Monday, May 7, 2018

ለመስከረም አበራ የተሰሠጠ መልስ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


ለመስከረም አበራ የተሰሠጠ መልስ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
ስለ ፎቶግራፉ ማብራሪያ
(ይህ ፎቶግራፍ ለታሪክ ያስቀመጥኩት ከቆየ ትችቶቼ ከኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ ማሕደር ውስጥ የተገኘ ፎቶግራፍ ነው።በወቅቱ ስለ ፎቶግራፉ እንዲህ ብየ ነበር -“በዚህ ፎቶግራፍ ላይ የሚታዩዋቸው ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ከኤርትራ ምድር ሸሽተው በበጎ አድራጊ ወገኖቻቸው እርዳታና ተባባሪነት በድብቅ ላይ ይገኛሉ። በግንቦት 7 ያዙልኝ ባይነት በሻዕቢያ አፋኝ ሰዎች እየታደኑ ስለሆኑ ተደብቀው ይገኛሉ። ታሪካቸው ወደ ታች እንመለከታለን።) ብየ ነበር በወቅቱ ስዘግብ። ከላይ ከሚታዩት ውስጥ ዛሬም እውጭ አገር ይገኛሉ።ከወደቀኝ በኩል መትረየስ ተሸክሞ ያለው በቅርቡ በዚህ አመት ከኤርትራ/ከትግሉ ተሰናብቶ እውጭ አገር የሚኖር ዘመነ ካሴ ነው። ታሪኩ እሱ ራሱ የሚነግራችሁ ይመስለኛል። ሚዲያዎች በዚህ ሥራ ብትሰማሩ ትመሰገናላችሁ።

እመሃል “ኣር ቢ ጂ” ላውንቸር ሮኬት ተሸክሞ የሚታየው የወፌ ላላ ስቃይ ቀምሶ አምልጠው ከመጡት አንዱ ማስረሻ ነው (የስልጠናው ክፍል ሐላፊ)። ሌላውም እንዲሁ (ቴድሮስ)።በወቅቱ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ታጋይ የነበረ ነው።  ስለ ቴዎድሮስ መታፈን እና ግድያ እንዲፈጸምበት ECADF በተባለ የግንቦት 7 አሽቃባጭ ድረገጽ ላይ አስፈሪ ማስታወቂያ ተለጥፎ ነበር። ሰው አደገኛ  ይፈለጋል!!የሚል ነበር። እነ ዳኒኤልም እንደ እነሱ ተደብቆ ህይወቱን ለማዳን ሱዳን ምድር ሊይዙት ሲያዋክቡት የነበረ ሰው ነው። ይህ እንግዲህ ለወ/ት መስከረም አበራ በአንዳርጋቸው ጽጌ ሥር የነበሩት ታጋዮች ያለፉት መከራ እንደ መግብያ ላስታውሳት ብየ ነው። ከላይ የምታዩት “ማስረሻ’ ወፌ ላላ ግርፋት ከደረሰባቸው አንዱ ሆኖ በልቅሶ እምባ የታጀበ ቃለ መጠይቁና ፎቶግራፉን በሚቀጥለው ይዤ እቀርባለሁ። አውድዮ መለጠፉን ስለማልችልበት እምቢ እያለኝ እንጂ ፎሪግራፉን ግን አቀርባለሁ።  (ከEthiopian Semay ፎቶ ክምችት). አሁን ወደ ውይይቱ እንግባ።

ክብርት እህት ወ/ት መስከረም አበራ ሆይ!
“አንዳርጋቸው ፅጌ፦ በጨቋኞች እጅ የወደቀ ሃብት!”  ብለሽ ሳተናው በተባለ ድረገጽ በፈረንጆች አቆጣጠር

ስለ አንዳርጋቸው መታሰር እና እንዲፈታ ስለ መብቱ መቆምሽ የተጠበቀ ስብእናሽ እያከበርኩልሽ፡ እንዲያም ሆኖ ስለ አንዳርጋቸው በጻፋቸውም ሆነ በድርጊቱ የኮራሽበት መሆኑን ነግረሽናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ለተቀመጣችሁ ጸሃፊዎች ለመነሻው ምክንያታችሁ ባይገባኝም እንዲህ ያሉ ጽሑፎች ለማንበብ ለጆሮኣችን አዲስ ነገር ኣይደለም። ምንም ይሁን ምንም አንቺ የሴቶች መብት የቆምኩኝ ነኝ እያልሽ የወንድ ልጅ እምባ ሲፈሰስ ግን አልተሰማሽም። ለሰብኣዊነት መቆም በሴቶች ብቻ የተወሰ ሳሆን ለሁሉም መቆም ነው። ሰው የሚያስብለውም ይህንን ሲሆን ነው።

