Monday, July 1, 2024

የጎጃሙ ፋኖ ቃል አቀባይ ድንቁርና እና እንደገና በተፈናቃዮች መልሶ የማቋቋም ስም የትግሬ “የሌቤንስራም ሕዳሴ” መርሃ-ግበር የማገርሸቱ ክስተት ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 7/1/24

 

የጎጃሙ ፋኖ ቃል አቀባይ ድንቁርና እና እንደገና በተፈናቃዮች መልሶ የማቋቋም ስም የትግሬ “የሌቤንስራም ሕዳሴ”  መርሃ-ግበር የማገርሸቱ ክስተት

ጌታቸው ረዳ 

Ethiopian Semay 

7/1/24

ፎቶው ላይ የምታዩት ወያኔ ወልቃይትን እንደያዘ አማራዎችን ከአለት ድንጋያማ ዋሻ ውስጥ አጣብቆ በመቀርቀር መፈናፈኛ በማሳጣት ይገርፋቸው እንደነበር የሚያሳይ ነው፡፡ ምንጭ Reflections on the Slave Dungeons of Ghana and the Death Camps of Welkait By Jemal Countess

ያንብቡ፡፡

 መጀመሪያ ኢትዮፕያን ሰማይ ድረገጽ የምታነቡ አንባቢዎች በዚህ ወር ከጠበቅኩት በታች ወደ 15970 ባቢ ብቻ አይቻለሁ፡፡ ነቃ ፤ ነቃ ብላችሁ አንብቡ፡፡ ከዚያ ወር በፊት ባንድ ቀን ብቻ 17 ሺ አንባቢ ነበር ፤ ስለዚህ (ሰው ሁሉ ድካም ወደ ማይጠይቀው ዩ ቱብ ሱስ አድረጎ ይዞታልና ፤ማንበብንም ልመዱት፡ እያልኩ ወደ ርእሴ ልገባ፡፡  

ሰለ ፋኖዎች አለመገባባት የምሰማው ሁሉ ላለማባባስ ትችት ከምሰጠት ተቆጠቤአለሁ፡ ከተገቢው በላይ ፈር እየለቀቀ ከቀጠለ ግን መተቸቴ አይቀርም፡፡ ይህ የዛሬው ግን መታለፍ የሌለበት ስለሆነ እርምት እንዲደረግበት እንደ ምክር እለግሳለሁ፡፡ የሃሳብ ገበታ ዋና አዘጋጅ መጎስ ተሾመ ትናንት በፕሮግራሙ ስለ የትግራይ ተፈናቃዮች እንዲሁም ሰለ የጎጃም ፋኖ ቃል አቀባይ ስሙ “ማርሸት” (ይመስለኛል ከተሳሳተኩ አርሙኝ) አስመልክቶ ያቀረበው ትችት ተስማመቶኛል፡፡ ከወያኔ ጋር እንዲሀ ያለ የፖለቲካ የዋህነት ባይገባና ወያኔ ያንን ቅን ምሰጋና ለቀጣይ “ጠብ ጫሪነቱ ባሕሪ” ለመጠቀም “እኔ እኮ ታግሸ ነበርኩኝ ሸፋን” እንዳይጠቀምበት እንዲህ ያለ የዋህነት ከወያኔ ጋር መለዋወጥ አያሰፈለግም፡፤

 መጎስ የተቸበት ቃል በቃል ባልጠቅስም “ፋኖ ማርሸት” <<ወያ ጦርነት እንዲከፍት ቢገፉትም በኛ ላይ ጦርነት ባለመክፈቱ ‘’እናመሰናለን’’ ብሎ የፋኖ ቃል አቀባዩ ወያኔን ማመስገኑ ልዙብ አነጋገር ቢሆንም በፖለቲካ ዓይን ግን የወያ ባሕሪ ያለማወቅ ነው>> ሲል መጎስ  ተክክለኛ ትኩረቱን አሰቀምጧል፡፡

