Wednesday, December 30, 2015

3ኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺዝም አብዮት! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)3ኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺዝም አብዮት!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)
ስትፈልጉ “From Fascism to Fascism (Aleme Eshete) ወይንም በኔው አገላለጽ The Recycling of the Ormo Fascism! The third cycle of the oromo Fascism” (Getachew Reda) ብላችሁ ርዕሱን መተርጎም፤ መረዳት ትችላላችሁ። ወደ ትንታኔዬ ከመግባቴ በፊት መጀመሪያ አርበኛው፤አገር ወዳዱ እውነተኛው የኦሮሞ ተወላጁ እጅግ የማከብረው ኢትዮጵያዊው ወዳጄ ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ የኢትዮጵያ መሬት በፋሺስቱ የወያኔ ቡድን ለሱዳኖች በገጸ በረከት በድብቅ ለመሸለም በምስጢር እየተሯሯጠ ባለበት ጊዜ እየተደረገ ያለ የአገር ክሕደት በተያያዘ ጉዳይ ሰሞኑን ተቃውሞውን በሰላ እውቀቱ በዝርዝር በማስረዳት፤ ለሕዝባችን ማስተማሩ እጅግ አክብሮቴን እየገለጽኩ፤ እንደ ደ/ር ፍቅሬና እዚህ አብሮን አካባቢያችን የሚኖሮው ወዳጄ ደ/ር ደምሴ ኦሉማ እና ስማቸው ለመጥራት እጅግ የበዙብኝ ሀቀኛ የኦሮሞ ነገዶች፤ ስለ ኢትዮጵያ አገራቸው ክብርና ሰላም በመቆማቸው፤ አንባቢዎቼ እንድያመሰግኗቸው ጥሬዬን አቀርባለሁ። በተለይ ሁለቱም ወዳጆቼ ከተገንጣይ ቡድኖች ጋር ከፍተኛ የሆነ አታካራ በመግጠም፤ በሕዝብ ፊት ሃቀኛ ኢትዮጲያዊነታቸውን በማመስከራቸው፤ በተገንጣዮቹ በመጥፎ ዓይን የሚታዩ ታጋዮቻችን ናቸው። ለዚህም ክብር ምስጋና ይገባቸዋል።

በዚህ ጽሑፌ ስለ ተመለከተው ርዕስ ስተነትን ፤ እነዚህና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦሮሞ ወታደሮች፤ምሁራን፤ገበሬዎች፤አትሌቶች፤የኪነት ሰዎች፤ሐኪሞች፤ የሃይማኖት መሪዎችና ምዕመናኖች፤ በአንድነት ሃይሉ የተሰገሰጉ ሃቀኛ ኦሮሞ ኢትዮጵያወዊያን ታጋዮች፤ጋዜጠኞች፤ ሰራተኞች፤የዛሬና የድሮ የኦሮሞ አርበኞችን እና የመሳሰሉ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ የኦሮሞ የሕብረተሰባችን ክፍሎች ፍጹም አይመለከትም። ይህ ርዕስ እና ትንታኔ የሚያተኩረው በኢትዮጵያ ሕዝብ ላብና መስዋእትነት ነፃነታቸውና ዜግነታቸው ጠብቆ “ለከፍተኛ ትምህርት” አድርሶ አስተምሮ፤ ለማዕረግ ያበቃቸውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማበጣበጥ በውጭ ጠላቶች እየታገዙ ኦሮሞን ከወገኖቹ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ነጥለው አገር ለመመስረት ለብዙ ዓመታት ሳያቆሙ እስከ ዛሬ ድረስ ብጥብጥ በመፍጠር ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ተገንጣይ ምሁራንን ነው የሚመለከተው።

በዚህ ሰሞን የተከሰተው የኦሮሞ ተማሪዎች በፋሺስቱ ወያኔ ላይ እያካሄዱት ያለውን የአንገዛም አምቢተኛነት በወያኔ ስርዓት ላይ ያነጣጠረ ይሁን እንጂ ከስሩ/ከንጣፉ በታች (ኣንደር ዘ ራግ) “የሚጨሰው/የሚቦነው የእምቢተኛነት አቧራ” ያነጣጠረው ‘ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች’ ኦሮሞ የሚባል ክልል የባለቤትነት መብት እንደሌላቸው” የተንጸባረቀበት እንቅስቃሴ ነው። መፈክሮቻቸው “ኦሮሚያ የግላችን የኦሮሞዎች ነው!” ይላል። ይህ መፈክር፤- “የግንጠላ ዜግነት” ፍለጋ ጎልቶ የወጣበት፤ ተገንጣይ ኦሮሞ መሪዎችና ድብቅ ኦሮሞ የግንጠላ አቀንቃኞች በየሚዲያው ወጥተው “የአንቀጽ 39 መብት” እና “የራስን በራስ ማስተዳዳር “የነገድ ክልል”/ *የግሩፕ* መብት” እንዲከበር የቀሰቀሱበት ትዕይንት ነው።
ይህ “ባንቱስታናዊ ክልል” ስንመለከት፤ “ወያኔም ሆነ ተቃዋሚዎቹ” “ተቀናቃኞች ሆነዋል”። ይህ ማለት  ለፖለቲካ የበላይነት የሚያደርጉት ግብግብ ውጤት ነው   

በዝግታ እየተራመደ ያለው የሁለቱም “ተቀናቃኝ” ክፍሎች ባሕሪ ፤ በነገድ ላይ ያነጣጠረ “አዛዡ እኔ ነኝ፤ የኔ ነው፤ የኔ ነው፤ የድምበር ባለቤትነት” ክርክር በመሆኑ፤ “ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በኦሮሞ ምድር የበባለቤትነት መብት የማያከብር -፤ ዜጎችን ባይተዋር ያደረገ” ስለሆነ፤_ ሁለቱም ተቀናቃኞች “ፋሺስታዊ ባሕሪያቸው” (ተማሪዎቹ የባንቱስታኒክ ክልል አክባሪዎች ሲሆኑ፤ ወያኔ ደግሞ ፋሺስት ነው) ወደ “ፈጣን ፋሺስታዊ የመገዳደል እምርታ” እንዲሸጋገር ፍላጎት አላቸው። ተዋናዮቹ ደግሞ፤ በውጭና በውስጥ ሆነው የመገንጠልንና ለባንቱስታናዊ የክልል መብት የቆሙት ሃይሎች፤ የሁለቱም ፍጥጫ በሰውም ብንብርትም የፈለገው ጉዳት ይምጣ ኣንዲገፉበት ይፈልጋሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ ኦሮሞ ወሰን አካባቢዎች ያሉት መሬቶች፤ በማስተር ፕላን ምከንያት  በብዙ መቶ ኪሎሜትሮች ርቀው የሚገኙ “በብዙ የኦሮሞ ከተማዎችና ክልሎች” የሚገኝ ኦሮሞዎች ተቃውሞው ለሳምንታት ሲዘልቅ “ከነጸብራቁ ብልጭታ” የሚነግረን ስዕል “ባንቱስታናዊም ሆነ ከዚያ ቢያልፍም የግንጣላ ፖለቲካ እውን እንዲሆን” ለፖለቲካ ሱፕረማሲ የሚደርጉት ግብግብ ነው። ኢትዮጵያዊነት የለውም የምልበትም ምክንያት ይህ ነው። ምክንያቱም “የአንድ ኦሮሞ ድምበር” ሲነካ ‘መላው ኦሮሞ አንደተነካ’ ተቃውሞአቸው በስፋት አስተጋቡ እንጂ 24 አመት  ሙሉ “የአንድ አማራ ድምበርና ህይወት በኦሮሞ ወረበሎች ሲደፈር፤ “መላው ኦሮሞ አንደተነካ አላሳዩንም”። ጥያቄአቸው፤ ባንቱስታናዊ እንጂ አገራዊ አይደለም የምልበትም ለዚህ ነው።   

 ይህም ቢሆን። በረብሻው ውስጥ የተጎዱ፤ህይወታቸው ያጡ በርካታ ኦሮሞ ወጣቶች “ነብስ ይማር” እያልኩኝ “ነብሰ ገዳዮቹም” ለፍርድ ቀርበው (ፍትሕ የለም እንጂ) ቅጣታቸው እንዲያገኙ የሚገባ መሆኑን እያመንኩ፦ ባጠቃላይ ቢያንስ “ለአንድ አመት ሙሉ” (ከአምና ጀምሮ) የታየው አመፅና የተደመጡት መፈክሮች የሚያሳየው  “የማስተር ፕላኑ” ጭቅጭቅ “ምክንያታዊ ደማሚት” ይሁን እንጂ “ሁለት ፋሺስታዊ ንቅናቄዎች” (ጊዜ ወስዳችሁ ተገንጠሉ የሚለው ብረት የታጠቀው ወያኔ እና በአንቀጽ 39 የግንጣላ ርዕዮት የታጠቀው ተገንጣይ የኦሮሞ ክፍል) አገርን በማፍረስ ላይ ያነጣጠረ “የግሩፕ ሱፕረማሲ ትግል” ስለሆነ፤በሁለቱ ክፍሎች እያየነው ያለው ግብግብ  ለአገራችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ “ፈንጆች” ስለሆኑ ሁለቱም ክፍሎች ፋሺስታዊ ርዕዮት የሚከተሉ ናቸውና ቅዋሜዬን አቀርባለሁ።

 ተቃዋሚዎቹ፤የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች እንደመሆናቸው መጠን “ሁላችንም ከነዚህ ወጣቶች የምንጠብቀው” የባንቱስታን አከላለል ‘በደም፤በቋንቋ፤በአጥንት፤በነገድ” መተዳደር “ናዚያዊ” ዘረኛነትን መከተል ስለሆነ እንቃወመዋለን እንዲሉ ነበር እንጂ “ባንቱስታናዊ ክልል” ሕጋዊ አድርገው እንዲተገበር የሚጠይቁ ወጣቶች ይከሰታሉ የሚል አምነት አልነበረንም። ስለሆነም ነው አደጋነቱን እንድታዩት የምፈልገው፡

ሁለቱም ግብግብ የገጠሙ ክፍሎች ፋሺስት ርዕዮት ያነገቡ ናቸው ብያለሁ። ፋሺስም ምን እንደሆነ ወደ ታች እንመለከታለን። ወያኔ ፋሺስት መሆኑን ሁላችንም የምናወቀው ሃቅ ነው። ኦሮሞዎች፤ የወያኔ ፋሺዝም “የኦሮሞ መሬትና ተፈጥሮአዊ ሃብት፤ ለኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪ “ብቻ” እንዲሆን ፋሺስታዊ ሕገመንግሥቱን አጽድቀወ፤ፈርመው አመስግነው ተቀብለውታል። ይህ ፋሺስታዊ ሕገ መንግሥት የቀየሱትም “እነ ሌንጮ ለታ/ኦነጎች” እንደሆኑ ሰሞኑን በግልጽ ነግረውናል (ጥንት የምናውቀው ምስጢር ቢሆንም)።

