Monday, December 21, 2009

ይልቁኑስ እርስዎ……

ይልቁኑስ እርስዎ…… ጌታቸዉ ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com ለዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ መልስ

ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ የጥንቱ “ፋፋ” ፋብሪካ ስራስኪያጅ ወያነ ትግራይ “በብሬክ ሱሩ” የሽምቅ ዉግያ በማካሄድ ወደ ሥልጣን ከመጣ በሗላም የወያነ ትግራይ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኛ የነበረዉ የዶክተር አስራት ወልደየስ ቀንደኛዉ ጠላት የነበረዉ የዳኛ መስፍን ግርማ (ምናልባትም የነ ሓጎስም) የቅርብ ጓደኛ እና አድናቂ ይመስላሉ፣፣ ዳኛ ወለወደሚካኤል መሸሻ በብዙዎቻችን በመጨረሻ ሰዓት በሰሯት አስመስጋኝ ጀግንነት ሁላችንም ልባችን ተነክቶ ያርበኝነት አቀባበል አድርገንላቸዉ በየከተማዉ ያለችንን ያቅማችን ገንዘብ በማዋጣት የክብር እንግዳችን ሆነዉ ካከበርናቸዉ አንዱ ነበሩ፣፣ ሳያቸዉ ሰዉየዉ ቀና ለፍትህ የቆሙ እና በጣም አስተዋይ መስለዉኝ ነበር እንጂ እንደዚሁ ቅሌት ዉስጥ ራሳቸዉን በማስገባት ከኩዴታ ፈጻሚ ጀኔራሎች/ወታደሮች (በዛ ዉስጥ ያለፍትህ በኩዴታ ፈጻሚዎቹ እጅ ባሰቃቂ ዐልቂት የተፈጁ ነብሳት ክብደት ሳይሰጡ) እስከ ብረሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸዉ ጽጌ እስከ ስዬ እና ነጋሶ ጊዳዳ…… ለእኚህ ከፍተኛ ዳኛ ሁሉም “እምየ” መሆናቸዉን ሳይሸሽጉ በህዋ ሰሌዳ ዉስጥ ስሜታቸዉን መዘክዘካቸዉ ሳነብብ “እዉነት ‘የሕግ’ ሰዉ ወይስ ፖለቲከኛ ነበሩ”? ብየ ነዉ ራሴን የጠየቅኩት፣፣ ፖለቲከኛ ከሆኑ “Deliberate Deception” (የተጠና የማሞኝያ ስልት) በመጠቀም ነባራዊዉን ሁኔታ በፖለቲከኛዉ ሥር እንዲዉል የሚጠቀምበት ዓይነተኛ መንገድ (role) ነዉና እንዲያ ቢያደርጉ የተለመደ ባሕሪይ ነዉ፣፣ ነገር ግን እኒህ ሰዉ በሙያቸዉ “የሕግ” ባለሙያ እንጂ ፖለቲከኛ አይመስለኝም (ለመሆን መብታቸዉ የተጠበቀ ቢሆንም)፣፣ የሕግ ሰዉ ደግሞ “በሃቅ እና በዉሸት” መካከል ግጭት ሲታይ የማየት ሕሊና ያለዉ ሰዉ ነዉ፣ ፣ የሕግ ሰዉ አንዴ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ከሃቅ መራቅ አይችልም፣- ሙያዉ አያስገድደዉም እና፣፣ ሁሌም ዉሸትን ሲያገለግል ከርሞ በአንድ ወቅት ዕዉነት ስለፈረደ ወይም ከእዉነት ጋር ስለተጎዘጎዘ “ዉሸትን ሲያገልግል ከርሞ (ዓመታት እንበለዉ) በዛች ባንድ ወቅት የፈጸማት ጀግንነት ምክንያት “confidence” እምነት እንኳ ማሳደር ቢቻልም ፣ የሰዉየዉ ያንድ ወቅት ጀግንነት በመንተራስ ከዚህ ወዲያ ዉሸትን ማገልገል አይቻላቸዉም ብለን መደምደም