ግን እንደ አንዳርጋቸው በመሳሰሉ የሰው መብት በተጋፉ ፖለቲከኞች ምክንያት የወንድ ልጅ እምባ ሲፈስስ ግን ይበልጥኑ መብት ረጋጩን በሰብኣዊ ጠበቃነት እና “በውድ ሃብትነት” የመሳልሽ ነገር ከመገረም አልፌ የሰው ልጅ መብት ምንነትም የገባሽ አትመስይም ወይንም አላሳሰበሺም። ያላሳሰበሸ ደግሞ ከ 4 አመት በፊት አንዳርጋቸው በሰብአዊ ጥሰት መካፈሉን በሰብአዊ መብት ጠበቃ ተሟጋቾች እና የፖለቲካ ተናጣፊዎች (አክቲቪሰት) ጉዳዩ ተነስቶ የተዘገቡትንና የተደረጉ ክርክሮችን የረሱት/ያላዩት/ያልሰሙ ሰዎች (አንቺንም ጨምሮ) እንዳይኖሩ በሚል ለማስታወስ እንዲረዳ መረጃውን ከጥቂት ቀን ሳይቀር (Welkait.com Ethiopatriots.com እና Ethiopanorama.com ድረገጾች) አቅርቤአለሁ። አንቺም አንብበሺዋል። ስለዚህ አላሳሰበሺም የሚል ድምዳኔ ደርሻለሁ።

ካሁን በፊት በቢሲ ትግርኛ ፕሮግራም ስለ ሴቶች መብት የጻፍሺውን (ቃለ መጠይቅ ?) ያንቺንና የውብዳር አሰፋ 9የገብሩ አስራት ሚስት) ጽሑፎች ወደ ትግርኛ ተርጉመው አንብቤው “ትግርኛ በሚያትሙ ድረገጾች” ላይ እንደ ማሳሰቢያ ጽፌ ነበር። ስለ ሴቶች መቆምሽ ልካም ተግባር እንኳ ቢሆንም አብሮ እንድታይው እና እንዳትረሺው አሳሳቢ በውጭ አገር የተከሰቱ ክስተቶች “በወንድ እምባ የሚደሰቱ፤ ወንድ ሲያነባ ከናቲራ ላይ ፎቶ ለጥፈው ከናቲራ የሚለብሱ መጠን ያለፈ የወንድ ተጋፊዎችንም አብረው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይፈጠሩብን አብረሽ እንድትመለከቺው እንደ ማሳሰቢያ አደራየን ለማሳሰብ የጻፍኩት ነበር” ። ስለዚህ ጽሑፎችቺሺን እከታተላለሁ ለማለት ነው። ዛሬ ስለ አንዳርጋቸው የጻፍሺው አሳስቦኛል። ስለ ሴቶች መብት መቆርቆርሽን ያህል የዜጎች መብት እንደ አንዳርጋቸው የመሳሰሉ ሽምቅ ተዋጊ ታጋዮች መብት ረጋጮችንም ጭምር እንደ የዩኒቨርሲቲ መምህርነትሺንም ጭምር ማሕደራቸው ማጥናትም ይኖርብሻል።

አማራ ‘በመሆናችን’ በግንቦት 7 አንዳርጋቸው እና ብርሃኑ እንዲሆም ኤፍሬም ማዴቦ በተባለው ጸረ አማራው የግንቦት 7 አመራር አባል በደል ደርሶብናል ብንጮህም አፍነውን ነበር አማራን ሲሳደቡ የነበሩ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ‘አቤት’ ብንልም ስብሰባ እንቀመጥ ብንልም፤ የቅሬታ ክስ ማመልከቻ ደብዳቤ ብንጽፍም ‘ዞር በሉ’….ተብለን ኤርትራ ምድርም ከመሰወር እስከ ግርፋት ድረስ ደርሶብን ለሚዲያ ጋዜጠኞች ብናመለከትም (ዘሐበሻ ወኪል -ሱዳን አግኝቶአቸው ስለ እሱ የጻፍኩት ልብ ይለዋል፤ እንዲሁም ኢሳት እና መሰል ሰሚ ወያኔዎች ናቸው እያልዋቸው) ‘እንድንገለል” ተደርጎ የሕሊና ስብራት ደርሶብናለል፡ ብለው ግማሹ የግድያ ዛቻ ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው፤የሚበሉት አጥተው እኔ እራሴም የተቻለኝን ፍራንክ እንዲደርሳቸው አድርጌ “ሲጨንቃቸው” ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በወየኔ ሚዲያ ቀርበው ብሶታቸው ሲናገሩና  ሲጮኹ ያንቺ ሰብአዊ ተሟጋችነት የት ተደብቆ ነበር?

