Thursday, April 17, 2008

“TPLF”, the Hostage of Meles Zenawi


መለስ
ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ ሲገለባበጥ
ሀወሐትም አብሮ ይገለባበጣል!


ይህ ወያነ ትግራይ በሚል መጠርያ የተሰየመ የግለሰዎችና ለኤርትራኖች ዓላማ መገለገያ ሆኖ የቀረዉ የብዙ ሺህ የትግራይ ተወላጆች ሕይወት የበላ ድርጅት ሲመሰረት በጣት በሚቆጠሩ ተራማጅ ተብለዉ በወቀቱ የሚታዩ ተማሪዎች እነደነበር ይታወቃል። ከመስረቾቹ አብዛኛዎቹ ከባላበትና ሐብታም ቤተሰብ የተገኙ፤ ስነ ባሕርያቸዉ ሁሉ ጎጠኝነት፡ አዉራጃዊነትና የበላይነት ስሜት ያጠቃቸዉ ሲሆኑ፦በተደጋጋሚ የሚተቹበትና በጠላትነት የፈረጁት “ለሸዋ አማራ” ያሳዩት አጸያፊ የንቀትና የጎጠኛነት ስሜት፤ በተሐህት ታጋዮችም ጭመር በማንጸባረቅ፤ ባዉራጃ የቡድን ስሜት በማጥመድ ታገዩን እየለያዩ ለስልጣናቸዉ አገልጋይ እንዲሆን በማሸበር፤በማስፈራራት አና በመግደል ድርጅቱ ትርምስ ዉስጥ ገበቶ እንደነበር ይታወሳል።

የድርጅቱ ታጋዮች ባላሰቡት ወጥመድ ዉስጥ ገብተዉ በእንደዚያ ዓይነት ወከባ ከተዋከቡ በሗላ፡ በስበሐት ነጋ እና ቡዱኑ መሪነት ያጠመዱት የጎሳ እና የቡድን ፖለቲካ፤ በድርጅቱ ስር ሰዶ እንዲጠናከር ለ10 ዓመት በፈላጭ ቆራጭነት ሲመራ የነበረዉ ስብሐት ነጋ ፤ ድርጅቱ በጠባብ ስሜት አንዲቀጥል ወጣት ጎጠኞችና ለኤርትራ የመገንጠል ዓላማ ሙሉ ድጋፍ የሚሰጡ ወጣቶች ሲያጠና ቆይቶ፤ ተስማሚ ሆኖ ያገኘዉ ጠማማዉና ጮሌዉ መለስ ዜናዊን ከታች በመምዘዝ የሊቀመንበርነቱን ቦታ እንዲይዘዉ አደረገ (በክፍፍሉ ጊዜ የስብሓት ነጋ የትግርኛዉ ቃለ መጠይቆቹን ያድምጡ) ።

ድርጅቱ ለመለስ ከተሰጠ በሗላ የድርጅቱ ባሕሪና የፖለቲካዉ ርዮተ ዓለም በቡድናዊ አሰላለፍ በካፋፍለህ ግዛ አሰራሩ መለስ ስልጣን ከመያዙ በፊት፤ ከዉጭ ሆኖ ሲለግሳቸዉ የነበረዉን አደገኛ የፖሊሲና የፖለቲካ ጽሁፎች ይበልጥኑ መጠናከር ጀመሩ። ድርጅቱ ከዛ ወዲህ የጠበቀ ያምባገነንነትና የክፋት ሥራዎች እየገፋበት በመሄድ የባላባት ስሜትነት የተጠናወተዉ “አቦይ ስብሐት” ለመለስ ዜናዊ ጡት አባትነት ከአረጋዊ በርሀ በመቀማት ከጎን እያስተባበረና እያማከረ “የመለስ ፈላጭ ቆራችነቱን ቦታ ገንኖ” ህወሐት በመለስ እጅ ባለቤትነት ስር እነዲወደቅ ከፍተኛ ሚና ተጫወተ!