ተማሪዎቹም እንደ ወያኔ ጀሌዎች “የፋሺስቶች ርዕዮት ተከታዮች” ናቸው። ወያኔዎችና ኦሮሞ ሊሂቃን ሕዝቡ እራሱ ወዴት እየመሩት አንደሆነ በሚገባ በግልጽ ያውቃል የሚል እምነት አለኝ። እየተጓዙበት ያለው አቅጣቻ፤ አምኖውበት ለ24 አመት ተቀብለውት እየተጓዘበት ያለው “የጎሰኛነት” (ፋሺስታዊ) ርዕዮት ቆም ብሎ የማሰብ ሁኔታ እያየን አይደለም። ስለሆነም ታማሪዎቹ፤ “ባልታወጀ በኦሮሚያ የዜግንት ምኞት” ሰክረዋል። ሕዝቡም፤ ኦሮሚያ የሚል ባንዴራ ተቀብሏል፤ላቲን ፊደል የኔ ነው ብሎ ተቀብሏል፤ኦሮሚያ የሚል ባንቱስታናዊ/የክልል ድምበር የኔ ነው ብሎ ተቀብሏል። ሰለሆነም የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር “ከፍተኛ” ብጥብጥ እፊቱ ላይ ተደቅኗል።

እኔ እንደ ትግሬነቴ ፤ለብዙ አመታት የትግሬ ሊሂቃን እና ሕዝብ የወያኔን ፕሮፓጋንዳ ተቀብለው ‘ጸረ አማራ” ሕሊና የመሸከማቸው ጉዳይ ባደባባይ ስኰንን እንደነበር ታወቃላችሁ። ኦሮሞዎቹም ከትግሬ ወገኖቼ የምትለዩበት ነገር የለም። ምናልባትም በባሰ መልኩ ኦሮሞዎች አፍራሽ ሃይሎችን ከውስጥም በውጭም ያሉት ጸረ አንድነት የሆኑ የኦሮሞ ምሁራንና ካድሬዎች እንደ መሪዎቹ በመቀበል፤ ኦሮሞዎች እየተጓዛቸሁበት ያለው “አደገኛ ድልድይ” መፈተሽ ይኖርባችሗል የምለውም ለዚህ ነው። ምስኪኑ ኦሮሞ ገበሬ ወደ እማያውቀውና ወደ አልተረዳው ገደል እየተገፋ ነው።

ይህ የተነጠፈላችሁ አደገኛ ድልድይ በቅጡ ካልፈተሻችሁት፤ ለናንተም ሆነ ለመላይቱ አገራችን ከፍተኛ አደጋ አለው። ይህ ደግሞ ሁላችንም እሳት ውስጥ የሚጠብስ አደጋ ነው። በገንጣይ ሃይላት ተገፋፍታችሁ ከመላ ሕዝብ ጋር ያስተሳሰራችሁን ክር ይልቅ “የባንቱስታናዊ የጎሳ ኑሮ” ይበልጠናል ብላችሁ ከበጠሳችሁት “እናንተንም ሆነ” “በኮሎኒያሊሰትነት የተፈረጅነው የተቀረነው ኢትዮጵያዊያን/ኢትዮጵያ” ክሩን መልሰን እንቀጥለው ቢባል ፍጹም የማይቻል ይሆናል። ወደ ሃዘን ጭለማ አብረን አንጓዛለን። አንዴ ወደ ጭለማ ከተገባ ገንጣዮቹ አብረዋችሁ አይገኙም። አፋቸው ከመለፍለፍና በንዚን ከማርከፍከፍ አልፈው በውጭ አገር የተደላደለ ኑሮአቸው ጥለው እናንተ ወደ “ወደቃችሁበት ጭለማ” መጥተው ይረዱናል ብላችሁ አታስቡ።

ካሁኑ ሽሽት ይዘው እየኖሩበት ያለውን “የተንደላቀቀ” የውጭ አገር ህይወታቸው ማስተማሪያ እንዲሆናችሁ ልብ በሉ።እዚህ ያሉት ኦሮሞ ምሁራንና ወጣቶች እንኳ በምሳሌ ብትወስዱዋቸው “ከፓልቶክ ፉከራና ራዲዮን ከፍተው በንዚን ከማርከፍከፍ” አልፈው፤ እያርከፈከፉበት ወደ አለው እናንተ ወደ እምትኖሩበት ጫካና ኑሮ “መጥተው” ለመዋጋትና መስዋዕት ለመሆን ዝግጁነት እንደሌላቸው የምታወቁት እውነታ ነው። ኤርትራዊያን እንኳ፤ ነፃ ለመውጣት አመታት ተዋግተው፤ነፃ ከተባሉ በኋላ አዋጊዎቻቸው፤ ተዋጊዎቹና ምሁራኖቻቸው ‘ከኤርትራ እየሸሹ”፤ የተደላደለ የውጭ ኑሮ መርጠዋል። ከዚህ ትምህርት ውሰዱ። ሞኛችሁን ፈልጉ! በሏቸው እላለሁ። ይህ አጭር ምክር ላብቃ እና ወደ ጉዳያችን እንግባ። 

ግንጣላን ለሚያቀነቅኑ መልስ እነሆ።
 እዚህ ላይ መዘንጋት የሌለው ጉዳይ፤ ታሪክ በምጠቅስበት ጊዜ፤ ታሪክ እንደታሪክነቱ መቅረብ ስላለበት፤ ቅር የሚላቸው ወገኖች ካሉ፤ እኔን ሳይሆን መቀየም ያለባቸው ለዚህ ትንታኔ እና ክርክር እንድንበቃ እየገፋፉን ላሉት የኦሮሞ ተግንጣዮችን እንደሆነ ለመግለጽ እፈልጋለሁ። እነሱ ሲያብዱ አንተስ ማበድ አለበህ ወይ? የሚሉ ሊኖሩ ይችላሉ፡ ነገር ግን መታወቅ ያለበት ቢያንስ ሌላውን ዘመን ትተን ፤ ለ24 አመት እንኳ የተዘረጋው ውሸትና በነዚህ መሰሪ “ፋሺስት ተገንጣይ ኦሮሞዎች” አበራታችነትና መሪነት፤ “አማራን ከኦሮሞ ለማበጣበጥ” የተገነቡ “የጥላቻ ሃውልቶችና  በየሚዚየሙ የተሰበሰቡ “የውሸት ቅሬቶች” እንዲሁም “የክልል-ድምበሮች” በተመለከተ ያለ ብዙ ተቃውሞ “ነገሩን ለማረጋጋት” እየተባለ በብዙ ወገኖች በትዕግስት እንደታለፈ ታውቃላችሁ። ይህ ውሸት ተደጋግሞ ያለ ተቃውሞ በመለቀቁ፤ ዛሬ ወጣት ኦሮሞዎች ውሸቱን እውነት አድርገው በመውሰድ

(አስገራሚ ቢሆንም፤ ወያኔን እና ተገንጣይ ሀይላትን እንቃወማለን የሚሉ አክቲቪስቶች ነን የሚሉ አንዳንድ ወገኖችም ሳይቀሩ፤ይህ ውሸት እውነት ነው ብለው የተቀበሉና፤ ኤርትራ ሄዳችሁ ስለ አማራ ይቅርታ ጠይቁ አንደተባሉ አንዳንድ “ሕሊናቸው የተነጠቁ” ግለሰቦች ባላነሰ መልኩ በመካከለችን የሚገኙ ተቃዋሚዎችም፤ “አማራ”  የተባለ ገዢ ሥርዓት “ኦሮሞውን”  አንደበደለ በማስመሰል ነገር እያምታቱ በየአዳራሹ በተቃዋሚ ጎራ ሆነው የሚዘላብዱና የሚጽፉ ይቅርታ ጠያቂዎችም ጭምር እብዳሉም አንስትም። የኦሮሞ ነገድ የሆነው ባንዳው ንአመን ዘለቀ (የሻዕቢያ ቱልቱላ) “ተገንጣያቹ ወደ ማሃል እየመጡ ነው” እያለ ስለ አንድነት የቆሙትን ሀይሎችን “ባለጌዎች” በሚል ዘለፋ በመዝለፍ ፤ በቅርብ ቀናት ሰሞን ጀሌዎቻቸው በሚሰበሰቡበት “ኢካዴፍ” በተባለ “ፓልቶክ ክፍል” የሰነዘረውን የተግማማ ባንዳዊ  ማጃጃያ ፕሮፓጋንዳውን ልብ በሉ። )

ውሸታቸውንም ለማጠናከር እንዲመቻቸው፤ አማራውን “በጡት ቆራጭነትና በገዢነት እየፈረጁ”፤ ኢትዮጵያ የምትባል አገር “የመቶ ምናምን ዕድሜ ያላት” ምኒሊክ የመሰረትዋት አገር እንደሆነችና “የኬኒያ፤የሶማሊ፤የታንዛኒያ…ኦሮሞዎች “ጋላ” የሚል ስም የሰጧቸው ምኒሊክ እና ሃይለስላሴ እንደሆኑ እና አሁንም የኬኒያ ጋላ ነገዶች ያንን ተቀብለው በዛው እየተጠሩ እንዳሉ በመዋሸት “ኦሮሚያ” የሚባል አገር፤ መንግሥትና ሰንደቃላማ የነበረው እንደነበረና፤ በሗላ ግን “አማራዎች” መጥተው እንደገዙት፤ አሁን ግን ከትግሬ እና ከአማራ “ኮሎኒያሊስቶች/ከኢምፓየር አቢሲኒያ” ነፃ መውጣት እንዳለበት ሰብከዋል።
ያንን ውሸት መሰረት አድርገው፤“ወያኔና ኦነግ” በቅጥፈትና በውሸት፤ አገሪቷን ለመዝረፍ እንዲያመቻቻው፤  
 ተማክረው በከለሉት ኦሮሞ በሚባል “የባንቱስታኒክ ክልል” ያለ መላው ኢትዮጵያ ሕዝብና የታሪክ ግኝት፤የቤተሰብ ትስስር፤ የሰብአዊ ነክ ፤የምጣኔ ዘርፍና የፀጥታ ጉዳይ አዋቂዎች እና ስለ አገሪቱ ጠቅላላ ህልውና ምክክርና ተሳትፎ ሳያደርጉ፤ “ብቻቸውን” በረሃ ላይ “ሴራውን” በመቀየስ “ኦሮሚያ” የተባለ “አዲስ የፈጠራ ክልል/አገር” መስርተው ከወያኔ ቁጥጥር “ነፃ” ለመውጣት የተቻላቸውን ያህል በማድረግ ላይ ናቸው። ወደ ግንጣላ የሚመራቸው የመጀመሪያው ጉዞ ጨርሰውታል። ይህም “ክልል” ይባላል። አሁን እየታየ ያለው “የቡራዩ ኬኛ፤ ሱሉልታ ኬኛ፤ ኦሮሚያ ኬኛ!” መፈክር ፤ ግንጠላውን ለማፋጠን የሚደረግ አዳጋቹ  “ሁለተኛውና የመጨረሻው ጉዞ” ፤የመጀመሪያው እርከን፤ የፍትጊያው እንቅስቃሴ ሂደት ጀምረውታል”።