አይቻለንም እና የዳኛ ወልደሚካኤል ጽሁፎች የያዙት መልክቶች እና አስተያየቶች ስንከታተል ፈረንጆች Distorted የሚሉዋቸዉ ወይንም ባበሻችን “የተሸዋረሩ” መልእክቶች የምንላቸዉ ለማስተላለፍ ሞክረዋል። በተለይ ነጋሶ እና በስየ አብርሃ ላይ እየተደረገ ያለዉ እሰጥ አገባ አልወደድኩትመ በማለት ለነዚህ የወያኔ ከፍተኛ ሹሟምንቶች ጥብቅና በመቆም ለመከላከል ያሳዩበት አንዳነድ ሃሳቦቻቸዉን አንስተን እንወያይ፣፣ ዳኛ ወልደሚካኤል እና የተቀሩት ጓደቻቸዉ በግንቦት 7 እና በዲያስፖራዉ ልዩ “የኤሊት- ቡድን” ስበት ዉስጥ እንዳሉ ምልክቶች አይተናል፣፣ ቢሆንም ሌሎቹ እንደ ዳኛ ወልደሚካኤል “ጉርጥ ዓይን” አዉጥተዉ በዲያስፖራዉ “ወልጋዳዉ ኤሊት” (distorted elite) ጥላ (Shield) ሥር ሙሉ በሙሉ በመጠለል “አለሁ - አለሁ’ አላሉም፣፣ ሌሎቹ ጓዶቻቸዉ የዉጪዉን ሚዛን ፣ባሕሪ ለማጥናት ረጋ ብለዉ እየወሰዱት ያሉትን ሚዛን የሚያስመሰግናቸዉ ሲሆን ባንጻሩ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ግን “… እየተስተዋለ ” የሚለዉን ተመልሰዉ እኛኑን “እየተስተዋለ..” (ስየን እና ነጋሶን” አትነካኩ በማለት ጥልቅ እያሉ የሚሰነዝራቸዉ አስተያየቶች እኛም ስላልወደድንለዎት “ይልቁኑስ እርስዎ ረጋ ይበሉ” እንላለን፣፣ ዳኛ ወልደሚካኤል አስቀድሜ እንደገለጽኩት በ1995 ግንቦት ምርጫ ምክንያት የተከተለዉ በወያነ ትግራይ መንግሥት ወታደሮች ጥይት ከሕግ ዉጭ የሰዉ ሕይት መጥፋቱ እና ለሕይወት እና ሰብአዊ ጥሰት ተጠያቂነቱ በማን ላይ እንደሆነ ለማጣራት ሲያገልግሉት በነበረዉ በመንግሥታቸዉ ታዝዘዉ ተመድበዉ ያስገኙት አርበኛዊ የፍትህ ዉጤት ( ሰኔ 27/2006 ፣- 8 ለ 2 ድምጽ ዉሳኔ በማሰለፍ መንግሥት ተጠያቂ ነዉ በማለት ከ8ንቱ አንዱ በመሆን ድምጽ ሰጥተዋል) በክብር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሰዉየዉ በቅርቡ ኢትዬ ፎሩም በተባለዉ ኢንተርኔት “አረ እየተስተዋለ …” በሚል ርዕስ ባስተላለፉት መልዕክት ለመቀበል ችግር አለብኝ፣፣ አንዳንዶቻችሁ ዳኛዉ የፈጸሙት አስመስጋኝ “ጀግንንት” ምንድነዉ እንዳትሉ እራሳቸዉ ባዉሮጳ ሕብረት ባለስልጣናት ዘንድ በአካል ተገኝተዉ የሰጡትን ቃለ ምስክርነት ልጥቀስ እና ወደ ሌላዉ ኩረቴ እንሰጋገራለን፣፣ Woldemickael Meshesha “Finally, I would like to ask the democratic countries especially the Eu in the name of those 193 innocent civilian, who were murdered in cold blood, and 680 who were suffering of life- threatened bullet wounds, and in the name of political leaders and