Wednesday, May 22, 2024

በዲሞክራሲ ስም “ሁሉም ይደመጥ” ዛሬም ያለታከመው የሚዲያ ባለቤቶች በሽታ ጌታቸው ረዳ 5/22/24


በዲሞክራሲ ስም “ሁሉም ይደመጥ” ታከመው የሚዲያ ባለቶች በሽ

ጌታቸው ረዳ

5/22/24

 የምትመለከቱት ፎቶ  የትግሬው ካቡጋ (አሉላ ሰለሞን) በፌስ ቡኩ ከለጠፈው የትግርኛ ጽሑፍ ሲሆን አማርኛ ትርጉሙም ከታች ይመልከቱ፡፡

አማርኛ ትርጉም እንዲህ ይላል፤

<< ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ፡፟

(አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች) በራሳቸው ሜዳ (ብሔራቸው ውስጥ) ትኩረት የሚሰጣቸው ሰው ሲያጡ ፤ ሌሎችን መስለው ጀግና፤ጀግና እንዲባልላቸው የመጣር አባዜ ይታይባቸዋል፡፡ ለምሳሌ ይህች በስዕልዋ የምትመለከትዋት ምስኪን እህታችን (የትግራይ ተወላጅ) በባልዋ እና በስነጥበብ ተማርካለች፡፡ ያች ኢምፓየር (ኢትዮጵያ) በትዳር (በጋብቻ)፤ ሃይማኖት፤ ስነጥበብ እና ሚዲያ ነው ዋና መጫወቻ ሜዳዋ ስንል በምክንያት ነው፡፡ ትግሬዎች ሆይ! ከትግራይ ተወላጆች ብቻ ጋብቻ መስርቱ>>  ይላል (አሉላ ሰለሞን) ትርጉም ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረ ገጽ አዘጋጅ)፡፡

ይህንን ለምን እንደለጠፍኩት ከታች እንመለክታለን፡፡

ከአምስት አመት በፊት (የአይ ኦሮሙማ ረዕዮት ወደ መንግሥት ከመምጣቱ በፊት) ወያኔን ሰንታገል ትግሉ አሰቸጋሩ ጉዞ ካደረጉት ዕንቀፋቶች ውስጥ ጽሑፎችና ቃለ መጠይቆች የሚስተናገዱባቸው ‘’የድረገጽ ባለብቶች’’ ደንቃራነት ነበር፡፡

ኔን የምትከታተሉኝ ነባር አባቢዎ በዚህ ጉዳይ ብዙ  ሳሰረዳ እንደነበር ታሰታውሳላችሁ፡፡ እንደ << ኢሳትዘሐበሻኢትዮ ሚዲያ...>> የመሳሰሉ ትልልቅ የውይይት መድረክ አስተናጋቾች “ውይይት እንልመድ” ፤ “ተገነጣዮች ወደ ኢትዮጵያዊነታቸው ተመለሰዋል፤ወንድሞቻችን ናቸው... ወዘተ..” በሚል ማጃጃያ  ለ “ኦ .ነ.ግ” ለ “ኦ.ብ.ነ.ግ” ለ “ሻ.ዕ.ቢ.ያ” ጽንፈኞችና ወንጀለኞችን ሰፊ መድረክ በመለገስ በሕዝብ ፊት ጸረ ሕዝብ እንዳይደሉ በማስመሰል እየጋበዙ መድረካቸው ልቅ አድርገውላቸው ፐሮፓጋንዳቸውን ሲለቁላቸው እኛም እየተቃወምን የኛ ተቃውሞ እንዳይለጠፍ ከፍተኛ እገዳ ሲደረገብን መኖሩን ታሰታወሳላቸሁ፡፡