ከዚህ እንቅስቃሴ በፊት እዛው ክልል ውስጥ ለዘመናት የኖረ ማሕበረሰብም በታጠቁ የኦሮሞ የክልል ወታደሮችና በኦነግ ወታደሮች ጥይትና ሳንጃ፤ የግድያ፤የዘረፋና የመባረር ከፍተኛ ወንጀል እንደተፈጸመበትና፤ በቅርቡም “በደቡብ  ምዕራብ  ሸዋ፣ አመያ ወረዳ በተባለ ወረዳ” በጅምላ ከተቃጠ ሉት የዐማሮች መኖሪያ መንደሮች  አንዱ  ከዚህ በታች የተመለከተው የፎቶ ማስረጃ ይመለከቱ። ዘርዝር ዘገባው ለማወቅ “ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት”ረቡዕ ታኅሣሥ ፲፫ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. ያወጣውን
 አንድነት ከማን ጋር? ሚለውን ሃተታውን ይመልከቱ። (ምንጭ፦ የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ቁጥር 22 ቅጽ 3 ታሕሣሥ 12 ቀን 2008 ዓ.ም.)   
Amhara land burned by Oromo secessionist thugs
ይህ የምታዩት የፈቶ ማስረጃ የተቃጠለ መንደር የአማራ ገበሬዎች መንደር ነው። በአመያ ወረዳ በሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች፦ ማለትም «አብቤ መድኃኒዓለም»፣ «ኩኖ ቁሊት (ቀርሳ ቁሊት)» እና «መሪ መገሪ (ባሬዳ)» በተሰኙት ነዋሪ የነበሩ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ንብረት ውስጥ 1,000(አንድ ሺህ) ቤቶች ማጀት በጎረሰ፣ ደጃፍ በመለሰ ያለ የሌለ ንብረታቸው ከነቤቶቹ ተቃጥለው ወደ አመድነት ተቀይረዋል። በእያንዳንዱ የቀበሌዋ ነዋሪ ዐማራ ከ70,000 (ሰባ ሺ) እስከ 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ብር የሚገመት በርበሬ ተቃጥሏል” (አባሪ ፎቶግራፍ ይመልከቱ)።

ይህ አማራ እየተገፋ ባለበት ትኩስ የግፍ ዜና ፤ያውም “በባንቱስታኒክ ኦሮሞዎች” ሲፈጸም፤ የወያኔ ተቃዋሚ ሃይሎች ነን የሚሉ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ውጭ አገርና ውስጥ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ ሃይሎች፤ ቡራኬአቸውና ድጋፋቸው የለገሱት እንዲሁም ጮክ ብለው እየጮሁላቸው ያሉት ለቡራዩ ኬኛ! ፤ለሱሉለታ ኬኛ!፤ለኦሮሚያ ኬኛ! “ባንቱስታኒክ” ፈካሪዎች መሆኑን ልባችንን አድምቶታል።

ይህ ሳንነጋገርበት ለ24 አመት በቸልተኝነት ዝም እየተባለ፤ ዛሬ “ወጣት ኦሮሞዎች” ከገንጣይና አስገንጣይ ክፍሎች የቀሰሙትን የ24 አመት ቅስቀሳ፤ ”ቡራየ፤ኬኛ፤ ሰበታ ኬኛ…….ኦሮሚያ ኬኛ….” ወደ እሚለው የግንጠላ መፈክር ደርሰዋል። አሁን ዝምታችን መስበር የግድ ነው!!!

ይህ ደግሞ በወያኔ ዘመን የተወለደ “ወጣት ኦሮሞ” ይህን “የፈጠራ ታሪክና የኤትኒክ ፌደራሊዝም አደገኛ አወቃቀር”  ከህጻንነቱ ጀምሮ እየተኮተኮተ “እውነትነት ያለውና ጤነኛ አስተዳዳር መስሎት” ያለ ምንም “ሕሊናዊ ምርመራ” አምኖ በመቀበሉ፤ በየታላላቅ የትምህርት ተቋማት ሳይቀር ፡ “ ኢሚፓየር ኢትዮጵያ” “ሳብጁጌሽን” የሚሉ ቃላቶችን በመጠቀም በግልጽ ሳይሸሽጉ፤ ሳያፍሩና ሳይሸማቀቁ “በዩቱብ አውድዮ እና ቲቪ ሚዲያዎች” የለጠፉት የተለያዩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኦሮሞዎች ተቃውሞ ተመልከቱ። አምና በተለቀቀው አውዲዮ ላይ ወደ መጨረሻ ገደማ የሚያሰሙትን መፈክር አድምጡ፡- የተቀረጸውን ስታደምጡ፤ ወጣቱ እውነትም ነጋሪ በማጥት ሕብረተሰቡም ሆነ እራሱን ይዞ ገደል እየገባ መሆኑን ማየት ትችላላችሁ።

እነኚህ አፍላ የኦሮሞ ወጣቶች ለብዙ ዘመናት “አፍሪካኖችና ጃማይካኖች” እንደ “ብሌን ዓይናቸው” የሚመለከትዋትን ሰንደቃላማችን “አያውቋትም”።  “ኦነጎች የቀየሱላቸው “የዋርካ ዛፍ ምስል” ያለበት እና ሌላው ደግሞ “በእስለማዊ እና በዓረብ አገሮች፡የሚውለበለቡ ቀለማት ያሉበት ባንዴራ” ነው አሁን ወጣቶቹ የሚያውለበልቡት (አገርም ውስጥም/ ውጭም)።

ችግሩ እርግጥ አገር ከመሰረቱ በሗላ ቀርቶ፤ ገና ኦሮሞዎቹ አገር ሳይመሰርቱ ዛሬ “እርስ በርስ” በመናከስ ኤርትራ እና እዚህ ሜኔሶታ/አሜሪካ ውስጥ ፍርድ ቤት ድረስ እየተካሰሱ “እኔ ነኝ ሕጋዊው ኦነግ”፤ “መሪያችን እገሌ እንጂ እገሌ አይደለም” “ስትፈልጉ እናንተ ስማችሁ ቀይሩ እንጂ ኦነግ እኛ ነን” ወዘተ…ወዘተ…በሚል አታካራ ገብተው “እየተራኮቱ” ናቸው። አገር ቢመሰርቱ ካሁን በፊት እንደገለጽኩት “ኦሮሞ እስላም/ከኦሮሞ አርቶዶክስ/ “አሮሞ ፕሮቶስታን/ ከኦሮሞ ኦርቶዶክስ” ኦሮሞ እስላም ከሁሉም እምነት፤ ሁሉም አምነቶች ከዋቆ፤ ዋቆ ከወዘተ…ካፒታሊዝም/ሊበራሊዝም/ገዳኢዝም/ሶሺያሊዝም/ካሊፋ-ኢዝም/ሸሪዓ-ኢዝም… ወዘተ.. ወዘተ…ወዘተ… እየተናከሱ “ምድሪቷ የአልሸባብ ሶማሌ ዓይነት ኦሮሚያ” እንደሚያደርጓት ሳይታለም የተፈታ ነው።

ስርዓቱም፤ ስፓኒሾች እንደሚሉት “ley de la calle” እንግሊዞቹ “mob rule” አማራዎቹ “ወሮ በላ ስርዓት” የሚሉት። በሳይንሳዊ የፖለቲካ ስሙ “ኮሎክቲቪዝም/ፋሺዝም/ማብ-ሩል/ማፍዮኢዝም/ኦሊጋርኪ” የሚባለው። በእነ ጃዋር “የትንቢተ ስርዓታቸው” ፖሊሲ “የሜንጫ ስርዓት” የሚሉት ማለት ነው።

የኦሮሞ ፋሺዝም አዙሪት ምን ማለት ነው? ፋሺዝምስ ምን ማለት ነው?

በውስጡ ባሉትና በዙርያው ባሉ ማሕበረሰብ ክፍሎች የራሱን ጎሳ የበላይነት (ኤትኒክ ሱፕረማሲ ‘ሴት/ንብረት/መሬት/ሥልጣን/ሃይማኖት…’) ለመንጠቅና ለማስፈን፤ ያንን የበላይነት እውን ለማድረግ ከመዋጋት አልፎ፤ ለማመን እና ለማየት እጅግ በሚዘገንን ጨካኝ ጭፍጨፋ’ዝርፊያና አመጽ” በሌሎቹና እሱን በሚቃወሙት የራሱ ጎሳዎች ሳይቀር “ሰይፍ በመምዘዝ” “ፀጥ” በማሰኘት ሕብረተሰቡን ሽብር ውስጥ አስገብቶ በፍርሃት የሚገዛ፤የሚያርበደብድ፤ሰላም የሚነሳ፤ ሁውከተኛ የብጥብጥ ስርዓት ነው።
የዘመኑ ፋሺዝም ብዙ ትንታኔዎችን ቢሩትም በቃላሉ “የሰው ልጅ ፤ከግለሰብ ነፃነት እየወጣ፤ በሕብረት መተዳዳር ከጀመረ ጀምሮ “ጀነሪክ ፋሺዝም” የሚሉት፤ አገርን በማውደምና መንደሮችን ማቃጠል፤ጭካኔን  ምርኩዝ እያደረገ፤ እረፍት የሚነሳ፤ በደም ጥራት የሚጓዝና የሚያስተዳድር፤ ጥቂት ወረበሎች የሚፈጥሩትና የሚመሩት የሽብር ስርዓት ነው፤ ፋሺዝም ማለት!”     