ስለ እነዚህ ሰዎች የጮኽን ሁሉ ባንቺው ብዕር  የአንዳርጋቸው መጽሐፍ የማይወዱት “አማራ ብሔረተኞች” ብለሽ ስም አንደምትለጥፊልን ሳይሆን አንዳርጋቸው ከሻዕቢያ ጋር ሆኖ የዜጎቻችን መብት ሲረግጥ የነበረ ብለን ስለጮኽን አንቺ “የሰብዕና ችግር”፤ “በተቃውሞውም ሆነ በገዥው ጎራ በተሰለፉ አብዛኞቹ ፖለቲከኞቻችን ልቦና ያደረ ክፉ ነቀርሳ…” እያልሽ ብዕርሽን እያቆነጃጀሽ የኛን ጩኸት ልታጥላሊ መሞከረሽ የሚያሳየኝ የስብዕናው ችግር እኛው ጋር ሳይሆን ያለው አንቺው ጋር ነው።

አንዳርጋቸው በድሎናል ‘ሄልኮፕተር በሚባል የግርፋት ስልት ቁልቁል ተዘቅዝቀን እንድንገረፍ “የወንድ ልጅ አምላክ እባካችሁ እርፍት ስጡኝ ስላቸው መላልሰው ሙሉ ቀን በውሃ ጥማት እየተቃጠልኩ ሲገርፉኝ ሲቀጠቅጡኝ ነበር።” ብለው እምባ እያፈሰሱ አንዳርጋቸው ስላስገረፋቸው ዜጎቻችን ነው የጮኽነው! አንዳርጋቸው የጻፈው ‘አማራ ሕዝብ ከየት ወዴት” በሚለው መጽሐፉ ላይ “አማራ ብሔረተኞች” መጽሐፉን አይወዱትም በዚህ በዝርዝር እምለስበታለሁ የምትይው “ቅብጥርጥርዮሽን-እስክናነብልሽ” ምን እንደምታቆነጃጂለት በገጉት እንጠብቅሻለን።

አንቺ ልክ የሴቶችን መብት መረገጥ እንደሚያምሽ ሁሉ እኛም ‘የወንድ ልጅ እምባ” ያሳምመናል ያንገበግበናል። ለአንዳርጋቸው መፈታት መታሰር መቆርቆር መታገል ሌላ ነገር ነው፤ ግን አንዳርጋቸው “የአገር ሃብት” ፤ “የነፃነት ታጋይ ፤ የሰው ልጅ መብት ተሟጋች” የምትይው ቅጥያ “ከቅጥያ” አያልፍም። አንዳርጋቸው ጽጌ ኤርትራ ምድር ተቀምጦ ከነ ሻዕቢያው ኮለኔል ፍጹም፤ከነ ዳዊት ጋር ሆኖ በወሰደው እርምጃ  ኢትዮጵያዊ የወንድ ልጅ እምባ እንደ ጎርፍ ሲፈስስ በቀዳነው አውድዮ ስናደምጥ አስቆጥቶናል። አንዳርጋቸውሽ የተሳተፈባቸው ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ የዜጎቻችን ጥሰት በውብ አማርኛሽ ስለ አንዳርጋቸው ሰብአዊነት በማስረጃ ማፍረስ ብትቺይ ምንኛ ደስ ባለኝ፡ ግን አትችይም! ያንቺው ዓይነት ውብ አማርኛ ጸሐፍቶች ብዙ ሰዎች ሞክረዋል።አልተቻላቸውም። የሰው ልጅ የግፍ እምባ ብታደርቀውም መልሶ ይፈሳል። አንዳርጋቸው ‘አምበሳ’ ተብሏል አንቺም ‘የአገር ሃብት’ ብለሺዋል፤ ሌሎቹም ‘ማንዴላ” ብለውታል፡ አውነታው ግን እውነት ለጊዜው እንድትጎነበስ ሊደረግ ይደረግ እንደሆን እንጂ በብዕር ጋጋታ፤ በስመ ዝናነት እውነትን ’ማጥፋት’ አይቻላችሁም።