ክዚያ ሁሉ “ወደ ኢትዮጵያዊነታቸው ተመለሰዋል” ማጃጃያ ሽፋን እነዚሀ ጽንፈኞች አብይ አሕመድ ሢነግሥ ያሳዩት ባሕሪ የምታውቁት ነው፡፡ ለውጥ መጣ ሲባል አብይ አሕመድ ያለምንም ውል ሁሉንም ወደ አገር ሲያስገባ ልክ Sepetemeber 18/2018 በኛ አቆጣጠር ደግሞ 2010 ዓ.ም ኦነግ ከየመአዝናቱ ኦሮሞ ጽንፈኞችን ብጭነት መኪና አስጭኖ ባንዴራውን እያውለበለበ ፤ ያዲስ አበባ ከተማዋን ግድግዳውን አሰፋልቱን መኪኖችን  በራሱ ባንራ ቀለም ቀብቶ እንደ ጣሊያን “ወራሪ መስሎ” በመግባት ከዚያም ቡራዩና አሸዋ  ላይ <<ጋሞና አማራን>> በገፍ ጨፈጨፈ፡፡

ሲያቃጥርለት ከነበረው ግንቦት 7 (ኢሳት) ጋርም አዲሰ አበባ ጎዳና ላይ በሰንደቅ ዓላማ ምክንያት ግጭት ገባና ተካሰሱ፤ተደባደቡ፡፡ 

ከዚያም  አንዳንዶቹ የባህል ሚኒስር የፓርላማ አባል፤ ወዘተ... ሆነው ሲሾሙ ፤ የዓድዋ በዓልን ማራከሰ፤ ማገድ፤ አማራንና ሚንሊክን ማጠልሸት ፤ አገር ሲመሰረቱ ያለሙዋትን የኦሮሚያ ካርታና የኦነግ ባንዴራ በጽሕፈት ታቸው በክብር በመስቀል ማንነታቸውን ሳይደብቁ ገለጹ፡፡

ሬም  ከዚያ ሳይማሩ “የሃሳብ ገበታ” (አዘጋጅ ‘መጎስ ተሾም’)፤ የመሳሰሉ በርካታ “የኢትዮጵያ መድረክ ነን የሚሉ” ሚዲያዎች በዚያው ፈለግ እየተቃኙ

በዲሞክራሲ ስም “ሁሉም ይደመጥ፡ የሚለው እጅግ አስገራሚ ማጃጃያና “ተሞክሮ የወደቀው” የሚዲያ ሚናን ያለመለየት “ቀይ መስመር” የጣሱ ጽንፈኞች ሁሉ በመጋበዝ ያንኑ ደግመውት እያየናቸው ነው፡፡

በተደጋጋሚ ‘’የሃሳብ ገበታ’’ የተባለው ሚዲያ እነ እስል ጋቢሳን ፤ የትግው ‘ካቡጋ’ አሉላ ሰለሞን፤ የመሳስሉ በርካታ ኦነጎች፤ አከራሪ እስላሞች ፤ በርካታ የትግራይ ፋሺት ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ሰዎችን እየጋበዘ የተቆጣን ሕዝብ ላይ መልሶ ጨው በመነስነስ ምን ታመጡ ዓይነት ብልሽው የመድረክ ግብዣ እያዘጋጀ ነው፡፡

መጎስ ተሾመ የሕግ ምሁር ነው፡፡  የዚህ ወጣት እውቀት ለመለካት ይህንን ድረገጼን በመጎብኘት የሚከተለውን አንብቡ፡፡ሰለ እሚታረዱት አማራዎች ናቸው፡ እንዲህ ይላል፡፡ “አራጆች የሚል ቃል ባንጠቀም ጥሩ ነው” “እኔ ሰው ስለመታረዱ አላውቅም” የሕግ ምሁር መጎስ ተሾመ! “አራጆችን አራጆች ካላልናቸው ምን እንበላቸው? “ሃኪሞች እንበላቸው?” (ጋዜጠኛ ተስፋየ ተሰማ) ትችት አቅራቢ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 8/3/23

https://ethiopiansemay.blogspot.com/2023/09/ethiopian-semay-8323.html

እንዲህ ያሉ ወጣቶች ሚዲያውን ሲያዘጋጁ የሚሰሩት ያውቃሉ ወይ የሚል ጥያ መጠየቅ ጠቃሚ ነው፡፡ የትግው ሩዋንዳ “ካቡጋ” ስለ መሳሰሉ ዘረኞች በእንግድነት መጋበዝ ብዙ ሰዎች ዛሬም ጉዳቱ አልገባቸውም፡፡

