አገላለጽ በመረጃ አስደግፌ ከነገ ወዲያ አቀርብላችሗለሁ። ስለ ስብሀታ ነጋ ለመተቸት ፈልጌ ነበር ሆኖም ተመሳሳይ ትችት ባይጋ ፎረም ስለቀረበ ሃሳቡን ለመውሰድ የሚከተለው ተመልክቱት። ሆኖም እኔም እላይ ከተሰነዘረው አስተያየት ትንሽ ልጨምርበት።ስብሐት ነጋ በቪ ኢ ኤ ትግርኛ ቃለ መጠይቁ “ይህ በድያለሁ የምትለው ነገር ወይንም የምትጸጸትበት ነገር ካለ ግለጽልኝ” ብሎ ጋዜጠኛው ሲጠይቀው “የሚጸጽተኝ ነገር የለም። ሁለት ነገሮች አሁንም ይጸጽቱኛል።  ሌሎችን ሳላማክር ያደረግኩት ከእስር ቤት ፈትቼ ማሰናበት ውሳኔ ጸጽቶኛል ብሏል። ጓደኛየ ኪዳነማርያም ፀጋይን ስላልገደለው ነው ጸጸተኝ የሚለው። ስብሓት ደም የጠማው በጣም አረመኔ እንደሆነ ብዙዎቹ ይናገራሉ። የጸጸተኝም አንድ ሁለት እስረኞችን ፈትቼ መልቀቄን እስካሁን ይጸጽተኛል።” ብሎ ያለውን አብሮ አደጌ እንደ ወንድማማቾች አሁንም የምንተሳሰብ እና የምንዋደድ ከጽዮን ቤተክርስትያን ጓሮ ባሉ መኖሪያ ቤቶቻችን አብረን አድገን አብረን የተማርነው ውድ ጓደኛዬ ዛሬ ካናዳ የሚኖር አክሱማዊው ኪዳነማርያም ፀጋይ (ሽሻይ) ደም ከጠማው ስብሐት እጅ ከሞት ማምለጡ  ብዙዎቹ ያውቃሉ።

ኪዳነማርያም ማስተርስ ዲግሪ ያለው ብርቱ የቀለም ሰው ሆኖ ያደገ፤ጐበዞች ተብለን ከተመደብን ክፍል ውስጥ አብረን የተማርን ነን። የከተማ አደራጅ ሆኖ ቆይቶ ወደ በረሃ ሄዶ ወያኔን ተቀላቅሎ በበሰለው ተከራካሪ አንደበቱ የስብሓት አሽከር ካድሬዎች እና ስብሐትንም ገጥሞ በፖለቲካ በፍልስፍና ክርክር ስለናቀው በዚህ ተቆጭቶ እስር ቤት አንዲበሰብስ ካደረገ በኋላ፤ የድርጅቱ ፖለቲካ የሚከተል አይደለም፤ ስለዚህም አደገኛ ክርክሩ ብዙ ታጋይ ሊበክል ስለሚችል በሰላም ተሰናብቶ በ24 ሰዓት ከድርጅቱ አንዲሰናበት፡ በማለት ስብሓት የወሰነበት ታጋይ ነው።

ውጭ አገር ለመሄድ ቢፈልግም 24 ሰዓት አልፎበት እነሱ ከሚቆጣጠሩት ነፃ መሬት ከተገኘ አንደሚረሸን ስለወሰኑበት፤ የነበረው አማራጭ ወደ ደርግ መግባት ነበር። ሳይወድ በግድ በሰብሓት ተጽዕኖ ወደ ደርግ እጁን ሰጠ። አክሱም አካባቢ ሲደርስ መንገድ ላይ አስቸኳይ ትዕዛዝ ተላልፎ ወደ ከተማ ከመግባቱ በፊት ታድኖ ተይዞ ወደ ጫካ እንዲመለስ በየ ብርጌዱ እና ተዋጊ ክፍሎች ተላልፎ፤ አምላክ ውጣ ሲለው ኪዳነ ማርያም ከመታደኑ በፊት አክሱም ከተማ እጁን ለደርግ ሰጠ።  ከዚያ በኋላ የነበረው ምርጫ የሚያውቀውን መናዘዝ ነው። ያም አድርጎ ደርግም ስቃዩን አሳይቶት፤ ማርያም ከደርግም ከወያኔም ግድያ ተከላክላለት አሁን ካናዳ ከቤተሰቦቹ ጋር በሰላም ይኖራል። ስብሓት ፀፀተኝ የሚለው ሰውን ባለመግደሉ የመጸጸቱ ኑዛዜው ይህ ነው። ኪዳነ ማርያም ወደ ደርግ አንዲገባ የገፋፋው ስብሐት ነው።

 ስብሐት በርሙዳ ተብሎ በሚጠራው የሀዘሞ እስር ቤት እየቀጠቀጠ የረሸናቸው እና ከእስር ቤቱ አምልጠው ያለ ዳኛ ሞት ከሚፈርድብህ ስብሐት ነጋ እጅ ከከሞት አምልጠው እዚሁ አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ እኔ የማውቃቸው የትግራይ ልጆች አሉ። ሌሎች ንጹሃንን እየደበደበ አንደረሸናቸው ኪዳነማርያምን ባለመግደሌ ይጸጽተኛል ብሎ የሚናገር ሰው  ህሊናው የተቃወሰበት መሆኑን ሚያሳይ ነው። ስብሓት በሕንፍሽፍሹ ጊዜ ስንት ታጋይ ተገደለ ተብሎ ሲጠየቅ 2 ሰው ብቻ ብሎ ሲል፤ ይህ ሰው “ውሸታም” ብቻ ሳይሆን፤ አንግሊዞች “ኮልድ ብላድድ መርደረር” የሚሉት አስፈሪ “ነብሰ ገዳይ” አረመኔ/ሞንስተር አንደሆነ ነው ውሸታም ባሕሪው እየገለጸልን ያለው። ስለ ውድ ጓደኛዬ ኪዳነ ማርያም ፀጋይ የምለው ለጊዜው ይኼ ነው። ስብሓት ሰንት ሰው አንደገደልክ አምላክ አንደ መለስ ዜናዊ ጎትቶ ወደ ሲኦል ከሚወስድህ በፊት ኑዛዜህን ለሕዝብ ብትናገር አምላክ ማሃሪ ነው እና ይቅርታ ይደረግልሃል። የቀረህ ዕድሜ በጣም በጣት የሚቆጠር ጊዜ ነው የሚቀርህ፤ ሰራቄ ሞት ከሰማዩ ጌታ ተልኮ ወደ አንተ እየመጣ በጉዞ ላይ ይገኛል። ሞት ላይቀር ታሪክ ስሩ ፡ ታሪክ የምትሰሩት ደግሞ በኑዛዜ ነው። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትየጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) getachre@aol.com (Ethiopian Semay)