ይህንን ስትይ ግን እውነት ካንጀቲሽ ነው? “(አንዳርጋቸው) የሰብአዊ መብት ረገጣን የሚጠየፍ…. ፤ ፊት ለፊት የሚሞግት የኢትዮጵያዊ ሁሉ ጠበቃ ነው፡፡ ብለሽ ተሟግተሺለታል።ሰብአዊ መብት ረገጣ ተጠያፊውና ኢትዮጵያዊ ሁሉ ጠበቃነቱን በተዋጣለት ብዕርሽ የሰው መብት ረገጣ ተጠያፊ’ ያደረግሺውን ስለ አንዳረጋቸው ትንሽ ምልክት ልስጥሽ። ብራስል ውስጥ ያለው እውንተኛው የሰው ልጅ መብት ጠበቃ ወጣቱ ብልህ ሰው “ያሬድ ሃይለማርያም” ስለ ጉዳዩ በሚመለከት ያለውን ልብ እንድትይበት እፈልጋለሁ። ኤርትራ ውስጥ አብረው አንዳርጋቸውን አምነው ሲታገሉ አንዳርጋቸው ለስቃይ የዳረጋቸው ሰዎችን ሁኔታ አስመለክቶ እንዲህ ያለውን ላስነብብሽ እና ምናልባትም የጀመረሽውን አጠያያቂ ውዳሴሽ ለማቆም ቢረዳሽ በዚህ ልደምድም።

የሰው ልጆች መብት ጠበቃ ወጣቱ አቶ ያሬድ ሃይለማርያም እንዲህ ይላል።
“ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ ጊዜያት በዶ/ ብርሃኑ እና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሚመራው ግንቦት 7 የቀረበላቸውን የትግል ጥሪ በመቀበል እና በድርጅቱና በአመራሮቹ ላይም እምነት ያደረባቸውና አገራቸው ነፃ እንድትወጣ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ፣ ከተለያዩ የአፍሪቃ አገራትና ከአውሮፓ ተመልምለው በኢሳያስ አፎርቄ መንግሥት ትብብር ወደ ኤርትራ ከተወሰዱ በኋላ ለከፋ የሰብአዊ መብት እረገጣ የተዳረጉ መሆኑን ተበዳዮቹ በአንደበታቸ የደረሰባቸውን ስቃይና እንግልት እያነቡ ገልጸዋል።

 እነኚህ ግለሰቦች ወደ ኤርትራ ከመጓዛቸው በፊት በግንቦት 7 አመራር አባላት ተደጋግሞ በኤርትራ ስላለው ሁኔታ እና ስለድርጅቱ አቋም ብዙ ነገር እንደተነገራቸው፤ ይሁንና የተነገራቸ ነገር ሁሉ ሥፍራው ላይ ሲደርሱ ሃሰት ሆኖ ማግኘታቸው፤ እንዲሁም የድርጅቱን ዝርክርክ አሰራርና ብልሹ አመራር አስመልክተው ጥያቄዎች በማንሳታቸው የተነሳ በግንቦት 7 አመራሮች ከተፈጸመባቸ በደል ባሻገር በቅጣት መልክ ተላልፈው ለኤርትራ የፀጥታ ኃይል መሰጠታቸውን ገልጸዋል። በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር ሆነውም እጅግ ለከፋ የእስር ሁኔታ፣ ለድብደባና የማሰቃየት ተግባር፣ ለበሽታና ለርሃብ የተዳረጉ መሆኑን፤ እንዲሁም ከመካከላቸው የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውን ነው ዝርዝር ማስረጃቾችን በመጥቀስ ገልጸዋል። በአሁን ወቅት በእስር ላይ ከሚገኙትም መካከል የአ.. ዩንቨርሲቲ ምሩቅ የሆነው አቶ ትእግስቱ ብርሃኑ እና አብረውት የሚገኙ ሌሎች እስረኞች በማናቸውም ጊዜ በኤርትራ መንግሥት ሊገደሉ እንደሚችሉ የወጡት ዘገባዎች ይጠቁማሉ።