በዲሞከራሲ ስም ወንጀል የፍጸሙ ጽንፈኞች ሕዝቡን ያለ ምንም ይቅርታ መጠየቃቸውና አለመጠየቃቸው ሳይነሳና ይቅርታ ሳይጠይቁ  <<ኢምፓየር>> ሰለሚሉዋት ኢትዮጵያችንን የችግር መፍትሔ ፈቺዎቹ አካል ተደርገው ለውይይት ይጋበዛሉ ወይንም አገር ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል፡፡

ለምሳሌ በዲሞከራሲ፤ በዕርቅና በሰላም ስም ታሪከ የማይረሳው ሴራ አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ያደረገው ንግግር  አስታውሱ፤

እንዲህ ይላል፡

<< አገር ለመገንጠልም ከፈለገ ለመገንጠል ወኪሉን ፓርላማ ውስጥ አስገብቶ አገር መመስረት ይችላል>>

 አብይ አሕመድ እንዳለው ሁሉ፤ እነ ልደቱም ስለ ‘’የተረገዘ ህጻን ከዕርጉዝ ሴት ሆድ ቀድዶ የሰው ሥጋ የሚበላ ጸረ አማራ፤ ግብረሰዶማዊው የኦነግ (ሸኔ በሚል የሚጠራው የመጠሪያ ሽፋን) ሽብርተኛ ቡድን” ልደቱ አያሌው ተጠይቆ ሲመልስም እንዲህ ይላል፡

 “ሽብርተኛ” ብየ አልጠራውም፤ ወያኔም ሽብረተኛ አይደለም ፤ የፈለጋቸው አጀንዳ ማራመድ መፍቀድ አለብን’’  (ልደቱ አያሌው፤ ምንጭ Ethiopian Semay)

በማለት በዲሞክራሲና በመቻቻል ስም “30 አመት የፈታነው ሱሪያችን” ዛሬም እነ ልደቱ “በዲሞክራሲና በመግባባት ስም” ለዳግም ሱሪ መፍታት እየሰበኩን ነው።

ያለፈው ካልተመለከትን መጪው ዘመንም አያስኬደንም።በመቻቻል ስም ፤ አገራዊ እሴቶች የሚባሉ በቀይ ፣መስመ የተሰመሩ መስመሮችን በመጣስ ፖለቲከኞችን በማመናችሁ አገራዊ ምሶሶዎችሰው ባሕርን ያክል ትልቅ ህይወት አስነጥቆናል።

 30 አመት ሙሉ በመግባባት ስም “ሦሰትኛ መንገድ” በሚል ገዢዎችን የሚያሞግስ (መለስ ሲሞት ደቱ የተናገረውን ባለፈው ጠቅሻለሁ) ቀበቶ አስፈቺ መንገድ ከተከተልንና ከተሰበክን 33 አመት ሆኖናል።

በመንጋ እየተነዳ በራሱና በኢትዮጵያ ሕይወት ላይ ያደረሰው የትግራይ ማሕበረሰብ ትግራይ ውስጥ በሰራዊቱ ላይ እና አማራን እየለየ ምን ጥቃት እንዳደረሰ ብዙ ጊ ገልጫሁ፡፡ መንጋ ነው ስል ብዙ ደንቆሮ አይወደውም፡፡ ለመንጋ መበራከት ገምቢዎቹም እነ “አሉላ ካቡጋ” (አሉላ ሰለሞን) ናቸው፡፡