ስለ ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው መልሶ መመለስ ተገቢ ቢሆንም እየተከሄደ ያለው መልሶ ማቋቋም አካሄድ ግን አንድ ወገን ብቻ ያሚቆጣጠረው ዓለም አቀፍ ታዛቢና ያገባናል ባዮች ሁሉ ያልጨመረ ስለሆነ ችግር አለበት ሲል ተክክለኛ አመለካከቱ አጋርቶናል፡፡

አዎ፤ ተፈናቃዮቸ ወደ ቦታቸውና ወደየ መኖሪያ ቤቶቻቸው የመመለሱ ሂደት ተገቢ ቢሆንም መጎሰ እንዳለው ተመላሾቹ በወል ከመፈናቀሉ ጋር የተያያዘ ተፈናቃዮች ናቸውና “ወያኔን ማመን ቀበሮ ነውና የወያኔ ተንኮልም ታሳቢ ተደርጎ ተመላሾቹ እነማን መሆናቸው መጻኢ ችግር ለመቀነስ እንዲያመች ከሚመለከታቸው ያገባኛል ከሚሉ ከሁሉም ወገኖች የተውጣጣ ኮሚቲ ሳይጠና ተፈናቃዮችን መመለስ ተጀምሯል፡፡ የአረጋ፤ የብርሃኑ ጁላ (አበይ) እና ወያነ ቡድን ኮሚቲ “ያንድ ሳንቲም ሁለት ምስል ስለሆኑ ሌሎችን መጨመር ሰላምዊ ፍትሕ ያመጣልና ያንን እሳቢ ያላደረገ ስለሆን ሰበብ አለው፡፡ (ልክ ሌሎች ያገለለው የፕሪቶሪያው ቡደን ስምምነት እዚህም ላይ አሁንም ከዚያ ሰሕተት ሳይማሩ ድግመውታል!!!) የመልሶ ማቋቋሙ ሂደት የግብር ይውጣ ፤ የሴራ ባሕሪ አለበት፡፡

ከሁሉም ወገን ፤ከዚያ አካባቢ የሚኖሩ አማራዎችና መሰል ሯሪዎች ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ሳይዋቀርበት ብርሃኑ ጁላና የወያነው ታደሰ ወረደ (ወዲ ወረደ) መሪነት (ማሰረጃው ሰላለኝ ነው) መካከል “ሆድ ምላሽ” (all you can eat ) እና ዊሰኪ እየተጎነጩ አዲስ አበባ ከተማ ባደረጉት ስምምነት መሰረት፡

<<በነበራቸሁበት ገብታቸሁ የፈለጋቸሁትን ተፈናቃይም አዲስ ሰፋሪም አስፈሩበትና የወያኔ ካድሬዎች፤ ዳኞች፤ ፖሊሶችና ሚሊሺያዎችና ነበሰ ገዳዮች  አማራውንም ረግጠው ፤ ያስተዳደሩት” በሚል የተደረገው እከከኝ ልከክልህ ሰምምነት “ወያነ ካሰራጨው ጽሑፍና የተፈናቃዮች አስተባባሪና “የሃገረ ትግራይ” ‘ማአከላዊ ኮሚቲ አባል’ ከሆነው ሰው ካደመጥኩት የትግርኛ ቃለ መጠይቁ መረጃ መሰረት ስመለከት ፤  ምስኪኑ የጎጃም ፋኖ ቃል  አቀባዩ ደግሞ ይህንን ሳያገናዝብ “ወያኔ በፋኖ ላይ (አማራ ላይ) ጦርነት ባለመክፈቱ” ቢያመሰግንም ፤ የኸው ተፈናቃዮቹ ጋር አብሮ እንዲገባና አካባቢው እንዲቆጣጠር የተፈቀደለት የትግራይ ታጣቂ እንደ ካሁን በፊት አማራ ሰዎች ላይ የዘር ማጽዳት እንደማይፈጽምና የአብይ አሕመድ አጋዥ ሆኖ ፋኖን እንደማይወጋ ምን ማረጋገጫ አለው?