members, journalists civil society and human rights leaders suffering in jail for unfounded reasons that the government officials who are directly or indirectly should be made responsible and face justice.I thank you for your attention.” (Woldemichael Meshesha). የዛሬዉን ሳናይ በትናንቱ መነጽር ብቻ እያየን ማዉገዝ ሲቀናን ማስተዋል ሰንበትበት አለ፣ ስለዚህም እየሰማሁ አላስችል አለኝ እና “አረ እየተስተዋለ…” በማለት ወንጀል በሰሩ የወያኔ ቀንደኛ ሰዎች እና ተባባሪዎቻቸዉ ላይ ዉገዘታችሁን አቁሙ ይሉናል “ዳኛዉ”፣፣ እኔ የገረመኝ እራሳቸዉን በዛ “አታዉግዟቸዉ” በሚሉት ቡድን ዉጭ በማስቀመጥ የነሱ ቡድን ማለትም የወያኔ መንግሥት የጭካኔ መዋቅር (ኢንስቲትዩሽን) ኣባል ሆነዉ እንዳላገለገሉ ቆጥረዉ “የተወሰኑ ሰዎች ስም በመጥቀስ” አታዉግዟቸዉ” ማለቱ ሲገርመኝ፣፣ እራሳቸዉ “አታዉግዙን’ ብለዉ ላለመቅረባቸዉ እሳቸዉስ ማን ነበሩና ነዉ እራሳቸዉን ከቡዱኑ አስወጥተዉ እንደተመልካች ሆነዉ “አታዉግዟቸዉ” እያሉን ያሉት? ዳኛ ወልደሚካል፣ ከርስዎ የሚጠበቅ ሃላፊነት ወደ መጨረሻዉ ሰዓትዎ ፈጸሙት እንጂ ከዛ በፊት እኮ ምን ይሰሩ እንደነበር በዝርዝር አልነገሩንም’ኮ፣፣ በእርስዎ ብዕር እና ዉሳኔ የተላለፉ ታላላቅ የሕግ ዉሳኔዎች አልነበሩም? ምነዋ በሰየ አብርሃ ታሪክ ብቻ ታጥረዉ ለብዙ ዓመታት በሕጉ ክፍል ተሰይመዉ ያገለገሉትን ወያኔ ትግራይን በእርስዎ እዉቅና ዉሳኔ የተከናወኑ የክስ እና የዉሳኔ መዛግብት እንደዚሁ አሳጠሩት? ከሕግ ሰዉ ሚጠበቀዉ ባለፈዉ ጊዜ ያከናወናቸዉ ጮርቃ ዉሳኔዎች እና በሳላም ሆኑ ጎጂ ዉሳኔዎች ለሕብረተሰቡ ዘግቦ ማቅረብ ተገቢ እና የሚጠበቅም ነዉ፣፣ እረስዎ ግን አስታራቂ እና መካሪ መስለዉ ይገቡ እና “ከእምየዎችዎ” ከእነ “ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸዉ ጽጌ” የቀሰሙትን የጭቃ ጅረፍዎን በታየ ወልደሰማያት እና በሃይሉ ሻዉል ማስጮህ ጀመሩ፣፣ ለመሆኑ ከአንድ የሕግ ምሁር ያዉም ወያኔን ለሚያክል ክፉ “አራዊት” በፍትህ መንበር ተቀምጦ ሲፈጽም እና ሲያስፈጽም የነበረ ብዙ ማስተዋል እና እርጋታ ከሚጠበቅበት እንደርስዎ ያለዉ የሕግ ምሁር በእንደዚህ ዓይነት “ሸርተቴ” ደፍረዉ ደጋግመዉ መመላለስዎ ድፍረትዎ ባደንቀዉም “እየተስተዋለ” የሚለዉ ምዕዳንዎ ለራስዎ ቢጠቀሙበት የተሻለ ነዉ እላለሁ፣፣ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ የሰዉ ልጅ እንደ ዓራዊት ባንድ አዳራሽ አስገብቶ በጥይት የሚቆሉትን ወታደሮ ሁሉ ጀግኖች እያሉ አነ ፕሮፌሰር አስራትን በእስር ቤት በሃሰት ተከስሰዉ ለሃሰተኛዉ ክስ ሕይወት በመስጠት ለስቃይ እንዲዳረጉ እና አያሌ ስማቸዉ ያልተዘገቡ የእነ መሰፍን ግርማ ፍርደገምድል ሰለባዎች ክበር ሳይሰጡ ፣- መስፍን ግርማ ምንም እንኳ ትግሬ ይሁን እንጂ “ወያኔ ይጠላ ነበር” በማለት በመከላከል የመሰከሩለት የጥንት ጋሻጃገሬዎ አቶ መስፍን ወያኔ ከገባ ጀምሮ በፍትህ መንበር ተቀምጦ ምን ይሰራ እንደነበር ለምን ሸሸጉን? የፍረድ ቤቶች ኢፍትሃዊነት በ1987 ዓ.