የትግራይ ሕዝብ ዕብሪት በወያኔ ባንዴራ እያጌጠ ሃገራዊ ሰንደቅአላማችንን ላለማክበር ቃል ገብቶ አሁንም በዛው ዕብሪት ለሌላ ውድመት እየተጓዘ ነው
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian
Semay
February, 19,
2023
የቱርኩ ፈላስፋና የኪነት ባለሞያው ኢልዳን እንዲህ ይላል፤
“Wherever there is an ignorant mass, you will see a flag of an ignorant leader fluctuating with glory!” “መሃይም ህዝብ ባለበት ቦታ ሁሉ የመሃይም መሪ ባንዲራ በክብር ሲዋዥቅ ታያለህ!”ይላል። ይህ እውነታ በኦሮሞ ሕዝብና በትግራይ ህዝብ እያየን ነው።
አውነት ነው። የትግራይ ሕዝብ ዛሬም ከዚያ ሁሉ ውድመትና ውርደት ሳይማር የፋሺቶች ፖለቲካ ከማንገብና ከመንከባከብ አልወጣም። ዛሬ በ48ኛው የየካቲት 11 ቀን የነብሰገዳዮችና አገር አፍራሾች በዓል በዕብሪትና በኩራት እያከበረው ነው። ካሁን በፊት በዓላቸውን ሲያከብሩ ሥልጣን ላይ ስለነበሩ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ሲያውለበልቡና ሲያከብሩ አይተናቸዋል።
ከ3 አመት በፊት ግን በዛው በየካቲት 11 ቀን ወደ መገንጠል ሲያዘነብሉ ወልቃይት በቁጥጥራቸው ሥር ስለነበረች ካሁን በፊት በዚህ ድረገጽና ፌስቡክ እንደገለጽኩት የከሰላን የሱዳን የባሕር ወደብ “ከትግራይ ሪፑብልክ” ምሰረታ በሗላ ለመጠቀም እንዲያመቻቸው የሱዳን ከሰላ ዋና አስተዳዳሪ የነበረው ጀኔራል መሐመድ ረቢኪያ እና የገዳሪፍ ድምበር አስተዳዳሪዎች ወደ መቀሌ ተጋብዘው ከሱዳኖቹ ለወያኔዎቹ የተበረከተላቸው የአዙዋችሁ “ተገንጠሉ” ማበረታቻ ለወያኔ ባለሥልጣናት ፤ማሕበራትና ለፖሊስ ወታደራዊ ድርጅቶች ሽልማት ሲሸልሙዋቸው እንደነበር ይታወሳል።
ያ ወቅት ወቅት፤ (እንደ ዛሬ 1,000,000 ሕዝብና መጠኑ ያልተገመተ ንብረት ከጠፋ በሓላ ለክቡር ጠ.ሚ ዶ/ር አብይ አሕመድ የላቀ ልዩ ምስጋና አቅርቡልኝ የሚልበት ወቅት ሳይሆን) ደብረጽዮን ለትግራይ ምክር ቤት አባሎች “የመገንጠል አዋጅ አውጁ” ብሎ በተናገረበት ወቅትና የታጠቅናቸው መሳሪያዎች አንዲትም ሳትቀር በጠላቶቻጭን ጀርባ ላይ እንረጫቸዋለን እያለ በዕብሪት ሲደነፋ በነበረበት ወቅት ነው።
ዛሬ ደግሞ የተከበረው የ48ኛው አመት የየካቲት 11 ቀን የሽፍቶች በዓልን በሚገርም አነጋገር “ትንሳኤ ትግራይ ነው” እያሉ የፋሺሰቶቹን ባንዴራ አንግተው ሲጨፍሩ በዚህ ቪዲዮና በሌሎቹ ማህደሮች ላይ እንደምታዩዋቸው አንዲትም ኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አንዳይውለበለብ ተደርጎ << ኢትዮጵያና ሰንደቃላማዋ የጠላት ባንዴራ ናት ተብላ>> ይኼው ዕብሪታቸው ዛሬም በግልጽ ቀጥለውበታል።
የኔ ጥያቄ ግን “ኢትዮጵያ አገሬ አይደለቺም ፤ ሰንደቃላማየ የወያኔ እንጂ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አላውቅም፤አላከብርም” ፡ የሚል ሕዝብ እስከመቸ ነው የኢትዮጵያን ሸቀጣሸቀጥ፤ምግብ፤ ባንክ፤ መብራት፤ ቴሌኮሚዩኒኬሽን፤ መጓጓዣና እንክብካቤ እየተደረገለት እንዲህ እየጨፈረ፤ በአገር ሉኣለዊነት እያሾፈየሚቀጥለው?