ገበናቸው ሳይጣራ ፤ ፍርድ ሳያዩ፤ ቦታዎቹን ጠንቀቀው የሚያውቁ፤ በጦረነቱ ላይ የተሳተፉ ነበሰ ገዳዮቸ የነበሩ፤ ልዩ የኮማንዶ ሥልጠና የወሰዱ ልዩ ሃይሎችና ፓሊሶች በዳኞቻቸው እየታገዙ “አማራ ነን የሚሉትን የየአካባቢው ሯሪዎች “ትግሬ  ነኝ ካላሉ እንደ ወትረው”  የዘር ማጽዳት እንደማይፈጽሙባቸው ማንም ሰው ማረጋገጫ ሊሰጠን አይችልም፡፡ አማርኛ የሚያስተምሩ በአማርኛ የሚቀድሱና የሚሰብኩ የሃየማኖት መሪዎች እንደ ትግራይ በትግርኛ ስበኩ ፤ በትግርኛ አሰተምሩ የማይባሉበት ማረጋገጫ ሊሰጡን አይችሉም፡፡ማረጋገጫ አላችሁ? የለም!!!!!!

የልብ ልብ ሰለተሰጣቸው (የፕሪቶሪያ ስምምነት የሚጥስ አመጽን የሚኮንን ዓንቀጽ 1 የሚጻረር አላማጣ ከተማ ገብተው ያለ ምንም ተጠያቂነት የአማራ ተወላጅ መረሸናቸውን  አስታወሱ)፡፡ የትግሬ ታጣቂዎች  ሰሞኑን በመቶዎች የሚቆጠሩ አብቶብሶች ተጭነው በሺዎቹ ከሚቆጠሩት ተመላሾች ጋር አብረው የትግራይ መከላከያ (እነሱ ለሽፋን “ሚሊሺያ” ይሉታል) እና (አገራዊ መከላከያ ስንለው የነበረው የአበይ አሕመድ ታዛዥ አገልጋይ የሆነው “መከላከያ”) በጋራ ከነ ትጥቃቸው በብርሃኑ ጁላና አብይ አሕመድ ፈቃጅነት በራያ በፀለምትና በማይፀብሪ ከተፈናቃዮች ጋር ግቡ ተብለው እንዲገቡ ተደረገዋል፡፡

ታዲያ “ፋኖ ማርሸትም” ሆነ በመንግሥታችን ሙሉ እምነት አለኝ፤ አብረን እየሰራን ነን ሲል የነበረው “አሳመነው ጽጌን “ከሃዲ” እያለ ሲዘለፈው የነበረው የአብይና የአገኘሁ ተሻገር “አቃጣሪው” ኮ/ል ደመቀ መኮንን አሁንስ <<ወያነ ታጥቆ በክልላችሁ ሰተት በሎ ተፈቀዶለት ገብቷልና>> አሁንስ ምን ትሉ ይሆን?  ሕዝባቸሁን እንደጥንቱ ትግርኛ ተናገር እያሉ ህጻናት ለጆቻችሁን የሚያስጨንቁ የወያነ ታጣቂዎችና አሰተዳዳሪዎች አፈሙዝ ወድረው መጥተውላችሃልና “እናመሰገናለን እያላቸሁ ፡ተቀበሉዋቸው”፡፡

በፕሪቶሪያው Article 6 የተመለከተ ስምምነት በመጣስ ሁለቱ አብይ አሕመድና ወያ ተሰማመተው የትግራይ ታጣቂዎች አጨቃጫቂ በሚባሉ ቦታዎችን ታጠቀው ድጋሚ እንዲቆጣጠሩት አድረገዋል፡፡

አንቅጽ 6 እንዲህ ይላል፦

·         Agree to finalize the overall disarmament of the TPLF combatants, including light weapons within 30 days from the signing of this Agreement;

·         ይህ ስምምነት ከተፈረመ 30 ቀናት ውስጥ የህወሓት ታጋዮችን ቀላል መሳሪያን ጨምሮ አጠቃላይ ትጥቅ የማስፈታቱን ሂደት ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል።ይላል፡፡

 