ኦሮሞዎች እንዲህ ዓይነት ጭካኔና ስርዓት ፈጽመዋል? የሚል ጥያቄ ሊቀርብ ይችላል። መልሱ፦ “አዎን፤ በሚገባ!!”። የጥንት ኦሮሞዎች ድሮ “ጋላ ሲባሉ የነበሩ ነገዶች፤ መንደር፤ሕዝብ፤አገር አውድመዋል። ይህንን ሲፈጽሙ እጅግ ዘግናኝ እርምጃ እየወሰዱ ነበር የፈጸሙት። “ዲሞክራሲ” ነበር እያሉ በውሸት የዛሬ የተማሩ ኦሮሞዎች የሚያሞግሱት “የገዳ ስርዓት” እንኳ ሳይቀር ስትመለከቱ “እጅግ ማመን የሚያዳግት” ባሕሪዎች ታይተውበታል። ይህ ደግሞ በጽሁፍ መረጃ “ኦሮሞዎች ወደ መሃል አገር፤ወደ “ከፋ” (እርግጥ ከፋ ውስጥ ጥቂት ነገዶች ከጋላዎቹ ጭፍጨፋ ድነዋል፤ለዚህ ምክንያት “የደኑ ብዛት” የኦሮሞዎቹ ከብቶች ማስገባት ወደ ውስጥ ሰርስረው መዝለው ስላቃታቸው፤ ወደ ውስጥ ደን ገብተው ነዋሪውን መጨፍጨፍ አልቻሉምና ከመአቱ የዳኑ ጎሳዎች እንደነበሩ እንደዳኑ፤ታሪኩን ያጠኑ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ።) እንዲሁም “ጅማ”፤ ሸዋ፤ትግሬ፤ወሎ፤ጎጃም ጎንደር……ሲስፋፉ በወቅቱ የተፈጸመ ድርጊት፤ ፋሺስታዊ ዘግናኝ ጭፍጨፋና ዘረፋ ተካሂዷል።

ይህ አሁን “ኦሮሚያ ኬኛ” እያሉ ወጣቶች የሚዘምሩት መፈክር፤ በዘረፋና ባሰቃቂ ጭፍጨፋ የድሮ ጋላዎች ከነባር ኗሪዎች የነጠቁት መሬት እንደነበር በግልጽ ማወቅ ይኖርባቸዋል። በወቅቱ እንዲህ ያለ ፈጣን እና ባጭር ወቅት ወደ ኢትዮጵያ የተስፋፉበት ምክንያት ፤በወቅቱ” ኢትዮጵያ “በግራኝ አህመድ” ጂሃዳዊ ወረራ ምክንያት ሃይሏ ተዳክሞ ሕዝቧ አልቆና በጦርነቱ ደክሞ፤ ታርዞና መዋጋት ሰልችቶት ስለነበር፤ ኦሮሞዎቹ ከታች ከኢትዮጵያ ድምብር ገሰግሰው በመምጣት አጋጣሚውን ተጠቅመው ሰፊውን መሬት ከኗሪው እየነጠቁ ዛሬ ለራሳቸው አድርገውታል። ሃቁ ይህ ነው።

ከወረራው በፊትና በወረራው ወቅት የነበሩ ግዛቶችና “የቦታ ስሞች” በውጭ አገር ጎብኚዎች በወቅቱ የተነሱ የካርታ ምስክሮች ዛሬም በሊቃውንት ቤቶችና መጽሐፍት ቤቶች ይገኛሉ። እነሱ ማን ምን ይባል እንደነበር ቁልጭ አድርገው ይነግሩናል። የተረሳው ፋሺስታዊ አዙሪት ነብስ ዘርቶ እንደገና ሌላ ዘላቂ ‘የሁውከት” አዙሪት ከመደገሙ “ግልፅ ግልፁን” በመነጋጋር እንዲህ ማዝገም ስለሌለበት ዝምታችን መስበር የግድ ነው!!! አማራው ሕዝብ “በባንቱስታኒክ ኦሮሞዎች” ቤቱና ህይወቱ እየወደመ “ወደ መሃል እየመጡ ነው” “ግንጠላን ትተዋል” የሚሉንን ደላሎችና ከጂዎችን ማመን አቁሙ! (በዚህ በሰሜን ክፍላችን ደግሞ የወልቃይት አማራ ወገኖቻችንን “በትግሬ ፋሺዝም ተስፋፊ አይዲኦሎጂ” ምክንያት እየደረሰባቸውና የገጠማቸው ፋሺስታዊ የዘር ማጥፋት በትልቁ ሳይረሳ ማለቴ ነው!!!!)

በ15ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የታየ አገርና መንደርን ማውደም፤ ዛሬ በቃ ማለት ጊዜው ነው! ጥንት በኦሮሞ ከብት አርቢ ወራሪዎች “በአማራ፤ በጉራጌ፤በሐረሬ፤በሲዳማ፤በጋሞ…በወላይታ…ወዘተ…ኗሪዎች ግፍ ፈጽመዋል።  በወቅቱ የነበሩ ጅማ “ሙርጡላ ማርያም” (?ከተሳሳትኩ አርሙኝ) ገዳም  ውስጥ የነበሩ ሊቃውንት (ለምሳሌ አባ ባሕርይ) የመሳሰሉ በዓይናቸው ያዩት “ፋሺስታዊ ዘግናኝ ድርጊት” በጽሑፍ መዝግበው ትተውልናል። በነገራችን ላይ መነኩሴው አባ ባሕርይ የኦሮሞን ባሕል፤ታሪክ፤ነገድ አመጣጥ/ትውለደ ሐረግ… ከማንኛውም ኦሮሞ ነኝ ባይ እንደሳቸው አውጣጥቶ በንፁር የዘገበ የለም። ለኦሮሞውና ለተቀረነው ትውልዶች መዝግብው የተውለትና ያስተማሩት ባለውለታ ናቸው። በኦሮሞዎቹ የታሪክ ምሁራን በእነ ዶ/ር መሐመድ አህመድ ፧ ሳይቀሩ የአባ ባሕሪ የኦሮሞዎች ትውልደ ሐረግ ዝርዝር/ጥናት አምነው በአክብሮት የተቀበሉት ሃቅ ዩሆነ ሰነድ ነው።

ባለውለታ ናቸው የምልበትም ምክንያቱም “ጋላዎቹም” ሆኑ የዛሬዎቹ “ኦሮሞዎች” የንግግር እንጂ “የጽሑፍ ሥልጣኔ ቋንቋ” ስለሌላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በግዕዝ ጽሑፍ ጽፈው “የጋላ ትውለድና ክፍሎች፤ እና አስተዳዳር” በሚገርም አተናተን ዘርዝረው ስለተውላቸው ብዙ ኦሮሞዎችና የውጭ ምሁራን/ተመራማሪዎች ያንን የመጀመሪያና ብቸኛ ትምህርትና፤የዓይን ምስክርነት ሰነድ ምንጭ ሰለሆነ ኦሮሞዎች ዛሬ ሐረጋቸው እየቆጠሩ ያሉት እሳቸው ሰንደው በተውላቸው ሰነድ ነው።

 ሆኖም እሱም (ዶ/ር መሃመድ አሕመድ) ሆነ የመሳሰሉ ተገንጣኢ ኦሮሞ ምሁራን “ያቺን የሃይማኖት ችግራቸውና ተገንጣይነት” ሉጓም ሆና ስለምትይዛቸው፤ ሙሉ በሙሉ አባ ባሕሪን አያመሰግኗቸውም። ስለሆነም ተገንጣዮቹ የአባ ባሕርይ የዓይን ምስክርነት መፋቅ ስለማይቻላቸው ለግንጣላ ታሪክ አልመች ስለምትል የሳቸውን እና ሌሎችን “የሃገር ውስጥ ምንጮችን አይቀበሉም”። ካለመቀበል አልፈውም “ያጥላላሉ”።የደብተራ ጥናትም ሲሉ ያጥላሉታል። ግብዝነት አደጋ ነው፤ ይባል የለ!

ክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ እንዲህ  ይላሉ፤

   “የሀገር ውስጥ ምንጮችን የሚያጥላሉ ዘመናዊ ታሪክ ጸሐፊዎች ካሉ ባይመዘገብ የሚወዱት ስለተመዘገበ ነው….።”(ጌታቸው ሃይሌ፤  ገጽ 31 የአባ ባሕርይ ድርሰቶች፤ ኦሮሞዎችን ከሚመለከቱ ሌሎች ሰነዶች ጋር)። እውነት ነው። ይህ ወርቃማ አገላለጽ፤ ከሺህ ገጽ መጽሐፍ በበለጠ ከፍተኛ ትርጉም እና ቀላል አገላልጽ የያዘች ዓረፍተነገር ስለሆነች፤ ምን ማለት እንደሆነ ሁላችሁም በትኩረት መገንዘብ አለባችሁ።  ባይመዘገብ የሚወዱት ክፍሎች እነማን ናቸው? በውሸት የሚጓዙ የጋላ ታሪክ ባይመዘግብ የሚመርጡ እንደ እነ ኦነጎች የመሳሰሉ ፋሺስት ክፍሎች ናቸው።  በወቅቱ “ጋላ” ተብለው ሲጠሩ የነበሩት “የኛ ዘሮች ናቸው” የሚሏቸው የዛሬዎቹ ኦሮሞ ምሁራን (ጋላዎቹ እርግጥ ከወረራ በሗላ ከተቀረነው ኢትዮጵያዊያን በደም በስጋ ስለተዋሃዱ፤ እነ አባ ባሕርይ በነበሩበት ጊዜ የነበሩ ንፁሕ “ጋሎች” አይደሉም የዛሬ ኦሮሞ ነን እያሉ እየነገሩን ያሉት “ኦሮሞዎች”።

ምክንያቱም አሁን ያሉት “ኦሮሞ ነን” የሚሉት “ከተቀረነው ጋር” ከተደበላለቁ በሗላ የመጣ ድብልቅ/ክልስ የጋላዎቹ ትውልደ ሐረግ መሆኑን አንባቢዎቼ ልብ አንድትሉ እፈልጋለሁ። ምናልባትም ብዙዎቹ ኦሮሚኛ ስለሚናገሩ ከዘመናት የመደባለቅ ሂደት በላ ኦሮምኛ ተናጋሪ ይሁኑ እንጂ “ኦሮሞዎች” ያልሆኑ በሚሊዮኖች እንደሚቆጠሩ እርግጠኛ ነኝ። ትግሬዎች በመባል እየተጠራን ያለን የዛሬዎቹ ትግሬዎች “የድሮ አክሱማዊያን” “ያልተደባለቀን ንጹሕ “አክሱማዊያን”/”አጋአዚያን”…ማለት የዛሬዎቹ ትግሬዎች ነን ብለን በልበ ሙሉነት መናገር አንደማንችል ሁሉ (የሚያገናኛቸው ነገርና ሐረግ ቢኖርም የዛሬ ትግሬዎች የድሮ አክሱሞች ነን ብለን 100/100 እርግጠኛ ልንሆን አንችልም) ፤ ኦሮሞም የድሮዎቹ ንፁሃን ጋላዎች፤ የዛሬዎቹ “ክልስ ኦሮሞዎች” “ንፁህ /ያልተደባለቅን ጋላዎች/ኦሮሞዎች፤ ነን” ቢሉም “ከስሜትና ከቅዠት” የተነሳ “ድንቁርና እና ፋሺስታዊ ስሜት ያሰከረው  ንፁህ ደም” ፍለጋ ባሻገር ከመሆን ዘልሎ ሊሄድ አይችልም። ታሪክ ነው እየተነጋገርን ያለነውና ታሪከ እንደ ታሪኩ እንድትረዱልኝ እፈልጋለሁ። ግልፅ ግልፁን! አለ ወዳጄ ጋዜጠኛው ድምጸ መረዋው “ኢሳያስ ልሳኑ”!