በግንቦት 7 እና በኤርትራ መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጥቃት ሰለባ የሆኑት አብዛኛዎቹ ግለሰቦች በቅርቡ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይልበሚል ለአንድ አመት ያህል በበርካታ ድኅረ-ገጾች፤ በተለይም የኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮሁለገብጋዜጠኞች አማካኝነት በርካታ ፕሮግራሞችን እየተዘጋጁ ያስተዋውቁን የነበረው ቡድን አባላት ናቸው። እንደውም አንዳንዶቹ በነዚህ የመገናኛ ብዙሃን በስልክ እንዲቀርቡ እየተደረገ የወሬ ዘመቻውን ነጋሪት ጎሣሚዎች ነበሩ።
 
ዛሬ እነዚህ ወገኖች ህይወታቸው በአደጋ ላይ ሲወድቅ እናየከፋ የመብት እረገጣ ተፈጽሞብናል፣ ተሰቃይተናል፣ ነፍሳችንን አድኑን፣ ግንቦት 7 ከኤርትራ መንግሥት ጋር በመሆን የሚፈጽመውን ሕገ ወጥ ተግባራትና በገዛ አባላቱ ላይ የሚያደርሰውን አፈናና ወከባ ሕዝብ ይወቅልን፣ ሌሎች ወገኖቻችንም እውነተኛ ትግል ያለ መስሏቸው ተታለው ወደ ኤርትራ ምድር እንዳይሄዱና እኛን የገጠመን አይነት መከራ እንዳይደርስባቸው ታደጉዋቸውበሚል ጥሪ ሲያቀርቡ የሰማቸ ያለ አይመስለኝም።

 እርግጥ ነው የግንቦት 7 ልሳን የሆነውኢሳትእንዲህ ያሉ የሕዝብ ብሶቶችን በካድሬ መነጽር ስለሆነ የሚመነዝረው ምንም እንኳን ጉዳዩ ኢትዮጵያዊያንን እና ኢትዮጵያን የሚመለከት ቢሆንም የግንቦት 7 አካሄድ የሚያደናቀፍ ወይም የሚገታ መስሎ የታየውን ማንኛውንም ጉዳይ ለማስተናገድ ተፈጥሮው ስለማይፈቅድለት በድርጅት ልሳንነቱ ልንተወው እንችላለን። ይሁንና በውስጡ የሚሰሩትጋዜጠኞችለእንዲህ አይነቱ ጉዳይ የሚራራ ልቦና እና እውነቱን ለሕዝብ እንዲታወቅ ለማድረግ የሚያስችል መንፈሳዊ ብርታት ማጣታቸው ግን ትንሽ ያስገርማል። ይህ አይነቱ ክሽፈት በኢሳትና በኢሳት ጋዜጠኞች ብቻ ሳይሆን በሌሎች በእዚሁ ሙያ የተሰማሩ የሕዝብ የመረጃ ምንጭ ለመሆን ለራሳቸው ቃል ገብተው የተለያዩ የመገናኛ መድረኮችን የተቆጣጠሩ ባለሙያዎች ተመሳሳይ ግርዶሽ ውስጥ መሆናቸው ከማስገረም አልፎ የሚያሳስብ ነው።

ግንቦት 7 በተመለከተ እና በተለይም የድርጅቱ አመራ አባላት ከላይ የተጠቀሱትን ንጹሐን ዜጎችን በነፃነት ትግልስም ወደ ኤርትራ እየወሰዱ እያደረሱባቸው ስላለው በደል እና ግፍ ወደፊት በዝርዝር እመለስበታለሁ በዝርዝር ስል የተበዳዮችን ማንነት፣ የደረሰባቸን የመብት እረገጣ፣ በማን እና እንዴት፣ የግንቦት 7 አመራሮች ያላቸውን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ተሳትፎ፣ ስንት ሰዎች በእስር እንደተጉላሉ፣ ስንቶች ሕይወታቸው እንዳለፈ፣ ስንቶች ከኬንያ ተመልምለው ወደ ኤርትራ ከተወሰዱ በኋላ ይህ ነው ያማይባል ስቃይና መከራ አይተው በድጋሚ ከኤርትራ ተወስደው በኡጋንዳና በኬንያ ከተሞች እንደተበተኑ እና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን ወደፊት ሁኔታው እንዳመቸ ለሕዝብ ይፋ አደርጋለሁ። 

