Wednesday, June 5, 2024

ድርድርና ምክክር የሦስት ትውልድ ቅጣት በኢትዮጵያ ጌታቸው ረዳ / Ethiopian Semay 6/5/24

 ድርድርና ምክክር የሦስት ትውልድ ቅጣት በኢትዮጵያ

ጌታቸው ረዳ    / Ethiopian Semay

6/5/24

እንት ሰነበታችሁ? 

27 አመትከትግራይ’ የመጡ ትግርኛ ተናጋሪ አሸባሪዎች አሁን ደግሞ ከኦሮሚያ’ የመጡ ኦሮሞኛ ተናጋሪ አሸባሪ “ጋንጎች” 6 አመት ሙሉ በውስጥ የቅኝ (ኢንተርናል አፓርታይድ) አስተዳደር  ከጣሊያኖች በከፋ ሁኔታ ሕዝቧ ፍዳውን እያየ እንደሚገኝ እንደ ዱሮውአሌ ብላችሁልትሞግቱኝ እንደማትችሉ ዛሬ እርግጠኛ ነኝ። አሌ የሚሉ ቢኖሩ በየፌስቡኩ እና አገር ውስጥም ያው የአፓርታይዱ እበላ ባይ ወይንም ግብዝ ሕሊና የተሸከሙ የጽዳት ሠራተኛና ከንቲባ” አበበች አደኔን <<ከፈጣሪ በላይ ፈጣሪያችን አንቺ ነሽ>> ሲሉ የተደመጡ ምናምንቴ አሽከሮች እዚህም እዛም አሉ።

የኔ ትኩረት  የወቅቱ ፓለቲካ አልገባ ብሎአቸው በአዝጋሚ ሂደት እንደምትጓዘው “tortoise/ኤሊ  የሚንፏቀቁትን ሳይሆን 27 አመት ወያኔ ዛሬም 6 አመት ሙሉ በወያኔ እግር የተተካው የወንጀለኞችና የሽብርተኞች ስብስብ ቡድን (አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ፓርላማ ተብየው ውስጥ በአንደበቱ አሸባሪዎችና ገራፊዎች ነን ብሎ እንዳመነው እና ዛሬም ሽብሩን እየቀጠለበት ያለው የወንጀለኞች ስብስብ) የሙታን ሬሳ ድብቅ በሆነ ወህኒ ቤት ማሰር ሲጀምር ‘የኦሮሙማ ፋሺስቶች’ ከዚህ ውዲያ ወንጀል ከሰብአዊነትና ከባሕላችን ውጪ ያላደረጉት የቀራቸው ነውር ምን ይሆን የሚል የኢትዮጵያን ባሕል የምንከተል ኢትዮጵያዊያን አስድንግጦን ከዚህ ወዲህ ምን እርምጃ ወስደን ይህ “አረመን/አረመኔ” ማስወገድ ይቻላል?

ሰሜን ኮሪያ የማትረሳቸው ሦስት መሪዎችን ታውቃለች፤”Kim 11 Sung ፤ Kim Jong 11 ፤Kim Jong Un” ከአባት ወደ ልጅ ከልጅ ወደ ልጅ ልጅ የተላለፈው በሰሜን ኮሪያ  የነገሡት የኪም አል ትውልዶች  'የሦስት ትውልድ ቅጣት' የሚባል አምባገነኖቹ የጻፉት ሕግ አላቸው። አንድ ሰው የነዚህ መሪዎች ዝና ያጎደፈ፤ ወይንም ሥርዓታቸው  የነቀፈ  ተከሳሽ ልጆቹ እና የልጅ ልጆቹ ሙሉ ቅጣትን ይቀበላሉ፡፡ይህም ብዙ ጊዜ የእድሜ ልክ እስራትን ያካትታል።

በጅማ ገጠር ኦሮሞዎች ያሳደጉት ከእስልምና ወደ ‘’ ቆንጤ’’ ሃይማኖት በመግባት ዛር እንደያዘው ሰው እቤተጸሎታቸው ስሚንቶ ወለል ላይ የእምብርክክ እየተንፏቀቀና እየተንከባለለ እመባ እያለቀሰና እንደ እብድ እጮኸ በቪዲዮ ያየነው አብይ አሕመድ የተባለው በሕሊና ስብራት የሚሰቃይ ሕክምና ማየት የሚገባው ይህ ሰው  ጰን ቆንጤ “ፓስተር”  እንደሆነ ቢነገርለትም፤   በማጭበርበር ወደ መንግሥታዊ ሥልጣን ከመጣ ውዲህ “ከአሕመድ ግራኝ” ጭካ ባልተናነሰ ባሕሪ እየተመራ ጥንታዊ ቅርሶችና ሃውልቶች በተከታዮቹ እየተደረመሱ የክርስትያንና የአማራዎች ሕይወት ኩፉኛ እንዲመሰቃቀል አድርጓል፡፡