አሁን በተግባር ላይ ያለው ግን  ትጥቅ ማሰፈታትስ ይቅርና አላማጣ ውስጥ ሰው መግደል ጀምረዋል፡፡ ሑሞራ ይዘውታል፤ ማይፀበሪና ፀለምቲ ገበተዋል፡፡ ወልቃይት ገብተው ምን እንደሚያደርጉ እየጠበቅን ነው፡፡ የመጨረሻ ግባቸው <<ወልቃይትና ራስ ዳሸን እንዲሁም መተማ” ነው፡፡ ሃገረ ትግራይ ቆይቶም ምፅዋና ዓሰብን ካርታ ያጠቃለለቺው የሃገረ ትግራይ ግብ በዝግታ ይቀጥላል፡፡ አንዱ የትግራይ በሔረተኛ እንዳለው “ዛሬ በዚህ ሰዓት የትምክሕት ሃየሉ ወራሪያችን  አማራ ጸለምቲና አላማጣን ትቶ እንደ ጥንቸል ፍርጥጦ ወደ ጎንደር መሮጥ ጀምሯልነገ መተማ ፤ ክዚያም ማሳዋ/ምፅዋ/” ሲል መስመር የሚሉትን የሃገረ ትግራይ የመጨራሻ ግብ ነገሮናል፡፡

አከሱም መስራችና ባላደራ ፤ የሁሉም ፈጣሪ “አወራ ዘር” ነኝ የሚለው <<ሃገረ ትግራይን><  ለመመስረት  ትግራይን  አከሱማዊ ክብሯ፣  ኩራቷ እና ታላቅነቷ ለመመለስ የታቀደው ዓላማ እንደገና በማደስ የታጠቀውን ጠመንጃ ሳይፈታ ሕዝባዊ ንቅናቄና የቦታ መሰፋፋት “ሌቤንስራም ሕዳሴ ውስጥ ገብተዋል።

እየተመለከትናቸው ያሉት <<የትግራይ አብዮታዊ ጥሪ>> የሚያሳየው ከታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት ለመውጣት አሁንም  <<የትግራዊ ብሔርተኝነት>>  መመሪያ (መስመር/መርህ) የሆነው “ የሃገረ ትግራይ ምስረታ” ለማረጋገጥ ቁልፍ  መንገድ “ለም መትና ወደ ሱዳን “በር መውጫ” የሚጠቀምበት በጉልበትም ሆነ በምንም መያዝ ነው፡፡  

እነኚህን ቦታዎቸ መቆጣጠር ማለት ጆግራፊያዊ ስበት  (እስትራተጂክ) እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ  እና ፖለቲካዊ ስኬት ሰላለው ወያኔም ስልጣኑን አስጠብቆ ለመቆየት (ልክ እንደ ኢሳያስ ባድመ በመያዙ በድጋሚ  ግዛን የሚለው ከኤርትራኖች ጭብጨባ እንዳስገኘለት ሁሉ) ወያኔም ቀጣይነት ያለው የቦታ መሰፋፋት  ጀርመኖች ሌቤንስራም የሉታል፤ ትግርዎች ደግሞ “መረበትና” ይሉታል (ጥንታዊ የበቀልንበት ይዞታ ማለት ነው) መርሃግብር የሚያበረታታ የፕሮፓጋንዳ ስርጭት በሁሉም የባህል እና የመረጃ መገናኛ ዘዴዎች እያሰራጨ ይገኛል

አነኚህ ቦታዎቸ ሕጋዊ ባልሆነ መልኩ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ የኢትዮጵያ መጣኔ ሃብት በመበዝበዝ ላይ ያለቺው <<ዲፋክቶ እስተት ኦፍ ትግራይ>>  ያስታጠቀቻቸው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የማያውለበልቡ እንደወራሪ የባእድ ሃይል የራሳቸው <<የሃገረ ትግራይ>> ባንዴራ የያዙ ዳኞች ፤ ፖሊሶች፤ ታጣቂዎችና አስተዳዳሪዎች ገበተው ኢትዮጵያዊ የሆነን ቦታ ሁሉ እንዲይዙት ሰለተፈቀደላቸው “በናንተ ሥር አንገዛም” ስንደቃላማችሁንም አናውለበልብም የሚል አማራ ሲገኝ ከፕሮፓጋንዳው ማሽኑ ስር ያለው የሽብር መሳሪያ ሲሆን በሁሉም ቦታ የሚገኙ ሚስጥራዊ ፖሊሶችና ሰላዮቻቸው በማሰራጨት ለ27 አመት ራያና ወልቃይት በሽብር እንደአሰተዳደሩት ሁሉ ዛሬም የማጎሪያ ካምፖችና ማሰቃያ እስር ቤቶች  በማዘጋጀት ድጋሚ የዘር ፍጅት እንደማይፍጽሙ ማረጋገጫ የለም