የጀመርኩት ጭብጥ ከመቀጠሌ በፊት ግን ይህ “ጋላ” የሚባል ነገድ ዛሬ በኬኒያ በሶማሌ እና በመሳሰሉ እንዳሉ ይታወቃል። የኛዎቹ “ኦሮሚያ ነን” የሚሉ አስገራሚና አስቂኝ ኦሮሞ ተገንጣዮች “ጋላ” የሚለው ስያሜ “ስድብ” ነው ብሎ፡የነገራቸው ማን እንደሆነ እና ስድብ ነው የሚል የትኛው መጽሐፍ  እንዳገኙት ባናወቅም፤ “ጋላ” የሚለው ትከክለኛ የተከበረ የድሮ የጋላ ነገድ ስም (የተከበሩ ክቡራን ወላጆቻቸው “የጋሊቷ ልጅ” እያሉ ወላጆቻቸው በቀና እውነተኛ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ሲፎክሩበት አንዳልነበረ ሁሉ) ነውር ነው/ደሮጋቶሪ ነው//አስጸያፊ ስም ነው” ፤ እያሉ ብዙ ኦሮሞዎች በፈጠራ ፕሮፓጋንዳ  ተታልለው በብዛት ተቀብለውታል።የለወጡትም በደረግ ጊዜ ነው። ደርግ ሲመጣ፤ የደርግ ስርዓት የመሩት ኦሮሞዎች ስለነበሩ” ያንን ስም ወደ ሁለተኛው ስም በቀላሉ ወደ ሁለተኛ ስማቸው ወደ “ኦሮሞነት” እንዲለወጥ በማድረግ፤ “ጋላ የሚለው ሌላኛው “ከጥንት ጀምሮ እስከ ኬኒያ፤ ሶማሌ… ድረስ ሲጠራበት የነበረ ሕጋዊ የነገዱ አጠራር” “ስድብ” ነው፤ ብለው “ብረይን ኮንትሮል ፍሪኮቹ” አስቁመውታል። ይህ ሲሆን፤ በውሸት ወጣቱንና ሕዝቡን አሳመኑት።

 ይህንን በሚመለከት ከኢትዮጵያ ድምበር አልፈው ሌላ አገር ድረስ፤ ማለትም ኬኒያ ድረስ ተሻግረው ጋላ የሚለው ስያሜአቸው ወደ ኦሮሞ እንዲለዉጡ “ሌላ አገር” የሚኖረውን ሰላማዊው “የጋላ” ነገድ “ኦሮሞ ተብሎ አንዲጠራ ኢትዮጵያን አገራችንን “በጥብጠው”፤ በሰው አገር ድረስ ተሻግረው ለማበጣበጥና “ሕጋዊ የነገዳቸውን ስማቸውን” ለማስቀየር የጻፉትን ማመልከቻ ከዚህ በታች ያለውን ለማስረጃ ባጭሩ ተመልከቱልኝና ወደ እዛው እንቀጥላለን።
ባጭሩ አንዲህ ይላል፦
FROM: OROMO REFUGEE TEACHERS, THE OROMO
REFUGEE COMMUNITY LEADERS, KENYA.
December 20, 2013
TO: KENYAN EDUCATION MINISTRY
NAIROBI, KENYA.
P.O.BOX 30040-00100,

REQUEST TO REMOVE AND BAN THE USAGE OF TERM GALLA IN KENYA.
We, the Oromo teachers from Oromo refugee community in Kenya, are writing to you to bring into your attention the negative impact of the usage of a derogative and abusive word Galla to identify the Oromo in the text books of social studies used in primary and secondary education in Kenya. It is wrong terminology usage against Oromo identity which is unjustifiable historically to educate the nation.

In fact the people identify themselves as Oromo and their language as Afan Oromo, which is the correct terminology usage.
Although the Oromo nation is the second largest in Africa, it is forgotten by or still unknown to the majority of the world today, even the name Oromo. This is partly because of the colonial Ethiopian Emperors Menelik and Haile Sellesie and their successors which continued until today to treat Oromo with utmost cruelty due to their resistance to colony. The Oromo people endured a stagnant existence where ignorance and famine have been coupled with ruthless oppression, subjugation, and exploitation in all spheres of  life and above all extermination. Everything possible was done to destroy Oromo identity, language, culture, custom, tradition, name and origin.

In short, the colonizers maintained the general policy of genocide against the Oromo and use the term Galla to dehumanize and victimize Oromo and to destroy their identity and language. Such insulting name to the nation were abolished and eradicated by oppressed nation of 1974 revolution in Ethiopia and the usage of the term Galla is officially banned.

And sadly, to deny the Oromo the right to identity and as if this is not enough and to add insults to injuries, the term Galla is in use interchangeably for Oromo in text books of social studies used for education system in Kenya. To cite few books; the Evolution World, a History and Government course Form 1, by Oxford new edition 2010, under the topic Cushitic…………………the  Cushites group comprised of……….Galla(Oromo)………>> on page 78 and under the topic  Borana…………..the Boran are branch the Oromo or Galla people……….they speak Cushitic language called Galligna……on page 81 and also in other course book-Milestone in History and Government Form 1 by Longhorn publishers…..reprinted in 2010 under the topic Eastern Cushitic comprise of the Elmolo, Gabra, Oromo(Galla)…..on page 40. And also in some many other course books published by Kenya Literature Bureau.
Hence, as we clearly tried to indicate above, such wrong terminology usage for Oromo identity  is illegal and it allows subjugation and victimization of Oromo children and people at large,infact it is clear violation of basic human Right Declaration of children’s basic right to good education and right to identify of Oromo nation.And this should not be allowed to continue by free and Democratic nation of Kenya and Africa.

Therefore,kindly we the Oromo refugees in Kenya would like to request the honourable education office and concerned authorities of institutions to totally remove the use of the term  Galla from educational books and further ban the usage of such abusive term against people in any written or oral form in Kenya.
THANKS FOR YOUR UNDERSTANDING AND LEGAL ACTION!
YOURS TRULY,
THE OROMO REFUGEE TEACHERS
THE OROMO REFUGEE COMMUNITY LEADERS
KENYA

ክቡራን አንባቢዎቼ ሆይ!
ይህ ጉደኛ ደብዳቤ ተጻፈው ከሁለት አመት በፊት ነው ወደ 2013 አካባቢ ‘በፈረንጅ’። አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ፤ “ጋላ” የሚለው ስያሜ የሰጡት አፄ ምኒሊክና አፄ ሃይለስላሴ በማስመሰል፤ ኬኒያ ፤ሶማሊ፤ኢትዮጵያ፤ ሌሎች አገሮችም ካሉ፤ እራሳቸው ይዘርዝሩት፤…… ሁለቱ ንጉሦች ጋላ ብለው የሰየሙዋቸው ይመስል፤ በውሸት እየከሰሱ፤ ይህ ኦሮሞ የተባለ የነገድ ስም “ጋላ” እንደተባለ እና “ሰፊው” የኦሮሞ ሕዝብ (ሰፊ፤ትንሽ፤ ትልቅ፤ማይኖሪቲ/ማጆሪቴ የሚለው የትምክህት/ኢጎ/ ትንታኔ ምን ማለት እንደሆነ ባይገባኝም) “በዓለም ሕዝብ” እንደ “አገር” አንዳይታወቅ ያደረጉት እነኚህ ሁለት ንጉሦች መሆናቸውን ባስቂኝ ደብዳቤአቸው ገልጸዋል።

እነኚህ ተገንጣያችና ፋሺስቶች እያመለከቱ ያሉት “ለኬኒያ” ነው። ኬኒያ ደግሞ ኢትዮጵያ አይደለም። ምኒሊክም ሆኑ ተፈሪ አልገዙትም፤ ስለሆነም ጋላ ብለው ነገዱን አልሰየሙትም። ጋላ ማለት ነውር ነው ብለው የነገድ ስም ለማስቀየርና ብጥብጥ ለማስነሳት እየጣሩ ያሉት፤ ባዕድ አገር ሆነው ነው። እየነሩት ያሉትም በጥገኛነት ነው። የኬኒያ መንግሥት እነዚህ ሰዎች አያውቃቸውም; ዜጎቹ ሳይሆኑ ስደተኞች ናቸው፤፡  እዛው ኬኒያ ያሉ የጋላ ነገዶችም እነኚህ ነገሥታት እንደገዟቸው አስመስለው ነው ስማቸው በዓለም እንዳይጠራ አድርገው እነዚህ ነገሥታትን እየከሰሱዋቸው ያሉት። ጋላ የሚለው ስም አማራዎች ሰጡን ሲሉን የነበረው፤ አሁን ደግሞ ኬኒያ ያሉት አውነተኛ ጋሎችን “አማራ” የሚባል ገዢ  (ምናልባትም በፋሺስቶቹና ተገንጣዬቹ ውንጀላ ‘በምኒሊክ/በሃይለስላሴ’) እንደተሰጠ አስመስለው ነው “ስለ የኬኒያ ጋላ ነገዶች” ተቆርቁረው “ኦሮሞ እንዲባሉ” ነው ለኬኒያ የትምህርት ሚኒስትር ደብዳቤ የጻፉት።

ይህንን ዕብደት ስትመለከቱ በምን ቃላት ልትገልጹት ትችላላችሁ፤ “እናንተየ!!”? በስደት እየኖሩ በሰው ጋር ሄደው የሌላ አገርን ነገድ ስም ይቀየር ብለው ሲሟገቱና የዛው አካባቢ “ነገደ ጋላ” ባላሰበውና ባላስተነተነው ዓላማ “ለማቃዠትና ለማነሳሳት” ሞመከራቸው፡ እነኚህ ተገንጣዮች፤ ለመሆኑ ድምበር፤ ዜጋ፤መንግሥትና ስርዓት እንዲሁም “ስደተኛ” ማለት ምን ማለት አንደሆነ ያወቃሉ? ወይስ የኬኒያ ጋላዎችቹንም ኢትዮጵያዊያኑን ኦሮሞዎች እንዳሳሳትዋቸው ጭምር የኬኒያዎችንም እንዲሁ እያሳሳቱ “ከኬኒያ ገንጥለው” ኦሮሚያ ለምትባል አዲስ የቅዠትና የፋሺስቶች  ቅርምት ሊጨምሯቸው ዕቅድ ስላላቸው?

