Monday, December 23, 2019

ከኢትዮጵያ ሰማይ ድረገጽ ተከታታዮች ከሚደርሱኝ ደብዳቤዎች አንዱን ስለ ኤትርትራኖች የተላከልኝ ደብዳቤ ልጋብዛችሁ፡ከኢትዮጵያ ሰማይ ድረገጽ ተከታታዮች ከሚደርሱኝ ደብዳቤዎች አንዱን ስለ ኤትርትራኖች የተላከልኝ ደብዳቤ ልጋብዛችሁ፡

ፎቶ ጌታቸው ረዳ

ይህ ደብዳቤ ሲላክልኝ ሰሞኑን አንዲት ታዋቂ እህታችን በዚህ ፌስቡክ መገናኛ ከተጃጃሉት ኢትዮጵያውያን ዜጎች መካከል አንድ ቡድን ወደባሕረ ነጋሽ” (ኤርትራ) ሄዶ የአማርኛን እስክስታ ሲደልቁ የሚያሳይ ፎቶግራፍ ለጥፋ ትርጉሙ በማይታወቅ ስሜት ለመኩራራት የቃጣትን አስመልክቶ ኤርትራ ሄዶ ሓላፊነቱን ሲወጣ በጦርነቱ ወቅት አካሉ የጎደለ የቀድሞ ወታደር የሆነው ካንድ ወዳጄ ምነውይህችን ወጣት መልስ ብትሰጥልን ብሎ ቁጭቱን ልኮልኝ አንብቤ ሳልጨርስ ወዲያውኑ አንድ ሌላ የቅርብ ወዳጄ ደግሞ ኤርትራውያንን አስመልክቶ የሚከተለውን ደብዳቤ ላከለኝ እና ደብዳቤው ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘሁት ከናንተው ጋር ብጋራው አይከፋም ብየ ይኼውአብይ አሕመድበተባለውበወያኔው ኩሊየተከፈተላችሁ የኤርትራውያኖቻችሁ ግንኙነት ከመጠን በላይ ለምትቀብጡ ቀበጥ ማሃይሞች ይህንን ደብዳቤ አንብቡና ኢትዮጵያችሁ በተለይአማራ ክልላችሁእምን ጉድ እንደሚገኝ ላስነብባችሁ።


የወዳጄ ደብዳቤ እንዲህ ይላል

አቶ ጌታቸው ከዛ አገር ጥሩ ነገር ላይሰማ ንግርቱ ነው መሰል፡፡ ኤርትራ የሚባል አገር ሀብቱ ከአንድ የመርካቶ ነጋዴ የማይበልጥ ተምበርክኮ የአማራ ከልል መጋበዙ ምን ማለት ነው? ሲጀመር ሻቢያ አማራ ክልል ምን ይሰራል? አማራዉን ምጥጥ አድርጎ የጨረስ ሻቢያ ይህ ክብር ይገባዋል ወይ? በእርግጥ ብአዴን ዉስጥአማሮችአሉብት ወይ? ይሄ ነገር ግራ እያጋባኝ ሂዷል፡፡ 700000 የሚበልጡ ሻቢያኖች ኢትዮጵያ ዉስጥ ይኖራሉ ይባላል ውርደት ቀለቡ የሆነ ህዝብ፡፡ ባለፈው ዘረሰናይ አንድ ከበሮ ለቀነኒሳ ልኮለት በአንድ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ጋዜጠኞች በጣም ምርጥ ነዉ ብለው ሰማይ ሲሰቅሉት ብታይ በጣም ያሳዘናል እንደዉም አንደኛዋ "እንደዉም ከኤርትራ መጥቶ በጣም ነው የሚያምረው" ብላ ስታሞግስ አይቼ በጣም አዘንኩ እንደሚመስለኝ ሚዲያዉን ሳይቆጣጠሩት አይቀሩም ቀጥሎ ኢንቨስትመንት ውስጥ ይገቡና አገሩን ባዶ ያደርጉታል፡፡

ይገርምህል ኮለኔል በዛብህ ጴጥሮስ ኤርትራ ተመትቶ ሲወድቅ ፓርቲ አድርገው ሲጨፍሩ የነበሩ ኤርትራውያን ጠቅላላ አዲስ አበባ ገብተው ቤት ገዝተው፤ መኪና ከነ ተሳቢዉ ገዝተው ንግዱንና ሌብነቱን እያጧጧፉት ነው እንዲህ ነች ኢትዮጵያ ያሳዝናል፡፡”  ይላል ከወዳጄ የተላከልኝ ደብዳቤ።

ይህ ወዳጄ ኢትዮጵያ ሄዶ በነበረበት ወቅት አብይ እና ኢትዮጵያ በሚመለከት የጻፈው አስገራሚ ሰፊ ዘገባ በየድረገጹ ተሰራጭቶ እንደነበር አስታውሳለሁ። ዛሬም አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዜጎችአማራዎች ወደ ኤርትራ ሄደውየጎንደርኛ/ጎጃምኛ..” ዳንኪራ ስለመቱ ሰማይ የሚጨብጡ ዜጎች የሰጣቸው ትርጉም ምን እንደሆነ አልገባኝም። ዳንኪራ መቺዎቹ በወላጆቻቸውና ወንድም እህቶቻቸው አጥንት በተቀበረበት መድረክ ሆነው ነው እየጨፈሩ ያሉት። ይህ ለምን አንደሚያስደስት አልገባኝም።

የእነ ታደሰ ሙሉነህ አሰቃቂ እስራትና ስለ እነ ኮለኔል በዛብህ ጴጥሮስ ሕይወት እና ስለ ኣእላፍ ወታደሮችቻችን ተጋድሎ የማትጨነቁ ኢትዮጵያውያን የሻዕቢያን ባንዴራ እያውለበለባችሁ ኤርትራ ውስጥ አማርኛ እስክስታ ስለተዘፈነ የምታሽቃብጡ ግብዞች ኢትዮጵያውያን ባሳፋሪ የታሪክ ሃዲድ እየተጓዛችሁያስረከብናችሁን አገርአታዋርዷት!!! በሴራ የተነጠቀውን ሉአላዊ መሬት ማስመለስ የናንተ ሓላፊነት መሆኑን አውቃችሁ ካሁኑኑ ኢትዮጵያዊነትን አጥብቁ።

ወደባሕረ ነጋሽሄደው የወላጆቻቸውን ዳር ድምበር ለማስከበር የክብር ሞት ለሞቱት ኢትዮጵያውያን ወታደሮች እና ሲቪል አርበኞች የታገሉት ትግል በዚህ አሳፋሪና28 አመት ግብዝ ብሄረተኛ ትውልድቢናቅም የእምየ ኢትዮጵያ ሉአላዊ መሬት የሚንገበገብላት ሌላ ትንታግ ትውልድና ትንታግ መሪ አንድ ቀን እንደሚነሳ ጥርጥር የለኝም።
ድል-ለኢትዮጵያ
ጌታቸው ረዳ
(ኢትዮ ሰማይ)