 ለነገሩ ይህ አይነቱ በዜጎች ሕይወትና ተስፋ የመቀለዱ ተግባር የተጀመረው ዛሬ ሳይሆን ገና ግንቦት 7 ለማቋቋም ሸርጉድ ከሚባልበት ጊዜ ጀምሮ ስለሆነ ታሪኩ ብዙ ነው። የብዙ ወጣት ኢትዮጵያዊያኖችም ሕይወት በዚህ መያዣና መጨበጫ በሌለው የግንቦት 7 ቅዥት ተደናቅፏል፣ በርካቶችም ለወያኔ የደህንነት ኃይሎች ሲሳይ ሆነውና በሽብርተኝነት ተወንጅለው በሃሰት የበርካታ አመታት እሥራትን ተከናንበው በየማጎሪያ ቤቱ ፍዳቸውን እይቆጠሩ የገኛሉ፤ ከታሳሪዎቹ መካከል የተወሰኑት ቤተሰቦቻቸውም ተበትነዋል።

እንግዲህ ነፃነትን የማያውቁት ገዢዎቻችን ብቻ ሳይሆኑነፃ አውጪዎቻችንምጭምር እንደሆኑ ልብ ልንል የገባል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በመጽሐፋቸው ርዕስነፃነትን የማያውቁ ነፃ አውጪዎችበሚል የገለጹት የገዢው መንግሥት ባህሪ እርሳቸውንና ድርጅታቸውንም የተጠናወተው መሆኑ ልብ ሊሉ ይገባል። ለዚህም እርቀን መሄድ ሳያሻ በቅርቡ ከወደ አስመራ ብቅ ብለው የራሱን ሕዝብ በማፈን፣ በማሰቃየት፣ ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን በማዋከብ፣ በመግደልና ለአመታት አስሮ በማሰቃየት፤ በጥቅሉ ሰብአዊ መብቶችን በከፋ ሁኔታ በመጣስ አለም ያወቀውን አንባገነናዊ የአቶ ኢሳያስን አስተዳደር ሲያሞካሹና ዲሞክራት አድርገ ሲያቀርቡ ሰምተናል ለዚህ ምስክርነታቸው ከበርካታ ኤርትራዊያን እና ለሰብአዊ መብቶች መከበር ከቆሙ ኢትዮጵያዊያን በቂ ምላሽ ስለተሰጣቸው በዚህ ጉዳይ ብዙ ከማለት እቆጥባለው። ነገር ግን እሳቸውንም ሆነ ድርጅታቸውን ለማሳሰብ የምወደው የኤርትራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ባለው ግፍ እና መከር በዚ መልኩ መሳለቅ፤ እንዲሁም የአቶ ኢሳያስ መንግስት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ደባና የመብት እረገጣ ችላ በማለት አብሮ መቆም ወደፊት በታሪክም ሆነ በሕግ እሳቸውን፣ ድርጅታቸውን እና የአመራር አባላቱን የሚያሰጠይቃቸው መሆኑን ነው
 
ለነገሩ ይህ ሂደት ባጭሩ ታሪክ እራሱን እየደገመ እንደሆነ ነው የሚያሳየው። የአንባገነኑን የደርግን ሥፍራ ወያኔ ከነ ጎሰኝነት መርዙ፣ የወያኔን በሻቢያ ጉያ ስር ተወሽቆ ኢትዮጵያን የማተራመሱን ተግባር የዛሬው ታጣቂ ግንቦት 7 ሻቢያ ያንኑ ቦታውን ሳይለቅ ገዢም፣ ነጻ አውጭም፣ ተባባሪው ሻቢያም አንድም ሦስትም ሆነው ቀጥለዋል። ሰብአዊ መብቶችን፣ ዲሞክራሲን፣ ፍትሕንና የሕግ የበላይነትን በተመለከተ በነዚህ አካላት መካከል ምንም አይነት ልዩነት አይታይም። አንድ አይነት ባህሪይ ነው የሚታይባቸው። ልዩነታቸው የሚገኙበት ሥርፍራና ድርጅታው ተልኳቸው ነው። ተልኳቸም የሚያስፈጽሙበት መንገድ ግን ከሞላ ጎደል አንድ ነው።…” የግንቦት 7 የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታያሬድ ኃይለማርያም   (ጥር 29 ቀን 2006 ..ከብራስል) Human Rights in Ethiopia) (ቢጫ ቀለም እና ሰረዝ የተጨመረ።)

የግንቦት 7 የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታያሬድ ኃይለማርያም   (ጥር 29 ቀን 2006 ..ከብራስል) Human Rights in Ethiopia)

አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)