እነዚህ ክፍሎች “የዜጋነትና የድምበር ትርጉም ስለማይገባቸው” ድምበር እየተሻገሩ፤ አንዲህ ያለ ብጥብጥ እየፈጠሩ ስለታዘቡ መሰለኝ ባለፈው ወር፤ በኢትዮጵያና በኬኒያ የፀታ የጋራ ስምምነት ሲያደርጉ “ኦ ኤል ኤፍ” የተባለ “thug” “ወረበላ” ሲሉ የኬኒያ ጋዜጦች፤ቃል በቃሉ፤“thug” “ወረበላ” ሲሉ ጽፈውባቸዋል። ኬኒያኖቹ እራሳቸው በደምብ አድርገው የዚህ ወረበላ /mob ምንነት ስለሚያውቁ፤ የኬኒያ ጋሎችን ሰብከው ኬኒያንም ለማበጣበጥ፤ እስከ ታንዛኒያ ድረስ እየሰበኩ እንደነበረ አንድ ሰነድ ሳነብ አጅግ ገርሞኛል። ይህ ዕብደት ከማለት አልፋችሁ ከዚህ የከፋ ሌላ ቃላት ካላችሁ እባካችሁ ፈልጋችሁ በክፍተቱ ሙሉት።

እንግዲህ ይህን ላሳያችሁ የፈለግኩት ውሸታሞቹ ወደ ኬኒያ ድረስ ማመልክቻ እየጻፉ ኬኒያዎችንም “ጋላ” አይደላችሁም” ኦሮሞ ነው የምትባሉት እያሉ የስደተኛ ህይታቸው የኬኒያን ሕግና ስርዓተ ትምሕርት አክብረው ህይወታቸው እንዳይገፉ፤ አገራቸው ያልሆነውን ኬኒያን ሌላ ብጥብጥ ለመፍጠር የኬኒያ ዜጎች ምንም ሳይሰማቸው፤ ስለ እነሱ አፈቀላጤ ሆነው “ጋላ” የሚለው የጥንቱ እውነተኛ የነገድ ስም “ኦሮሞ” እንዲባል እዛም በስደት እየኖሩ በህፃናት ሕሊና ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው “ሁውከትና የራስ የበታችነት ስሜት” ለመፍጠር፤ ድምበር ተሻግረው እንኳ ሳይቀር የሚሰሩት ባሕርይ ለመግለጽ ነው መረጃው የጠቀስኩት። የኬኒያ የጋላ ነገዶች ከተቀረው የኬኒያ ሕዝብ ጋር በስም ለውጥና አጠራር ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ባሕሪያቸው ድምበር ሸገርም አልተዋቸውም።

እሺ ኢትዮጵያ ያሉትንስ “አማራዎች/ምኒሊክ/ሃይለስላሴ…..” ጋላ ብለው ስሙን ሰጡን ይበሉ፤ እሺ፤ ኬኒያና ሶማሌ ያሉትንስ ስማቸው ካልሆነ ጋላ ብሎ ማን ሰየማቸው? ምኒሊክ/ሃይለስላሴ/አማራ? በየት በየት ተሻግረው? አረ እባካችሁ እነኚህ ሀፍረተቢሶች በምን ቃላት አንደምገልጻቸው አሁንስ እየጨነቀኝ ነው!?
እንግዲህ ጋላ የሚባል ስም ለምን እንዳስጠላቸው፤ እራሳቸው ከሚፈለስፉት ቅዠት በቀር ሌላ መረጃ የላቸውም። EEDN በኖርኩበት የውይይት መድረክ ውስጥ ይህንን ለብዙ አማታት እንዲያብራሩልኝ ፤ምንጫቸውም እንዲያቀርቡ ጠይቄአቸው፤ ከመሪዎቹም ቢሆን አንድም መልስ ለመስጠት አልቻለም። ዛሬም “ድፈን፤ድፈን ነው መልሳቸው”። አሳዛኙ ግን፤ የዚህ ነገድ ክፍሎች በራሳቸው ላይ “የበታችነት ስሜት የሚፈጥሩ የአሮሞ ምሁራን ግን፤ ከዚህ ሊማሩ አልቻሉም። ኦሮሞ የሚለው አንዳንዱ “ሖሮሞ” “ዎሮሞ” “ሃራሙያ” እያለ ገበሬው ስለሚጠራው እሱንም አስጠልቶናል እና ‘ኦሮሞ’ የሚለው ትትን “ሌላ ስም ለውጠናል” ይሉን ይሆናል። ማን ያውቃል! ከጋሊቷ ልጅ ኢትዮጵያዊ ፉከራ ፤ ወደ ኦሮሚቷ ልጅ ከዚያ ደግሞ “ነገ ሌላ ስም ሊፈጥሩ ይሆናል (ልክ እንደ ተለያዩ ባንዳራዎቻቸው፤ መጠሪያቸውም እንደዚሁ)።ማን ያውቃል። ጠርጥር! ያለ ማን ነው፤አንድ ፀሐፊ አንቢቤአለሁ፤ ጥሩ አባባል; ጠርጥር!

ወደ ርዕሳችን እንመለስ።ኢትዮጵያ ሳይሆን አቢሲኒያ ነው የሚሉን። እኛ ኦሮሞዎች በዲሞክራሲ እንተዳደር ነበር፤ ግን አቢሲኒያዎች/ምንሊክ “የቅኝ ተገዢአቸው አደረጉን” ገዙን ይሉናል። አንድ ባንድ እንመለከታለን።፡የጋላ ነገድ ዲሞክራሲ ነበር እያሉ ይዋሻሉ። ስሙም “የጋዳ ሥርዓት” ይባላል ይላሉ። እኔ ግን “ፕሪሚቲቭ/ፐሪማቱር ፋሺዝም” እለዋለሁ። በዝርዝር ባጭሩ እንመለከተዋለን። የዛሬዎቹ “የግንጠላ ጠበቃዎችና፤ የኦሮሞ ባንቱስታን የክልል አስተዳዳር አቀንቃኞች” የሆኑ የኦሮሞ ፋሺስቶች ባሕሪ መነሻ የሚያደርጉት፤ “ከዚያ ከፕሪማቱር የገዳ ፋሺዝም ዘመን የመነጨ” ባሕሪ ነው። ያንን ያከብሩታል። ለኦሮሞ ህልውናም ዛሬ እያሳዩን ያለውን “የቦታ ሄጂመኒ/ነጠቃ/ወረራ/” መሰረታዊ መመሪያቸው ሲሆን፤ ከዚያ ዘመን ጀምሮ ወደ ሰፊዋ ኢትዮጵያ፤ ከዚያም ኦሮሞዎች “ደርግ የሚል ወታደራዊ ስርዓት መስርተውና ተሰግስገው ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ” ያሳዩት ፋሺስታዊ ስነምግባር እና ከዚያም ሲወድቁ፤ ያደራጁትን “ኦነግ” የተባለው ገንጣይና እጅግ “ፋሺስታዊ” የሆነ ወንጀለኛ ድርጅት ከወያኔ ጋር ሰምሮ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማራዎችና ኦሮሞ ወታደሮች በትኖ፤ ለልመና ዳርጎ፤ የቀሩትንም ጨፍጭፎ፤ከክልሉ አስወጥቶ የሰራውን ግፍ፤ ታሪክ ዘግቦታል።

(ደርግ ኦሮሞዎች ነበሩ ያስተዳዳሩት ሲባል፤ ግራ የሚገባቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ምስጢር ነው የተገለጸልን። አስገራሚው ደግሞ “ደርግ” አማራ እያሉ ኦነጎች አውቀው ሲወነጅሉት፤ ደርግን የመሩ አማራዎች ሳይሆኑ አብዛኛዎቹ “እራሳቸው ኦሮሞዎች ነበሩ”። ወንጀለኛው ኦነግም፤መኢሶንም የደርግ ዋና የቀይ ሽብርና የወንጀል ታካፋዮች ነበሩ።ከቁንጮው ከሊቀመንብር መንግሥቱ ጀምሮ፤ተካ ቱሉ፤ተስፋዬ ገብረኪዳን፤ ደበላ ዲንሳ፤ደምሴ ቡልቶ፤ መርዕድ ንጉሴ፤ ረጋሳ ጂማ፤ ወብሸት ደሴ… ስንቱን ኦሮሞ ባለስልጣኖችንና ወታደራዊ አዛዦችና ደብዳቢ ካድሬ ኦሮሞዎች የነበሩትን ስንት ብለን እንቁጠር….! የፖለቲካ ክፍሉን የመሩት እነ ነገደ ጎበዜና፤ሃይሉ ፊዳ የማሳሉትን  የፖለቲካ ቀያሾቹ  ስንት ብለን እንቁጠራቸው! አሁን፤ አሁን፤  ደርግን በአማራነት እየከሰሱ “አማራውን” ሲያብለጠልጡት መስማት አጅግ ይገርማል። አስገራሚው ደግሞ “ባለፉት ግፈኛ ስርዐቶች” ኦሮሞ ሕዘብ ተበድሏል ይላሉ፤! ደብዳቢው፤ግፈኛውማ ገዢው፤ማን እንደነበር እየተዋወቅን! ) ‘ ውሸቱ እንደካሁን በፊቱ ውሸት እየተቀበልን በቸልተኛነት መቀጠል የለበንም፤! ግልፅ ግልፁን! እንነጋገር።

ቀስ በቀስ በለመዱት ብልጣብልጥ ስልታቸው፤ ቀስ ብለው በወያኔ ትከሻ ተንጠልጥለው፤ የገቡት፤ ኦነግ ብቻ ሳይሆኑ፤ የኦሮሞ “አክራሪ” እስላማዊ ፋሺስታዊ ኦሮሞ ድርጅቶች” እንዲሁም፤ ለ24 አመት የቀጠለ “የቀኝ አክራሪ ፋሺስታዊ ኦሮሞ ምሁር” እና አሁን እንደ አዲስ የተፈጠረው “በወጣት ኦሮሞ ምሁራን” የቀጠለው አዲሱ “የሜንጫ ኦሮሚያ አብዮት” የሚባለው ምሁራን የሚመሩት ፋሺስታዊ ቅስቀሳውን ባጭሩ ዳስሰን እንሰናበት።