መለስ ከመጀመርያዉኑ በትሁትነቱ ረጋ ባለ ባህርይ የታወቀዉ ከአባይ ጸሀየ ጋር ተጠግቶ ማሕበራዊና ዲሲፕሊናዊ የድርጅት አሰራር ከቀሰመ በሗላ መጥቆ ያደገዉ ፖለቲካዊ ብስለቱና ጠማማነቱ ሁሉንም ገለባብጦ ከስሩ እነዲታዘዙት አደረገ (አረጋዊ በርሀ እና የብስራት አማረን ጸሁፎች ይመለከቱ)።ከዚያ ወዲህ ድርጅቱ በመለስ ትእዛዝ አና ባሕሪ መንቀሳቀስ፤ በመለስ ሳመባ ማሰተንፈስና ማሰብ ጀመረ።መለስ ከአንድ ሀሳብ ወደ ሌላ ሀሳብ ሲገለባበጥ ህወሓትም አብሮ ይገለባበጥ ጀመር ።

በህወሐት በመረጃ ክፍል ከፍተኛ ቦታ ተመድቦ ሲታገል የነበረዉ አቶ ብስራት አማረ ካናዳ ዉስጥ ባማርኛ የሚታተመዉ ሐዋርያ ጋዜጣ ላይ <<ከዚህ ያደረሰ መንገድ ሲመረመር!>> በሚል ረዕስ ሰፋ ያለ የእያንዳንዱ መሪ ባሕሪና የፈጸሙት ወንጀል በዘረዘረበት ጊዜ መለስ እና ህወሐት በባህሪም በተግበርም የተያያዙ፤ “ህወሐት ማለት መለስ- መለስ ማለት ህወሐት” መሆናቸዉን አነዲህ ሲል ገልጾት ነበር፦