አንድ ወታደር የገጠመው እንዲህ ይላል፡፡ 

<< ከአማራ ሕዝብ ላይ ጠብ የለንም ይላሉ በሌላ በኩል ደግሞ የአማራን ልጆች ከጦሩ እየለዩ ሲረሽኑ ነበር።>> ወያዎቹ እነ ታቸው ረዳና እነ አሉላ ሰለሞንም ያንን “ከአማራ ሕዝብ ላይ ጠብ የለንም” የምትለዋ ስንኝ ያስደመጡና አማራ ጋር እንዳትጋቡ ሲሉ ያወጃሉ፡፡

ለምሳ በጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም “በርካታ ካምፖች የትግራይ እናቶች ሠራዊቱ ሲታፈን ፈንድሻ እየተበተኑ፤ቄጠሜማ እየነሰነሱ ከበሮ እየመቱ የሠራዊቱን አስከ እምቧለሌ እየዞሩ ጨፍረውበታል፡ “ገድላችሁ ደማቸውን አሳዩን” ያሉ የእናት አንጀት የሌላቸው እናቶች ደግሞ ወጣቱን አነሳስተው ሠራዊቱን አስጨፍጭፈዋል።” ይህ ሁሉ የመንጋ ስሜት የተመራው ከላይ በጠቀስኩት በካቡጋና በመሳስሉ የትግራይ መሁራን ምክያት ነው፡፡

ይህ ሁሉ የነ አሉላ ሰለሞን ሥራ ግልጽ ሆኖ እያለ ኢትዮጵያ በሚባሉ ሚዲያዎች እየተጋበዙ ላደረጉት አናካሽ አዋጃቸው ይቅርታ ሳይጠይቁ እንደ ቅን ፖለቲከኛ ተደጋጋሚ መድረክ እየተሽራቸው ያለ ምንም ተቃውሞ ኢምፓየር ስለሚለዋት አገራችን ተንታኞችና መፍት ቀያሾች ነው እያደመጥናቸው ነው፡፡

 ዋናው ችግራችን ሁለት ነገሮች በማጣታችን ነው። አንዱ የተጀመረ ስለመሰለኝ ልተውና ወደ ሁለተኛው ላምራ፤

2) ኢትዮጵያዊ ብሔረተኛ (ብሔረተኛ ቀጥተኛ ትርጉሙ ሃገራዊ ማለት ነው) መሪ በማጣታችን ቀይ መስመር እንዲጣስ ያደረጉ ወንጀለኛ በለሥልጣናትን ዛሬም እየደጋጋሙ ሥልጣን ላይ በመውጣት፤ ለ33 አመት በሚሊዮኖች ነብሳት እያሳለቁ እርስ በርስ በመተቃቀፍ አንደኛቸውም ሳይታሰሩ ዛሬም እየገዙን ነው።

 “ተሾመ ቶጋ” የሰላም ኮሚሽነር ሆኖ ሲመጣ፤ የኦግ መሪ የባሕል ሚኒስቴር ፤ የዘመናዊውም ይሁን የባህል ትምህርት ያልጎበኘው “ማይሙ” አባ ዱላ ገመዳን ፤ በትግራይ ፋሺስት ተዋጊዎች በሺዎች የተማረኩት ወታደሮችን በሰልፍ ሲታዩ “ቆርጦ ቀጥል የካርቱን ምስል ነው” ያለንን “ባጫ ደበሌን” አምባሳደር አድርጎ መሾምን፤ ‘ሓጫሉን የገደሉት ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው ያለቺንን ፤ “ትግሬዎችን ፈቅደን ብናኖራቸው ጠገቡ" ያለቺንን ኦነግዋ ‘አበበች አዳኔን’ በከንቲባነት መሾምን ፤ ሬድዋን ሁሴን ስለ ኢትዮጵያዊነት ተደራዳሪ ሲሆን ማየት መሪ ማጣታችን ነው።