ይህ የ48 አመት ዕብሪታቸው አሁንም ህያው ነው። እየቀጠለ አገር ለማፍረስ በግልጽ እየዛቱና ሰንደቃላማቸውንም እያውለበለቡ ለመጪዋ ትግራይ እንታገል እያሉ ሲያስተጋቡ እንዴት ነው ለዕብረታቸው ደርት የማይደረግለት መንግሥት ያጣነው? በነሱ ምክንያት አገራችን ለቀቅን፡ ሕዝባችን ከውድመት ወደ ውድመት አሸጋግረዋታል። መንግሥት የለም ፤ ይህንን አውቃለሁ። ያለው መንግሥት አብይ ነው፤የነሱ ተጋሪ ወንጀለኛ ነው። አብይ ትግራይ እንድትገነጠል ይፈልጋል; አንቀጽ 39 የተባለውም አከብራለሁ ብሎ በግልጽ ተናግሯል። ፓርላማ ውስጥም ተገንጣይ ኦነጎችና መሪዎቻቸው ገብተውበታል። ምኒሰቴርም ሆነው ተሹመዋል። ወያኔም ነገ ፓርላማ ገብቶ የመገንጠሉ ጥያቄ ህጋዊ ሊያደርገው በመስራት ላይ ነው። ፓርላማው የተሞላው በተገንጣይና በአገር አፍራሽ ብኩን ሆዳም ነው የተሞላው።
ጉዳዩ ጊዜ እየጠበቀለት እንጂ አገር ከመመስረት ኢትዮጵያን ከማፍረስ የወያኔ መሪዎችም ሆኑ የትግራይ ሕዝብ ፍላጎትና ስምምነት መኖሩን ከሚጨፍሩተና ከሚያሳዩት ዕብሪት ማየት እንችላለን። የኔ ጥያቄ ግን አገር የማያከብር፤ ሃገራዊ ሰንደቃላማ “የጠላት ነች” ብሎ የሚመለከት ማሕበረሰብ ለምንድ ነው አሁንም ጠላት ከሚባለው ሕዝብና አገር ያለምንም ገደብ በጭነት እየተጫነ የምጣኔ አቅርቦት የባንክና የመብራት የምግብ አቅርቦት እየጎረፈለት ያለው? ለምን? ትግሬዎች ኢትዮጵያዊነታቸው በግልጽ እንደለቀቁት እያሳዩን ነው። ታዲያ ይህ የኔ ብቸኛ የተቃውሞ ድምጽ ሌሎቻችሁ እንዴት ታዩታላችሁ?
እስኪ ይሄ “ጀነሳይድ ምናም የሚል ንትርክና “ወገኖቻችን ናቸው” የሚሉን የዋህና ተመጻዳቂ ተፈላሳፊ ፖለቲከኞች “ዠዋዠዌ” ወደ ጎን ተወት አድርጋችሁ በድፍረትና ከነባራዊው እውነታ ተጋፍጣችሁ እስኪ ይህንን የኔን ድምጽ አስተጋቡና እንነጋገርበት?
እውነት ግን ኢያስ አፈወርቂ “እነዚህ ሰዎች ምን አያደረጉ እንደሆነ አያውቁም” ብሎ ሲላቸው እውነታ ያለው አይመስላችሁም?
ህዝቢ ከተማ ውቕሮን ወረዳ ክልተ ኣውላዕሎን ተረኽቡ ዘሎ ኣፋፉኖት ሰላም ብምዕቃብ ንዳግመ ህንፀት ትግራይ ከምዝሰርሕ
ኣፍሊጡ፡፡