ኢሳያስ አፈወርቂ በሚያስተዳደራት ርትራ ተብላ በምትጠራ ላኛዋ “የሲኦል ምድር” ውስጥም ሁለቱም አምባገነኖች የተቃዋሚዎቻቸው ሬሳ በተወለዱበት መሬት እንዳይቀበሩ በማገድ ታሪክ መዝግቦአቸዋል፡፡

ለምሳሌ ናይዝጊ ክፍሉ የተባለ የኢሳያስ አፈወርቂ ቀኝ እጅ የነበረውና በሻዕቢያ የበረሃ ዘመናቸው የሻዕቢያ ሥራ አሰፈጻሚ አመራር አባልና የግድያ ንድፍ አውጪ የነበረ፤መንግሥት ከሆኑ ወዲህም በአገዛዙ በሚኒስትር ደረጃ ያገለገለውና ዋና የኢሳያስ ቀኝ እጅ የነበረው ወዳጁ ሟቹ ናይዝጊ ለሕክምና እንግሊዝ አገር በነበረበት ወቅት ምስጢር አውጥቷል ወይንም ከተቃዋሚ ጋር አብሯል በሚል ምክንያት ሰውየው ሲታከም ቆይቶ ከዚህ ዓለም ሲሰናበት

ከእንግሊዝ አገር ወደ ትውልድ አገሩ ለቀብር ሲሸኝ ወዳጁ ኢሳያስ አፈወርቂ  የናይዝጊ ከፈሉ ሬሳ ወደ አገር እንዳይገባ ከመከልከሉ የተነሳ፤ ከኢሳያስ ልጆች ጋር አብራ ሰትጫወት ያደገቺው ኢሳያስን “አጎትየ” ብላ ስትጠራው የነበረቺው የናይዝጊ ትንሿ ታዳጊ ልጁ ወደ ኢሳያስ ሄዳ  የአባትዋን የናይዝጊ ክፍሉ አስከሬን ወደ አገር ገብቶ እንዲቀበር ፈቃዱ እንዲሆን ብትለምነውም “አይገባም ፤አይሆንም” ብሎ እምቢ ስላለ በኢሳያስ አፈወርቂ እምቢተኛነት የአዳም አፈር ሳይለብስ ሬሳው ሳይቀበር ከ43 ቀናት በላይ ለንደን በሚገኘው በበረዶ የሬሳ ክፍል ውስጥ ታሽጎ ቆይቶ በኋላ ለንደን በ2004 (በኛ ዘመን አቆጣጠር) ተቀብሯል።

ከዚህ አፎ ባለፈው ሰሞን ባሰነበብኳችሁ ዘገባ በድብደባ ብዛት የሚሞቱ እስረኞችሓሽፈራይ” በተባለ “ሞቃታ የኤርትራ እስርቤት”  ተደብድበው የሚሞቱ እስረኞች የሦስት ዘንዶዎች ምግብ እንደሚሆኑ ያነበባችሁት ወይንም ቪዲዮውን ያደመጣችሁ ታስታወሳላቸሁ፡፡