ባጭር አገላለጽ፤ አሁን ላለው “ኦሮሚያ ኬኛ” የተማሪዎች መፈክር ምንጩ የሚከተለው ይሆናል።

 1)  ጋላዎች ከቦታ ቦታ፤ ካገር አገር፤ከግጦሽ ወደ ግጦሽ፤ በመዘዋወር ጥንት ከብት በማርባት ሲኖሩበት ከነበሩበት “ገላን” ከተባለ ከታች የኢትዮጵያ ጠረፍ በመነሳት እነኚህ “ጋላ” በመባል የታወቁ የተለያዩ የጋላ ነገዶች ወደ መሃልና ወደ ከፍተኛው ቦታ፤ አንዲሁም ምስራቅና ምዕራብ፤ እንዲሁም ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ  በየማአዝናቱ ተከፋፍለው ንብረት/አገር/መሬት/ሴት/ከብት ለመዝረፍ የተከተሉት ፋሺስታዊ የወረራ ጭፍጨፋና ቤቶችን ገዳማትን በማቃጠል፤ የተፈጸመ ፋሺዝም  እንመለከታለን፡

 2) በደርግ ወቅት የተካሄደው ኦሮሞዎች የመሩት ፋሺስታዊ ስርዓት

3) በወጣት ምሁራን ኦሮሞዎች የተካሄደው ኦነግ፤ እና “ኢስላማዊ ኦነግ” እንዲሁም “የሜኒጫ አብዮት” ተብሎ የሚታወቀው “የኦሮሞ ፋሺዝም” ያካሄደው በአማራ ነገድ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ።
እነዚህ የኦሮሞ ፋሺስታዊ ስርዓቶች ማለትም “From Fascism to Fascism (Aleme Eshete) ወይንም በኔው አገላለጽ “The Recycling of the Ormo Fascism!” The third cycle of the oromo Fascism” (Getachew Reda) ወይንም “ሦስተኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺስታዊ አብዮት” ምንነት በየተራ እንመለከታቸዋለን።           

የገዳ ሰርዓት የጀመረው እጅግ ላ ቀር የሆነ የጭካኔ አስተዳደሩን እንመለከታለን፤ ከዚያ ያነሳሁዋቸው በየደረጃቸው ያሳዩት ፋሺስታዊ ድርጊቶችን ባጭር ባጭሩ እንመለከታለን። ከዚያ ማን ነው የተበደለው? ማን ነበር ስርዓት ላይ የነበረ፤ አሁን ኦሮሞዎች “የኛ ነው” እያሉ ማንም ሰው መግባት ማረስ፤መውጣት፤ማስተማር ፤ማስተዳዳር፤መኖር፤ ካለ ኦሮሞዎች በጎ ፈቃድነት “አይፈቀድለትም” በማለት የራሳቸው አጥር አጥረው ለግንጠላ እየተበረታቱ ያሉ ወጣቶችን “ራስ በራስ” ማስተዳዳር ማለት “ሞብ ሩል” የወረበሎች/ኦሊጋርኪ ስርዓት እንጂ “የግለሰብ ነፃነት” የሚባል ነገር “በነገድ ፌደራሊዝም ከቶ መጠበቅ ቅዠትና ስህተት መሆኑን እንመለከታለን።

እነዚህ አሁን ሰፊ መሬት አለን፤ ሰፊ ነን፤የኛ ነው፤ ማጆሪቱ ሩል….ወያኔ ራሳችን አንድናስተዳዳድር “በነገድ ፌደራሊዘም ሕገመንግሥት ተፈቅዶልናል” ወዘተ እያሉ የሚፎክሩበት “ክልል” የማን መሬት ነው? የኢትዮጵያ ሕዝብ መሬት ነው! አይደለም እንዴ? ዜጎች አይደለንም የሚሉ ከሆነ ተማሪዎቹ በግልጽ ይንገሩን።
ሆኖም እነሱ ወደ እሚሉንም ብንሄድም፤ ‘መብታችን በሕገመንግሥቱ መሰረት” ራስችን እንድናስተዳድር ይፈቀድልን፤ የሚለው ቅዠት፤ የክልል ፌደራሊዝም ስርዓት “ሞብ ሩል/የወረበሎች/ ያካባቢ የመሳፍንቶች ሰርዓት አስተዳደር ነው” ነው። ማንኛውንም ኗሪ ራሱን ሊያስተዳድር ኣይፈቅድለትም። ምክንያቱም “ፈቃጅ ካለ፤ በማንኛውም ጊዜ ፈቃጁ የሰጠህን ፈቃድ ሊነጥቅህ ይችላል”። ምክንያቱም ኤትኒክ ፌደራሊዝም “ሞብ ሩል” ስለሆነ” “ዐለም ዓቀፍ መስፈርት የተከተለ “ሰውን እንደ ሰውነቱ” በሕግ አያውቀውም።  ፀባዩ አይፈቅድለትም። “ኮለክቲቭ ራይት” ብቻ ነው የሚያውቀው።

ሁሌም የጅብ መንጋዎች ከታችም ከውጭም፤ከላይም ስለሚያፈራ “ኦሊጋሪኪ/ሩል” እንጂ ግለሰቦች ነፃነት የላቸውም። መሬት የመንግስት ነው፤ የክልል ነው። የግለሰብ አይደለም። ስለሆነም፤ ንብረት ስለሌለህ “ነጻ’ ልትሆን አትችልም፡ “የፌደራልና የክልሉ ዴፐንዳንት/ጥገኛ ነህ”። ልትሸጥ፤ልትለውጥ አትችልም። ተከራይ ጭሰኛ ነህ። ቴናንት ነህ። ዜጋ አይደለህም። የክልሉ ወይንም የማአከላዊ ፌደራል መንግሥቱ ጭሰኛ ነህ ከሆንክም፤ “ነፃ” ዜጋ አይደለህም። የክልሉ መንግሥት ጭሰኛና ተከራይ እስከሆንክ ድረስ ስለ የመሬትና ንብርት መከራከር መብት “የቅዠት መብት” ብቻ ነው ሊኖርህ የሚችለው። ክልል ፌደራሊዝም ያንተው የግለሰብ ሁለተኛው ላንድ ሎርድ/ጌታህ ሲሆን/ የእርሱም ዋናው ጌታ “ማዕከላዊ መንግስት/ፌደራል” የሚባል “በሞብ ሩል ሕግ” የሚመራ አካል አለ። በነዚህ ውስጥ “አንተ” የሁለቱም “ጭሰኛ ነህ”። አራት ነጥብ!!!!!!!!

አሁን ኦሮሞዎች የያዙት መሬት እንዴትና ከማን ነጠቁት?  

ስለ ጋዳ  ስርዓት  ትንሽ ልበልና ልደምድም። እውነት ነው ጋላዎች የተለያዩ ጎሳዎች ነበሩ። በዘመኑ ወደ መሃል ኢትዮጵያ የተስፋፉ “ጋላዎች” አንድነት አልነበራቸውም። እርስ በርስ ሲጋደሉና ሲዘራረፉ አንደነበር ሊቁ ጌታቸው ሃይሌ ገልጸውልናል። ቀደም ብየ የገለጽኩት መጽሐፋቸውን (የአባ ባሕርይ ድርሰት ተመረኩዘው ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጎሙልንን ተመልከት)፤ ለዘመናት ጀምሮ የተረጋጋን የኢትዮጵያ መንግሥት “ጋላዎቹ” ከገቡ በላ፤ አገሪቷን ብትንትኗ  እንዳወጧት አባ ባሕርይ ንብረታቸውና መጽሐፍታቸው እንዲሁም ገዳማቸው ጅማ ውስጥ ሲያቃጥሉላቸው ያዩትን ነግረውናል።

ጋዳ ወይንም “ሉባ” (ኦሮሞዎች አስተዳደር ዲሞክራሲ ነው) ተብሏል። ምን ማለት ነው? እኔ “ፋሽሰታዊ የወንዶች ራስን በራስ የማስተዳዳር ስርዓት” እለዋለሁ። 5ቱ ጋላ ነገዶች  8ት፤ 8ት አመት ይሾማሉ፤ የተሾመው መሪ “ሉባ” ይሉታል። ስርዓቱ ወንዶችን በየበላይነት ያስቀመጠ፤ ወንድም ቢሆን ለሥልጣን እርከን ለመድረስ ፤ግድያ፤ብልት ሰለባ ፤ጸጉር በቅማልና በቁጫጭ መበላትን፤ ልጆችን መጣልን ወዘተ…ወዘተ.. ያጠቃልላል። ዲሞክራሲ የሚሉት ይህንን ፋሺስታዊ ባሕሪ ያካተተ ነው ዲሞክራሲ ነው እያሉ ወጣቱን በዛሬው ባሕሪ እንዲጓዝ የሚመሩት።

ይህ ሁሉ የዛሬዎች ኦሮሞ ምሁራን ውሸት ከጥንት ጀምሮ “ከጋላ” ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ሕዝባዊ ዲሚክራሲ ነበረን፤ አቢሲኒያዎች/አማራዎች/ምኒሊክ…ወዘተ..  ነጠቀን፤ የሚሉትን ቅዠታቸውን እስኪ ታሪኩን ባጭሩ እንመልከትና እንደምድም።

የጋሎችን ታሪክ የተወሉንን የመጀመሪያው የዓይን ምስክርና የጋላ ታሪክ ዘጋቢ አባ ባሕሪይ የጻፉትን በሊቁ ጌታቸው ሃይሌ የተተረጎመ (የአባ ባሕሪይ ድረሰቶች በገጽ 152 የተዘገበውን እንመልከት።
“…ከማህላቸው አባ ሙዳ የሚሉትን አንዱን ወንድ አይሁድ ሙሴን፤እስላሞች መሐመድን እንደሚተማመኑበት ይተማመኑበታል። ከሩቅ አገር ድረስ ወደእሱ እየሄዱ እጅ እየነሱ የማሸነፊያ ቡራኬና የመዝረፊያ ቡራኬ ይባረካሉ። ምራቁን በድኝ ላይ ይተፋላቸዋል፤ እነሱም ከሚወጉት ዘንድ ሁሉ የውጊያ ዕለት ተስፋ እንዲሆናቸው (ምራቁን) በድኝ ቋጥረው ይይዙታል።

ደግሞ ጋሎች ሁሉ በየነገዳቸው ሁነው አምስት መደቦች ናቸው። (አምስቱ መደቦች) በየተራቸው በየስምንት ዓመት ይሾማሉ። የተሾሙት ባለተራዎች ሉባ ይባላሉ። ይኸ ሹመት ማለት ሉብነት እስኪደርሳቸው ድረስ እስኪታቸውን አይገዘሩም፤ወንድም ሆነ ሴት (ልጅ) ሲወልዱ (ልጆቹን) እደጅ ይጥሏቸዋል እንጂ  እንደወላጆች ሥርዓት አያሳድጓቸውም።