ጽንፈኞቹ ሥልጣን ላይ ስለቀጠሉ ኢትዮጵያ ብሔረተኛነት እንደ ጨፍላቂ እየታየ በማይገባ ትርጉም ተሰጥቶት፤ ተገፊ እያለ እንደ ገፊ እየታየ፤ ያንን ትርጉም የተሳሰተ ነው ብሎ ከመከራከር ይልቅ በተስፋ ቆራጭነትና ተሞዳማጅነት ባሕሪ ምክንያት ሚዲያዎችም ሆኑ ፖለቲከኞቹ እነ ልደቱ አያሌውና መሰሎቹ አዲሰ ቃል ፈልስፈን “ብሔር”፤ “ንኡስ ብሔር”…. ብንል ጽንፈኞቹ ይቀዘቅዙ ይሆን ወይ እያሉ ራሳቸውን አሞኝተው ቀበቶ ለማስፈታት የአንጎል አጠባ ጀምረዋል።

የተለያዩ ፓርቲዎች ፖለቲከኞች ለመደራደር ሲቀርቡ “በሰጥቶ መቀበል ስም ፤ በመቻቻል ስም” ቀይ መስመር እንዲጣስ እያደረጉ በማንወጣው አዘቅት ገብተን እነ አንዳንዶቻችን አገራችን ሳናይ እዚህ ማለፋችን ነው፡፡

ኢትዮጵያዊ አገራዊያን ፖለቲከኞች ከሌላኛው ወገን ጋር መስማማት ቢጀምሩ መደራደሪያ ነጥባቸው ቀይ መስመር ለድርድር መቅረብ የለበትም፡፡ በመሞዳሞድ አገር አይመሰረትም፡፡ ሁሉንም በጥርጣሬ መመልከት አለባቸው። 33 አመት ሙሉ ተሞኝተናል እና!!! “የኦሮሞና የትግሬ ጥቅም አስጠባቂ ሥልጣን ላይ የለም” የሚለው ጅልነትም አይልመድባችሁ፡፡

የዚያ የሚዲያዎች የ30 አመት መሞዳሞድ አመል ዛሬ እነዚያን የተኩ አዳዲስ ሚዲያዎች ደግሞ የድሮ ጽንፈኞችና እንደ እነ የትግሬው የወያኔው ቄስ  ሰረቀብርሃን እና ካቡጋው “አሉላ ሰለሞን” የመሳሰሉ የዘር ጽዳት ሰባኪዎች ለጸር አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ያወጁት የጥላቻ ዓዋጃቸው ይቅርታ ሳይጠይቁ በርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ ቴድሮስ ፀጋየ እና በ የሃሳብ ገበታ አዘጋጅ መጎስ ተሾመ በኩል (አሉላ ሰለሞንን) ነጻ መድረክ ተሰጥቷቸው ቅን ሰዎች መሰለው ስለ ትግራይና ኢትዮጵያ ፖሊቲካ ሲዘባርቁ እየሰማን ነው፡፡

የጥላቻ ሰባኪዎች እንደ እነ ኦነጎቹ እነ ፕሮፌሰር እስቄል ጋቢሳ የመሳሰሉትን በርካታ ጽንፈኞች ሚዲያ ላይ ያለምንም መሸማቀቅ ጠንካራ ተቃወሞና ጥያቄ ሳያቀርቡላቸው ይስተናገዳሉ፡፡

እኛ የጠላት ንግግሮችን የመርሳት ልምድ ሰላለን ነው እየደገምኩ የማሰታውሳችሁ፡፡

ለመሳአባ ሠረቀ ብርሃን እንዲህ ይላል፦ ከዚያም ወደ ጋባዡ ርዮት ሚዲያ እመለሳለሁ (ሚዲያው እንት እንደ ተራ ተጋባዥ በነጻ እንደሚለቃቸው ላሳያችሁ ነው)

 “ትግሬዎች ኢትዮጵያ የሚባል ቃል ከአንደበታችን እንዳይደመጥ”፤ “ኢትዮጵያ” የሚል ቃል ካንደበቱ የሚደመጥ ትግሬ ካለ እሱ የተረገመ ነው”።