ም እስከ 1990 ከዚያም ቀጥሎ ነበር እርስዎ ለቅቀዉ እስከወቱ ድረስ እስካሁንም ድረስ አለ።.- እነ ታለጌታ፣ ዶ/ር ታየ አቶ ገብረጻዲቅ ሃይለማርያም መቶ አለቃ ጫኔ ወዘተ..ወዘተ…በድብደባ የጥርስ ዉልቃት ፣የኮረንቲ ሰቆቃ የመሳሰሉት ሁሉ ሲደርስባቸዉ እርስዎ የወያኔ የፍትህ አካል አገልጋይ ነበሩ አልነበሩም? መስፍን በወቅቱ እንዚህ ሰዎች በሃሰት የተቀነባበረ ክስ ሲቀርብባቸዉ የርስዎ ወዳጅ መስፍን የነማን ጉዳይ ይዞ ነበር? ምነዋ እርስዎ በፒለቲካ ቅልጥፍናዎን ለማሳየት በሸርተቴዉ ከመመላለስ እና ከመጣደፍ ይልቅ የተደበቁ የፍትሕ ታሪኮች ለጆሮአችን ቢያሰሙን አይበጅም ነበር? የተደበቀ የፍትህ ታሪክ አያዉቁም አንልም፣ እንኳን አርስዎ ከ “ፋፋ” ኩባንያ አስተዳዳሪነት ወጥቶ በወያነ ትግራይ መንገሥት ያገሪቱ ከፍተኛ ፍረድቤት ዳኛ ሆኖ የዜጎች ሕይወት እና የጨቋኙን ሥርዓት ግንኙነት በብዕሩ እና በሕሊናዉ በ ዓይኑ በግብር የቃኘ የወሰነ የመረመረ የተመለከተ፣ ቀርቶ ተራ ዜጋ እንኳ የፍረድቤቶች ዉሎ ታሪኮች እና ዘገባዎች እንደ እርስዎ ጠለቅ ብሎ ባይሆንም ከሚዘገቡት የፍረድ ቤት ዉሎዎች ካነበባቸዉ ጋዜጦች ያዉቃል፣፣ ትግሬዉ መስፍን ግርማ ምንም እንኳ ትገሬ ቢሆንም የወያኔ አካሄድ አላማረዉም ነበር በማለት የፍትህ ሰዉ ነበር ሲሉ የነገሩንን የሥራ ባልደረባዎ በነበረቺዉ በብርቱካን መዲቅሳ አንደበት የተነገረለት ስለመስፍን ግርማ ከዚህ በታች ያንብቡ። የኢሚግሬሽን ሃላፊ በሙስና ጉዳይ እኛ ችሎት ቀርበዉ ነበር።የጊዜ ቀጠሮ ሰጠንና ምርመራዉ ሲጠናቀቅ አቃቤ ሕግም አልቃወምም ብሎ በዋስትና ለቀቅናቸዉ። በወቅቱ የነበሩት ሚ/ር ወረደወልድ ምክትላቸዉ አቶ መስፍን ግርማ (አሁን በሕይወት የሉም) ጉዳዩን በጣም ሊያጮሁት ሞክረዉ ነበር። አቶ መስፍን “ጁሪስ ፕሩደንስ (የሕግ ፍልስፍና ማለት ነዉ) ያለ እንዳይመስላችሁ” በማለት ለ አቶ መንበረ ፀሃይ ነገሩ። አቶ መንበረም ለምን እንዲህ አደረጋችሁ በማለት ጥያቄ አቀረቡ። ሁሉም ነገር አስረዳናቸዉ። ጉዳዩን ሲያዩ ምንም የሚያከራክር ነገር አልነበረም። ያሚግሬሽን ሃላፊዉ፣ አልተለቀቁም ነበር። ፍ/ቤት ቀረቡና እንዲለቀቁ አድርገናል።” ይህ በብርቱካን የተነገረ ታሪክ ነዉ። በሌሎች ደግሞ ሌላ ሊኖር እንደሚችል አርግጠኛ ነኝ። ታዲያ ምነዋ እርስዎ ይህንን የፖለቲካ የሸርተቴ ጎዳና መመላለሱን ቢተዉትና ስለ ነበረዉ የፍትህ ብልሽት እና የእርስዎ ሚና ቢያስተምሩን ምን ነበረበት?