እኛ ጋር ስንመጣ ደግሞ በደርግም በወያኔም ሬሳ በገንዘብ ተሽጠዋል፤ እንዳይቀበሩም ለቅሶ እንዳይደረግም ታግዶ በየተገደሉበት እንዲጣሉ ተድርጋል፡፡ ዛሬ ደግሞ የጴንጤዎች ፓሰተር ነው ተበሎ ተምበረክኮ ከባለቤቱ ጋር መሬት ለመሬት  እየተንፏቀቀ እያለቅሰና ፈጣሪን ሲለምን ያየነው ይህ አሰመሳይ የ <<ሲ አይ ኤ >> ምልምል (ራሱም አሜሪካኖቹ ጋር አብሮ በምስጢር ቅብብል አብሮ ሲሰራ እንደነበር ‘’ለኒውዮርከር’’ ጋዜጠኛ ያመነለትን አስታውሱ) ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ በስዕሉ ላይ ክታች ከእነ ናሁሰናይ ጋር ይሚታየው ታዳጊ ወጣት ዲያቆን በቀይ ሽብር በአደባባይ “ጅማ ውስጥ” (ይመስለኛል፤ ሰሙና ቦታው ዝንግቸዋለሁ) የፍጥኝ አስሮ ቤተሰብ እያዩ ከመረሸን አልፎ ልክ እንደ  ሩዋንዳው የሑቱው “አካዙ” (Akazu- small circle of Hutu ruling elite)  የተባለ በሑቱው ፕረዚዳንት ሃቢአሪማና ሚስት የበላይነት የሚታዘዘው “ዜሮ-ኔትወርክ” (zero Network) በመባል ሲጠራ የነበረው መሰጢራዊ  የግድያ ቡድን  እንደነበረው ሁሉ ኢትዮጵያ ውሰጥም አብይ አሕመድና የኦሮሚያ ክልል ዋና ገዢ ሺመልስ አብዲሳ በበላይነት የሚመሩት “ኮሬ ነጌኛ” የተባለ “መሰጢራዊ ነብሰ ገዳይ” በማደራጀት ተቃዋሚያቸውን አፍነው እየገደሉና እየሰወሩ 6 አመት ሙሉ ዛሬም መሰጢራዊ ግድያው እየቀጠለ እንዳለ “Reuters” secretive committee of senior officials in Ethiopia’s largest and most populous region, Oromiya, has ordered extra-judicial killings and illegal detentions to crush an insurgency there, a Reuters investigation has found. 

https://www.reuters.com/investigates/special-report/ethiopia-violence-committee/ 

ይፋ አድርጎታል፡

ይህ እንዲሀ እንዳለ በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ገብተው የሥርዓቱ አሽከሮችን ለመግደል የተሰማሩት ሻለቃ ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አብነዘር ጋሻው የተባሉ ሁለት የፋኖ ወጣት ታግዮች በቶክስ ልውውጥ በመገደላቸው ሬሳቸው በተወለዱበት ከተማ በክብር እንዲቀበሩ ወላጆቻቸው “የአጋንንቱ ፓስተር” አበይ አሕመድን ቢማጸኑም አሻፈረኝ ብሎ ሁለቱን ሬሳ በድብቅ እስር ቤት አሽጎ ምን ሊያደርጋቸው እንደሆነ ለሰሚ ዕንቆቁልሽ ከሆነበት ከሚያዚያ ወር 2016 ዓ/ም ጀምሮ እነሆ ወራቶች አስቆጥሯል፡፡

ሰወየው ሕሊናው የቀወሰ ለሰው ሕይወት የማይራራ “አረመን/አረመኔ”ሰው ነውና “ሙታኖቹን ምን ያደርጋቸው ይሆን” በማለት ሌላ ግምት ውስጥ የገባን ሰዎች አለን፡፡

አሳዛኝ ያደረገው ደግሞ የሟቾቹ ሬሳ በሌለበት በየትውልድ መንደራቸው የቀብራቸው ሥነ ሥርዓት ሰሞኑን መከናወኑ የወላጆች ዕምባና ዋይታ በተቀረፀው የቪዲዮ ፊልም ስንመለከት የጣሊያኖች ዘመን በየት ዞሮ መጣብን? ያሰኛል፡፡

እንዲሀ ካለው  ሬሳ ከሚያስር ‘ዱርየ መሪ’  የፖለቲካ ውይይት ይደረግ ቢባልና ተመካካሪዎቹም ሆኑ ተደራዳሪዎቹ እሺ ብለው ቢደራደሩ ሰውየው በምን “የሰውነት ባሕሪ” መለኪያ ተደራዳሪዎቹ ጋር ቀርቦ እንደ ሰው ልጅ ቀርቦ ነው የሚደራደረው? የሚል ጥያቄ እንኳ ቢጠየቅ፤ ተደራዳሪዎቹና ተመካካሪዎቹስ ፣ምን ዓይነት ወፍራም ቆዳ ቢይዙ ነው ከዚህ  ሬሳ አሳሪ ጋር ቁጭ ብለው ምን ትርፍ ልያገኙበት ነው የሚነጋገሩት? የሚልም ሌላው ፈተና ነው፡፡

በአንድ ማሕበረሰብ አንድ መሪ ገዳይ ሲሆን ወይንም የሙታን ሬሳዎች ሲያስር  እናስወግደዋለን እንጂ እንዴት እናወያየዋለን? መደራደር የግድ ቢሆን እን የገዳዩን ያክል ስይፍና ታንክ ይዞ እንጂ ክላሽና ሽጉጥ ብቻ ወይንም ብርና ወረቀት ይዞ ለድርድር መጠጋት የሰውየው እድ ከማራዘም  ምን እርባና ያሰገኛል (ያውም አሁን እጅግ አደገኛ ወረበላውና ለግንጠላ በመራመድ ላይ ያለው የትግሬው ወያ ጋር የጋራ አንድነት በፈጠሩበት ወቅት)!!