ያ የእርግማን ውግዘት ለእንደ  የመሰሉ ትግሬዎችን ነው፡፡

ለአማራዎች ደግሞ እንዲህ ይላል

<< አማራ የጠራ ዘር ስሌለው ከዚያም ከዚያም ተጠራቅሞ የመጣ ዘር ስለሆነ አማራ የሚባል ዘር የለም ! ቢኖርማ ያስብ ነበር። ስለዚህም ነውየአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ’ የሚለው። የራሱ የሚባል ዘር የለውም። ከዚህ መጣ ስለማይባል፤ ከትግራይ ከዚያም ከዚያም የተወጣጣ ስለሆነ ራሱን ችሎ የመጣ ዘር ስሌለው ሁልጌዜ ሊሸፈን የሚፈልገው ኢትዮጵያ በምትባለው አገር ነው። ለዚህ ነው ሌላ ነገር አይናገርም። ኢትዮጵያዊ ነኝ ብቻ የሚለው።…….

ስለ ኦሮሞና ትግሬዎች ደግሞ እንዲህ ይላል፡

<< ………ኦሮሞም ኦሮሞኖቱን ይዞ ኢትዮጵያዊ ነው፤ ትግራይም ትግራዋይነቱን ይዞ ኢትዮጵያዊነቱን ይዞ ነው የመጣ፡አማራ ግን አማራነቱን ይዞ ኢትዮጵያዊነት የሚለው ስሌለው፤አማራ የሚባል ዘር ስሌለው፤ ’የሚንጠለጠልበት ዘር ስሌለው’ ኢትዮጵያ በሚለው ተሸፍኖ እየሰራ ስለመጣ “Shame on you! በጣም አፍርባችኋለሁ

………..የትግራይ ሕዝብ ሆይ! በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጀነሳይድ እነዚህ አካላት ክደውሃል፡ አማራ ክዶሃል! እመነኝ! እመነኝ! አስረግጬ እነግርሃለሁ። ኢትዮጵያ የምትባል ብትከዳህም እግዚአብሔር አልካደህም!”>>

 ሲል የላቻ ዓዋጁ በአደባባይ አውጆ መኖሩን ታሰታወሳላችሁ፡፡

ናዚዎች ዓለምን የሚገልጽዋት ልክ እንደ “አባ ሠረቀ ብርሃን” በቆሸሸ ዘር እና ያልተቀላቀለ ወጥ በሆነ የጸዳ ዘር መካከል በሚደረግ ትግል እንደሆነ ያምኑ ነበር። የናዚ ዘረኝነት ስለ ዘር እና ስነፍጥረት ልዩነት በየትምህርት ቤቶችና ተቋማት ያንሸራሽሩና በአዋጅ ያስነግሩ ነበር። የተቀላቀሉ ዘሮችና አካለ ስንኩላን የማይፈለጉ ፍጡራን ስለሆኑ መወገዝና መጥፋት አንዳለባቸው አውጀዋል።

ስለሆነም ዘርን እንደመታገያ ወስደው የጀርመን ምሁራን እና ሃይማኖት መሪዎች ሁሉንም የዕለት ተዕለት ኑሮ እና ፖለቲካ በዘር ጥራትና በወጥነት እምነት ተቀርጸው ዘር የሌላቸው (ዘረ ቢሶች) የሚሉዋቸውን ይሁዶችን የተለየ እና የበታች ዘር ናቸው የሚለውን አስተሳሰብ ተራውን የጀርመን ሕዝብ እንዲከተለው በማድረግ ጸረ ይሁዳነት እንዲሰፍን አድርገዋል።

ሠረቀ ብርሃን እና መሰሎቹ አማራ ወጥ ዘር ስሌለው ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ሕዝብ ነውና፤ ስለሆነም የኔ ዘር ነው የሚልበት ዘር ስሌላው የበታች ዘር (ሎው ካስት) ስለሆነ ሁሌም “አትዮጵያ በምትባለዋ አገር ተጠልሎ የሚኖር ሕዝብ ነው።” ብሏል።