የተከበሩ ዳኛ ወልደሚካኤል ሆይ፣- ለመሆኑ ጋዙጦች ሲታሰሩበት ሲንገላቱበት የነበረዉ ዋነናዉ ምክንያት ያስታዉሳሉ? እርስዎ እና እንደ እርስዎ የመሳሰሉት ዳኞች ወያኔን ሲያገለግሉ በነበረበት ወቅት ሲያዩት ነበሩት እና ሲያዳምጡት የነበረዉን የድሆች ፣የወያኔ ትግራይ ሰለባዎች እንባ ሲዘግቡ በመያዛቸዉ ነዉ፣፣ ያቺን አንድ ቀን አርበኝነትዎ እንዳለ ሆኖ፣ ከ እርስዎ እኮ ብዙ ይጠበቃል፣፣ ማን ምን እንደወሰነ ማን ምን ስለሰራ ወደ መግደያ ወደ አስር ወደ ስቃይ ገንዳ እንደተላለፈ፣ ያገሪቱ ባለሥልጠናት ሲመዘብሩት ነበረዉን ንብረት የት ይሸጋገር እንደነበር ለምን አልነገሩንም? መቶ አለቃ አበረ አዳሙ እንኳ የሚያዉቁትን ያክል ብዙ የፍትህ ብልሽት ማሕደሮች በመዘርዘር በምርመራ ጣቢያ ጽ/ቤቱ በሕዝብ እና በፖሊሶች ምርመራ ክትትል ተከስሰዉ የቀረቡትን የባለሥልታኖች ስም ዘር እና የፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሌቦች ጋር በመመሳጠር የነበረዉ ሰንሰለት እንዴት ያለ ዘረፋ ይፈጸም እንደነበረ እና መንግሥት ተብየዉ ያስቀመጣቸዉ ዳኞች በፍትሕ ተቋሟት ላይ ምን ይፈጽሙ እንደነበረና ዘራፊ እና ሌቦች ባለሥልጣናችን ምን ዓይነት ከለላ ያደርጉላቸዉ እንደነበረ በዝርዝር ገልጸልናል፣፣ (መቶ አለቃ አበረ ዕድሜህ አማልክ ያስረዝመዉ ትግልህንም ይስመር እላለሁ)፣፣ ምናዋ ክቡር ዳኛ ወልደሚካል ትንሽ አንኳ እንደ እነ ገብረመድህን አርአያ የወያኔን ጉድ እንዘረዘሩት እርስዋ በከፍተኛ የወያኔ የፍትሕ ተቋም ተሹመዉ ለብዙ ዓመታት ሲያገለግሉ ቆይተዉ የተደበቁ ማሕደሮች ቢያካፍሉን? ፍስሃ ሃይለማርያም እንኳ የፕሮፌሰር አስራት ዶሴ እንዴት ተቀነባብሮ ለሞት እንደተዳረጉ እና እነ ማን በዛ ወንጀል እንደተሳተፉ ብሎም ፍረድ ቤቶች ምን ሚና እንደተጫወቱ ለታሪክ ትቶልን በወያ ጥይት ከዚህ ዓለም ሲወገድ እንደ እርስዎ የመሳሰሉት ታላላቅ ዳኞች ጋዜጠኞች ሊያገኛቸዉ ያልቻሉትን ታላለቅ ድብቅ ፍርደገምድል ዉሳኔዎች እና “የታሸጉ የፍርድ ምስጢሮች” ጀባ ቢሉን?

እርስዎም ሆነ ገብሩ ወይንም ስየ እና ሌሎቻችሁ ባንድ ሥርዓት ላንድ “ወያነ ትግራይ ለተባለ ዓራዊት” በማደር ስታገለግሉት እንደነበር ይታወቃል፣፣ ከ እናንተ እና መሰሎቻችሁ የሚጠበቃዉ በ አንድ ጉዳይ ማጋለጥ የሚወሰን ሳይሆን በፍትሕ እና በሰዉ ልጆች፣ በዜጎች ሕይወት ላይ የመኖር አለመኖር ዉሳኔ በመስጠት የመጨረሻ ዉሳኔ በማስተላለፍ ከፈጣሪ ሳይሆን ከፈጣሪ በላይ ወሳኞች እንደነባራችሁ ማለትም ያንድ ዜጋ ሕይወት ከነቤተሰቦቹ ጨምሮ በናንተ ያንዲት ዲቂቃ ዉሳኔ የተመረኮዘ እንደነበረ ከእርስዎ የተጋረደ አይደለም፣፣ ስለዚህ እናንተ ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ የሰዉ ሕይወት ደም የፈሰሰበት እና ሰቆቃ የተላለፈበት ስርዓት ስለነበር እናንተን