<< አተኩሮ በጥልቀት ላስተወለ ሰዉ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (TPLF) ፖለቲካዊ ታሪክና ጉዞ ከመለስ ዜናዊ የፖለቲካ ፀባይና ባህርይ ብዙም ተለይቶ አይታይም። የመለስ አመለካከትና እምነት እየሆነ ደረጃ በደረጃና ባልተቋረጠ እንቅስቃሴዉ አንዲሆን አድርጎታል። ህወሐት እንደ ፖለቲካ ጥርት ቁርጥ ያለ የፖለቲካ ፕሮግራምና አላማ በቀጣይነት ለአምስት ዓመትም ቢሆን በአቋም አራምዶ አያዉቅም። አንዱን ይዞ ሌላናዉን በላዩ ላይ ደራርቦ ሁለትና ሦስት ተጻራሪ የፖለቲካ መስመሮችን እየምታታ ተሸክሞ የመሄድ ባህርይ አለዉ። ይህ ባህርይ ድርጅቱ ከመለስ የወረሰዉ ቅርስ ነዉ። ድርጅቱ በሚከተለዉ በተሳሳተና በተምታታ የፖለቲካ አቋሞቹ ምክንያት ቋሚ መርህ ሊኖረዉ አልቻለም ። የመለስ ካንድ ሀሳብ ወደ ሌላ ሀሳብ መገለባበጥ እንደ ድርጅቱ ጠባይ ስለተለመደ አባለቱ ከፖሊት ቢሮ ጀምሮ አስከታችኛዉ ካድሬ 90 በመቶ በግለሰብ ደረጃም ቢሆን ራሱንና የሚያምነዉን ሀሳብ ጨብጦ በአቋም ጸንቶ ለቆሞ የሚችል ሰዉ ሊፈጥር አለመቻሉ፤ በጣም የሚአሳዝን ታሪክ ይሆናል። መለስ በተቀየረ ቁጥር አብሮት አክሮባት የሚሰራ፤ ተሳስተሃል፤ መስመር ተላልፈሃል፤ ፡ አዚህ አቁም የማለት ብቃት ያነሰዉ ማዕከላዊ ኮሚቴና ካድሬ ላንድ ግለሰብ በመሳርያነት መቆሙ ለሕዝባችንና ለሀገራችን ለታጋዩ እንዲሁም ለመለስ ጭምር ከጉዳት ዉጭ ሌላ ፋይዳ ለያመጣ አልቻለም። መለስ የድርጅቱን ፕሮገራም መጽሄቶችና ዕምነት የሚጽፍ፤ የሚያዘጋጅና ለድርጅዩ አባላትም ፤ፓሊት ቢሮዉንም ጭምር የሚያወያይና የሚያስተምር በመሆኑ ድርጅቱን በራሱ ምስልና አመለካከት ሊቀርፀዉ ቀላል እንደነበር አያጠያይቅም ።ከሁሉም የባሰዉ ደግሞ መለስ በማንናቸዉም መልኩ ድርጅቱ አጃጅቶና አናግቶ የሰራዉ የመበተን ተግባር ይሆናል። በ1978 ዓ/ም አመራሮቹ ዲሞክራሲያዊ አሰራር የተላበሱ ባይሆኑም በ አገር ጉዳይና ባንዳንድ የህዝብ ጉዳዮች፤ የተሻለ አቋም የነበረቸዉ አንጋፋ የድርጅቱን አመራሮች በማሃለቸዉ ተጻራሪ ልዩነቶች በመለኮስና በማጥላላት የሚገርም የብተና ሥራ እነዲከናወን አመራር ሰጠ። አከታትሎም በተወሰነ ደረጃ ለየት ያለ ሀሳብና ዝንባሌ ያሳየ በማሰር፤ በማባረርና አልፎም ሕይወት በማጥፋት ለ10 ዓመት በብዙ መስዋትነትና ኪሳራ ተሳስሮ የነበረዉን አጠቃላይ የድርጅቱን አባል፤ በተለይም ደግሞ በአመራር አካባቢ ክፉኛ በታኝ ምት በማሳረፍና በተለይም የተለየ ሃሳብ ይዘዉ በድርጅቱ ዉስጥ ወይም በትግራይ አካካቢ ከሕዝቡ ጋር አብሮዉ እነዳይኖሩ በማገድ ትግሉንና አገራቸዉን ለቀዉ ወደ ስደት አገር አነዲሰደደዱ አደርጓል። በማከታተልም ከ1979 ዓ/ም አስካሁን ባለዉ ጊዜ “የቻለ ይሩጥ፤ያልቻለ ቀስ ብሎ ይራመድ፤የተቻኮለ ይወገድ! ” የሚል የበታኞች ፍለስፍና በድርጅቱና በሕዝባችን ላይ በማወጅና በማስተጋበት 75 መበቶ ነባር ታጋዮችና አባሎችን ጭምር እስሮና አንገላቶ ከተሰለፉበት ድርጅትና ከኑሯቸዉ አፈናቅሎ በማባረር ታጋዩን አርስ በርስ እንዳይተማመንና አንዲነጣጠል በመጎትጎት የብተና ስራዎቹን አጠናቀቀ። መለስን አስከዚህ ድረስ ሊደረስ ምክንያት ሆኑት፦የድሮ የድርጅቱ መሪዎች መለስን ልቅ በመተዉ ስሕተቶች ሲሰራም በቸልተኝነት አልፈዉታል። ለሌሎች የሚስከስስና የሚያስገድል ጥፋት ለመለስ ግን ሹመትና ምስጋና ይሆናል። የፈለገዉ የፖለቲካ አቋም ይዞ ሲቀርብ ሲያመሰግኑት አንጂ ሲቃወሙትና ሲከሱት አልታዩም። የማሌሊት/ህወሐት አመራር፤- በተለይ የሗለኞቹ (እነ ስየ አብራሃ፤ ገብሩ አስራት) ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገዉ ለመለስ ዜናዊ አሽከርነት በመሰለፋቸዉ ሰዉየዉ መንገዱ ጨርቅ ሆኖለት በፈለገዉ ሰዓት የፈለገዉን ለመናገርና የፈለገዉን ዉሳኔ አሳልፎ በተከታየቹ ተግባራዊ እነደሚሆን በመተማመን፤ አሰብ የኢትዮጵያ አይደለም፤ ያኤርትራ ነዉ ብሎ ደግሞ ደጋግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ በትረ-ስልጣን ተጠቅሞ ሞግቷል። የኮሎኒያል የወሰን ዉል የሚለዉ የሻዕቢያ መሟገቻ ነጥብ ይዞ በአለም አቀፍ አደባባይ ፊት ጉለበትም ጭምር ተጠቅሞ ተሟግቷል። ይህ ድረጊት ባትዮጵያ ትግል ታሪክ ባስነዋሪነቱና አሳዛኝነቱ ቀዳሚዉ ቦታ ይዞ እነደሚኖር አያጠያይቅም>> (ብስራት አመረ፦)