 ይህ ከመከሰቱ በፊት ወልቃይት ስይዙ ወዲያው ባይሆንም ዝግ ብሎ ከፍተኛ ውግያ ይኖራል፡፡ ፍልሚያው ሕዝብን ይጨምራል፡፡ ካሁን በፊት እንደገለጽኩት እነ “ወዲ ወረደ” አብይ አሕመድ ጋር ተመሳጥረው እሰከ ባሕረዳርና ወሎ ድረስ በመዘለቅ የማያባራ ውግያ የከፍታሉ (ይህንንም የፕሪቶረያ ሰምምነት ከተደረገ በማግስቱ ሁሉም ሲጨፍር የጻፍኩትን አሰታወሱ፡፡ አሁን ምልክቱ እየታየ ነው፡፡)

ሌቤንስራም አዲሰ የመኖሪያ ቦታመፍጠር የናዚ ጀርመኖችና የጣሊያን ፋሺስቶች ቅጅ ቢሆንም የትግራይ መሁርንና ድርጅታቸው “ሃገረ ትግራይ” ለመፍጠር የሚያስችላቸው የቆየ ግባቸው ስለሆነ ቢሞቱም ይህንን ዓላማቸው አይተውትምና ፤ ራያና ውለቃይት የማነ ነው? ለሚለው ጠያቄ መልሱ የምናገኘው ዛሬ በባንዳነት ተሰልፎ ስለ “ሃገረ ትግራይ” መመስረት እያሳከከው የሚፎክር “ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት” እያለ ያለ መሰልቸት የሚመኝ የራያ ተወላጁ የኢትዮ-ሚድያ ዋና አዘጋጅ የነበረው ፤ ያኔ በደጉ ጊዜ “አብርሃ በላይ” የነገረንን መልስ እንመልከትና በዚሁ ልሰናበታቸሁ፡፡

ወልቃይትም የወልቃይት ነው፣ (2008)

ራያም የራያዎች ነው!

አብርሃ በላይ

የኢትዮሚዲያ ድህረ ገፅ መስራችና ኤዲተር-

እኔ የምለው ኢትዮጵያውያንን በዘር ከፋፍሎ ማዳከም የጠላት (ህወሃት) ፖሊሲ ነው። ወያኔ ወልቃይትን ወደ ትግራይ ሲያካልል፣ የትግራይ ህዝብ ወልቃይትን ስጡኝኮ አላለም። ማናባቱ አዘዘው? ግን እንዳልኩት፣ የጠላት መሰሪ አላማው ገና ከጥንት ከጥዋቱ አንድ ሆኖ የኖረውን የጎንደር እና የትግራይ ህዝብን በይገባኛል ጥያቄ በማያባራ ግጭት ከቶ ሲያናቁር ለመኖር ነው።

የትግራይ ህዝብ መብት ቢኖርውማ የሚጠይቀው ነገር ቢኖር የነ አሉላ አባነጋ ያከበሩትን የቀይ-ባህር ዳርቻችንን ከወደባችን አሰብ ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ የሚል ይሆን ነበር። ጠላት ግን ቀይ-ባህር ቀርቶ አሰብ ወደብ ይገባናል ስንል ስንቱን በሰይፍ እንዳስተናገደ ያደባባይ ሚስጥር ነው።

በኔ አስተያየት መፍትሄውሁሉም ቦታዎች ወያኔ ስልጣን ከመያዙ በፊት ወደ ነበሩበት አስተዳደር መመለስ አለባቸው። ስለዚህ ወልቃይትም ወደ ነበረበት ወደ ጎንደር አስተዳደር ይመለሳል። አስተውሉወልቃይት ለሱዳን ወይም ለኤርትራ ይሰጥ እያልኩኝ አይደለም ያለሁት። እሱ የባንዳ ሥራ ነው።

ራያስ ቢሆን?