“አባ ሠረቀ ብርሃን” እየነገረን ያለውን በንጽጽር ስንመለከት “ናዚዎች ይሁዶችን” ዘርቢስ የሆኑ በዓለም ውስጥ ተበታትኖ የሚኖር የራሱ “ወጥ (ኢንዲፐንዳንት) የሆነ ዘርና አገር የሌለው “ዝቅተኛ ዘር” የሆነ ጀርመን ነኝ እያለ “የጀርመን ዘር የሚበክል” ጀርመንን እንደ መከለያው አድርጎ የሚኖር ጥገኛ ዘር (ዝቅተኛ ዘር) ነው የሚሉ የናዚዎች አዋጅ  በመቅዳት ነው ‘ቄስ ሠረቀ ብርሃን’ አማራውን “ሎው ካስት” ነው ሲል ያወጀ።

 በሃይማኖት የተጠለለ ይህ የትግራይ ናዚ በርዕዮት ሚዲያ ተጋበዞ << ይህንን ደፍሮ የሚከራከረኝ አማራ የለም፤ካለም ይቅረብ እያለ (በድፍረት ተናግሯል) እውነትም ደፍሮ የገጠመው አማራ ስላላየሁ ስለ ድፍረቱ እያደነቅኩ (ይህ ማይምን የሚያሳፈር አማራ ታቶ ሳይሆን ሁሉንም ቸል የማለት ልምድ ስለሚያጠቃቸው ነው)፤ በሚገርም ሁኔታ ግን የርዕዮት ሚዲያ ቴድሮሰ ጸጋዬ <<ይቅርታ መጠየቅ ካለበዎት የሚሉት ነገር ካለ ዕድሉን እነሆ >> (ማለቱ ባመሰግነውም ፡ አባ ናዚው ሠረቀ ብርሃንን ጋብዞ ያለ ምንም “ከባድ ጥያቄና ሊቀርቡ የሚገባቸው ሰረቀ ብርሃን የተናገራቸው የቪዲዮ ሰነዶች ሆን ብሎ የሆነች ትንሽ መናኛ የንግግሩ ክፍል በሴለፎኑ ለአድማጮቹ  በማስሰማት እራሱንም አስገምቶ ሠረቀ ብርሃንን እንደልቡ እንዲጋልብ አድርጓል”

 የሃይማኖት መጽሃፉ የሚነግረን “የጽድቅ ሰባኪ የሆነ ሁሉ በኃጢአተኞች መንገድ ሲቆም፣ ንስሐው እንደ ኃጢአቱ እስኪታወቅ ድረስ በታላቁ ጉባኤ ውስጥ እንደገና ከንፈሩን መክፈት የለበትም” ይላል  (ዛ  በሚገርም ክስተት የትግ አባ ሰላማ ተብሎ ብትግሬ ሕዝብ ተወድዶለት ተሰይሟል (ጉድና ጅረት ከወደ ኋላ የሚባለው ትግሬ ውስጥ ተከስተ )። ይህ ውሸተኛ ቄስ  ውሸቱን በማስረዳት ወይም በማመካኘት ኃጢአቱን ያዋህዳል ወይንስ በትህትና እና በጽድቅ ንስሃ ለመግባት ድፍረት በማግኘቱ ሃላፊነቱን ይወስዳል? የሚል የማይታሰብ ጥያ ስለሆነ የትግራይ ሕዝብ ይጨነቅበት፡፡

በተደጋጋሚ በነዚህ ወራት ውስጥ በኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች ደግሞ ደጋግሞ ቱሩናፋው ሲለቅ የሰነበተው ላው የትግራይ ናዚ እና ወያ ለማአከላዊ አባልነት መርጦት የነበረው የትግራይ ካቡጋው “አሉላ ሰለሞን” የሕግ መሁር የሆነው “መጎሰ ተሾመ” በሚያዘጋጀው በሃሳብ ገበታ ሚዲያ ላይ መደበኛ የትግራይና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትንታኝ ሆኖ ያ ሁሉ አጭበርባሪ ብልጣብልጥ ዘረኛነቱነቱን ተሸክሞ ፖለቲካ ሊተነትን ተፈቅዶለታል (ኢምፓየር ነች ስለሚላት አገር ምን አገባው? ነው የኔ ጥያቄ)፡፡

መግባባትን የምንፈልገው ያጣነውን ለማስመለስና ተጨማሪ ላለመስጠት ነው እንጂ፤ ያለምንም ፀፀትና ንስሃ ሳንሰማባቸው እንደ ቅን ሰው ሽፋን ተሰጥቶአቸው በድጋሚ ሊጋልቡብን አንፈቅድም።

ሩዋንዳን የሚያክል አስፈሪ መበላላት የተፈጸመባት አገር ዛሬ የኢትዮጵያ መሪ ተብየ ዱርየዎች ምክያት ከሩዋንዳ ሳትማር 33 አመት እየተራመደቺበት ነው፡፡ ለዚህ ክስተት እነ አሉላ ሰለሞን ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡

ሩሲያ፤ሰን ኮርያ፤አሜሪካም ሆነ እስራኤል የተከበሩበት መንገድ በውይይት ሳይሆን በብረት ነው። ሰላም ያልገዛው ነጻነት ሃይል ይገዛዋል። ሱሬ መፍታት በፖለቲካ ውስጥ መጥፎ ቃል ነው:: ዛሬም ጽንፈኞችን ወደ መሃል ለመሳብና ለማለሳለስ በሚል ቀበቶን የሚያስፈታ የ30 አመት ከንቱ መሞዳሞድ ሱሬን ፈትቶ እንደ መግባባት የሚያዩ ፖቲከኞችን ዛም ሲደገም ስናይ ያሰጋልና ፖለቲክኞችና ሚዲያዎችን የሚሠሩት ሁሉ ባይነ ቁራኛ (በጥንቃቄ) ማየት አለብን።

የፋኖ የሽምቅ ተዋጊዎችን የወደድኩላቸውና እንዲመሰረቱ ስወተውት የነበረው ምክንያት ለኛ ኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎች እነሱን በጀርባ መያዝ አስፈላጊነቱ መደገፍ አለብን፡፡ ለምን ቢሉ የኦሮሞና የትግራይ ጽንፈኞች ጉልበት እስካላቸው ድረስ አንድ ኢንች ስትሰጣቸው ስንዝር ይጠይቃሉ ፤ ከስንዝር ወደ ክንድ፤ ከዚያም የፈለገ ብትሰጣቸውም ምንም የሚረኩበት ማቆሚያ የላቸውም። መለሳለስ፤መሞዳሞድ ማቆሚያው ዛሬ ነው!

በገጀራ የቆረጡ ፤ በመጥረቢያ የፈለጡ፤  በድንጋይ የቀጠቀጡ፤ በምላሳቸው የዘር ጭፍጨፋ ያወጁ፤በጭፍጨፋ የተካፈሉ፤ የዘረፉ ፤ የሰው ሥጋና ደም አርደው የበሉና የጠጡ ፤ አገራችን እንድትፈርስ የጣሩ ፤ አስከሬንን በመኪና የረገጡ ፤ ቁስለኛን በታንክ የጨፈለቁ ፤ የፍጥኝ አስረው ገደል የለቀቁ ፤ ጥንታዊ ቅርሶችና ሃውልቶች ያፈረሱ ፤ አብያተ ጸሎት ያቃጠሉ ፤ በነገዶች መካከል ጋብቻና ፍቅር እንዲፈርስ ያወጁ ፤ በጎች መካከል የሱቅና \ምግብ ቶች የንግድ ግንኙነት እንዳይካሄድ ካምሳያ ብሔራቸው ብቻ እንዲገበያዩ፤ ያወጁ፤ ካምሳያ ሔራቸው በተገነቡ  መስጊድና  ቤተክርስትያን በቻ ሄደው እንዲፀልዩ ያወጁ... ሁሉ ፤ ቢያንስ ፀፀት ሳያስሰሙ በኢትዮጵያዊያን ሚዲያዎች ተጋብዘው እንደገና እንዲንቁን መደረግ የለበትም፡፡

አመሰግናለሁ!

ጌታቸው ረዳ