አቶ ብስራት በመቀጠል በኤርትራ ሕዝብ ታሪከና ትግል በርከታ ጽሁፎችን አንደጻፈ አና አነደተከራከረ፤ በተለይም ሁለት ትልልቅ መጻህፍቶቹ- አንዱ ስለ ኤርትራ ሕዝብ ትግል አንዱ ደግሞ የቻይና፣ ሩስያ፤የቬትናም እና የአልባንያ ሕዝብ ታሪክና ገድል ሲጽፍ፡ አገሬ ናት እታገልላታለሁ ብሎ “ለቆመላት አትዮጵያ” ግን አንድም ቀንም ቢሆን ጽፎ ሲያስተምር ሰምተነዉ አናዉቅም”። ያሉት አቶ ብስራት፦ አለፎ አለፎ ስለ ኢትዮጵያ እንዳጋጣሚ ቢነሳም አሉታዊዉና ደካማ ጎንዋን በቻ መባዉሳት አወግዟት ያልፋል። በለዉ ነበር።

በዕንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ አንዲሉ ሆነና ባለመታደል እየመራት ላለችዉ አገር ሕዝበን የሚአስቀይምና የሚያነቋሽሽ ንግግሮችን በሬድዮ ሳይቀር የኢትዮጵያን ሰንደቃላማን “ጨርቅ” ነዉ፦ “የአክሱም ሐወልት ለከመበታዉ ለኦሮሞዉ ምኑ ነዉ” ሲል፤ እነዚህ አባባሎች ከአንድ መሪ ሲወጡ ያላቸዉ ትርጉም ስለማይገባዉ ሆኖ ነዉ? ወይስ ከዉስጡ እየነጠቀዉ እየፈነዳ ያስቸገረዉ ለአገሪቱ ያለዉን ጥላቻ? በቀላል ቋንቋ ግን አንድ ነገር ማለት ይቻላል፦ መለስ “ኢትዮጵያን አይወድም”። በማለት አቶ ብስራት አማረ ስለመለስ ዜናዊ ማንነት፤ባህርይና ስለ ሀወሐት ድርጅት የመለስ የግል ንብረትናትና ፤መለስ ካንድ ሀሳብ ወደሌላ ሲገለባበጥ ህወሐትም አብሮት እነደሚገለባበጥ በማያሻማ ቋንቋ ለታሪክ የሚቀር እንደ ዉስጥ አዋቂነቱ በሚገባ ዘግቦታል።

ከዚህ የተነሳም ሊሆን ይችላል ብዙ ሰዎች የመለስን ከድርጅቱ ማስወገድ ወሳኝነት እንዳለዉ ሲከራከሩበት የነበረ። ግራም ቀኝም ነፈሰ ፦ ላገሪቱ የወደብ ማጣት፤ ዉድቀት ዉርደት፤ሞትና ጦርነት በሃላፊነት የሚጠየቁት የህወሐት መሪዎች ቢሆኑም በመለስ ሳምባ ለሚተነፍሰዉና በመለስ ጭንቅላት ለሚንቀሳቀሰዉ ለህወሐት መኖርና ዉደቀት ወሳኙ መለስ ዜናዊ መሆኑን ለክርክር የሚቀርብ ኤይደለም።

በቅርቡ ዓይናችሁን ሸፍኑ ላሞኛችሁ ዓይነቱ የለመደበት የልጆች ጨዋታዉ የምርጫ ሂደት የተጫወተዉ የወየኔው ቡድን፦ አምላክ ከመንበሩ ከኢትዮጵያ ሰማየ ሰማየት በፀሃይ መስኮቱ ብቅ ብሎ የዘገበዉ ታሪክ ምስክርነት ለወደፊቱ ሳናየዉ አንቀርም። ፍርድ ይዘገያል አንጂ አይቀርም።
የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚያነኳስሱ ባንዳዎች መቸዉንም ቢሆን የህሊና እስረኞች ናቸዉና አስከወድያኛዉ ድረስ ጥፋታቸዉ ሲቆጫቸዉ ይኖራል።


አትዮጵያ ለዘላም ትኑር!
ጌታቸዉ ረዳ
ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያEthiopia Ethiopia Ethiopia Ethiopia Ethiopia Ethiopia Ethiopia Ethiopia Ethiopia