ሰሞኑን ‘’የምክክር ኮሚሺን’’ ምናም የሚል ‘’የፋሺሰቶች የተለመደ የልት ቡድን’’ መስርቶ ኑና ተደራደሩኝ እያለ ‘’ሲያሾፍ’’ ስንበል፡፡  የገረመኝ የሰውየው ‘ልት’ ሳይሆን ለልቱ ጥሪው ምላሸ የሰጡ ፖለቲከኞች “የሽግግር መንግሥት ይመሥረትና በዛው ሽግግር ውስጥ ‘’ሁሉም አቀፍ የሽግግር መንግሥት’’ ይመስረት ያሉትን ተቃዋሚዎች” አሰገረሙኝ፡፡ ምኞታቸው በጎ ቢሆንም

ከዱርየዎቹ ጋር ለመደራደር አቅም መገንባት ያስፈለጋል፡፡

አምባገነን የሆኑበት ዋናው መሰሶ ሥልጣን ላይ ባሉበት ወቀት ራሳቸውን ከክስ ነፃ ለማድረግ የተጻፈና ያልተጻፈ ህግ አውጥተዋል። አሁንም በሽግግር ወቅት( ለወደፊቱ የሚኖር ከሆነ) እነዚሀ ወንጀለኞች በድርድሩ ከገቡ ራሳቸውን ከክስ ነፃ ለማድረግ ካልሆነ ምን ይፈይደናል ብለው ታሰቦ ነው ሽግግር፤ድርድሩና ምክክር የሚባለው ቀርበው የሚነጋገሩት?

እራሳቸውን ከሰሩት ወንጀል ክከስ ነጻ ማውጣት ካልቻሉ ታጥቀዋልና “ጦርነት የከፍቱብሃል”፡፡ ለዚያ ነው፤ ከነሱ ጉልበት እኩል ወይንም የላቀ ታጣቂ ኅይል ማደራጀት ከድርድሩ ወይንም ከሽግግር በፊት  መሆን አለበት የምለው (ሰሚ ታጣ እንጂ ለ33 አመት ስለው የነበረው ጉዳይ ነው)፡፡ ቢያንሰ “ውይይት፤ምክክር” እንጂ “ሽግግር አልፈቅድም” ቢል (አሁን እንደተናገረው) በትጥቅ እንዲገደድ ወይንም እንዲንበርክከ ማድረግ ካላደረግክ ሰላማዊ ውይይት የሚባለው አምራጭ አይልሰራም ወይንም ዝግ ነው፡፡

ጦርነት ይብቃ የሚሉ ምኞተኞች አሉ፡፡፟ ያለ “ጠብ መንጃ”  አስገዳጅነት ኢትዮጵያ  ውሰጥ የተነሰራፋው 'የሦስት ትውልድ ቅጣት' የሚባል በአምባገነኖቹ ሕሊና የተጻፈ ሆኖም በሕገመንግሥት ተብያቸውም ባልተደነገገ (ልጅ ባጠፋ ውላጅና ዘመድ አዝማድ በተዋረድ ማሳዘን ማስረና መቅጣት’ ማስቀረት አይቻልም)፡፡ በተለይ እነዚህ ለ33 አመት ኢትዮጵያን ያንበረከኩ ቡደኖች በጫካ ሕግ የሚተዳደሩ “ሱፉና ክራባት” ያጠለቁ ብዙ ወንጀሎችን የፈጸሙ የቤተ መንግሥትና  የጫካና  ዱርየዎች ናቸው፡፡ እስካሁን ለ33 ዓመት ሕግ ፊት ያልቀረቡበት የማምለጫ ጉለበታቸው ምን እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ በመጡበት ሰይፍ ካልተወገዱ ወንጀለኛ ዱርየንውይይት ማስወገድ አይቻልም፡፡ በቃ ይህ ሃቅ ተቀበሉኝ!

ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ እየተፈራረቁ እሰከ አሁን 2016 ዓ/ም የሦስት ትውልድ ቅጣት' ሕግ የደነገጉብን ፋሺስቶች ብዛት ያላቸው ለዘመናት ያሳደግዋቸው ሰው የሚመስሉ “በግ” ተከታይ አሉዋቸው፡፡ ተከታዮቻቸውም የታጠቁ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ጋር አብሮ የጋራ መንግሥትን መመሥረት ሳይሆን ተቀናቃኝ ሆኖ ማስወገድና ወደ ሕግ ተከስሰው ካልተቀጡ መከራው ቀጣይ ነው፡፡

ጦረነት ኢትዮጵያ ወስጥ ቀጣይ የሆነበት ምክንያት አገራችን የውጭና የወስጥ ተቀናቃኞች ሕልውናዋን ለማጥፋት ለዘመናት የተቀናቀኑበት ተከታታይ ትግል ሰለሆነ በቅጥረኞችና በአገር ወዳዶች መካክል የሚደረግ ከዘመነ አክሱም ጀምሮ በዓለም ታሪክ አገሮች ያልታየ እስከዛሬ 2016 ዓ/ም ቀጣይ እልሕ አስጨራሽ ፍልሚያ ማድረጉ ጎጂ ቢሆንም  በሁኔታው በአሰገዳጅነት ጦርነቱ ቀጣይ ሆኗል፡፡ ይህ ሕዝብ በወስጥና በውጭ ጠላቶች ቀለበት ውስጥ ተከብቦ ለዘመናት ሲታገላቸው ያዩ ጠላቶቹ ኢትዮጵያ ጦርነት ወዳጅ ነች ብለው የሚወቅት ክፍሎች ደግሞ የተገላቢጦሽ የጦረነቱ አፈላቂዎቹና ቀጥረኞቻቸው ናቸው፡፡

የጦርነቱ ቀጣይነት ከለየላቸው የውጨና የውሰጥ ጸረ ኢትዮጵያ ቡደኖች ጋር ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ችግር እየሆነ ያለው ደግሞ አጋሰሱ ምሁር ነው፡፡

ይህ ክፍል አልሰማ ብሎ ይኼው የዋሁን ሕዝባችን ለስቃይ በመዳረግ ዛሬም ሐፍረት ሳይሰማው  ከገዢዎች ጋር እየጨፈረ አልመከር ብሎ አንዳንዱ አማራ ላይ ጀነሳይ አልተፈጸመም እያለ፤ አንዳንዱም ኦነግዋን ከንቲባአዳነች አበቤንየዓድዋዋ አርበኛ እተጌ ጣይቱ ነች እያለ ሲያሽቃብጥ፤ አዝማሪውም የአፍሪካ ምልክት አዳነች አሸበረቀቺ እያለ ክራር ሲከረክር አንዳንዱምክቡር /ሚኒስተራችን አብይ አሕመድን እደግፍ ነበር አሁን ሙሉ በሙሉ ባልደግፈውም አንዳንድ ራሺናልአስተሳሰቡን አሁንም እደግፋለሁ ወዘተእያለ ከዚያው አሽከርነት ላለመውጣት እንደ አሳማ ጭቃ ውስጥ እየተጨማለቀ አስቸግሯል።

ትናትም ዛሬም አገራችን በቅኝ ግዛት እንድትያዝ ያደረገው ይኸየው ዝግምተኛውኢቮሊሽኑያላገባደደው ምሁር ነኝ ባዩና ጋዜጠኛ ነኝ ባዩ  አንደቶረተይልስ/ኤሊእየተንፏቀቀ የወንጀለኞቹ ፎቶግራፎችና ንግግሮችን በየፌስቡኩ እያዳመቀ ያለ ምንም ሐፍረት  የሚለጥፈውበግብዝነት የሚንሿዋሻውመንጋ ካድሬዎቹም  አብረው እያጫፈሩ አፓርታይዱ መሪ  የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ መርቆ ሲከፍት በደሰታ የሚሆኑት ያጣሉ

6 አመት በፊት ወንጀለኞች ነን “ሸበረተኞችና ገራፊዎች ነን ፤ ሳናጣራ አናስርም” ብለው አምነውምለው ጥለውአይደግመንን ብለው ሕዝብን አሞኝተው ወደሥልጣን ዕርካብከወጡ በኋላ የከፋ ጭፍጨፋ እያደረሱበት እያለና በዙ የአማራ መሁራን እየታፈኑ ባሉበት ወቅት ፋኖዎች እያደረጉት ካለው የብረት ትግል አማራጭ (ታአመረኛው አርበኛ እስክንድር ነጋ ከሞከረው እልሕ አስጨራሽ ሠላማዊ ትግል) ያልተሞከረ ሌላ አማራጭ ካለ ንገሩን?