የሚያወግዙ ዜጎች ሲገኙ እንደ በታኝ እንደ እርጉም አድረጎ የመመልከቱን ባሕሪአችሁን አቁሙ እንላለን፣፣ ከናንተ የምንጠይቀዉ “ይቅርታችሁን ለዜጎች መጠየቅ” ካልወደዳችሁት ገደል ጨምሩት! ከናንተ የምንጠብቀዉ ብያንስ “ሰዉን አትነካኩ” ነዉ፣፣ የናንተ ሰለባ የነበረ እና ብዙ ቤተሰብ በዘነዚህ ነብሰ ገዳዬች የተገረፉበተር እና የተሰወሩበት አድራሻቸዉ ያልታወቀ ጠፍተዉ የቀሩ በናፍቆት ሌት ተቀን ሚሰቃዩት ቤተሰቦቻቸዉን እና በናንተ ሥርዓት ታስረዉ ተገርፈዉ ተንገላትተዉ ኑሯቸዉ የተበላሸባቸዉን ዜጎች ክብር ስጡ “አትተነኳኩሱ” ነዉ የኛ ልመናችን “ክቡር ዳኛ ሆይ!”፣፣

ብርቱካን እንኳ ሳትሸሽግ ለ5 ዓመት ከዛም በላይ ከስየ ጋር የተያያዙ የባንክ ሠራተኞች እንደዘሁም ከሱኳር ንግድ የተያያዘ የሃሰት ክስ ተመስርቶባቸዉ በቀጠሮ በይደር ተጉላልቶ ነገሩ ወደ ሌላ ፍረድቤት ከተላለፈ በሗላ የዋስትና መብት የሚያግድ አዋጅ በመዉጣቱ ለረዢም ዓመታትበ ታስረዉ በነፃ ስለተለቀቁ ሰዎች ጉዳይ “ጊሊቲነስ” ጸጸት እንዳደረባት ገልጻለች። ይሄ ልባምነት እና ንፀህነትን ያሳያል። ያገሪቱ እና የዓለም ታለላቅ ሰዎች የተባሉ ኢትዬኦጵያዊአን ዜጎች እንደ እነ ማሞ ወልዴ የመሳሰሉት እኮ ታሪካቸዉን ሳናዉቅ ታስረዉ ተንገላትተዉ ከዚህ ኣለም ተሰናብተዋል። ዳኛ ነዎት እና ለምን ስለ እነሱ ዓያወጉንም? እነ አበራ የማነአብ የመሳሰሉት ኤርትራዊ ኢትዬጵያዊያን አስካሁን ታጉረዋል፤ እነ ፊታዉራሪ መኮንን ዶሪም አሁንም አሉ ይሙቱ ይኑሩ አናዉቅም። ስለነሱ ያዉጉን እንጂ? እንደ እናንተዉ ያሉ የሕግ ሰዎች ካልነገሩን ታሪካቸዉ ማን ይናገር? ከዳኞች እኮ ብዙ ይጠበቃል። አንድ ስለ የመን አምባሲ ጉዳይ ሲገልጽ የነበረ በዲፕሎማሲዉ ረገድ ተሰልፎ የነበረ ሰዉ የተቻለዉን ለማስተማር እና ለማጋለጥ ጥሮ እንደነር ተመልክቻለሁ። እንደዚያ ዓይነት ድጋፍ ከእርስዎ በከፍተኛ ደረጃ እንጠብቃለን። ካልሆነ እማ እንዴት ተብሎ ባገር እና በሰላማዊ ሕዝብ ወንጀል የሰሩ አምባገነኖች የወደፊት ማሕደራቸዉ ልናዉቅ ይቻለናል? ወይስ አዲስ እና አሮጌ መነጽር የሚሉት የሕግ ፍልስፍናዎ ጋርደዎት ነዉ? ስለ የድሮ ባለስልጣናት እና የጫካ ገራፊዎች ስንተች እኛኑን በድሮ መነጽር አትመልከቱ ባሁኑ ባዲሱ መነጽር (በ እርስዎ በ እነ ገብሩ በ እነ ስየ እና በመሰሎች መነጽር ማለት ነዉ መሰለኝ) መመልከት የግድ አለብን? ያለፈዉ አልፏል፣ ማንዴላን ተመልከቱ የሚሉትን ምክርዎ/ክርክርዎ እንደዚሁም አለፍ ብሎም “ስድብ” የለገሱልንን ስመለከት “ማንዴላ” የወንጀለኞች እና ያጭበርባሪዎች ደም ያፈሰሱ ቡድኖች መሸፈኛ ማድረግዎ “ሃጢያት” ነዉ፣፣ ማንዴላ ወንጀለኛ አይወገዝ፣ አይቀጣ አላለም፣፣ እገሌን ገድያለሁ በእገሌ ሕይወት የማኢገባ የሃሰት ፍርድ አስተላልፌአለሁ፣ እገሌን ገርፌዋለሁ፣ እገሌ ታፍኖ እንዲጠፋ ወስኜ ነበር እያሉ ለሕዝባቸዉ እና ለዓለም ኑዛዜ ከሰጡ በሗላ ነዉ ይቅርታ ተደርጎላቸዉ ወደ ሰላም የተሸጋገሩት፣፣ አናጋልጥም፣ ብለዉ ምስጢሮችን/ወንጀሎችን በሆዳቸዉ ደብቀዉ ወደ ፖለቲካ መንበር እንደባለቅ ያሉትን ግን ዉግዘት ብቻ ሳይሆን የደረሰባቸዉ ተመስክሮባቸዉ የታሰሩም አሉ፣፣ ታዲያ እኛ አቶ ወልደሚካኤል መሸሻ ወደ ዳኝነቱ እንደገና ተሰይመዉ እስኪዳኙን ድረስ እኛኑንም ሆኑ የድርጅት መሪዎቻችንን ዛሬም “በወያኔ ነበር” ባለስልጣናት ሲተነኰሱ እና ስድብ ዘለፋ ሲጀምሩብን ወንጀለኞቹን አታዉጉዙ ማለት የትኛዉ ትምህርት ቤት ነዉ እርስዎ እንደዚህ ዓይነት ሕግ ተማሩት? ወይስ መስፍን ግርማ ያስተማረዎትን ይዘዉ ነዉ ወንጀለኞቹ ኣሁንም ምላሳቸዉ ልቅ ይሁን እና ይዝለፉዋችሁ እያሉን ያሉት? (መስፍን አስተማሪየ ነበር ብለዉናል እና)። ወይንስ በማፍያዎች “በድራግ ኪንግ ፒኖች” ሕግ መሰረት “ዱርየን ዱርየ ብቻ ነዉ ከስልጠን ማስወገድ የሚቻለዉ” በሚለዉ መርሖ ተንተርሰዉ ነዉ ስየ ወይንመ ገብሩ አልያም ነጋሶ ብቻ ናቸዉ ወያኔን ማስወገድ የሚቻለዉ ተብሎ ታምኖበት? ወያኔ የነበረ ካልሆነ ሌላዉ “ሴታ ሴት” ሆነበዎት? ቢሉም እዉነትም አይፈረድበዎትም። ለዚህ ነበር 18 ዓመት ምሁሩ በቂጡ ተቀምጦ ዓይን ላይን ሲናቆር ይሔዉ ለ እነ ስየ ለ እነ ነጋሶ መድረኩ ወለል ብሎ የተለቀቀላቸዉ። መጨረሻም በ እነ ታየ እና በ እነ ሃይሉ ሻዉል ላይ ለጊዜዉ አቋርጠዉት ከነበረዉ የቀድሞዉ “ነፍጠኛ ፤አክራሪ፤ፀረ ትግራይ” የሚሉትን ስም የማጉደፍ ዘመቻቸዉ እንዲ ቀጡልበት የተመቻቸላቸዉ። ወይ አገሬ! ጉድ እኮ ነዉ እናንተ የ!

እርስዎ ለመሆኑ የሚከተለዉን በራስዎ “ይግባኝ እና አቤቱታ ለዉጭ መንግሥታት” ሲጠይቁ“ በ 1995 ግንቦት ምርጫ ሰበብ በወያኔ ደህንነት እና ወታደሮች የተገደሉት 196 ሰዎች በማንዴላ “ዘይቤ” ይቅርታ ይደረግላቸዉ ብለዉ ነበር የጠየቁት? ወይስ ቅጣታቸዉን ይቀበሉ፣ ብለዉ ነበር ስለ ፍትሕ የተሟገቱት? ልጥቀስዎት፣ -

Finally, I would like to ask the democratic countries especially the Eu in the name of those 193 innocent civilian, who were murdered in cold blood, and 680 who were suffering of life- threatened bullet wounds, and in the name of political leaders and members, journalists civil society and human rights leaders suffering in jail for unfounded reasons that the government officials who are directly or indirectly should be made responsible and face justice.I thank you for your attention Woldemichael Meshesha.