ደግሞ በሹመታቸው ዘመን ሰው ካልገደሉ የራሳቸው ጠጉር አይላጩም። የሞት ፍርድ እንደተፈረደበት ዘወትር እያለቀሱ በሐዘን ላይ ይኖራሉ እንጂ ሰው ለመግደላቸውም ምልክት (የሚሆነውን) ቁንጮ አያወጡም።

  እነዚህን የጋላ ልምዶች ሁሉ ንጉሥ ሥልጣን ሰገድ አስተዋቸው። በአብ፡ በወልድ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዲያጠምቋቸው አዘዘ። ወረነሻዎች ሁሉም ተጠመቁ። የጌታችን የመድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስን የሥጋውንና የደሙን ምስጢር ተቀበሉ። (ቆረቡ)። ከክርስትያኖቹ ሁሉ ጋራ ያንድ እረኛ አንድ መንጋ ሆኑ። ወረንሻዎች ከሰባቱ በረንቱማ ነገዶች አንዱ ነገድ ናቸው።” (ጌታቸው ሃይሌ - እንደላይኛው ገጽና ምንጭ)።
ክቡራን አንባቢዎቼ፤ ይህ እውነታ ነው የኦሮሞ ምሁራን “ዲሞክራሲ ነበረን” እያሉ ሳይሸማቀቁ በየጋዜጣ፤መጽሐፍት ጭምር እየጻፉ አግላይና፤ በነገድ ሐረግ ብቻ የሚተዳደር ስርዓት፤ ወንድ የሚነግሥበት፤ ሴት የምትናቅበት፤ለዚህ ስርዓት መሪ ለመሆንም “ዘግናኝ የሆነ፤ ሰውን በመግደልና በመስለብ ጭካኔን እንደ አዋቂና አስተዳዳሪ ማሳያ ተደርጎ፤ የሚወሰድ “የጫካ ሕግ” ነው፤ ዲሞክራሲ ነበር እያሉ ማሕበረሰቡንና የዋህ ፈረንጆችን እየዋሹ የሚያሳስትዋቸው።

ይህ ስርዓት ነው፤ራስን በራስ በዲሞክራሲ ስንተዳዳር የነበረውን ሥርዓታችን አቢሲኒያዎች አፍርሰው ኮሎኒ አደረጉን እያሉ የሚመጻደቁብንና ወጣት ኦሮሞውን የሚያጃጅሉት (ልክ አንደ ኤርትራ አሳፋሪ ውዥምብራም ፤ውሸታም ሊሂቃኖች)። እነኚህ ነገዶች “ሉባ” በሚባለው ዝርፍያውና ወረራው እንዲቀናቸው እየመረቀ ወደ ወረራ ሲያሰናብታቸው፤ አሁን ድረስ ተንሰራፍተውበት የሚታዩትን እስከ ትግሬ ድረስ መጥተው የሰፈሩበት ምክንያት በሰላም ሳይሆን “ወረራና የጭፍጨፋ” ድርጊት እየፈጸሙ ነበር የያዙት፦

ከላይ የጠቀስኩት ምንጭ እንዲህ ይላል፤-

(መስከረም የ 1633 ዓ.ም መጀመሪያ፤ዕለት ቅዳሜ፤(ዘመኑ) ማቴዎስ፤
(ንጉሡ) ጎጃም ሄደ። በዚህ ዓመት ስሙ ለበቻ፤ መጠኑ አርባ ሺሕ የሆነ ጋላ ወደ ትግሬ መጣ፤ ሰራዌንም አወደማት። ሲመለስ የፅራዕና የተምቤን ሹማምንት በምድረ አላ ላይ ከበው ምንም ሳያስተርፉ ፈጁት። ንጉሡ በዶቢት ተቀመጠ። የበኽር ልጁ አቤቶ ቄስጠንጢኖስ ሞተ። (ምንጭ የአባ ባሕሪይ ድርሰቶች፤ ደራሲ ጌታቸው ሃይሌ፤ ገጽ 136)

 እንግዲህ በአለም የተደነቀ ራስን በራስ የማስተዳዳር ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ኦሮሞች ነበራቸው፤እያሉ የሚዋሹንን የጋላዎች ዲሞክራሲ እስከ ትግሬ ድረስ በዝርፊያ፤በግድያና በወረራ የመስፋፋት ባሕሪይ በየክፍላተ ምድሩ “ጥንታዊ ፋሺዝም” ኦሮሞዎችም እንዴት ያራምዱት እንደነበረ ባጭሩ ለማየት በቅተናል። ይህ ሁሉ ርቀት ተጉዘው ባጭር ጊዜ የኢትዮጵያን ሰፊ መሬት ሊቆጣጠሩ የቻሉበት ምክንያት አስቀድሜ እንደገለጽኩት፤ የተመለከትናቸው የጋላ ከብት አርቢዎች፤ ያገሪቱ /ኢንዲጅነስ “ነባር ሕዝብ” እያባረሩ፤ ሰው የሌለበት ጭር ያለ “ቤት የሚጠብቅ” ጠባቂ “ከልብ” (ውሻ) ሳይቀር፤ በጦር እየወጉ፤ መሬቱ፤ሚስቱ፤ንብረቱ፤እርሻውና ቤቱ፤የተነጠቀበት ምክንያት “ግራኝ አህመድ” አገሪቷን አቃጥሎ ስላዳከማት፤ ክፍት ቦታ አግኝተው ፤ ሰተት ብለው መላውን ሰፊ ቦታ ተቆጣጥረው፤ ዛሬ “ኦረሚያ ኬኛ” (ኦረሚያ የኛ) ወደ ማለት የደረሱበት ዋና ምንጩ “አገር ያወደመ” የጋሎቹ ወረራ ውጤት ተጠቅመው ነው ዛሬ “በክልላችን ማንም ሰው ዝር እንዳይል” በማለት ክልል የተባለ ባንቱስታናዊ “ዘረኛ አስተዳዳርን” በአክብሮት ተቀብለው ወደ ግንጠላ ጉዞ እያዘነበሉ “አንቀጽ 39ኝን” ማስፈራሪያ ካርድ እያሳዩ ሊያስፈራሩን እየሞከሩ የሚገኙት።

ለማጠቃለል፤በ24 አመት ውስጥ ለእልፍ አእላፍ አማራ ሕብረተሰብና ገበሬ ከኦሮሞ አካባቢ አገርህ አይደለም “ውጣ” እየተባለ የተባረረ፤እርጉዞች ማህጸናቸውና ሆዳቸው በቢላዋ የተዘረገፉበት፤ህጻናት በፋሺስታዊ ቢላዋ “አንገታቸው የታረዱበት” ንግዳቸውና አንብረታቸው  እየተዘረፉ፤በግፍ የተጨፈጨፉ አማራዎች “ዜግነታቸው” የተነጠቁበት ምክንያት “የኦሮሞ ባንቱሳናዊ “የክልል” አስተዳዳር ቀያሾችና ጀሌዎቻቸው ምክንያት የቀየሱት “ሦስተኛው ዙር *የኦሮሞዎች የፋሺዝም* አብዮት ውጤት መሆኑን ልነገራችሁ እፈልጋለሁ።

“ሦስተኛው ዙር *የኦሮሞዎች የፋሺዝም* አብዮት ተጠያቂዎች እነማን ናቸው? ወያኔዎችና የወያኔ ጀሌ ኦሮሞዎች፤እንዲሁም፤ በዕድሜ የገፉ “የኦነግ መሪዎች”፤ እንዲሁም “የሜኒጫ አብዮት” ተብሎ በእስላም የኦሮሞ ምሁራን ወጣቶች ልብ ያደረው እነ “ጃራ” የመሰረቱት “እስልምናን ከፖለቲካ አቀናጅቶ፤ የኦሮሞ እስላም ማሕበረሰብ፤ ኦሮሚያን ነፃ አድርጎ፤ እስላማዊት ለማድረግ፤ የተመሰረተው “ኦሮሞአዊ ፖለቲካል ኢስላም” አራማጆችና ተከታዮቻቸው ናቸው።

የኦሮሞ ፋሺዝም” ያካሄደው በአማራ ነገድ ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ አልፎ፤ ‘አሮሚያ” ነፃ ካወጡ ፤ኦሮሞ ማሕበረስብ እንደሚቀዳጅ የተሰበከውን “ማርና ወተት፤ራስን በራስ ማስተዳዳር ዲሞክራሲ ያገኙ ይሆን? ወይስ ኢስላሚክ ኦሮሚያ፤ በሸሪዓ እንድትተዳዳር በሚሉ ክፍሎችና፤ “ሞብ ሩል” በሚከተሉ “ኦነጎችና መሰል ተመጻዳቂ ምሁራን ኦሮሞዎች” ፍጥጫና እንደ ሶመሌ “የዕርስ በርስ” ፍጅት ተከትሎ “የኦሮሞ ሜንጫ ካሊፋት አብየተኞች” የበላይነት ይዳኙ ይሆን? ይህ ከሆነ ወጣት ኦሮሞ ሴቶች ምን ይገጥማቸው ይሆን?  “ማስተማሪያ አትንሳኝ” ይባላል እና ትምህርት ቢሆናቸው የአፍጋኒስታናዊያን ወጣት ሴት ልጃገረዶች የተናገሩትን ትምህርት “በጥቅስ የተናገሩትን” አንብቡና እንሰናበታለን።

"Every girl," recalled Saira Noorani, a female surgeon, "could go to high school and university.We could go where we wanted and wear what we liked. We used to go to cafes and the cinema to see the latest Indian film on a Friday and listen to the latest music. It all started to go wrong when the mujaheddin started winning. They used to kill teachers and burn schools. We were terrified. It was funny and sad to think these were the people the West supported."

ኦሮሚያ ተመስርታ ያ ሁሉ ቀውስ ቢመጣ፤ ካፌና ሲነማ መሄድ የለም፤ እምየ ኢትዮጵያ ሞታለች፤  መሰደጃ፤መላወሻ መረማመጃ፤መሸሺያና መጠለያ መንገድ አይኖርም። ሁሉም እንዴት እዚህ አረንቋ ልንገባ ቻልን? የሚል ሶማሌዎች መልስ ያጡበት ጥያቄ “በየአጥሩ ታጥሮ” “እየተጫፋጨፈ” መልስ ሊያገኝ ቢለፋ፤ መልስ ሰጪ አይኖርምና ከዚያ ከመአቱ ይሰውረን!  አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ Ethiopian Semay)  getachre@aol.com