ሰፊና ለም መሬት ላይ የኖረው የራያ ህዝብ የራሱ የሆነ ታሪክ፣ ወግና ማዕረግ ያለው ህዝብ ነው። ራያ ኢትዮጵያዊነቱን ለድርድር የማያቀርብ፣ አገራችን ከጠላት ለመታደግ በተደረጉ ጦርነቶች ሁሉ አኩሪ የተጋድሎ ታሪክ ያስመዘገበ ህዝብ ነው። ይህ ህዝብ ችግር ላይ የወደቀው ወንበዴው ስልጣን ከያዘ በኋላ ነው።

አይበገሬ የራያ ህዝብን በቁጥጥር ስር ለማድረግ ስልጣን ላይ የኖረው የጠላት ቡዳን መጠነ-ሰፊ የሆነ ወንጀል በህዝቡ ላይ ፈጽሟል። አንቱታን ያተረፉ የአገር ሽማግሌዎች ሳይቀሩ በተራ የወንበዴ ዞምቢዎች በጠራራ ጸሃይ እየተገመገሙ ( እየተዋረዱ) የአ እምሮ በሽተኞች ሁነው ቀርተዋል።

የራያ ህዝብ የማያውቀውን ቋንቋ ጭኖበታል። በብሄራዊ ቋንቋችን በአማርኛ ሲማር የነበረውን ወጣት ትውልድ በአንድ ጀምበር በአካባቢው በማይነገር ትግርኛ እንዲማር አስገድዶታል። 27 አመት ቢያልፍም፣ ወጣቱ ግን ጊዜ እየጠበቀ ነው፣ የራሱን ቋንቋ ለማስመለስ።

ራያ እንደ ወልቃይት ህዝብ ብዙ ብዙ ስቃይ የተሸከመ ህዝብ ነው። ለም መሬቱን ካድሬዎቹ ስለሚፈልጉት፣ ቤት መስራት አቅሙ ከሌሎችሁ ልቀቁ እያሉ በከተማ ልማት ስም የራያን ህዝብ ለስደት እና ለድህነት ዳርገውት ይኖራሉ። እንደኔ አመለካከት፣ የራያ ህዝብ የራሱ የሆነ ልዩ መስተዳደር ተፈጥሮለት፣ ህዝቡ በመረጠው ቋንቋ እየተዳደረ ቢኖር እመርጣለሁ። ወጣቱ ወንድሜ / ተበጀ እንዳለው፣የራያ ህዝብ ዝቅ ቢል ራያ፣ ከፍ ቢል ኢትዮጵያዊነትንእንጂ በሌላ ልትፈርጀው የማይገባ ፍቅር የሆነ ህዝብ ነው።

ወደ አሜሪካ ከመምጣቴ በፊት፣ ቤተሰቦቼን ራያ ውስጥ ተሰናብቼ ስሄድ፣ መኾኒ እና ኮረም ላይ የራያ ልጅ ጋዜጠኛ መሆኔን አውቀው፣ በሰልፍ ሚስጥራቸውን አካፍለውኛል። ራያዎች እንዲህ ብለው ነበር ያጠቃለሉት፤እድሜ ልካችን ደርግን ስንዋጋ አሳለፍነው፣ በስተእርጅናችን ግን ወያኔ የሚሉት ክፉ ጠላት ደረሰብን!”ልብ የሚነካ አባባል።

ለራሴም ቃል-ኪዳን ገባሁኝ። እስከመጨረሻው ድረስ በመለስ ዜናዊ የሚመራውን የጠላት ቡድን አቅሜ እስከፈቀደልኝ ድረስ ተዋግቶ ለመጣል።

መጨረሻው ደግሞ እግዚአብሄር ያሳየን!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ሞት ለባንዳዎች!

በሎ ነበረ አበረሃ በላይ  የዛሬ አያድርገውና ፤ያሬ በደጉ ሕሊና!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