በመጨረሻ ጽሑፌ ከዚሀ በታች በእነ ክርስትያን ታደለ፤ ዮሃንስ  ቧ ያለው ፤ መምሕርት መስከረም አበራ ወዘተ,,፤ በተባሉ መሁራን ላይ ወደ 60 የሚያክሉ በነገዳቸው አማራ በመሆናቸው ብቻና እየደረሰ ያለው ግፍ በመቃወማቸው በነዚህ ታሳሪዎች ላይ የተፈጸመ ግፍ አንብቡና ይህ ግፍ ለማሰቆም አብይ አሕመድ በጠራው የቧልት ምክክር ወይስ በጠመንጃ ማስቆም አማራጩ የትኛው ነው ትላላችሁ?

ታሳሪዎቹ እንዲህ ይላሉ፤

<< ዐማራ ታሳሪዎች በኤሌትሪክ ተቃጥለዋል፣ ጥፍራቸው ተነቅሏል፣ አካላቸው በቀዝቃዛ ውሃ ከተጠመቀ በኋላ ተገርፏል። በደረሰባቸው የአካል ድብደባ አፍንጫቸውና አፋቸው የሚደማ እስረኞች አሉ። አንዱ ታሳሩ እንዲህ ይላል፡፡

እኛ የደረሰብንን ቅጣት ሳስብ፣ የአይሁድ ሕዝብ በሂትለር የደረሰበት ዓይነት አያያዝ ነው። በዚህ እስር ቤት የተደረገብን አያያዝ ሂትለር በአይሁዶች ላይ ካደረገው ጋር ተመሳሳይ ነው። ሂትለር አይሁዶች የሰው ልጅ ይህን የመሰለ ጨካኝ አገዛዝ እስከመቼ ሊቋቋመው እንደሚችል ለማወቅ በኬሚካል በተረጨ በታሸገ አዳራሽ አፍኖ አሰቃይቶ ገድላቸዋል። በእኛ ሁኔታ 42 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የሙቀት መጠን ባለው የታሸገ እና በጣም በተጨናነቀ ሕዋስ ውስጥ ታፍነን ታስረናል፡ የሰው ልጅ ምን ያህል የሙቀት መጠን መቋቋም እንደቻለ ለማወቅ መንግሥት በእኛ ላይ ሙከራ በማካሄድ እንዲህ ላለው የሙቀት መጠን በኛ ላይ ሙከራ እያደረገ ነው። ዐማሮች ይህን የመሰለ ጨካኝ የእስር አገዛዝ እየተፈፀመባቸው ነው። ይህ አገዛዝ ሰውነታችን በከፍተኛ የሙቀት መጠን መሟሟትና መበታተን እስከሚጀምርበት ደረጃ ድረስ እንድንሰቃይ ከማድረግ በላይ እንደ ሰው ምን ሊያደርገን እንደሚችል አላውቅም።

ብዙዎች 5, 10, 15 እስከ 18 ኪሎ ግራም ክብደት ቀንሰዋል፡፡ መከራን በማድረስ ያላደረጉብን ነገር ቢኖር ናዚዎች በአይሁዳውያን እስረኞች ላይ እንዳደረጉት አጥንታችንን መፍጨትና ሳሙና ማዘጋጀት ብቻ ነው እስካሁን ይህንን ካላደረጉት ከናዚዎች በተለየ መልኩ አጥንትን በሳሙና የማቀነባበር ቴክኖሎጂ እና ፋብሪካ ስለሌላቸው ነው።”

በማለት ይህ መሳይ አሰቃቂ  'የሦስት ትውልድ ቅጣት እንዲሆን በመጣር ላይ ያለው በጥላቻ ትርክት የሰከረ ፤ ሥልጣ ካልጎበኘው "በፈጣሪና በኢትዮጵያ ባሕል የማይገዛ አረመ" ከሆነው  “ከአስከሬን አሳሪ”  አብይ አሕመድ ጋር በነፍጥ ካልሆነ  ጠረጴዛ ላይ በባዶ እጅ ብዕር እና ወረቀት ይዞ በመቀመጥ እሱ ባዘጋጀው በቧልት “ምክክር” ላይ መሳተፍ 'የሦስት ትውልድ ቅጣት (1966፣ 1983 ፣ 2010) ቀጣይነት ማስቆም አይቻልም፡፡

ጌታቸው ረዳ

ሰላም ለናንተ ይሁን