እኛ ታዲያ በቤተሰቦቻችን እና በአገራቺን ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዉብናል ብያንስ እኛኑን እና መሪዎቻችንን ከመተንኮስ ይታቀቡ ካልሆነ “ወንጀለኞቹ” በያሉበት ይታደኑ! ይወገዙ፣ አሁንም አናምናቸዉም እና ከፖለቲካዉ ጨዋታ ይታቀቡ” ብለን ስላልን እርስዎ ምነዉ ይህ የፍትህ ጥያቀዎቻችን እንደ ምጥሚጣ ትዕግስትዎን አስጨረሰዎ? በ ኤሌክትሪክ ንዝረት ሲያሰቃዩ የነበሩ ፣ በ እሳት አዛዉንት ሲያቃትሉ የነበሩ በ እንቅልፍ ላይ የተኛ እስረኛቸን በጥይት እንደተኛ ሲረሽኑ እና ሲያስረሽኑ የነበሩ ጨካኝ አራዊቶች እርስዎን ሚያክል የሕግ ሰዉ በዚህ ዓለም ፈትህ ባለበት ኣለም እየኖራችሁ ከጓደኘችዎ ጋር ተባብረዉ እስካሁን እምባቸዉ እያፈሰሱ የሚገኙ ጠበቃ ያጡ ሰዎች ማሕደር አሰባስባችሁ በእነ ዚህ ዓራዊቶች ክስ ከመመስረት ይልቅ ፣ በጥቂት “ወልጋዳ የሊሂቃን ቡድን” በቀየሱት የሸርተቴ ሃዲድ ራስዎን በማስገባት ተገቢ ነዉ? በሸርተቴ ደጋግሞ መመለላሱ ብዙ ጊዜ በኩራት ማለፍ ቢቻልም አንድ ቀን ፈጠንኩ ብለዉ ሸርተቴዉ ቢያዳልጥዎት ኩፍኛ ተከስክሰዉ ቢወድቁ መነሳት የሚያቅትበት ሁኔታ ሊገጥም ይችላል እና አቶ አሰፋ ጫቦ በአንድ ጽሁፋቸዉ ስለ ሂሳብ ማወራረድ እንዲህ ብለዉ ነበር “ጨክኖ ሂአሰብ ማወራረድ” የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ሂሳብ ካልተወራረደ “የፖለቲካዉ መድረክ” ቢሣካለት እንኻ “ሂሳብ አወራርድ የሚል ኦዲተር (Haunt) በየጊዜዉ በር ምምታቱ የማይቀር ነዉ። በጊዜ ቁጭ ብሎ ከ (30 ዓመት በሗላ በጊዜ ማለቱ ጎልቶ ቢመስልም) ሂሳብ ቢወራረድ ጥሩ ነዉ። የገቢና የወጭ መዝገብ (ሠንጠረዥ) ሠርቶ ማየት ነዉ። ማንኛዉም ሂሳብ ሲጋራ የትርፍና የኪሳራ አምድ አለዉ። የኪሳራዩ አምድ ከሀብቱ (asset) በልጦ ከሆነ ሱቁን መዝጋት ነዉ። ለ አዲስ አበዳሪ መሯሯጥ ዋጋ የለዉም።…….” ብለዉ ነበር። እዉነትም ሂሳብ ማወራረድ! እነ ስየ እነ ነጋሶ ያልዘጉዋቸዉ “ኦዲት” ያልተደረጉ ብዙ የፍትሃዊ፤የብሄራዊ፤የሰብአዊና ሕገመንግሥታዊ ነክ ጉዳዬች ከሰለባዎቻቸዉ እና ለትዉልድ የሚተላለፍ ጠንቅ እና ካደረሱብን ብሐራዊ ጉዳት አንጻር ያላወራረዷቸዉ መዛግብት ስላሉ “የሂሳብ ማወራረድ“ ጥያቄ ሲነሳ እርስዎን የሚያቁነጠንጥዎ ነገር ለምን እንደሆነ አልገባኝም። በመጨረሻ አንድ ያነበብኩት የወላጆቻችን ጨዋታ ላጫዉትዎት እና ልደምድም። “ለመሆኑ ሰይጣን ልጅ አለዉ ወይ?” ለሚል ጥያቄ አንድ አዛዉንት ሲመልሱ በተግባር መጥፎነት የሚያዉቋቸዉን የሁለት ሰዎች ስም ጠርተዉ “እከሌና እከሌ የበኹር ልጆቹ ናቸዉ ሌላዉማ ስንቱ ተቆጥሮ?” አሉ ይባላል። ”ይልቁንስ እረስዎ…” አንድ ጌዜ ጎሹ አንዴ ጥቁር አንበሳ አንዴ ከፋኝ አሁን ደግሞ ዥንጉርጉር የግንቦት አንበሳ ሆነዉ የሚመጡብንን “እምየ” ከማለት በሕግ ሙያዎ ጥፋተኞችን ያድኑ/ ለሕግ ያቅርቡ። ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com